es
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Ir al canal en Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 294
Suscriptores
Sin datos24 horas
-137 días
-8030 días
Archivo de publicaciones
🇮🇷⚡️🇺🇸 ‘በኢራን ማንም ትራምፕን ለማስደሰት ብሎ ምላሽ አይቀርጽም። ትራምፕ የማይቀበለው ከሆነ፣ እንዲያውም በተፈጥሮው የተሻለ ነው። ትራምፕ እውነታን አይወድም፣ ለዛም ነው በኢራን እየተሸነ
🇮🇷⚡️🇺🇸 ‘በኢራን ማንም ትራምፕን ለማስደሰት ብሎ ምላሽ አይቀርጽም። ትራምፕ የማይቀበለው ከሆነ፣ እንዲያውም በተፈጥሮው የተሻለ ነው። ትራምፕ እውነታን አይወድም፣ ለዛም ነው በኢራን እየተሸነፈ ያለው — Tasnim

ትራምፕ፡ የኢራንን ምላሽ ምኑንም አልወደድኩትም። በጭራሽም አልቀበለውም!
ትራምፕ፡ የኢራንን ምላሽ ምኑንም አልወደድኩትም። በጭራሽም አልቀበለውም!

🇺🇸⚡️🇨🇺 ምልክቶች አሜሪካ በኩባ ላይ ዘመቻ ልትከፍት እንደሆ ያመለክታሉ​ ➡ በኩባ አቅራቢያ የሚገኙ የአሜሪካ የስለላ በረራዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል​ ➡ ከየካቲት 4 ጀምሮ የዩኤስ
🇺🇸⚡️🇨🇺 ምልክቶች አሜሪካ በኩባ ላይ ዘመቻ ልትከፍት እንደሆ ያመለክታሉ​ ➡ በኩባ አቅራቢያ የሚገኙ የአሜሪካ የስለላ በረራዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል​ ➡ ከየካቲት 4 ጀምሮ የዩኤስ የባሕር ኃይል እና አየር ሃይል በሀገሪቱ ትልልቅ ከተሞች አቅራቢያ ቢያንስ 25 አውሮፕላኖችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ያካተቱ በረራዎችን ማካሄዳቸው ተዘግቧል​ ➡ ቀደም ሲል አሜሪካ በቬንዙዌላ እና በኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከማድረጓ በፊት ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች በኩባ ዙሪያ እየተደረጉ ይታያሉ። ➡ ትራምፕ ዛሬ፣ ኩባ "ደስተኛ ትሆናለች" እና አሜሪካ በቅርቡ "እንደምታቋቁማት" በድጋሚ ተናግረዋል። ቬንዙዌላም እንዲሁ ነበረች፣ "ሁሉም ነገር ከመቀየሩ በፊት" "ደስተኛ አልነበረችም" ሲል አስታውሷል​ ➡ በኩባ ላይ ሊደረግ ለሚችለው ዘመቻ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን እየያዘ ያለ ይመስላል።

⚡️🇺🇸🇮🇱🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ለአሜሪካ ፕሮፖዛል የሰጠችውን ምላሽ ከተቀበለ በኋላ፣ መግለጫ አውጥቶአል። ኢራን ለ47 ዓመታት ጨዋታዎችን ተጫውታለች በማለት ከስሶ፣ የኦባማ አስተዳደ
⚡️🇺🇸🇮🇱🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ለአሜሪካ ፕሮፖዛል የሰጠችውን ምላሽ ከተቀበለ በኋላ፣ መግለጫ አውጥቶአል። ኢራን ለ47 ዓመታት ጨዋታዎችን ተጫውታለች በማለት ከስሶ፣ የኦባማ አስተዳደር ለቴህራን በመቶ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ሰጥቷታል ሲል ተችትዋል። ትራምፕ ኢራን ከእንግዲህ ወዲያ እንደማትስቅ ተናግሯል።

