Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና
Ir al canal en Telegram
- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
761
Suscriptores
+2324 horas
+1617 días
+36130 días
Archivo de publicaciones
ወደ ማለዳ አካባቢ እንዳለው ሰላም አዘል የንጋት ድባብ የህይወታችን ምሽትም የራሱ ንጋት አለው።
ኢንሻአላህ!
"....እሷ ከተስተካከለች አካል በሙሉ ይስተካከላል እሷ ከተበላሸች አካል በሙሉ ይበላሻል" ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ
ክፍል 2. ነፍስ
-ፊጥራ
-ነፍስ
-ሩህ
-አቅል/አይምሮ
-ቀልብ/ልብ
-ተዝኪየቱ ነፍስ/ራስን ከወንጀል ማፅዳት
ለዛሬ ነፍስን በጣም በአጭሩ እናያለን ኢንሸአላህ!
ነፍስ ምንድነው?
ነፍስ 'ራስ' (self or soul) ማለት ነው። ወይም በኢስላማዊ የሳይኮሎጂ ትርጓሜው 'የውስጥ ዝንባሌ' ወደ ማለት የቀረበ ትርጓሜ አለው።
ነፍስ በተለያየ የእድገት እርከን ውስጥ የምታልፍ ሲሆን እነዚህም በ3 ተከፋፍላወ ቁርአን ላይ በሚከተለው መንገድ ይገኛሉ።
የነፍስ ደረጃዎች
1. ነፍሱል - አል - አማራ:- ('አዛዥ ነፍስ') ወደ መጥፎ ዝንባሌዎች እንዲሁም ወደ ሀጥያታዊ ሀሳቦች የምትመራ ስትሆን ዝቅተኛውን የነፍስ ደረጃ ትወክላለች። ስጋዊ እና ደመ ነፍሳዊ ፍላጎቶችን ሰዎች እንዲፈፅሙም ትጎተጉታለች።
2, ነፍስ አል - ለዋማህ:- ራሷን ወቃሸ ነፍስ - ከፍ ያለ የሰውን ልጅ ንቃት ስትወክል ድክመቷን እና ወንጀሎቿን የምታውቅ ፣ ስህተት ላይ ስትወድቅም ራሷን የምትወቅስ ራስ አወቅ እና ሞራል ገዝ የሰው ልጅ የህሊና ደውል ድምጽ ናት።
3, ነፍስ አል - ሙጥመኢነህ:- የሰከነች ነፍስ - ይህ ውስጣዊ ህብረት እና ሰላም የሚገኝበት ከፍተኛው የመንፈስ ልህቀት እና ራስን የመግዛት ደረጃ ነው።
ከምእራብያውያን ስነልቦና አንፃር ይህ አስተሳሰብ ሲታይ:-
እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ሶስት የነፍስ እድገት እርከን ሀሳቦች ከ ሲግመንድ ፍሩይድ id, ego እና super ego ጋር በቀጥታ አያይዘው የሚተረጉሙት ሰዎች አሉ። የተወሰነ የፅንሰ ሀሳብ መመሳሰል ባይጠፋም ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ላይ ይህ ፅንሰ ሀሳብ መንፈሳዊ ይዘቱ እና አምላካዊ መሠረቱ ጠንካራ ሲሆን የሲግመንድ ሀሳብ ግን ከምድር እና ከስጋዊነት ገደብ ያልተላቀቀ አካላዊ/bodily እና አይምሯዊውን የሰው ልጅ ስሜታዊ እና ሞራላዊ እድገት የሚገልፅ የተገደበ የአስተምህሮ ዘርፍ ነው።
በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ውስጥ የ ነፍስ ጥናት
ደረጃ በደረጃ የሰውን ልጅ በነዚህ እርከኖች ተጉዞ ከፍተኛውን የመስከን/ሙጥመኢና (tranquility) ከፍታ ላይ እንዲወጣ ማስቻል መንፈሳዊ ንቃት እና እርካታ ላይ በማድረስ ከፈጣሪው እና ከራሱ ጋር ያለውን ህብረት የሚያሳድግበት እርከን ሲሆን ፤ በወንጀል ድጋሚ ወደ ታች ቢወርድም ወደ ቀመሳት የስክነት የከፍታ ጣእም ሳይሰለች እንዲመላለስ የማድረግ ራስን ከመጥፎ ባህሪያት እና መንፈስን ከወንጀል የማፅዳት/ተዝኪያ የትግል መንገድ/ሱሉክ ነው።
✍️
ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ
አዘጋጅ እና ፀሀፊ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ)
ኢንሻአላህ ይቀጥላል...
