es
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Ir al canal en Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 294
Suscriptores
Sin datos24 horas
-137 días
-8030 días
Archivo de publicaciones
🇬🇧⚡️ - የብሪታንያ ሕብረተሰብ አስገራሚ ወቅታዊ ውቅር
🇬🇧⚡️ - የብሪታንያ ሕብረተሰብ አስገራሚ ወቅታዊ ውቅር

🇺🇸🚫🇮🇷 የአሜሪካ የስለላ ድርጅት የኢራን ጠቅላይ መሪ ሙጅተባ ካሚኔይ፣ ከሕዝብ እይታ ውጪ ቢሆኑም ከኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን የጦርነት ስትራቴጂን በመቅረጽ ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን ገምግሟል።

🇮🇷 🇧🇭 እንደ ባህሬን ያሉ አናሳ ግዛቶችን ጨምሮ፣ መንግስታት፣ በአሜሪካ ከሚደገፈውን የውሳኔ ሓሳብ ጎን መቆም ከባድ መዘዝ እንደሚያስከትልባቸው እናስጠነቅቃለን። የሆርሙዝ ወሽመጥ ወሳኝ የሕይ
🇮🇷 🇧🇭 እንደ ባህሬን ያሉ አናሳ ግዛቶችን ጨምሮ፣ መንግስታት፣ በአሜሪካ ከሚደገፈውን የውሳኔ ሓሳብ ጎን መቆም ከባድ መዘዝ እንደሚያስከትልባቸው እናስጠነቅቃለን። የሆርሙዝ ወሽመጥ ወሳኝ የሕይወት መስመር ነው፣ በራሳችሁ ላይ ለዘላለሙ እንዲዘጋባችሁ ራሳችሁን አደጋ ላይ አትጣሉ። - ኢብራሂም አዚዚ፣ የኢራን ፓርላማ የብሔራዊ ደህንነት ኮሚሽን ኃላፊ

🇮🇷 🇱🇧 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ፡ "ጦርነቱ ይቁም" ብለን ስንል፣ በሁሉም ግንባሮች ማለታችን ነው፣ በተለይ በሊባኖስ።

+1
.— 🇮🇱 /🇱🇧/ 🇮🇷 IDF በሊባኖስ ውስጥ የFPV ድሮኖችን ስጋት ለመቋቋም፣ ለጠመንጃዎች 'SMASH' የተባሉ አባሪዎችን በጅምላ መግጠም ጀምሯል። 'SMASH Handheld' ወይም በዕብራይስጠኛ  'Pigyon' ኢላማዎችን የሚከታተል እና የተሳካ ስኬት ለማግኘት ምላጩ መቼ መሳብ እንዳለበት በትክክል የሚያሰላ የጠመንጃ አባሪ ነው። ቀደም ሲል በጋዛ ውስጥ በIDF በተወሰነ መጠን ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ እዚያም የመምታት መጠንን በ 4x ሲጨምር ታይቷል። ነገር ግን በ FPV ድሮኖች ላይ የበለጠ ውጤታማ ነው ተብሏል።

+1
🇱🇧🇱🇧❌🇮🇱 - ሂዝቦላህ፣ የእስራኤል ወታደር ትናንት በደቡባዊ ሊባኖስ አልማል ሽ-ሻዓብ ከደረሰው ጥቃት ለማምለጥ ሲሞክር እና ድሮኑ የIDF ን መርካቫ ታንክ ሲመታ የሚያሳይ ምስል አውጥቷል። እነዚህ የ$100 ዶላር FPV ድሮን፣ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በመሬት ጨዋታውን እየቀየሩት ነው። ሂዝቦላ FBV ድሮንን መጠቀም የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም፣ በእነዚህ ምክኒያት በእስራኤል ጦር ላይ ለማመን የሚከብድ ጫና ፈጥሯል።

🇨🇳🤝🇮🇷 - አሜሪካ ሦስት የቻይና የግል ኩባንያዎችን ለ IRGC የሳተላይት ምስል አገልግሎት ሰጥተዋል በሚል ማዕቀብ አድርጋባቸዋለች። ከእነዚህ መካከል The Earth Eye እና MizarVision ድርጅቶች ይገኙበታል። ይህ የተገለፀው፣ ትራምፕ ወደ ቤጂንግ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሚያደርጉት ጉዞ ቀደም ብሎ ነው። The Wall Street Journal

የዩክሬን ጦር ኃይሎች በሴንት ፒተርስበርግ በሚገኙ ሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መሞከራቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ ​ዛሬ ጠዋት የሩሲያ ወታደሮች በላቲቪያ የአየር ክልል ውስጥ ስድስት ድሮኖችን የተመለከቱ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ አምስቱ በሬዜክኔ ከተማ አቅራቢያ መሰወራቸውን ገልጸዋል። ​ከእነዚህ ድሮኖች መካከል አንዱ ወደ ሩሲያ የአየር ክልል የገባ ሲሆን ወዲያውኑ ተመትቶ ወድቋል። የወደቀው ፍርስራሽ ላይ በተደረገ ምርመራ አውሮፕላኑ በዩክሬን የተመረተ "ሊዩቲ"  የተሰኘ ድሮን መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ​ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ምስል በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