🇮🇷❌️🇺🇸 一 WSJ መረጃ የሰጡ ምንጮችን በመጥቀስ፡ ኢራን ለአሜሪካ ፕሮፖዛል ባለ ብዙ ገጽ ምላሽ እንደላከች ዘግቧል። የኢራን ምላሽ የኒውክሌር ፕሮግራሟን እና የበለፀገ ዩራኒየምን በተመለከተ የአሜሪካን ፍላጎት አያሟላም። ኢራን የበለፀገውን የዩራኒየም ክምችት በማሟሟት የተወሰነውን ከአሜሪካ ውጪ ወደ ሶስተኛ ሀገር ለማዛወር ሀሳብ አቅርባለች። ኢራን የዩራኒየም ማበልፀጊያዋንም ለማቆም ተስማምታለች፣ ነገር ግን ከ20 ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማድረግ ነው ያሰበችው። የኒውክሌር ተቋሞቿን በተመለከተ፣ ለሰላማዊ ጥቅም የሚውሉ ናቸው በማለት ለማፍረስ ፈቃደኛ አልሆነችም። ኢራን ድርድሩ ካልተሳካ ወይም ዩናይትድ ስቴትስ ከስምምነቱ ከወጣች የበለፀገውን ዩራኒየም ከሦስተኛው ሀገር እንዲመለስ ትጠይቃለች።

🇺🇸🇮🇷🇱🇧 - አል-ማያዲን እንደዘገበው በሊባኖስ ያለውን ጦርነት ማቆም ለኢራን ቀይ መስመር ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ እና ኢራን የአሜሪካን ማዕቀብ ለማንሳት እና የተያዙባትን ገንዘቦች ለማስመለስ እየፈለገች እንደሆነ ዘግቧል። የኢራን ምላሽ የኢራን የሆርሙዝ ባሕርን መቆጣጠርንም ያካትታል። አል-ማያዲን የአሜሪካ-ኢራን ድርድር በፓኪስታን ሽምግልና በጽሁፍ እንደሚቀጥል ዘግቧል።

🇺🇸🇮🇷 - አልጀዚራ እንደዘገበው ኢራን ለዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ጊዜ የሰላም ፕሮፖዛል ምላሽ ሰጥታለች። የኢራን ምላሽ የሚያተኩረው በመካከለኛው ምስራቅ፣ ሊባኖስን ጨምሮ፣ በመላው ቀጠና ያለውን ጦርነት በማቆም እና በኢራን ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ለማንሳት የሚያስችል ዘዴ በመፍጠር ላይ ነው።

🇮🇱🚫🇵🇸🇵🇸 የእስራኤል ቻናል 13 እንደዘገበው፣ ባለፈው ሳምንት ለእስራኤል የፖለቲካ አመራር የቀረበ ከፍተኛ ሚስጥራዊ ሰነድ ሃማስ በጋዛ ያለውን አቅም መልሶ እየገነባ መሆኑን ያስጠነቅቃል። ይህም በእስራኤል ጦር ላይ የስለላ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን በሻለቃ መመልመል እና በየወሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፈንጂዎችን፣ የሞርታር ዛጎሎችን እና ፀረ-ታንክ ሮኬቶችን ማምረትን ጨምሮ፣ ቡድኑ እያንሰራራ ነው። ሰነዱ በተጨማሪም ሃማስ የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቢኖርም ስልጠናውን እንደቀጠለ ገልጿል፣ የተኩስ አቁም ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ እስከ በመቶዎች የሚቆጠሩ የስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን በማካሄድ በአሁኑ ጊዜ አዳዲስ ዋሻዎችን ሳይቆፍር እንዳልቀረ እና ነባር መሠረተ ልማቶችን እያጠናከረ እንደሆነ ተገልጿል። በሪፖርቱ ውስጥ የተጠቀሱት የደህንነት ምንጮች እነዚህ እድገቶች የሃማስን የወደፊት የአሠራር አቅም በጊዜ ሂደት በእጅጉ ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ይገምግማሉ።

🇮🇱⚡️🇱🇧 ሂዝቦላህ ዛሬ የእስራኤልን IRON DOME በድሮን ሲመታ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል። ጥቃቶቹ በሁለት ድሮኖች የተፈፀሙ ናቸው። በአንደኛው፣ ድሮኑ በቀጥታ Iron Dome System ን ሲመታ ያሳያል። በሁለተኛው ድሮን፣ የተመታውን Iron Dome እየጫኑ የሚወስዱ ወታደሮችን ሲመታ ያሳያል። ጥቃቶቹ በሁለት ቀናት የሆኑ ናቸው።

