ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more3 632
Subscribers
+124 hours
+3977 days
+1 06030 days
Posts Archive
ዕድሜ ልካቸውን ነብስ ለማዳን የሚሰሩት ወንድም እህቶቻችን ነብሰ በላው አገዛዝ በአማራነታቸው በግፍ የገደላቸው ዶክተሮች‼️
------
ኢትዮጵያ ወስጥ አንድ ዶክተር አስተምሮ ለማስመርቅ 27 ዓመት በላይ ይፈጃል። በአጠቃላይ ያሉት ዶክተሮች ለ130 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም አነስተኛ ይህም በሒሳብ ስሌት ቢቀመጥ አንድ ስፔሻሊስት ዶክተር በአማካይ ለአንደ ሚሊየን ሕዝብ እያገለገለ ነው ያለው ማለት ነው ። ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት ጦርነት በከፍተኛ ደረጃ የህክምና ባለሞያዎችን አስቀድሞ የመግደል የዘር ማጥፋት ስልት እየተከተለ ይገኛል። እረኛውን ምታው መንጋው ይበተናል የሚል የዘር ጨፍጫፊዎች የዘር ማጥፍት መፈክር እንደ ስልት የሚከተለው አብይ አህመድ አሊ ባለፋት ሰባት ዓመታት ብቻ እጅግ በጣም ብዙ የጤና ባለሞያዎች ተገድለዋል። ዕድሜ ልካቸውን ነብስ ለማዳን የሚሰሩት ወንድም እህቶቻችን ነብሰ በላው አገዛዝ በግፍ የገደላቸው የአማራ ዶክተሮች:-
1 - ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ :- እውቁ የሰርጀሪ ህክምና ባለሙያ ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ እሁድ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ የጠዋት ሩጫ በማድረግ ላይ ሳሉ ግድያ እንደተፈፀመባቸው ታውቋል።
2- ዶ/ር ኤልሳቤት ተሾመ :- በሚያዝያ 14 ቀን 2016፣ በደብረ ማርቆስ ከተማ (ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ)፣ የአብይ አገዛዝ ሀይሎች (ሚሊሻዎች) ዶ/ር ኤልሳቤት ተሾመ ከስራ ወጥታ ወደ መኖሪያ ቤቷ እየተመለሰች ባለችበት በጥይት መተው መግደላቸውን አረጋግጧል።
3- ዶ/ር ገብረ ሚካኤል ወልደ አማኑኤል :- ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ ከአለም ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ልዩ ስሙ ማጋስ ቀበሌ መሳለሚያ በተባለ ቦታ መከላከያ በሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ ጥዋት 2:30 በከፈተው ጥቃት የአለም ከተማ እናት ሆስፒታል ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ የሆነው ዶ/ር ገ/ሚካኤል ወ/አማኑኤል፣ የ1 ዓመት ጨቅላ ሕፃን እና ስምንት ሰዎች ተገድለዋል።
4- ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ
በጥር 24 ቀን 2017፣ የኦሮሞ ብልፅግና አገዛዝ ወታደሮች በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ የተባሉ ሰላማዊ ሰው መግደላቸውን ማወቅ ችሏል።
5- ዶ/ር ሜሪ አበበ በጎንደር ዩንቨርስቲ ጀማሪ ዶክተር።
6- ዶክተር ጥበቡ አለነ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የ2ኛ ዓመት የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ፕ/ት ሐኪም የነበረው ዶ/ር ጥበቡ አለነ ከሆስፒታሉ በር ፊትለፊት በአገዛዙ ተግድሎ ተጥሎ ተገኝቶል።
7- ዶክተር እስራኤል ጥላሁን በአገዛዙ ተረኛ በመሀል አዲስ አበባ ቦሌ በጥይት ግንባሩ ተመቶ የተገደለ።
8- ዶክተር ሜሮን ደምሌ:- አዲስ የተመረቀች የህክምና ዶክተር በጎንደር ዩንቨርስቲ በጠቅላላ የህክምና ዶክተርነት ስታገለግል የነበረች።
9- ዶክተር ፀጋሁን ስሜን ጥር 26/2018 ዓ.ም የአገዛዙ ቅጥረኛ ወታደሮች ከሚሰራበት ስፍራ እየደበደቡ ወሰዱት። በዕለቱ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ ቤተሰቦቹ ወደ ስፍራው በመሄድ አስክሬኑን እንዲውስዱ በገዳይ ኃይላት መጠየቃቸው ታውቋል።
10- ዶክተር አበኔዘር ጌታቸው
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ አመት የቀዶ ህክምና ተማሪ
11- ዶ/ር ሄኖክ ተስፋዬ ህዳር 21 /2016 ዓ.ም በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በምትገኘዉ ወገልጤና በተባለ ቦታ በአምቡላንስ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ተገደለ።
12- ዶ/ር በውቀቱ አንዳርጌ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 6ኛ ዓመት የሕክምና ዶክትሬት
ነፍስ በሰላም ትረፍ!!
ከአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር የፋኖ ሠራዊትን መልምሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መሰልጠን የምትፈልጉ ወጣቶች ከታች ባለው መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ወጣት መመዝገብ ይችላል።
1.ብሔር አማራ የሆነ/የሆነች
እድሜው ከ18 እስከ 45 ዓመት ድረስ የሆነ/የሆነች
2. ጾታ አይለይም ሴቶችን እናበረታታለን
3.ጤናው ሙሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች
4. ህዝቡን እና ድርጅቱን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል የሚፈልግ/የምትፈልግ
5.የመመዝገቢያ ጊዜ ከቀን 18/06/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 05 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ መመዝገብ ይችላሉ።
የምዝገባው ቦታ አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር በተቆጣጠራቸው ቀበሌ እና በማጀቴ ቀበሌ እንዲሁም ሠራዊት ባለበት ቦታ መጥተው መመዝገብ ይችላሉ።
አጼ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር እና ድርጅቱ መረጃ ከፈለጉ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን
0906039200
0905918609
ማሳሰቢያ፦ የቀድሞ የሠራዊት አባል የነበራችሁ በሙሉ በተለያዩ ምክንያቶች ከትግሉ እራሳችሁን አግልላችሁ የቆያችሁ አባላት መለሳችሁ ወደ ሠራዊቱ መቀላቀል የምትፈልጉ ከሆነ የመመዝገቢያ ቦታ መጥታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።
ክብር ለተሰዉት
ድል ለአማራ ፋኖ
የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ኃይል ንፁኋኖችን በመግደል ሀብት ንብረት በማውደም ጥብቅ ደኖችን ጨምሮ ፓርኮችንና ታሪካዊ ስፍራዎችን በእሳት አቃጥሎ በማውደም የሚፈፅመው የበቀል እርምጃ ተባብሶ ቀጥሏል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አባናደው ክፍለጦር የካቲት 15/2018 ዓ/ም ባካሄደው ውጊያ የጠላት አከርካሪን በመስበር አንፀባራቂ ድል መቀዳጀቱ ታውቋል።
ተጋድሎው የተደረገው በምስራቅ አማራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች መካከል አንዷ በሆነችው በአማራ ሣይንት ወረዳ ልዩ ስሙ በለጩማ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ነው።
በዚህ አውደ ውጊያ በሳጅን አባናደው ክፍለጦር ስር 4ኛ ሬጅመንት አባላት በወሰዱት የፀረ ማጥቃት እርምጃ ከ32 በላይ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አሳውቋል።