🇺🇸🇨🇴 ዩናይትድ ስቴትስ የቀረውን የበለፀገ ዩራኒየም ከቬንዙዌላ አስወግዳለች። የዩናይትድ ስቴትስ የኢነርጂ ዲፓርትመንት ብሔራዊ የኑክሌር ደህንነት አስተዳደር፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ በ
🇺🇸🇨🇴 ዩናይትድ ስቴትስ የቀረውን የበለፀገ ዩራኒየም ከቬንዙዌላ አስወግዳለች። የዩናይትድ ስቴትስ የኢነርጂ ዲፓርትመንት ብሔራዊ የኑክሌር ደህንነት አስተዳደር፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ በቬንዙዌላ ከሚገኘው አሮጌ የምርምር ሬአክተር የቀረውን የበለፀገ ዩራኒየም ማስወገድ ሥራ ማጠናቀቃቸውን አስታውቋል።

⚡️🇮🇷🇺🇸 WSJ፡ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት የባሕር ትራፊክን እያስተጓጎለ በመምጣቱ፣ ከ20,000 በላይ መርከበኞች እና 800 መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ መፈናፈኛ አጥተው ለወራቶች ቆመዋል። ሰራተኞቹ የምግብ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦት እጥረት እያጋጠማቸው ሲሆን በባህር ዳርቻው በኩል የሚደረገው የንግድ ጭነት፣ በሚሳኤል ጥቃት፣ በባሕር ኃይል ግጭቶች እና በቀውሶች መባባስ ፍራቻ፣ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። መርከበኞች ከእገዳው ለማምለጥ በሞከሩ መርከቦች ላይ በተቃጣ የኢራን ጥቃት የተበላ ቆዳቸውን እና የተከፈቱ ቁስሎችን ለሪፖርተራችን አጋርተዋል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 abc NEWS: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ Marco Rubio: ከኢራን ለስምምነቱ መልስ ዓርብ እንጠብቃለን፣ ብሏል። አያይዞም፣ "ደደብ ሀገሮች ብቻ ናቸው እሳትን በእሳት የማ
+1
🇮🇷⚡️🇺🇸 abc NEWS: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ Marco Rubio: ከኢራን ለስምምነቱ መልስ ዓርብ እንጠብቃለን፣ ብሏል። አያይዞም፣ "ደደብ ሀገሮች ብቻ ናቸው እሳትን በእሳት የማይመልሱት። እኛ ያደረግነው ያንን ነው" ሲልም ተናግሯል፣ በሆርሙዝ ከኢራን ጋር የነበረውን የትናንቱን ግጭት በተመለከተ። "ቀይ መስመሩ ግልፅ ነው" ያለው Rubio, "አሜሪካን የተተናኮሉ ይቀምሳሉ!"፣ ብሏል።

🇺🇸🇮🇱🇮🇷 - አንድ እስራኤላዊ ባለስልጣን ለቻናል 12 እንዲህ ብሏል -
"እስራኤል ለዋሽንግተን 'ኢራን አሁን ባለችበት ምስል መቀጠል አትችልም፣ ልትጠፋ ይገባል' የሚል መልእክት ልካለች። ማንኛውም ጦርነት እንደገና ከተጀመረ፣ የኢራንን የኢነርጂ መሠረተ ልማት ማጥፋትን ማካተት አለበት። የኢራን የኢነርጂ መሠረተ ልማት በ24 ሰዓታት ውስጥ ሊወድም የሚችል ሲሆን፣ ማጥፋቱ ቴህራን ወደ ድርድር እንድትገባ ያስገድዳታል። እስራኤል፣ የኢራን የኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ ማነጣጠር በድርድር ለውጥ ለማየት ብቸኛው መንገድ መሆኑን ለዋሽንግተን ለማስተላለፍ እየሞከረች ነው።

🇺🇸 በአሜሪካ ጦር የተወሰደው አንድ በጣም እንግዳ ቪዲዮ የኮከብ ቅርጽ ያለው ነገር በፍጥነት በሰማይ ላይ ሲንቀሳቀስ ያሳያል።

🇺🇸 ትኩስ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ፔንታጎን በጣም ጥብቅ የዩፎ ሰነዶችን አውጥቷል። አንዳንድ ምስሎች ምንነታቸው ያልታወቁ የኮከብ ቅርጽ ያላቸው ሥሪቶችን ያሳያሉ። ሌሎች ደግሞ በአፖሎ 11 ጨረቃ ማረፊያ
+3
🇺🇸 ትኩስ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ፔንታጎን በጣም ጥብቅ የዩፎ ሰነዶችን አውጥቷል። አንዳንድ ምስሎች ምንነታቸው ያልታወቁ የኮከብ ቅርጽ ያላቸው ሥሪቶችን ያሳያሉ። ሌሎች ደግሞ በአፖሎ 11 ጨረቃ ማረፊያ ወቅት በሰማይ ላይ እንግዳ የሆኑ መብራቶችን እና ቅርጾችን ያሳያሉ። የተለቀቁት ቪዲዮዎች ምንም አይነት የሚታወቅ የማስፈንጠሪያም ሆነ የሞተር ስርዓቶች ሳይኖራቸው በሰማይ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሉሎችን ያሳያሉ። 

