en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 387
Subscribers
-324 hours
+2587 days
+1 43630 days
Posts Archive
የአማራ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር 3ተኛ መብረቅ ሻለቃ ኃይልን ለማፈን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር ሰራዊት በምዕራብ ወሎ ግንባር ጃማ ወረዳ ቀይ አፈር ታዳጊ ከተማ ውስጥ ሌሊቱን ከበባ የፈፀመ ቢሆንም እነ ሞት አይፈሬ ጥይት አዝንበውበት ከባድ ሰብአዊ ኪሳራ በጠላት ላይ አድርሰው በጀግንነት በመውጣት ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: የ3ኛ መብረቅ ሻለቃ የተወሰነ ኃይል ከተማይቱ ውስጥ መኖሩን በመረጃ ሰዎቹ አማካኝነት ያረጋገጠው ጠላት ስፍር ቁጥር የሌለው መከላከያ ሰራዊት፣ አድማ ብተና፣ ፓሊስ እና ሰላም አስከባሪዎችን አሰልፎ በሌሊት ከበባ ቢፈፅምም እነ ሞት አይፈሬ በተወሰነ ኃይል ብቻ በርካታ ጠላት በመምታት ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈጽመዋል:: የጃማ ወረዳ መቀመጫ ከሆነችው ደጎሎ ከተማ 2 አምቡላንሶች ወደ ቀይ አፈር ተጉዘው የጠላትን አስከሬን እና ቁስለኛውን ጭነው መመለሳቸውም ታውቋል:: አሁን አመሻሽ ላይ ጭምር አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል አስከሬን ስንዴ ማሳ ውስጥ መገኘቱን ምንጮች ጠቁመዋል:: በዛሬው ውጊያ በድምሩ ከ10 ያላነሰ የጠላት ኃይል መመታቱ ተረጋግጧል:: የ3ተኛ ሻለቃ ብሬን ተኳሹ አርበኛ ሙሀመድ ጀማል በጀግንነት ተፋልሞ ሙሉ ኃይሉን ይዞ መውጣት የቻለ ሲሆን በዚሁ ውጊያ አርበኛ ሼህ አሊ ሀሰን ገነቴ የተባለ ጀግናም እጅ ስጥ ያሉትን የጠላት ኃይል አባላት እረፍርፎ ጥሶ መውጣት ችላል:: "እኔ የአሳምነው ልጅ ነኝ እጅ አልሰጥም" በማለት በጣጥሷቸው የወጣው አርበኛ ሼህ አሊ ሀሰን ከዚህ ቀደም የአማራ ልዩ ኃይል መክት ክፍለ ጦር አባል የነበረና በፋኖ ትግል ሂደትም በሸዋ እና በወሎ ቤተ አምሓራ ግንባሮች የጦር ሜዳ ጀብዱ ሲፈፅም የከረመ መሆኑን ነው ለማረጋገጥ የቻልነው:: የጠላት ኃይል የ3ተኛ መብረቅ ሻለቃ ብሬን ተካሽ የሆነውን አርበኛ ሙሀመድ ጀማልንም ለማፈን ጥረት ያደረገና እጅ ስጥ ያለ ቢሆንም አርበኛውም  "አላስለመድንም" በማለት ብሬኑን አንስቶ ግራ ቀኝ እሳት በማዝነብ ከበባ ሊሰብር ችሏል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የመቄት ወረዳ ጊዜያዊ ሕዝብ አስተዳደር ሕዝባዊ ውይይት መድረኮችን በተለያዩ ቀበሌዎች አጠናክሮ ቀጥሏል። በሰሜን ወሎ የመቄት ወረዳ ጊዜያዊ ሕዝብ አስተዳደር ዋና አስተዳደሪ መምህር በሪሁን ደምሌ በተገኘበት ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ የወይይት መድረክ የተደረገ ሲሆን ሕዝቡም በመቄትና አካባቢው ካሉ የፋኖ ኃይሎች ጋር የተጀመረው ትስስር እና አንድነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ምክር-ሃሳቦችን የተሰጠ ሲሆን ፋኖ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የትምህርት ፣የጤና ፣ የግብርና እና ሌሎች አገልግሎቶች በአግባቡ እንዲፈፀሙ ፋኖ እያደረገ ያለውን አዎንታዊ ድጋፍ አድንቀው በህዝብ ሀብት የተገዛውን የ 9 ጤና ጣቢያዎች መድሃኒት በአብይ የፀጥታ አካላት ፍላቂት ላይ መታገቱ  የአብይ ስርዓት ለህዝብ ያለውን ጥላቻ  አጉልቶ ያሳየ ነው ብለዋል። የወረዳው ጊዜያዊ ሕዝብ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚዎች በተለያዩ ቦታዎች በመገኘት መድረኩን የመሩ ሲሆን የወረዳው ዋና አስተዳደሪ መምህር በሪሁን ደምሌ ትግሉ ስለደረሰበት ደረጃ ፣ ለምን የአማራ ሕዝብ እየታገለ እንዳለ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ሃሳቦችን ለውይይት ታዳሚዎች ገለፃ አድርጓል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 14/2018 ዓ.ም

ቀን 14.03.2018ዓ/ም እራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በአግባቡ ተወቃ!!! አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ክ/ጦር በኢንጅነር ልጆች ሲወቃ አረፈደ። ባለፈው በ12.03.2018 ዓ.ም በደምበጫ ወረዳ ዋድ እና አካባቢውን ለመውረር በሶስት አቅጢጫ ቢንቀሳቀስም በደምበጫ ፋኖዎች መመከት መቻሉን መዘገባችን ይታወቃል። የፋኖን በትር መቋቋም ያልቻለ ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሰየመ የእናት ጡት ነካሽ አራዊት ሰራዊት በትላንትናው እለት በቀን 12.03.2018 ዓ.ም ባጣው ሰራዊት ላይ በመተካት እና መጠነ ብዙ የሰው ሀይል እና ዙ23 በመያዝ በጭፍን ፖለቲካ ሰክሮ በአደንዛዠ እፅ ደንዝዞ ከዋድ ወደ የዘለቃ እንቅስቃሴ እያደረገ ሁለት ሞተሮቹን አቃጥለ። በሞተሮች መቃጠል  የፋኖን እንቅስቃሴ የገታሁ የመሰለው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት አስቴቦጅ  እና አኳትማ በሚባል ቦታ ፈንጠዝያ ላይ እያለ በሻለቃ ይርሳው ደምስ እየተመራ የገባው 99ኛ ክ/ጦር የኢንጅነር ክበር ተመስገን ልጆች እሬሳና ቁስለኛ ብቻ አድርገውታል ።''ስጭኝ ያለሁሽ በርበሬ የሰጠሽኝ ቃርያ '' እንዳሉት አባቶች ፋኖ ሌላ ንፁኃን ማንገላታት ሌላ ። ድል ለፋኖ ድል ለአማራ ሕዝብ ድል ለተገፉ ኢትዮጵያውያን!!!   አፋብኃ 109ኛ ኮር 99ከ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ።

ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል:: ፀረ-አማራው የአብይ አህመዱ አገዛዝ ዛሬ ህዳር 14/2018 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ አብዩ ጎርባ የተባለች ታዳጊ ከተማ ላይ ባይራክታር ቲቢ2 (Bayraktar TB2) በተባለ ቱርክ ሰራሽ ድሮን ጥቃት የፈፀመ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ነው:: የድሮን ጥቃቱ ከቀኑ 8:10 አካባቢ የተፈፀመ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመበት ግለሰብ ሁኔታውን ሲገልፅ፦ ወትሮ እኔም ሆነ ባለቤቴ ቤታችንን አለቅም ነበር ዛሬ ማለዳ ግን አላህ በምክንያት ትረፍ ሲለኝ ባለቤቴ አባታቸው ስለታመሙ ጠይቀሻቸው ነይ አልኳትና ሄደች:: እኔም ለአጨዳ የደረሰ ጤፍ ስላለኝ እሱን ለማየት ወደ እርሻየ ሄድኩኝ ይላል በሁኔታው እየተገረመ:: በጥቃቱ ቤትና ንብረቱ ወድሟል:: ስለሆነም ድሮን በጣም የረቀቀ ቴክኖዎሎጂና ማጥቃት ያለበትን ለይቶ የሚያውቅ ቢሆንም የብልፅግናው አገዛዝ ግን በዚህ መልኩ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት በመፈፀም የታጠቀውን ፋኖን ሳይሆን የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ እየጨፈጨፈ ይገኛል::   መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 14/2018 ዓ.ም

በቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት በተሻሻለው የዘርፉ መምሪያ መሰረት የትግሉን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ወታደራዊና እና ፖለቲካዊ ዜናዎች መረጃዎች እና ልዩልዩ ክንዋኔዎችን በተሻለ ፍጥነት ለ
በቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት በተሻሻለው የዘርፉ መምሪያ መሰረት የትግሉን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ወታደራዊና እና ፖለቲካዊ ዜናዎች መረጃዎች እና ልዩልዩ ክንዋኔዎችን በተሻለ ፍጥነት ለህዝባችን፣ለደጋፊውና ለመላው ሰራዊታችን ለማድረስ ወጥ እና ታማኝነት ያለው የሚዲያ አጠቃቀም ለመተግበር ኮሩ የድርጅቱን መመሪያ መሰረት ያደረገ ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። በተሻሻለው የህዝብ ግንኙነት መመሪያ መሰረት በ206ኛ ኮር ካሉ ክፍለ ጦሮች መካከል በሚገኘው 14ኛ ክ/ጦር የሚተላለፉ መልዕክቶችን ዜናዎችንና እና መረጃዎችን በተሻለ ፍጥነት የሚያደርሰውን የክ/ጦሩን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዘመን ባሳዝነው ይፋዊ facebook ገጽ በመወዳጀት የሚዲያ አገልግሎቱን ለማሳለጥ አጋር ሁኑ።

#በጣም አሳዛኚ እና ልብ ሰባሪ መረጃ መተከል ቡለን ወረዳ ላይ 50 የሚደርሱ ንፁኋኖች ተገደሉ! በቡለን ወረዳ ልዩ ስሙ በኩጂ በተባለ አከባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በፈፀሙት የጅምላ ግድያ 50 የሚደ
#በጣም አሳዛኚ እና ልብ ሰባሪ መረጃ መተከል ቡለን ወረዳ ላይ 50 የሚደርሱ ንፁኋኖች ተገደሉ! በቡለን ወረዳ ልዩ ስሙ በኩጂ በተባለ አከባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በፈፀሙት የጅምላ ግድያ 50 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች መገደላቸው ተሰምቷል። በአከባቢው የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ከሁለት ቀናት በፊት አከባቢውን ለቀው ከመውጣታቸው ነው ጥቃቱ የተፈፀመው የሚሉት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ ታጣቂዎቹ ከአገዛዙ ሰዎች ጋር በመናበብ የፈፀሙት የጅምላ እልቂት ነው ብለዋል። የጅምላ እልቂት ጥቃቱ የተከፈተው ትናንት ህዳር 13/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ ሲሆን፡ በዚህም እስካሁን ባለው 50 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል፡ ቀሪው የሕብረተሰብ ክፍልም ሕይወቱን ለማትረፍ ሽሽት ላይ ነው ተብሏል። በዚህ አከባቢ ከዓመታት በፊት የጅምላ ግድያ ተፈጽሞ የሰው ልጅ በግሬደር ታፍሶ የተቀበረበት ልብ ሰባሪ ክስተት አይዘነጋም። #ፋኖ መንበረ መንግስቱን ተቆጣጥሮ ነፃ እስክትወጣ ድረስ ከክልሉ ውጭ የምትኖር አማራ ተደራጂተህ እራስህን እንድታድን ጥሪ እናቀርባለን።