አገዛዙ በውጊያው ከተገደሉበት በተጨማሪ የቆሰሉበትን ከ23 በላይ ወታደሮችን በአምስት አምቡላንስ ጭኖ ወደ ለጋምቦ አቃስታ ከተማ ለሕክምና የወሰደ ሲሆን፡ ከቁስለኞቹ መካከል ስድስቱ የድሽቃ ተኳሾችና እረዳቶች ናቸው።
በአውደ ውጊያው ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችና ሌሎች ወታደራዊ ግብአቶች በፋኖ ተማርከዋል ብሏል አባናደው ክፍለጦር በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ።
በዚህ አውደ ውጊያ ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ከባድ ኪሳራን የተከናነበው የአገዛዙ ኃይል በአከባቢው ከ25 ጊዜ በላይ የሞርተር ድብደባ በመፈፀም ውድመት አድርሷል።
የሞርተር ጥቃቱ የተፈፀመው የአከባቢውን አየር ንብረት ለመጠበቅ ማሕበረሰቡ የደን ችግኞችን ተክሎበት በነበረ ማሣ ነው።
+1
አፋብን በላይ ዕዝ ዳ/ቴድሮስ 5ኛ ኮር መብረቅ ክፍለ-ጦር አዲዘመን ከተማ ውስጥ በሰራው አስገራሚ ኦፕሬሽን ቀንደ*ኛውን የሚነሻ አዛዥ በመ*ም*ታት ሙሉ ትጥቁን የማረከ*ችው ጀግና እህታችን ይች ነች 💪
ዳግማዊ ጣይቱ ብለንሻል✊💪
ለአመታት በግፍ እስር ላይ የነበረው ረ/ፕ ሲሳይ አውግቸው በዋስ እንዲለቀቅ ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከተወሰነና በዛሬው ዕለት ከቀኑ 11 ሰኣት ገደማ ሂደቱን ጨርሶ ከወጣ በኋላ ወድያውኑ በታጠቁና ጭምብል በለበሱ የመንግስት ኃይሎች መስታወቱ ጥቁር በሆነ መኪና ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱ ታውቋል።
#የጥንቃቄመልዕክት‼️
ከደቡብ አቸፈር እና ሰሜን አቸፈር የተውጣጣ ኃይል ወደ ሻሁራ ጉዞ ጀምሮ ሊበን ደርሷል።.
በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ ኮር + ጎጠግዕ በጌምድር ክፍለጦር ጥንቃቄ አይለያቹ 🙏
ባህር ዳር እየተከበበች ነው !!
የጣና ዳር ከተማዋና የክልሉ ርዕሰ መዲና ባህር ዳር በጎንደርም፣ በጎጃምም በኩል ቀለበት ውስጥ እየገባች ነው።
በደራ፣ ፎገራ፣ ከምከም፣ ጎንደር ዙሪያ፣ ደምቢያ፣ ጣቁሳ፣ አለፋ በኩል ሀይቁን ከቦታል ፋኖ። በጎጃም በኩልም በአዴት፣ መራዊ፣ አቼፈር በኩል ቀለበት ውሰጥ ናት።
አሁንም የምንለው ውጊያወች መደረግ ያለባቸው Significant ቦታወችን ለመቆጣጠር መሆን አለበት።
በዋናነት ክልሉ ላይ የዞን ወረዳወች ዙሪያና ባህር ዳር ላይ። ከዛ አዲስ አበባ ብቻ መሆን አለባቸው።
ብልፅግና በደብረታቦር ውጊያ በሀገሪቱ ታሪክ በአንድ ጀምበር የተጣለው የድሮን አረር ሪከርድ ይዞ ያንን ሁሉ ባሩድ ያወረደው ከተማው ቢያዝበት ብዙ ነገር እንደሚከስር ስለሚያውቅ ነው።
ተሳክቶ ፋኖ ወደ ከተማው ቢገባና ሁለት ቀናትን ቢቆይ የብልፅግና ራቁትነት ዓለም ያይ ነበር። አሁንም ትኩረታቹህ የ fb ሚዲያን ለማስደሰት ሳይሆን ዓለሙን ለመሳብ መሆን አለበት !!
