ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more3 721
Subscribers
+4524 hours
+1767 days
+1 15530 days
Posts Archive
ሰማታ ይሆን እንዴ?
ቅንጭሪት አያሌው መንበሩ ምንም እንኳን ደቡብ ጎንደርን እንደ ጋሽ መንበሩ ማሳ እያየች እኔ ጎልጉዬ ካልዘራሁበት መሬት እያፈራም ወደማለቱ ደርሳ ነበር።
ይህች ቅንጭራም ከአርብ ገበያ አፈርናዋት ቀበሌ ተንደርድራ የወልቃይትን ሰሊጥ መዝገንን የመጨረሻ ህልሟ ያደረገች የከርሷ መናኝ ሰምታ ይሆን? ደቡብ ጎንደር የቅንጭሪትን አለቆች አርባ አለንጋ እየገረፉለት ነው። እንግዲህ እሪሪሪ በየ ቅንጭሪት! ለማነኛውም እኛ ከግንባር መሬት ላይ ያለውን እውነት አብረን ከትግል ጓዴቻችን ጋር እውነተኛው የፋኖ መርጃ ስናደርሳችሁ ከምንም በላይ ክብር ይሰማናል እና አላችሁን ወይ ቤተሰብ ይወዳጁን አንድ አማራ እስከ እለተ ምፃት ድርስ
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር ድልን ተቀዳጀ።
ዛሬ የካቲት 02/2018 ዓ.ም የተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ወልቃይት ብርጌድ አባሎች ከእስቴ ወረዳ መካነ እየሱስ ከተማ ተነስቶ ወደ ልዋየ እንቅስቃሴ ላይ የነበረን የአገዛዙ ኃይል ላይ እርምጃ የወሰደች ሲሆን፡በዚህም
01--------ዲሽቃ
01-------ብሬን
10-----ክላሽ ኮፕ
4------አብራረው
01------የድሽቃ አፈሙዝ
በርካታ ያልተቆጠረ ተተኳሽ ማርካ ታጥቃለች ሲል የኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል።
###
በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በዛሬው ዕለት በደቡባዊ ጎንደር ዞን 2 ዲሽቃዎችን ከጠላት ማርኳል። በተመሳሳይ በላይ ዘለቀ ዕዝም 2 ዲሽቃዎችን በዚሁ ቀጠና ከጠላት ማርኳል። ጠቅለል ሲል 4 ዲሽቃ በሰሜን አማራ ቀጠና ናደቡባዊው አከባቢ ተማርኳል። ከዚህ በተረፈ የተማረከው ብሬን ፣ ስናይፐር ፣ ክላሽንኮቭ ገና በቆጠራ ላይ ያለ ሲሆን የተጣራ ውጤቱን ይዘን እንመለሳለን።
አራት ዲሽቃን ምርኮ ጨምሮ ጉድ የሚያስብሉ የድል መረጃወች ✊✊
፨ ጋይንት ሁለቱም ወረዳወች ነፃ ወጥተዋል። ትልቁ ማረሚያ ቤት ተሰብሯል። ከ 200 በላይ ክላሽን ጨምሮ ስናይፐርና መትረጊስ ተማርኳል።
፨ አርማጭሆ ማሰሮ ደምብ የነበረው ሚሊሻና አድማ ብተና ሙሉበሙሉ እጅ ሰጥቷል። በግሉ ደም ያለበት ተደ#ምስ#ሷል። በተመሳሳይም ከ 200 የሚበልጥ ክላሽ ተማርኳል።
፨ ጣቁሳ ድኩል አርባ ላይ ምሽጎቹ ፈራርሰው ተከቧል። እጅ ለመሴጠት እየተሰናዳ ነው።
፨ እስቴና ጋይንት ጫፍ ላይ ሌላውን መሳሪያና ተተኳሽ ትተነው አራት ዲሽቃ ተማርኳል። አራት ✊ ተራራው ራስ ጉና አንድ፣ እስቴ ዴንሳ ሁለት፣ ደጄን ብርጌድ አንድ ማርከዋል።
፨ በለሳ ያለው ሀይል ለቆ ሲወጣ ከጀርባው በተደረገበት ቆረጣ ከ 25 በላይ የሚሆኑ መካላከያ ከጥቅም ውጭ ሁነዋል። የተረፉት ማክሰኝት ገብተዋል።
ፋኖነት✊✊
አማራነት✊✊
ብሩህ ተስፋ✊✊
+2
የጀግንነትና የፅናት ተምሳሌቶች
የአማራ እናት "አምጣ የወለደቻቸው ጀግኖች አርበኛ ሽመልስ ንጉሴ እና አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ በጦር ሜዳ ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን፣ በሁሉም ስብዕናዎች የተገነቡ እንደ እሳት የሚነድ የትግል ወኔ ቢኖራቸውም፣ ያ ወኔ በእውቀትና በአስተሳሰብ የተገራ ፈጣሪ የሰጣቸው የመልካምነትና የትሕትና ጸጋ ያላቸው፣ የሸዋ ፋኖ ጠንሳሾችና መሠረት ጣዮች እነዚህ አርበኞች ዛሬ ለደረሰው የፋኖ ትግል ስር የሰደደ መሠረት የጣሉ ጎልቶ የሚታይላቸው።
ትግሉ ገና በጅምር በነበረበት ግዜ ብዙዎች ግራ በሚጋቡበት ወቅት ሳይሰለቹና ተስፋ ሳይቆርጡ መዋቀራቸውን የበርሃው ቃጠሎ፣ የተራራው ቁልቁለት እና ብርዱ ሳይበግራቸው ለዓላማቸው የቆሙ
የጂኦግራፊያዊ የትግል ስፋት የጀግኖቹን የትግል አሻራ ከኤፍራታ እስከ ደራ፣ ከከሰም እስከ መንዝ ድረስ ባለው ስፋት የሕዝብን አንድነት በመፍጠርና ታጋዮችን በማደራጀት ረገድ የነበራቸው ትግላቸው በአንድ መንደር ያልተገደበ፣ መላውን የሸዋን ፋኖ ያነቃቃው የታሪክ ተተኪነት (የሚኒልክ ልጆች) የሚኒልክን ታሪክ እየደገሙ ያሉ የሸዋ አናብስቶች።
እንደ ዳግማዊ ምኒልክ ሁሉ ለሀገርና ለወገን ሉዓላዊነትና ክብር የሚቆሙ። መስዋዕትነትን በመክፈል ረገድ ወደ ኋላ የማይሉና የታሪክ አደራን የተረከቡ አርበኛ ሽመልስ ንጉሴ እና አርበኛኢሳያስ ደመቀ የፋኖን ትግል በፅኑ መሠረት ላይ እንዲቆም ያደረጉ፣ በሰውነት ባህሪያቸው የተመሰገኑ እና በጀግንነታቸው የጥንቱን ታሪክ ያደሱ የዘመኑ ጀግኖች ናቸው ይቀጥላል ....!
+2
ታጭዶ የተከመረው የጠላት መሳሪያ‼️‼️
በዛሬዉ ዕለት ፓዊ ወረዳ መንደር 21 ቀበሌ የተማረኩ የጦር መሳሪያ በከፊል !!!
በመተከል አዉራጃ ፓዊ ወረዳ ፋኖ የተቆጣጠራቸዉ ቀበሌዎች መንደር 29፣28፣12፣11፣26፣24፣17፣21 ናቸዉ።
አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ-ዕዝ 105ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
#የ3ዕዝ_ጥምር_ተጋድሎ💪
በመደራጀት ላይ ያለው ራስ አንችም ክፍለ ጦር ዘመቻ ማንደፍሮ ሙላቴ ንፋስ መውጫ ላይ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::
የአማራ ፋኖ ብራሔዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር በመደራጀት ላይ የምትገኘው ራስ-አንችም ክፍለ ጦር የክፍለጦሩ ዘመቻ በነበረው "ማንደፍሮ ሙላቴ" የተሰየመ ግዳጅ ከሌሎች የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እና በላይ ዕዝ የተለያዩ አሃዶች ጋር በመሆን በደቡብ ጎንደር ጋይንት ንፋስ-መውጫ ከታማ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ።
የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ በሆነው አርበኛ ሙቀት ሞላ መሪነት ከሌሎች ወንድም አሃዶች ጋር በማስተሳሰር ግዳጁን የመራ ሲሆን በርካታ የጠላት ዘብ ተደምስሷል ፣ በርካታው ምርኮ የተደረገ ሲሆን ብዙዎቹ ደግሞ ቀስለዋል።
