es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Ir al canal en Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
912
Suscriptores
-224 horas
-127 días
+5130 días
Archivo de publicaciones
ندوة علمية بعنوان أصول أهل السنة في العقيدة
ضيوف الندوة
فضيلة الشيخ العلامة المحدث ربيع بن هادي المدخلي-رحمه الله- فضيلة الشيخ العلامة علي بن ناصر الفقيهي-رحمه الله- فضيلة الشيخ العلامة صالح بن سعد السحيمي-حفظه الله-
المقدم
فضيلة الشيخ الدكتور عبد الرزاق البدر حفظه الله تعالى https://t.me/DrRabeeM/3127 الدال على الخير كفاعله

✅ አብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- አላህ የወሰነውን ነገር “ባያደርገው ኖሮ” ብዬ ከምናገር ይልቅ የሚነድ ፍም እሳትን  እስኪቀዘቅዝ ድረስ ነክሼ ብይዝ እመርጣለሁ።
📚الزهد لأبي داود
t.me/MohamedAliEdris

Repost from Abu Hayder Aliy
اللَّهُمَّ أَصْلِحْ قُلُوبَنَا، وَاسْتُرْ عُيُوبَنَا، وَاغْفِرْ ذُنُوبَنَا، وَأَحْسِنْ خَاتِمَتَنَا، يَا رَبَّ الْعَالَمِينَ.
اللَّهُمَّ أَصْلِحْ قُلُوبَنَا، وَاسْتُرْ عُيُوبَنَا، وَاغْفِرْ ذُنُوبَنَا، وَأَحْسِنْ خَاتِمَتَنَا، يَا رَبَّ الْعَالَمِينَ. አላህ ሆይ! ልቦቻችንን አስተካክልልን፣ ጉድለቶቻችንን ሸፍንልን፣ ኃጢአቶቻችንን ማርልን፣ መጨረሻችንንም አሳምርልን መልካም አድርግልን! 🤲 https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

نقض شبهة أهل الباطل في المطالبة بالتسوية بين المخطئ وبين المعاند العاطل ​قال فضيلة الشيخ أ د أحمد بن عمر سالم بازمول -حفظه الله- فكثيراً ما يستدل أهل الباطل المخالفين لمنهج السلف الصالح في ردودهم على أهل السنة بكون فلان من العلماء السلفيين قال بنفس ما يقوله متبوعهم وكبيرهم ويطالبون بالتسوية في الحكم عليه بذلك العالم ؟ وهذه شبهة شيطانية المقصود منها التسوية بين الواقع في الخطأ دون قصد وبين المخطئ المصر المعاند ؟! والسلفيون يفرقون بين وقوع العالم في الزلة وبين وقوعه في الفتنة: فالفرق بين زلة العالم وفتنته: أن زلته خطؤه بلا تعمد، وأما فتنته فمخالفته للحق وانحرافه عن تعمد، وإصراره على هذا الانحراف قال تعالى ﴿فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَنْ تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ﴾ قال شيخ الإسلام ابن تيمية كما في مجموع الفتاوى (29/43-45): "سبب الفرق بين أهل العلم وأهل الأهواء مع وجود الاختلاف في قول كل منهما أن العالم قد فعل ما أمر به من حسن القصد والاجتهاد وهو مأمور في الظاهر باعتقاد ما قام عنده دليله وإن لم يكن مطابقاً لكن اعتقاداً ليس بيقيني ... فالمجتهد الاجتهاد العلمي المحض ليس له غرض سوى الحق وقد سلك طريقه وأما متبع الهوى المحض فهو من يعلم الحق ويعاند عنه. وثم قسم آخر وهو غالب الناس وهو أن يكون له هوى فيه شبهة فتجتمع الشهوة والشبهة. فالمجتهد المحض مغفور له ومأجور وصاحب الهوى المحض مستوجب للعذاب وأما المجتهد الاجتهاد المركب من شبهة وهوى فهو مسيء وهم في ذلك على درجات بحسب ما يغلب وبحسب الحسنات الماحية وأكثر المتأخرين من المنتسبين إلى فقه أو تصوف مبتلون بذلك" فزلة العالم ليست هوى إنما خطأ غير متعمد، بخلاف فتنته فهو انحراف وسلوك غير الحق بالتعمد، فلا يعذر. ولذلك يطعن على من فتن في دينه ولا يطعن على من زل، ومن سوَّى بينهما فقد أخطأ، قال الشيخ العلامة حامل راية الجرح والتعديل ربيع المدخلي -حفظه الله تعالى-: "كل من وقع في البدع لا يبدع لكن إذا عرفنا منه الهوى، وعرفنا منه سوء القصد، وعرفنا منه أشياء تدل على أنه يريد البدعة هذا يبدع؛ لهذا تجدهم: حكموا على كثير من الناس بأنهم مبتدعة. وكثير من الناس وقعوا في أخطاء ما سموهم مبتدعة؛ لأنهم عرفوا سلامة مقصدهم، وحسن نواياهم، وتحريهم للحق وسلامة المنهج الذي يسيرون عليه" انتهى خطورة تتبع الشواذ والأفراد من أخطاء العلماء: ومن هنا حذر أهل العلم من تتبع الشواذ من الأقوال واتخاذها ديناً: قال الأوزاعي: "من أخذ بنوادر العلماء خرج من الإسلام" وقال خالد بن الحارث قال لي سليمان التيمي: "لو أخذت برخصة كل عالم أو زلة كل عالم اجتمع فيك الشر كله" وعلق ابن عبد البر على قول التيمي: "هذا إجماع لا أعلم فيه خلافاً" كما في جامع بيان العلم وفضله (2/91). وقال ابن قيم الجوزية في إعلام الموقعين (2/192): "... مِنْ الْمَعْلُومِ أَنَّ الْمَخُوفَ في زَلَّةِ الْعَالِمِ تَقْلِيدُهُ فيها إذْ لَوْلَا التَّقْلِيدُ لم يَخَفْ من زَلَّةِ الْعَالِمِ على غَيْرِهِ. فإذا عَرَفَ أنها زَلَّةً لم يَجُزْ له أَنْ يَتْبَعَهُ فيها بِاتِّفَاقِ الْمُسْلِمِينَ فإنه اتِّبَاعٌ لِلْخَطَأِ على عَمْدٍ وَمَنْ لم يَعْرِفْ أنها زَلَّةٌ فَهُوَ أَعْذَرُ منه وَكِلَاهُمَا مُفْرِطٌ فِيمَا أُمِرَ بِهِ" فمن نسب لأهل السنة التسوية بين المخطئ وبين المعاند فقد بغى وتعدى وظلم والله حسيبه! وانظر: صلاة التراويح (35-39) للعلامة السلفي بحق وصدق وعدل محمد ناصر الدين الألباني رحمه الله تعالى، منقول رابط مجموعة التليغرام: t.me/Multeka_Selefiyin t.me/Multeka_Selefiyin