ታላቅ ፈተና እና ሽልማት
እዚህች አለም ላይ ያልተሰሙ ብሶቶች ፣ ያላታዩ ህመሞች እና ጠራጊ ያጡ እንባዎች በርካታ ናቸው።
መደመጥ ብቻ የሚፈልግ ፥ 'አይዞህ' ብቻ ቢባል የመኖር ተስፋው የሚያንሰራራ ፣ 'አለሁልህ ቢባል' ተስፋ ቆርጦ ያቆመውን ሙከራውን የሚቀጥል... ብዙ በሰው ተከቦ ሰው የተራበ ወይም በብቸኝነት ብርድ የተመታ ሰው አለ....ሌላም ሌላም...።
እኔም አላህ በዚህ የሰው ልጆች ስቃይና እና ህመም የሚጎርፍበት የስራ ዘርፍ እና ህመም ሳታቋርጥ ለምትሰማበት የሙያ አይነት ስላጨኝ ታላቅ ፈተና እና ሽልማት መሆኑን እረዳለው።እዚህ ቦታ ላይም ስቆም ጥቂት ህመም ባቃልል የተወሰኑ ሀዘኖችን ብቀንስ ብዬ ነው።
ሀዘናችሁን ልሰማ ጭንቀታችሁን ልጋራ ከማንም የደበቃችሁትን ቁስል ገልጣችሁ እንድታሳዩኝ አላህ ስለመረጠኝ ትልቅ እድል እና እዝነት ነው ለኔ።
ብዙ ልብ የሚነካ ታሪኮችን እና የሚያስተክዙ አንዳንዴም የሚስነቡ ህይወቶችን እሰማለሁ....የሰው ልጅ በማትገምቱት ህመም እና መከራ ውስጥ ያልፋል። ሁሉም ጓዳ የሸሸገው የራሱ ጉድ አለው።
ሁሌም የልቤ በር ልናንተ ክፍት ነው። የምችለውን ላግዛችሁ ከጎናችሁ ልቆም በአላህ ስም ቃል እገባለሁ።
ይህ ኢስላማዊ ምናባዊ/virtual የስነልቦና መዕከላችን ከሀሳብነት ወደ ተጨባጭ ማዕከልነት ተቀይሮ ብዙዎችን እንዲታደግ ወደ አለምነው ለመድረስ የምናደርገውን ጉዞ ከጎናችን በመሆን ለምታሳዩን ፍቅር በቅድሚያ እያመሰገንን የዘውትር ዱአችሁ እና አብሮነታችሁ እንዳይለየን በድጋሚ እንጠይቃለን።
አሁንም ስራችን በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል....
@usmanoman ላይ ፃፉልኝ ለማንኛውም አገልግሎት እና ሀሳብ
✍️usman mus
from Usmanic islamic psychology
በብዛት እንዲለቀቅ የምትፈልጉት እና የወደዳችሁት የዚህ ቻናል ዝግጅት ምንድነው?
የሚፈውስ ዱአ
اللّهُمّ إني أسألك العفو والعافية في الدنيا والآخرة.
