ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 136
Subscribers
+724 hours
+2087 days
+1 20130 days
Posts Archive
206ኛ ኮር የጠላትን ተልዕኮ ተቀብለው ለ9 ወራት መረጃ ሲያቀብሉ በነበሩ ባንዳዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
ታህሳስ/2018 ዓ.ም
ቃል ኪዳን እና ሙያነሽ ትውልዳቸው በደብረ ኤልያስ ወረዳ የቀጋት እና ጓይ ቀበሌዎች ሲሆን በጎዛምን ወረዳ የማይ አንገታም ቀበሌ ተወላጅ የሆነችው መልካም ጭምር በአረመኔው ሰራዊት ለመረጃ ደህንነት ተመልምለው በተለያዩ ቀጠናዎች መንቀሳቀስ የጀመሩት በመጋቢት 2017/ ዓ.ም መሆኑን ተናግረዋል።
በመከላከያ ሰራዊት የመረጃ እና ደህንነት ክፍል በ፲ አለቃ ሲሳይ፣በሚኒሻ አስተባባሪዎች ዘውዱና ሀብቴ አማካኝነት የመረጃ ልውውጥ የሚያደርጉት ሶስቱ ሴቶች በደብረ ኤልያስ ወረዳ ፣ጓይ፣ማርዘነብ፣የቀጋት፣ገነት ከተማ እና ደጎልማ ከተማ የፋኖ ካምፕ አለበት በተባለበት ሁሉ እየተዘዋወሩ መረጃ ሲያቀብሉ እንደነበር ተረጋግጧል።
በደብረ ኤልያስ ወረዳ በረሀማ አካባቢ ጠሸት በረሀ፣ሰይጣን መልካ በረሀ፣አሱላ ገዳ በረሀ በመውረድ ባለሀብቶች ባዘጋጁት የሰራተኞች ካምፕ ሰርጎ በመግባት የሰሊጥ አጫድ እና የሰራተኞች ምግብ አብሳይ በመሆን በረሀውን በማሰስ መረጃዎችን ካሰባሰቡ በኋላ ደብረ ኤልያስ ከተማ በመመለስ ለጠላት ግብዓት ሲሰጡ እንደነበር ተጠርጣሪዎች በአንደበታቸው መስክረዋል።
ባለፉት የክረምት ወራት ጀምሮ በጓይ በረሀ የሚገኘውን የስላሴ አንድነት ገዳምን አስሰው መረጃ እንዲያመጡ ከዘውደ፣ ፲ አለቃ ሲሳይና ፣ከሀብቴ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ተቀብለው የፋኖን ወታደራዊ ማሰልጠኛ፣ ካምፕ እና ምሽግ በማፈላለግ ከወራት በላይ በገዳሙ አቅራቢያ ተደብቀው ሲሰልሉ እንደነበር አስታውቀዋል።
የመልመያ መስፈርቱን ፆታዊ ግንኙነት በማድረግ አስነዋሪ ተግባራትን በመፈፀም የመረጃ ሰዎችን የሚያሰማራው የአረመኔው የመረጃ ቡድን በተጠርጣሪዎች ላይ ተመሳሳይ ተግባር ይፈፅሙ እንደነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት ሴት የደህንነት አባላት ገልጸዋል።
በደብረ ኤልያስ ወረዳ የምትንቀሳቀሰውን የቀስተ ደመና ሻለቃን ለማጥቃት ያመች ዘንድ የተሰማሩ እነዚ ሴቶች ከመጋቢት 2017 ዓ.ም እስከ ህዳር 2018/ ዓ.ም ባሉት ዘጠኝ ወራት በደብረ ኤልያስ፣ደብረ ማርቆስ አማኑኤል ከተሞች ሰፊ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በጎዛምን ወረዳ የሚንቀሳቀሰውን የጅበላ ሙተራ ሻለቃ ለማስመታት በማይአንገታም፣ደምባ፣ቸርተከል፣እና ሊባኖስ ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ መረጃ ሲያቀብሉ እንደነበረም ተረጋግጧል።
-በሀብታሙ እሱባለው -----የደብረ ኤልያስ ወረዳ አስተዳዳሪ
-በደምስ አለህኝ ----በደብረ ኤልያስ ወረዳ መረጃና ደህንነት ኃላፊ
-መለሰ ኃይሉ-----የደብረ ኤልያስ ወረዳ ሚኒሻ ጽ/ቤት ኃላፊ
- የ32ኛ ክ/ጦር አዛዥ በኮረኔል አለምሰገድ አስተባባሪነት የሚመራውን የጠላት የመረጃና ደህንነት ሰንሰለት ተከትሎ ፣ሴቶችን በልዩነት ከአድማ ብተና፣ከሚኒሻና ከአረመኔው ሰራዊት አባላት ጋር ፆታዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ በጀት በመመደብ ከተመለመሉት በርካታ ሴቶች መካከል የሚገኙት፣ቃልኪዳን፣መልካምና ሙያነሽ ከጠላት የሰራዊት አባላት ጋር የፈፀሙት አስነዋሪ ድርጊት ለጠላት አገልጋይ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።
በደብረ ኤልያስ ከተማ እና ዙሪያ ቀበሌዎች በርካታ ሴቶች ፣የቤት ሰራተኛ፣ የቀን ሰራተኛ፣ አብሳይ፣ልብስ አጣቢ፣ሻይ ቤት የሚሰሩ በመምሰል የጠላትን ስምሪት ተቀብለው እንደሚንቀሳቀሱ የተናገሩ ሲሆን።
የአረመኔው ሰራዊት አሰማርቷቸው ለ9ወራት በተለያዩ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው በርካታ ስራዎችን ለጠላት ሲፈፅሙ የነበሩት እነዚህ ተጠርጣሪዎች በአለቆቻቸው ትዕዛዝ የቀስተ ዳመና ሻለቃ የምትሰጠውን የፋኖ ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱ ምልምሎችን በመመሳሰል በስልጠናው ተካተውለምዝገባ በቀረቡበት ወቅት በተደረገው ጥብቅ ክትትል በመጨረሻም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተጠርጣሪዎች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጠዋል።
ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል አስፈላጊውን ምርመራ ያደረገው 206ኛ ኮር ባገኘው የስልክ ማስረጃ፣ የሰው ምስክርነትና ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን መፈፀማቸውን ማመናቸውን ተከትሎ የጠላትን ተልዕኮ ተቀብለው የወገንን ኃይል በመመረጅ ላደረሱት ክህደት፣በሰራዊቱ እና በህዝቡ ለደረሰው የህይወት፣የሀብት እና ንብረት ጉዳት ተጠያቂ በመሆናቸው ሌሎችን ያስተምራል በማለት በተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ወስዷል።
የትግሉን እና የሰራዊቱን ደህንነት ማስጠበቅ ተቀደሚ ተግባር አድርጎ የሚንቀሳቀሰው 206ኛ ኮር የጠላትን ተልዕኮ ተቀብሎ የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም አካል ተካታትሎ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ድል ለተገፋውአማራ !
ድል ለጀግናው ፋኖ 💪!!
ጉዳያችን አማራዊ ነው ስንል...# አማራ ሁነን በተግባር በመገኘት ነው!!
የበላይ ዕዝ ...ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ
የበላይ ዕዝ ...ም/ሰብሳቢ አርበኛ ባዬ ቀናው
ሰበር ዜና
የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር የዙፋን ጠባቂውን ከፍተኛ አመራር ከነ አጃቢዎቹ ፓትሮል ላይ ባለበት ጥቃት በመፈፀምና ያጀበውን ዙ23 በማቃጠል ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር ታላቅ ድልን ተጎናፅፏል!
