قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Ir al canal en Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
901
Suscriptores
-424 horas
-167 días
+4030 días
Archivo de publicaciones
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የእስልምና ሃይማኖት ገርነት
~
ከአቡ ሁረይረህ (አላህ ይውደድላቸው) ተይዞ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" إن الدين يسر، ولن يشاد الدين أحد إلا غلبه، فسددوا وقاربوا، وأبشروا، واستعينوا بالغدوة والروحة وشيء من الدلجة "
“የኢስላም ሃይማኖት ገር ነው። ማንም ሰው ይህን ሃይማኖት አጉል ለማጥበቅ አይታገልም፣ የሚረታው ቢሆን እንጂ። ስለሆነም አስተካክሉ፣ አጠጋጉ፣ መልካምን ነገርንም ተስፋ አድርጉ። በጠዋት፣ በማምሻ እና በሌሊቱ ክፍል በመጓዝም ታገዙ።”
[ቡኻሪይ (39) እና ሙስሊም (2816) ዘግበውታል።]
ከሐዲሡ የሚወሰዱ ትምህርቶች፦
=
1. የእስልምናን ሃይማኖት ገርነትና ቀላልነቱን፣ የግዴታዎች ውስን መሆን እና ከማጨናነቅና ከጽንፈኝነት የራቀ እንደሆነ ይገልፃል።
2. “የሐዲሡ መልእክት በሃይማኖታዊ ተግባር ላይ አጉል የሚያጠብቅና እዝነትን የሚተው ሰው ሁሉ ተረትቶ ከመስመር መውጣቱ አይቀርም ማለት ነው።” (ፈትሑል ባሪ፣ ኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒይ (1/117))
3. ኢብኑል ሙነይዪር (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፦ “በዚህ ሐዲሥ ውስጥ የነብይነታቸው ማረጋገጫ ምልክት አለ። ይሄውም እኛም፣ ከኛ በፊት የነበሩ ሰዎችም በሃይማኖት ድንበር ማለፍ ውስጥ የሚገባ ሰው መጨረሻው የሚርረታ መሆኑን በርግጥም አይተናል።” (ፈትሑል ባሪ፡ (1/117))
4. የኢስላም ጥብቅ ህግጋቱ ለአፈፃፀም የሚያስቸግር ሁኔታ ሲገጥም የፈፃሚውን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ይላላሉ። ለምሳሌ ቆሞ መስገድ ያልቻለ ተቀምጦ ይህንንም ያልቻለ ተኝቶ ይሰግዳል። ለውዱእ ውሃ ያጣ ወይም ውሃ መጠቀሙ የሚጎዳው የሆነ ሰው ተየሙም ይፈቀድለታል። ጥብቅ ሁኔታ የገጠመው ሰው ዐስርና ዙህርን ወይም መግሪብና ዒሻእን በአንደኛው ወቅት ስብስቦ (ጀምዕ አድርጎ) መስገድ መስገድ ተፈቅዷል። መንገደኛ ሰው ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት አድርጎ ይሰግዳል። በህመም ወይም በጉዞ መፆም የተቸገረ ሰው አፍጥሮ ሌላ ጊዜ እንዲፆም ተፈቅዷል። በእርግዝናና በማጥባት እንዲሁ። ምሳሌዎቹ በጣም ብዙ ናቸው። እንዳጠቃላይ "አስገዳጅ ችግር የማይፈቀድን ነገር ያስፈቅዳል" የሚለው መርህ የታወቀ የፊቅህ ህግ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
﴿يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ وَعْدَ اللهِ حَقٌّ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِاللهِ الْغَرُورُ • إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَاتَّخِذُوهُ عَدُوًّا إِنَّمَا يَدْعُو حِزْبَهُ لِيَكُونُوا مِنْ أَصْحَابِ السَّعِيرِ﴾.
«اللَّهُمَّ إنَّا نَعُوذُ بِكَ مِنْ دُنْيَا تَمْنَعُ خَيْرَ العَمَلِ وَمِنْ حَيَاةٍ تَمْنَعُ خَيْرَ المَمَاتِ».
