ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 393
Subscribers
+724 hours
+2667 days
+1 44330 days
Posts Archive
+1
የ74ክፍለጦር አመራሮች 3 ወረዳወችን ከጊዜያዊ መንግስት ጋር ውይይት ተካሄደ!
የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ
201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የክ/ጦር አመራሩን በ3ቱ ወረዳዎች ማለትም እናርጅ እናውጋ ፣ጎንቻ ሲሶ እነሴና እና አነብሴ ሳርምድር ወረዳዎች ችግርፈች የሆነ ስምሪት በመውጣት ከሻለቃዎች እና የወረዳዎች ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ ዘላቂ እና ችግር ፈች ድጋፎችን እያደረጉ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ።
1. የአደረጃጀታዊ አወቃቀር ድጋፍና ግምገማ
2. የድጋፍ አሰባሰብ፤
3. የማህበረሰብ አስ/ር ስርዓት ማዘመን
4. የሰራዊት አያያዝና ክትትል በተመለከተ ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል።
አዲስ ተውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስተስፋ
የቴወድሮስ እዝ201ኛ ኮርህዝብ ግንኙነት
ህዳር20/2018 ዓ.ም
#ዛሬም_ከኋላ_ደጀኑ_ህዝባችን_ጋር_መክርናል!!
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ቁጥቋጥ እና አካባቢው ቀበሌ ከኋላ ደጀኑ ህዝባችን ጋር እንዲሁም በእነማይ ወረዳ የረዝ፣ ሀገረ ህይወት ቀበሌ እና ደብረ ቅዱሳን ቀበሌዎች ላይ ህዳር 19/2018 ዓ.ም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በ201ኛ ኮር ስር የሚገኘው 64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች እና ከሸበል በረንታ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች
ጋር በመሆን በሸበል በረንታ ቁጥቋጥና አካባቢው ማህበርሰብን ጋር በመገኘት ሰፋ ያለ ውይይት በማድርግ ትግሉ ያለበትን ወቅታዊ ቁመና በማስረዳት የኋላ ደጀኑ ህዝባችንን ሰንሰለቱን በጠበቀ አደረጃጀት ተዋቅሯል።
በመድርኩ የተገኙት የኋላ ደጀኑ ህዝባችን እንደተናገሩት በአገዛዙ የአብይ አህመድ አገዛዝ እንዲጠፋ የተፈረደበት የአማራ ህዝብ እራሱን አደራጅቶ ከክላሽ እንኮብ መሳሪያ ተነስቶ ዛሬ ላይ ከጠላት ያላነሰ የቡድን መሳሪያ ታጥቆ እዚህ ደርሶል። በመሆኑም እኛም ዛሬ እንደ ትላንቱ ከፋኖ አባላት ጋር በመሆን ድርጅቱ የሚሰጠንን የትኛውም አይነት ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት በእነማይ ወረዳ የረዝ፣ ሀገረ ህይወት ቀበሌ እና ደብረ ቅዱሳን ቀበሌዎች ላይ ህዝባዊ ውይይት በማድርግ የቀበሌ አመራሮችን አዋቅሯል።
➛የቀበሌ ሊቀመንበር
➛የቀበሌ ም/ሊቀመንበር
➛የቀበሌ ፀሀፊ
➛የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ (3)
➛የቀበሌ ገቢና ሀብት አሰባሰብ
➛የቀበሌ ፀጥታና ምክትል
➛የቀበሌ የወጣት ጉዳይ
➛የቀበሌ የጎጥ ሽማግሌ (3)
➛የቀበሌ የሀገር ሽማግሌ በቀበሌ (7)
➛ህዝብ ያመነባቸው አስታራቂ የሀገር ሽማግሌዎችን አዋቅሯል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
የ206ኛ ኮር አደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየፈፀመ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ መዋቅርን በማሻሻል ሰራዊቱን ለተሻለ ግዳጅ እያበቃ ሲሆን በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ ትኩረት ሰጦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር በስሩ ያሉ ክ/ጦሮችን በማደራጀት ሰራዊቱን በጠንካራ ሻለቆች እያዋቀረ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን አጠቃሎ በአዲስ የተደራጀው ጊዜያዊ መንግስት በኮሩ ቀጠናዎች ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ቢሮ በመክፈት አገልግሎት መጀመሩን ያረጋገጠው የ206ኛ ኮር አደረጃጀት መምሪያ የተሰጠውን ድርጅታዊ ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ኮሩ የስራ ስምሪት ወስዶ ከተንቀሳቀሰ ጀምሮ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ያወሳው መምሪያው 24ኛ ክ/ጦርን በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ ሙሉለሙሉ ያዋቀረ ሲሆን የክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስን ጨምሮ ቀጠናውን ሸፍነው የሚንቀሳቀሱ ጠንካራ ሻለቆችን በማደራጀት ክ/ጦሩ የሚሰጠውን ግዳጅ በብቃት ለመወጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ አክሎ ገልጿል።
ከመልሶ ማደራጀት ትግበራው ጎን ለጎን ከአካባቢው ማህበረሰብ ፣ከሀገር ሽማግሌዎች፣ሴቶችና ነጋዴዎች እንዲሁም ከመላው ሰራዊቱ ጋር አስቀድሞ ውይይት ያደረገው 206ኛ ኮር ግዳጆችን በብቃት ለመወጣት የማህበረሰቡ ተሳትፎ አይነተኛ ሚና እንደነበረው የ206ኛ ኮር አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ ፲አለቃ ደርሳችሁ አትንኩት ከ206ኛ ኮር የሚዲያ ክፍል ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
"#ድሉ_ይቅናህ_በሰላም_ተመለስ_ልጄ" ተብሎ የእናት ምርቃት ማገኘት መታደል ነው።
#የጀግና_እናት ብቻ አይገልፃቸውም መላው የአማራ ሕዝብ እናት ናቸው።ሙሉ ጤና ረዥም ዕድሜ ይስጠዎት የኔ እናት።
በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር በዕዙና በኮሩ የተሰጡትን የስራ አቅጣጫዎች ተቀብሎ ወደ ስራ ተገብቷል።
ህዳር 19/2018 ዓ.ም አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኮር 77ተኛ ክ/ጦር አካል ከሆነው ራስ ደረሶ ሻለቃ ጋር ችግር ፈች የሆኑ ውይይቶችን ከሻለቃው አመራሩና አባሉ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮችና በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ መጠነ ሰፊ ውይይቶችን ማካሄድ ተችሏል።
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር በከፍተኛ አመራሮች የተሰጡትን የስራ አቅጣጫዎች በመቀበል በአዲሱ አደረጃጀት የክ/ጦሩ አመራር ስብሰባ በማድረግ የመጀመሪያ ስራውን በይፋ የጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በዚህ ክፍለጦር አካል በሆነችው ራስ ደረሶ ሻለቃ የተሰጡትን የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች በመያዝ
1-የድርጅታችን የመዋቀር ለውጥ የኮርና የክፍለጦር ምስረታውን አስመልክቶ ለሰራዊቱ ነፃ የሆነ መድረክ በመፍጠር በሰፊው ተወያይተዋል፡፡
2- የክፍለጦሩን የሰራዊት ፕወዛ እና የካምፕ ቅድመ ዝግጂት አስመልክቶ ሰፍ ያሉ ሀሳቦች ተነስተው በክፍለጦሩ ሰብሳቢ መልስ ተሰጦባቸዋል፡፡
3- ክፍለጦራችን በአምሰት(5) ሬጂመንት እንዲሁምበአንድ(1) ቃኝና ምሀንዲስ የሚዋቀርበት ሂደት ላይ ሰፍ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡
4-ከሻለቃዋ ላይም ሀያ(20) የቀኝና መሀንዲስ አባላትን የመምረጥና የመልመል ሂደቶች በማስጀመር የክፍለጦሩ አመራር እና የሻለቃ አመራሩ ጦሩን እንደሚፐወዝ ተልኮ በመስጠት እንዲሁም ከሰራዊቱም ያልተፐወዘ ሰራዊት ከመንደር ያልወጣ ሰራዊት እንደሆነና ትግሉን ወደ ኻላ እንደጎተተባቸው የገለፁ ሲሆን በፕወዛው ግን በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የክፍለጦሩ አመራሩ ቀጠናውን ከጠላት በመጠበቅ ለቀጠይ ሰራዊት ወደሚመደብበት ቀጠና እንዲገባ ተልዕኮ በመስጠት የዕለቱ አጀንዳ ተጠናቋል፡፡
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
መልካም የስራ ዘመን!!!!!