እኛ ብንሆን ኖሮስ! ~ ለኢማሙ አሕመድ የሆነ ሰው ስም ተነሳላቸው። * "እኔ ስለሱ መልካምን እንጂ አላውቅም" አሉ። * "አንተ በሱ ላይ የምትናገረው እሱ ባንተ ላይ ከሚናገረው ይለያል" አላቸው አንዱ። (በክፉ ያነሳሀል ማለቱ ነው።) * ፈገግ ብለው "እኔ ስለሱ መልካምን እንጂ አላውቅም። ስለሚናገረው እሱ ያውቃል። የማላውቀውን እንድናገር ነው የምትፈልገው?" አሉ። ቀጥለውም እንዲህ አሉ፦ "ሳሊምን አላህ ይዘንላቸው። (ሳሊም የኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ልጅ ናቸው።) አንዴ ግመላቸው የሌላን ሰው ግመል ገፋች። ሰውየው በዚህን ጊዜ ለሳሊም፡ 'ክፉ ሽማግሌ ትመስለኛለህ!' አላቸው። 'አልራቅክም!' አሉት። (ልክ ነህ! እያሉት ነው። ኢማሙ አሕመድም ለራሳቸው ተመሳሳይ ነገር መጠቀማቸው ነው።) ምንጭ፦ [አልወረዕ ሊልመርወዚ፡ 197] * እስኪ እራሳችንን በሳሊም ቦታ አድርገን እናስብ። ምን ይሆን ነበር ምላሻችን? አላሁል ሙስተዓን! * እስኪ እራሳችንን በኢማሙ አሕመድ ቦታ አድርገን እናስብ። ምን ይሆን ነበር ምላሻችን? አላህ ይድረስልን። ~ የቴሌግራም ቻላል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

✍ የሆነ ሰው ይቅርታ ሲልህ ግዴታ አጥፍቷል አንተ ደግሞ ትክክል ነህ ማለት ላይሆን ይችላል። ምናልባትም በማካከላችን ያለውን ትስስር ከክብሩ እንደሚበልጥ ሊነግርህ ፈልጎ ሊሆን ይችላል። 👉ይቅርታ የምትለዋ ቃል አንዳንዴ ምንም ብታደርግ ላጣህ አልፈልግም የሚል መልዕክት የያዘች ቃል ትሆናለች። በዚህ ጊዜ ከልክ ያለፈ ራስን ከፍ የሚያደርግ አባዜ ሊይዝህ አይገባም። የዚህን ሰው ክብር በፍጥነት ልትገነባለትም ይገባል። ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ሰዎች በየቀኑ ማግኘት አይቻልም። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ አል አቅሷ መስጂድን የገነባው ነብይ ማን ነው ?