ባህርዳር ለመግባት ብትሞክሩ፤ ወረዳ ከመያዝ የተሻለ ትርፍ አለው❤
በርቱ ❤
ፋኖነት✊✊
አማራነት✊✊
ብሩህ ተስፋ✊✊
#ደልጊ_ጣቁሳ💪
"አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጌምድር ክፍለ ጦር እና ዞብ ጃኖ ክፍለ ጦር ዘመቻ ታድሎ በጣና ትዩዩ ለባህር ዳርም ለጎንደርም ቅርብ እና ስትራቲጅክ ቦታ የሆነችዉን ጣቁሳ ወረዳን የጣናዋ ፈርጥ ደልጊ ከተማን ጠላትን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ እንዲሁም ምርኮኞ እና ቁስለኛ በማድረግ ከተማዋን ተቆጣጥሯል‼️
ከደልጊ ከተማ እግሬን አዉጭኝ ብሎ *** ቀበሌ የተመጠ ጠላት የምህረት አዋጁን ተጠቅሞ እጅ ይሰጣል እምቢ ካለም በተገቢው ቋንቋ አናብስቶች ያናግሩታል💪
18/ዐ6/2018 ዓ.ም
የድል መረጃዎች!!
✅የመይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር አለፋ ወረዳን በተቆጣጠረበት የውጊያ ግንባር አመርቂ ሁለንተናዊ ድል መመዝገቡ ተረጋግጧል!!
በ2ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ማንዴላ እያዩ ፣አርበኛ ባበይ አምባዬ፣አርበኛ በሊሁን ጌታቸው፣አርበኛ ጌታቸው አማረ ፣በበላይ ዕዝ የ2ኛ ኮር አስተባባሪ ግ/ኃይል እና ሌሎች አመራሮች የተመራው የሻውራ ወታደራዊ ዘመቻ በድል ተቋጭቷል።
ይህ አውደ ውጊያ የኮርና የክ/ር አመራሮች ከብርጌድና የሻለቃ መሪዎች ጋር በመተሳሰር፤ ቋራ ኦሜድላ ክ/ር፣ ካራማራ ክ/ር፣ አድዋ ክ/ር፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር ካላቸው ሀይል በማውጣጣት የካቲት 15/2018 7:30 የጀመረው አውደ ውጊያ የአገዛዙን አሸርጋጅ አድማ በታኝ፣ ሚሊሻ፣ ፖሊስና የስርአቱ አሸርጋጅ ባንዳዎችን በመደምሰስ እና በመማረክ ከ7 በላይ ከተማ ውስጥ የተሰሩ የቁም ምሽጎችን በመሰባበር ሻሁራ ከተማን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
የአብይ አህመድ የሚተማመንበት እና በየሚድያው እንደ ማስፈራሪያ የሚጠቀምበት የድሮን ጥቃት ለማድረስ የሚችለውን ያህል ሙከራ ቢያደርግም ክንደ ነበልባሎችን የመይሳው ካሳ ልጆችን የሚያቆማቸው ግን አልነበረም፤ እንዲሁም ይህ አውደ ውጊያ የተሳካ እንዲሆን አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በጌምድር ክ/ጦር ጣና ብርጌድ ወደ ቀጠናው ተጨማሪ የጠላት ሰራዊት እንዳይንቀሳቀስ መስመር ቆርጠው በመዝጋት ለውጊያ ድጋፍ በተጠንቀቅ ቁመዋል።
ክንደ ነበልባሎቹ ጠላትን ከሻሁራ ከተማ ጠራርጎ በማስወጣት የካቲት 16/2018 በየስርቻው የተደበቀውን እና ለማምለጥ የሞከረውን የአገዛዙ አሸርጋጅ ቡድን በየገባበት እየተፈለገ እጅ ያልሰጠውን እርምጃ በመውሰድ፣ ከሞት ያመለጠው የብልፅግናው ካቢኔ እና ባንዳ ሰራዊቱ በእግሩ እየማቀቀ ወደ ባ/ዳር ፈርጥጦ ሲያመልጥ በየቦታው በእጁ የያዘውን ትጥቅና ስንቅ እያዝረከረከ፤ እንዲሁም ሙትና ቁስለኛ መሸከፍ ባለመቻሉ የአካባቢው ማህበረሰብ ሁለቱንም ቀን በየቦታውና በየምሽጉ የወደቀውን አስክሬን ሊቀብር ችሏል።
