en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 389
Subscribers
-324 hours
+2587 days
+1 43630 days
Posts Archive
‎የ66ኛ ክ/ጦር ግዜያዊ መንግስት በይፋ ስራ ጀመረ ‎የአፋብሃ ቴወድሮስ ዕዝና 105ኛ ኮር ከ66ኛ ክ/ጦር ግዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት አደረገ። ‎በ66ኛ ክ/ጦር የጃዊ ወረዳ፤ ፓዊ
‎የ66ኛ ክ/ጦር ግዜያዊ መንግስት በይፋ ስራ ጀመረ ‎የአፋብሃ ቴወድሮስ ዕዝና 105ኛ ኮር ከ66ኛ ክ/ጦር ግዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት አደረገ። ‎በ66ኛ ክ/ጦር የጃዊ ወረዳ፤ ፓዊ ወረዳና ዳንጉር ወረዳ ግዜያዊ መንግስት አመራሮች የእርስ በርዕስ ትውውቅ፤ ተግባርና ኃላፊነትና በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት በኮርና ድርጅት አመራር አማካኝነት ተደርጓል። በውይይቱም ከ3ቱ ወረዳዎች ማለትም ከመተከል ዞን ፓዊና ዳንጉር እንዲሁም ጃዊ ወረዳ የብልጽግናው ወረዳ የተቋጣጠረውን የቀበሌ መዋቅር ሙሉ በሙሉ መፈራረሱ ይታወቃል። በምትኩም የፋኖ ነጻ ወረዳ በማስፋት ግዜያዊ መንግስት መዋቅር ከዋና አስተዳዳሪ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ሸንጎ መዋቀሩ ሠፊው ማህበረሰባችን በደስታ ማዕበል ይገኛል በማለት የወረዳ አመራሮቹ አስተያየቶቻቸውን ገልጸዋል። ‎ #መተከል_ብረሳሽ_ቀኘ_ትርሳኝ! Demelash Andnew ‎

ጄኔራሉን ፍለጋ? ወይስ ጉብኝት? ይችን ዜና እንዴት አያችኋት? ጉብኝት የሚያደርጉ ይመስላሉ? ወይስ የጠፋ ነገር እየፈለጉ? መከላከያ፣አድማ፣ ብተና፣ ፖሊስ፣ ጥምር ጦር... ይሄ ሁሉ አንድ ፋኖን ለመ
ጄኔራሉን ፍለጋ? ወይስ ጉብኝት? ይችን ዜና እንዴት አያችኋት? ጉብኝት የሚያደርጉ ይመስላሉ? ወይስ የጠፋ ነገር እየፈለጉ? መከላከያ፣አድማ፣ ብተና፣ ፖሊስ፣ ጥምር ጦር... ይሄ ሁሉ አንድ ፋኖን ለመግጠም ነው? ለማንኛውም ዙ 23 እና ወታደሮቹን አስከትሎ የጠፋውን ጄኔራል ፍለጋ በሚል ከትናንት ጀምሮ በዚሁ ዜናው ላይ በተጠቀሰው አካባቢ የተደረገው የአሰሳ ዘመቻ ውጤት ሳይገኝበት ቀርቷል። አሰሳው አልሳካ ሲል "ጉብኝት" ይላሉ እንዴ? ምኑን ነው የሚጎበኙት?!

