ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 413
Subscribers
+2224 hours
+437 days
+1 38430 days
Posts Archive
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር
በምእራብ ጎንደር መተማ ወረዳ የአገዛዙ ደም መጣጭ ቡድን ክፉኛ እየተቀጣ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል።
ቀጠናው ላይ በተደረገው ተደጋጋሚ ሽንፈት የተነሳ ጭማሪ ሀይል ለማስገባት ፣ በትናንትናው እለት ጥቅምት 25/2018 የአገዛዙ ግብስብስ ፀረ አማራ የአውሬው ስርአት አስፈፃሚ ሀይል መነሻውን ምዕራብ አርማጭሆ ማሰሮ ተነስቶ ወደ መተማ ወረዳ ለመግባት ሲንቀሳቀስ ፣ በአናብስቶቹ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ባባየ ብርጌድ በአርበኛ ገ/ህይወት እየተመራ እና ደጃዝማች 4ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦ በላይ ዘለቀ ብርጌድ በአርበኛ ተስፋየ እየተመራ ፣ ይህንኑ ግብስብስ ሀይል ሁለቱ ብርጌዶች ወሳኝ የሞት ወረዳ ታጉር ከምትባል ቦታ ደፈጣ በማድረግ ከቀኑ 9:00 ስአት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል። በዚህ ፈጣን የማጥቃት የደፈጣ ውጊያ የደነገጠው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ አራጅ ቡድንና ሆዳም የብልፅግና ተስፋ ቆራጭ በራሳቸው መተማመን የሌላቸው ትንንሽ ጭንቅላቶች በአሁኑ ስአት በቀጠናው ከፍተኛ ሽንፈትንና ድንጋጤን ፈጥሮባቸዋል። ይህንኑ በደፈጣ የጀመረው ውጊያ በአሁኑ ስአት ወደ መደበኛ አውደ ውጊያ ተቀይሮ ፣ የአገዛዙ ጥምር ሀይል ቀለበት ውስጥ ገብቶ ክፋኛ እየተቀጠቀጠ መውጫ መግቢያ አጦ ይገኛል።የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህዝብ ግንኙነት አርበኛ ግዛት አለበል ከቦታው እንዳደረሰን አውደ ውጊያው በአስፈሪነቱና በድል እንደቀጠለ እንዳልተቋጨ አድርሶናል።
ከ9:00__11:00 ስአት በተደረገው ውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት = 27
ቁስለኛ = 35
የሞርተር ቅምቡላ = 4
የዲሽቃ ተተኳሽ = 1 ሳጥን
ወታደራዊ ሻንጣ = ከ30 በላይ
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጥቅምት 26/2018
#የጠላት_እንቅስቃሴ‼️
6:25 ላይ ከደብረማርቆስ ከተማ በአዲሱ አስፖልት በኩል ወደ አማኑኤል (ባህርዳር መስመር) 9 ሲኖ የመከላከያ ኃይል ተንቀሳቅሷል ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዋል።
አናብስቱ 6ኛ ክፍለ ጦር በበርካታ ግንበር ጠላትን እያበራየው ይገኛል💪
መረጀው ሸርርርር ይደረግ‼️
26/ዐ2/2018 ዓ.ም
አንድ ሰው በምድር ሲኖር የሚሞትለት አላማ ከሌለው ኖረ ሊባል አይችልም።
አዲሱ የአማራ ትውልድ ደግሞ የሚሞትለት አላማው የአማራን ሕዝብ ከህልውና ስጋት ነፃ ማውጣት ነው። ስለዚህ ይህ ትውልድ በዓለም፣ በታሪክ እና በነፍስም ህያው የሆነ ትውልድ ነው። ህልሙን የኖረ ተብሎ የሚነገርለት እድለኛ ትውልድ ነው።
በዚህ ሂደት ውስጥ በርካታ ግላዊ፣ ቡድናዊ እና ድርጅታዊ ፈተናዎች የሚጠበቁ ናቸው ። ትግላችን ብዙውን ፈተና ተወጦ ከተራራው ጫፍ እየደረሰ ነው። መጠያየቅና መርህ ማስከበርን ካሰፈንን አመታትን አሳልፈናል። ድርጅት የሚያድግ ስለሆነ የሚጎልን እና ያልታዩን በሚሰጡ አስተያይቶች እና ትችቶች እያረምንና እያስተካከልን እየበረርን እንገኛለን።