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ለመንጋዎቹ አድርሱልኝ⁉️
----------------------
ውብ መንሀጃችንን በውብ የምንስላት፡
ዘወትር ጧት ማታ የምናዜምላት፡
እኛ ንፁሀን ነን ለማለት አይደለም፡
ወንጀለኛ በሉን ስደቡን ግደለም፡
አጥላሉን ስደቡን ለኛ አትጨነቁ፡
ግን ደግሞ በዚህ ልክ አትጨማለቁ፡
በመንጋ ጫጫታ ሀቅን አትልቀቁ፡
አይበጅም አሏህ ዘንድ አይጠቅምም ሀቂቃ፡
የሀሰት ትርክቱ ይበቃናል በቃ፡
ሁሌም አትዋሹባት በተዋበው ስሟ፡
እሷን አታጠልሹ ፅኑ ነው አቋሟ፡
በህጓ ባንፀናም እንሞትላታለን፡
ከራሳችን በላይ ለሷ ክብር አለን፡
......ደግሞ...
መንሀጅ ተረድቶ ሐቅን ላወቀው፡
በክፉ ፀባይ ሰው ለሚንቀው፡
ዱዐዕ አድርጉለት ምላሱ ልቡን እንድታረቀው፡
.....ይገርማል ብቻ...!
በምላስ የቆሙ በሀሳብ የሞቱ፡
ትልልቅ ህፃናት ስለበረከቱ፡
እስኪ ለመንጋዎች መዳኒት አምርቱ፡
መንሀጅ ገብቶኛል የሚለን አካል፡
በየትም ሔዶ ፊትና ያቦካል፡
ታዲያ ይሔ ሰው ለህክምና ወደት ይላካል⁉️
ጀረህ ወተዕዲል፤
ገብቶኛል የሚል በስሜት ሰክሮ እየደለቀ፡
መንጋ ሰብስቦ፤
ያልበላውን ሲያክ ጥፍሩ ላለቀ፡
ማን አለ እንደዚህ
ከክብር ማማ ወደታች ወርዶ ለስሜቱ ሲል የተዋደቀ፡
ማን አለ ታውቃላችሁ⁉️
አንዳንዱ ጥፍራም በአፉ ይለካል፡
ገደል ለመግባት ጣራ ይነካል፡
በየትም ቦታ ፊትናን ይሰብካል፡
ሐቅ ሲነገር አ'ትሽሽ አትደንብር፡
ቢመርም ዋጠው ለመንሀጅ ክብር፡
....በኑረዲን አል-ዓረብ....
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
ባህሩ ተካ የተባለ ግለሰብ <<በሀገራችን ከኢብኑ ሙነወር በላይ ለሱና ጠላት የለም>> ይለናል።
ማንነትህን እና የውር ድንብር አካሄድህን #ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ለሰለፍያ ሳይሆን #ለኔ ብትል ይቀል ነበር።
<<አልተቀየርንም፤ ለሰዎች የሚገባቸዉን ቦታ መስጠት አወቀንበት እንጂ።>>
✍️ ኡስታዝ አቡ ሱፍያን አላህ ይጠብቀው
ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ ኢብኑ ተይሚያ አንድ ጊዜ እንዲህ ሲሉ መከሩኝ፦
👉 «ቀልብህን የፈሰሰበትን ሁሉ እንደሚመጠውና ሲጨምቁትም ያንኑ እንደሚተፋው #እስፖንጅ አታድርገው። ይልቁንስ እንደ #መስታወት አድርገው። ብዥታዎች በገፅታው ላይ ያልፋሉንጂ ወደ ውስጡ አይገቡም። አጥርቶ ይመለከታቸዋል፣ በጠጣርነቱ ደግሞ ይመልሳቸዋል። አንተም ባንተ ላይ የመጣውን ብዥታ ሁሉ ለልብህ ካጠጣኸው የብዥታዎች መኖሪያ ይሆናል።»
=
የቴሌግራም ቻናል፦
http://t.me/Abulabas1444
http://t.me/Abulabas1444
📚 ۞ مفتاح دار السعادة【1/443】۞
ሀዳድዮች እና ለተምዮች ማለት''የሚጮሁትን የማይኖሩ #አጃዒብ ሰዎች ናቸው።''
Repost from Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)
ሙሓደራ ቁጥር 241
ክፍል 5
ርዕስ= ረድ በ ሙስጠፋ አብደላህ ላይ
"መስዓለቱል ዑዝር ቢል ጀሕል''
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም)
https://t.me/UstazKedirAhmed
موعظة بليغة
سيسالك الله يوم القيامة عن هذا الجهاز الذي تحمله في يدك
🎙:-الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله
"አላህን ማውሳትን ከሚያስረሳ ፀጋ፤
ወደ አላህ የሚያዞርህ መከራ በላጭ ነው።"
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላ፞ህ
(ጃሚዑል መሳኢል: 9/387)
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከማንም ጋር በገባበት ልንገባ፣ በወጣበት ልንወጣ የህይወት ዘመን ውል የለንም። መንሃጅ ያገናኘናል። መንሃጅ ይለያየናል። መንሃጅ ከለያየን ከትላንት ቀርቶ ከዛሬ ወዳጅም ጋር እንለያያለን። መንሃጅ ካገናኘን ዛሬ ከምንርቃቸው አካላት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን እንጓዛለን። መለኪያችን የሰለፊያ መንሃጅ ብቻ ነው። ትላንት አንድ የነበርን የተለየናቸው አሉ። ትላንት ተወጋግዘን ዛሬ ከልብ የምንወዳቸው ብዙ ናቸው። አላህ በሰለፊያ ላይ ያፅናን።
