Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና
Відкрити в Telegram
- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
787
Підписники
+2324 години
+1617 днів
+36130 днів
Архів дописів
ታሪኳን ካነበባችሁ በኋላ ትክክል ነው የምትሉትን ውሳኔ ምረጡ (ምርጫው ከአምስት ቀን በኋላ ይዘጋል)
+1
ታሪክ ሁለት
የእህታችን ልብ የሚነካ ታሪክ! እንደዚህ አጋርታናለች።ካነበባችሁ በኋላ ሃሳባችሁን ከታች የምናያይዘው poll/መምርጫው ላይ አስፍሩ።
ለእህታችን የቀረበ የማጠቃለያ ተጨማሪ የመፍትሔ ሀሳብ እና መልስ
እህታችን በዚህ አጭር የአለም ቆይታዋ የአባቷ ሞት ፣ ሁለት ያልተሳኩ ትዳሮች እና ሌሎችም በዙ የህይወት ውጣ ውረዶችን አልፋለች።
በቅድሚ አላህ ታላቅ ትዕግስትን እና መፅናናትን እንዲለግስሽ እንማፀነዋለን ፤ ጉዳዮችሽንም ገር ያደርግልሽ። በመቀጠል ህይወትሽን የሚመለከቱ የተወሰኑ ነጥቦች ለማየት በአላህ ፍቃድ እንሞክራለን።
እህታች ካጋጠማት ያልተጠበቀ የህይወት ምስቅልቅል ለማምለጥ ብላ የገባችበት 2 ትዳር ሁለቱም ሳይሳኩ መቅረታቸው ሌላ ተደራቢ የህይወት ሸክም እና ጫና ፈጥሮባታል። ትዳርን የሚያህል ብዙ ማሰብ እና በትክክል የመወሰንን አቅም የሚጠይቅ የህይወት ምእራፍ በለጋ እድሜዋ እና በችኮላ መግባት ትልቅ አደጋ ያለው ውሳኔ ነበር።
በሁለት ያልተሳኩ ትዳሮች ውስጥ ማለፍ ደግሞ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይሆንም። ይህም ለራስ ያለን ግምት በማዛባት በራስ መተማመንን (self-esteem) ሊጎዳ ይችላል።
ውሳኔዎቻችን ፦ አስተዳደጋችንን ፣ ተፈጥሯዊ የማንነት ዝንባሌያችንን ፣ እና አስተሳሰባችንን... ይመስላሉ። አንዳንድ ሰዎች ለደረሰባቸው ችግር አቋራጭ መፍትሔ ሲፈልጉ ( ትዳርን ፣መሠደድን ፣ መለያየትን ...)ሌሎች ደግሞ መሠረታዊ ለውጥ በማድረግ ህይወታቸው በአካባቢያቸው እና በራሳቸው ላይ በመስራት ከራሳቸው አልፈው ለሌላው ሰው ተፅፃኖ ማድረስ የሚችል ማንነት ይገነባሉ።
የእህታችን ህይወት ላይ ተደጋጋሚ ሁለት በችኮላ የተወሰኑ ውሳኔዎች በጉልህ ይታያሉ። የዚህ ምክንያት ካለችበት የኑሮ ጫና ሁኔታ ከግል ባህሪዋ እና ከሌላም ምክንያት ሊቀዳ ይችላል።