የአገዛዙ ሰራዊት ከሁለት አመት ተኩል በላይ መሽጎበት የነበረው የቁም ምሽጎችን ከመሰባበር ባሻገር ስቶሮችን በፍጥነት በመቆጣጠር ተተኳሾችን፣ መሳሪያዎችን እና መሰል ትጥቆችን በእጃችን ማስገባት ችለናል።
🔸 የአገዛዙ ስርአት የፋኖ ቤተሰብ በማለት እና በውሀ ቀጠነ ለስርአቱ አልተመቸንም የሚሉትን ንፁሀንን ከ45 በላይ እስረኞችን ማስፈታት ተችሏል።
🔸 የተደመሰሰ= 231 በላይ የጠላት ኃይል ተደምስሷል።
🔸 የጠላት የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የፖሊስ አዛዡ ዋና ኢንስፔክተር ውባንተ ይርሳው እና ወንጀል መከላከል ኮማንደር ገብሬ እና በጊዜው አብረው የነበሩ የፖሊስ አባላት አና የሚኒሻ ፅ/ቤት ኃላፊው ጌታነህን ጨምሮ ሌሎችም ተደምስሰዋል።
🔸 የተማረከ እጅ የሰጠ...53
🔸 ከ67 በለይ...የቆሰለ
🔸በአውደ ውጊያው የተማረከ(የተገኘ) ንብረት
🔸ዲሽቃ= 2
🔸ብሬን= 2
🔸ክላሽንኮቭ= 259
🔸አብራራው= 22
🔸አስር ጎራሽ= 28
🔸1 ስታር ሽጉጥ
🔸የክላሽ ተተኳሽ= 31,000
🔸የብሬን ተተኳሽ= 9000
🔸የዲሽቃ ተተኳሽ= 21,000
🔸የክላሽ ካዝና= ከ700
🔸ወታደራዊ ኮዳ= 50
🔸ወታደራዊ ሻንጣ= ከ100 በላይ
🔸ረጅም እርቀት ወታደራዊ መገናኛ ሬድዮ= 2
🔸የአገዛዙ ሰራዊት የሚጠቀምባቸውን ሙሉ ቁሳቁስ እና 2 ተሳቢ ጭነት የሚሆን ሬሽን
✅ በሌላ ግንባር
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ ባህር ሌላ ተጨማሪ ድል አስመዝግበዋል።
የካቲት 16/2018 ፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ር ከታጠቅ ብርጌድ እና ባይተኩስ ብርጌድ የተውጣጡ ሰራዊታችን በዚሁ ቀን ተጠግቶ በማደር የአገዛዙን የሚኒሻ አባላትና አድማ በታኝ በመሸገበት ሰርጎ በመግባት አዳኝ አገር ጫቆ ነጋዴ ባህር ልዩ ቦታው አቸራ በር ላይ ረፍርፈውታል።
በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል:
🔸የተደመሰሰ= 23
🔸የቆሰለ= 12
🔸የተማረከ እጅ የሰጠ= 5
የተገኘ ንብረት:
🔸ክላሽንኮቭ= 17
🔸 ብሬን= 1
🔸የክላሽ ተተኳሽ= 1000
🔸የብሬን ተተኳሽ= 1200
በዚህ ስአት በመየሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ስር የምትገኘው ሻሁራ ከተማ ሁሉም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ባንኮችን ጨምሮ መደበኛ ስራቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ የዘወትር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዋን እያደረገች ትገኛለች። በተሞላበት መንገድ እየሰሩ ይገኛሉ።
በፋኖ የቀረበውን የይቅርታና የምህረት ዕድል እየተጠቀማችሁ ከዓብይ አህመድ ርስበርስ የማጫረስ ሴራ በመራቅ እየቀረባችሁ ችግራችሁን እንድትፈቱና ሻጥሩን እንድታከሽፉ ለፀጥታና ለፖለቲካ አመራርና ዓባላት አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ ጥሪ ያደርጋል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
ይካቲት 18/2018 ዓ.ም
ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማ ልጆቿን ናፍቃለች!!