አሳምነው እዝ ከሰም ኮር2 ነበልባል ክፈለጦ የክፍለጦሩ ተወርዋሪ ሻለቃ

ጎንደሮ ገና ከእናቱ ሆድ ሲወጣ በጀግንነት እየፎከረ ነው። የአፄ ቴዎድሮስ ልጆች የአዛዙን ሰራዊት በእጃቸው ገጥመው ማርከው እየወቀጡት ነው። ጎንደሬ ሆ ብሎ ሲነሳ ኢትዮጵያ ትድናለች ! በአራቱም ማዕ
ጎንደሮ ገና ከእናቱ ሆድ ሲወጣ በጀግንነት እየፎከረ ነው። የአፄ ቴዎድሮስ ልጆች የአዛዙን ሰራዊት በእጃቸው ገጥመው ማርከው እየወቀጡት ነው። ጎንደሬ ሆ ብሎ ሲነሳ ኢትዮጵያ ትድናለች ! በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር፡ ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር የተላለፈ ጥሪ !                                ህዳር 14/2018 ዓ.ም    አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር፡ ኃይለማርም ማሞ ክ/ጦር ላለፉት ሁለት አመታት እየተደረገ ባለው የህልውና ትግል ከአገዛዙ ጥምር ጦር ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲደረግ ቆይቷል ፥ አሁንም እያደረገ ይገኛል ። ክፍለጦሩ በቀድሞው ከሰም ክ/ጦር ስር በብርጌድ አደረጃጀት በነበረበት ወቅት ከሌሎች የከሰም ክፍለጦር የብርጌድ አደረጃጀቶች ጋር በመሆን በሸዋ ቀጠና በከሰም ሀገረማርያም ወረዳ፣ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ፣ በበረኸት ወረዳ እና በአሳግርት ወረዳ የጥምር አውደ-ውጊያ በማድረግ አገዛዙ አለኝ የሚለውን የአጋዚ ኮማንዶ፣ አየር-ወለደ እና ሪፐፕሊካን ጋርድ እንዲሁም ለጥምር ሰራዊቱ የእግር እሳት ሆኖበት ቆይቷል ። የቀድሞው የኃለማርያም ማሞ ብርጌድ በሸዋ አራት ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በህልውና ትግሉ የራሱን ከፍ-ያለ አስተዋፅኦ አበርክቷል ። ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ከአዲስ አበባ አፍንጫ ስር እንደ መገኘቱ ጠላት ያለ የሌለውን ሀይል አሰማርቶ ውጊያ ቢከፍትም ክንደ-ብርቶዎቹ የኃለማርያም ማሞ ልጆች የአባቶቻቸውን የአይበገሬነት መንፈስ ተላብሰው እየተፋለሙት ይገኛል ። በመሆኑም የቀድሞው የኃለማርያም ማሞ ብርጌድ ስር የነበራችሁ የሰራዊት አባላት ማለትም፤ በጤና እክል፣ ቤተሰብ ለመጠየቅ፣ በውስጥ ችግር ምክንያት የወጣችሁ እና እስካሁን ያልተመለሳችሁ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ወደ ቀድሞው ታሪካዊ የትግል ህይወት እንድትመለሱ እና የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት በጅምላ የማጥፋት አደጋ ነፃ ለማውጣት በሚደረገው ተጋድሎ ከዚህ በፊት የነበራችሁን የትግል ወኔ ሰንቃችሁ ኃለማርያም ማሞ ክ/ጦርን እንድትቀላቀሉ ሲል ክፍለጦሩ በአማራ ህዝብ ስም ጥሪ አቅርቧል ። አሁን ላይ ክፍለጦሩ የከሰም ሀገረማርያም ወረዳ 19 የገጠር ቀበሌዎችን በቆጣጠር የአከባቢው ህዝብ አባቶች የትናንት የስነ-ህዝብ ሥልጡን የአስተዳደር ጥበብን በመጠቀም እያስተዳደረ ይገኛል ። ውድ የተከበራችሁ የቀድሞው የኃለማርያም ማሞ ብርጌድ የሰራዊት አባላት እንዲሁም በተለያዩ ችግር ምክንያት፣ በጤና እክል እንዲሁም ቤተሰብ ለመጠየቅ ሄዳችሁ ያልተመለሳችሁ ውድ የሰራዊት አባላት አሁን ላይ ሰራዊቱ በድርጅቱ መመሪያ መሠረት የሚመራ በመሆኑ የአሠራር ችግር እና ክፍተት ካለም በመመሪያው መሠረት የሚጠየቅበት ህግና መመሪያ ስለወጣ አሰራራችን ከወትሮው በተለየ እና በተሻለ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ጥሩና አኩሪ ስራዎችን እየተቀዳጀ ይገኛል ። በመሆኑም በተለያዩ ችግር ምክንያት የወጣችሁ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ያ! የአሰራር ክፍተት ሙሉ በሙሉ የተቀረፈ እና አሰራሩም በአፋብኃ ድርጅት መመሪያ እና ደምብ መሠረት የሚተገበር በመሆኑ ወደ ቀድሞው ቤታችሁ ተመልሳችሁ የራሳችሁን ታሪካዊ አበርክቶ እንድታደርጉ የኃለማርያም ማሞ ክ/ጦር በድጋሜ በተከበረው በአማራ ህዝብ ስም ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል ።   -  የአፋብኃ ደ.አ.ቀ.አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር       ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር !!!