መንስኤው ምንም ይሁን በትክልል ሳያስቡ በፍጥነት አንዱን ጥሎ ሌላን ቶሎ ለማንሳት
መሯሯጥ ተመሳሳይ ጥሩ ያልሆነ ውጤትን ማስከተሉ አይቀርም።
በመንታ መንገድ መሀል ላይ የቆመችው እህታችን አሁን የዩኒቨርስቲ ነጥብ ቢመጣ ግቢ ልግባ ወይስ ወደ ቀጣይ የትዳር ምእራፍ ልሻገር ? የሚል 'መወሰን የሚያስቸገር' ያለችው ሁኔታ ውስጥ እንደወደቀች ትናገራለች።
እህቴ ሆይ! ህይወት በሁለት አማራጭ ብቻ የተከበበች ጠባብ የትግል ሜዳ አይደለችም።ወይ ማግባት ወይ መስራት ወይ መማር ወይ አለመማር ብቻ በሚል የታጠረችም አይደለችም ።
ህይወት ፈርጀ ብዙ እና የተለያዩ ነገሮችን በተመሳሳይ ጊዜ በብቃት የማካሄድ የምትፈልግ የፍልሚያ ስፍራ ነች።
በህይወትሽ ላይ ያለፈው ሁሉ አላህ የወሰነው ነው እና በፀፀት ራስሽን ሳትቀጪ ማዕበሉ እያናወጠሽም ቢሆን ቆም ብለሽ በተረጋጋ መንፈስ እና በጥሞና ስለ ቀጣይ የህይወት እቅዶችሽ በተረጋጋ መንፈስ ለማሰብ ሞክሪ።እቅዶችሽን ፃፍያቸው።
ትምህርትሽ ሳይቆም የምትሰሪበት ፣ ራስሽን የተለያዩ ከህሎቶች የምታሰለጥኝበት ፣ዲንሽን የምትማሪበት መንገድ አመቻችተሽ ራስሽን በእውቀት እና በ ክህሎት የተሟላች ልበ ሙሉ እና የምትፈልገውን የምታውቅ ሴት ለመሆን ራስሽ ላይ ሳታቋርጪ ስሪ።
ትዳር ትልቅ የነፍሶች መስከኛ የልቦች መረጋጊያ ደሴት ሁለት ልቦች በፍቅር የሁለት አለም ደስታቸውን የሚገነቡበት የትውልድ መፍለቂያ የተቀደሰ ማእከል እንጂ ከሆነ ነገር የሚያመልጡበት መሸሸጊያ ስፍራ ሊሆን አይገባውም። ከሆነም መጥፎ ውጤት ያስከትላል።
አሁን ያለሽበት ሁኔታ ባትወጂውም የነገን ተስፋሽን ለመስራት ጥሩ መሠረት ነው እና ከእናትሽ ጋር ሁነሽ ራስሽን እያበቃሽ ከሷ ተሞክሮዎች እየተማርሽ ትምህርትሽን በአቅራቢያ ቦታ እየተማርሽ ከአላማሽ የሚያሰናክሉ ለሀራም ጥያቄዎች በርሽን ቆልፈሽ በፆም እና በስግደት ታግሰሽ ይህን ጊዜ ለማሳለፍ እና በጥራት ማሰብ የምትችይበት የህሊና አቋም ላይ ለመድረስ ጥረት አድርጊ።
ከዚያ የሚሆንሽን ሰው በትክክል መምረጥ እና ማወቅ የምትችይበት የአስተሳሰብ እድገት ላይ ስትደርሺ ሁሉም ነገር ጊዜውን ጠብቆ ይሆናል። አትዘግዩ ፣ አትቸኩዪ በመሀከል ያለው ተረጋግቶ አሰቦ የመወንን ልምድ አዳብሪ።
አላህ መልካም ትዳርን ለእህቶቻችን በሙሉ ይስጣቸው!!