- 🇮🇱 / 🇮🇷 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ - ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት አላበቃም ምክንያቱም አሁንም ከኢራን መወሰድ ያለበት የበለፀገ ዩራኒየም አለ። አሁንም መፍረስ ያለባቸው የማበልፀጊያ ቦታዎች አሉ። አሁንም ኢራን የምትደግፋቸው ፕሮክሲዎች እና ማምረት የሚፈልጓቸው ባለስቲክ ሚሳኤሎች አሉ። ብዙ አድቅቀናታል፣ ነገር ግን የቀረ የሚሠራ ሥራ አሁንም አለ።

🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ እሁድ ኢራንን በ AI troll ሲያደርግ አርፍዷል።
+2
🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ እሁድ ኢራንን በ AI troll ሲያደርግ አርፍዷል።

— 🇷🇺/🇺🇦 President Putin: የዩክሬን ጦርነት በቅርቡ ወደ መጠናቀቁ እየመጣ ይመስለኛል።

🇺🇸 Barak Ravid - ባራክ ራቪድ- የ AXIOS ሚዲያ መስራች፣ "ለሞሳድ ይሰራ ነበር" በሚል ለመጣበት ክሥ መልስ ሰጥቷል። "ይህ የኢራን ፕሮፓጋንዲስቶች ስሜን ለማጥፋት የሚያሰራጩት የሓሰት
🇺🇸 Barak Ravid - ባራክ ራቪድ- የ AXIOS ሚዲያ መስራች፣ "ለሞሳድ ይሰራ ነበር" በሚል ለመጣበት ክሥ መልስ ሰጥቷል። "ይህ የኢራን ፕሮፓጋንዲስቶች ስሜን ለማጥፋት የሚያሰራጩት የሓሰት ወሬ ነው፣ እኔ የሠራሁት ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ለ IDF ደህንነት ነው (ምድብ 8200)፣ በዛ ደግሞ እኮራለሁ" ብሏል። AXIOS ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ካለው "ያልተገባ" ቀረቤታ እና ጦርነቱን በመሞረድ ላይ ዋይት ሀውስን በመወከል እየተጫወተ ያለው ሚና፣ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ሲያስተቸው ቆይቷል። AXIOS በሚያቀርባቸው ሪፖርቶች ውስጠ-ወይራ በሆነ መልኩ ትራምፕ ለእስራኤል ኢንተረስት እንዲሰራ ሲያደርገውና ሲጠመዝዘው ቆይቷል፣ የሚልንም ትችት ሲያስተናግድ ሰንብቷል፣ መስራቹ ባራክ።

🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 ኢራን ለአሜሪካ ፕሮፖዛል በፖኪስታን በኩል መልስ መስጠቷ ታውቋል። ዝርዝሩ እስካሁን አልታወቀም— IRNA

🇮🇷 🇺🇸 ኢራን፣ የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት ልጅ በመውለዷ፣ 'እንኳን ደስ ያለሽ' ብላታለች። "አለቃሽ በሚናብ ትምህርት ቤት የገደላቸው 168 ልጆች... አንቺ ግድያውን ያጸደቅሽ
🇮🇷 🇺🇸 ኢራን፣ የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት ልጅ በመውለዷ፣ 'እንኳን ደስ ያለሽ' ብላታለች። "አለቃሽ በሚናብ ትምህርት ቤት የገደላቸው 168 ልጆች... አንቺ ግድያውን ያጸደቅሽባቸው፤ እነርሱም ሕፃናት ነበሩ" "ልጅሽን ስትስሚ፣ የእነዚያን ልጆች እናቶችን አስቢ።"