መርህና አሰራር በተከበረበት ድርጅት ደግሞ በሚዲያ በሚደረግ ሙገሳ እና ወቀሳ የሚቀየር አንዳች ነገር አይኖርም። ለሙገሳውም ሆነ ለወቀሳው ተጨባጭ ማስረጃዎች በድርጅት ቀርበው የሚታዩና ውሳኔ የሚያርፍባቸው ይሆናሉ። በደማችንና በላባችን የገነባነው ድርጅት ደግሞ ከዚህደረጃ በላይ የደረሰ ጠንካራ ዕዝና ሰንሰለት ያለው ድርጅት ነው።
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ኢንጅነር እስቲበል ዓለሙ
"በሰባት ጡት ቆራጮች አፈር መልሰናል" የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ዘመቻ መሪ
════════════❁✿❁════════════
(ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም፣ ነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት)
ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ቋሪት ወረዳ የገባው ወራሪ ጡት ቆራጭ ሠራዊት በነበልባሎቹ በሳል የውጊያ ጥበብ ብልጫ ተወስዶበታል።
በዚህም "ቀበሌዎችን እቆጣጠራለሁ" ብሎ ወደ ደጋማው አካባቢዎች ከፍተኛ ቊጥር ያለው መዝባሪ ሠራዊት ቢያሰማራም በደጃች ማተብ ልጆች ብርቱ ትግል ቀጠናውን ነፃ ማድረግ ተችሏል።
በትላንትናው ዕለት በተካሄደው ውጊያም አገዛዙ ባላነሳችው ሰባት ጡት ቆራጮች አፈር መልሰናል ያሉን የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ዘመቻ መሪ ፻ አለቃ ዘገዬ ምኒበል ናቸው።
የአካባቢው አርሶ አደር ከቀበራቸው ሰባት አባላት በተጨማሪ በርካታ ሙትና ቁስለኛ እንዳለ የውስጥ ቀኘዎች ተናግረዋል።
"እኒህ ትራፊኮች የሚሠሩት ሥራ፣
ሕዝቡ ቀኝ እንሂድ እነርሱ በግራ፣
ደግሞ መዘጋጃ የሚሠራው ሥራ፣
እነርሱ እናፍርሰው ሕዝቡ ቤት እንሥራ፣
እንዲህ ብለው ብለው ያመጡት መከራ፣
ቃብር ብቻ አረጉት የዐማራን ተራራ።" ወቅታዊ #የሕዝብ ግጥም
ድል ለፋኖ !!!!
አንድ አማራ !! ለሁሉም አማራ !!
ሁሉም አማራ !! ለአንድ አማራ !!
አዲስ አመት !! አዲስ ተስፋ !!
+3
#አፋብኃ_እንደ_ንስር_ከፍብሎ_በመብረርላይ_ይገኛል
የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ እዝ የ201ኛ ኮር ምስረታ ተጠናቋል። በስሩ ያሉት ክፍለ ጦሮች
54ኛ ክ/ጦር
64ኛ ክ/ጦር
74ኛክ/ጦርን በማቀፍ ምስረታው ተጠናቆ የኮሩ አመራሮችም በጋራ ትውውቅ በማድረግ ለቀጣይ ስራወች እራሳቸውን ዝግጅ በማድርግ ተልዕኮወችን በመስጠት በአዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ወደተግባር ተገብቷል።
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
የኮሩ አመራሮች በከፊል
+3
🔥#አሰልጣኝ_ቡድኑ‼️
በአፋብኃ ምስራቅ አምራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል!
26/ዐ2/2018 ዓ.ም
🔥#የአርበኛ_ሳሙኤል_ባለድል_መልዕክት‼️
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የመጀመሪያ ዙር ድርጅታዊ ጉባኤውን ለ14 ቀናት የወሰደ ጥልቅ ግምገማ እና ውይይት በማድረግ #የጎንደርንም ሆነ #የአማራን_አንድነት በተመለከተ እንዲሁም የአማራን ወሰን እና እርስት ዘላቂ ጥቅም በጠበቀ መልኩ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር መስራት እንደሚገባም ጥልቅ ወይይት መደረጉን የገለጸ ሲሆን በዚህም #የአማራን_አፅመ_እርስቶች በተመለከተ አንዱ የመታገያ አጀንዳቸው መሆኑን በማስቀመጥ አጠቃላይ ትግሉን ድርጅት መር በሆነ ትግል የነበሩ ተግዳሮቶቹን በጥልቅ ግምገማ በመገምገም ጨርሷል።
እሱን አስመልክቶ የዕዙ ወታደራዊ አዛዥ በሆነው በአርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል ጠቀለል ብሎ እንደሚከተለው ጉባኤውን አስመልክቶ ለተወሰኑ ውሳኔዎችን ማብራሪያ ሰጧል !!