የአውደ ውጊያ ሜዳውን ከግሸን መገጠያ እስከ ተሪ ተራራዎች በዘረጋው በረሀ ላይ ከፍተኛ አመራሩ፤ዙ-23ቱና የፓትሮሏ ሹፊር እድሁም በርካታ መከላከያ ተደመሰሱ::
ታህሳስ 20/2018 ዓ/ም ፓትሮል ላይ የነበረ ከፍተኛ አመራር ሲቆስል የፓትሮሏ ሹፌር ተደምስሷል።ሰባት የመከላከያ ሰራዊቶች እድሁ ሲሸኙ ዘጠኙ ከባድ ቁስለኛ ሆነው ሌሎች ሶስቱ መካከለኛ ቁስለኛ ተደርገዋል። አንድ ዙ-23 ሙሉ በሙሉ በድሽቃ ተመቶ ተቃጥሏል።
አመሻሽ ላይ በተደረገ አውደ ውጊያ የአካልና ቁስ እድሁም የሞራል ኪሳራን ያስተናገደው በህይወት የተረፈው የብርሀኑ ጁላ ቅጥረኛ ሰራዊት በረሀ ለበረሀ ፈርጥጦ በየ ጥሻው ተሸርኩቶ ነፍሱን አትርፎ ወደ ተንታ ወረዳ ሌቱ ሲነጋ የፈረጠጠ ሲሆን ሌሎቹ "ይዘገያል እንጅ አህያ የጅብ ናት" የሚለው ቢህል የገባው እጁን ለፋኖ እየሰጠም ይገኛል።
የምርኮ በረከት የሆኑት የጦር መኮነኖች ኮሎኔሉና ሻለቃ መሪው ባጋጠማቸው ሞትና ውድመት የተነሳ በከዘራ ሲዛለጡም አድረዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
#INBOX የጀኔራል ባጫ ደበሌ ነገር መቋጫ አግኝቷል'' ብቻ ያሳፍራል፣ አጭር ነች አንብቧት'' አምባሳደሩ ጀኔራል የተናገረው ይህን ማለት ፈልጎ ነው
ጀነራል ባጫ ደበሌ "የጦርነት አስከፊነት የሚያውቀው የሞተ ሰው ብቻ ነው" ያለው የአንድ ታዋቂ ፈላስፋ በስሙ George Santayana የተባለ የተናገረውን እናገራለው በማለት በትክክል ሳይተረጉመው ወይም ገልብጦ ተርጉሞት ነው።
ፈላስፋው ያለው እንዲህ ነው "only the dead have seen the end of war" ይህም ሲተረጎም የጦርነትን መጨረሻ ያየው ወይም የሚያየው የሞተ ነው።
ይህም ማለት የጦርነት መጨረሻ ሞት ነው እንደማለት ነው'' ወደ አማርኛ ስንተረጉመው'' ነገር ግን ባጫ ደበሌ ያለው "የጦርነትን አስከፊነት የሚያውቀው የሞተ ነው" ነው ያለው ይህ ደሞ ሊሆን አይችልም የጦርነትን አስከፊነት በጦርነት የተሳተፈ፣ ያየ፣ የሰማ፣ ቤተሰቡ የሞተበት፣ የተጎዳ ሁሉም ደረጃው ቢለያይም ያውቀዋል።
ግን የአንድን ግለሰብ ንግግር በአማርኛ ወይም በሚችለው ቋንቋ መተርጎም ወይም በትክክል መረዳት መግለጽ የማይችል ሰው እንዴት መፃፍ ሊጽፍ ይችላል።
በነገራችን ላይ ሰሞኑን ባጫ መጽሐፍ አስመርቀዋል አስቡት መጽሀፉ ውስጥ ስንት እንዲህ የተወናበደ ነገር ጽፎ እንደሆነ በእውነት ያሳፍራል።
ታህሣስ 29 የሚከበረው ዓመታዊው የቅዱስ ላሊበላ የልደት በዓልን ለመታደም ወደ ላሊበላ ከተማ ሲጓዙ የነበሩ ንፁኃኖች የከባድ መሣሪያ ጥቃት ተፈፀመባቸው!