በኮሜንት ሀሳብ በመስጠት እና ምርጫ መስጫው ላይ በመምረጥ ለተሳተፋችሁ በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬን በአላህ ስም አቀርባለሁ።
✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ።
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።ምስጢራዊነቱ
"የፊታቸው ሰማይ ላይ ፈገግታ የማትጠልቅ የዘውትር ፀሀይ ነበረች ፥ ገፃቸው ለተመለከታቸው በሙሉ ደስታን የሚያጋባ የሀሴት ድግስ ነው። በትህትና የተቀመረ የማማር አክሊልል ደፍተዋል ፣ በነቢይነት ስክነት ሞገስ እና በሰውነት ጨዋ ማንነት ገፃቸው የረጋ ነው...።"
(መሰል ውብ አንቀፆችን ስለ ውዱ ነብይ (ﷺ) የሚያገኙበትን 'ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ' መፅሐፍ በመግዛት ከመልእክተኛው ጋር በጥልቀት እና በውበት ይተዋወቁ።)
የኢስላማዊ ሳይኮሎጂ መፅሀፌ እስኪደርስ እቺ ስለ ውዱ ነቢይ (ﷺ) በውብ ቋንቋ እና በጥልቅ ሀሳብ የከተብኳትን መፅሀፍ ውሰዱ።
ርእስ= ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ
ፀሀፊ = ኡስማን ሙስጠፋ
የህትመት ጊዜ= ነሀሴ 2017 ዓ.ል
መፅሐፉን ለማግኘት በቴሌግራም ዩዘርኔም @usmanoman ወይም በስልክ 0921390122/ 0912027023 ላይ ያናግሩን
መልስ/ ክፍል ሁለት
ይህን የወንድማችንን ጥያቄ በሁለት ዙር እንድናየው ያስገደደን ነገር ነገሩ ከግለሰብ ችግር በላይ የሆነ የማህበረሰቡ ህመም እና የ
ሁሉንም በነፍስ ወከፍ የሚነካ ጉዳይ ስለሆነ ነው።
ግን አሁን ግለሰባዊ ትኩረት ሰጥተን ለዚህ ጥያቄ መልስ በመስጠት ለጊዜው ይህን ጉዳይ እንቋጨው።
ወንድሜ አሁን አንተን ይመታህ ፍላፃ አለም ላይ ብዙ ቢሊዮን ሰዎች እየተሰቃዩበት ቤተሰቦች እየፈረሱበት እና ማህበረሰብን ጥልቅ ዝቅጠት ውስጥ ከቶ ጥቂት ሺ ስግብግብ ሰዎችን ሀብታም በሚያደርግ የሰዎችን ገላ ሽጦ ገንዘበ ለማግኘት በተፈጠረ የህሙማን የቁማር ንግድ ነው።
አንተ ውስጥ የሚታየው ትልቁ ተስፋ ያልሞተችው የህሊናህ ደውል እና ራሷን ወቃሽ ነፍስ ናት።በክፉ አዛዧ ነፍስ ተጠልፎ በመውደቅ እና ራሷን በምትወቅሰው ነፍስ መሀከል ተነስቶ መንገድን የመቀጠል የተውበት/የንስሀ ምልልስ ይታይብሀል።
የወጣትነት ስሜትህ እና አለማግባትህ ለዚህ ተደጋጋሚ ስህተትህ በሰበብነት የሚጠቀሱ ጉዳዮች ቢሆኑም ለሁሉም የወንጀል መዳረሻዎች መፍትሄ አቅጣጫ ያስቀመጠው ኢስላም ያላገቡት የምግብ ሚዛናቸውን በመጠበቅ በፆም እንዲሁም እይታቸውን በማስተካከል ስሜታቸውን መቆጣጠር እንዲችሉ ይመክራል።
አላህ መልካም ትዳር እስኪለግስህ ድረስ በፆም የሚገኘውን ስሜት የመቆጣጠር አካላዊ እና መንፈሳዊ ጥቅም ለማግኘት ሞክር/ታገል።
በአይንህ የሚገቡ መሰል በተጨባጩ አለምም ሆነ በሞባይል የምታየችውን ወሲብ ቀስቃሽ ነገሮች አላህን ተመርኩዘህ ለማቆም ወስን።
ትእግስት እና ጥራት ያለው ሶላትም ስሜትን ለማረቅ ታላቅ መፍትሔ ነው።