ድል ለአማራ ፋኖ
የአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል
በኢትዮጵያ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ለማስቆም አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት ጥሪ ቀን፡ ህዳር 2 ቀን 2025
ለ፡
የእስራኤል መንግስት ፕሬዝዳንት - ሚስተር ቻይም ሄርዞግ፣ የፕሬዝዳንቱ መኖሪያ
የእስራኤል ፕሬዝዳንት - ሚስተር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ
የክኔሴት አፈ ጉባኤ - ሚስተር አሚር ኦሃዮን፣ የእስራኤል ክኔሴት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - ሚስተር ጊዲዮን ሰዓር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የመከላከያ ሚኒስትር - ሚስተር እስራኤል ካትዝ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር
የክኔሴት አባል ሚስተር ቦዝ ቢስሙት - የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ኮሚቴ ሊቀመንበር
ርዕሰ ጉዳይ፡
በኢትዮጵያ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ለማስቆም አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት ጥሪ
እኛ የእስራኤል መንግስት ዜጎች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በኢትዮጵያ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ለማስቆም ይህንን ልባዊ እና አስቸኳይ ጥሪ ለእስራኤል መንግስት - ዲፕሎማሲያዊ፣ ሰብአዊ እና አለም አቀፍ - እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለን።
ከ2023 ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ማህበረሰብ አባላት ላይ ስልታዊ ዘመቻ አካሂዷል፤ ከእነዚህም መካከል የአየር ድብደባ፣ የጅምላ እስራት፣ ማሰቃየት፣ ግድያ እና ሆን ተብሎ የተፈጸሙ ጥቃቶች ይገኙበታል፤ ከእነዚህም መካከል ሴቶች፣ ህጻናት እና አረጋውያን ይገኙበታል። ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) የተገኙ ሰነዶችን ጨምሮ በርካታ ሪፖርቶች የእነዚህን ጭካኔዎች መጠን ያረጋግጣሉ።
በጥቅምት 2025 ብቻ የኢትዮጵያ መንግስት ከ40 በላይ የድሮን ጥቃቶችን በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ሆስፒታሎችን እና የህክምና ማዕከላትን ጨምሮ። እነዚህ ጥቃቶች ነፍሰ ጡር ሴትን ጨምሮ በርካታ ንፁሃን ሲቪሎችን ህይወት አጥተዋል። እንደዚህ አይነት ድርጊቶች የአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግን እና መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችን መርሆዎች በግልጽ የሚጥሱ ናቸው።
ጭካኔዎቹ በሲቪሎች ላይ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ። እጅ የሰጡ የአማራ ታጋዮች ለከባድ ስቃይ እና ለጭካኔ የተዳረጉ ናቸው። ከቅርብ ጊዜ ተጎጂዎች መካከል የ19 ዓመቷ ሴት ታጋይ ወ/ሮ ባሌም ዋሴ እና ወ/ሮ ትግስት ወዳጆ ይመር በስቃይ፣ አስከሬናቸው ረከሰ እና በይፋ ተዋርደዋል። እንደ ዘገባዎች ከሆነ፣ የወ/ሮ ዋሴ ቆዳ በጭካኔ በተቆረጠበት አካባቢ 'አማራ' የሚል ንቅሳት ተቆርጧል - ይህ አስፈሪ ድርጊት በአማራ ማህበረሰብ መካከል ፍርሃትን ለመፍጠር እና የዘር ጥላቻን በአደገኛ የረጅም ጊዜ ውጤቶች ለማቀጣጠል የታሰበ ነው።
