en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 363
Subscribers
+5424 hours
+2347 days
+1 43730 days
Posts Archive
የ14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጠላት ላይ ታላቅ ድልን ተጎናጸፈ! ታኅሳስ 02/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ
+2
የ14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጠላት ላይ ታላቅ ድልን ተጎናጸፈ! ታኅሳስ 02/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ የሠራዊት አባላት በዘራፊው የብልጽግና ሠራዊት ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል። የአርሶ አደሩን ሰብል ለመዝረፍና የማሕበረሰቡን ቤት ለመበርበር በጠዋቱ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስቶ ወደ ሊባኖስ ቀበሌ ያመራውን የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት ጀግኖቹ የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ፋኖዎች አስቀድመው ደፈጣ ጥለው በመጠበቅ ከጠዋት ጀምረው እስከ ምሽት ድረስ የቋያ እሳት ክንዳቸውን ሲያሳርፉበት ውለዋል። ሻለቃዋን በትኛታለሁ እያለ ተረቱን ሲነዛ የነበረው የብልጽግና ሠራዊት ከተጠና የከተማ ኦፐሬሽን እስከ መደበኛ የውጊያ ጥበብን የተካኑት ጀግኖቹ ጠላትን በልሳነ አፈሙዝ ሲያናዝዙት ውለው አምሽተዋል። ከደንባ እስከ ሊባኖስ ባካለለው ቀጠና በተደረገው ውጊያ ከፍተኛ መናበብና አስደናቂ የውጊያ ጥበብ የታየበት ከመሆኑም በላይ ምሽጎች ከመሰበራቸውም በላይ በርካታ ቁጥር ያለው ጡት ቆራጩ የምርኮኛው ጁላ ሠራዊትና ሆዳም አድማ ብተና እንደ ቅጠል ረግፎ ቀርቷል። በውጊያም ➠ ሶስት ምሽግ ተሰብሯል ➠ አንድ የአድማ ብተና የሻለቃ አመራር ተደምስሷል ➠ ከ37በላይ የጠላት ኃይል ተደምስሷል በአሁኑ ሰዓትም ጠላት መድፍ እያስወነጨፈ ይገኛል። ድል ለአማራ ፋኖ! የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት

ዋርካው በስራ ላይ

#አገዛዙ_በቢቸና_ከተማ_የሐሰት_ወሪ_የሚነዙ__የfacebook_አርበኛ_ሰራዊት_ማዘጋጀቱን_አረጋግጠናል።               ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ የሚገኘው ሆድ አደር የብአዴን አመራር በ64ኛ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ጠንካራ አመራሮች እና የፋኖ አባላትን ለማህበረሰባችንን እና ለትግሉ ደጋፊ የተሰሳተ የሐሰት መረጃ ለማድርስ እና ለመመረዝ በቢቸና ከተማ በአገዛዙ የብአዴን አመራሮች የወር ደሞዝ የተመቻቸላቸው ግለሰቦችን ማዘጋጀቱን አረጋግጠናል። በቢቸና ከተማ ከአማራነታቹህ ይልቅ ሆዳቹህ የበለጠባቸው ግለሰቦች የውሸት #የfacebook አካውንት በመክፈት የሐሰት መረጃ ልታደርሱ የተዘጋጃቹህ ግለሰቦች ሙሉ ስም ዝርዝር እና ልትሰሩት የተሰጣቹህ ትዛዝ ዝርዝር በእጃችን የገባ ስለሆነ በተራ ገንዘብ የታለላቹህ ግለሰቦች ከእንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ እንድታቆሙ ስንል በጥብቅ እናሳስባል። በመሆኑም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ትዛዝ ተላልፋቹህ የሐሰት መረጃ የምታሰራጩ ከሆነ የግለሰቦችን ስም ዝርዝር ይፋ በማውጣት በግለሰቦቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑንን በጥብቅ እናስጠነቅቃለን። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!          ታሳስ 02/2018 ዓ.ም

፻ አለቃውን ጨምሮ 37 የጠላት ሰራዊት በጅበላ ሙተራ ሻለቃ ተደመሰሱ። ታህሳስ 2 /2018 ዓ.ም ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስቶ ወደ ሊባኖስ ደምባ የተንቀሳሰው ጠላት በ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በተደረገ ታላቅ ትንቅንቅ የአረመኔውን ሰራዊት ድባቅ ተመቷል። ከአነጋጉ 12:00 ጀምሮ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ የጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጥልቀት በፈፀመችው የማጥቃት ውጊያ የጠላትን ተደራራቢ 3 ምሽጎች በመስበር ጠላትን 7 ሰዓታት በመፋለም በየ ምሽጉ  አጋድማዋለች። ከደንባ ደብረ ማርቆስ ከተማ ማረሚያ ቤት ድረስ እያጣደፉ ጠላትን ያራገበችው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ 37 የጠላት ሰራዊት ጨምሮ ከዘራ ይዞ ሲያዋጋ የነበረውን ፻ አለቃ በስናይፐር ጭንቅላቱን በስተው ጥለውታል። እንደ ንስር ታድሳ በቁጭት ጠላትን የተናነቀችው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ያለምንም መስዋትነት በጠላት ላይ ድል የተቀናጀች ሲሆን እስከ ምሽት 1:00 ስዓት በወሰደው አውደ ውጊያ አስክሬን ማንሳት ያልቻለው የአረመኔው ስርዓት ከደብረ ማርቆስ ከተማ መድፍ እየተኮሰ ይገኛል ። በመልሶ ማደራጀት ትግበራው በ206ኛ ኮር እጁ የተቆረጠበት ጠላት ጅበላ ሙተራ ሻለቃን ሶስት ጊዜ ለማጥቃት የሞከረ ሲሆን በዛሬው ትንቅንቅ ጥቃቱን መቋቋም አቅቶት 4 ኪ.ሜ ወደ ኋላ ሲፈረጥጥ በርካታ አስክሬኖችን ማንሳት አልቻለም ። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አገዛዝ ብልፅግና የጥፋት ቡድን ሰሜን ሸዋ ዞን በግሸ ወረዳ ትምህርት ቤት ላይ የድሮን ጥቃት በመፈፀም የ1ኛ ደረጃ ህፃናት ተማሪዎችን ገደለ:: የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን
+2
የፋሽስቱ አብይ አህመድ አገዛዝ ብልፅግና የጥፋት ቡድን ሰሜን ሸዋ ዞን በግሸ ወረዳ ትምህርት ቤት ላይ የድሮን ጥቃት በመፈፀም የ1ኛ ደረጃ ህፃናት ተማሪዎችን ገደለ:: የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን በሰሜን ሸዋ ግሸ ወረዳ ልዩ ቦታው ደል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፈጸመው የድሮን ጥቃት በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ ሁለት ተማሪዎች ሲሰው በርካቶች ቁስለኛ ሆነዋል:: የፋኖን ሐይል በአውደ ውጊያ ማሸነፍ ያልቻለው የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን በደል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም ከጧቱ 5:00 የፈጸመው የድሮን ጥቃት ለህጻናት እንኳን የማይራራ መሆኑን በተግባር አሳይቷል:: በዚህ የድሮን ጥቃት አንድ የመማሪያ ክፍል ሙሉ በሙሉ ሲወድም ከ10 በላይ ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለው ወደ ህክምና ተወስደዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም

ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ቀናቶችን ባስቆጠረ ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ በደሴ ዙሪያ ወረዳ እያደረጉት ያለው ከባድ ተጋድሎ ዛሬ ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ጠላት ከፍተኛ የሚባል ሰብዓዊ ኪሳራ እያስተናገደ ተጋድሎው በድል ታጅቦ አሁንም እደቀጠለ ነው:: ህዳር 29/2018 ዓ.ም በደሴ ዙሪያ ወረዳ ሞቴ ከተማና አስግዶ ላይ ከባድ ጉዳትና ኪሳራ የደረሰበት ሚሊሻና የደሴ ፖሊስ በዲጋሜ ህዳር 30/2018 ዓ.ም የመከላከያ ሰራዊት ሚኒሻና ፖሊስ ጥምር ዙፋን ጠባቂ ጦር በ4 አቅጣጫ ከደሴ ከተማ በአስግዶና ሞቴ -በጉጉፍቱ አጥት መስበሪያ - በቆላ ገራዶ - በጓሳ ሜዳ ከኩታበር -በተንታ አጅባር በአራቱም አቅጣጫ ፋኖን ይዞታውንና ቀጠናውን አስለቅቃለሁ ብሎ የገባው ጠላት ባሰበው ልክ ሳይሆን በተቃራኒው በየጫካውና በየጉድጓዱ አስከሬኑ ወድቆ ቀርቷል:: በዚህም ጠላት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን በየቦታው ወድቆ የቀረበትን አስከሬን ለማሳትና ለማውጣት ሌላ ተጨማሪ ሃይል እያስገባ እዛው እደገባ ሳይመለስ ይሄው ዛሬ ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል:: ተጋድሎው አሁንም ተጠናክሮ እደቀጠለ ነው!  ዝርዝር ቁጥራዊ መረጃውን በቀጣይ የምናደርስ ይሆናል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም

#በኢትዮጵያዊው የታሪክ ሙህር #ፕሮፌሰር #ገብሩ #ታረቀ የተፃፈውን #The #Ethiopian #Revolution #War in the #Horn of #Africa በሚል ርዕስ ባሳተመው መፅሐፉ ውስጥ #Red #Star #Operation/ቀይ-ኮከብ ዘመቻን አስቀምጦታል። እንደምናስታውሰው ቀይ ኮከብ ዘመቻ #የደርግ #መንግስት በ #total #strategy በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ነፃ አውጭዎችን ለማጥፋት ያለመ ነበር። ሙህሩ በግልፅ በጥናቱ እንደሚያስቀምጡት በወቅቱ ለዘመቻ የተንቀሳቀሰው የደርግ ሰራዊት ከምድር ኃይል እስከ አየር ኃይል የተቀናጀ እንደሆነና የተሻለ ትጥቅ እንደነበረው ነው። የሆነው ግን የተገላቢጦሽ ነው። ወደ ቀጠናው ከገባ በኋላ #በየአውደ ውጊያው እጅ ይሰጣል። የመዋጋት አቅሙና