አጠቃላይ ግዳጁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ድርጅታዊ አንድነትን በእጅጉ ያስመሰከረ ሲሆን የሶስቱም ዕዝ አሃዶች የድሉ ባለቤት ሆነው ውለዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
02/ዐ6/2018 ዓ.ም
#አትፈልጉ_ከፋኖ_ጋር_ናቸው‼️
የአገዛዙ ኃይል 25ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት 2ኛ ሻምበል አባል የሆኑት
👉መሰረታዊ ወታደር ከድርና
👉መሰረታዊ ወታደር ሰይፕ የተበሉ የአምቦ ልጆች ፈለገብርሀን ልዩ ስሙ ኩሪ ሜዳ ከመሸገው የአገዛዙ ኃይል በመክዳት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮርን ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል ሲሉ አናብስቶች ለንስር አማራ ገልፀዋል‼️
02/ዐ6/2018 ዓ.ም
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ✊
ትናንት በ''ሥማዳ'' የጀመረው አኩሪ ድል ዛሬ በ''ዘመቻ መንግሥት ጥላኹን'' ሥም በእሥቴ መዳረሻ በአኩሪ ድል ሲደገም በጀነራል ነጋ ተገኝ መዳረሻ ደራም ላይ እየተሰለሰ ይገኛል❗
[የካቲት 02/2018ዓ.ም]
የካቲት 02/2018ዓ.ም
01. እሥቴ መካነ ኢየሱስ ከተማ
✅ጉና ክፍለ ጦር፦
👉እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ
👉ገብረ መሥቀል ብርጌድ
👉አንዳ ቤት ብርጌድ
👉መቅደላ አምባ ብርጌድ
👉ገብረ መሥቀል ብርጌድ እና
✅ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
ብረትን መቀጥቀጥ እንደ ጋለ ነው ይሉት ብሒለ ዓምሐራን ዘረ ውባንተዎቹ/ፈለገ ውባንተዎቹ መንትያ ክፍለ ጦሮች የተገበሩት፦
''ከዓምሐራ ሠማይ ሥር ዘራፍ ያለው ማን ነው?
ያ ውብ-አንተ አባተ የአሣምነዉ ልጅ ነው''።
በማለት ነበር። ሥማዳ ላይ በተደረገው ውጊያ ጠላቶቹን ረፍርፎ በጀግንነት የክብር መሥዋዕትነትን በተቀበለው አርበኛ ''መንግሥት ጥላኹን'' ሥም በእልህና በቁጭት ጠላትን ከሕይወት መዝገብ ሲሰርዙ ውለዋል። ዘመቻ መንግሥት ጥላኹን በተሳካ ሁኔታ የጠላትን አንገት አሥደፍቶ የወገንን ወኔ ሞልቶ ዓምሐራነትን በአሸናፊነት መንፈሥ በድል ሲተነፍሥ ውሏል። በዚህ ውጊያ ጉና ክፍለ ጦርና ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ጠላትን ምሽግ ካሥነቀሉት በኋላ ዓቢይ ያድነኛል ወዳለበት ቦታ ሁሉ እግሬ አውጭኝ ሲል ወደ ደብረ ታቦር ሲፈረጥጥ በአርበኛ ተመሥገን እና አርበኛ ያብባል ፈለቀ የሚመራው ተራራው ራሥ ጉና ክፍለ ጦር ከጉናዋ መቅደላ አምባ ብርጌድ ጋር በመሆን የጠላትን በር ጠርቅመውበታል።
ጠላት የመዋጋት ወኔ ክዶት በእሣተ ገሞራው የአማራ ፋኖ ሲምበረከክ ውሏል። በዚህ ውጊያም ብዛት ያለው ምርኮ ሲገኝ ከምርኮቹ መካከልም፦
👉05 ብሬን
👉02 ሥናይፐር
👉02 ዲሽቃ
👉አንድ ፓትሮል ሙሉ ክላሽ
👉አንድ ፓትሮል ሙሉ የክላሽና ብሬን ተተኳሽ
👉03 ሲኖ ትራክ ምርኮኛ ታጣቂ
👉ብዛት ያለው ታጣቂ የተደመሰሰ
👉87 የፖለቲካ እሥረኞች ከግዞት ነጻ የሆኑበት
👉መካነኢዬሡሥ ከተማ ከአገዛዙ ነጻ የሆነበት...