ከአማራ መካከል የተውጣጡ ታዋቂ የነፃነት ታጋዮች ቡድን የሆነው የፋኖ ንቅናቄ - ሲቪሎችን ከእልቂት እና ከስደት ለመጠበቅ በግድ ተነስቷል። አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም፣ የፋኖ ታጋዮች በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ መንፈስ ሲንቀሳቀሱ፣ ሲቪሎችን እየጠበቁ እና እስረኞችን በሰብአዊነት ይንከባከባሉ።
እስራኤል፣ ከሆሎኮስት አመድ የተወለደች የአይሁድ መንግስት - በአይሁድ ታሪክ ውስጥ ትልቁ አሳዛኝ ክስተት - በዓለም ላይ የሞራል ድምጽ እንድትሆን እና በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ለማስቆም እንድትሰራ እንጠይቃለን። እንደ ማንነታችን የተሳደድን እና የተገደለን ህዝብ ታሪካችን ሌላ ሀገር በመነሻው ሲጠፋ ዝም እንዳንል ያስገድደናል።
ስለዚህ፣ እንጠይቃለን፡
1. የእስራኤል መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ወንጀል በይፋ እንዲያወግዝ።
2. እስራኤል በአማራ ውስጥ በጦርነት ወንጀሎች እና በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግላት በአለም አቀፍ እና በክልል ተቋማት እና ማህበረሰቦች ውስጥ እርምጃ እንድትወስድ።
3. የሲቪል ሰዎችን ሕይወት ለመጠበቅ ፈጣን የሰብአዊ እና የዲፕሎማሲያዊ እርዳታ ግምት ውስጥ መግባት አለበት።
የእስራኤል መንግሥት እና ተቋማቶቿ የሚፈለገው እርምጃ የእስራኤል መንግሥት የተመሰረተባቸውን እሴቶች - ፍትህ፣ ሥነ ምግባር እና የሰውን ሕይወት ጥበቃ - ስም ነው። በዚሁ መሠረት እርምጃ እንድትወስዱ እንጠይቃለን።
በዚህ አጋጣሚ፣ አሳሳቢውን ሁኔታ በዝርዝር ለማስረዳት ከእርስዎ ጋር በመገናኘታችን ክብር ይሰማናል።
በአክብሮት፣
የእስራኤል ግዛት ዜጎች፣ የሕዝብ ታዋቂ ሰዎች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች
1. አቶ ሽሎሞ ሞላ - የቀድሞ የክኔሴት አባል እና የክኔሴት ምክትል አፈ-ጉባኤ
2. አቶ ሰሎሞን ኃይሌ - የሕግ ጠበቃ
3. አቶ ወንዴሁ ገድላው - አብራሪ እና የሕዝብ አክቲቪስት
4. አቶ አበበ መለሰ - ደራሲ፣ ገጣሚ፣ አቀናባሪ እና አርቲስት
5. አቶ ተዛዝ ዛውዱ - የ"የአማራ አንድነት በእስራኤል" ማህበር ሊቀመንበር
6. አቶ አዲሱ ተባጄ - ገንዘብ ያዥ፣ "የአማራ አንድነት በእስራኤል" ማህበር
7. አቶ አባተ በሪሁን - ከፍተኛ ሙዚቀኛ እና አርቲስት
የእውቂያ ቁጥሮች፡ 050-6200035, 050-6785522, 054-9397310, 053-2394820
ለጥያቄዎች ኢሜይሎች፡ mollazemene@gmail.com | solomomhailelaw@gmail.com
በእነ የተከበሩ ዮሐንስ ቧያለው የሽብር መዝገብ ተከሳሽ የሆኑት ሻንበል አድማሱ አለሙ ታየ በዛሬው እለት ከፍተኛ ቀዶ ጥገና ተደረገላቸው !!!!
በእነ ተከበሩ ዮሐንስ ቧያለው የሽብር መዝገብ አማራነትን እንደ ወንጀል በቆጠረው አገዛዝ ተይዘው የሽብር መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኛ የሆኑት ሻምበል አድማሱ አለሙ ታየ ከ ነሐሴ 3/2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በእስር ላይ እየተንገላቱ እና እየተሰቃዩ ይገኛሉ ።