"ከዚህ በኋላ "ቅዝናም አማራ" እየተባልን አንቀጥልም! ቀጣይ ምን አልባትም ከመካከላችን አንዳችንን ልታጡ ትችላላችሁ። ከመጋፈጥ ወደ ኋላ አንልም!... ይሄ ሰውዬ ይብቃን! " የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው~ ሕዳር 16/2018 ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ልደታ ም/ችሎት ከተናገሩት የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው ሕዳር 16/2018 በፌደራል ከፍተኛ ቤት ልደታ ም/ችሎት ተከሳሾች በቀረቡበት ወቅት የቂሊንጦ ማ/ቤትን እና የግቢው ጥበቃ እና ደህንነት ኃላፊ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታን በተመለከተ ካቀረቧቸው አቤቱታዎች መካከል:- ✍️ ክቡር ዳኞች ልታዳምጡን ይገባል። መስማት ካልቻላችሁ ግን ከዚህ በኋላ በሕይወታችን ጉዳይ ኃላፊነት የምትወስዱ እናንተ ናችሁ! ✍️ ዳኛው ከቤቱታችሁን በጽሁፍ አቅርቡልን ሲሉ የሰጡት ምላሽ ~ "ትንሿን ይህችን ሰሙን ፤ ይህን እናንተ ሌላውን መንግስት እንደሚያደርገው እናውቃለን። " ✍️ ከዚህ በፊት የተፈቀደው መብታቸው ሳይነካ ተፈጻሚ ይሁን ብላችሁ ትዕዛዝ እና አለፍ ብላችሁም ምክር ጭምር መስጠታችሁ እየታወቀ ነገር ግን እስካሁን አንድም ትዕዛዝ ተፈጻሚ አልሆነም። ✍️ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታ "ብትከሱ ምን ታመጣላችሁ ከላይ እስከ ታች ያለነው እኛው ነን" ያሉትን ተግብረውታል። ✍️ ቤተሰብ ጥየቃ የለም ፤ ቤተሰቦቻችን ቢመጡም ምግብ እንደ ውሻ ጥለውልን እንዲመለሱ ነው የሚያደርጉት። ✍️ ግፍና መከራ፣ ወከባ ፣ ስድብና ማስፈራራት በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተሰቦቻችን ላይ ጭምር እንደቀጠለ ነው። ✍️ ከዚህ በኋላ "ቅዝናም አማራ" እየተባልን አንቀጥልም! ቀጣይ ምን አልባትም ከመካከላችን አንዳችንን ልታጡ ትችላላችሁ። ከመጋፈጥ ወደ ኋላ አንልም! ✍️ አትክልት እና ፍራፍሬ እንዳይገባ ከልክለዋል! እኛ ኦርቶዶክሶች ነን ፤ የ40 ቀን ጾም እንጾማለን። ከጤናም አንጻር ቀላል ያለ ምግብ ~ አትክልትና ፍራፍሬ እንጠቀማለን። በሙዝ ውስጥ ሲም ካርድ ተገኘ ይሉናል ፤ እኛ ምን አገባን? ይህ የእኛ ስራ አይደለም! ✍️ ፌደራል ፖሊስ በኢ/ር ድሪባ ላይ የወንጀል ፍሬ ነገሩን እንዲያጣራ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር ፤ ፖሊስ ግን እስካሁን አንድም ምርመራ አላደረገም! ✍️ ዐቃቤ ሕግ ይህን እንዴት ያየዋል? የአማራ ሕዝብ የዐቃቤ ሕግ እና የመንግሥት አይደለም ? ✍️ የታጠቁ ሸፍቶች ናቸው እየጠበቁን ያሉት። እንድንገደል እንደተፈረደብን ነው የምንቆጥረው ! ✍️ ከአሁን በኋላ ዳኝነት ካላገኘን ቤተሰቦቻችን እየተሰደቡ ፣ አማራነት እየተዋረደ አንቀጥልም ፤ ከዚህ ሰውዬ  አውጡን! ይሄ ሰውዬ ይብቃን!    (አውሎግሶን አንድነት ፣ ሕዳር 17/2018)

ጥብቅ መልዕክት !! ዛሬ 17/03/2018 ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ ደምበጫ ገብርኤል ኮብል ደጋ ዳሞት መዞሪያ እና ሌሎችም የገብያ መግቢያዎች ላይ ከገጠር የሚገባን አርሶ አደር እና ወጣት እያፈሱ ነው
ጥብቅ መልዕክት !! ዛሬ 17/03/2018 ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ ደምበጫ ገብርኤል ኮብል ደጋ ዳሞት መዞሪያ እና ሌሎችም የገብያ መግቢያዎች ላይ ከገጠር የሚገባን አርሶ አደር እና ወጣት እያፈሱ ነው ። " ዞረብኝ በል ስትዞር ዋልና " አይነት ድርጊት ነውኮ የገጠመን ጎበዝ በርህ ድረስ ሊበላህ መጦ አማራ ተደራጅ ስንልህ ፌዝና ሳቅ የያዝክ የአማራ ወጣት የአማራ ህልውና ለማስከበር ከተደራጁ የአማራ ፋኖ ወንድሞችህ ጋርየትግል አደረጃጀት ግባና ጠላቶችህን ታገል ስንልህ ቁጭ ብለህ እያየህ አፈሱኝ አትበል ። ተደራጅ ተደራጅ አሁንም ተደራጅ ከተማ ውስጥ ከጠላቶችህ ጋር አትርመስመስ ደምህና የአማራ የዘር ማንነት የማይፈቅደውን ከጠላቶችህ እግር ስር አትርመጥመጥ !