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
🔘አጭር እና ቆንጆ የጁሙዓ ኹጥባ
👤 ኹጥባውን ያደረጉት፡ ሸይኽ አህመድ (ከሳዑዲ ኤምባሲ)
📍 ቦታ፡ አዲስ አበባ — ቦሌ ጀዕፈር መስጂድ
🗣 ቋንቋ፡ በአረብኛ ቋንቋ የተደረገ
📖 በኹጥባው ላይ የተዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች
① ተውሂዱል ኡሉሂያ (የአላህን ብቸኛ ተመላኪነት)
🔘 የኢባዳ ዓይነቶች በሙሉ ለአላህ ብቻ እንደሚገቡ በሰፊው ተዳሷል።
② የተውሂድ አሳሳቢነትና ታላቅነት
🔘የሰው ልጅ የተፈጠረበት ዋና ዓላማና የእስልምና መሠረት መሆኑ በሰፊው ተብራርቷል።
③ የሽርክ አስከፊነት
🔘አላህ ዘንድ የማይማር ትልቅ ወንጀልና የሥራዎችን ዋጋ የሚያሳጣ መሆኑ በሰፊው ተብራርቷል።
④ ስለ ቢድዓ ምንነት
🔘ቢድዓ በዲን ላይ የሚያስከትለው አደጋና ትክክለኛው መንገድ ምን እንደሆነ በሰፊው ተወስቷል።
⑤ ኢኽላስ እና ሙታባዓ በዒባዳ ላይ ያላቸው አስፈላጊነት
🔘ማንኛውም መልካም ሥራ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ለአላህ ተብሎ ጥራት ተደርጎ የተሰራ(ኢኽላስ) እና የነቢዩን ሱና መከተል (ኢትባዕ) ግዴታ መሆናቸው ተብራርቷል።
⑥ ስለ ተቅዋ (አላህን መፍራት)
🔘የአላህን ትእዛዝ ማክበር፣ ክልከላዎቹን መራቅና የልብ መረጋጋትን ስለሚያስገኘው ተቅዋ ምክር ተለግሷል።
አላህ የሰማነውን ሰምተው ከሚተገብሩትና የተውሂድ ባለቤቶች ከሆኑት ባሮቹ ያድርገን!
ሼር ይደረግ🔗🔗🔗https://t.me/ansuar_muhammed_0088
Repost from የአብዱረሕማን አቡ ዑሠይሚን ሙሐደራዎች ስብስብ ቻናል
✺ የጁሙዓህ ~ ኹጥባ
──────⊱◈◈◈⊰───
❑ርእስ፦ « የነብዩሏህ ዒሳ ታሪክ »
« በሶፈር 17 / 1448 ھ የተደረገ »
🎙 አብዱረሕማን አቡ ዑሠይሚን
⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍⬍
t.me/MuhaderahChannel/1373
ዛሬ ጁመዓ ነው
اللهم صلّ على نبينا محمد ﷺ وآله وسلم🤍
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሙሓደራ ክፍል 189
አዲስ ሙሓደራ ክፍል 01
ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ
የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇
““የ አብዱል ሀሚድ አልለተሚይ እና ሁሰይን ሙሀመድ ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም)
https://t.me/UstazKedirAhmed
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
""ሙሓደራ ክፍል 190 ""
አዲስ ሙሓደራ ክፍል 02
ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ
የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇
““የ አቡዘር (አቡ ጦልሓ) ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም)
https://t.me/UstazKedirAhmed
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
""ሙሓደራ ክፍል 191""
አዲስ ሙሓደራ ክፍል 03
ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ
የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇
👉““የ አብዱልሀሚድ ፣ሀሰይን እና አቡዘር ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““
👉 እርስ በ እርስ ባልተግባቡበት ነጥብ አንድ ነን ማለታቸው
👉 ለከት የሌለው የተገጫጨ ንግግራቸውን ማጋለጥ
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም)
https://t.me/UstazKedirAhmed
