en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 480
Subscribers
-524 hours
+677 days
+84830 days
Posts Archive
ዶክተር ሮዳስ🙏 ብቻህን በእወነት አንተ ከናሳ በላይ የምርምር ተቋም ነህ! የቤተክርስቲያን እውቀት ድግምት ሳይሆን ጥበብ እንደሆነ ይህ ማሳያ ነው። ወደ ምድር በጥልቅ ወርዳ ወደ ሰማይ በግርማ ወጥታ
+2
ዶክተር ሮዳስ🙏 ብቻህን በእወነት አንተ ከናሳ በላይ የምርምር ተቋም ነህ! የቤተክርስቲያን እውቀት ድግምት ሳይሆን ጥበብ እንደሆነ ይህ ማሳያ ነው። ወደ ምድር በጥልቅ ወርዳ ወደ ሰማይ በግርማ ወጥታ እውቀት የምትበረብረው ቅድስት ቤተክርስቲያን ሞጎሳ መለኮት ነው።

➾አርበኛ ዘመነ ካሴ በአፋብኃ ሲምፖዚየም ያስተላለፈው ታሪካዊ መልዕክት እና ድንቅ ንግግር‼ የተከበራችሁ የዚህ ውይይት ተሳታፊዎችና ተከታታዮች ክቡራን የማሕበራት ተወካዮች የተወደዳችሁ የመገናኛ ብዙሃን ሙያያተኞችና ድርጅቶች ውድ የድርጅታችን አፋብኃ አመራሮችና የሠራዊታችን አባላት ሁላችሁም በመላው ዓለም ያላችሁ አማራዎችና የአማራ ወዳጆች፤ በቅድሚያ የአክብሮት ሠላምታዬ ይድረሳችሁ!! ከትናንት ጀምሮ እየተካሔደ ያለው ውይይትና እየቀረበ ያለው መልዕክት የአማራ ወገናችን ራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ለመታደግ የሚያደርገው የሕልውና እና የፍትሕ ርትዕ ትግል አንድ ሁነኛ መገለጫ ነው። ዛሬ በዚህ መድረክ ተሰባስበን ስንመክር በአማራነታችን ላይ የታወጀውን ጥፋት ለመመከት፡ ከምንግዜውም በላይ ንቃት ፈጥረን፡ አደረጃጀት አበጅተን፡ የትናንትን ጉድለት በዛሬ ጥረት አሟልተን ፡ነጋችንን የተሻለ የማድረግ ቁርጠኝነታችንን የምናድስበት ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት የአማራነት ንቃትና መሰባሰብ ከእነውስንነቶቹ  አመርቂ የሚባል እድገት አሳይቷል። ግዙፍ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም በመፍጠር የመደራጀት ያደረ የቤት ስራችንን መመለስና ማረም ጀምረናል!! በአማራነት ላይ የተፈጠረው ንቃትና መሰባሰብ የዘመናት የጥቃት አዙሪትን ለመስበር በሚያስችል ግለት ውስጥ ይገኛል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ራሳችንን አጠናክረናል !! ለሕልውናው የሚሰለፍ ሕዝባዊ ኃይል ፈጥረናል!! ሊያጠፋን የተነሳውን ጠላት በመመከት ማሸነፍ እንደምንችል አረጋግጠናል !! የዕጣፈንታችን ወሳኞች እኛ ነን ብለን ስንነሳ የመናጆነት፣ የተከታይነት፣ የአጃቢነት ልማዶችን ሰብረን የአማራዊ ማንነታችን እና ፍላጎቶቻችን በአማራ ልጆች የሚወሰንበት ምዕራፍ ለመክፈት ነውና ጀምረነው ብዙ ርቀት ሔደናል። የተከበራችሁ የዚህ መድረክ ተሳታፊዎች፤ አማራዎች ራሳችንን ብሎም አገራችንን ለማዳን አብዛኛውን የትግል መንገድ ሞክረነዋል። በዜግነት ፖለቲካና በአገር አንድነት ትግል አልፈናል። ሆኖም በአማራነታችን ላይ የታወጀውን ጥፋት አልመከትነውም። በዚያ መንገድ ኢትዮጵያን ከመስቀለኛ መንገድ መታደግ አልተቻለም። አሁን ለረጅም ጊዜ ያልሔድንበት በአማራነት ተደራጅቶ ራስን የመታደግ ትግል የጊዜው ቁልፍ ተልዕኮ ነው። አማራና አማራነት የዚህ ዘመን ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ በአማራነት ላይ በተከፈቱ ጥቃቶች ውስጥ ገና ከማለዳው እነደጃዝማች ፀሐዩ እንቁስላሴ የገለጡት የወል ጥቃት መረዳት ተዳፍኖ የቀረ ነበር። ኋላም እነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያነሳሱት የአማራ ንቃት ቅስቀሳ ብዙም ሳይሻገር ቀርቷል። በረጅሙ ታሪካችን ውስጥ አማራነታችን ላይ ጥቃቶች በቀጠሉበት፥ በአማራነት መሰባሰብ እና የጋራ ተቋም መፍጠር ሳንችል ቀርተን አማራን የሚያሕል ሕዝብ የሕልውና አደጋ ውስጥ ይገኛል። ተቃርኖው ይገርማል !! አገር የመሠረተ ሕዝብ ፣ ይብዛም ይነስም የአገሪቱን ተቋማት የመሠረተና የመራ ሕዝብ፣ ለሺህ ዘመን ፀንተው የቆሙ መንፈሳዊ ተቋማትን ያደራጀ ሕዝብ ፣ ለዘመናት አገር የጠበቀ አርበኝነት ያለው ሕዝብ ፥ ራሱን ከሕልውና ጥቃት የሚመክትባቸው ተቋማት አጥቶ ዛሬ ላይ ደረሰ። አማራዎች ራሳችንን የምንጠብቅበት ሥርዓት፣ ፍላጎታችንን የምንገልጥባቸው አማራዊ ተቋማትን መፍጠር ዳገት ሆኖብን መኖራችን መገታት አለበት። ይህ ትግል "የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ሕልውና በዘላቂነት የማረጋገጥ ነው" ስንል የሕልውና መሠረቶቻችንን የሚሸከሙ ተቋማትን የመትከል መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም። የፋኖ አንድነት ተቋማዊ ጉዞ የዚያ ምሰሶ ይሆናል!! በአማራነት ተለይቶ መጠቃት በታወጀበት ዘመን እንኳ አባቶቻችንና እናቶቻችን ስለአገር እንጂ ስለአማራነታቸው አልመከሩም ፡ አልተሰባሰቡም፡  አልተደራጁም። ስለአገር ዋጋ መክፈላቸው ባልከፋ ፥ ሲከፍሉት የኖሩት ዋጋ ግን በአማራነታቸው ላይ የተከፈተውን የጥፋት ጦርነት ሊያስቆመው አልቻለም። የትናንት አለመደራጀት ለዛሬ ያወረሰን ምን እንደሆነ በውል ተገንዝበን ተነስተናል !! ትናንት ያልሠራነው ሥራ ቁጭት ካወረሰንና ለዛሬ ብርቱ ትግል ስንቅ ከሆነን በቂ ነው። ነጋችንን የምናሳምረው ግን በዛሬ የተባበረ ጥረታችን ነው!! ይሕ ትውልድ ለነገ የሚያሻግረው የጥቃት ውርስ ሊኖር አይገባም !! ይሕ የእኛ ትውልድ  የቤት ሥራውን ሳይሠራ ቀርቶ የነገው ትውልድ ጥፋትን እና ፈፅሞ መገፋትን ሊወርስ አይገባም!! ስለዚህ እንሰባሰብ !! በአማራነታችን እንደራጅ !! በአማራነት የመደራጀትና የመታገል ጉዳይ ግለሰባዊ እና ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎትን መተው ይፈልጋል። በመካከለችን ያለ ትናንሽና መለስተኛ ቅራኔና ፀብን፥ ኩርፊያና ልዩነትን በመተውና በማቆየት ለወል ፍላጎታችን መሰለፍን ይጠይቃል። ብሔርተኝነት እንደዚያ ነው !! ከትናንትም ሆነ ከዛሬ ነገሮቻችን መካከል መርጦ መዘንጋት እና ለይቶ ማንሳትን ይፈልጋል !! ስለጋራ አማራዊ ፍላጎታችን የመሰለፍ ጥሪ ነው !! ያን ስናደርግ እንኳን ለአማራ ትውልድ፥ ለኢትዮጵያ እና ለሰው ልጆች ሁሉ የሚተርፍ ቁምነገር እንሠራለን!! የጋራ ጥቃት አንገሽግሾን የወጣን ታጋዮች ሁሉ እንደአማራ ስንመክር፣ እንደፋኖ ስንነጋገር  ከባድ የመሠለን ቀላል እንደሚሆን አይተናል። የራሳችንን ጉዳዮች በራሳችን ለመወሰን "የእብድ ገላጋይ..." አያሻንም።   