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته هل يشترط اقامة الحجة قبل الحكم بالتبديع الجواب وعليكم السلام ورحمة الله وبركاته أما بعد: فالبدعة منها ما هو جلي ومنها ما هو خفي، والمرتكب للبدعة قد يكون سلفيا وقد يكون صاحب أصول فاسدة أو مجهولا. فمن كان سلفيا أو صاحب أصول فاسدة أو مجهولا ووقع في أمر جلي من أمور البدع التي لا تخفى أنها بدعة فهذا لا يشترط فيه إقامة الحجة. بل يجوز إطلاق الابتداع عليه. وأما في الأمور الخفية فهذه تحتاج إلى إقامة الحجة في حق من كان سلفيا أو مجهولا، ولا يحتاج ذلك في صاحب الأصول الفاسدة. والله أعلم وصلى الله وسلم على نبينا محمد. كتبه: أسامة بن عطايا بن عثمان العتيبي 11/ 11 / 1435هـ

Repost from fezekir
خطبة جمعة بعنوان: طلب الرزق الشيخ صالح الفوزان #خطبة_جمعة #الشيخ_صالح_الفوزان

«እንረጋጋ ለመፍረድ አንቸኩል» ----------------------------- ሁለት ዓይኖች እያሉህ፣ ለምን ሰዎችን በጆሮህ ታያቸዋለህ⁉️» አንዳንዴ አንድን ሰው በደንብ አታውቀውም። አብረኸው ተቀምጠህ አላወራህም፣ ታሪኩን አልሰማህም፣ ምን እንዳሳለፈም አታውቅም። ........ ግን አንድ ሰው «እሱ እንዲህ ነው» ስላለህ፣ ስለ እሱ ውሳኔ ሰጥተሃል። ከማወቅህ በፊት ርቀኸዋል፤ ከማዳመጥህ በፊት ፈርደህበታል። ሰውየው ያንተን ቅዝቃዜ ያያል። ሰላም ሲልህ የምትመልስበትን መንገድ፣ ከእሱ ለመራቅ የምታደርገውን ጥረት ያስተውላል። .......ግን ምን እንዳደረገህ አያውቅም። ስለ እሱ ምን እንደሰማህ እንኳን ላያውቅ ይችላል። አንተ የሰማኸውን ታሪክ እያስታወስክ ትርቀዋለህ፤ እሱ ግን «ምን አደረግሁ?» እያለ ይቀራል። ♦️እስቲ ቦታውን ወስደህ አስብ። አንተ በሌለህበት የተነገረ ታሪክ፣ በሰዎች ፊት ማንነትህ ቢሆንስ⁉️ ያልተናገርከው ቃል፣ ያላደረግከው ተግባር ወይም አንተ ብቻ ምክንያቱን የምታውቀው ውሳኔ፣ አንተን ለመፍረድ መለኪያ ቢደረግስ⁉️ ምናልባት የምትጠይቀው አንድ ነገር ብቻ ነው፦ «ከመፍረዳችሁ በፊት፣ እኔንም ስሙኝ።» .........ስለ ሰው የምንሰማው ነገር ሁሉ ውሸት ነው ማለት አይደለም። ግን የተነገረን ነገር ሁሉ እውነት ነው ብሎ መቀበል #ጤነኝነት አይደለም።........እውነት ቢኖረው እንኳን የተነገረው  ሙሉው ታሪክ ላይሆን ይችላልና ሙሉውን ከባለቤቱ እናረጋግጥ። ...........አንድ አለመግባባት፣ የተሳሳተ ግንዛቤ ወይም ያልተነገረ ሌላ ክፍል ሊኖር ይችላል። ስለዚህ «#ሰምቻለሁ» ከሚለው ወደ «አውቃለሁ» ለመሄድ አትቸኩል። መስማትና እውነቱን ማወቅ አንድ አይደሉም። ......➛#ዝምተኛ የሆነን ሰው «#ትዕቢተኛ ነው» ከማለትህ በፊት፣ ምናልባት ከሰዎች ጋር ለመቀራረብ ጊዜ እንደሚፈልግ አስብ። ....አንድ ግብዣ ያልመጣን ሰው «#አያከብረንም» ከማለትህ በፊት፣ ያልነገረህ ችግር ሊኖረው እንደሚችል አስብ። ......➛ ይህ ለሁሉም ተግባር ምክንያት መፈለግ አይደለም፤ የማታውቀው ነገር እንዳለ ቦታ መተው ነው። በዓይንህ ያየኸውም አንድ ቅጽበት፣ የሰውን ሕይወት ሙሉ በሙሉ አይገልጽም። ስለዚህ የጥቅሱ ጥሪ፣ ጆሮህን ዝጋና በዓይንህ ብቻ እመን የሚል አይደለም። ➛ሰውን በወሬ ብቻ አትለካ፣ ➛የሰማኸውን አመዛዝን፣ በቂ ግንዛቤ ሳይኖርህ በፍርድ አትቸኩል የሚል ማስታወሻ ነው። .....ይህ ማለት ግን ማስጠንቀቂያዎችን ችላ በል ማለት አይደለም። ራስህን ለመጠበቅ ጥንቃቄ ማድረግና ወሰን ማስቀመጥ ትችላለህ። እውነቱን ለማወቅ ስትል ራስህን ለአደጋ ማጋለጥ አያስፈልግህም። ጥንቃቄ ማድረግ አንድ ነገር ነው፤ ያልተረጋገጠ ወሬ በማሰራጨት የሰውን #ስም_ማጥፋት ሌላ ነው። ስለ አንድ ሰው የተነገረህን ነገር ለሌላ ከማስተላለፍህ በፊት፣ ትንሽ ቆም በል። «ይህ እውነት መሆኑን አውቃለሁ? ማስተላለፌ ማንን ይጠቅማል? ሰውየው እዚህ ቢኖር፣ በዚህ መንገድ እናገረው ነበር⁉️» ብለህ ራስህን ጠይቅ። ....አንዳንዴ የምታደርገው ትልቁ ደግነት፣ እውነትነቱን የማታውቀውን ወሬ እዚያው ማቆም ነው። .......ቀድመህ በሰማኸው ነገር ተመርተህ አንድን ሰው በስህተት ፈርደህበት ከሆነም፣ አመለካከትህን መቀየር ትችላለህ። «ሳላውቅህ ፈርጄብህ ነበር፤ ተሳስቻለሁ» ማለት ድክመት አይደለም። ከራስህ ኩራት ይልቅ፣ ለእውነትና ለሰው ክብር ቦታ መስጠት #ታላቅነት ነው። .......አንተም በሌሎች ወሬ ምክንያት ያለ አግባብ ተፈርዶብህ ከሆነ፣ ያ ታሪክ ማንነትህን ሙሉ በሙሉ እንዲወስን አትፍቀድ። ማስተካከል የምትችለውን በእርጋታ አስተካክል፣ የሚሰሙህን ሰዎች አነጋግር። ያ ገጠመኝም፣ አንተ ሌላውን ከመፍረድህ በፊት እንድታዳምጥ ማስታወሻ ይሁንልህ። ሰውን በሰማኸው ወሬ ብቻ አትለካው። ታሪኩን ለመስማት፣ ተግባሩን ለማየትና እውነቱን ለማወቅ ጊዜ ስጥ። ስለ እሱ ብዙ መስማትህ....እሱን በደንብ ታውቀዋለህ ማለት አይደለም። በሰማኸው ነገር ምክንያት ርቀኸው፣ ከተዋወቅከው በኋላ አመለካከትህ የተቀየረበት ሰው አለ አስተውል። «አሏህ ለሁላችንም ልቦና ይስጠን» t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

