es
Feedback
Sinksar tube(ስንክሳር)

Sinksar tube(ስንክሳር)

Ir al canal en Telegram

እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
2 519
Suscriptores
+2724 horas
+1207 días
+47530 días

Carga de datos en curso...

Canales Similares
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
septiembre '26
septiembre '26
+294
en 0 canales
agosto '26
+679
en 1 canales
Get PRO
julio '26
+754
en 1 canales
Get PRO
junio '26
+1 392
en 1 canales
Get PRO
mayo '260
en 0 canales
Get PRO
abril '260
en 0 canales
Get PRO
marzo '260
en 0 canales
Get PRO
febrero '260
en 0 canales
Get PRO
enero '260
en 0 canales
Get PRO
diciembre '250
en 0 canales
Get PRO
noviembre '250
en 0 canales
Get PRO
octubre '250
en 0 canales
Get PRO
septiembre '250
en 0 canales
Get PRO
agosto '250
en 0 canales
Get PRO
julio '250
en 206 canales
Get PRO
junio '25
+2
en 0 canales
Get PRO
mayo '250
en 154 canales
Get PRO
abril '25
+35
en 157 canales
Fecha
Crecimiento de Suscriptores
Menciones
Canales
11 septiembre0
10 septiembre+43
09 septiembre+57
08 septiembre+36
07 septiembre+42
06 septiembre0
05 septiembre+1
04 septiembre+2
03 septiembre+27
02 septiembre+57
01 septiembre+29
Publicaciones del Canal
🌻🌻🌻✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝✝✝ ‹‹‹ እንኳን አደረሳችሁ ››› ✝ #መስከረም 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት =>ይህች ዕለት እጅግ ክብርትና ልዕልት ናት:: አዲስ ዓመት: አዲስ ሕይወት: አዲስ ተስፋ: አዲስ በረከትን እናገኝ ዘንድ እርሱ በቸርነቱ ከዚህች ዕለት አድርሶናልና:: ለእርሱ ምን ይከፈለዋል? "ተመስገን" ከማለት በቀር:: =>ይህቺ ዕለት ብዙ ስያሜዎች ቢኖሯትም እነዚህን እንጠቅሳለን:- 1.ቅዱስ ዮሐንስ (መጥምቁ ዮሐንስ ርዕሰ ቅዱሳን ስለሆነ በእርሱ ተሰይማለች) 2.ርዕሰ ዐውደ ዓመት (የዐውደ ዓመቶች ራስ) 3.እንቁጣጣሽ (ንግስተ ሳባንና ንጉሥ ሰሎሞንን አንድ ያደረገች ዕለት) 4.ዕለተ ማዕዶት (መሸጋገሪያ) 5.ጥንተ ዕለታት (የዕለታት መጀመሪያ) 6.ዕለተ ብርሃን (የአዲሱን ዓመት ብርሃን የምናይባት) =>ከምንም በላይ ግን ይህች ዕለት የአዝማነ መንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት:: አሮጌው ዓመት የዚህ ዓለም ምሳሌ ሲሆን አዲሱ ደግሞ የሰማያዊው ሕይወት ምሳሌ ነው:: ዻጉሜን ደግሞ የዘመነ ምጽዓት ምሳሌ ናት:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዕለቷ ክብርት ናት:: *" ምንተ ንግበር / ምን እናድርግ? "* +እግዚአብሔር ከእኛ ብዙና ከባድ ነገሮችን አይፈልግም:: ደግሞም አይጠብቅም:: እርሱ ቸር ነውና በአዲሱ ዓመት ከእኛ:- 1.