ህዳር 17/2016 ዓ.ም‼️ 🕯🕯🕯ዝክረ ሰማዓታት🕯🕯🕯 እለተ ሰኞ ህዳር 17/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ሰዓት ልክ በዛሬው እለት የአብይ አህመድ አረመኔው ሀይል ከ18 በላይ ዋበር ከተማ
+2
ህዳር 17/2016 ዓ.ም‼️ 🕯🕯🕯ዝክረ ሰማዓታት🕯🕯🕯 እለተ ሰኞ ህዳር 17/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ሰዓት ልክ በዛሬው እለት የአብይ አህመድ አረመኔው ሀይል ከ18 በላይ ዋበር ከተማ ከግለሰብ ቤተ ላይ በተጠቀመው ድሮን የተሰው አመራሮቻችን 2ኛ ዓመት ሙእተ ዓመት በከተማው ወጣቶች እና በጎዶቻቸው ታስበው ውሎሏል። እናተ የተሰዋላቹህለትን አላማቹህን ለማሳካት  ዛሬ ላይ ሽወችን ፍሬ አፍርቷል። 🕯ነፍሳቹህን በአፀደ ገነት ያኑርልን🕯 🕯🕯ትግለ ቅብብሎሽ ነው🕯🕯 ህዳር 17/2018 ዓ.ም

ኅዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም ገለልተኛ መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ ምርመራ እንዲደረግ ሁሉም የበኩሉን ግፊት እንዲያደርግ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የቀረበ ጥሪ!!! ሰሞኑን የሰው እጅ በመጥረቢያ ሲቆረጥ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ታይቷል። ይህ አይነት ድርጊት በማንም ይፈፀም በየትኛውም ቦታ ይደረግ በሰው ልጆች ላይ ሁሉ ሊፈፀም የማይገባ አሳፋሪ ድርጊት በመሆኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ድርጊቱን ፈፅሞ ያወግዛል። ይሁን እንጅ መሰል ድርጊቶችን በእጅ አዙር እና በቀጥታ በመፈፀም የሰው አካላትን መበለትን መደበኛ ተግባሩ ያደረገ ሰራዊት በአማራ ክልል ያሰማራው የብልፅግና መዋቅር አፈ-ቀላጤወች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የፋኖ መዋቅርን እየከሰሱ ይገኛሉ። ዓለም አቀፍ የጦር ህግን አክብሮ የማረካቸውን የጠላት ሰራዊት አባላት እንኳን በምንም መመዘኛ ልዩነት ሳያደርግ ፍፁም ሰብአዊነትን በተላበሰ መንገድ የሚታገለውን ሰራዊታችንን በማይገልፅ መንገድ እና መዋቅራችን በማያውቀው ድርጊት መነሻነት በተከፈተው የስም ማጥፋት እና ትግሉን ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ ግብረ ገባዊ ግብራችንን ጠንቅቆ የሚያውቀው ህዝባችን እንደማይደናገር  እናምናለን። አገዛዙ በደረሰበት የዲፕሎማሲ ኪሳራ፣ በሰብአዊነት ላይ እየፈፀማቸው ያሉት ወንጀሎች መጋለጥ፣ በተጀማመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ምክንያት ቅርቃር ውስጥ መግባቱን ተከትሎ መሰል ነውረኛ ተግባራትን በስውር በማስፈፀም እና በሚዲያ በማስተጋባት ህዝብን ማደናገር የዘወትር ስልቱ መሆኑም ይታወቃል። የፋኖን የህልዉና ትግል ከህዝብ ለመነጠል በደህንነት መ/ቤቱ እና ሌሎች የጥፋት መዋቅሮቹ አረመኔ ነፍሰ-ገዳዮችን በማዘጋጀት በቡድን ሴቶችን መድፈርን ጨምሮ ከሰብአዊነት በወጣ መንገድ በመጥረቢያ የሰውን አካል በመቆራረጥ፤ በአሰቃቂ ሁኔታ የሰው ልጆችን አንገት በስለት በማረድ ይህንንም በመቅረፅ በወገን ሰራዊት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ይከፍታል። ከሰሞኑ በአማራ ክልል እየፈፀማቸው ያሉት ድርጊቶች በቅርቡ በአርሲ እና በመተከል-ቡለን ከተፈጠረው ጅምላ ፍጅት የቀጠለ የአገዛዙ ስልት ነው። ለአብነት በምዕራብ ጎጃም ሰከላ ወረዳ ንፁሃንን በመረሸን እና ምላሳቸውን በመቁረጥ፤ ግንቦት 9/2016 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ በረከት ወረዳ መጥተህ ብላ ከተማ አድዬ አክሊለ የተባለች ግለሰብን በቡድን አስገድዶ ከደፈሩ በኋላ ጡቷን እና እጆቿን ቆራርጠው በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል አረመኔነቱን አሳይቷል።  