«እንረጋጋ ለመፍረድ አንቸኩል» ----------------------------- ሁለት ዓይኖች እያሉህ፣ ለምን ሰዎችን በጆሮህ ታያቸዋለህ⁉️» አንዳንዴ አንድን ሰው በደንብ አታውቀውም። አብረኸው ተቀምጠህ አላወራህም፣ ታሪኩን አልሰማህም፣ ምን እንዳሳለፈም አታውቅም። ........ ግን አንድ ሰው «እሱ እንዲህ ነው» ስላለህ፣ ስለ እሱ ውሳኔ ሰጥተሃል። ከማወቅህ በፊት ርቀኸዋል፤ ከማዳመጥህ በፊት ፈርደህበታል። ሰውየው ያንተን ቅዝቃዜ ያያል። ሰላም ሲልህ የምትመልስበትን መንገድ፣ ከእሱ ለመራቅ የምታደርገውን ጥረት ያስተውላል። .......ግን ምን እንዳደረገህ አያውቅም። ስለ እሱ ምን እንደሰማህ እንኳን ላያውቅ ይችላል። አንተ የሰማኸውን ታሪክ እያስታወስክ ትርቀዋለህ፤ እሱ ግን «ምን አደረግሁ?» እያለ ይቀራል። ♦️እስቲ ቦታውን ወስደህ አስብ። አንተ በሌለህበት የተነገረ ታሪክ፣ በሰዎች ፊት ማንነትህ ቢሆንስ⁉️ ያልተናገርከው ቃል፣ ያላደረግከው ተግባር ወይም አንተ ብቻ ምክንያቱን የምታውቀው ውሳኔ፣ አንተን ለመፍረድ መለኪያ ቢደረግስ⁉️ ምናልባት የምትጠይቀው አንድ ነገር ብቻ ነው፦ «ከመፍረዳችሁ በፊት፣ እኔንም ስሙኝ።» .........ስለ ሰው የምንሰማው ነገር ሁሉ ውሸት ነው ማለት አይደለም። ግን የተነገረን ነገር ሁሉ እውነት ነው ብሎ መቀበል #ጤነኝነት አይደለም።........እውነት ቢኖረው እንኳን የተነገረው ሙሉው ታሪክ ላይሆን ይችላልና ሙሉውን ከባለቤቱ እናረጋግጥ። ...........አንድ አለመግባባት፣ የተሳሳተ ግንዛቤ ወይም ያልተነገረ ሌላ ክፍል ሊኖር ይችላል። ስለዚህ «#ሰምቻለሁ» ከሚለው ወደ «አውቃለሁ» ለመሄድ አትቸኩል። መስማትና እውነቱን ማወቅ አንድ አይደሉም። ......➛#ዝምተኛ የሆነን ሰው «#ትዕቢተኛ ነው» ከማለትህ በፊት፣ ምናልባት ከሰዎች ጋር ለመቀራረብ ጊዜ እንደሚፈልግ አስብ። ....አንድ ግብዣ ያልመጣን ሰው «#አያከብረንም» ከማለትህ በፊት፣ ያልነገረህ ችግር ሊኖረው እንደሚችል አስብ። ......➛ ይህ ለሁሉም ተግባር ምክንያት መፈለግ አይደለም፤ የማታውቀው ነገር እንዳለ ቦታ መተው ነው። በዓይንህ ያየኸውም አንድ ቅጽበት፣ የሰውን ሕይወት ሙሉ በሙሉ አይገልጽም። ስለዚህ የጥቅሱ ጥሪ፣ ጆሮህን ዝጋና በዓይንህ ብቻ እመን የሚል አይደለም። ➛ሰውን በወሬ ብቻ አትለካ፣ ➛የሰማኸውን አመዛዝን፣ በቂ ግንዛቤ ሳይኖርህ በፍርድ አትቸኩል የሚል ማስታወሻ ነው። .....ይህ ማለት ግን ማስጠንቀቂያዎችን ችላ በል ማለት አይደለም። ራስህን ለመጠበቅ ጥንቃቄ ማድረግና ወሰን ማስቀመጥ ትችላለህ። እውነቱን ለማወቅ ስትል ራስህን ለአደጋ ማጋለጥ አያስፈልግህም። ጥንቃቄ ማድረግ አንድ ነገር ነው፤ ያልተረጋገጠ ወሬ በማሰራጨት የሰውን #ስም_ማጥፋት ሌላ ነው። ስለ አንድ ሰው የተነገረህን ነገር ለሌላ ከማስተላለፍህ በፊት፣ ትንሽ ቆም በል። «ይህ እውነት መሆኑን አውቃለሁ? ማስተላለፌ ማንን ይጠቅማል? ሰውየው እዚህ ቢኖር፣ በዚህ መንገድ እናገረው ነበር⁉️» ብለህ ራስህን ጠይቅ። ....አንዳንዴ የምታደርገው ትልቁ ደግነት፣ እውነትነቱን የማታውቀውን ወሬ እዚያው ማቆም ነው። .......ቀድመህ በሰማኸው ነገር ተመርተህ አንድን ሰው በስህተት ፈርደህበት ከሆነም፣ አመለካከትህን መቀየር ትችላለህ። «ሳላውቅህ ፈርጄብህ ነበር፤ ተሳስቻለሁ» ማለት ድክመት አይደለም። ከራስህ ኩራት ይልቅ፣ ለእውነትና ለሰው ክብር ቦታ መስጠት #ታላቅነት ነው። .......አንተም በሌሎች ወሬ ምክንያት ያለ አግባብ ተፈርዶብህ ከሆነ፣ ያ ታሪክ ማንነትህን ሙሉ በሙሉ እንዲወስን አትፍቀድ። ማስተካከል የምትችለውን በእርጋታ አስተካክል፣ የሚሰሙህን ሰዎች አነጋግር። ያ ገጠመኝም፣ አንተ ሌላውን ከመፍረድህ በፊት እንድታዳምጥ ማስታወሻ ይሁንልህ። ሰውን በሰማኸው ወሬ ብቻ አትለካው። ታሪኩን ለመስማት፣ ተግባሩን ለማየትና እውነቱን ለማወቅ ጊዜ ስጥ። ስለ እሱ ብዙ መስማትህ....እሱን በደንብ ታውቀዋለህ ማለት አይደለም። በሰማኸው ነገር ምክንያት ርቀኸው፣ ከተዋወቅከው በኋላ አመለካከትህ የተቀየረበት ሰው አለ አስተውል። «አሏህ ለሁላችንም ልቦና ይስጠን» t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ ዩኒቨርሲቲያችን ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በ26 እና በ27 ፍሬሽ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ባች እንዲገቡ ጥሪ ማድረጉ የሚታወቅ ነው። በመሆኑም ጀማዓችን አዲስ የሚገቡ ወንድም እና እህቶቻችን እንዳይቸገሩ በማሰብ ከዚህ በታች ስልክ ቁጥሮችን አስቀምጧል። በተጨማሪም ጀማዓችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልክቱን እያስተላለፈ ከታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር በመደወል ስለ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ እንድሁም ሌሎች መረጃዎች ካስፈለጋችሁ መጠየቅ እንደምትችሉ ሲያሳውቅ በታላቅ ደስታ ነው። 1. 0975292817 📲 ወንድም መስዑድ ሰይድ 2.0946505128 📲 ወንድም ዑመር አወል 3.0924033273 📲 ወንድም ሙሀመድ ሀሰን 4.0903830776 📲 ወንድም ሀቢብ ማህሙድ 📢 ማሳሰቢያ : እህቶች በ 0990333299 በመደወል የአሚሪቷን ቁጥር ማግኘት ትችላላችሁ። እንዲሁም የቻናል ባለቤት የሆናችሁ ወንድም እና እህቶች share በማድረግ ለሁሉም እንዲዳረስ አድርጉት። وَالسَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ            👇 our telegram channel https://t.me/wdumuslimstu