ጀግኖች ልጆቿም የእናታቸው ነገር አይሆንላቸውም።በስስት እቅፍፍፍፍ አድርገዋታል!!
ልጆቿ እነ ቆስቁስ💪💪💪
ላንጨርሰው የተጀመረ አብዮት የለም!!
-----------------------------------
ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት የተሻጋገረው የአማራ ህዝብ ትግል በድል ይጠናቀቃል።
በጀግኖች እርሾነት የተጀመረው አብዮት ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት የተሻጋገረ በመሆኑ መራራው አብዮት እያሸነፈ ይገኛል!!
በውጤቱም ስትራቴጅካዊ ግባችንን ይሳካል።
አማራነት በሃገሪቱ ሰማይ ስር እውን ሆኖ የህዝባችን ማህበራዊ ህላዌ በእኩልነት የመኖር መብቱ ሳይረጋገጥ የሚቆም ትግል የለም!!ማሸነፍ፤ማሸነፍ፤ማሸነፍ እና በማሸነፍ ብቻ ይቋጫል!!
በትግላችን ውስጥ ልጓም የለሺ ፍላጎቶች እና ጣልቃ ገብነቶችም በድርጅታዊ አሰራር እና በመርህ እየተስተካከሉ እንቀጥላለን!!
ነባራዊ ሁናቴን እየገመገሙ መቀጠል ለነገ ስንቅ ነው።
ዓላማችን ህዝባችን ከገጠመው ብሔራዊ ስጋት ወጥቶ ከሰሜን እሰከ ደቡብ፤ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በማንነቱ ተከብሮ እና ህልውናው ተጠብቆ እንዲኖር እና አማራው ህዝባችን ማህበራዊ ዕረፍት እንዲያገኝ ነው።
ደካማው እና ዕምነት የማይጣልበትን የብልፅግናን ስርዓት በመገርሰስ በምትኩ አድስ ስርዓት መትከል ለሃገረ መንግስቱ አንድነት እና ቀጣይ ዕጣ ፋንታ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑም ሊታወቅ ይገባል።
የብልፅግናው ስርዓት ሃገር እያፈረሰ እና ህዝብ እያፈለሰ ሊቀጥል አይገባም።
የሃገሪቱ ዕጣ ፋንታ የሚያሳስባቸው ሁሉ ከአማራ ፋኖ ጎን ሊቆሙም ይገባል እንላለን!!
የአማራ ህዝብ ትግል ከተከላከይነት ጊዜውን ጠብቆ ወደ አጥቂነት እንደተሻጋገረው ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ ያሸንፋል!!
"ላንጨርስ የጀመርነው ትግል የለም" ማለት እኮ በከሰከስነው አጥንት እና ባፈሰስነው ደም የህዝባችን ሁለንተናዊ መብት እና ጥቅም እናስከብራለን ማለት ነው።
ስለዚህ በትግላችን እና በአማራነት ውስጥ ሰበብ እያበዙ እና ስም እየሰጡ ህዝብን ማደናገር አይቻልም!!