የስልጠና ብቃቱ በአንፃራዊነት ደካማ እንደነበር ነው። በበላይ አመራሩ እና በታችኛው ሰራዊት ከፍተኛ ልዩነት ነበር። የበላይ አመራሩ ለነፃ አውጭዎች መረጃ አሳልፎ ይሰጥ ነበር። እንዲመራና እንዲያዋጋ የተሰጠውን ለመምራት #incompetent ነበር። በተጨማሪም ስርዓቱ በንፁሐን ላይ ሲያደርሰው የነበረው ማስፈራራት፣ ማስደንገጥና ጭፍጨፋ በተዋጊው ሰራዊት ላይ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ጫና ከማስከተሉም በላይ ሞራሉ #እንዲላሽቅ አድርጎታል። በአጠቃላይ #ወታደራዊ #ስርዓቱ ሲያደርጋቸው በነበሩ #catastrophic ድርጊቶች ሁሉ ተዳምረው ከህዝብ ልብ ውልቅ ብሎ እንዲወጣ አድርገውታል። በአጭሩም ቢሆን ወደ #አብይ #አህመድ ሰራዊት እንመለስ እስኪ! ባሳለፍናቸው ጊዜያት በርካታ እስከ 30 የሚሉ #ኦፕሬሽኖችን አቅዶ ተንቀሳቅሷል። ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ለአማራ ፋኖ የበለጠ ቀጠና ለቋል። በተደረጉ አውደ ውጊያዎች በሁሉም በሚባል ደረጃ የታጠቀውን መሳሪያ ተማርኳል። በየጊዜው ከአመራር እስከ ታችኛው ሰራዊት እጅ ይሰጣል። የስልጠና ብቃት የላቸውም። አንዳንዶቹ ወደ ማሰልጠኛ ያልገቡ #ተጋፍፈው የመጡ ናቸው። በየቀኑ ወደ አማራ ፋኖ ሰራዊት እየፈረሰ የሚመጣውም በርካታ ነው። የአገዛዙ ሰራዊት በየትኛውም ቀጠና ሲገባ ንፁሐንን ይረሽናል፤ ንብረትም ይዘርፋል። በሰራዊቱ መካከልም ከፍተኛ የሆነ #የብሔር ልዩነት አለ። የአማራ ተወላጅ የሆኑ ከፊት ሆነው ውጊያ እንዲገቡ ይደረጋል። አንዳንድ የሰራዊት አባላትም #በንፁሐን ላይ የሚደረገውን ዘረፋና ጭፍጨፋ ይቃወማሉ፤ ነገር ግን ይረሸናሉ። ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት በኮር፣ በክፍለ ጦርና በሬጅመንት ደረጃ የታቀፉ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት #demobilized ሆነዋል። ከነብስ-ወከብ እስከ #ዲሽቃና #ሞርተር ድረስ እየተማረኩ ፈርሰዋል። ለምሳሌም ያህል በጎንደር አካባቢ #503ኛ፣504ኛ ኮሮች የአማራ ፋኖ ዱላ እጣ ደርሷቸዋል። በቅርቡ በወሎ በምስራቅ አማራ ፋኖ ወይም በምንሊክ ዕዝ በአባ ናደው operation የተገኘው ድልም የበለጠ አስረጅነቱ የጎላ ነው። In the 17-day 'Aba Nadew' operation, our battle-tested armed forces neutralized more than three thousand enemy combatants and captured close to seven hundred combatants. ከላይ የተቀመጠው የእንግሊዘኛ ፁሁፍ ምንሊክ ዕዝ Google ላይ ካስቀመጠው በቀጥታ የተወሰደ ነው። የአብይ ሰራዊት በህዝቡ ላይ በሚወስደው አስከፊ እርምጃም ከህዝብ ልብ ሙሉ በሙሉ እንደወጣ ከላይ የቀረቡት ማሳያዎች በቂ ናቸው። ፁሑፌን ሳጠቃልል ይህ ሰራዊት እንደ ተቋምም መቀጠል የማይችልበት ደረጃ certain ሆኗል። ወደ ፊት ብቻ! Anteneh Dires