+2
አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ኃይል ለልማት በወጣ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ‼️
ራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው የአማራ ጠሉ አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ በመንገድ ጠረጋ ልማት በተሰማራ ሕዝብ ላይ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት መካናይዝድና የቡድን መሳሪያ በመጠቀም በስድስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል::
በዚህም ፋሽስቱ የአብይ አህመድ አገዛዝ ሕዝብ ጠል ፣ ልማት ጠል ፣ ማንነት ጠልና ፍፁም ሰብዓዊነትም የሌለው መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበሩ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል
20/ዐ3/2018 ዓ.ም
+2
የአራቱ ማኅበራት መግለጫ
1. የሰሜን አሜሪካ ካሪቢያን እና ላቲን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች ኅብረት፣
2. ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣
3. የማኅበረ በዓለ ወልድ በሰሜን አሜሪካ
4. ዋልድባን እንታደግ ሰሜን አሜሪካ
ብዙዎች ትናንት ሀገራችንን እና ህዝባችንን አጋድመው ሲግጡ የነበሩ ሙሁራን ነን ባዮች ዛሬ ሕዝባችን ጥፋት ታውጆበት ሀገር እንደቆዳ ስትወጠር እነሱ የሉም።ገሚሱም ባገኘው አጋጣሚ ከህዝቡ የመነተፈውን ረብጣ ገንዘም ጠቅልሎ ህዝቡን አይደለም ሀገሪቱን አያሳየኝ ብሎ ጠጠር ወርውሮ ፈርጠጧል።
ትናንትም ሀገሬ ምን አረገችልኝ ሳይሆን ለሀገሬ ምን አደረኩላት ብለው ሀገርን ከወራሪ ህዝብን ከጥፋት ለመታደግ ፣ከራስ በላይ ለህዝብ የታመኑ ሰው በጠፋ ጊዜ ሰው ሆነው የተገኙ ግፍ እና ግፈኞችን የተፀየፉ ሩቅ አሳቢ ጥቂቶች ቀድመው ነቅተው የጠላትን ብትር በብቸኝነት የተጋፈጡ እና ብዙዎችን ከድንዛዜ ካነቁት መካከል አርበኛ ሀብቴ ወልዴ አንዱ ነው።
ቀደም ብሎ ጠላቶቹን ካላሸነፈ ረፍት እንዴሌለው የተረዳው አርበኛ ሀብቴ በዚህ ውጣ ውረድ በሌለው የፋኖ ትግል ከፊት መሪ አታጋይ ሆኖ እንኳን ድምፁ አይሰማም።በፋኖ ቤት የልዩነት ክር ሲመዘዝ አየሩን ሁሉ በአሉቧልታ ጉም የሚሸፍኑት ሚዲያዎች እንኳን የሱን ስም ለመጥራት ትናጋቸው ይቆለፋል። እሱ ግን ጉዳዩ አይደለም ።ስራና ስራው ላይ ብቻ ነው። ምክንያቱ የአባቱ የጀነራል አሳምነው ፅጌ የመንፈስ ልጅ ነው። የራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ፣የዋርካው ምሬ ወዳጆ፣የአርበኛ ደሳለኝ፣የአርበኛ ደረጀ በላይ የአርበኛ መከታው ማሞ ወንድም ነው!!
አርበኛው ሰው በጠፋ ጊዜ ሰው ሆነው ከተገኙት የዘመኑ ባለታሪኮች መካከል አንዱ ነህና በርታ!!