ሻምበል አድማሱ አለሙ በአዋሽ አርባ በሚገኘው የብዙ አማራወች ህይወት የተቀጠፈበት ጓንታናሞ ማሰቃያ ለ6 ወራት በስቃይ ከቆዩ በኋላ እንደገና በፊደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በማለት በሚጠራው የማሰቃያ ቦታ በጨለማ ቤት ለሁለት ወር በሁለቱም ቦታወች ምንም አይነት ህክምና እንዳያገኙ ሲደረጉ ቢቆዩም ካለፈው አመት ታህሳስ ወር/2017ዓ/ም ጀምሮ በማረሚያ ቤቱ እና በቃሊቲ ማረሚያ አጠቃላይ ሆስፒታል ላለፈው አንድ ዓመት ህክምና ሲከታተሉ ቢቆዩም የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው በሀኪሞች በተወሰነው መሠረት እንደገና ቀዶ ጥገናው እኛ ጋር አይሰጥም በማለት ወደ ፖሊስ ሆስፒታል በመላክ በተሰጣቸው ቀጠሮ ከሁለት ዓመት የስቃይ እና የእንግልት ጊዜ በኋላ በዛሬው እለት ቀዶ ጥገና ቢደረግላቸውም የሆስፒታሉ ዶክተሮች ምንም አይነት ማስታገሻ መድሀኒት እንዲሁም ከባድ ቀዶ ጥገና ህክምና አድርገው እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው እየታወቀ በእንግልት ህመም እያሰቃያቸው ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተመልሰዋል
ሻምበል አድማሱ አለሙ ከፍተኛ የሀገር ባለውለታ ናቸዉ።
በቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ፣በገነት ጦር ት/ቤት ለአራት አመት እጩ መኮንኖች በአሰልጣኝነት ፣ ሁርሶ ጦር ትምህርት ቤት እጩ መኮንኖች በአሰልጣኝነት ሲያገለግሉ ቆይተው በህወሓት መራሹ ሀይል እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል እንደገናም ሻብያ ሀገር በወረረበት ወቅት የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል።
በዛላንበሳ እጋሳ ግንባር ፣አዲፍታው ግንባር ፣ራማ አዲበርበሬ ግንባር እንዲሁም አዲነበረኢድ ዘግር ግንባር ግዳጃቸውን በጀግንነት የተወጡ ቢሆንም ቂመኛው ህወሓት የቀድሞውን ሰራዊት የተውጣጡ ቢሆንም መንግስን ለማፈናቀል ያዘጋጁት ሰራዊት ነው በማለት በጀነራል ፃድቃን እና ስየ አብርሃ ሴራ ያለምንም ካሳ ሰራዊቱን ሲያሰናብት እሳቸውም ከሰራዊቱ አልለይም በማለት ከመከላከያ ነሀሴ 30/1993ዓ/ም እራሳቸውን ያለምንም ካሳ እና ጡሮታ አግልለዋል ። በመቀጠልም በሲቪል ኢትዮጵያ ፈንጂ አምካኝ ጽ/ቤት በዋና አሰልጣኝነት በመቀጠር በሱማሊያ ወረራ እንዲሁም በእርስበርስ ጦርነት ተቀበሩ ፈንጆችን እንዲፀዱ እና በሻብያ ወረራ ወቅትም የተቀበሩ ፈንጆችን በቡሬ ግንባር እስከ ሱዳን ጠረፍ እንዲፀዳ ከጓዶቻቸው ጋር የአንበሳውን ድርሻ ተወጠዋል ሻምበል አድማሱ አለሙ ታየ ያለቸው ከፍተኛ የሞያ ዘርፎች መካከል
1. አለማቀፍ የፈንጂ ማምከን ባለሞያ በመሆን ለ6 ዓመት አገልግለዋል ( በማኑዋል ፣ሜካኒካል ፣ፈንጂ አነፍናፊ ውሾች ፈንጂ ማፅዳት እናማስወገድ)
2. የጆግራፊ ወይም የቶፖግራፊ ባለሞያ
3. ወታደራዊ ማህንዲስ (ተዋጊ መሀንዲስ ) ጥምር ባለሞያ ነቸው።
ነገርግን በወቅቱ የነበረው አገዛዝ ምርጫ ዘጠና ሰባት (97)ተከትሎ በተፈጠረዉ ግርግር የቅንጅት ደጋፊ ነህ በማለት አንዳንድ የድርጅቱ ከፍተኛ ተልኮ አስፈፃሚ አመራሮች ባሳደረባቸው ተፅኖ እና ተንኮል ፅህፈት ቤቱን ታህሳስ 2000 ዓ/ም በመልቀቅ ለአስር አመት ለስደት እና ለእንግልት ተዳርገዋል በ2010ዓ/ም የመጣውን ለውጥ ተስፋ በማድረግ 2013 ዓ/ም ወደሀገር በመመለስ የግል ኑሯቸውን ለመምራት በትውልድ አካባቢያቸው አማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ አገዛዙ ደህንነቶች በሚያደርጉባቸው ክትትል አላስቀምጥ እንዲሁም ማሸማቀቅ በአማራ ክልል የተከሰተውን ቀውስ በማስመልከት ማንነት ተኮር እንዲሁም ያላቸውን የሞያ አቅም እና ችሎታ በመፍራት ከነሀሴ 3/2015/ ዓ/ም በአገዛዙ ማጎሪያ ቤቶች በግፍ እስር እና የህመም ስቃይ እያስተናገዱ ይገኛሉ።
አሁንም በቂ ክትትል እና ህክምና እንደሚያስፈልጋቸዉ ቤተሰቦቻቸዉ ለሚዲያችን ተናግረዋል።
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አባ ናደው የተገኙ ድሎችን አስጠብቆ አዳዲስ ድሎችንም እያስመዘገበ ቀጥሏል!
በሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎችና ታዳጊ ከተሞች:ኮን፣እስታይሽ፣ሃሙሲት፣አሁንተገኝ፣ ቀበሮ ሜዳ እና ሌሎች ታዳጊ ከተሞች በምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ገብተዋል:: እነዚህ ድሎች እየተመዘገቡ ያሉት አዲስ በተደራጀው በኮሩ ሰብሳቢ በሻለቃ ሃብቴ እባቡ እና በወታደራዊ አዛዡ አርበኛ ተመስገን አለባቸው የሚመራው የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች ሲሆን የዞብል አምባ ክፍለጦር አሃድ የሆነችው 5ኛ ሻለቃም የበኩሏን ጉልህ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች::
ተጋድሎው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ዳውንት ወረዳ ሙሉ ለሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ነው:: ደላንታ ወረዳ ከወረዳ መቀመጫው ወገልጤና ከተማ ውጭ ሙሉ ለሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ነው:: መቄትና ጋሼና ከከተሞቹ ውጭ ያሉ ቀበሌዎች 100% በምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ናቸው:: ሌሎች ቁልፍ ወታደራዊ ቦታዎችም በቅርቡ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ይሆናል::
ከዘመቻ አባናደው በድል መጠናቀቅ በኋላ በርካታ ቁጥር ያለው እግረኛና ኮማንዶ ሰራዊት ወደ ቤተ-አማራ በማስገባት በመካናይዝድና በአየር ሃይል በጄትና በድሮን ታግዞ በሙሉ አቅም ወደ ማጥቃት የገባውን የፋሽስቱን ሰራዊት ምሽግ ለቆ ወደ ፋኖ ቀጠናዎች እንዲገባ በማድረግ በአውደ ውጊያ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም በመማረክ ከአውደ ውጊያ ውጭ በማስኮብለል ብትንትኑን እያወጣነው እንገኛለን::
ፋሽስቱ ብልፅግና በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ እና ደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ምስራቃዊ ቀጠናዎች እስከ አፋር አጎራባች አካባቢዎች ባለፉት አምስት ቀናቶች ከባድ ማጥቃት ቢያደርግም በምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር በኮሩ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ደባሽ መምሬ እና በኮሩ ዘመቻ አርበኛ እንድሪስ ጉድሌ አጋፋሪነት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው አሳፍረው በዘረራ ቀጠናውን ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና
በሁለቱ ክፍለ ጦሮች በተውጣጡ የአሳምነው ልጆች የጠላት ኃይል ድባቅ ተመታ!!
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው እዝ አፄ ዘርያቆብ ፩ ኮር ከአፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር እና ከናደው ክፍለ ጦር በተወጣጡ የአሳምነው አናብስቶች ከሁለቴና ከዛም በላይ በተጠና ልዩ ኦፕሪሽን የ101ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ በሁለት መኪና ሆኖ ከሬማ ተነስቶ ወደ መርሃቤቴ በመጎዝ ላይ እያለ በአገሪት ቁማባ ቀበሌ ላይ በደፈጣ ውጊያ አይቀጡ ቅጣት ተቀጣ።
የአብይ አህመድ ጦሩ በመራቤቴ አውራጃ ከተለያዩ ቦታዎቹ ጡት ቆራጩን አረመኒያዊ ኃይል በማምጣት ያላሰበው የጦር ስልት የለም ሆኖም ግን የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር እና ከናደው ክፍለ ጦር በወሰዱት የደፈጣ እርምጃዎች እየተቀጣ ይገኛል።
በሌላ ዜና ይበንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ ጡት ቆራጩ ኃይል በኤፍራታ ግድም ወረዳ በዚህ ሳምንት በይፋ የኦሮሚያ ባንዲራ በማውለብለብ ከአጣዬ ከተማ ተነስቶ ወደ በርግቢ ካንፑ በመገንባት የአማራን የጥላቻን አይን ያሳየበት ከመሆኑም አንፃር በትናንትናው ማለትም በቀን 24/02/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ደመላሽ ሻለቃ ፋኖዎች ይገኛሉ በተባለው ቦታ በሰራባ ወርዶ ቁንዲ በምትባል ቦታ ዘልቆ በመግባት በማህበረሰቡ ላይ ዲሽቃ ለሶስት ስዓት ያህል በመተኮስ ላይ እያለ የአያሳምነው አናብስቶች በወሰዱት አጣፋ ምላሽ ዕራሱን ለማዳን ወደ መጣበት እንዲመለስ ተደርጓል።
መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
የነቁ ወንድሞቻችን ዛሬም በክብር እየመጡ ነዉ!!!
