🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
Ir al canal en Telegram
Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
1 370
Suscriptores
+1824 horas
+3637 días
+64630 días
Archivo de publicaciones
🌸ቁርአን ማለት...
ሀዘን ሲሰማን :- የነቢያትን ታሪክ አውግቶ ያጽናናል።
ድካም ሲሰማን :- የጀነትን ውበት ገልጾ ኃይል ይሰጠናል።
ግራ ሲገባን:- "ሀቅ" እና "ባጢልን" ለይቶ ያሳየናል።
ብቸኝነት ሲሰማን:- አላህ ከእኛ ጋር መሆኑን ያስታውሰናል።
💧እህቴ ሆይ ! ለይልሶላት ላይበርች!!
አላህተባረከወተኣላእንዲህ ይላል፦
يَا أَيُّهَا الْمُزَّمِّلُ
አልሙዘሚል1
አንተ ተከናናቢው ሆይ፡፡
قُمِ اللَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا
አልሙዘሚል2
ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤ (ስገደ)፡፡
በሌላአንቀፅምየሌሊትንሶላትደረጃና ምንዳእንዲህበማለትይነግረናል* ፦
وَأَقِمِ الصَّلَاةَ طَرَفَيِ النَّهَارِ وَزُلَفًا مِّنَ اللَّيْلِ ۚ إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ ۚ ذَٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ
ሱረቱሁድ : 114
ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፡፡ መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና፡፡ ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው፡፡
وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا
ሱረቱአል - ኢስራእ79
ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ (በቁርኣን) ስገድ፡፡ ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡
ረሱልﷺ በእዝነት ሲያበስሩን እንዲህ ይላሉ፦ በሌሊት ተነስቶ ሰግዶ ከዚያም ሚስቱን የቀሰቀሰ ሰው አላህ ይዘንለት። ሚስቱ ከእንቅልፏ ለመነሳት ፈቃደኛ ባትሆን እንኳ ፊቷ ላይ ውሃ ይረጭባታል። በሌሊት ተነስታ ሰግዳ ከዚያም ባሏን የቀሰቀሰች ሴትንም አላህ ይዘንላት። ባሏ ከእንቅልፉ ለመነሳት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳ ፊቱ ላይ ውሃ ትረጭበታለች። ረሱል ﷺ
❶#ነገር_አዋሳጅ_ጀነት_አይገባም።
2, ነገረኛ የሸይጧን ተላላኪ ነው
ነገረኞች እባካችሁ አስታርቁ እንጂ አጣሉ አራርቁ የሚል መመሪያ የለንም።
ነገረኛ ሰምተሽ በእህትሽ ላይ የዘመትሽው እህቴ ሆይ ነገረኛ አይታመንምና ነገር የሚያመጣልሽን ሰው ማንንም አትመኝ....!!
ሰወች ነገረኛ የሚሆኑት ወይ ሲቀኑ ወይ እሳቸው ያጡትን ነገር ስታገኝ በምቀኝነት ወይም ደግሞ በጥላቻና በውሸት ነው ።
ደግሞ ለአንች የነገረችሽ ከአንችም ወስዳ ለሌላዋ እንደምትናገር አትዘንጊ!!!
✍ምናልባት ሁሌ ዱዓ ስታደርጉለት የነበረው
ነገር ልታገኙት በጣም ትንሽ ጊዜ ነው
የቀራችሁ....
........እናም በመጨረሻው ሰዓት ተስፋ
እንዳትቆርጡ::
☝️ኢላሂ ጤና መብቃቃትን ለዱንያም ለአኼራ የሚበጀንን ወፍቀን🤲
Repost from ፍቅር እስከ ጀነት | ራማስ አል ሀናኒ
✅ልዩ ማበረታቻ ለጠንካራ የሱና እህቶቻችን!