🇮🇱🇱🇧 ዛሬም በተመሳሳይ አስነዋሪ ተግባር፣ የእስራኤል ወታደር በድንግል ማርያም ሐውልት ላይ ሲጋራ በመሰካት እያስጨሰ ሲያላግጥ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል። ከጥቂት ቀናት በፊት በዚሁ በደቡብ ሊባኖስ ቀጠና አንድ ፎቶግራፍ አንድ IDF አባል በተመሳሳይ መልኩ የክርስቶስን እናት ሐውልት ሲያራክስ ታይቶ ነበር። ከጥቂት ሳምንታት በፊትም የተሰቀለ የክርስቶስ ሐውልትን በመዶሻ ሲያፈርስ የሚያሳይ ምስል እንዲሁ መለቀቁ የሚታወስ ነው። ክስተቶቹ፣ የእስራኤል ጦር በክርስቲያን ምልክቶች እና ማህበረሰቦች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን እየፈፀሙ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

⚡️🇮🇷🇺🇸 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ ትናንት ማታ የአሜሪካ እርምጃ የዓለም አቀፍ ሕግን እና የተኩስ አቁም ስምምነትን በግልፅ የጣሰ ነው ብለዋል። "የጠላት ጦር በከባድ ተመትቷል እና ሙሉ ኃይላቸውን ወደ ኋላ እንዲመልሱ ተገሀዋል" ብለዋል። ባጋይ አክለውም፣ የኢራን ጦር ኃይሎች ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተው ሁኔታውን በትክክል እየተከታተሉ መሆናቸውን እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሙሉ ኃይላቸው ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። ስለ ድርድሩ ሲጠየቁ ባጋይ፣ ጉዳዩ አሁንም በግምገማ ላይ መሆኑን እና የመጨረሻ ውጤት ከደረሰ በኋላ ይፋ እንደሚሆን ተናግሯል።

🇮🇷⚡️🇮🇱🇺🇸 2 የUS የጦር መርከቦች፣ 'አስጨናቂ የኢራን ጥቃት ውስጥ' ነበሩ። — CBS NEWS. USS Truxtun እና USS Mason መርከቦች በፈጣን የኢራን አጥቂ ጀልባዎች፣ በድሮ
🇮🇷⚡️🇮🇱🇺🇸 2 የUS የጦር መርከቦች፣ 'አስጨናቂ የኢራን ጥቃት ውስጥ' ነበሩ። — CBS NEWS. USS Truxtun እና USS Mason መርከቦች በፈጣን የኢራን አጥቂ ጀልባዎች፣ በድሮኖች እና በሚሳኤሎች 'ተውጠው' ነበር።

—❗️🇺🇸/🇮🇷 U.S. ማዕከላዊ ኮማንድ: "መርከቦቻችን በተፈቀዱ የዓለም አቀፍ መስመሮች፣ በወሽመጡ፣ ለማለፍ ሲሞክሩ፣ ባላሰቡበት በኢራን ተኩስ ተከፍቶባቸዋል … በድሮን፣ በሚሳዬል፣ እና በፈጣ
—❗️🇺🇸/🇮🇷 U.S. ማዕከላዊ ኮማንድ: "መርከቦቻችን በተፈቀዱ የዓለም አቀፍ መስመሮች፣ በወሽመጡ፣ ለማለፍ ሲሞክሩ፣ ባላሰቡበት በኢራን ተኩስ ተከፍቶባቸዋል … በድሮን፣ በሚሳዬል፣ እና በፈጣን ጀልባዎች የተከፈተውን ጥቃት፣ ጦር ሠራዊታችን እንደ አመጣጡ በተገቢው መንገድ መልሷል …… በምላሹ፣ ጥቃቶቹ ተነስተውበታል ተብለው የታሰቡ ሥፍራዎችን፣ ጦራችን ደብድቧል …… "

🇺🇸🇮🇷🇮🇱⚡️ - በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ባለው የሁኔታዎች መባባስ ምክንያት፣ ሁሉም የእስራኤል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መደበኛ ስርጭቶቻቸውን ለ"የአደጋ ጊዜ" ስርጭት አቋርጠዋል። የእስራኤል Home Front Command ሁሉም ነዋሪዎች በመጠለያ አቅራቢያ እንዲቆዩ አሳስቧል።

🇺🇸 🇮🇷❗️ሰበር- ኢራን: ዋሽንግተን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች።