🥀𐚁ΜαℓιΚα ρσៜτៜ𐚁👑
Open in Telegram
🥀Assalamualekum🥀 🌷Ɯɛℓcσмɛ тσ тнιƨ cнαт🌷 🦋Ɩƨℓαмιc ρσɛм🦋 αи∂ ριc🦋
Show more241
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+1330 days
Posts Archive
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ አንዴት ናችሁ ያአህባብ
ጽሑፍ ስለ ምን እንጻፍላችሁ አና ምን ፕሮግራም ይጨመር
https://ngl.link/sabitnii85
بسم الله الرحمن الرحيم
ልብሽን ከአላህ ጋር አያይዢ!
አንዳንድ ጊዜ ዓለም በችግሮች ትከብዳለች፤ ልብሽም በጭንቀት ይሞላል። ነገር ግን የአላህን ምሕረት አትርሺ። ወደ እርሱ በዱዓ ተመለሺ፣ ሶላትሽን ጠብቂ፣ በትእግስትም ተገኚ።
🌸 አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦
﴿ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ ﴾ «ንቁ! ልቦች በአላህ ዝክር ይረጋጋሉ።»📚 ሱረቱ አር-ረዕድ፣ 13:28 🕊️ እህቴ ሆይ! ዱንያ ጊዜያዊ ናት፤ የአኼራ ሕይወት ግን ዘላለማዊ ነው። ስለዚህ ልብሽን በኢማን አሳምሪ፣ ምላስሽን በዝክር አርጥቢ፣ ሥራሽንም በመልካም አሳምሪ። 🤲 اللَّهُمَّ ثَبِّتْ قُلُوبَنَا عَلَى دِينِكَ የአላህ ሆይ! ልቦቻችንን በዲንህ ላይ አጽናቸው። አሚን! 🌷 ይህ መክር ለሌላ ሰውም መልካም ከሆነ አጋሩት።🌸 Join us🥰 @amilanmana
بسم الله الرحمن الرحيم
ልብሽን ከአላህ ጋር አያይዢ!
አንዳንድ ጊዜ ዓለም በችግሮች ትከብዳለች፤ ልብሽም በጭንቀት ይሞላል። ነገር ግን የአላህን ምሕረት አትርሺ። ወደ እርሱ በዱዓ ተመለሺ፣ ሶላትሽን ጠብቂ፣ በትእግስትም ተገኚ።
🌸 አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦
﴿ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ ﴾ «ንቁ! ልቦች በአላህ ዝክር ይረጋጋሉ።»📚 ሱረቱ አር-ረዕድ፣ 13:28 🕊️ እህቴ ሆይ! ዱንያ ጊዜያዊ ናት፤ የአኼራ ሕይወት ግን ዘላለማዊ ነው። ስለዚህ ልብሽን በኢማን አሳምሪ፣ ምላስሽን በዝክር አርጥቢ፣ ሥራሽንም በመልካም አሳምሪ። 🤲 اللَّهُمَّ ثَبِّتْ قُلُوبَنَا عَلَى دِينِكَ የአላህ ሆይ! ልቦቻችንን በዲንህ ላይ አጽናቸው። አሚን! 🌷 ይህ መክር ለሌላ ሰውም መልካም ከሆነ አጋሩት።🌸 Join us🥰 @amilanmana
فَبِأَيِّ ألَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ ❤️
ከጌታቹህ ፀጋዎች በየትኛው ታስተባብላላቹሁ???
በዲያሊሲስ ወቅት ደም በቀይ ቱቦ ከሰውነት ይወጣል ከዚያም በማሽን ውስጥ ካለፈ በኋላ እንደገና በሰማያዊ ቱቦ ወደ ሰውነታችን ይገባል.
የዲያሊሲስ ሂደት ለ 4 ሰዓታት ያህል የሚቆይ ሲሆን በሽተኛው በሳምንት ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ ሂደቱን መድገም አለበት ከከባድ ህመም ና ድካም ጋር ።
በሌላ በኩል ኩላሊታቸው ጤናማ በሆኑ ሰዎች አካል ውስጥ በቀን 36 ጊዜ ተመሳሳይ ሂደት ካለ ምንም አይነት ህመም ና ድካም ይከናወናል።
ታዲያ #ሳንከፍል #ሳንደክም ለተሰጠን ሙሉ ጤና #አልሃምዱሊላህ እንበላ!
Copy
በ ህይወትህ ማወቅ ያለብህ
8 ነገሮች:
1- ደስታ?
👉"ሰላትን በጊዜዋ ስገድ"
2 የፊት ብርሃን?
👉''ለይል ስገድ፤ ፈጅርንም አታስመልጥ"
3 ጤና?
👉"ፁም "
4 - እርጋታ እና ሰላም?
👉"ቁርዓን ቅራ"
5 - ፈረጃ?
👉"እስቲግፋር አብዛ"
6 - የጭንቀት መወገድ?
👉"ዱዓ ማድረግ አዘውትር - አብዛ"
7 - በረካ?
👉"ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት አውርድ።'
8 - የመከራ መወገድ?
👉"(ላ ሃውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ) ማለት አብዛ።''
ሸይኽ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
#ለአላህ_ብለው_የሚዋደዱ_ሰዎች 💚💚ውዴታቸው በዱንያ ጉዳዮች የተነሳ አይቋረጥም፣እነርሱ ለአላህ ብሎ የሚዋደዱ ስለሆነ ከሞት በስተቀር ሌላ የሚለያያቸው ነገር አይኖርም፣አንዱ በሌላው ላይ ስሕተትን ቢፈፅም፣ ሐቁን ቢያጓድልበትም እንኳ እንዲህ ያሉ ነገሮች አያስጨንቃቸውም።
📚📚ሸርሑ ሪያድ ሳሊሒን(3/263
👉ወደ መስጅድ በመሄድ የጀመዓ ሶላት መስገድ
ያለው ጠቀሜታ :-
አብደላ ኢብን መኽቱም
( ረ. ዐ ) አንድ ጊዜ
ነቢዩን ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) እንዲህ በማለት
ጠየቃቸው :-
" የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! መዲና በመርዘኛ ነፍሳት በጎጂ አውሬዎች የተሞላች ናት :: እነዚህ
ነፍሳት የሚናከሱ አውሬዎች ይጎዱኛል ብዬ እፈራለሁ :: ወደ መስጊድ ከመምጣት ይልቅ እቤቴ
ሆኜ መስገድ እንድችል አይፈቅዱልኝምን ? "
የአላህ መልዕክተኛ ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
እንዲህ አሉ :-
👉 " ሃያ አለ ሶላህ (ወደ ሶላት ኑ ) ፣ ሃያ አለል ፈላህ
( ወደ ተሳከ ሕይወት ኑ ) የሚለውን ጥሪ ትሰማለህ ? እንደዚያ ከሆነ ወደ መስጊድ መምጣት አለብህ ። "
( አቡ ዳውድ እንደዘገቡት )
👉ምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ቢገጥመን
የሶላት ጥሪ ( አዛን ) ከሰማን መልስ የመስጠት ግዴታ እንዳለብን ነው :: ነቢዩ ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) በአንፅኦት ያሰገነዘቡን ::
ሰዎች ወደ መስጊድ ይመጡ ዘንድ የአላህ መልዕክተኛ ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ማስጠንቀቂያ ይሰጡ ነበር ::
ኡበይ ኢብን ከዓብ ( ረ . ዐ . ) እንዲህ ይላል :-
" አንድ እለት የአላህ መልዕክተኛ ( ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም ) የፈጅር ሶላት ከሰገዱ በሗላ እንዲህ አሉ
" እገሌና እገሌ ለሶላት መጥተዋልን ? "
አልመጡም የሚል መልስ ተሰጣቸው ::
" አገሌና እገሌስ አልመጡምን ? " አሉ ::
" አልመጡም " የሚል መልስ ሰጧቸው ::
በዚህ ጊዜ እንደህ አሉ :- " እነዚህ ሁለት ሶላቶች
( የፈጅር እና የኢሻ ሶላት ) ናቸው በመናፍቃን ላይ
ከባድ የሚሆኑት ::
እነዚህ ሶላቶች የያዙትን ትርፍና ትሩፋት ብታውቁ ኖሮ በእንብርክካቹሁ እየዳሃቹሁ መጥታቹሁ በጀመዓ ትሰግዱ ነበር ::
👉የመጀመሪያው አወል ሶፍ ልክ እንደመላእክት ሶፍ
ነው : የሚቆጠረው በእርሱ ውስጥ ያለውን ትሩፋት ብታውቁ ኖሮ ቦታውን ለመያዝ ትሽቀደደሙ ነበር ::
አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር በመሆን የሚሰግደው ሶላት ብቻውን ከሚሰግደው ሶላት ይልቅ ብዙ ትሩፋትና ብዙ ምንዳ ( አጅር ) ያስገኝለታል :: ከሁለት ሰዎች ጋር በመሆን የሚሰገድ ሶላት ከአንድ ሰው ጋር ሆኖ ከሚሰገድ ሶላት ይልቅ በላጭና ብዙ ትርፋማ ነው ::
የሰጋጆች ቁጥር በበዛ ቁጥር የልቅናባለቤት የሆነው ጌታችን አላህ ይደሰታል ::
( አቡ ዳውድ ፣ ነሳኢ )
👉በቅዱስ ቁርኣን ፡ - ጌታችን ፈጣሪያችን እንዲህ ብሏል :-
" አላህን ከማውሳትና ሶላት ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው
ልቦችና አይኖች በእርሱ የሚገለባበጡበትን ቀን
የሚፈሩ የሆኑ ሰዎች ( ያጠሩታል ) ::
( አል - ኑር : 37 )
ኢማም አሽ-ሻፊዒ ረሂመሁሏህ " ስለ ዐደብ ስትሰማ ያለህ ጉጉት እንዴት ነው?” ተብለው ሲጠየቁ...
“አንዲት እናት ብቸኛ ልጇ ጠፍቶባት የምትፈልገውን ያህል ጉጉት አለኝ” ብለዋል።
ዐደብ አላህ ይስጠን!🤲🥀🤍
🧕🏻 ለሙስሊም እህቶቼ 🌸
ውዷ የኢስላም እህቴ!
ውበትሽ በውጫዊ ገጽታሽ ብቻ አይደለም፤ በመልካም ሥነ ምግባርሽ፣ በሐያእሽ፣ በኢማንሽ እና በአላህ ዘንድ ያለሽ ትጋት ውስጥም ነው። 🤍
አላህ ከሚወዳቸው ባሮቹ ያድርገን።
آمين 🤲