እንፋቀር ዘንድ 2.ንስሃ እንገባ ዘንድ እና 3.የቀናውን ጐዳና እንድንመርጥ ብቻ ይፈልጋል:: *በተሠማራንበት ሥራ ሁሉ: ባለንበትም ሃገር ሁሉ እግዚአብሔርን እናክብር: ድንግል እመቤታችንን እናፍቅር: ቅዱሳንን እናስብ ዘንድ ልንተጋ ይገባል:: ለዚህም ደግሞ የሥላሴ ቸርነት: የእመ ብርሃን አማላጅነት: የቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከት ይደርብን:: ✝ ዘመኑን የፍቅር: የሰላምና የበረከት ያድርግልን:: ✝ +*" ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ "*+ ✝ ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው:: (ማቴ. 10:3) ነገር ግን ዜና ሕይወቱ በስፋት ሲተረክ አንሰማም:: ቅዱሱ ሐዋርያ እንደ ሌሎቹ ወንድሞቹ ዓለምን በወንጌል ትምሕርት አብርቷል:: በትውፊት ትምሕርት መሠረት 'በርተሎሜዎስ' የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታችን ሲሆን ትርጉሙም 'ተክሎችን የሚያጠጣ' ማለት ነው:: *ከሐዋርያትም ጌታ አስቀድሞ የስም ቅያሪ ያደረገለት ለእርሱ እንደ ሆነ ይታመናል:: በርተሎሜዎስ የግብርና ሥራውን ትቶ: የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ: ከዋለበት እየዋለ: ካደረበትም እያደረ ምሥጢረ ወንጌልን ተምሯል:: *ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላም ከሐዋርያት ጋር ዓለምን በዕጣ ተካፍሏል:: ሃገረ ስብከቱም 'እልዋህ' እና 'አርማንያ' ናቸው:: የአርማንያ መንበርም የእርሱ ነው:: ቅዱሱ ገድሉ እንደሚለው አሕዛብን በስብከቱና በሚያስደነግጡ ተአምራቱ አሳምኗል:: *ከቅዱስ ዼጥሮስ: ከቅዱስ እንድርያስ: ከክርስቶፎሮስና ከሌሎቹም ሰባክያን ጋር ዓለምን ዙሯል:: ሙታንን አስነስቶ: ድውያንን ፈውሶ: አጋንንትን አውጥቶ: ብዙወችን ወደ ሕይወት መልሷል:: የደረቁ እንጨቶችም በእጁ ላይ እንዳሉ ለምልመው: አብበው ያፈሩ ነበር:: *ቅዱስ በርተሎሜዎስ እያስተማረ ወደ ኢትዮዽያም ደርሶ እንደ ነበር ይነገራል:: በመጨረሻም 'ለሚስቶቻችን ንጽሕናን አስተምረሃል' በሚል ተከሶ: ንጉሥ አግሪዻ በሰቅ (ጸጉር) ጠቅልሎ: አሸዋ ሞልቶ: ባሕር ውስጥ ጥሎታል:: በዚያውም ዐርፏል:: +*" ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ "*+ ✝ይህቺ ሃገረ ቁልዝም ግብጽ ውስጥ የምትገኝ ስትሆን ብዙ ቅዱሳንን አፍርታለች:: በተለይ የአባ እንጦንስና የልጆቹ ማረፊያ ከመሆኗ ባሻገር ቅዱስ አባ ሚልኪም ወጥቶባታል:: ቅዱሱ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ: የስለት ልጅም ነው:: ጥሩ ክርስቲያኖች የነበሩት ወላጆቹ እጅግ ባለጸጐችም ነበሩ:: *በስለት መንታ ልጆችን (ሚልኪና ስፍናን) ወልደው: በሥርዓት አሳድገዋል:: ቅዱስ ሚልኪ በሕጻንነት ወራቱ ስቆና ከሕጻናት ጋር ተጫውቶ አያውቅም:: ብሉያትና ሐዲሳትን ጠንቆቆ ካጠና በኋላ እድሜው 19 ሲደርስ ወላጆቹ "እንዳርህ" አሉት:: የልቡን እያወቀ "እሺ" አላቸው:: *ቀጥሎም "ባልንጀሮቼን ልጋብዝበት" ብሎ: 1,000 ወቄት ወርቅ ተቀብሎ: በፈረስ ተቀምጦ ሔደ:: መንገድ ላይ መቶውን ለተከተሉት: 9 መቶውን ወቄት ለነዳያን: ፈረሱን ደግሞ ለአንድ ደሃ ሰጥቶ: ጡር (ጢር) ወደ ሚባል በርሃ ገሰገሰ:: *መጥፋቱ በቤተሰብ ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: እናቱም ዐይኗ ተሰወረ:: እርሱ ግን አባ አውጊን ከሚባል ባሕታዊ ሒዶ ደቀ መዝሙሩ ሆነ:: ለ3 ዓመታትም ተፈትኖ መነኮሰ:: *ከዚያም በጠባቡ ጐዳና ገብቶ በጾም: በጸሎት: በትሩፋት ከፍ ከፍ አለ:: ከቅድስናው ብዛት የተነሳ አጋንንት ገና ከርቀት ሲያዩት ይሸሹት ነበር:: የነካቸውም ሁሉ ይፈወሱለት ነበር:: በእርሱ ጸሎትም በፋርስና በሮም ሰላም ሆነ:: *አንድ ቀን የዳዊትን መዝሙር እየዘመረ ሲሔድ የአገረ ገዥውን ልጅ ዘንዶ በልቶት ሲለቀስ ደረሰ:: ጸሎት አድርጐ ዘንዶውን ጠራውና "እንደ ነበረ አድርገህ ትፋው" ሲል አዘዘው:: ዘንዶውም ተፋው: ሰይጣኑም ሸሽቶ አመለጠ:: *ሃገረ ገዥው ደስ ቢለው 300 ቤቶች ያሉት ገዳም ለማር ቅዱስ ሚልኪ አነጸለት:: በዚያም 300 መነኮሳት ተሰብስበው ትልቅ ገዳም ሆነ:: ማር ሚልኪ ሁሉን ካሰናዳ በኋላ "ከዚህ አልወጣም" ብሎ በዓቱን ዘጋ:: ሰይጣን ግን "አስወጣሃለሁ" ብሎ ፎክሮ ሒዶ በንጉሡ ልጅ አደረባትና አሳበዳት:: *"ከሚልኪ በቀር የሚያሰወጣኝ የለም" አለ:: ንጉሡ ወታደሮቹን ጠርቶ "ሒዳችሁ: አባ ሚልኪን ይዛችሁ ብትመጡ ሽልማት: ካልሆነ ግን ሞት ይጠብቃችሁአል" አላቸው:: እነርሱም በጭንቅ አግኝተው "እንሒድ" አሉት:: "በሮም ከተማ በር ላይ እንገናኝ" አላቸው:: *ልክ በዓመቱ እነርሱ ሮም ሲደርሱ ማር ሚልኪ ደመና ጠቅሶ ከተፍ አለ:: ልጅቱንም አቅርቦ ሰይጣንን "እየታየህ ውጣ" አለው:: ወደል ጐረምሳ ሆኖ ወጣ:: ወስዶም አሰረው:: ከቀናት በኋላ ሕዝቡና ንጉሡ እያዩ ማር ሚልኪ ደመና ላይ ተቀምጦ: ሰይጣኑን የድንጋይ ገንዳ አሸክሞ እየነዳ ወሰደው:: *ሕዝቡም ደስ ብሏቸው በታላቅ ዝማሬና እልልታ ሸኙት:: ሰይጣኑንም ለዘለዓለም አሰረው:: ቅዱስ ሚልኪ በገዳሙ ለዓመታት ከተጋደለ በኋላ በዚህች ቀን ቅዱሳን አባ እንጦንስ: መቃርስ: ሲኖዳና ሌሎችም መጥተው: በክብር ተቀብለውት ዐርፏል:: አበው 'ትሩፈ ምግባር' ይሉታል:: +" ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት "+ ✝ከዘጠኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን በብርሃናት ላይ ተሹሟል:: ለሃገራችን ልዩ ፍቅር ያለው መልአኩ ከሔኖክ ጀምሮ የብዙ ቅዱሳን ረዳት ነው:: ዛሬ በዓለ ሲመቱ ነው:: +" ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ "+ ✝ታላቁ ጻድቅ: የትእግስትም አባቷ ቅዱስ ኢዮብ በጭንቅ ደዌ ለብዙ ዘመናት በመከራ ከኖረ በኋላ በዚህች ቀን በፈሳሽ ውሃ (በዮርዳኖስ) ታጥቦ ሰውነቱ ታድሷል:: ክብርም ተመልሶለታል:: በፈሳሽ ውሃ የምንጠመቅበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው:: +የበርተሎሜዎስ አምላክ ፍቅሩን: የሚልኪ አምላክ ትሩፋቱን: የራጉኤል አምላክ ረድኤቱን: የኢዮብ አምላክ ትእግስቱን ያሳድርብን:: +መስከረም 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ርዕሰ ዓውደ ዓመት 2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 3.ቅዱስ /ማር/ ሚልኪ (ትሩፈ ምግባር) 4.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት 5.ቅዱስ ኢዮብ ተአጋሲ 6. ሜልዮስ ሊቀ ዻዻሳት

2
+9
Sin texto...