በአራቱም ማዕዘን 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአፋብሃ ምዕራብ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር አካል የሆነው 88ኛ ክ/ጦር ለግዳጅ ዝግጁ መሆኑ ተገለፀ።
********//
የአፋብኃ ምዕ/ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ከደረሰበት የእድገት ደረጃ ጋር የሚመጥን መንግስት ተክ አደረጃጅት የፈጠረ ሲሆን ዕዙ ወታደራዊ ኃይሉን በ5 ኮሮች አደራጅቷል። ከኮሮቹ አንዱ 109 ኮር ሲሆን በስሩ ካሉት ክ/ጦሮች 88ኛ ክ/ጦር ይገኝበታል። ክ/ጦሩ በ5 ሻለቆች፣ በ1 ሻለቃ ቃኝና ማኃንዲስ እንዲሁም በ3 የወረዳ ሲብል አስተዳድሮችን በማደራጀት የተሳካ መዋቅራዊ ለውጥ አካይዷል።
88ኛ ክ/ጦር የቀድሞ ወምበርማ፣ ጓጉሳ እና ወርቃባይ እህት ብርጌዶችን አጣምሮ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም አንጋፋውን የታሪክ ሙህሩ አርበኛ ይስማው በላይን መሪ አድርጎ ከተቋቋመ ጀምሮ የአጭር፣ የመሃከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅድ አቅዶ አብይ ተግባራትን በትጋት እየፈፀመ ይገኛል። የክ/ጦሩን መቀመጫ ካምፕ መምረጥና ሁኔታዎችን ለስራ ዝግጁ ማድረግን ቅድሚያ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪ የ3ቱን ብርጌድ ኃይል ማሰባጠር እነዲሁም የሻለቆችን መቀመጫ መለየትና ማስተካከል ቅድሚያ እንዲፈፀሙ ከታቀዱት ተራ የሚመደብ ነው።
በአማራ ሁለንተናዊ የትግል ታሪክ ውስጥ ትልቁ የእድገት እጥፍት ኃይልን ከአውራጃዊነት እና ወንዜነት እሳቤ እንዲወጣ በማድረግ የአማራ አለፍ ሲልም የኢትዮጵያ አርበኝነትን ማላበስ ታሳቢ ያደረገ የኃይል ማሰባጠር በእነ አርበኛ ግሩም ምሳሌ፣ አማረ ካሴ፣ ወርቅነህ የኔጌጥ፣ ይስማው በላይ እና በመላው የክ/ጦሩ አመራሮች ባለሰለሰ ጥረት ሞቅ ደመቅ ባለ ሁኔታ ህዳር 18/2018 ዓ.ም በታሪካዊዋ ኮኪ ቀበሌ ተፈፅሟል።
የተሰባጠረው ኃይል የበፊቱን የብርጌድ አደረጃጅት ሙሉ በሙሉ ያከሰመ ሲሆን በአዲስ የትግል ሞራል እና መንፈስ የአባቶቹን ታሪካዊ አንድነት ስነ ልቦናዊ ውቅር ባገናዘበ መልኩ መፈፀሙ ያስደሰታቸው መሆኑን ያነጋገርናቸው ታጋይ አባላት ገልፀውልናል።
ታሪክ እንደሚነግረን ከ1983 በፊት ጓጉሳ ወምበርማ 58 ቀበሌዎች ያሉት በአንድ አውራጃ ይመራ የነበረ ሲሆን የህወሃት መሩ ኢሃዲግ በከፋፍለህ ግዛ እሳቤ አማራን የማሳሳት ስውር ደባ አማራ አይደለህም የሚል ስዕል ለማስያዝም ጭምር በ1986 በአቶ ደመቀ መኮነን መሪነት ከ3 የወረዳ አስተዳድር ከፋፍሎታል። ዳሩ የጠላት ፖለቲካዊ አሻጥር ማህበረሰባችንን ባሰቡት ልክ መለያየት አልቻለም። አልተሳካላቸውም። ምስጋና ይግባና ለወቅቱ የአማራ ትግል አንድነቱን የሚያፀናበትን እድል መልሶ አግኝቷል።
#ለእነ አርበኛ ግሩም ምሳሌ፣ አማረ ካሴ እና ወርቅነህ የኔጊጥን ክ/ጦራችንን ከማደራጀት ባለፈ ጠንካራ ቁመና ላይ እንዲገኝ ምቹ ሁኔታ በሌለበት የተለያዩ ውጣ ውረዶች ሳይበግሯችሁ ላበረከታችሁት ሁለንተናዊ አስተዋፅዖ በትግሉ ሠማዕታት ስም ክ/ጦሩ ምስጋናውን ይገልፃል። 🙏ክብር ይስጥልን።
🙏ክብር ለውጤቱ ለደከማችሁ!