ብቸኝነትህን የምታጠፋበት ኑሮ የሚጋራህ ሷሊህ/በጎ መንገድ የሚመራህ የወንድ ጓደኛ ቢኖርህ ብቻህን ሆነህ ለሰይጣን ሹክሹክታ እና ከነፍስ ወስዋስ ከመጋለጥ ራስህን ትታደጋለህ።
አስተዳደግህ ጥሩ የኢስላም መሠረት ያለው መሆኑን የጠቀስክ ሲሆን ለዚህም የወላጆችህ ወይም የአሳዳጊዎችህ ውለታ የላቀ መሆኑን ያሳያል።
ያንተ ታሪክ ግን የሚያስተምረን በቀና መስመር ውስጥ ማደግ ብቻ ከወንጀል የፀዳ ህይወት ለመምራት መሠረት እንጂ ዋስትና መሆን እንደማይችል ሲሆን። ድሮ ወደነበርክበት የፊጥራ/ተፈጥሯዊ የንፅህና እና የኢማን ጥንካሬ ለመመለስ ደጋግመህ በንስሐ ውሃ እየታጠብክ ነተውበትህን መንገድ ሳታቋርጥ ቀጥል።
ሰይጣን ተስፋ ሊያስቆርጥህ ደጋግመህ መውደቅህን ያስታውስህ ይሆናል ግን ተንኮሉን በ 'አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧን ረጂም እየታገልክ ፣ በ ቁል አኡዙዎች እየታከምክ ፈጅር ቢያመልጥህ ዙህርን እየሰገድክ አሱር ቢያልፍህ መግሪብን እየታገልክ ቋሚ የሆነ የአሰጋገድ ስርአት ውስጥ እስክትገባ ድረስ ሙከራህን ቀጥል ፤ ሶላትህን ባለማቆም ራስህን አግዝ።
በዱአ በርታ። አላህ ወጣቶቻችንን ከዚህ አጀገኛ እፅ ይሰውርልን።መልካም ትዳርም ይሰጣቸው።ይስጠን።
✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ።
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን
ወደ ማለዳ አካባቢ እንዳለው ሰላም አዘል የንጋት ድባብ የህይወታችን ምሽትም የራሱ ንጋት አለው።
ኢንሻአላህ!
"....እሷ ከተስተካከለች አካል በሙሉ ይስተካከላል እሷ ከተበላሸች አካል በሙሉ ይበላሻል" ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ
ክፍል 2. ነፍስ
-ፊጥራ
-ነፍስ
-ሩህ
-አቅል/አይምሮ
-ቀልብ/ልብ
-ተዝኪየቱ ነፍስ/ራስን ከወንጀል ማፅዳት
ለዛሬ ነፍስን በጣም በአጭሩ እናያለን ኢንሸአላህ!
ነፍስ ምንድነው?
ነፍስ 'ራስ' (self or soul) ማለት ነው። ወይም በኢስላማዊ የሳይኮሎጂ ትርጓሜው 'የውስጥ ዝንባሌ' ወደ ማለት የቀረበ ትርጓሜ አለው።
ነፍስ በተለያየ የእድገት እርከን ውስጥ የምታልፍ ሲሆን እነዚህም በ3 ተከፋፍላወ ቁርአን ላይ በሚከተለው መንገድ ይገኛሉ።
የነፍስ ደረጃዎች
1. ነፍሱል - አል - አማራ:- ('አዛዥ ነፍስ') ወደ መጥፎ ዝንባሌዎች እንዲሁም ወደ ሀጥያታዊ ሀሳቦች የምትመራ ስትሆን ዝቅተኛውን የነፍስ ደረጃ ትወክላለች። ስጋዊ እና ደመ ነፍሳዊ ፍላጎቶችን ሰዎች እንዲፈፅሙም ትጎተጉታለች።
2, ነፍስ አል - ለዋማህ:- ራሷን ወቃሸ ነፍስ - ከፍ ያለ የሰውን ልጅ ንቃት ስትወክል ድክመቷን እና ወንጀሎቿን የምታውቅ ፣ ስህተት ላይ ስትወድቅም ራሷን የምትወቅስ ራስ አወቅ እና ሞራል ገዝ የሰው ልጅ የህሊና ደውል ድምጽ ናት።
3, ነፍስ አል - ሙጥመኢነህ:- የሰከነች ነፍስ - ይህ ውስጣዊ ህብረት እና ሰላም የሚገኝበት ከፍተኛው የመንፈስ ልህቀት እና ራስን የመግዛት ደረጃ ነው።
ከምእራብያውያን ስነልቦና አንፃር ይህ አስተሳሰብ ሲታይ:-
እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ሶስት የነፍስ እድገት እርከን ሀሳቦች ከ ሲግመንድ ፍሩይድ id, ego እና super ego ጋር በቀጥታ አያይዘው የሚተረጉሙት ሰዎች አሉ። የተወሰነ የፅንሰ ሀሳብ መመሳሰል ባይጠፋም ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ላይ ይህ ፅንሰ ሀሳብ መንፈሳዊ ይዘቱ እና አምላካዊ መሠረቱ ጠንካራ ሲሆን የሲግመንድ ሀሳብ ግን ከምድር እና ከስጋዊነት ገደብ ያልተላቀቀ አካላዊ/bodily እና አይምሯዊውን የሰው ልጅ ስሜታዊ እና ሞራላዊ እድገት የሚገልፅ የተገደበ የአስተምህሮ ዘርፍ ነው።
በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ውስጥ የ ነፍስ ጥናት
ደረጃ በደረጃ የሰውን ልጅ በነዚህ እርከኖች ተጉዞ ከፍተኛውን የመስከን/ሙጥመኢና (tranquility) ከፍታ ላይ እንዲወጣ ማስቻል መንፈሳዊ ንቃት እና እርካታ ላይ በማድረስ ከፈጣሪው እና ከራሱ ጋር ያለውን ህብረት የሚያሳድግበት እርከን ሲሆን ፤ በወንጀል ድጋሚ ወደ ታች ቢወርድም ወደ ቀመሳት የስክነት የከፍታ ጣእም ሳይሰለች እንዲመላለስ የማድረግ ራስን ከመጥፎ ባህሪያት እና መንፈስን ከወንጀል የማፅዳት/ተዝኪያ የትግል መንገድ/ሱሉክ ነው።
✍️
ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ
አዘጋጅ እና ፀሀፊ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ)
ኢንሻአላህ ይቀጥላል...
ታላቅ ፈተና እና ሽልማት
እዚህች አለም ላይ ያልተሰሙ ብሶቶች ፣ ያላታዩ ህመሞች እና ጠራጊ ያጡ እንባዎች በርካታ ናቸው።
መደመጥ ብቻ የሚፈልግ ፥ 'አይዞህ' ብቻ ቢባል የመኖር ተስፋው የሚያንሰራራ ፣ 'አለሁልህ ቢባል' ተስፋ ቆርጦ ያቆመውን ሙከራውን የሚቀጥል... ብዙ በሰው ተከቦ ሰው የተራበ ወይም በብቸኝነት ብርድ የተመታ ሰው አለ....ሌላም ሌላም...።
እኔም አላህ በዚህ የሰው ልጆች ስቃይና እና ህመም የሚጎርፍበት የስራ ዘርፍ እና ህመም ሳታቋርጥ ለምትሰማበት የሙያ አይነት ስላጨኝ ታላቅ ፈተና እና ሽልማት መሆኑን እረዳለው።እዚህ ቦታ ላይም ስቆም ጥቂት ህመም ባቃልል የተወሰኑ ሀዘኖችን ብቀንስ ብዬ ነው።
ሀዘናችሁን ልሰማ ጭንቀታችሁን ልጋራ ከማንም የደበቃችሁትን ቁስል ገልጣችሁ እንድታሳዩኝ አላህ ስለመረጠኝ ትልቅ እድል እና እዝነት ነው ለኔ።
ብዙ ልብ የሚነካ ታሪኮችን እና የሚያስተክዙ አንዳንዴም የሚስነቡ ህይወቶችን እሰማለሁ....የሰው ልጅ በማትገምቱት ህመም እና መከራ ውስጥ ያልፋል። ሁሉም ጓዳ የሸሸገው የራሱ ጉድ አለው።
ሁሌም የልቤ በር ልናንተ ክፍት ነው። የምችለውን ላግዛችሁ ከጎናችሁ ልቆም በአላህ ስም ቃል እገባለሁ።
ይህ ኢስላማዊ ምናባዊ/virtual የስነልቦና መዕከላችን ከሀሳብነት ወደ ተጨባጭ ማዕከልነት ተቀይሮ ብዙዎችን እንዲታደግ ወደ አለምነው ለመድረስ የምናደርገውን ጉዞ ከጎናችን በመሆን ለምታሳዩን ፍቅር በቅድሚያ እያመሰገንን የዘውትር ዱአችሁ እና አብሮነታችሁ እንዳይለየን በድጋሚ እንጠይቃለን።
አሁንም ስራችን በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል....