"አላህ ሆይ ይቅርታህን እና ደህንነትን/ጤናን በዚህ አለም እና በቀጣዩ አለም እጠይቃለሁ።"
ሼር የማድረግ ጥሪ/ቻሌንጅ
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አዲሱ የኢስላሚክ የስነልቦና አገልግሎት የሚሰጥ የቴሌግራም ቻናል ተከፈተ
- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች
- የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ።
- ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ።
ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ
ለወዳጅ ዘመድ ማጋራት አይርሱ
join ለማለት 👇👇
https://t.me/usmanic_psychology
መልስ ሁለት ክፍል 1
በአይን የሚገባው የዘመኑ አደገኛው እፅ (የፖርን ፊልም)
ማህበረሰቡ የማይነጋገርባቸው እና ማውራቱንም እንደ ነውር (taboo) አድርጎ ከሚቆጥራቸው
የህዝብ የቤተሰብ እና የመንፈሳዊነት መርዝ የሆነው እርቃን እና ወሲባዊ ትእይንቶችን የመመልከት ሱስ ከምን ጊዜውም በላይ በጣም እየተሰራጨ ነው።
ይህ 'ኢንዱስትሪ' ከ 10 ቢሊዮን ዶላር እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር በአመት የሚያንቀሳቅስ ሲሆን የተመልካቹ ቁጥርም በየጊዜው እየጨመረ እንደመጣ ጥናቶች ያሳያሉ።
በፊት በፊት ወንዶች ይህን ነገር በዋነኛነት እና በስፋት እንደሚያዩ ቢገመትም አሁን ግን የሴቶች ወደ እዚህ መረብ ተጠልፈው እንዲገቡ አዘጋጆቹ ስልታዊ እና ይዘታዊ ለውጦችን በማካሄድ የሴት ተጠቃሚዎችን ቁጥር መጨመር ችለዋል።
በአለም ላይ ከ 70 - 90% ወንዶች እና ከ 30-70% of ደግሞ ሴቶች ይህን አደገኛ ፊልም እንደሚያዩ አንዳንድ ጥናቶች ይጠቁማሉ።
ከእድሜ አንፃር ስናየው ሴቶች 60% እና ወንዶች ደግሞ 90% ተመልካቾች ከ 18 - 30 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው
'computer in human behavior' ጆርናል ይዞት በወጣው መረጃ መሠረት ለዚህ (porn) ወሲባዊ ፊልም አንድ ሰው የሚጋለጥበት አማካይ እድሜ በአለም አቀፍ ደረጃ 11 አመት ነዉ።
አሰቡት እንግዲህ ምን ያህል ለጋ አይምሮዎች ለዚህ መርዛማ ትእይንት ያለ እድሜያቸው እንደሚጋለጡ
አንድ መሰል ነገሮችን (የፖርን ፊልሞችን) ማሠራጫ ፕላትፎርም ብቻ ባወጣው መረጃ በ 2019 ብቻ እስከ 42 ቢሊዮን traffic/ እይታዎች ከተለያዩ የአለም ክፍሎች አግኝቷል።
ይህ ማለትም የአለምን ህዝብ ብዙ እጥፍ የሚበልጥ ቁጥር ሲሆን ምን ያህል ተመሳሳይ ሰዎች በተደጋጋሚ ይህን ነገረ የመመልከት ሱስ ውስጥ እንደወደቁ ያሳያል። ይህ የተመዘገበው ደግሞ በአንድ የማሳያ ቦታ ብቻ ነው።
መሰል የእርቃን ፊልሞችን የመመልከት ልማድ እና ሱስ ለአይምሮ ጤንነት መቃወስ ትልቅ አሉታዊ አስተዋጽኦ አለው ፣ ለተዛባ የወሲብ ህይወት ፣ ለወሲብ የሚሰጥ የተጋነነ ግምት ፣ ሴሰኝነት ፣ መደበኛ ያላሆነ የወሲብ ልማድ እና ኢ ተፈጥሯዊ የሆነ የግንኙነት ምኞት ወዘተ...ከሚያስከትላቸው ተፅእኖዎች በጥቂቱ ነው
ብር ያመጣ ነገር በሙሉ በሚሰራበት በዚህ የሞራል ሚዛን በተንሻፈፈበት ዘመን ሁሉም ነገር የሚሸጥ እቃ ሁሉም ሰውም ገቢ እስካመጣ ድረስ ስሜቱን ህሊናውን እና ማንነቱን ገብሮ ለገንዘብ አምላኪዎች በእጅ አዙር ተገዢ የሚሆንበት የስርአት አልበኛ መተራመሻ የሆነች አለም ላይ እየኖር ነው።
ራሳችንን ከነፍሲያ ጉትጎታ ከሰይጣን ሹክሹክታ እና በስጋዊ ፍላጎት እሳት ከመቃጠል በሶላት በትግስት እና ወደ አላህ በመቅረብ ውሀ በማብረድ የአይምሯችንን ደህንነት የሚሰልበውን ይህን አደገኛ ሱስ እንዋጋ።
(ይህ ስለ ነገሩ አሳሳቢነት ጥያቄውን እንደመነሻ በመጠቀም የቀረበ የክፍል 1 ማስታወሻ ሲሆን ለወንድማችን ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ በክፍል 2 ምላሽ ላይ ይሰጣል)
ኢንሻአላህ
✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ።
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።
የሚገራላችሁ ወይም ወይም መተግበር የሚቀላችሁ የኢባዳ/የአምልኮ ዘርፍ የቱ ነው?