ከፋኖ ጋር እጅ በእጅ ውጊያ ገጥሞ ማሸነፍ ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል፡ " ሁሉም አማራ ፋኖ ነው" በሚል የዘፈቀደ የከባድ መሣሪያ ድብደባ በመፈፀም ንፁኋንን በገፍ ጨ-ፍ-ጭ-ፏል።
ይህ ፀረ አማራ ኃይል፡ ታህሳስ 29/2018 ዓ/ም የሚከበረውን ዓመታዊው የቅዱስ ላሊበላ የልደት በዓልን ለመታደም ወደ ላሊበላ ከተማ ሲጓዙ በነበሩ ንፁኋኖች ላይ በፈፀመው የከባድ መሣሪያ ድ-ብ-ደባ ሁለት ንፁ-ኃ-ኖች ሲገደሉ ዘጠኝ ንፁኋኖች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን የመረብ ለማረጋገጥ ችለናል።
በዓሉን ለመታደም ወደ ላሊበላ ከተማ ጉዞ የጀመሩት ንፁኋኑ፡ ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም በተደረገ የጨበጣ ውጊያ 282 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች የተደመሰሱበት በቡግና ወረዳ ብርኮ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ሲደርሱ ነው ጥ-ቃ%ቱ የተፈፀመባቸው።
በሰዓቱ የአገዛዙ ኃይል በአከባቢው ሙትና ቁስለኛውን ካነሳ በኋላ፡ የብርኮ ቀበሌን በከባድ መሣሪያ እ-የደ-በደበ ነበረ።
የብርኮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም የአገዛዙ ኃይሎች በፈፀሙት የዘፈቀደ የከባድ መሣሪያ ድ-ብ-ደባ መውደሙ ታውቋል።
በተጨማሪም ከፋኖ ጋር እጅ በእጅ ውጊያ ገጥሞ ማሸነፍ ያልቻለው ይኸው ፀረ አማራ የአገዛዙ ኃይል፡ "ልጆቻችሁ ጓዶቻችንን ገድለውብናል" በሚል ሁለት እናቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉንም ዘጋቢዎቻችን አረጋግጠዋል።
ሟቾቹ የ32 እና የ35 ዕድሜ ያላቸው ወላድ እናቶች ናቸው።
(ምስል፦ የከባድ መሣሪያ ጥቃት የተፈፀመበት የብርኮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት)
መረብ ሚዲያ
አርበኝነት ልክ እንደ ሚኒልክ የተላበሰው ጀግናው አሞተ ኮስታራው ኢሳያስ ደመቀ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ!!
የውጊያ መረጃ !!
ከመከላከያ መንገድ መሪነት የዘለለ ጥቅም የሌለው ሚሊሻ በየጢሻው መውደቁን ቀጥሎበታል። ትናንት ረፋዱን ጀምሮ በቢቸና ዙሪያ ቀበሌ ለዘረፋ የተሰማራው የጠላት ኃይል እንደለመደው በርካታ ሚሊሻዎችን በመንገድ መሪነት ይዞ ቢንቀሳቀስም የደሃ ንብረት እጭንበታለሁ ያለውን ተሽከርካሪ የሚሊሻ አስከሬን እና ቁስለኛ ሲያመላልስበት ውሏል።
ከሳምንት በፊት በቢቸና ከተማ ለአዳራሽ ዲስኩር ቃላት ሲደረድር የነበረ ሚሊሻ በ64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ወደ 7ኛው ሰማይ ተሸኝተዋል። ገሚሶቹም በሞትና በህይወት መካከል ሆብነው ሆስፒታል ገብተዋል።
በዚህም:- ➣ቁጥሩ ያልታወቀ መከላከያ ሞቷል
➣ አስረሳኸኝ ጎሌ የተባለ የጎተራ ተወላጅን ጨምሮ አምስት(5)ሚሊሻ አፈር ሲቀምስ ዘጠኝ(9)ሚሊሾች ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል።ከቁስለኞቹ መካከል :-
➣ታደለ አበበ
➣አለኸኝ ጌቴ
➣ስመኝ ደባስ በስም ታውቀዋል።
#የመንገድ_ክልከላ_መነሳትን_ስለማሳወቅ‼️
➯ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር ከቀን 22,03,2018ዓ.ም ጀምሮ የይልማና ዴንሳ ወረዳ ቀጠናዎችን የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ ጥሎ መቆየቱ ይታወቃል።
➯ ስለሆነም ከህዝቡ በመጡ ጥያቄዎች መሠረት የህዝባችን ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት
🔹ህዝቡ መጭውን የገና በዓል ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ተገበያይቶ እንዲያከብር ከቀን 21,04,2018ዓ.ም ጀምሮ ክልከላው የተነሳና መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ክፍት መሆናቸውን እናሳውቃለን።
ምስጋና:- የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ አክብራችሁ ስለቆያችሁ መላው ማህበረሰባችን ከልብ እናመሰግናለን።
ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር።
ታህሳስ 21,2018ዓ.ም
ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ!አዲስአስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!