በመሆኑም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አብይ አህመድና ተላላኪዎቹ እየፈፀሙ ያሉትን አሰቃቂ ድርጊት እንዲያወግዙ እና ገለልተኛ መርማሪ ቡድን እንዲቋቋምና ምርመራ እንዲጣራ ግፊት እንድታደርጉ ጥሪያችንን እያስተላለፋን በእኛ በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን።                   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማዕከላዊ ኮማንድ

‎የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር በ66ኛ ክ/ጦር ቀጠና ግዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት አደረገ‼️ ‎በ66ኛ ክ/ጦር ቀጠና በጃዊ ፤ ፓዊ እና ዳንጉር ወረዳ ግዚያዊ መንግስት አመራ
+4
‎የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ  የ105ኛ ኮር በ66ኛ ክ/ጦር ቀጠና  ግዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት አደረገ‼️ ‎በ66ኛ ክ/ጦር ቀጠና  በጃዊ ፤ ፓዊ እና ዳንጉር ወረዳ ግዚያዊ መንግስት አመራሮች የእርስ በርዕስ ትውውቅ፤ ተግባርና ኃላፊነትን በተመለከተ እንዲሁም በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት  የድርጅት አመራርና የ105ኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት  ተደርጓል። በተደረገው ውይይትም  ከሶስቱ ወረዳዎች ማለትም ፦ከመተከል ዞን ፓዊና ዳንጉር ወረዳ እና  ጃዊ ወረዳ  ውስጥ በቴዎድሮስ ዕዝ  የተቆጣጠርነውን ሙሉ የቀበሌ መዋቅር ፍትህ የመስጠት፣የማስተዳደር ፤ መሰል ህዝባዊ አገልግሎቶችን እንዲሁም  የተለመደ የዕለት ከዕለት ተግባራትን ፣ህዝባዊ አገልግሎት እና ህዝባችን ከድርጅታችኝ  የሚፈልገውን ሁሉን  አቀፍ ግልጋሎት በተገቢው ሁኔታ ለማከናወን ያስችል ዘንድ  ለጊዚያዊ የወረዳ አመራሮች መመሪያ ተሰጧል፤የስምሪት አቅጣጫ ተቀምጧል ። በዚሁ አጋጣሚ  ከላይ በተጠቀሱት  ወረዳዎች የቀበሌ መዋቅር ሙሉ በሙሉ መፈራረሱ የሚታወቅ ሲሆን  ፥ በምትኩም የፋኖ ነጻ ወረዳ በማስፋት ግዚያዊ መንግስት መዋቅር ከዋና አስተዳዳሪ ጀምሮ እስከ ቀበሌ  የፍርድ ሸንጎ መዋቅር በመዘርጋት ሠፊው የማህበረሰብ ክፍል  በድርጅታችን መምሪያ መሰረት ተገቢውን አገልግሎት እያገኘ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን ።ድርጅታችን ይህንን ተግባርና ሃላፊነቱን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የጀመረውን መዋቅራዊ እንቅስቃሴውን  በቀጣይ ነፃ በሚወጡ ቀጠናዎች  ሁሉ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንን  እንገልጻለን ። ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!! አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!!! Hailemichael Bayeh ‎