ታላቅ አማራዊ ጥሪ‼️ ወታደራዊ ስልጠና ወስዳቹህ በተለያዩ ቦታወች የምትገኙ #በጎንቻ_እናርጅ_እና_እነብሴ_ሳርምድር ወረዳወች ውስጥ የምትገኙ ወጣቶች ታላቅ አማራን የመታደግ ጥሪ ቀርቦላቹሀል ። ስርአ
ታላቅ አማራዊ ጥሪ‼️ ወታደራዊ ስልጠና ወስዳቹህ በተለያዩ ቦታወች የምትገኙ #በጎንቻ_እናርጅ_እና_እነብሴ_ሳርምድር ወረዳወች ውስጥ የምትገኙ ወጣቶች ታላቅ አማራን የመታደግ ጥሪ ቀርቦላቹሀል ። ስርአቱ ንፁሀንን በጅምላ ማሰር እና መረሸኑ የእለት ተእለት ተግባር አድርጎታል። ስለዚህ እራሳችን እንደ አማራ ማደራጀት እና መመከት ስላለብን ከዚህ በፊት #አድማብተና_መከላከያ_ፓሊስ #እና_ልዩሀይል መልስ የነበራቹህ እስከህር 19 /2018.ዓ.ም በወረዳው በመገኘት እንድትመዘገቡ በ201ኛ ኮር የ74ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ጥሪ አቅርበዋል ። ለበለጠመረጃ 09 20 18 82 31....ጎንቻ 09 27 73 43 34 ....እናርጅ 09 00 98 52 02....እነብሴ ህዳር 14/2018 ዓ.ም

ጎንደሮ ገና ከእናቱ ሆድ ሲወጣ በጀግንነት እየፎከረ ነው። የአፄ ቴዎድሮስ ልጆች የአዛዙን ሰራዊት በእጃቸው ገጥመው ማርከው እየወቀጡት ነው። ጎንደሬ ሆ ብሎ ሲነሳ ኢትዮጵያ ትድናለች !
ጎንደሮ ገና ከእናቱ ሆድ ሲወጣ በጀግንነት እየፎከረ ነው። የአፄ ቴዎድሮስ ልጆች የአዛዙን ሰራዊት በእጃቸው ገጥመው ማርከው እየወቀጡት ነው። ጎንደሬ ሆ ብሎ ሲነሳ ኢትዮጵያ ትድናለች !

ቤተክርስተያኑ በእሳት አደጋ ለሊት ሙሉ በሙሉ ወደመ የወይራ ሠፈር ኆኅተ ገነት ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ቀጠሎ ወደመ። በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኮሎፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተ
+2
ቤተክርስተያኑ በእሳት አደጋ ለሊት ሙሉ በሙሉ ወደመ የወይራ ሠፈር ኆኅተ ገነት ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ቀጠሎ ወደመ። በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኮሎፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የወይራ ሠፈር ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማና መንበረ ብርሃን እጨጌ አቡነ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ሌሊት በእሳት አደጋ ምክንያት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የቃጠሎው መነሻ የኤሌክትሪክ መስመር ችግር እንደሆነም የተገለጸ ሲሆን ከታቦቱ በስተቀር ሌሎች ንዋየተ ቅድሳት ሙሉ በሙሉ በአደጋው ምክንያት መውደማቸው ነው የተገለጸው ሲል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ዘግበዋል።