@<<< ከባህሩ የሚሰማው ጩኸት የእንቁራሪቶች ነው ማለት ባህሩ የእንቁራሪቶች ብቻ ነው ማለት አይደለም። በባህሩ ውስጥ ዝም ያሉ ብዙ አሳዎች ይኖራሉ>>> የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የምስራቅ አማራ ኮር አንድ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ጌታሁን ሲሳይ ይባላል። ይህ ጀግና ለየት ያለ ባህሪ አለው ያሰበውን ወታደራዊ እቅድ ሳያሳካ አይመለስም። ባለፈው ወራቶች ቃሊም ላይ ሙሉ በሙሉ አንድ ሻለቃ መከላከያን ከነሙሉ ትጥቁ የማረከ |አባ ስበር | የሚል ቅጥል ስም የተሰጠው ጀግና ልጅ ነው። አርበኛ ጌታሁን ሲሳይ በአንድ ወቅት ለወታደራዊ ግዳጅ ወደ ሌላ ቀጠና ይጓዛል። በጉዞው ላይ እያለ በቀጠናው ያሉ የሌላ አደረጃጀቶች ጋር ይገናኛል። በወቅቱ << አባ ስበርን >> አላወቁትም ነበር። እንዲህም ሲሉ ጠየቁት ማነህ? ሲሉት በአንድ ቃል የምስራቁ አላቸው። ጠያቂው ለምን በእዚህ መጣህ? አማራ አይደለም እንዴ አይ ነው ግን ወዴት እየሄድክ ነው ? አባ ስበርም ወደ ወንድሞቼ ነዋ (ቆጣ በማለት) በመጨረሻም ጠያቂው በእዚህ መስመር እንዳትመለስ ይለዋል። የአርበኛው መልስ ግን እንደ አራስ ነብር ተቆጥቶ ችግር የለውም ስመለስ እዚህ ጠብቀኝ ብቻ ነበር ያለው ✊ መንገዱንም ቀጠለ ከሚፈልግበት ቦታ ደርሶ በሄደበት መንገድ ሲመለስ ለጥላት መረጃ በመስጠት ጥላት ለማጥቃት ቦታ ይዞ ጠበቀው ነገር ግን የምስራቁ ኮከብ ተናዳፊዎቹ የብልፅግናን ሰራዊት እንዳልነበር አድርገው ረፈረፉት ከወገን አንድ ብቻ ነበር የቆሰለብን 💪 አባ ስበር እጅግ ሲበዛ የዋህ ነው። ጎጠኝነትን ይፀየፋል ነገር ግን በእዛው ልክ ከተቆጣ ምንም ነገር አያስቆመውም። ከእሱ ፊት ሌላ ክፍለ ጦር ስታማ ወይም ሌላ ቀጠና ያሉ ፋኖዎችን ስትዘልፍ ከሰማህ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስርሃል ሁሉም የእኛ ናቸው ብሎ የሚያምን የወንዶች ልክ ነው። << የዋርካው ወንድም የጠቆርቋሬ ሲስቅ እንደሰው ሲቆጣ እንዳውሬ >>

ብልፅግና የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊቷን ከዳር እስከ ዳር ብታሰማራም መሬት ላይ ያለውን ሀቅ መቀየር አልቻለችም።
ብልፅግና የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊቷን ከዳር እስከ ዳር ብታሰማራም መሬት ላይ ያለውን ሀቅ መቀየር አልቻለችም።

#በአማራ_ህዝብ_እየደረሰ_ያለው_መከራ በአብይ አህመድ ስርዓት  እግሩን ያጣው አባት #እጡቤ_ቢተውልኝ የካቲት 07/2016 ዓ.ም ቢቡኝ_ወረዳ ልዩስሙ ቆሎ መሻጫ ‼️

#የንጹሓን_ፍጅት_በምሥራቅ_ወለጋ ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጊዳ አያና ወረዳ፣ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ልዩ ቦታው አሊ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እጅግ ሰቅጣጭ ግድያ በመንግሥታዊ መዋቅር እየተፈጸመ ነው።" ከ 20 ታታ ተሽከርካሪ በላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተራግፏል፤ ንጹሓንንም ዒላማ ያደረገ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ነው። በቅድሚያ መከላከያው ሕዝብ ጋር በመመካከር፣ እንጠብቃችኋለንም በማለት ሕዝቡ አምኖ መሣሪያውን እንዲያስረክብ ተደርጓል። ያ እንደኾነ ከታወቀ በኋላ ይመስላል በቅንጅት ከማክሰኞ ኅዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በስለት ጭምር ንጹሓን በአሰቃቂ ኹኔታ ያለከልካይ እየተጨፈጨፉ ነው፤ አስከሬናቸውም አልተናሳም" የሚሉት በጭንቅ ውስጥ ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች የነዋሪው በሥጋት በየጫካው በመሰደዱ የሟቾችን ቍጥር በውል ማወቅ ያስቸግራል፡፡ በአካባቢው ሸኔ(የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት) ወይም ፋኖ እንደማይንቀሳቀሱ ዋናው ዒላማ ንጹሓን እንደኾነ ይናገራሉ። ፓርቲያችን ይኽን ዓይነቱ አካሄድ ለከፍተኛ ዘር ፍጅት ዝግጅትና ምልክት አድርጎ ይገነዘበዋል፤ ድርጊቱንም በጽኑ ያወግዛል። አካባቢው ከዚኽ ቀደምም ተደጋጋሚ ዘር ፍጅት ይካሄድበት የነበረ መኾኑ ይታወቃል፡፡ ስለኾነም በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የክልል ልዩ ኃይል እንዲኽ ካለው እኩይ ድርጊት እንዲታቀብና መከላከያ ሠራዊቱ በቦታው ተተክቶ መሣሪያ ሲያስወርድ ቃል በገባው መሠረት ሕዝቡን እንዲጠብቅ፣ ያ ካልኾነም የሕዝቡን መሣሪያ እንዲመልስና ሕዝቡ ቢያንስ ራሱን እንዲከላከል እንዲደረግ እየጠየቅን ይኽ ሳይኾን ቢቀር እና ለሚደርሰው ፍጅትም መንግሥት ሙሉ ኃላፊነቱን  እንደሚወስድ ለማሳሰብ እንወዳለን። ፓርቲያችን ለሞቱት እረፍተ ነፍስን ለወዳጅ ዘመድና ለአካባቢው ማኅበረሰብም መጽናናትን ይመኛል። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ ታኅሣስ ፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

አማራ ሁነህ እንደት ይሄን ትረሳለህ ጓድ የትግላችንን አላማ ጠንቅቀን እናውቃለን
አማራ ሁነህ እንደት ይሄን ትረሳለህ ጓድ የትግላችንን አላማ ጠንቅቀን እናውቃለን

አብይ አህመድ ልመና ይሳካልኛል እያለ እየለመነ እየቀፈለ የሚገዛቸው መኪኖችና መሳሪያዎች በክብር ወደ ቦታቸው (ወደ ፋኖዎች እየገቡነው ። ራስ ተሰማ ሳይንቴ እንዳለው "አዲስ መኪና ታርጋው 00 የሆነ
አብይ አህመድ ልመና ይሳካልኛል እያለ እየለመነ እየቀፈለ የሚገዛቸው መኪኖችና መሳሪያዎች በክብር ወደ ቦታቸው (ወደ ፋኖዎች እየገቡነው ። ራስ ተሰማ ሳይንቴ እንዳለው "አዲስ መኪና ታርጋው 00 የሆነ ገና ለካድሬ ከመድረሱ በክብር ተረክበናል መኪናው ከተገዛ ገና አንድ ወሩ እንደሆነም አረጋግጠናልደ። ተመሳሳይ የሆኑ ሌሎች 2 አዳዲስ መኪኖችም ማምሻውን ይደርሱናል።ለብልጽግና የተለመደ ምስጋናችን ይድረስልን "ብለዋል። የእምዬ ምኒልክ ልጆች !✊

ሙሉ ቲሙ ፋኖን ተቀላቅሏል! አዲስ ቅዳም ከተማ ከሚገኘዉ የጠላት ካምፕ በቲም ደረጃ በመዉጣት የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃን በሰላም ተቀላቅለዋል። በ
+2