ጀግናው ዘራፌዋ ጀግናው ፋኖ በሉ ጀግናው ዘራፌዋ ምነው ዝም አላቹ ሀገር በወንበዴ ወድቃ ተከባቹ ወጡና ከቆላ በሉት ለሀገራቹህ ፋኖ ዘራፌዋ .....አኸኸ ከጀግናው ጆን የአማራ ልጅ የተገኘ ለአማራ ማህበረሰብ የተላለፈ የሙዚቃ ስራ ነው ለሁሉም አማራ እንዲደርስ መልክታችን ነው።

አውሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ «ይፈፀማል» ያሉትን ግድያ በሠልፍ አወገዙ ጀርመን እና በአጎራባች የአውሮጳ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ  ውስጥ በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ ይፈፀማል ያሉትን ግድያ፣ ግፍና ማፈናቀል ዛሬ በርሊን-ጀርመን ውስጥ ባደረጉት የአደባባይ ሠልፍ አወገዙ። ሰልፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት የተጠራ ሲሆን በተለያዩ የጀርመን ከተሞች፤ እንዲሁም በጀርመን አጎራባች የአውሮጳ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል። ሰልፈኞቹ እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አካባባቢዎች «በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ» የሚፈፀመውን ግድያና ግፍ እስካሁን ማስቆም አልቻለም። «ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የሚፈጸመው በቃላት ተገልጾ የሚያልቅ አይደለም» ያሉት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ከተሰላፊዎቹ አንዱ የሆኑት በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሥራችና የኮሎኝ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ ተበጀ፤ «ሰዎች በቋንቋቸው፤ እንደዚሁም በሃይማኖታቸው ተለይተው እየታረዱ፣ እየተጨረሰ ይህን ያህል ግፍ ሲፈጸምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬ ይህን ሰቆቃ ሊያስቆም አልቻለም» በማለት ዛሬ ድምጻቸውን በዓለም ሸንጎ ለማሰማት መውጣታቸውን ገልጸዋል። የሰልፉ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያውያን ካህናትና ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ሃገራት ዜጎችም አብረዋቸው ድምጻቸውን እያሰሙ እንደሆነም አመልክተዋል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ፤ ጅማ፤ ወለጋ፣ ሻሸመኔ፣ እንዲሁም በሐረር ክርስቲያኖች መገደላቸውን የገለጹት ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ፤ ባጠቃላይ «በሀገሪቱ ግፍ እየተፈጸመ ነው» በማለት በጀርመንዋ ዋና ከተማ በርሊን ለሰልፍ ያስወጣቸውን ምክንያት ዘርዝረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለው «ዓለም ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው» ያሉት የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ መዊ ልሳነ ወርቅ ውቤ በበኩላቸው ከሚገደሉት ሌላ «የታፈኑ፤የታገቱ፤ የተፈናቀሉ እና ሀብት ንብረታቸው የተወሰደባቸው፤ እንደው ጨረቃ ላይ የቀሩ፤ በረሃብ እያለቁ ያሉ፤ አካለ ስንኩላን የሆኑ ክርስቲያኖች ናቸው » በማለት እነዚህ ወገኖች የሚደርስላቸው አጥተዋል ነው ያሉት። በዋና ከተማ በርሊን ሰልፉ የተካሄደው የኢትዮ ጀርመን የኤኮኖሚ ትብብር ጉባኤ እየተከናወነ ባለበት ዕለት