✅በዳዕዋው ዘርፍ፣ ቁርኣን በማቅራት፣ ጠቃሚ መረጃዎችን በማጋራት እና ለሌሎችም አርአያ በመሆን ሌት ተቀን የሚለፉ ምርጥ የሱና እህቶች አሉን።
🧕የእነዚህን ውድ እህቶቻችንን ልፋት አሏህ በትልቁ የሚመነዳቸው ቢሆንም እኛም ለስራቸው ተገቢ ምስክር መሆን ማበረታታት እና ማድነቅ ተገቢ ነው ! እናም ቻናሎቻቸውን በቋሚነት ለማሳደግ እና ለሌሎችም መነቃቃት ይሆን ዘንድ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል! ከሚጠቆሙት ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ (Like) የሚያገኙትን ከ1ኛ እስከ 5ኛ የሚወጡ እህቶችን በመለየት ቻናላቸውን በቋሚነት የምናሳድግ ይሆናል።
✅ ምን ማድረግ ይጠበቅቦታል?
ይህቺ እህት ልትበረታታ፣ ልትደገፍ እና ልትመሰገን ይገባታል! የምትሏትን ጠንካራ አርአያ ሴት ስሟን እና የቻናሏን ሊንክ (Link) ከታች ባለው ቦት (Bot) ላኩልን። ብዙ ድጋፍ (Like) ያገኙት አሸናፊ ይሆናሉ! 💪
✔️ ማሳሰቢያ፦
ጥቆማ የምንቀበለው እስከ ዛሬ ማታ 6 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው! አሁን ጀምሮ እጩዎችን ፖስት ማድረግ ስለምንጀምር ጊዜ ሳያጠፉ አሁኑኑ ይላኩልን።
👇 ስማቸውን እና የቻናላቸው ሊንክ ለመላክ ይህንን ቦት ይጠቀሙ ⬇
👉 @fkr_eske_Jenet_Bot 👈
= t.me/FKR_ESKE_JENET
Repost from قناةُ النِّساءِ السَّلفْيَّاتِ لِلْمذاكرات المفيد كما قال الله تعالى فذكِّرْ إنَّمَا أنت مذكر
🍂የነብዩ ሙሐመድ ﷺ ሚስቶች
1,ኸድጃ ቢንት ኹወይሊድ /ረደሏሁ ዐንሀ
2, ሰውዳ ቢንት ዘምዐህ/ረደሏሁ ዐንሀ
3/ዓኢሻ አቡበክር /ረደሏሁ ዐንሀ
4/ዘይነብ ቢንት ጀህሽ ረደሏሁ ዐንሀ
5/ሐፍሷህ ቢንት ዑመር/ረደሏሁ ዐንሁ
6/ኡሙ ሀቢባህ ረምላህ ቢንት አቡ ሱፍያን
7/መይሙና ቢንት አልሀሪስ ረደሏሁ ዐንሀ
8/ጁወይሪያህ ቢንት ሀሪስ ረደሏሁ ዐንሀ
9/ማሪያ አል ቂብጢያ/ ረደሏሁ ዐንሀ
10/ ሪሀና ቢንት ዘይድ ረዲሏህ ዐንሀ
11/ሶፊያ ቢንት ሁሀይ ረደሏሁ ዐንሀ
Repost from አህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ
ተጀመረ
📖ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ
🎙በኡስታዝ አቡ ኢምራን
የኪታቡን PDF ለማግኘት
https://t.me/sefinetunuh/9009
ደረሱ የሚሰጠዉ
🌙በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ
- -
ሸር አድርጉት
https://t.me/sefinetunuh?livestream=2aa0f105b7a048c75d
ፈጥኖ ማን ቀድሞ ይመልስ 🚀
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት ሀሰት በማለት መልሱ ።
የጀሀነም በር ጠባቂ መላዒካ ማሊክ ይባላል፡፡
ዛሬ ለራሳችን ትንሽ ርህራሄ እንስጥ…
ሁሉንም ነገር ዛሬ መፍታት አይጠበቅብንም።
ሁሉንም መልስ ዛሬ ማግኘትም አይጠበቅብንም።
አንዳንድ ቀናት የሚፈለገው ብዙ ነገር ሳይሆን፣