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 📣 አስደሳች ዜና ለዒልም ፈላጊዎች በሙሉ! በአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ፈቃድ ታላቅ የኦንላይን የኪታብ ቂረአት አዘጋጅተንልዎታል። ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌግራም የዲን እውቀትዎን የሚያስፉበት ወርቃማ እድል! 📚የሚጀመረው ኪታብ ስም وصايا السلف للشباب ሚን ወሷያ ሰለፊ ሊሸባብ የሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር ቀረአቱ የሚሰጠው 👇 🎙በኡስታዝ አቡ ዑሰይሚን ኢብኑ ሻፊ ⏰ሰአት ከምሽቱ 3:30 📱ቦታ = የከለላ ሙስሊም ወጣቶች ጀመአ ቴሌግራም ግሩፕ ቂረአቱ በተለየ ሁኔታ የሚሰጠው አያምልጣችሁ ፍጠኑ ተመዝገቡ 🔔ከምንም አይነት ክፍያ ነፃ ነው ቂረአቱ ሲያልቅ ፈተና አለው ለመመዝገብ @abuharis5707 ይህንን ኸይር ስራ ለሌሎች ወንድምና እህቶች በማጋራት (Share) የኸይሩ ተካፋይ ይሁኑ በተለየ የቻናል እና የግሩፕ አድሚኖች ሸር አደርጉት ቂረአቱ የሚሰጥበት የቴሌግራም ግሩፕ👇👇👇 https://t.me/YekelelaWetatoce_gemah