#የአገዛዙ_ቅጥረኛ_ሚሊሻ_ሰብል_ሊሰበስብ_የመጠው_አረመኔዊ_ዘራፊ_ሰራዊት_ሙት_እና_ቁስለኛ_ሆኗል።
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በእነማይ ወረዳ አንስላል/ማንቆርቆሪያ ቀበሌ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ ሰብል ለመሰብሰብ በመጣው የጠላት ኃይል ላይ ጀግኖቹ የኮስትር እና የሽፈራው ገረባው ልጆች ሲለበልቡት ውለዋል።
የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ከእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ እና ሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ ሀይል በረካታ ሀይል በመያዝ ወደ አንስላል/ማንቆረቆሪያ ቀበሌ የሚሊሻን ሰብል አርሶ አደሩን በማስገደድ ለማሰብሰብ ቢሞክርም በአንስላል/ማንቆርቆሪያ ቀበሌ ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት የጀመረው ውጊያ የውጊያ አድማሱን አስፍቶ በእነማይ ወረዳ ባንጃ ሸረር እና ደንሳ እነቆራ ቀበሌዎች ላይ እስከ 8:30 በ64ኛ ክፍለ ጦር ወታደራዊ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም የወረዳው ጊ/መንግስት አመራር በታገዘው ውጊያ በረካታ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ሆኗል።
የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ እና የሽፈራው ገረባው ልጆች 64ኛ ክፍለ ጦር ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ከአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ጋር ባአደረገው አመረቂ ውጊያ ከደመሰሱት እና ከአቆሰሉት መካከል:-
➣በፖትሮል ላይ #በሸራ ተጠቅልሎ የነበር ቁጥሩን ማወቅ ያልቻልነው በረካታ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ተደምስሶ በስውር ተቀብረዋል።
➣ ሚሊሻ አስረሳሀኝ ጎሌ ጎተራ ቀበሌ ጨምሮ ከአምስት በላይ የሚሊሻ አባላት እስከ ወዳኘው ተወግደዋል።
➣ በቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል እና ጤና ጣብያ ዘጠኝ የሚሊሻ አባላት ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ የገባ ቢሆንም ከእነዚህም ውስጥ:-
1ኛ. ሌላ ተጨማሪ አንድ ሚሊሻ በህክምና ላይ እናዳለ አሸልቦል።
2ኛ. ሚሊሻ ታደለ አበበ ቁስለኛ
3ኛ. ሚሊሻ አለህኝ ጌቴ ቁስለኛ
4ኛ. ሚሊሻ ስመኝ ደባስ ቁስለኛ
5ኛ. ሁለቱ ሚሊሻዎች ከፍተኛ የአጥንት መሰበር ችግር ስለገጠማቸው #ሪፈር በመባል ደ/ማርቆስ ሆሲፒታል መላካቸው ተረጋግጦል።
ክብር ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ብለው በጀግንነት እና በክብር ለተዋደቁ ፋኖዎች🙏🙏🙏
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
🔜የድሮን አሰሳ ሜጫና አካባቢው:-
ዛሬ ታህሳስ ጥዋት 21/2018 ሜጫ ቀጠና በሳንጊና: ዳጊ ና ናዳ የድሮን አሰሳ ስላለ የወገን ሀይል አሥፈላጊውን ጥንቃቄ እንዳይለየን።
የነ አሰፋ ቸኮለ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዛሬም በድጋሚ አከርካሪው ተሰብሯል!
በዕዙ ስር በዘመቻ አባናደው ከባድ ጉዳት ደርሶባት ዳግም የተደራጀችው 61ኛ ክ/ጦር ትናንት በስቲያ በተደረገ ውጊያ የሰው ኃይሏን ጨምሮ 197 ወታደሮቿ ሲገደሉ ከ85 በላይ የሚሆኑት ቁስለኛ ተደርገውባታል።
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በአርበኛ አምሳ አለቃ ጌታየ ተፈሪ የሚመራው ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦርና ዋግሹም ብርጌድ እንዲሁም ከአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ኮር የተውጣጡ የፋኖ ኃይሎች በጥምረት ባደረጉት አውደ ውጊያ የጠላት አከርካሪን በመስበር ታላቅ ድል መቀዳጀታቸውን ምኒልክ ዕዝ አስታውቋል።
ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 803ኛ ኮር ስር በሻምበል ጫላ የሚመራው 61ኛ ክ/ጦር ከዕዙ ሜካናይዝድ ጋር በመሆን መነሻውን ከአይና ቡግና ከተማ አድርጎ ወደ ብርኮ በአራት አቅጣጫ ማለትም በብርኮ ገብርኤል አቅጣጫ፣በጤና ጣቢያው አቅጣጫ፣በጭቃው አቅጣጫ እና በብርኮ ኪዳነ ምህረት አቅጣጫ ለማጥቃት አስቦ ተኩስ የጀመረ ቢሆንም፡ ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን የፀረ ማጥቃት እርምጃን መከላከል ሳይችል ቀርቶ ከባድ የሆነ የሰብአዊ፣ ቁሣዊና ሞራላዊ ኪሳራን ተከናንቧል።
በዙ-23፣ በሁለት ሞርታር በበርካታ ዲሽቃና በሌሎች የቡድንና ከባባድ ሜካናይዝድ ታግዞ ተሰልፎ የነበረው የጠላት ኃይል፡ ልብ እና እውነት ከሌለው መሣሪያ ብቻውን ዋጋቢስ መሆኑን አስመስክሮበታል ተብሏል።
የ61ኛ ክፍለ ጦር የሰው ኃይል ኃላፊና ሌሎች የክፍለጦሩ አመራሮችን ጨምሮ 197 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ፡ ከ85 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቁስለኛ ተደርገዋል፣ ሰባት ወታደሮች እጅ ከፈንጅ ተማርከዋል ብሏል ምኒልክ ዕዝ አስታውቋል።
በተጨማሪም ሁለት ብሬን፣43 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 84 ወታደራዊ ሻንጣ፣ 2ሺ 850 የብሬን ተተኳሽ፣2ሺ 200 የክላሽ ተተኳሽ ፋኖ ማርኮ ታጥቋል።
#የአገዛዙ_ቅጥረኛ_ሚሊሻ_ሰብል_ሊሰበስብ_የመጠው_አረመኔዊ_ዘራፊ_ሰራዊት_ሙት_እና_ቁስለኛ_ሆኗል።
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በእነማይ ወረዳ አንስላል/ማንቆርቆሪያ ቀበሌ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ ሰብል ለመሰብሰብ በመጣው የጠላት ኃይል ላይ ጀግኖቹ የኮስትር እና የሽፈራው ገረባው ልጆች ሲለበልቡት ውለዋል።
የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ከእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ እና ሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ ሀይል በረካታ ሀይል በመያዝ ወደ አንስላል/ማንቆረቆሪያ ቀበሌ የሚሊሻን ሰብል አርሶ አደሩን በማስገደድ ለማሰብሰብ ቢሞክርም በአንስላል/ማንቆርቆሪያ ቀበሌ ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት የጀመረው ውጊያ የውጊያ አድማሱን አስፍቶ በእነማይ ወረዳ ባንጃ ሸረር እና ደንሳ እነቆራ ቀበሌዎች ላይ እስከ 8:30 በ64ኛ ክፍለ ጦር ወታደራዊ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም የወረዳው ጊ/መንግስት አመራር በታገዘው ውጊያ በረካታ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ሆኗል።
የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ እና የሽፈራው ገረባው ልጆች 64ኛ ክፍለ ጦር ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ከአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ጋር ባአደረገው አመረቂ ውጊያ ከደመሰሱት እና ከአቆሰሉት መካከል:-