እስካሁን በአስተያየት እና በምርጫ ለተሳተፋችሁ ሁላችሁም የላቀ ምስጋናዬን እየገለፅኩኝ ለእህታችን የህይወት ምርጫና እና ውሳኔ ላይ የሁላችሁም አስተያየት ትልቅ ግብአት ነው።
እናንተም መሰል የህይወት ውሳኔ ግርታ እና ግራ መጋባት ካጋጠማችሁ በውስጥ መስመር @usmanoman ላይ በፅፉልን የባለሙያዎችን ድጋፍ እና እንደ አስፈላጊነቱ ደግሞ ማንነታችሁ ሳይገለፅ ለህዝብ አስተያየት ክፍት እናደርገዋለን።
በአላህ ፍቃድ የተጀመሩት ኢስላማዊ የስነልቦና አገልግሎት እና ሌሎቹም ነገሮች እንዲቀጥሉ ከጎናችን ሁኑ።
እኔም በዚህ ታሪክ ላይ የማጠቃለያ መልስ እና ሌሎችንም ፅሁፎች እቀጥላለው ኢንሻአላህ!
አሰላሙአለይኩም ኢስላማዊ የስነልቦና ድጋፍ እና የምክክር አገልግሎት እንዲሁም ፅሁፎችን ለብዙዎች ተደራሸ የማድረግ ስራ ከጀመርን ከራረምን
የላወቁ እንዲያውቁ ወደ እዚህ ግሩፕ አድ በማድረግ ተጠቃሚዎችን ያብዙ። እናመሠግናለን
ወደ እዚህ ሊንክ በመግባት አድ ያድርጉ።
https://t.me/+XYW03GmihQM3Yzhk
+2
የእህታችን ልብ የሚነካ ታሪክ! እንደዚህ አጋርታናለች።ካነበባችሁ በኋላ ሃሳባችሁን ከታች የምናያይዘው poll/መምርጫው ላይ አስፍሩ።
ፈጅር ተነስተን 'ከምድር ከራሷ እና በውስጧ ካለው በላይ የሚልቀውን'' ቀብሊያ/የቅድሚያ ሱና መሰገድ የላቀ የሆነው የአዱኒያ እና የአኼራ የመልካም ስራ በር ለማስከፈት ታላቅ እድል ይሰጣል።
መልካም ፈጅር
ጥያቄ ሁለት
አሰላሙአለይኩም እኔ የ 27 አመት ወጣት ወንድ ነኝ።በአንድ አሳሳቢ ነገር ተለክፍያለው።
እሱም ፖርን (የወሲብ ፊልም) የማየት ሱስ ነው። መች እንደ ጀመርኩ በቅጡ ባላስታውሰውም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቼ ሞባይል ስልካቸው ላይ ሲመለከቱ ማየት ግን የተለመደ ነገር ነበር።
ጠንካራ ኢስላማዊ መሠረት ያለው አሰተዳደግ ውስጥ ስላለፍኩኝ በጊዜው በጣም የምፀየፈው ነገር የነበረ ብቻ ሳይሆን እኩዮቼንም መመልከት እንዲያቆሙ እመክራቸው ነበር።
አሁን ብቻዬን ነው የምኖረው። በሚያሳዝን ሁኔታ ከብዙ አመታት በኋላ እኔም እዚህ ውስጥ ተዘፍቄ መገኘቴ በጣም የሚያስገርመኝ እና የሚያሳስበኝ ጉዳይ ነው።
ይህን ተከትሎም ሶላት ላይ መሳነፍ የስራ ተነሳሽነት ማጣት ህይወትን መጥላት እና ተስፋ መቁረጥ ይሰማኛል።
ካደረግኩት በኋላ ብዙ ሀፍረት እና ፀፀት ውስጥ እወድቃለሁ።ዳግም ላልመለስ አልቅሼ ተውበት ባደርግም ዳግም ራሴን እዛው ላይ አገኘዋለሁ።
ወደዚህ እይታ የሚመራኝ ተፈጥሯዊ ወሲባዊ ስሜቴ ሲሆን። ያማከርኳቸው ሰዎች እንዳገባ ይመክሩኛል ግን ይህን የማድረግ የሞራል እና የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ አልደረስኩም።
ከዚህ ለከት ከሌለው ስሜቴ እና ሱሴ እንዴት ልላቀቅ እባክህ ምክርህን ብትለግሰኝ።
[ጥያቄው በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተዋቀረ (case study) ነው።]
(የጥያቄውን ምላሽ ቻናላችን ላይ ይጠብቁ ኢንሻአላህ!)