@usmanoman ላይ ፃፉልኝ ለማንኛውም አገልግሎት እና ሀሳብ
✍️usman mus
from Usmanic islamic psychology
በብዛት እንዲለቀቅ የምትፈልጉት እና የወደዳችሁት የዚህ ቻናል ዝግጅት ምንድነው?
የሚፈውስ ዱአ
اللّهُمّ إني أسألك العفو والعافية في الدنيا والآخرة.
"አላህ ሆይ ይቅርታህን እና ደህንነትን/ጤናን በዚህ አለም እና በቀጣዩ አለም እጠይቃለሁ።"
ሼር የማድረግ ጥሪ/ቻሌንጅ
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አዲሱ የኢስላሚክ የስነልቦና አገልግሎት የሚሰጥ የቴሌግራም ቻናል ተከፈተ
- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች
- የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ።
- ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ።
ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ
ለወዳጅ ዘመድ ማጋራት አይርሱ
join ለማለት 👇👇
https://t.me/usmanic_psychology
መልስ ሁለት ክፍል 1
በአይን የሚገባው የዘመኑ አደገኛው እፅ (የፖርን ፊልም)
ማህበረሰቡ የማይነጋገርባቸው እና ማውራቱንም እንደ ነውር (taboo) አድርጎ ከሚቆጥራቸው
የህዝብ የቤተሰብ እና የመንፈሳዊነት መርዝ የሆነው እርቃን እና ወሲባዊ ትእይንቶችን የመመልከት ሱስ ከምን ጊዜውም በላይ በጣም እየተሰራጨ ነው።
ይህ 'ኢንዱስትሪ' ከ 10 ቢሊዮን ዶላር እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር በአመት የሚያንቀሳቅስ ሲሆን የተመልካቹ ቁጥርም በየጊዜው እየጨመረ እንደመጣ ጥናቶች ያሳያሉ።
በፊት በፊት ወንዶች ይህን ነገር በዋነኛነት እና በስፋት እንደሚያዩ ቢገመትም አሁን ግን የሴቶች ወደ እዚህ መረብ ተጠልፈው እንዲገቡ አዘጋጆቹ ስልታዊ እና ይዘታዊ ለውጦችን በማካሄድ የሴት ተጠቃሚዎችን ቁጥር መጨመር ችለዋል።
በአለም ላይ ከ 70 - 90% ወንዶች እና ከ 30-70% of ደግሞ ሴቶች ይህን አደገኛ ፊልም እንደሚያዩ አንዳንድ ጥናቶች ይጠቁማሉ።
ከእድሜ አንፃር ስናየው ሴቶች 60% እና ወንዶች ደግሞ 90% ተመልካቾች ከ 18 - 30 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው
'computer in human behavior' ጆርናል ይዞት በወጣው መረጃ መሠረት ለዚህ (porn) ወሲባዊ ፊልም አንድ ሰው የሚጋለጥበት አማካይ እድሜ በአለም አቀፍ ደረጃ 11 አመት ነዉ።
አሰቡት እንግዲህ ምን ያህል ለጋ አይምሮዎች ለዚህ መርዛማ ትእይንት ያለ እድሜያቸው እንደሚጋለጡ
አንድ መሰል ነገሮችን (የፖርን ፊልሞችን) ማሠራጫ ፕላትፎርም ብቻ ባወጣው መረጃ በ 2019 ብቻ እስከ 42 ቢሊዮን traffic/ እይታዎች ከተለያዩ የአለም ክፍሎች አግኝቷል።