➣በፖትሮል ላይ #በሸራ ተጠቅልሎ የነበር ቁጥሩን ማወቅ ያልቻልነው በረካታ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ተደምስሶ በስውር ተቀብረዋል።
➣ ሚሊሻ አስረሳሀኝ ጎሌ ጎተራ ቀበሌ ጨምሮ ከአምስት በላይ የሚሊሻ አባላት እስከ ወዳኘው ተወግደዋል።
➣ በቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል እና ጤና ጣብያ ዘጠኝ የሚሊሻ አባላት ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ የገባ ቢሆንም ከእነዚህም ውስጥ:-
1ኛ. ሌላ ተጨማሪ አንድ ሚሊሻ በህክምና ላይ እናዳለ አሸልቦል።
2ኛ. ሚሊሻ ታደለ አበበ ቁስለኛ
3ኛ. ሚሊሻ አለህኝ ጌቴ ቁስለኛ
4ኛ. ሚሊሻ ስመኝ ደባስ ቁስለኛ
5ኛ. ሁለቱ ሚሊሻዎች ከፍተኛ የአጥንት መሰበር ችግር ስለገጠማቸው #ሪፈር በመባል ደ/ማርቆስ ሆሲፒታል መላካቸው ተረጋግጦል።
ክብር ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ብለው በጀግንነት እና በክብር ለተዋደቁ ፋኖዎች🙏🙏🙏
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
የድል ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ከሰም 2ኛ ኮር ቡልጋ ክፍለጦር በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ድል ተቀዳጀ።
መነሻዉን ከመተሀራ ከተማ ያደረገዉ የብልፅግና ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ወደ መተህብላ ከተማ ለመግባት ያደረገዉ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።
ካሁን በፊት ከሞጆ ከተማ ተነስቶ አረርቲ ከተማ አድርጎ መተህብላ ከተማ ለመድረስ ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍል የነበረዉ የጠላት ሀይል አሁን ደግሞ መነሻዬ ከሞጆ ይልቅ መተሀራ ይሻለኛል ብሎ ቢመጣም ያልጠበቀዉ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማስተናገድ ወደ መጣበት ለመመለስ ተገዷል።
በዚህ አዉደ ዉጊያ የአብይ አህመድ የግል ሰራዊቶች ከመተሀራ ከተማ እሬሽን እና መተህብላ ከተማ ያለዉን ሰራዊት የሚቀይር ሌላ ተጨማሪ ሰራዊት ይዞ ቢመጣም በቡልጋ ክፍለጦር አናብስቶች አርበኛ ቸርነት አማረ ሻለቃ ከደመቆ እና ዋንሴ ቀበሌ አባት አርበኞች ጋር በመሆን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ወደ መጣበት እንዲመለስ ሆኗል።
ያሰበዉን ማሳካት አቅቶት ወደ ኋላ የተመለሰዉ የጠላት ኃይል ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን በዚህ አዉደ ዉጊያ የጠላት ተሽከርካሪዎች የተመቱበት እና ከፍተኛ የሆነ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ የሆነበት ዉጊያ እንደመሆኑ መጠን ጠላት ከፍተኛ የሆነ መደናገጥ ዉስጥ ገብቶ የተመታበትን መኪኖች በሌላ ተሽከርካሪዎች እየጎተተ የወጣበት እና መተህብላ ከተማ የነበረዉ ተቀያሪ ሰራዊት ወደ ኋላ በመመለስ የጫነዉን ፍራሽ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለማራገፍ ተገዷል።
በሥተመጫረሻም የአገዛዙ ሰራዊት ክንደ ብርቱወን የቡልጋ ክፍለ ጦር የፋኖ አናብስቶችን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው የያዘውን ይዞ ቀሪውን ጓዙን አንጠባጥቦ ወደኋላ ተመልሷል።
መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም 2ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አርበኛ ይታገስ ጌታሁን ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
+1
ይሀ ከላይ የለጥፈኩላችሁ ሰው አንዲ ደቡብ ወሎ አካባቢ ነኝ ይላል በወስጥ የፈኖ ታጋዮችን እያደነጋገር መረጃ እየፈለገ የአብይን አህመድ ስራት ለማስቀጠል ሌትና ቀን ተጥዶ የሚሰራ አረመኔያዊ ሰው ስለሆነ ጥንቃቄ አይላያችሁ።
