የቀጠናው ተመልካች
الذهاب إلى القناة على Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 303
المشتركون
+824 ساعات
-47 أيام
-7130 أيام
أرشيف المشاركات
4 303
🇮🇱🇮🇶🇮🇷 - የኢራቅ ጦር ኃይሎች- "ኃይሎቻችን በመጋቢት ወር በካርባላ በረሃ ውስጥ በአውሮፕላኖች ከሚደገፉ ማንነታቸው ያልታወቁ እና ያልተፈቀዱ ክፍሎች ጋር ተጋጭተዋል።
በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ግዛት ላይ ያልተፈቀዱ ሃይሎች ወይም ጦር ሰፈሮች አለመኖራቸውን እናረጋግጣለን።
4 303
🇱🇻 በላቲቪያ ፖሊሶች አንዲትን ሴት 'የቦርሳሽ ቀለም ውቅር የሩሲያን ባንዲራ ያሳያል' በሚል አቁመው ሲጠይቋት በተንቀሳቃሽ ምስሉ ይታያል፣ ምንም እንኳ የቦርሳው ቀለም የ Tommy Hilfiger ብራንድ ቀለም ቢሆንም።
በላትቪያ፣ እንደ ዩክሬን ሁሉ፣ የሩሲያን ባንዲራ በምንም ሁኔታ መያዝ አይቻልም። በልብስ፣ በጥልፍ፣ በዕቃ … ቀለሙን ማሳየት በገንዘብ ያስቀጣል። ላትቪያ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ላይ አይደለችም፣ ግን ባንዲራውን በምንም ሁኔታ ማሳየት ወንጀል ነው።
ባለፈው ዓመት በላትቪያ በነበረ የEuro Basktball ግጥሚያ፣ ፖሊስ ተመልካቾች ይዘውት የነበረን የሰርቢያ ባንዲራ፣ ቀለሙ ከሩሲያ ጋር ስለሚመሳሰል ብቻ መቀማታቸው ይታወሳል።
ነገሩ፣ የባለፉትን የኢትዮጵያ ባንዲራ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ይዞ መገኘትን ይመስላል።
Total Paranoia!
4 303
⚡️🇮🇷🇺🇸 የኢራን ፓርላማ አፈጉባኤ የኢራን ጦር ኃይሎች ለማንኛውም ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ የተሳሳቱ ስልቶች እና ውሳኔዎች ሁል ጊዜ ወደ ተሳሳተ ውጤት እንደሚመያሩ እና "መላው ዓለም ይህንን ተረድቷል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
አክለውም፣ "ለሁሉም አማራጮች ተዘጋጅተናል፣ እናስደነግጣቸዋለን" ብለዋል።
4 303
- 🇺🇸 /🇮🇱/ 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድርድሩ መደናቀፉን ተከትሎ፣ በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደገና ለመጀመር እያሰበ ሲሆን፣ ዛሬ ከጄኔራሎቹ ጋር ይገናኛል።
የሚቀርቡት አማራጮች በሆርሙዝ ወሽመጥ መርከቦችን አጅቦ የመሄዱን 'ፕሮጀክት ነፃነት' እንደገና ማስጀመርን ያካትታል ተብሏል።
ሌላው አማራጭ፣ በኢራን ውስጥ እስካሁን ያልተመታ 25% ተለይተው የሚታወቁ ኢላማዎች ላይ ጥቃቱን እንደገና ማስጀመር ነው።
በተጨማሪም፣ እስራኤል የኢራንን የበለፀገ ዩራኒየም በልዩ ኦፕራሽን ከኢራን ማውጣቱን በተመለከተ ትራምፕ እንዲፈቅድ ጫና እያደረገች ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንቱ ኦፕሬሽኑ ሊያስከትል በሚችለው ከፍተኛ አደጋ ምክንያት እያመነታ ይገኛል።
4 303
- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ 'የኢራን መሪዎች ክብር የጎደላቸው ሰዎች ናቸው። ለማዘጋጀት 10 ደቂቃ ሊወስድ የሚገባውን የወረቀት ምላሻቸውን፣ 4 ቀን ፈጅቶባቸው ነው የላኩት። በዚያ ላይ ቆሻሻ ነበር።'
4 303
- 🇺🇸 / 🇮🇷 ኢራን ኳታርን፣ ባህሬንን፣ ኩዌትን ሳዑዲ አረቢያን አጠቃች - በሁሉም ቦታ ጥቃት ሰንዝረዋል።
ማንም ሰው እነዚህን ሀገሮች ያጠቋቸዋል ብሎ አልጠበቀም፣ ያንን ማድረግ አልነበረባቸውም። ነገር ግን አደረጉት፣ ሚሳዬሎቻቸውን አባከኑ። ብክነት ነበር። እነዚያን ሁሉ ሚሳኤሎችና ማስወንጨፊያዎቻቸውን በሚያማምሩ ፔትሪዮት ሚሳዬሎቻችን አንኮታኮትንባቸው።
4 303