በዴንሳ ተራራ ጠላት ሲረግፍ፣ ምርኮ ሲበዛ በተቃራኒው የዓምሐራ ፋኖ ዕይታው ከወረዳ፣ ዞንና ክልል አልፎ ዕይታውን ከክልሉ ውጭ ያደርጋል።
02. ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር
በደራ ምድር ከአምበሳሜ ወደ ሐሙሲት ጓዙን ጠቅልሎ የፈረጠጠው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ከቀኑ 11:00 ጀምሮ ''ግብጻዊት ማርያም እና ገነት ወንዝ'' ላይ የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሕዋሥ የሆነችው ጣና ብርጌድ ከፊት ዘግታ ሥትመታው ከኋላ ደግሞ አፈር ውኋ ዕናት ብርጌድ እና አምበሶ ብርጌድ በብርሐን ፍጥነት ደርሰው ጠላትን አይቀጡ ቅጣት እዬሰጡት ይጠኛሉ። የአቢይ አሕመድ ወምበር ጠባቂ ቡድን በዘረ ውባንተዎቹ በሁሉም የኮሩ መዳረሻ በተጠና ዕቅድ ሲገረፍ እሥከ ምሽቱ 01:00 ውጊያው የቀጠለ ሲሆን የዓምሐራ ፋኖ የበላይነቱን ወሥዷል።
የካቲት 01/2018 ዓ.ም
03. ሥማዳ/ወገዳ
በሥማዳ ወገዳ ከተማ 24:00 የፈጀ ውጊያ ቀንና ሌሊት ሲከወን የአገዛዙ ኮንክሪት ምሽጎች ተሰባብረዋል፣ የጠላት ኃይል ሙሉ በሙሉ ተደምሥሧል። በዚህ ውጊያ የጉና ክፍለ ጦር ሕዋሶች እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ እና ሐገረ ቢዘን ብርጌድ ተሳታፊ ናቸው። በቁጥር ደረጃ የተገኘው ድልም፦
✅265 ተደምስሷል
✅22 ተማርኳል።
✅ቁጥሩ ያልታወቀ በኖ የጠፋ አለ።
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕዝባዊነትን ባሥቀደመ መልኩ፣ ሰራዊቱን እያሰለጠነና እያደራጀ፣ የሕዝብ አደረጃጀቶችን እያዘመነ ፊቱን የባርነት ቀምበር ወደ ጫነብን የኦሕዴዶ አገዛዝ በሙሉ ልብ ያዞራል።
ክብርና ሞገሥ ለዓምሐራነት ደማቸውን ላፈሰሱ፣ አጥንታቸውን ለከሰከሱና ክቡር የሕይወት መሥዋዕትነትን ለተቀበሉ የነጻነት ታጋዮች ኹሉ ይሁን።
የትግል መለያ ሊትመሳችን ምልዑው ሜ/ጀነራል ውብ-አንተ አባተ ነው❗
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗
ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA✊👊
አፋብን ሰሜን ዓምሐራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
ቋሚ ምሥል፦ በሥማዳ ወገዳ ከተማ ሸረፍ ጎዴ ላይ በጀግንነት ጠላቶቹን ረፍርፎ በክብር የተሰዋው ሻለቃ መንግሥት ጥላኹን
የብልፅግና ስርዓት ያሰለጠናቸው ሽፍቶችን የማፅዳት ዘመቻው ተጠናክሮ ቀጥሏል‼️
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ቃኝ የህዝብ ሰላም የሚነሱ ፀረ-አማሮችን ደምስሳለች!!