በኮ/ቻ ከተማ በመስጅደል አንሷር በሸይኽ አቢል ሀሠን አሊይ ቢን አህመድ የተሠጠ ኮርስ ✍️ማሳሰቢያ ይህ ቻናል የሠለፍዮች ዳዕዋ የሚለቀቅበት ቻናል ስለሆነ በቻላችሁት መጠን ለሁሉም ተደራሽ አድርጉት ወደ ቻናል ለመቀላቀል 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin

ሸይኽ አብደላህ አል-ዱወይሽ (አላህ ይዘንላቸውና) በዚህ ኪታባቸው ላይ 181 የሚሆን የአቂዳ (የእምነት) ስህተቶችን ከዚላል-አልቁርዐን ላይ ብቻ አውጥተውበታል። አረብኛ የምትረዱ አንብቡት፤ በመፅሀፉ ላይ ያሉትን ስህተቶች ከነ እርማታቸው በዚህ መጽሀፍ ተቀምጧል። በራሳችን እናንብብና እንሞክረው ብለን ዓቂዳችንን ከመበከል እንጠንቀቅ፤ ባረከላሁ ፊኩም። @qireat6k

የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ
[ክፍል ⓶0➑]
ቁርአን
ለደረቀ ልብ ማረስረሻ ወደ ጀነት መዳረሻ የውስጥን ህመም መፈወሻ ሀዘን ጭንቀትን ማስረሻ ቁረአን የሙእሚን ጋሻ
https://t.me/KedmiyaLetewhid9