⚡️🇱🇧 የደቡብ ሊባኖሷ ቢንት ጅቤይል ከተማ ሙሉ በሙሉ በIDF ቁጥጥር ሥር ወድቃለች። ከተማዋ በሙሉ አሁን 'ባዶ' ተብሎ ተቆጥሯል፣ ከህንጻዋ ወይም ከሲቪሎች ምንም የቀረ ነገር የለም።
በከተማው ወሰን ውስጥ ያለው የትጥቅ ተቃውሞ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ተብሎ ይታሰባል፣ ከሰሜናዊ አቅጣጫ ከሂዝቦላህ ወደ IDF ከሚደረጉ ጥቃቶች በስተቀር።
4 303
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የአሜሪካ አየር ሐይል F- 35A Lightning II Stealth ጀት ዛሬ፣ በዚህች ሰዓት፣ በሆርሙዝ ባሕር አቅራቢያ በኦማን ባሕረ ሰላጤ ላይ የአደጋ ጊዜ ኮድ እያጮኸ እንደነበር፣ ከዚያም በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የአየር ክልል ላይ መጥፋቱ ታውቋል።
አውሮፕላኑ (13-5067 የተመዘገበ) ከኦማን ባሕረ ሰላጤ ከተሻገረ በኋላ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላይ ሲበር የዓለም አቀፍ የአደጋ ጊዜ ጭንቀት ምልክትን አስተላልፏል። ከዚያም የጀት ትራንስፖንደሩ ጠፍቷል።
የኢራን የመንግስት ሚዲያዎች F-35 በኢራን ጦር ተመቷል ይላሉ። ይህ፣ በተናጥል አልተረጋገጠም። አሜሪካ እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠችም።
4 303
🇮🇷⚡️🇺🇸 ‘በኢራን ማንም ትራምፕን ለማስደሰት ብሎ ምላሽ አይቀርጽም።
ትራምፕ የማይቀበለው ከሆነ፣ እንዲያውም በተፈጥሮው የተሻለ ነው።
ትራምፕ እውነታን አይወድም፣ ለዛም ነው በኢራን እየተሸነፈ ያለው — Tasnim
4 303
🇺🇸⚡️🇨🇺 ምልክቶች አሜሪካ በኩባ ላይ ዘመቻ ልትከፍት እንደሆ ያመለክታሉ
➡ በኩባ አቅራቢያ የሚገኙ የአሜሪካ የስለላ በረራዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል
➡ ከየካቲት 4 ጀምሮ የዩኤስ የባሕር ኃይል እና አየር ሃይል በሀገሪቱ ትልልቅ ከተሞች አቅራቢያ ቢያንስ 25 አውሮፕላኖችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ያካተቱ በረራዎችን ማካሄዳቸው ተዘግቧል
➡ ቀደም ሲል አሜሪካ በቬንዙዌላ እና በኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከማድረጓ በፊት ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች በኩባ ዙሪያ እየተደረጉ ይታያሉ።
➡ ትራምፕ ዛሬ፣ ኩባ "ደስተኛ ትሆናለች" እና አሜሪካ በቅርቡ "እንደምታቋቁማት" በድጋሚ ተናግረዋል። ቬንዙዌላም እንዲሁ ነበረች፣ "ሁሉም ነገር ከመቀየሩ በፊት" "ደስተኛ አልነበረችም" ሲል አስታውሷል
➡ በኩባ ላይ ሊደረግ ለሚችለው ዘመቻ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን እየያዘ ያለ ይመስላል።
4 303
⚡️🇺🇸🇮🇱🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ለአሜሪካ ፕሮፖዛል የሰጠችውን ምላሽ ከተቀበለ በኋላ፣ መግለጫ አውጥቶአል። ኢራን ለ47 ዓመታት ጨዋታዎችን ተጫውታለች በማለት ከስሶ፣ የኦባማ አስተዳደር ለቴህራን በመቶ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ሰጥቷታል ሲል ተችትዋል።
ትራምፕ ኢራን ከእንግዲህ ወዲያ እንደማትስቅ ተናግሯል።
4 303
🇮🇷❌️🇺🇸 一 WSJ መረጃ የሰጡ ምንጮችን በመጥቀስ፡ ኢራን ለአሜሪካ ፕሮፖዛል ባለ ብዙ ገጽ ምላሽ እንደላከች ዘግቧል።
የኢራን ምላሽ የኒውክሌር ፕሮግራሟን እና የበለፀገ ዩራኒየምን በተመለከተ የአሜሪካን ፍላጎት አያሟላም። ኢራን የበለፀገውን የዩራኒየም ክምችት በማሟሟት የተወሰነውን ከአሜሪካ ውጪ ወደ ሶስተኛ ሀገር ለማዛወር ሀሳብ አቅርባለች።