🇮🇱 🇮🇶 እስራኤል በኢራቅ ውስጥ፣ የኢራቅ መንግሥት የማያውቀው ሚስጥራዊ የጦር ሰፈር አላት። ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል በሜይ 9፣ 2026 እስራኤል ከእስራኤል-ኢራን ጦርነት በፊት በኢራቅ ምዕራባ
🇮🇱 🇮🇶 እስራኤል በኢራቅ ውስጥ፣ የኢራቅ መንግሥት የማያውቀው ሚስጥራዊ የጦር ሰፈር አላት። ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል በሜይ 9፣ 2026 እስራኤል ከእስራኤል-ኢራን ጦርነት በፊት በኢራቅ ምዕራባዊ በረሃ በድብቅ ወታደራዊ ጦር እንዳቋቋመች በመግለጽ ዘገባ አሳትሟል። በሪፖርቱ መሰረት፣ ይህ ጦር ሰፈር በኢራን ላይ የእስራኤል የአየር እንቅስቃሴን ደግፏል። - ልዩ ሃይሎች እና የፍለጋ እና የማዳን ቡድኖችን የተካተቱበት ጦር ሰፈር ነው። - ለአሜሪካ ባለስልጣናት ይታወቅ ነበር። - አንድ እረኛ አጠራጣሪ የሄሊኮፕተር እንቅስቃሴን ከዘገበ በኋላ ሊጋለጥ ተቃርቦ እንደነበር፣ የኢራቅ ወታደሮች ወደ አካባቢው ሲቃረቡ በእስራኤል የአየር ድብደባ ተደርጎባቸው እንደነበር ያትታል። - በክስተቱ አንድ የኢራቅ ወታደር መገደሉን እና ሁለት መቁሰላቸውን ፅፏል። - እስራኤል በይፋ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነችም።

🇮🇷🤝🇷🇺 ሩሲያ እና ኢራን በካስፒያን ባሕር በኩል የንግድ ልውውጥን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል። በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የመርከብ ገደቦች
🇮🇷🤝🇷🇺 ሩሲያ እና ኢራን በካስፒያን ባሕር በኩል የንግድ ልውውጥን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል። በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የመርከብ ገደቦች ከተደረጉ በኋላ መንገዱ ከሆርሙዝ ባሕር፣ ሌላ አማራጭ ሆኗል። ስንዴ፣ በቆሎ፣ የእንስሳት መኖ፣ የሱፍ አበባ ዘይት እና ሌሎች እቃዎች አሁን በካስፒያን በኩል ወደ ኢራን ይላካሉ። አራት የኢራን ወደቦች በካስፒያን 24/7 ይሰራሉ፣ እና በሩሲያ እና በኢራን መካከል ያሉ መርከቦች እንቅስቃሴያቸውን ለመደበቅ በመደበኛነት ትራንስፖንደርዎቻቸውን ያጠፋሉ፣ ብሏል ጋዜጣው።

🇮🇷🚫🇺🇸 የኢራን የባሕር ኃይል ጦር አባል በቪዲዮው ላይ ለሚከተላቸው እና በፍጥነት ከቦታው እየሄዱ ለሚታዩት ለአሜሪካ ደምሳሽ መርከቦች እንዲህ እያለ ሲናገር ይሰማል፡ "
አዎ ቀጥሉ! ሽሹ! መሸሽ ልምዳችሁ ነው። ይሄ የምድር መገኛ ነው፣ የኢራናውያን ምድር ይኸውና፣ የእስልምና ቁራጭ ክፍል ይኸውና!" 