ከአብይ አህመድ ወገን የሆነ ሁሉ ሞገስ ሊኖረው አይችልም። ሰውየው ስልጣን ላይ ከወጣ ግዜ ጀምሮ የተጠጉትን ብዙ ትላልቅ ሰብዕናወችን አቆሽሿል። ምሁራን እና ፈላስፋ የሚባሉቱ ተራ ሀሜተኛ እና አሉባልተኛ ሲሆኑ ታይተዋል። የቤተ-እምነት ሰዎች የዱርዬነት ሜዳውን ሲያጣብቡም ተመልክተናል። ወታደሮቹ ዋሽቶ አደሮች ሆነዋል፣ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪወች አፋችውን ለጉመዋል። ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ኮስማና አድርጓል።
በአጠቃላይ አብይ አህመድን የሚያክል የጥፋት እና የሽብር ፕሮጀክት የተሸከመ ሰው በሌሎች ፊት የሞራል እና የህሊና ጥያቄወችን ማለፍ ከቶ አይቻለዉም።
ማንም ውርደትን እና ንፅህናን መላበስ ቢኖርበት ከዚህ ሰው መራቅ ግዴታው ነው!!
በቁጥጥር ስር ውሏል
በፋኖና በሕዝቡ መካከል ቅሬታና ጥርጣሬን የመፍጠር ተልዕኮ ይዞ በዝርፊያ ድርጊት ተሰማርቶ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!
ግለሰቡ ከሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ዝርፊያውን የሚፈፅመው በፋኖ ስም እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፡ በመጨረሻም በፋኖ እጅ ከፈንጅ መያዙ ታውቋል።
አማራነትን ለመናኛ ጥቅም አናውለውም!!
----------------------------------
"አማራ ሆይ ተነስ፣ሩጥ፣ምታ - አባ ባህሪ
ከዛሬ 500 ዓመት በፊት 28 ነገዶችን አጥፍቶ የመጣው የኦሮሞ እንቅስቃሴ በእጅጉ አስፈርቷቸው ስለነበረ የደብረ ማሪያም ገዳሙ አበምኔት የጋሞው ተወላጅ አባ ባህሪ አማራ በማንነቱ ለሚመጣው ቀውስ ራሱን ያዘጋጅ ብለው መናገራቸው ይታወሳል።
ሆኖሚ ሰሚ ባለማግኘታቸው ከዛሬ 438 ዓመት በፊት የተናገሩት አባ ባህሪ እስከ ዛሬም ድረስ የረባ ለውጥ ያላመጣ ነገር ግን ደግሞ የዛ ዘመኑ ተስፋፊ ልሂቅ የጥንተ ጠላቶቻችን ውላጅ ለማስፈፀም ከ7 ትውልድ በሗላ በአሸባሪው አብይ አህመድ አማካኝነት አድስ የፈፅሞ ዘር መጥፋት ጥቃት ተፈፅሞብን በመመከት ላይ እንገኛለን።
በአበው ብሂል "ድመት መልኩሳ አመሏን አትረሳ" ሆኖብን ዛሬም እንደ ትናንቱ ብሔራዊ አደጋውን ከቀለበስነው በሗላም ሌላ ዙር እንጠብቅ ይሆን ወይስ እንደጀመርነው እንጨርሰው ??
መልሱን ለራሳችሁ ትቸዋለሁ??
በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ውስጥ በርካታ እጆች ብቻ ሳይሆን በርካታ ዓላማ ቢስ ሃይሎች ሰርገው ገብተዋል።
የህዝባችንን የመከራ ዘመን ከመቀልበስ እና ያጋጠመንን ብሔራዊ አደጋ ከመመከትም አልፎ አማራን እንደ ኩርድ ለመበተን ከሚሰሩ ህዳጣን እና ታሪክ አልባዎች ጋር ህብረት የፈጠረ ቡድን አለ።
ነገር ግን ፈፅሞ አይሳካላቸውም!!
የሚናበብ ሰራዊት እና አመራር በመፍጠር እኩይ አስተሳሰብ ያላቸውን ሁሉ እየጠረግናቸው እንቀጥላለን።
አማራነት በደም የታተም እውነተኛ ማንነታችን እንደሆነ ለሰራዊታችን፣ ለእውነተኛ ደጋፊዎቻችን እና የትግሉ ባለቤት ለሆነው ህዝባችን በተግባር እየሞትን አሳይተነዋል።
አማራነትን ለመናኛ ጥቅም አናውለውም።
ደም የገበረንበትን ትግል አሳልፈን ለመስጠት የጀመርነው አብዮት የለም።
አማራነት በሃገሪቱ ሰማይ ስር እውን ሆኖ የህዝባችን ማህበራዊ ህላዌ እና በእኩልነት የመኖር መብቱ ሳይረጋጥ የሚቆም ትግል አልጀመርንም!!