ኢራን የዩራኒየም ማበልፀጊያዋንም ለማቆም ተስማምታለች፣ ነገር ግን ከ20 ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማድረግ ነው ያሰበችው።
የኒውክሌር ተቋሞቿን በተመለከተ፣ ለሰላማዊ ጥቅም የሚውሉ ናቸው በማለት ለማፍረስ ፈቃደኛ አልሆነችም።
ኢራን ድርድሩ ካልተሳካ ወይም ዩናይትድ ስቴትስ ከስምምነቱ ከወጣች የበለፀገውን ዩራኒየም ከሦስተኛው ሀገር እንዲመለስ ትጠይቃለች።
4 303
🇺🇸🇮🇷🇱🇧 - አል-ማያዲን እንደዘገበው በሊባኖስ ያለውን ጦርነት ማቆም ለኢራን ቀይ መስመር ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ እና ኢራን የአሜሪካን ማዕቀብ ለማንሳት እና የተያዙባትን ገንዘቦች ለማስመለስ እየፈለገች እንደሆነ ዘግቧል።
የኢራን ምላሽ የኢራን የሆርሙዝ ባሕርን መቆጣጠርንም ያካትታል። አል-ማያዲን የአሜሪካ-ኢራን ድርድር በፓኪስታን ሽምግልና በጽሁፍ እንደሚቀጥል ዘግቧል።
4 303
🇺🇸🇮🇷 - አልጀዚራ እንደዘገበው ኢራን ለዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ጊዜ የሰላም ፕሮፖዛል ምላሽ ሰጥታለች። የኢራን ምላሽ የሚያተኩረው በመካከለኛው ምስራቅ፣ ሊባኖስን ጨምሮ፣ በመላው ቀጠና ያለውን ጦርነት በማቆም እና በኢራን ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ለማንሳት የሚያስችል ዘዴ በመፍጠር ላይ ነው።
4 303
🇮🇱🚫🇵🇸🇵🇸 የእስራኤል ቻናል 13 እንደዘገበው፣ ባለፈው ሳምንት ለእስራኤል የፖለቲካ አመራር የቀረበ ከፍተኛ ሚስጥራዊ ሰነድ ሃማስ በጋዛ ያለውን አቅም መልሶ እየገነባ መሆኑን ያስጠነቅቃል። ይህም በእስራኤል ጦር ላይ የስለላ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን በሻለቃ መመልመል እና በየወሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፈንጂዎችን፣ የሞርታር ዛጎሎችን እና ፀረ-ታንክ ሮኬቶችን ማምረትን ጨምሮ፣ ቡድኑ እያንሰራራ ነው።
ሰነዱ በተጨማሪም ሃማስ የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቢኖርም ስልጠናውን እንደቀጠለ ገልጿል፣ የተኩስ አቁም ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ እስከ በመቶዎች የሚቆጠሩ የስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን በማካሄድ በአሁኑ ጊዜ አዳዲስ ዋሻዎችን ሳይቆፍር እንዳልቀረ እና ነባር መሠረተ ልማቶችን እያጠናከረ እንደሆነ ተገልጿል።
በሪፖርቱ ውስጥ የተጠቀሱት የደህንነት ምንጮች እነዚህ እድገቶች የሃማስን የወደፊት የአሠራር አቅም በጊዜ ሂደት በእጅጉ ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ይገምግማሉ።
4 303
🇮🇱⚡️🇱🇧 ሂዝቦላህ ዛሬ የእስራኤልን IRON DOME በድሮን ሲመታ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል። ጥቃቶቹ በሁለት ድሮኖች የተፈፀሙ ናቸው።
በአንደኛው፣ ድሮኑ በቀጥታ Iron Dome System ን ሲመታ ያሳያል። በሁለተኛው ድሮን፣ የተመታውን Iron Dome እየጫኑ የሚወስዱ ወታደሮችን ሲመታ ያሳያል።
ጥቃቶቹ በሁለት ቀናት የሆኑ ናቸው።
4 303
- 🇮🇱 / 🇮🇷 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ - ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት አላበቃም ምክንያቱም አሁንም ከኢራን መወሰድ ያለበት የበለፀገ ዩራኒየም አለ። አሁንም መፍረስ ያለባቸው የማበልፀጊያ ቦታዎች አሉ። አሁንም ኢራን የምትደግፋቸው ፕሮክሲዎች እና ማምረት የሚፈልጓቸው ባለስቲክ ሚሳኤሎች አሉ። ብዙ አድቅቀናታል፣ ነገር ግን የቀረ የሚሠራ ሥራ አሁንም አለ።