👌ሙተን እንጅ ዋሽተን የምናስቀጥለው ሃገር አይኖርም !!! 👉 ለአይን ከቅንድብ የቀረበ አካል የለውም አይን ግን ቅንድብን አይቶት አያውቅም እኛም ብዙ ያላየናቸው እውነቶች አሉ ውሸቶችም አሉ አሁን ሁለቱን የምንለይበት ምራፍ ላይ እንገኛለን :: እስካሁን ያላየናቸው እውነቶችን ልተውና ውሸቶችን ሳይ በትግላችን ውስጥ ከመሆን ይልቅ መምሰል የሚፈልጉ ሃይሎችን አይቻለው ፣ ከአንድነት ይልቅ ልዩነት የሚፈልጉ ሃይሎችን አይቻለው ፣ ከውስጣችን በሬ ወለደ ብለው የሚያወሩ ሰወችን አይቻለው ፣ እኛን ትተው እኔን የሚል የስግብግብነት አባዜ ያለባቸው ሰወችን አይቻለው ፣ አማራ ሆኖ አማራን የከዳና ያስከዳ ባንዳ አይቻለው ፣ በሰወች ሞት ድልን ናፋቂ ሰወች እንዳሉ አይቻለው ፣ የወጣ ለማን እንደሆነ ሳያውቅ ውደሳና ሙገሳ ፈላጊውን እሱ ይቁጠረው ። እውነትን በውሸት ደብቆ ህዝብን የዘረፉ ያገቱ ሰወችን አይቻለው ፣ ውሸታሞች እውነተኞችን በሴራ ሲጠመዝዟቸው አይቻለው ፣ ስለ እውነት ታግለው ስለ እውነት የተሰውትን ያልሆነ ስም ሲሰጧቸው አይቻለው ። በአንድ እራስ ሁለት ምላስ አይነት ሁለት አዠንዳ ይዘው የሚጓዙ ቢሞቅ በማኪያ ቢቀዘቅዝ በጣቴ👈 ፣ ፋኖ ስትላቸው ብልፅግና ብልፅግና ስትላቸው ፋኖ ከሁለት ሁነው የሚዋልሉ ሰወችን ታዝቢያለው ። ገንዘብ አምላኪወችን ሚስጥር አባካኞችን አይቸ ታዝቢያለው ። የአማራን የህልውና ትግል ለግል አላማው ተጠቅሞ ጠላቱን ሲጎዳበት ፣ ወገኑን ሲጠቅምበት አይቻለው ለዚህ ነው ባለፋው ባጋረዋቹ ፁፌ ከተናገርነው ይልቅ ታዝበን ዝም ያልነው ይበልጣል ያልኩኝ ። እንደ አጋጣሚ ሁኖ ይህን ሁሉ ነገር ባይም ውጤታቸውን እያየን ነው ልጅ ቢሮጥ እስከ ዳቦ ቤቱ እና የውሸታሞችም እድሜ እያጠረ ነው ። በውሸታሞችም ውስጥ ሁነው እውነትን የያዙ ለአማራ በክብር ለተሰው ስማቸውን በወርቅ ቀለም ፅፈው አልፈዋል ። እውነተኞች ወንድሞቻችን ያስቀጥሉታል ይህን ትግል ፣ አሁን ለደረሰበት ቁመና ያደረሱት ዉሸታሞች ሳይሆኑ እውነተኞች ናቸው ። አይተኬ ህይወታቸውን የገበሩ የአማራ አይተኬ ልጆች ናቸው ። አይን ቅንድብን አይቶ አያውቅም እንበል እንጅ እኛ ግን ከብዶን የቆየ ማየት ሳይሆን መለየት ነበር ። አሁን ግን የተጀመረው እንደጎንደር የአንድነት ጉዞ ይህን ሁሉ ችግር አይቶ እና ለይቶ ይፈተዋል ብየ አምናለው ። አ/ፋ/ብ/ኀ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ዉባንተ አባተ ኮር ( ፩ኛ ኮር) ፋኖ አመኑ አለምአንተ ©Amenu Alemante

33ኛ ክ/ጦር ዳግም ወደ ታሪካዊ አንድነታቸው  የመለሳቸው የገረመው ወንዳውክ እና የዮሐንስ ዓለማየሁ ልጆች ጠላትን በማንበርከክ አሳፍረው መለሱ ════════════❁✿❁════════════ (ኅዳር 13/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) የዐፋብኀ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር ዳግም ወደ ታሪካዊ አንድነታቸው  የመለሳቸው የቋሪቱ ገረመው ወንዳውክ እና የጎንጂው ዮሐንስ ዓለማየሁ ልጆች ጠላትን በማፈራረስ አሳፍረው መልሰውታል። አሥራ አንድ አባላቱን ያስቀነሰው አገዛዙ፤  አመሻሹን ከወይበይኝ ጤና ጣቢያ ሁለት ካሶኒ ቁስለኛ አዝሎ ወደ ገበዘማርያም እየተመለሰ ነው። በተመሳሳይ ዜና ጡት ቆራጩ አረመኔ ሠራዊት በገነት አቦ አቅራቢያ ሮቢት በሚባል ቦታ ለአፈና በሄደበት በማይነጣጠሉት አረንዛው ዳሞት እና ገረመው ወንዳውክ ወንድማማች ልጆች በከበባ ሲወቀጥ ውሏል። የ33ኛ ክፍለ ጦር አንድ አባል በገነት አቦ አቅራቢያ ትንኮሳ አድርጎ ከተመለሰው አረመኔ ሠራዊት ምሽግ ሠርጎ በመግባት በዱላ ማጅራቱን በመምታት መሣሪያዉን ማርኮ ወጥቷል። የዚህን ዜና ዝርዝር መረጃ በቅርቡ ይዘን እንመለሳለን።