የአማራ ህዝብ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ የትግሉ ባለቤትም እንደሆነ እናምናለን።
ነገር ግን ትግሉን በእጅ መንሻ እያመሃኙ እናቡካው፣እንጋግረው እና እንምራው ማለት ፋሺኑ አልፏል።
በተግባር እና ድርጊት ብቻ የትግላችን ፍላጎት እውን ይሆናል!!
አማራነት ዕውን እስኪሆን ድረስ ጠላት የሚሰራቸውን አሉታዊ እና አዎንታዊ ፕሮፖጋንዳዎች በተግባር ፕሮፖጋንዳ ዕውን እያደረግን በፋሺስቱ ሰራዊት ላይ የምናደረገውን መራራ ተጋድሎ አጠናክረን እንቀጥላለን።
የህልውና ትግላችን ማጠንጠኛ የሆነው አማራነት ያሸንፋል🙏❤
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
አርሲ የሰማዕታት ምድር አሁንም ዕረፍት አላገኘችም
በምስራቅ አርሲ ዞን በመርቲ ወረዳ በፈረቀሳ ቀበሌ በቀን 17/06/2018 ለ18 አጥቢያ ከአስር ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው በተደጋጋሚ ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ የሚታወቁት አክራሪ እስላሞች ብዙ ጥፋትና ውድመት አድርሰዋል። ስምዐ ተዋሕዶ ከአካባቢው ከሞት ያመለጡ ሰዎች የሰጡት መረጃ እንደሚያመለክተው በግምት አስር ሰዓት በጀመረው ግድያ በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውን ለጊዜው በስም የተለዩት ግን አራት ሰዎች መሆናቸውን እነሱም ሲሳይ ገዛኸኝ፣ታደሰ ገነነ ፣ደሰያለው ዝቄ እና አብቲ ከድር በመባል የሚታወቁ ኦርቶዶክሳውያን ሰማዕትነት መቀበላቸውን አረጋግጠናል።
ጽንፈኛው ቡድን ከግድያው በተጨማሪ ከዚህ በታች በዝርዝር ያስቀመጥናቸውን ክርስቲያኖች ቤት ከነ ሙሉ ንብረት አቃጥለዋል።
1.አልታየ ፀጋዬ
2.እንዳሻው ገነነ
3.ጌታ ወጋየሁ
4.አልማዝ አሰፋ
5.ግርማ ሙሉነህ
6. ኢሳያስ አለሙ
7.አደም እጅጉሁ
8.ሰይፈ ላቀው
9. ከበደ ወልዴ
10. ስንታየሁ ወልዴ
11. ከተማ አሰፋ
እንደረሰን መረጃ ከሆነ የአካባቢው ክርስቲያኖች መከላከያ ከአሁን አሁን ደርሶ ያድነናል ብለው ቢጠብቁም፤ የመንግስት ድጋፍ እንዳለው በሚያሳብቅ ሁኔታ መንገድ ተዘግቶ ምንም እንዳይገባ በማድረግ በአሁኑ ሰዓት ጽንፈኞቹ ከተማው ላይ መትረየስ ማጥመዳቸውን አረጋግጠናል። በዚህ ሳቢያ እስከአሁን የሞቱ ቤተቦቻቸውን አስከሬን ማንሳት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ክርስቲያኖችም ታግተው መወሰዳቸውን ለማወቅ ችለናል። ከግድያው ያመለጡትን አንዳንዶቹን ክርስቲያኖች ደግሞ እግራቸው ወደመራቸው ቦታዎች እየተሰደዱ ነው። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን።
#በሃገራችን_ኢትዮጵያ_እየተፈጸመ_ያለው_የኦርቶዶክሳውያን_እልቂት_የመንግሥት_መዋቅር_የሚያውቀው_የሚደግፈው_ሽፋን_እየሰጠ_የሚያበረታታው_እንጂ_ባልታወቁ_ኃይሎች_የሚፈጸም_ወንጀል_አይደለም
©ስምዓ ተዋሕዶ