12
3
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፤ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣ በየዓመቱ የይቅርታ እጁን እየዘረጋ የሚመግበን እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ወደ ዘመነ ሉቃስ ሁለት ሺሕ ዓሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወይእዜኒ ነስሑ ወተጠመቁ፤ ወይደመሰስ ለክሙ ኃጢኣትክሙ፤ ወይመጽእ ለክሙ መዋዕለ ሣህል እምቅድመ ገጹ ለእግዚአብሔር፤ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላችሁ፣ ኃጢአታችሁም እንዲደመሰስ አሁንም ንስሐ ግቡ ተመለሱም” (የሐ.ሥራ ፫፡፲፱) የሰው ልጅ በስሑት ስራውና አእምሮው ምክንያት የኃጢአት ማዕበል በሚያናውጠው ባሕረ ዓለም እንደሚኖር ይታወቃል፤ የዓለሙ ባሕር በማዕበሉ በተናጠ ቁጥር በመርከቡ ተሳፍረው የሚጓዙ ሁሉ ጭንቀት ላይ መውደቃቸው የማይቀር ነው፤ በዚህ ጊዜ የሚያጽናና የቊርጥ ቀን ረዳትና ኃይል ያስፈልጋቸዋል፤ ሆኖም ረዳት በፍጥነት እንዲደርስላቸው መጮኽና መጣራት ከነሱ ያስፈልጋል፤ የምንኖርባት ዓለም ወይም ፕላኔት የክፋትና የጭካኔ ማዕበል በእጅጉ እየበረታባት መጥቶአል፤ ዓለማችን በስጋትና በፍርሓት፣ በራስ ወዳድነትና ባለመተማመን ተከባለች፣ በመሆኑም ዓለማችን ከምን ጊዜውም በላይ የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላት ትሻለች፤ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ የሰጠ አምላክ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው፤ ይሁንና እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልጋቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ በማያሻማ ሁኔታ አሳውቆአል፤ ከእነሱም መካከል በእውነተኛው መንፈስ ንስሐ መግባት፤ መጸጸትና መመለስ ናቸው፤ የዓለምን ሕዝብ በወሳኝነት ማጽናናት የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እኛ ራሳችንን በራሳችን ለማጽናናት እንኳ በቂና ዘላቂ ዓቅም የሌለን ውሱኖች ነን፤ ይህንን እውነት ዓውቀን የእርሱን ርዳታ እንድንሻ እግዚአብሔር ይፈልጋል፤ ይህንንም ከልብ በመጸጸትና ከቀደመው ስሑት ተግባራችን በመመለስ በፊቱ ተንበርክከን መታዘዛችንን በተጨባጭ እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት! እግዚአብሔር ከታላቅ ቸርነቱ የተነሣ የመታደስ ዘመንን በየዓመቱ ከመስጠት አልተቈጠበም፤ እንደ ሁሉጊዜ አሁንም አዲሱን ዘመን ባርኮ ሰጥቶናል፤ ሆኖም አዲሱ ዘመን የመጽናናት ዓመት እንዲሆንልን የእኛ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው መዘንጋት የለብንም፤ ከሁሉ በፊት ያለፈውን ዓመት እንደ ግልም፣ እንደ ማኅበረ ሰብም፣ እንደ ሃገርም፤ እንደ ሃይማኖትም በኅሊናችን ልናስበውና ልንገመግመው ይገባል፤ ያለፈውን ዓመት በንጹህ ኅሊናችን በጥልቀት ስንገመግመው፤ የመጣንበትና ያለፍንበት ስለሆነ ኮለል ብሎ በፊታችን ይታያል፤ ጥቅሙም ሆነ ጉዳቱ በሙሉ ከኛ የራቀ ስለማይሆን ዳኝነት ለመስጠትና ውሳኔ ለመወሰን አንቸገርም፤ በመሆኑም ለፈጸምነው ስሕተት ይቅርታን ከመጠየቅ ባሻገር ድጋሚ ላንደግመው መወሰንና ለተግባራዊነቱ በጽናት መቆም አለብን፤ እኛ በዚህ ደረጃ ከቀደመው ስሕተታችን ተጸጽተን ንስሐ ከገባን እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገውን አግኝቶአል ማለት ነው፤ በመካከላችንም ትክክለኛ መግባባት ተፈጥሮአል ማለት ነው፤ በዚህ ጊዜ እሱም ዘላቂ የሆነ የመጽናናት ዘመን ለኛ ይሰጣል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት! በዓለሙ እንዳለው ሁሉ እኛም ወዲያና ወዲህ ከሚያወዛውዝ ፈተና አላመለጥንም ያለፈውን ዓመት በንጹሁ አእምሮአችን ስንመዝነው፤ ጥሩ የሚባል አልነበረም፤ በየአካባቢው ግጭቶች የቀጠሉበት፣ የሰው ደም የፈሰሰበት፣ ዕገታዎች የተፈጸሙበት፣ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የተቃጠሉበት፣ ምእመናን የተገደሉበትና የተፈናቀሉበት፣ ስጋት ያየለበት፣ ኑሮም የተወደደበት፣ ሌላም ሌላም ለሰው ልጅ የማይበጁ ነገሮች የተከሠቱበት ዓመት አሳልፈናል፤ ታዲያ አዲሱን ዘመን ስንቀበል እነዚህን ሁሉ እንዳሉ ይዘናቸው እንቀጥል ይሆን? ይህስ ከሆነ ‹‹እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሳችሁ›› መባባሉ ትርጉም ይኖረው ይሆን? እንዲህስ ልንሆን ፈጽሞ አይገባም፤ ይልቁንም ባለፈው ዓመት