ይህ ማለትም የአለምን ህዝብ ብዙ እጥፍ የሚበልጥ ቁጥር ሲሆን ምን ያህል ተመሳሳይ ሰዎች በተደጋጋሚ ይህን ነገረ የመመልከት ሱስ ውስጥ እንደወደቁ ያሳያል። ይህ የተመዘገበው ደግሞ በአንድ የማሳያ ቦታ ብቻ ነው።
መሰል የእርቃን ፊልሞችን የመመልከት ልማድ እና ሱስ ለአይምሮ ጤንነት መቃወስ ትልቅ አሉታዊ አስተዋጽኦ አለው ፣ ለተዛባ የወሲብ ህይወት ፣ ለወሲብ የሚሰጥ የተጋነነ ግምት ፣ ሴሰኝነት ፣ መደበኛ ያላሆነ የወሲብ ልማድ እና ኢ ተፈጥሯዊ የሆነ የግንኙነት ምኞት ወዘተ...ከሚያስከትላቸው ተፅእኖዎች በጥቂቱ ነው
ብር ያመጣ ነገር በሙሉ በሚሰራበት በዚህ የሞራል ሚዛን በተንሻፈፈበት ዘመን ሁሉም ነገር የሚሸጥ እቃ ሁሉም ሰውም ገቢ እስካመጣ ድረስ ስሜቱን ህሊናውን እና ማንነቱን ገብሮ ለገንዘብ አምላኪዎች በእጅ አዙር ተገዢ የሚሆንበት የስርአት አልበኛ መተራመሻ የሆነች አለም ላይ እየኖር ነው።
ራሳችንን ከነፍሲያ ጉትጎታ ከሰይጣን ሹክሹክታ እና በስጋዊ ፍላጎት እሳት ከመቃጠል በሶላት በትግስት እና ወደ አላህ በመቅረብ ውሀ በማብረድ የአይምሯችንን ደህንነት የሚሰልበውን ይህን አደገኛ ሱስ እንዋጋ።
(ይህ ስለ ነገሩ አሳሳቢነት ጥያቄውን እንደመነሻ በመጠቀም የቀረበ የክፍል 1 ማስታወሻ ሲሆን ለወንድማችን ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ በክፍል 2 ምላሽ ላይ ይሰጣል)
ኢንሻአላህ
✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ።
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።
የሚገራላችሁ ወይም ወይም መተግበር የሚቀላችሁ የኢባዳ/የአምልኮ ዘርፍ የቱ ነው?
እስካሁን በአስተያየት እና በምርጫ ለተሳተፋችሁ ሁላችሁም የላቀ ምስጋናዬን እየገለፅኩኝ ለእህታችን የህይወት ምርጫና እና ውሳኔ ላይ የሁላችሁም አስተያየት ትልቅ ግብአት ነው።
እናንተም መሰል የህይወት ውሳኔ ግርታ እና ግራ መጋባት ካጋጠማችሁ በውስጥ መስመር @usmanoman ላይ በፅፉልን የባለሙያዎችን ድጋፍ እና እንደ አስፈላጊነቱ ደግሞ ማንነታችሁ ሳይገለፅ ለህዝብ አስተያየት ክፍት እናደርገዋለን።
በአላህ ፍቃድ የተጀመሩት ኢስላማዊ የስነልቦና አገልግሎት እና ሌሎቹም ነገሮች እንዲቀጥሉ ከጎናችን ሁኑ።
እኔም በዚህ ታሪክ ላይ የማጠቃለያ መልስ እና ሌሎችንም ፅሁፎች እቀጥላለው ኢንሻአላህ!
አሰላሙአለይኩም ኢስላማዊ የስነልቦና ድጋፍ እና የምክክር አገልግሎት እንዲሁም ፅሁፎችን ለብዙዎች ተደራሸ የማድረግ ስራ ከጀመርን ከራረምን
የላወቁ እንዲያውቁ ወደ እዚህ ግሩፕ አድ በማድረግ ተጠቃሚዎችን ያብዙ። እናመሠግናለን
ወደ እዚህ ሊንክ በመግባት አድ ያድርጉ።
https://t.me/+XYW03GmihQM3Yzhk
+2
የእህታችን ልብ የሚነካ ታሪክ! እንደዚህ አጋርታናለች።ካነበባችሁ በኋላ ሃሳባችሁን ከታች የምናያይዘው poll/መምርጫው ላይ አስፍሩ።