ሙሉ ቲሙ ፋኖን ተቀላቅሏል! አዲስ ቅዳም ከተማ ከሚገኘዉ የጠላት ካምፕ በቲም ደረጃ በመዉጣት የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃን በሰላም ተቀላቅለዋል። በ ፲ አለቃ ቻላቸዉ ባንቲገኝ መሪነት ከጠላት ካምፕ ወጥተዉ ሻለቃችንን ከተቀላቀሉት ዉስጥ፦ 1. ፲/አ ቻላቸዉ ባንቲገኝ |ችሎት 2. አንደበት ፀጋየ 3. መላኩ ሽቱ 4. ባዘዘዉ ደጀኔ 5. ደነቀዉ ካሳሁን 6. አንዳርጌ አያና 7. ሞላ ደጉ የሚገኙ ሲሆን አፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ዋና ሰብሳቢ #ፋኖ_አንሙት_ጌታሁንን ጨምሮ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል። ከእነዚህ ወንድሞቻችን ዉስጥ ፲/አ ቻላቸዉ ባንቲገኝ፣ ሞላ ደጉ እና አንደበት ፀጋየ እያንዳንዳቸዉ ሁለት ሁለት ክላሽንኮቭ መሳሪያ በመያዝ በልዩ ጀብድ ሻለቃችንን ተቀላቅለዋል። አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም

ማስረሻ ሰጤ ያለህን ዝና ተጠቅመህ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰራዊትን በማፍረስ የኛን ኃይል እንዲደራጅ አላደረክም-----" ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም በፎቶው የምትመለከቱት ሰው "ከፌ" ይባላል በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ተወላጅ ሲሆን የህዝባዊ ግንባሩ በጎጃም ቀጠና ፋይናስ ክፍል በመሆን ሰራዊቱ እንዲበታተን ከዲያስፖራው እና ከ360 ሚዲያ ጋር ሰፊ ስራ የሰራ ነው። በጎንቻ ጠንካራ የሚባለውን ብርጌድ በመሰነጣጠቅ ግጭቶችን በመቀስቀስ በቀጠናው የነበረውን ትግል መራራ ያደረገብን የዶላር ቀለብተኛ ነበር።በወቅቱ ውስብስብ የነበረውን ችግር ብቻችንን ጥርሳችንን ነክሰን በመታገል ቀጠናውን በማስለቀቅ በረሀ ለቀናቸዋል። በጎንቻም በእነብሴም የነበሩ አፈንጋጭ ኃይሎች በእነብሴ በረሀ (ዞባር) ላይ በመመሸግ ከመርጡለ ማርያም(ጎጃም)መካነሰላም (ወሎ) የሚወስደውን ድልድይ ከ71ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮረኔል አዱኛው ጋር በመመሳጠር ለኮረኔሉ በቀን 50,000 ሺህ ብር በመክፈል ለ5 ወራት ቆይተዋል። ይህንን መሰረት በማድረግ በወቅቱ የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ጠንካራ ኦፕሬሽን በማድረግ መጋቢት 5 ጀምሮ በወሰደው ድርጅትን የማስጠበቅ ተልዕኮ ማስረሻ ሰጤን ጨምሮ ውጅሌዎችን በሁለት ቀናት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ በመጥረግ 200 ሰራዊት ወደ እናት ብርጌዳቸው እንዲመለሱ በማድረግ ከጠላት ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ከሀዲዎችን ዳውንት ድረስ አጣድፈናቸዋል። ቀጠናውን ተቆጣጥረን ፍተሻ ሲደረግ ከተገኙት ማስታወሻ መካከል በፎቶው የሚታየው የከፌ ይገኙበታል ። የማስታዋሻ ገጾችን አንድ በአንድ በማገላበጽ ተመልክቻቸዋለሁ ከበርካታ ገጾች መካከል በጥር ወር 2017 ዓ.