በፋኖነት ስም ብልፅግና ባሰማራቸው ዘራፊ እና ገዳይ ቡድኖች ላይ የደጋው መብረቅ ኮር ቃኝ የማያዳግም እርምጃ ወሰደች። የአማራን ሕዝብ ትግል ሕዝባዊ ቅቡልነት እንዳይኖረው በፋኖ ስም ጠላት ብልፅግና በዘረፋና በንፁሃን ግድያ እና እገታ ያሰማራቸው የጠላት አንጃዎች ላይ ከበባ በመፈፀም የሽፍቶቹ መሪና አምስቱ(5) ግብረአበሮቹን ጨምሮ ሲደመሰሱ፤ቀሪዎች ተማርከዋል።
በዋድላ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ከጠላት ብልፅግና ጋር እየተናበቡ ሲዘርፉ እና ሕዝብን ሲያሰቃይ የነበረው የቡድኑን መሪ አዲስ ደምሌን ጨምሮ አምስት ግብረ አበሮቹ ጋር ሲደመሰሱ ከስርዓቱ የሚላክላቸው በርካታ የክላሽ ተተኳሽ ጭምር ተማርኳል።
ከዚህ ቀደም ጥር 22/2018ዓ/ም በዋድላ ወረዳ 011 ቀበሌ ከ10 በላይ የአርሶአደር የቁም ከብት፣ 4 ንፁሃንን የገደለ እና ሁለት ንፁሃንን ያቆሰለ ሲሆን የደጋው መብረቅ ኮር ቃኝ ባደረገችው ከበባ የተሳካ ኦፕሬሽን በመስራት ወደ ሲዖል ሸኝታቸዋለች። የጠላትን አጀንዳ በሚያሰፈፅም ማንኛውም አንጃ ላይ እርምጃችንን አጠናክረን የምንቀጠል መሆኑን እና ሕዝባዊነትን የሚያስቀድመው ትግላችን አሁንም በሌቦች፣ ዘራፊዎች እና ትግልን በምስር ወጥ በሚሸጡና በሸጡ ሀይሎች እርምጃችንን የምንቀጥል መሆኑን እያሳሰብን ከወዶ ገቦች(ሞተ በፍቃዱ) ጭምር እጅ እናሳጥራለን።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ መምሪያ
የካቲት 2/2018 ዓ.ም
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የፋኖ አመራር ቤተሰቦችን መዝረፍ ማሰር ማሳደዱንና ማፈናቀሉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል‼️
አህመድ ሱማሌው ይባላል የባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረውና የምስራቅ አማራ ኮር 1 ዘመቻ መሪ የሆነው የአርበኛ እንድሪስ ጉደሌ ታላቅ ወንድም ነው:: የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ካድሬዎች የትውልድ ቀየውን አስለቅቀውት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ ህይወትን እየገፋ ባለበት ፋሽስቱ አገዛዝ አዲስ አበባ ላይ አፍኖ 1700000 (አንድ ሚሊየን ሰባት መቶ ሽ) ብር ቀምተውታል::
የአርበኛውን ወንድም የአገዛዙ ሰዎች አዲስ አበባ አፍነው በግፍ ከተቀበሉት ገንዘብ በተጨማሪም አሁንም ጦር ሃይሎች አስረው እየደበደቡትና ግፍ እየፈፀሙበት ይገኛል:: ይህ የሃገሪቱ መዲና ላይ የተፈፀመ ተግባር የብልፅግናን አገዛዝ አገር አቀፍ ዘረፋና ወንጀል በግልፅ የሚያሳይ መሆኑን ያሳበቀ ነው::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 2/2018 ዓ.ም
02/ዐ6/2018 ዓ.ም
አፋብን የሚያቆመው እንደለለ አስመሰከረ ።
የደቡብ ጎንደር ጀግኖቻችን ዛሬ ብልፅግናን እንደ ተልባ እያንጫጩት፣ እንደ ኑግ እየወቀጡት ሲውሉ ከአያሌው መንበረ እስከ ይርጋ ሲሳይ፣ ከአረጋ ከበደ እስከ ተመስገን ጥሩነህ ድረስ እለቅሶ ላይ ናቸው እያሱ አባተ አፈረሰው የተባለው ፋኖ ብልፅግናን አፈራርሶ ከብሬን እስከ ዲሽቃ ፣ከክላሽንኮብ እስከ ስናይፐር ፣ከብር እስከ መኪና ተረክቦ በቁሙ ገሎታል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄን (አፋብን ) ምድር ላይ የሚያቆመው ምንም ሀይል እንደለለ ከጎንደር እስከ ሸዋ ከወሎ እስከ ጎጃም ፣ ከጋንቤላ እስከ ወለጋ እያሳየ ምላሳሞች እየጮሁ ስራዎቻችን በተግባር እያስመሰከረ ጉዞውን ሲቀጥል ዛሬ የካቲት 2/2018 በመቅደላ አደባባይ ዘረ ውባንተዎቹ የአባቶቻቸውን ታሪክ በመድገም ለሸዋ ጓዶቹ እየመጣን ነው ፣ ለወሎዎቹ ጠብቁን አብረን እንጓዝ ፣ለጎጃሜዎቹ ባህር ዳር እንዴት ናት መልዕክት አስተላልፈው ውለዋል ።