የሆኑትን ሁሉ ላንደግማቸው ሁላችንም እንወስን፤ እነሱንም ማስቀረት እንችላለን፤ ምክንያቱም ችግሮቻችን በሙሉ ሰው ሰራሽ እንጂ የተፈጥሮ አይደሉም፤ ሰው ሰራሽ ችግሮች ደግሞ በሰው እንደመጡ ሁሉ በሰው ሊቀሩ የሚችሉ ናቸውና እናስቀራቸው፤ ጦርነቱን፣ ዕገታውን፣ ጥላቻውን፣ ፉክክሩን፣ እልከኝነቱን፣ ጭካኔውን ራስ ወዳድነቱን ግድያውን፣ አብያተ ሃይማኖት ማቃጠሉንና ማፍረሱን እኛው እንዳመጣነው እኛው ማስቀረት እንችላለን፤ ስንተወው እኮ ይቀራል፡፡ ስለሆነም ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን እንዳለች የጋራ ዕድልና ሃብት አድርጋችሁ ተቀበሉ፤ ሌላውን ረጅም ጊዜ ሰጥታችሁም ቢሆን በውይይትና በመግባባት እየፈታችሁ በአንድነት ቀጥሉ፤ በይቅርታመንፈስ በአንድነት ተቃቅፎ ከመቀጠል ውጭ ሌላ የተሻለ ዕድል እንደሌለ በውል ተገንዘቡ፤ ለዚህ ሁላችሁም የበኩላችሁን ልባዊ ጥረት ከማድረግ አትቈጠቡ ብለን ከልብ እንመክራለን፡፡ በመጨረሻም፤ ለሁሉም መድኃኒቱ ቀና አእምሮ ነውና በአዲሱ ዓመት እግዚአብሔር ቅንና በጎ አሳቢ አእምሮ እንዲሰጠን በሱም ያሉብንን ጉድለቶች አርመንና አስተካክለን ሰላም የሰፈነበትን የመጽናናት ዘመን ማየት እንችል ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችንን እንለምን፤ እኛም በንስሐ እንመለስ እያልን በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ በማለት አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን ፡፡ እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዘመን ያድርግልን፡፡ እግዚአብሔር ኣምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኣሜን!! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ መስከረም ፩ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
9
4
“ስለዚህ በዓሉን የምናከብረው እንደ አረማዊ በዓል ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ነው በዓለማዊው መንገድ ሳይሆን ከዓለም በላይ በሆነ መንገድ ነው።የራሳችን ጉዳይ  ሳይሆን የኛ የሆነውን ወይም የጌታችንን ጉዳይ የምናከብረው ስለ ሕመም ሳይሆን ስለ ፈውስ ነው።                                                                              ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ 
20
5
🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው 1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ 2️⃣ ለወጣ  250 ብር ካርድ 3️⃣ ለወጣ  100 ብር ካርድ 👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
2
6
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 h
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
3
7
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ _ 🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼 °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ 🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼 °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ _ 🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼 °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
1
8
+1
Sin texto...
32
9
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❀ የ፳፻፲፰ (2018) ዓ/ም ዝክረ_ቅዱሳን በእግዚአብሔር ቸርነት ደረሰ፡፡ ተፈጸመ፡፡ ✞ ዘአቅረብኩ ማኅሌተ . . . ✞ ☞"ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ" (አእላፍ ቅዱሳንን አዘክሬ ምስጋናን አቀረብኩልህ) ☞"እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ" (እሊህ ቅዱሳንም ዘወትር አንተን ያገለገሉህ ናቸው) ☞"ለእለ አነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ" (በድኅነቴ የማነብልህን መጽሐፍ /ምስጋና/ ተቀበል) ☞"እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ: እም እለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ" (አንተ ብዙ ባለ ጠጐች ካገቡት ይልቅ የድሃዋን መበለት ስጦታን ተቀብለሃልና) ☞"ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባክያን" (ቅዱሳን የሆናችሁ ነቢያት: ለማስተማር የተመረጣችሁ ሐዋርያት) ☞"ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን" (ሰማዕታት: ጻድቃን: ትጉሃን የሆናችሁ መላእክት) ☞"ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ሔራን" (እናንተም ደናግል: ቸር የሃናችሁ መነኮሳት) ☞"ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን" (ይህችን ጉባኤ /አንድነታችንን/ መባረክን ባርኩ) ☞"እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕጻን" (ስትባርኩም ከሕጻናቱ ጀምራችሁ እስከ ሽማግሌው ድረስ ይሁን) ☞"ለዘጸሐፎ በክርስታስ" (በብራና: በወረቀት የጻፈውን) ☞"ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ" (ሊያስደርስ በገንዘቡ ዋጅቶ ያጻፈውን) ☞"ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ" (አምኖ ያነበበውን: ወደ ሌላ ልሳን የተረጐመውንም) ☞"ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ" (በዕዝነ ልቡና አምኖ የሰማውን) ☞"በጸሎተ እሙ ማርያም አራቂተ ኩሉ እምባዕስ" (ከጠብ ከክርክር: ከመከራ ከችግር በምትሰውር በእናቱ በማርያም ጸሎት) ☞"ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ" (ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችን አንድ ላይ ይማረን) ☞"ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ" (ቅዱስ መንፈሱንም ይላክልን) ☞"እምይእዜ ወእስከ ለዓለም አሜን" (ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለሙ አሜን) ✝✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::
32
10
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇 👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ 👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 👤ዘማሪ አቤል መክብብ 👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ 👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው 👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 👤 ዘማሪት ወርቅነሽ 👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ 👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ 🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
2
11
🌻🌼 ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ አመጣጥና ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ያገኙበታል።👇
🌻🌼 ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ አመጣጥና ሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ያገኙበታል።👇
2
12
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN በሉት ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 h
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
4
13
⏰ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል ⚪️የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ! 🔴የዘንድሮው ጷግሜ ወር ስንት ቀን ነው ⁉️
⏰ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል ⚪️የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ! 🔴የዘንድሮው ጷግሜ ወር ስንት ቀን ነው ⁉️
2
14
🎉 እንኳን ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት! 50GB ነፃ የሞባይል ዳታ። Celebrate and claim free 50GB data