ዛሬ ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ዳንግላ ከተማ ከሚገኘዉ የጠላት ካምፕ በመዉጣት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይልን ከተቀላቀሉት ዉስጥ የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ አባል ሁነዉ መታገል የፈለጉ ሁለት ወንድሞቻችን በሰላም እና በክብር ብርጌዳችንን ተቀላቅለዋል።
ሰበር ዜና
በሌሊት ወደ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቀጠና የገባው የአገዛዙ ጡት ቆራጭ ሀይል ተመታ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የፋሲለደስ ብርጌድ ጀግኖች ዛሬ ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ከጠዳ እና ጎንደር ከተሞች ተወጣጥቶ በሌሊት መረጃ አጥፍቶ ወደ ቀጠናው የገባው የአገዛዙን ጡት ቆራጭ ሀይል ልዩ ስሟ ወይንየ ላይ ተመትቶና ተዋርዶ ተመልሷል።
አገዛዙ አሁን ላይ ቀቢሰ ተስፋ አድርጎ በሌሊት ማጥቃትን እየተጠቀመ ቢገኝም ከሞትና ከሸንፈት ግን መዳን አልቻለም ።
የፋሲለደስ ብርጌድ አባላት ዛሬ ወደ እነርሱ ቀጠና የመጣውን የአገዛዙን ሀይል
3 ሙት
5 ቱን በማቁሰል እርምጃ ሲወስዱበት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ በመግባቱ ያመጣውን ሀይሉን ሰባስቦ እግሬ አውጭኝ ፈርጥጦ ወደ መጣበት ተመልሷል።
በተመሳሳይ ዜና ዛሬ ቡርቧክስ ቀበሌ ላይ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆነችው ቃኘው ብርጌድ በቀጠናው ለመንቀሳቀስ የሞከረውን የአገዛዙን ቅልብ ሀይል በቀይ ጥይት ቁርስ አቅምሶ ሙትና ቁስለኛውን እየጎተተ እንዲሄድ አድርገውታል ።
በሁለቱም አውደ ውጊያ ጠላት ያልጠበቀው ነገር ገጥሞት ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ሽንፈት ደርሶበት እኛ ወንድሞቻቸው ነን አይምቱን አይግደሉን ተገደን ነው የመጣን መንግስት ነገ ይወድቃል እኛ እና እናንተ ግን አብረን እንኖራለን እያሉ እንዲጠፋ የወሰኑበትን ማህበረሰብ እየለመኑና እየተማፀኑ ወደ መጡበት ተመልሰዋል ።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጥቅምት 25/2018 ዓም
ዛሬ በ 25/02/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር ጃዊ መተከል ቀጠና የሻለቃዎች ጥምረት ባደረጉት የደፈጣ ዉጊያ በጣላት ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።
ብሔራዊ ተብሎ ከሚጠራዉ ቀጠና ላይ በተደረገ ዉጊያ ጠላትን ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
በሌላ ዜና አረመኔው የመንግስት ስርዓት ተላላኪ ሰራዊት በገባበት ቀጠና ሁሉ በንፁሃን ላይ የግድያ፣ የዘረፋ ፣ የድብደባ እና መሰል አፀያፊ እኩይ ተግባራትን ፈፅሟል።
1.ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ላይ ባህር ዳር የሚኖር ዘይኑ የሚባል ሙስሊም በአረመኔው መንግስት ሰራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ተረሽኗል።
2.ደሳለኝ ጥላሁን የተባለ የባምቡልክ ቀበሌ ነዋሪ በግፍ ተረሽኗል። እንዲሁም በዚሁ ቀጠና ከአንድ ግለሰብ 20,000 ብር ዘርፈዉ ወስደዋል። የባምቡልክን ጤና ጣቢያ መድሃኒት በማዉደም ሰራተኞችን እንዳትሰሩ በማለት አንገራግረዋል።
3.ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ላይ የቀን ሰራኞችን በማፈስ ፋኖ ማርከናል እያሉ የቂልነት አስቂኝ ድራማ ሰርተዋል።
4.በገቡበት ቀጠና ሁሉ በተለይ የተዘጉ ቤቶችን በመክፈት ያገኙትን እቃ ሁሉ ዘርፈዋል።እንደ ወርቅ እና ብር መሰል ጌጣጌጦችን ወስደዋል።
4.የማህበረሰቡን አዝመራ የምሽግ መቆፈሪያ እና የአስከሬን መቅበሪያ አድርገዉታል።
5.ከወፍጮ ቤት በመግባት ናፍታ ቀድተዉ ወስደዋል።
6.ቁስለኛ በመያዝ አለም አቀፍ የጦርነት ህግ በመጣስ በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽነዋል።
7.ፊልፊል ቀበሌ ላይ የጤና ኬላ ሰራተኞች ቤት በመግባት ከልብስ ጀምሮ እስከ ትልልቅ እቃዎች ድረስ ዘረፋ ፈፅመዋል።
ሰበር ዜና
ከሬማ ወደ መርሀ-ቤቴ አለም ከተማ በሁለት ተሽከርካሪ ተጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ የ101ኛ አየር ወለድ ኮማዶ ክፍለጦር በአፋብኃ ተደመሰሰ።