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተሰጠ መግለጫ፦
ለሁለት ዓመት ከሰባት ወር ገደማ በአማራ ፋኖ ብርቱ ክንድ ሲቀጠቀጥ የከረመኔው አረመኔ ስርዓት፤ የፋኖን ሀይል ‹‹አዳክሜያለው›› እያለ የከሰረ ፕሮፓጋንዳ ሲሰራ ቢከርምም፤ ሰሞኑን በሁሉም የአማራ ቀጠናዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመታ ይገኛል።
ነጣጥለህ ምታው በሚል መርህ ሰሞኑን በሸዋ ወንድሞቻችን ላይ የተደራጀና የተጠናከረ ውጊያ ከፍቶ ንጹሀንን ዒላማ ያደረገ ጭፍጨፋ ቢፈጽምም፤ አይበገሬዎቹ የሸዋ አናብስቶች የስርዓቱን ኃይል እንደ ዘላን ላም ማርከው እየነዱ አሳይተውናል።
በተመሳሳይ መልኩ በጎንደር፣ በጎጃም እና በወሎ ቤተ አማራም ከፍተኛ መነቃቃትና ድርብርብ ጀብድ እየተሰራ የአረመኔው ስርዓት ዘቦች እየተገረፉ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም፤ የፋኖ ብርቱ ክንድ የበረታበት ሥርዓት፤ ሰሞኑን በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በሚደረገው ውጊያ፤ አንዳንድ ከተሞችን በውጊያ የተወሰኑትን ደግሞ ያለ ውጊያ እየለቀቃቸው ይገኛል።
ለምን ከተሞችን እየለቀቃቸው እንደሚወጣ ግልጽ የሆነ ነገር ባይኖርም፤ የተለያዩ መላምቶች ግን እየተሰጡ ይገኛሉ። የስርዓቱ ኃይል እየለቀቀ የሚወጣበት ምክንያት ተደርጎ እየተነገረ ያለው፤ በዋናነት የህውሐትና የሻዕቢያ ጥምር ሐኃል በሰሜን ምዕራብ አማራ በኩል ተከዜን ተሻግረው ለወረራ ሊመጡ ነው የሚል እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።
በምንም ይሁን በምን፤ እየተለቀቁ ያሉ ከተሞች እጣ ፋንታ ጉዳይ በአማራ ፋኖ እጅ ሆኗል። እነዚህ አሁን የስርዓቱ ኃይል እየለቀቃቸው ያሉ ከተሞች ስርዓቱ ይዞ በሚያስተዳድርበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ስርቆት፣ ዘረፋ፣ ግድያ፣ አስገድዶ መደፈር፣ ሙስና እና ሌሎች ብልሹ አሰራሮች በስርዓቱ ጋሻ ጃግረዎች ሲፈፀምባቸው የከረሙ ከተሞች ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ለሚኒሻ ደመወዝና ለመከላከያ ድጎማ የሚል ድርብርብ ወጭ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ሲያስተናግዱ የኖሩ አካባቢዎች ናቸው። ይህ ህጋዊና ህገወጥ ሌቦች ሲመዘብሩት የኖረ ማህበረሰብ፤ እንደ ገጠሩ ማህበረሰብ እና ፋኖ እንደተቆቆጣጠራቸው ከተሞች ነፃነቱን አግኝቶ የሚኖርበትን ቀን ሲናፍቅ የቆየ ማህበረሰብ ነው።
በመሆኑም ወደ ከተማው የሚንቀሳቀስ የፋኖ ኃይል በሙሉ የሚያደርገው እንቅስቃሴ፤ የተጠና እና የማህበረሰብ ልጅነትን ግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ግድ ይላል። በመሆኑም ከተሞችን በምንይዝበት ወቅት፤ መተግበር ያለባቸው መመሪያዎችና ጥሪዎች እንደሚከተለው ይቀርባል፦