#ኡስማኒክ_ኢስላማዊ_ስነልቦና
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ
ክፍል 1
-ፊጥራ
-ነፍስ
-ሩህ/spirit
-አቅል/አይምሮ
-ቀልብ/ልብ
-ተዝኪየቱ ነፍስ/ራስን ከወንጀል ማፅዳት
ለዛሬ ፊጥራን በአጭሩ እናያለን ኢንሸአላህ!
ፊጥራ ምንድነው?
ፊጥራ-: ተፈጥሮ ማለት ሲሆን የአንድ ነገር የመጀመሪያ ያልተነካካ ምንነት ነው። ሁሉም የሰው ልጅ አላህ ውስጡ ባስቀመጠው አካላዊ መንፈሳዊ እና ባህሪያዊ የማንነት አይነት እና ቅርፅ ውስጥ ሆኖ ይወለዳል። ይህም ፊጥራ ይባላል።
በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ውስጥ የፊጥራ ጥናት
የሰው ልጅ ዝንባሌ ተሰጥኦ እና ራእይን አላህ ሲሰራው ከሰጠው ተፈጥሮአዊ አቅም ላይ ተመርኩዞ እንዲወጣ አለም ላይም አስተዋጽኦዎን አሳርፎ መሄድ የሚችል ምርታማ እና ደስተኛ ሰው ለማፍራት የተለያዩ ስነ ዘዴዎችን የሚጠቀም ሰው አገዝ አንድ የኢስላሚክ ስነልቦና ዘርፍ ነው።
(✍️
ከኢስላሚክ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ የተወሰደ
አዘጋጅ እና ፀሀፊ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ)
ኢንሻአላህ ይቀጥላል ....ፈጅር ተነስታችሁ በመስገድ የአይምሮ ጤናችሁን ጠብቁ።
አብዛኛው የጭንቀት የድባቴ እና የአይምሮ መታወክ መንስኤ ከፈጣሪያችን ጋር ያለን ግንኙነት በመበላሸቱ ነው።
እሱ ሀኪም ነው ያክመናል። እሱ የተበቃቃ ነው ይሰጠናል። እሱ አዛኝ ነው ያነሳናል።
አይዞን!!
በኢስላም አስተምህሮ መሠረት ጭንቀትን ለመቀነስ የሚረዳው የኢባዳ/አምልኮአዊ ተግባር የቱ ነው?
ኢስላማዊ የስነልቦና አገልግሎት ለምትፈልጉ በሙሉ
የትዳር የቤተሰብ እና የስራ ጉዳይ ድብርት ወይም ጭንቀት ውስጥ ካላችሁ ወይም ለሌላ ማንኛውም ጉዳይ @usmanoman ላይ አዋሩኝ (ሁሉም በሚስጥር የሚጠበቅ ነው)
ወይም 0912027023/ 0921390122 ደውሉ
ከታች የተያያዘውን ሊንክ በመንካት ፎርም መሙላት አይርሱ ሲጨርሱ ከላይ በሰፈሩት አድራሻዎች ያሳውቁን። 👇👇👇
____
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdl5ehGATYpwQpFCLs66NcS26Laedz36GRjQze0Gxyw1SzzBA/viewform?usp=header 🔗📝
__