Repost from Abu Hayder Aliy
🌿🌿🌿🌹🌹🌹❤️❤️❤️ልባችንን ከምቀኝነት እንጠብቅ፤ ደግነትን እንለማመድ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ! አንድ ሙስሊም ሰው ልቡን ከሚያበላሹ ነገሮች መጠበቅ ይገባዋል። ከእነዚህም መካከል ምቀኝነት፣ ጥላቻ፣ ቂምና ለሌላ ሰው የሚደርሰውን መልካም ነገር አለመውደድ ናቸው። በተቃራኒው ደግነት፣ መልካም ምግባር፣ ለሌሎች መልካም መመኘትና ልብን ከጥላቻ ማጽዳት ከታላላቅ የኢስላም ባሕርያት ናቸው። 1. ምቀኝነት አደገኛ የልብ በሽታ ነው አላህ سبحانه وتعالى ምቀኝነትን ከክፉ ነገሮች መካከል ጠቅሶ እንዲህ ብሏል፦ ﴿وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ﴾ «ከሚቀና ሰው በሚቀናበት ጊዜ ከሚያመጣው ክፋት እጠበቃለሁ።» — ሱረቱል-ፈለቅ፦ 5 ይህ አንድ ትልቅ ትምህርት አለው፤ ምቀኝነት በልብ ውስጥ ብቻ ተቀምጦ የሚቀር ሳይሆን ሰውን ወደ ክፉ ተግባር ሊመራው ይችላል። ስለዚህ ሙስሊም ሰው ልቡን ይመርምር፦ «ወንድሜ በረከት ሲያገኝ ደስ ይለኛልን? ወይስ ከእኔ እንዲወገድ እመኛለሁ?» ብሎ ራሱን መጠየቅ ይገባዋል። 2. ነቢዩ ﷺ እርስ በርሳችን እንዳንቀና አስጠንቅቀዋል ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «لا تَحاسَدوا، ولا تَباغَضوا، ولا تَدابَروا، وكونوا عبادَ اللهِ إخوانًا» «እርስ በርሳችሁ አትቀናኑ፤ አትጠላሉ፤ እርስ በርሳችሁ ጀርባ አትስጡ፤ የአላህም ባሮች እንደ ወንድማማች ሁኑ።» — ሶሒሕ አል-ቡኻሪ፣ ሶሒሕ ሙስሊም እዚህ ላይ ነቢዩ ﷺ ምቀኝነትን ከጥላቻና ከመተያየት ጋር አብረው ጠቅሰዋል። ምክንያቱም ምቀኝነት ካልታከመ ጥላቻን ያመጣል፤ ጥላቻም ወደ ግጭትና ወደ ዝምድና መቋረጥ ሊመራ ይችላል። 3. ለወንድምህ የምትወደውን ለራስህ ውደድለት ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «لا يؤمن أحدكم حتى يحب لأخيه ما يحب لنفسه» «ከእናንተ አንዳችሁ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ ፍጹም አማኝ አይሆንም።» — ሶሒሕ አል-ቡኻሪና ሶሒሕ ሙስሊም ይህ ሐዲስ ምቀኝነትን ለማስወገድ ትልቅ መድኃኒት ነው። አንተ ገንዘብ እንዲኖርህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም እንዲኖረው ውደድ። አንተ ጤና እንዲኖርህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም ጤና ውደድ። አንተ አላህ እንዲመራህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም ሂዳያ ውደድ። ይህ ነው እውነተኛ የእምነት ባሕርይ። 4. ለሌሎች መልካም ማድረግ አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦ ﴿إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالإِحْسَانِ﴾ «እርግጥ አላህ በፍትሕና በመልካም ሥራ ያዛል።» — ሱረቱ አን-ነሕል፦ 90 ደግነት በገንዘብ ብቻ አይደለም። ጥሩ ቃል መናገር፣ የተቸገረን መርዳት፣ የተራበን ማብላት፣ የታመመን መጠየቅ፣ ለሰው መልካም መመኘትና ከሰዎች ጉዳትን ማራቅም ደግነት ነው። 5. የምቀኝነት ተቃራኒ የሆነው መልካም ልብ አላህ سبحانه وتعالى ስለ ምእመናን እንዲህ ብሏል፦ ﴿وَالَّذِينَ جَاءُوا مِن بَعْدِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا اغْفِرْ لَنَا وَلِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ سَبَقُونَا بِالإِيمَانِ وَلَا تَجْعَلْ فِي قُلُوبِنَا غِلًّا لِّلَّذِينَ آمَنُوا﴾ «ከእነርሱ በኋላ የመጡትም፦ ‘ጌታችን ሆይ! ለእኛና በእምነት ከእኛ በፊት ለቀደሙት ወንድሞቻችን ምሕረትን ስጠን፤ በልባችንም በአማኞች ላይ ቂም አታድርግብን’ ይላሉ።» — ሱረቱል-ሐሽር፦ 10 ይህ ለእያንዳንዱ ሙስሊም ታላቅ ዱዓ ነው። ልባችን ከቂም፣ ከጥላቻና ከምቀኝነት እንዲጸዳ አላህን እንጠይቅ። 