1/ እነደሚታወቀው ቀጠናው ከ2008 ዓ.ም ሃምሌ ወር ጀምሮ ለተከታታይ አስር ዓመታት ያለ ዕረፍት በጦርነት እየወደመ የሚገኝ አካባቢ ነው። በመሆኑም ለፋኖ መገልገያ የሚውል የስርዓቱ ሐብት ካለ በተቋምና በበላይ አመራር ይሁንታ መሰረት መጠቀም የማይከለከል ሆኖ፤ ከዚህ በዘለለ ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ በእሳት ማቃጠል፣ማውደምና መዝረፍ ግን ፍፁም ለመንግስትነት ከሚታገል ኃይል የማይጠበቅ ተግባር መሆኑ ታውቆ፤ አንድም ንብረት በቃጠሎና በዘረፋ እንዳይወድም።
2/ በግል ቂም ተነሳስቶ ያለ ተቋም እና የበላይ ኃላፊ እውቅና፤ ማህበረሰብን አስሮ ማንገላታት ፍፁም የተከለከለ ነው። የተለየ የግል ጉዳይ ያለው አባል ካለ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ክስ መስርቶ አስፈርዶ በተቋሙ ማስቀጣት ይቻላል።
3/ ተቋምና የበላይ አካል በማያውቀው መልኩ፤ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰብ መርሐግብር (አስገድዶም ሆነ በፈቃደኝነትም ቢሆን) ገቢ መሰብሰብ ፍፁም የተከለከለ ነው። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና ከታመነበት፤ አስቻይነቱ በተቋም ተገምግሞ ህጋዊነቱን ጠብቆ መፈፀም ይቻላል።
4/ ለግዳጅ ወይም ለሌላ የግል ስራ በተቋምና በበላይ ኃላፊ የተፈቀደለት አካል ካልሆነ በስተቀር፤ ከተማ በማንኛውም ሰዓት ገብቶ መዝረክረክ ፍፁም የተከለከለ ነው። እንደ አስፈላጊነቱ ከከተማ ቅርብ እርቀት ተንቀሳቃሽ ካምፕ አዘጋጅቶ መቀመጥ ይቻላል።
5/ ሥርዓቱ የለቀቃቸው ከተሞች ላይ የድሮን ጥቃት ሊኖር ስለሚችል፤ ማህበረሰቡም አባሉም ባለመሰባሰብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ።
6/ለሥርዓቱ አገልጋዮች በሙሉ ለሚሊሻ፣ ለአድማ ብተና፣ ለመከላከያ ሰራዊት አባላትና በየደረጃው ላላችሁ የሲቪል አመራሮች በሙሉ፤ አስኪ በቃን ተገዳድለናል፤ በየቀኑ ዓላማ ቢስ ሞት ሞታችኋል፤ በእርግጠኝነት ለመማር ዝግጁ ከሆናችሁ እስካሁን በበቂ ሁኔታ ተምራችኋል፤ በመሆኑም ከእንግዲህ ወዲህ መገዳደል አቁመን በጋራ እንድንታገል የተለመደ ጥሪያችን እያቀረብን፤ መታገል ለሚፈልግ በፍላጎቱ እንዲታገል ለማይፈልግ ደግሞ መደበኛ ኑሮውን እንዲኖር እንደምንፈቅድ ማሳስብ እንወዳለን።
7/ለማህበረሰቡ በሙሉ በፋኖ ስም ለሚንቀሳቀስ አባላችን በሙሉ የተለመደውን ትብብር ማድረግ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አላስፈላጊ የሆነ ድርጊት የሚፈፅም አባል ሲኖር ግን አስፈላጊውን ጥቆማ በመስጠት እንድትተባበሩ እና ወንጀልን በጋራ እንድንከላከል ማሳሰብ እንወዳለን።
8/ከበላይ ዕዝ ጋር የጋራ ኮሚቴ በማዋቀር ስራችን የጋራ በማድረግ የምንስራ ይሆናል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ
የካቲት 02 ቀን 2018 ዓ.ም
ጎንደር-አማራ- ኢትዮጵያ
206ኛ ኮር በመተከል አውራጃ ፓዊ ወረዳ ቀበሌ 21 በካምፕ ውስጥ በተጠረነፉ ሚኒሻና አድማ በትኖች ላይ በተፈፀመ የከበባ ጥቃት 13 ክላሽ ማርኳል።
===================================
በመተከል አውራጃ ፓዊ ወረዳ ቀበሌ 21 በካምፕ በተጠረነፉ ሚኒሻና አድማ በትኖች ላይ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር እና 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ 3:00 ሰዓት ባደረጉት አውደ ውጊያ ከ50 በላይ ክላሽ 2 ብሬን የተማረከ ሲሆን የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ 13 ክላሽና 200 ጥይት የያዘ የብሬን ሸንሸል ማርከዋል።