ነው። በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አውሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ «ይፈፀማል» ያሉትን ግድያ በሠልፍ አወገዙ ጀርመን እና በአጎራባች የአውሮጳ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ ይፈፀማል ያሉትን ግድያ፣ ግፍና ማፈናቀል ዛሬ በርሊን-ጀርመን ውስጥ ባደረጉት የአደባባይ ሠልፍ አወገዙ። ሰልፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት የተጠራ ሲሆን በተለያዩ የጀርመን ከተሞች፤ እንዲሁም በጀርመን አጎራባች የአውሮጳ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል። ሰልፈኞቹ እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አካባባቢዎች «በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ» የሚፈፀመውን ግድያና ግፍ እስካሁን ማስቆም አልቻለም። «ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የሚፈጸመው በቃላት ተገልጾ የሚያልቅ አይደለም» ያሉት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ከተሰላፊዎቹ አንዱ የሆኑት በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሥራችና የኮሎኝ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ ተበጀ፤ «ሰዎች በቋንቋቸው፤ እንደዚሁም በሃይማኖታቸው ተለይተው እየታረዱ፣ እየተጨረሰ ይህን ያህል ግፍ ሲፈጸምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬ ይህን ሰቆቃ ሊያስቆም አልቻለም» በማለት ዛሬ ድምጻቸውን በዓለም ሸንጎ ለማሰማት መውጣታቸውን ገልጸዋል። የሰልፉ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያውያን ካህናትና ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ሃገራት ዜጎችም አብረዋቸው ድምጻቸውን እያሰሙ እንደሆነም አመልክተዋል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ፤ ጅማ፤ ወለጋ፣ ሻሸመኔ፣ እንዲሁም በሐረር ክርስቲያኖች መገደላቸውን የገለጹት ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ፤ ባጠቃላይ «በሀገሪቱ ግፍ እየተፈጸመ ነው» በማለት በጀርመንዋ ዋና ከተማ በርሊን ለሰልፍ ያስወጣቸውን ምክንያት ዘርዝረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለው «ዓለም ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው» ያሉት የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ መዊ ልሳነ ወርቅ ውቤ በበኩላቸው ከሚገደሉት ሌላ «የታፈኑ፤የታገቱ፤ የተፈናቀሉ እና ሀብት ንብረታቸው የተወሰደባቸው፤ እንደው ጨረቃ ላይ የቀሩ፤ በረሃብ እያለቁ ያሉ፤ አካለ ስንኩላን የሆኑ ክርስቲያኖች ናቸው » በማለት እነዚህ ወገኖች የሚደርስላቸው አጥተዋል ነው ያሉት። በዋና ከተማ በርሊን ሰልፉ የተካሄደው የኢትዮ ጀርመን የኤኮኖሚ ትብብር ጉባኤ እየተከናወነ ባለበት ዕለት ነው።