ም በነበራቸው ውይይት "ማስረሻ ሰጤ ያለህን ስምና ዝና በመጠቀም የአማራ ፋኖ በጎጃምን ሰራዊት በማፍረስ የኛ ኃይል እንዲደራጅ አላደረክም ለዚህ ስራ ማስፈፀሚያ የተሰጠህ 7,000,000(ሰባት ሚሊዮን ) ብር የት እንዳደረስከው አይታወቅም የሚል ትችትን ከፌ ማቅረቡን የሚያሳይ መረጃ በራሱ የእጅ ጹሑፍ አስፍሯል። በቀጣይ ባሉት ገጾች በአንዳድ የጎጃም ቀጠና አሉ የሚሏቸውን አፈንጋጮችና ኃይል የሚያስኮበለሉትን ሰዎችና ቀጠናዎችን በመለየት በገንዘብ ለመግዛት የቀረበውንም ዝርዝር አግንተናል። የትግሉን ተፈጥሯዊ ባህሪ በመረዳት በህዝባችን እና በሰራዊታችን ላይ የተጣበቁ ሚዝጌሮችን በወቅቱ እጅግ መራር ትግል በማድረግ መንቀል በመቻላችን የጎጃም ትግል ወጥ ሁኖ እንዲመራ ለማድረግ በአደረግነው ግብግብ እንደነዚህ ያሉ የእፍኝት ልጆች ትልቅ ዋጋ አስከፍለውናል። የጎጃምን ቀጠና ለማወክ የተንቀሳቀሱትን ቡችላዎች በማጥዳት ቆሻሻ ገንዳ የወረወርናቸውን በማንሳት ብልፅግና ሰው ያገኘ መስሎት ጮቤ እየረገጠ ይገኛል። ከፌ በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በፈለገ ብርሀን ከተማ የ17 አመት ታዳጊ አስገድዶ በመድፈር፣በጎንቻ ሲሶ እነሴ በባርጃኖ እና አውጃ ቀበሌ ሁለት ተጨማሪ ታዳጊ ሴቶችን አስገድዶ የደፈረ መሆኑን በተጎጅ ቤተሰቦች በወቅቱ የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ እና 9ኛ ክ/ጦሮች ቀርበው የከሰሱ ሲሆን ሁለት ንፁሀንን በመግደል በወንጀል የሚፈለግ ሰላቶ ነበር ። የብልፅግና ስርዓት እንደዚህ ያሉ ነውረኞችን ከፊት በማድረግ ህዝብን ለማደናገር የሚሔድበት እርቀት ሽንፈቱን ያመነበት አጋጣሚ መሆኑን ማስገንዘብ እፈልጋለሁ። እነዚህን ጣፊያዎችን በመታገል በጽናት የቆማችሁ አመራሮች የሰራዊት አባላትና ህዝባችን የሌቦችን ፍፃሜ በማያታችን በእጅጉ ልትኮሩ ይገባል። አማራነት ወይም ሞት ክብር በጀግንነት ለተሰው ጓዶች አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

ገባሪው እና የቁጥቋጦው ስር ጉባኤተኛ ጭምብሉ ተገልጧል!! በፀረ-ብልፅግና ትግሉ ውስጥ የተደበቀው አሺክላ በስርገት ትግላችንን ሲፈትነው ከቆየ በሗላ ወደ መደበቂያ ዋሻው ማምራቱ የሚጠበቅ ነው። ጥር
+1
ገባሪው እና የቁጥቋጦው ስር ጉባኤተኛ ጭምብሉ ተገልጧል!! በፀረ-ብልፅግና ትግሉ ውስጥ የተደበቀው አሺክላ በስርገት ትግላችንን ሲፈትነው ከቆየ በሗላ ወደ መደበቂያ ዋሻው ማምራቱ የሚጠበቅ ነው። ጥር 2017 ዓም በጠራራ ፀሃይ ዳውንት ላይ ጉባኤውን አድርጎ የነበረው አፋህድ በእንጀራ ልጆቹ ተከድቷል። ህዝባችን እውነተኛ የትግል መሪዎቹን እና ድርጅቱን ይጠብቅ ስንል የነበረው መሰል ሰራጊዎችን ለመከላከል መሆኑን በተደጋጋሚ አሳውቀናል። ስለሆነም የአማራን ህዝብ ትግል ለመጥለፍ አበክረው የጠላትን አጀንዳ ሲገዙ ከነበሩት ጥቂቶቹ እንዲህ በግልፅ በህዝባችን ላይ ክህደትን ፈፅመዋል። አፋህድ አሁንም ራሱን ይፈትሺ እና ያጠራ ዘንድ እንጠይቃለን። አፋህድ በሰርጎ -ገቦች እና ቅጥረኛ ባንዳዎች የህልውና ትግላችን እየፈተነው ይገኛል በማለት ከዓመት በፊት ተናግረናል። የብዙዎች ጣልቃ ገብነት በህልውና ትግሉ ላይ እንቅፋት ቢሆኑም በአይበገሬ አማራዎች መራራ ተጋድሎ እዚህ ደርሷል። በዘመናት መራራ ተጋድሎ ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶችን አልፈናል!! በመሰል ከሃዲዎች የሚጠለፍ ትግል ፈፅሞ አይኖረንም!! አይበገሬው ትውልድ ያሸንፋል🙏 ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