እጅግ ፈጣን በሆነው አውደ ውጊያ የጠላትን አስክሬን ያዝረከረኩት 105ኛ እና 206ኛ ኮር በካምፑ የተጠረነፈውን የጠላት ኃይል ሙሉ ለሙሉ ደምስሰውታል። በሔዱበት ጠላትን በማናዘዝ አኩሪ ተጋድሎ የፈፀሙት የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ የጠላትን ጠንካራ ምሽግ በመስበር አውደ ውጊያው በድል እንዲጠናቀቅ የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት ተወጠዋል።
ድንበር አልባ ተንቀሳቃሽ ጦር የገነባው 206ኛ ኮር በዛሬው አውደ ውጊያ ይህንን ጠንካራ ወታደራዊ አቅም ያስመሰከረ ሲሆን ከ105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር አሀዶች ጋር አኩሪ ድል ያስመዘገበችው የ34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ መስዋትነት በመክፈል ጭምር ከጠላት ጉሮሮ 13 ክላሽ ጨብጣለች።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ጀኔራሎች ጭኖ ሲበር በነበረ አንቶኖፍ ላይ በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ጥቃት ተሰነዘረበት።
ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ክንፍ የሆነችዉ እሸት ክፍለ ጦር ጀኔራሎችን እና የብልፅግና ተላላኪ የሲቪል አመራሮችን አሳፍሮ ሲበር በነበረ አንቶኖፍ ላይ ጠቃት ሰነዘረችበት።
ጀኔረሎቹ እና የሲቪል አመራሮቹ ከ ሰቆጣ ከተማ የቆዩ ሲሆኑ ወደ ላሊበላ ኤሪፖርት (ሽምሽሃ)ቀበሌ ለመግባት በ 2 ክፍለ ጦር ታጅበዉ እየመጡ እያለም በ ሀይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እየተገረፈ እንደምንም ኤሪፖርቱ ላይ ቢደርሱም እሸት ክፍለ ጦርም ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጋለታለች።
ጀኔራሎችን ጭኖ የነበረዉ አንቶኖፉ በመጀመርያዉ በረራ ትንኩሳ ሲደረግበት አቅጣጫዉን ስቶ የበረረ ሲሆን በድጋሜ ተመልሶ ኤሪፖርቱ ጋር ያረፈ ቢሆንም በሁለተኛዉ በረራ በከባድ መሳርያ እገዛ እንደምንም ብሎ ያለፈ ሲሆን እግረኛ ሰራዊቱ ከከባድ መሳርያዉ በተጨማሪ በ 3 አቅጣጫ ቢዘረጋም በአንደኛዉ አቅጣጫ ዘርግቶ የነበረዉ ግትልትል ሰራዊት በተለምዶ ሳይና በር ላይ እምሽክ ተደርጎ ተበልቷል።
ትንቅንቁም በዛሬዉ ዕለት ማለትም የካቲት 2/2018 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን ብዛት ያለዉ የአገዛዙ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ሁኗል።
እሸት ክፍለ ጦር ከላሊበላ ኤሪፖርት(ሽምሽሃ) ቀበሌ በ10 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ እምትገኝ ክፍለ ጦር መሆኗም አይዘነጋም።
በመጨረሻም የእሸት ክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌም ''የአብይ አህመድ አፈ ቀላጤዎች በቅርቡ ከ ቱርክ እና ከአረብ አገር በ ክራይ በመጡ ድሮን እና ጀቶች በአየር ኃይል 90ኛ አመት ላይ ትርኢት ሲያሳዩ ''ሰማዩ የኛ ነዉ'' ያሉ ቢሆነም ሰማዩም ምድሩም የናንተ ሳይሆን የኛ ነዉ ሲል ተናግሯል''።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 2/2018 ዓ.ም