ባንዳዎች እና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ ላይ ከባድና የማያዳግም እርምጃ የመውሰዱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳን ሄሮሹማና ናጋሳኪ ሲያደርግ የነበረ ባንዳ ጥቁሩ ፋሽስት ሎሌ እና በርካታ የሚኒሻና የመከላከያ ሰራዊቶች በአንድም በሌላም ተሸኝተዋል። የአማራ ሳር ቅጠሉ ምድር ሰማዩ ሁሉ ጥላትን እየተፋለመው ይገኛል። ህዳር 17/2018 ዓ/ም በዋድላ ወረዳ የሚኒሻ አስተባባሪና ኮማንደር  የሆነው ሰይድ ስጦታው እና አምስትየሚኒሻ አባል እድሁም የፋሽስቱ መከላከያ መቶ አለቃና ሰባት የመከላከያ ሰራዊቶች የሞቱ ሲሆን፤አምስት ሚኒሻ ቁስለኛ፤ሶስት መከላከያዎችም ቁስለኛ ሆነዋል። ኮን የዶጌት ሚካኤል በተባለ ቦታ ላይ በመኪና ተጭነው ሲጓጓዙ ተሽከርካሪው ተገልብጦ ወደማይቀረው አለማቸው ተጉዘዋል። ኮማንደር ሰይድ በዋድላ ወረዳ የሚታወቅበት ከስሙ በላይ ቀድሞ የሚጠራበት የአማራን ንፁሀን በመግደል፣በመዝረፍና በመጨፍጨፍ እድሁም ሴቶችን አስገድዶ በመድፈር ነበር። ሰይድ የፋሽስቱ የአቶ አብይ አህመድ ታማኝ ተላላኪ ሲሆን የአማራ ህዝብ ግባር ቀደም ጥላት ሆኖ ሌባ ጎማ ተጭኖት እስኪሞት ድረስ አፀያፊ ተግባሩን ይፈፅም ነበር። ፋሽስቱ በሰጠው ስልጣን የግል ቂምበቀል የሚዎጣበት የፋሽስቱ ደጀንነትን ተጠቅሞ እደነበር ታሪኩ ይናገራል። የሰይድ የባንዳነት የታሪክ ፍፃሜ የተደመደመው እስከ ከርሰ ምድር በዘለቀው የሎሌነት ተግባሩ ሆኗል። ከፊደልና ከትምህርት ታቅቦ የተፈጠረው ሰይድ ከመቃብሩ ላይ ከሚጫነው ሸክም በላይ ያልነጠፈ የባንዳነት ታሪኩ ሰባተኛ መሬትን ሰርስሮ የተነጠፈ ጥቁር የታሪክ ባለቤት ፈፃሚም ነበር። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 17/2018 ዓ.ም

​🛡️ ፋኖነት እና አንድነት ​ፋኖ የኅብረተሰቡን ደህንነትና ክብር ለመጠበቅ በፈቃደኝነት የሚሰማራ የጀግንነት መገለጫ ነው። የፋኖዎች አንድነት ደግሞ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይይዛል፡- ​የጋራ
​🛡️ ፋኖነት እና አንድነት ​ፋኖ የኅብረተሰቡን ደህንነትና ክብር ለመጠበቅ በፈቃደኝነት የሚሰማራ የጀግንነት መገለጫ ነው። የፋኖዎች አንድነት ደግሞ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይይዛል፡- ​የጋራ ዓላማ: ፋኖዎች ከየትኛውም አካባቢ ወይም ማኅበራዊ ዳራ የመጡ ቢሆኑም፣ በዋናነት ለአማራ ሕዝብ ክብርና ደኅንነት እንዲሁም ለሀገር ሉዓላዊነት በጋራ መቆማቸው ነው። ይህ የጋራ ዓላማ የአንድነታቸው ዋነኛ መሠረት ነው። ​የአካባቢ ልዩነት የሌለበት ትስስር: የፋኖ እንቅስቃሴ ከተለያዩ የአማራ ክፍል አካባቢዎች የመጡ ግለሰቦችን ያቀፈ ነው። ይህ የአካባቢ ልዩነት የአንድነትን ጥንካሬ ያሳያል፤ ምክንያቱም በክፍል ሳይሆን በመንፈስ እና በግብ የተሳሰሩ ናቸው። ​መከባበርና መደጋገፍ: ፋኖነት ማለት በጦር ሜዳ ብቻ ሳይሆን፣ እርስ በእርስ በመረዳዳት፣ በመመካከርና የጋራ ግብ ላይ በማተኮር የሚገለጥ ወንድማማችነት ማለት ነው። ​ለሕዝብ ቆሞ መገኘት: የፋኖ አንድነት ከግል ጥቅም ይልቅ የሕዝብን ጥቅም እና የሀገርን ደህንነት በማስቀደም ላይ የተመሰረተ ነው። ​"የፋኖ አንድነት የሕዝብ ቃልኪዳን ነው" ​"በጋራ ቆመን፣ በጋራ እንዘልቃለን" ​"ክንዱ የተለያየ ልቡ ግን አንድ ነው" ​"ፋኖነት ለክብር እንጂ ለክፍል አይደለም" ​💡 ማጠቃለያ ​የአማራ ፋኖ አንድነት በሕዝብ ክብርና በሀገር ፍቅር ላይ የተመሠረተ፣ ለጋራ ዓላማ የቆመ፣ የብረት ያህል ጠንካራ የሆነ የአይበገሬነት መንፈስ መገለጫ ነው። ዴቭ ከግንባር ​