🇪🇹 የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ አክሱምን "ቅድስት ከተማ" ብሎ መሰየሙን እና ይህንኑ የሚያሳዩ "ሕጎችን እያወጣ" መሆኑን አስታወቀ I የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ ባደረገው ጉባኤ፤ የጥንታዊቷ አክሱም መጠሪያ "ቅድስት አክሱም ጽዮን ከተማ" እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ። ቤተ ክርስቲያኗ፤ ይህንን ውሳኔ ተከትሎ በከተማዋ እንደ "መጠጥ እና ጫት" ሽያጭ ያሉ ተግባራት ላይ ክልከላ እንዲጣል እንደምትፈልግ እንዲሁም "የቅድስና ምልክት እንድታሳይ የሚያደርጉ ሕጎችን" እያወጣች መሆኑን ገልጻለች። ውሳኔው ይፋ ከተደረገበት ሚያዝያ 28/2018 ዓ. ም. አንስቶ ከተማዋ በአጠቃላይ ቅድስት ተብላ እንደምትጠራ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አክሱም ከዚህ ቀደም ያላት ክብር እንዳለ ሆኖ በጠቅላላው ቅድስት ከተማ እንድትባል የሚያስችል ጥናት ቀርቦ ውሳኔው እንደተላለፈ ገልጸዋል። አክሱም ከተማ "ቅድስት ከተማ" በሚል በተለምዶ ትጠራ እንደነበር ጠቅሰው የአሁኑ ውሳኔ መጠሪያውን "ሕጋዊ" እንደሚያደርገው አስረድተዋል። አክሱም "ሕገ ልቦና፣ ሕገ ኦሪት፣ ሕገ ወንጌል ጠብቃ የኖረች የረዥም ዓመት የክርስትና ደሴት" ስለሆነች "ቅድስት" መሆኗን ብፁዕ አቡነ አረጋዊ አስረድተዋል። "ብዙ መንበረ ታቦተ ጽዮናት፣ መንበረ ጽላት፣ መንበረ ሳምራ፣ መንበረ ብዙ ቅዱሳን ስለሆነች ያላት ክብር እንዳለ ሆኖ ከአሁን በኋላ ደግሞ ከተማዋን ጠቅላላ ቅድስት የሚያስብላት ተጠንቶ ያለው ግብዓት ቀርቧል" በማለትም አብራርተዋል። "ከተማዋ በዚህ ዘመን ያላትን ቅድስና ቀጣዩ ትውልድ ይዞ እንዲሄድ" በሚል አጠቃላይ ከተማዋ ቅድስት ተብላ እንድትጠራ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን አክለዋል። የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በተለዩት አባቶች የተመሠረተው የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እንደተናገሩት፤ አክሱም በአጠቃላይ ቅድስት ከተማ እንድትባል በመወሰኑ ምክንያት መጠጥ እና ጫትን የመሳሰሉት ላይ ሙሉ በሙሉ ክልከላ ለመጣል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እያደረጉ ነው። "ለሆቴሎችም ሥርዓት የሚወጣበት ሕግ እያወጣን ነው. . . ከተማይቷ ቅድስት ከተባለች የቅድስና ሥራ ሊሠራ ይገባል። ጠቅላላ ከተማዋ የቅድስና ምልክት እንድታሳይ የሚያደርጉ ሕጎች እያወጣን ነው" ብለዋል። የከተማዋን "ጥንታዊ ታሪክ፣ ማንነቷን፣ ክብሯን ዓለም እንዲያውቀው" ማድረግም ዓላማቸው መሆኑን አክለዋል። አሁን ላይ ከተማዋ "ለቅድስና የሚበቁ ነገሮች ማድረግ ስላለባት" ቤተ ክርስቲያኒቷን፣ ሕዝቧን እና ምዕመኗንም "በደንብ እንደሚያስተምሩ" ተናግረዋል። ዘገባው የቢቢሰሲ አማርኛ ነው።

🇧🇭 በባህሬን የሺዓ እምነት አባቶች እስራት በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቷል -- የባህሬን ሰብዓዊ መብት የባህሬን ሕዝብ በአብዛኛው ሺዓ እምነት ተከታይ ሲሆን፣ መሪዎቹ አናሳ ቁጥር ካለው የሱኒ
🇧🇭 በባህሬን የሺዓ እምነት አባቶች እስራት በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ መጥቷል -- የባህሬን ሰብዓዊ መብት የባህሬን ሕዝብ በአብዛኛው ሺዓ እምነት ተከታይ ሲሆን፣ መሪዎቹ አናሳ ቁጥር ካለው የሱኒ ማህበረሰብ የወጡ ናቸው። በሳዑዲ መንግሥት ይደገፋሉ፣ ብዙ ተንታኞችም የድጋፉን ጥልቀት ተንተርሰው ባህሬን የሳዑዲ "ሳተላይት ሀገር" እንደሆነች ይናገራሉ። ይሄ አወቃቀር ነው በመሬት ያለመረጋጋት ምክኒያት ሆኖ የቆየው። ሕዝቡ አብዛኛው ሺዓ እንደመሆኑ፣ አቋሙ ወደ ኢራን ያንጋለለ ነው።