🎉 እንኳን ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት! 50GB ነፃ የሞባይል ዳታ። Celebrate and claim free 50GB data
3
15
⁉️ የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇 ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 1⃣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 2⃣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 3⃣ የብጹህ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 4⃣ የቅዱስ እንጦስ ትምህርቶች ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 5⃣ የቅዱስ ኤፍሬም ትምህርቶች ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 6⃣ የአባ ሕርያቆስ ትምህርቶች ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ የሁሉንም አባቶች ትምህርት ይፈልጋሉ❓️ --------------------------------------------------
3
16
⏰ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል ⚪️የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ! 🔴የዘንድሮው ጷግሜ ወር ስንት ቀን ነው ⁉️
⏰ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል ⚪️የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ! 🔴የዘንድሮው ጷግሜ ወር ስንት ቀን ነው ⁉️
1
17
🌼 የአዲስ ዓመት በዓል መዝሙሮችን ለማጥናት👇👇 🎶 ሆ ብለን መጣን 🎶 እሰይ ደስ ደስ ይበለን 🎶 አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር . 🎶 ዘመን ተሰጠን ለምስጋና 🎶 አዲስ ቀን መጣ 🎶 አዲሱን ቀን በምስጋና 🎶 አበባ አበባዬ ተመስገን ጌታዬ . 🎶 ዘመን እንደዋዛ 🎶 ደግ ደጉን አሳየን 🎶 መስከረም ጠባ 🎶 ባርክ ለነ . 🎶 ጌታ ሆይ ምን አቀድክ? 🎶 ጌታ ዘመንን ለወጠልን 🎶 የአዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሃ 🎶 አዲሱን ዓመት ባርክልን . 🎶አበባየሆሽ....ለምለም 🎶 መስቀል አበባ 🎶 አሮጌው አለፈ አዲስ ዘመን መጣ 🎶 የእንቁጣጣሽ መዝሙር... እነዚህን ለማጥናት Join አድርጉ     join join join      Join joinjoin
3
18
🎧🎵የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇 👤ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 👤 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ 👤ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 👤ዘማሪ አቤል መክብብ 👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ 👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 👤 ዘማሪት በዛወርቅ አስፋው 👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 👤 ዘማሪት ወርቅነሽ 👤 ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ 👤 ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ጻድቅ 🌐 ሁሉንም የኦርቶዶክስ መዝሙር 🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶
1
19
✝️ ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ ✝️ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ _ 🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼 °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ 🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼 °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ _ 🌼 ባለ ማኅተቦች ብቻ play ይበሉ 🌼 °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️ ⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
1
20
🌻 ክረምቱን ለበጋው ምን ለመለወጥ እና አዲሱን ዓመት እንዴት ለመቀበል አሰባችሁ? 2019 😇
🌻 ክረምቱን ለበጋው ምን ለመለወጥ እና አዲሱን ዓመት እንዴት ለመቀበል አሰባችሁ? 2019 😇
2