በአፋብፋ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ ፊትአውራሪ ባዩ አለባቸው የተመራው ይህ ልዩ ኦፕሬሽን መነሻውን ሬማ ከተማ መድረሻውን መርሀ-ቤቴ አለም ከተማ በማድረግ በሁለት ተሽከርካሪ ተጭኖ በንቀሳቀስ ላይ እያለ " አገሪት ቁማባ ቀበሌ" በተባለ ቦታ በተወሰደ ድንገተኛ ጥቃት ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል።
በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ከናደው ክ/ጦር እና ከአፄ ይኩኖ አምላክ ክ/ ጦር በተወጣጡ የልዩ ኦፕሬሽን አባላት አማካኝነት ከረዱ 5:00ሰ ሰዓት ላይ በተወሰደ በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳይቀር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል።
ዝርዝሩን የምንመለስበት ይሆናል።
መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
+2
የህዝብ ዉይይቶች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል‼️
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዓፄ ይኩኑ አምላክ ከፍለ ጦር የጠላትን እቅድ ለይቶ ከማዉጣት ጎኖ ለጎን ማህበረሰቡን ማወያየት ቀጥሎበታል።
በኤፍራታ ግድም ወርዳ የሉልጌ ሰረት ቀበሌ የህዝብ ሰፋ ያለ የህዝብ መድረክ በመፍጠር የትግሉን አጀማመርና አሁን የደረሰበትን የትግል ደረጃ ግልፅ በማድረግ፤ ሰፋ ያለ ዉይይት ተካህዷል።
እንመክራለን፣እንወያያለን፣እንደራጃለን፣እናቅዳለን፣ጠላትን ድባቅ እንመታለን።
መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና
በሁለቱ ክፍለ ጦሮች በተውጣጡ የአሳምነው ልጆች የጠላት ኃይል ድባቅ ተመታ!!
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው እዝ አፄ ዘርያቆብ ፩ ኮር ከአፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር እና ከናደው ክፍለ ጦር በተወጣጡ የአሳምነው አናብስቶች ከሁለቴና ከዛም በላይ በተጠና ልዩ ኦፕሪሽን የ101ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ በሁለት መኪና ሆኖ ከሬማ ተነስቶ ወደ መርሃቤቴ በመጎዝ ላይ እያለ በአገሪት ቁማባ ቀበሌ ላይ በደፈጣ ውጊያ አይቀጡ ቅጣት ተቀጣ።
የአብይ አህመድ ጦሩ በመራቤቴ አውራጃ ከተለያዩ ቦታዎቹ ጡት ቆራጩን አረመኒያዊ ኃይል በማምጣት ያላሰበው የጦር ስልት የለም ሆኖም ግን የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የዓፄ ይኩኑ አምላክ ክፍለ ጦር እና ከናደው ክፍለ ጦር በወሰዱት የደፈጣ እርምጃዎች እየተቀጣ ይገኛል።
በሌላ ዜና ይበንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ ጡት ቆራጩ ኃይል በኤፍራታ ግድም ወረዳ በዚህ ሳምንት በይፋ የኦሮሚያ ባንዲራ በማውለብለብ ከአጣዬ ከተማ ተነስቶ ወደ በርግቢ ካንፑ በመገንባት የአማራን የጥላቻን አይን ያሳየበት ከመሆኑም አንፃር በትናንትናው ማለትም በቀን 24/02/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ደመላሽ ሻለቃ ፋኖዎች ይገኛሉ በተባለው ቦታ በሰራባ ወርዶ ቁንዲ በምትባል ቦታ ዘልቆ በመግባት በማህበረሰቡ ላይ ዲሽቃ ለሶስት ስዓት ያህል በመተኮስ ላይ እያለ የአያሳምነው አናብስቶች በወሰዱት አጣፋ ምላሽ ዕራሱን ለማዳን ወደ መጣበት እንዲመለስ ተደርጓል።
መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም
+4
ትናንት ጥቅምት 24/2018 የተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተነገረ።
በምስራቅ አርሲ ከአቦምሳ ከተማ 12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትኘው ገዶ በምትባል ቀበሌ ውስጥ በአጨዳ ላይ እያሉ ትናንት ጥቅምት 24/2018 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ 5 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች መገደላቸውን መዘገባችን ይታወቃል።
በግፍ የተገደሉት ዛሬ አቦምሳ እንደተቀበሩ ከስፍራው መረጃውን አግኝተናል።
የተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ስም ዝርዝርም
1.ይርጋ ሲሳይ
2.የሺጥላ ሲሳይ
3.ጥበቡ ዝቅአርጋቸው
4.አሞኜ ኃይልዬ
5.ንጉሴ ከበደ
ከታች በምስሉ እንደምታዩት ስርአተ ቀብራቸው ሲፈፀም ነው።