6. ምቀኝነት ሲመጣ ምን እናድርግ? አንድ ሰው አንተ የሌለህ ነገር ቢያገኝ፣ ልብህ ቢቀና፣ ወዲያውኑ እንዲህ በል፦ «اللهم بارك له، وارزقني من فضلك» «አላህ ሆይ! ለእርሱ በረከት ስጠው፤ ከችሮታህም ለእኔ ስጠኝ።» ከዚያም ለእርሱ መልካም ዱዓ አድርግ። ይህ ልብህን ከምቀኝነት ለማጽዳት ይረዳሃል። አላህ የሰጠውን በማየት ከመቀናት ይልቅ የሰጠህን ተመልከት፤ አላህም ከችሮታው እንዲጨምርልህ ጠይቅ። 7. ደግነት የሰውን ልብ ይለውጣል የሙስሊም ሰው ባሕርይ ለሌሎች መልካም መሆን ነው። እርሱ ቢበደልም በቻለው መጠን ይቅር ይላል፤ ሰው ቢያስቸግረውም እርሱ ግን ክፉን በክፉ ለመመለስ አይቸኩልም። አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦ ﴿وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ﴾ «ቁጣቸውን የሚቆጣጠሩ፣ ከሰዎችም የሚምሩ ናቸው፤ አላህም መልካም አድራጊዎችን ይወዳል።» — ሱረቱ አሊ ዒምራን፦ 134 ስለዚህ ወንድሜና እህቴ! ልብህን አጽዳ። ለሰዎች መልካም ተመኝ። የሌላውን በረከት አትመኝ። አላህ ለሌላው የሰጠውን አንተም እንዲሰጥህ ጠይቅ። የሌላው ስኬት የአንተ ውድቀት አይደለም፤ አላህ ለእያንዳንዱ ባሪያ የሚሆነውን ያውቃል። 👇👇 ☝️☝️ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነገር አንድ ታሪክ እንዲህ ይተረካል፦ አንድ ጊዜ አንድ ሸይኽ ነበሩ። አንዲት ሴትንም አግብተው ነበር። ባለቤታቸው ግን ሁልጊዜ ጥያቄ መጠየቅ ትወድ ነበር። አንድ ቀን፦ «የሸይኽ ሆይ! ሰውን ጀነት እንዲገባ ከሚያደርጉት ነገሮች ታላቁ ምንድን ነው?» ብላ ጠየቀቻቸው። ሸይኹም፦ «ደግነትና መልካም ስነ-ምግባር ነው» ብለው መለሱላት። ከጊዜ በኋላ ሸይኹ ለጉዞ ሊወጡ ሲሉ ከቤተሰባቸው ተሰናብተው ለመሄድ ፈቃድ ጠየቁ። ባለቤታቸው ግን የባሏን ምክር ትታ፣ በልቧ ምቀኝነት ተሞልታ ነበር። እንዲህም አለች፦ «ቆይ፣ ስንቅ ልስጥህ» ብላ ስንቅ አዘጋጀችላቸው። ነገር ግን በስንቁ ውስጥ መርዝ አድርጋ ሰጠቻቸው። ሸይኹ ግን ይህንን ሳያውቁ የተሰጣቸውን ስንቅ ይዘው ጉዟቸውን ቀጠሉ። ወደ ሰፈራቸው ሲደርሱ ምግብ ፍለጋ የወጡ ሁለት ደረሶች ከሸይኹ ጋር ተገናኙ። ሸይኹም ልጆቹን አይተው በደግነት፦ «አቦ! ከእኔ ይልቅ እናንተ ትበሉት» ብለው፣ የያዙትን ምግብ ለሁለቱ ልጆች ሰጧቸው። ልጆቹም ምግቡን በሉ። ምግቡ ግን መርዝ ስለነበረበት ሁለቱም ልጆች ሞቱ። የሰፈሩ ነዋሪዎችም ልጆቹ የሷ መሆናቸውን  የሚያውቁት ስለነበሩ፣ ሟቾቹን ወደ እናታቸው ወስደው አደረሱላት። እናታቸውም ልጆቿን ሞተው ባየች ጊዜ እጅግ አዘነች፣ እያለቀሰችም እንዲህ አለች፦ «ቀን ሳለቅስ ውዬ ደገምኩት ሌሊቱን፤ ሥራ ይጓዳል ወይ እንዲህ ባለቤቱን!» ይህ ታሪክ እንደ ተረት ቢነገርም፣ የሚያስተምረን ትምህርት ግን ከቁርኣንና ከሶሒሕ ሐዲስ መሠረቶች ጋር የሚስማማ ነው፤ ማለትም ምቀኝነትንና ጥላቻን መተው፣ ለሌሎች መልካም መመኘትና ደግነትን መለማመድ ነው። የመጨረሻ ምክር ወንድሜ! ከሰዎች ጋር ስትኖር ልብህን አታበላሽ። ማንም ሰው አላህ የሰጠውን በረከት ሲያገኝ አትቀና። ይልቁንም በረከቱ እንዲጨምርለት ዱዓ አድርግ። አላህ ልባችንን ከምቀኝነት፣ ከጥላቻና ከቂም ያጽዳልን። ለሙስሊሞች ሁሉ መልካም የምንመኝ ባሮቹ ያድርገን። ደግነትንና መልካም ምግባርን ይስጠን። ከእኛም የሚወደውን ይቀበል። اللهم طهّر قلوبنا من الحسد والحقد والبغضاء، واجعلنا من أهل الإحسان وحسن الخلق، ووفّقنا لمحبة الخير للمسلمين، وبارك لنا ولهم فيما أعطيتنا وأعطيتهم. آمين. https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

⭐ሶባ ቢላል መስጅድ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ላይ የተደረገ ሙሀደራ ▫️ በ'ወንዲም 'አቡ ኢምራን ሙራድ 🕋 ✅:-ርዕስ: ✍منْ هُوَ الصَّحَابِيُّ الْجَلِيلُ بِلاَلُ بْنُ رَبَاحٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ؟ ቢላል ኢብኑ ረባህ ማነው?!! https://t.me/sobabilelmesjide https://t.me/sobabilelmesjide

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ እህቶች በሴት ኡስታዛ ቁርአንን በተጅዊድ ልቅም አድርጋችሁ መቅራት ምትፈልጉ ... ተአሉ ይሄ እድል ሳያመልጣችሁ 🎀 @Bint_Aliy54 በዚህ ኑ ልውሰዳችሁ