ግዙፉ ላስታ አሳመነዉ ኮር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ። አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር በዛሬዉ ዕለት ከ35 በላይ የአገዛዙ ሰራዊትን በመደምሰስና ከ40 በላይ የሚሆኑ የአገዛዙ ሰራዊትን በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፅፏል : የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳመነዉ ፅጌ ኮር ክንፍ የሆኑት እሸት ክፍለ ጦር ፣ ወባንተ አባተ ክፍለ ጦር ፣ በመደራጀት ላይ ያለው አሃድ ራስ አንችም፣ እንዲሁም ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በጋራ መናበብ ባደረጉት አውደ ዉጊያ ከ35 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ  ከ40 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። የአገዛዙ  የሰሜን ምስራቅ ዕዝ  የ65ኛ ክፍለ ጦር  እና የ61ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት  መነሻውን ከላስታ ወረዳ  ሽምሽሃ ቀበሌ (ላሊበላ አየር ማረፊያ) ከተማ በማድረግ የእሸት  ክፍለ ጦርን አፍናለሁ በሚል አጉል ምኞት ወደ  ገለሶት ቀበሌ በመጓዝ  ላይ እንዳለ ክፍለ ጦሩ ቀድሞ በደረሰው መረጃ መሠረት ከኮራችን ክንፎች ከሆኑ ሌሎች ክፍለ ጦሮች እና ብርጌዶች ጋር በመናበብ በጠላት ላይ ኪሳራ አድርሰዉበታል። በዚህም ዉጊያ ላይ እሸት ክፍለ ጦር በልዩ ስሙ እገርፋ፣ ተካይ መንደር ፣ማዶ ራንባ ተብሎ እሚጠራዉን ቦታ ሸፍና የተዋጋች ሲሆን  ዉባንተ አባተ ክፍለ ጦር ፣ራስ አንችም ክ/ጦር ፣ነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ በጥምረት  በመሆን ከላሊበላ ከተማ ወደ ጋሸና እሚወስደዉን አስፓልት መንገድ በተለምዶ በርታ፣   ግራኝ አንባ፣ ቻይና ካንፕ ድረስ በመዘርጋት ጠላትን ሲያረግፉት ዉለዋል። ህዳር 17/3/2018 ዓ/ም ከ ቀኑ 5:00  ሰዓት እስከ አመሻሽ 9:30 ከአራት ሰዓት በላይ በፈጀ ትንቅንቅ  ከ35 በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ40 በላይ ቆስለኛ ማድረግም ተችሏል። በዚህ አውደ ዉጊያ ጠላት የእሽት ክፍለ ጦርን ለማፈን አቅዶ የመጣ ቢሆንም ባላሰበውና ባልጠበቀው መንገድ ራሱ ታፍኖ በወገን ክንድ ሲቀጠቀጥ ውሎ ወደ መጣበት ሽምሽሃ ቀበሌ (ላሊበላ አየር ማረፊያ) ፈርጥጦ ተመልሷል። በዚህም ወጊያ ጠላት ሽምሽሃ ቀበሌ ኪኒሸር ከሚባል ቦታ ላይ 120 ሞርተር አጥምዶ በሚወረዉረዉ ቅንቡላ እርፋ እና ተካይ መንደር አካባቢ በንፁሃን ዜጎች ላይ አካላዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል። በትላንትናዉ ዕለትም የዚሁ ኮር አካል የሆነችዉ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር በአገዛዙ ሰራዊት ላይ አካላዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን መዘገባችን ይታወቃል። አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ  ፋኖ ደረበ መኮንን! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ህዳር 17/3/2018 ዓ.ም

‼️‼️ሰበር ዜና‼️‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ወደ ማይቀረው የድል ጉዞ ደረጃውን አሳድጎ እየመጣ ነው።  ታማኝ መረጃዎች ለማግኘት ከታች ባለው የሚዲያ ድምፆች፡፡               ተቀላቀሉት Join👇👇               "በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk https://t.me/abcdefghijklmnopqrstuvwxyz071167