ልባችንን በአላህ ላይ አስቀምጠን ቀኑን በሰላም መጀመር ብቻ ነው።
የዘገየው ሁሉ የተረሳ አይደለም።
የተዘጋው ሁሉ የተከለከለ አይደለም።
ዝም ያለው ሁሉ አላህ እንደተወን ነውጰማለት አይደለም።
በእምነት እንቀጥል፤
አላህ የልባችንን ድምፅ ከንግግራችን በፊት ያውቃል።
መልካም ውሎ
🚫 ሴትነት በኮሜንቶች ስር!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
• የሴትነት ክብር - በየ ኮሜንቱ ስር፤
• ጥፍጥናውን ትቶ - እንደ እሬት ሲመር፤
• መስፈሪያውን ስቶ - እንደ ቁራ ሲበር፤
• መቀመጫን ለቆ - በጎዳና ሲያድር፤
• መኖሪያውን ርቆ - በየሚዲያው ሲዞር፣
• በጣም ያሳዝናል - ያስኮንናል የምር፤
• ሰምተነው አናቅም - ከደጋጎች ሰፈር፤
• ታይቶም አይታወቅ - ከቅኖቹ መንደር፤
▬▬▬▬▬▬▬▬
• አይናፋሯ እንስት - ሐያእን ስታፈርጥ፤
• በየ ኮሜንቱ ስር - ለመፃፍ ስትሮጥ፤
• ካገኘችው ሁሉ - መልስ ስትሰጣጥ፤
• አድ አድርገዋት - እፍረቷ ሲመጠጥ፤
• ራሷም አድ አድርጋ - ክብሯን ስትረግጥ፤
• በግል እያዋራች - እሳት ስታጨበጥ፤
• ባሏን ችላ ብላ - በሚዲያ ስትማግጥ፤
• ከአጅነቢይ ጋር - በድፍረት ስትዘንጥ፤
▬▬▬▬▬▬▬▬
• አቤት ሲዘገንን - አቤት ሲሰቀጥጥ፤
• ማየት አይስችልም - ንዴትም አያስውጥ፤
• ሴቶችን ፈታኝ ሆይ - ማጃጃሉን አቋርጥ፤
• መልከስከሱን ትተህ - አቅጣጫህን ለውጥ፤
• ጌታችን ፊት ቀርበህ - በጥያቄ ሳትፈጥ፤
• ማምለጫ የለምና - አይገኝም ማምለጥ፤
• መናገር ይሻላል - ዝም ቦሎ ከማፍጥ፤
▬▬▬▬▬▬▬▬
Repost from هَذِهِ عَقيدَتُنَا
🌿 ውዷ እህቴ፣ ጀግና ሴት ሁኚ!
📚ዲንሽን በማንም አትለውጪ፤
📚ሐያእሽን ለማንም አትስጪ፤
📚ሱናን ለማንም አትልቀቂ። 🌿
📚 በእምነትሽ ላይ ጽኚ፤
ብቻሽን ብትቀሪም አትንበርከኪ!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/qdemiy_letwuhide
Repost from هَذِهِ عَقيدَتُنَا
አንድ ሙስሊም ሴት ሊኖሯት የሚገቡ አደቦች🎀
➺አሏህን ልትታዘዝ
➺ሰራዋንም ለአሏህ ብቻ ብላ መስራት
➺ የአሏህን መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ልትከተል ➺እንድሁም ከሌላ ጥመት መንገዶች ልትርቅ
➺እሷም ለልጆቿና እና ለእህቶቿ ጥሩ አምሳያ ልትሆን ➺እውቀትንም ልትማር ባወቀችውም ልትሠራ
➺ሌሎችንም ልታስተምር
➺በሚደርሱባት ችግሮች በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሶብር ልታደርግ
➺እንድሁም ሙስሊም የሆኑ እህቶችን ሁሉንም ልትመክር
👌➺ጀሊሉ እዉቀት ከአደብ ከተግባር ጋር ይስጠን መጨረሻችንን ያሳምርልን ═✿🍃🌺🍃✿═
t.me/qdemiy_letwuhide
አንዳንድ ጧቶች ቃል አይፈልጉም....
አንድ አዲስ ቀን፣
አንድ አዲስ ተስፋ፣
አንድ ዝምታ ውስጥ የተደበቀ ዱዓ ብቻ ይበቃቸዋል
ዛሬ ልባችን የሚፈልገውን ሁሉ ላይሰጠን ይችላል፤
ነገር ግን አላህ የሚያዘጋጀውን ምን እንደሚመስል አናውቅም
ስለዚህ ዛሬን በተስፋ እንጀምር
ምናልባት የጠበቅነው ነገር ከእኛ ይልቅ አላህ ዘንድ ቀድሞ ተዘጋጅቶ ይሆናል
አልሐምዱሊላህ ለዚህ ቀን