በትግላችን ውስጥ ልጓም የለሺ ፍላጎቶች እና ጣልቃ ገብነቶችም በአግባቡ ሊፈተሹ ይገባልም እንላለን።
ዓላማችን ህዝባችን ከገጠመው ብሔራዊ ስጋት ወጥቶ ከሰሜን እሰከ ደቡብ፤ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በማንነቱ ተከብሮ እና ህልውናው ተጠብቆ እንዲኖር እንጅ በከፈልነው መስዋአትነት በሞግዚት አስተዳዳሪነት ልንወክለው አይደለም።
የአማራ ህዝብ ትግል ከተከላከይነት ጊዜውን ጠብቆ ወደ አጥቂነት እንደተሻጋገረው ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ ያሸንፋል!!
"ላንጨርስ የጀመርነው ትግል የለም" ማለት እኮ በከሰከስነው አጥንት እና ባፈሰስነው ደም የህዝባችን ሁለንተናዊ መብት እና ጥቅም እናስከብራለን ማለት ነው።
ስለዚህ በትግላችን እና በአማራነት ውስጥ ሰበብ እያበዙ እና ስም እየሰጡ ህዝብን ማደናገር አይቻልም!!
የአማራ ህዝብ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ የትግሉ ባለቤትም እንደሆነ እናምናለን።
ነገር ግን ትግሉን በእጅ መንሻ አማካኝነት እናቡካው፣እንጋግረው እና እንምራው ማለት በፍፁም ነውረኝነት ነው።
ትግዕስቱም የለንም!!
አማራነት ዕውን እስኪሆን ድረስ ጠላት የሚሰራቸውን አሉታዊ እና አዎንታዊ ፕሮፓጋንዳዎች በተግባር ፕሮፓጋንዳ ዕውን እያደረግን በፋሺስቱ ሰራዊት ላይ የምናደረገውን መራራ ተጋድሎ አጠናክረን እንቀጥላለን።
በአማራ ህዝብ ስም እየማሉ እና እየተገዘቱ በኤጀንትነት እና በልዩ ጥቅም የተሸበባችሁ የትግላችን ሾተላዮች ከእኩይ ድርጊታችሁ እንዲትታቀቡ አበክረን ጠይቀናል።ከዚህ በሗላ ደግሞ አማራጭ መንገዶችን እናሰምራለን!!
የትግላችን መነሻ ምክንያት የሆነውን አማራነትም ፈፅሞ እንዳትዘንጉት አደራ እንላችሗለን።
አማራዊ ተጠይቅም ሊኖርባችሁ ይገባል!!
የህልውና ትግላችን ማጠንጠኛ አማራነት ፍኖተ መንገዳችን ነው።
መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ትግል ያሸንፋል።
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
አገዛዙ 200ሺህ ብር ከተቀበለ በኋላ በድጋሚ አግቷቸዋል።
አገዛዙ ከአንድ አመት ከ8ወር በላይ አስሮ በሽብር ከሶ ሲያሰቃያቸዉ ከርሞ የዉሸት ድራማ ክሱ አላዋጣ ሲለዉ በ200ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ከወሰነ በኋላ ከእያንዳንዱ 200ሺህ ብር ከተቀበለ በኋላ ዛሬ ህዳር 19/2018ዓ.ም ከቂሊንጦ ማረሚ ቤት በር ላይ በአገዛዙ ወታደሮች ታግተዉ ተወስደዋል።
ከታፈኑ ታጋቾች መካከል :-
1አቶ አብዱራህማን አህመዲን
2 አቶ ግዛቸው ታምር
3 አቶ መኮነን ደሳለኝ
ቤተሰቦቻቸው ዳኞች ቢለቋቸዉም ፖሊስ አግቶ ወስዷቸዋል ለማን አቤት እንበል ሲሉ ቤተሰቦቻቸዉ ለሳተናው ተናግረዋል።
አሁን ያሉበት አይታወቅም የሰባዊ መብት ተቆርቋሪዎች እና የሚዲያ አካላት ሁኔታዉን እንዲያጣራ ተማፅነዋል።