እናም የጀመርነው የአንድነት ጉዞ የተማከለ አማራዊ አታጋይ ተቋም በመመስረት የሚቋጭ ይሆናል። ይሕ የአዲሱ አመት ድላችን ሆኖ ይመዘገባል!! የተወደዳችሁ የሕልውና ትግሉ ተሰላፊ ምሑራንና ማሕበራት፤ ያለነው እንቅልፍ አልባ ዘመን ነው። እኛን ለማጥፋት ፍፁም ጭካኔ እና ሙሉ ቆራጥነት ያለው ገዢ ጠላት ነው የገጠመን። የምናሸንፈው ከአጥፊው ጠላታችን በላይ ስንጨክን፣ ከገጠመን ደመኛ በላይ ስንተጋ፣ ከእነሱ በላይ ስንደራጅና አንድ ስንሆን፣ ከጠላቶቻችን በላይ ቆራጦች ስንሆን ነው። ከእነሱ በላይ ስንሠራ እንጂ በእነሱ ልክ እየተራመድንም አይደለም። ስለሆነም በዓለም ዙሪያ ያላችሁ የአማራ ምሑራን፣ የዲያስፖራ ማሕበራት፣ ሰፊው በወጭ አገር ያለህ ወገናችን እንድትሰባሰቡ በአንድ እንድትቆሙ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ። ስለወገናችን የምንቻቻልበት፣ ስለራሳችን የምንመክርበት፣ የምንተሳሰብበት ፣ በእያንዳንዳችን ላይ ልዩ ተልዕኮ የወደቀብን ወቅት አሁን ነው። ከዚህ ወቅት በቀር ስለአማራና አማራነት የምንሰለፍበት የምንሠራበት የተለየ ጊዜ የለም። ዛሬ ነው !! እናም የአማራ ማሕበራት ከተበታተነ ጉዞ ውጡና ተሰባሰቡ!! በየአሕጉሩ አንድ ጠንካራ ሕብረት አቁሙ!! ምሳሌ ሁኑ!!  የአንድነት ፤ የዲፕሎማሲ ፣ የአድቮኬሲና ትብብር ምሳሌ ሁኑ!! በመጨረሻ ግን በዋነኛነት ፥ በመላው ዓለም የምትገኙ ማሕበራት፣ ምሑራንና መገናኛ ብዙሃን ሁሉንአቀፍ አማራዊ ጉዳዮቻችን የሚመከሩበት "የአማራ የምክክር ጉባኤ" በፍጥነት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀርባለሁ። አርበኛ ዘመነ ካሴ የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ሰብሳቢ አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ተሰፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ‼ አንድ አምኃራ እስከ ምፅአት አምኃራ‼ ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

~ የተከበራችሁ በውጭው ዓለም የምትኖሩ የኅልውና ትግላችን ደጋፊ ወገኖቻችን፣ የተከበራችሁ በሞት፣ በመፈናቀል፣ በሰቆቃ ላይ የምትገኙ ግፉአን አማራዎች፣ የተከበራችሁ የአማራውን ሥርዓታዊ ግፍ በሃሳብም በግብርም የምትቃወሙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፣ ክቡራትና ክቡራን!!! ከሁሉ አስቀድሜ ከሠላማዊ ትግል እስከ ፖለቲካዊ የትጥቅ ትግላችን ውድ ሕይወታቸውን ለከፈሉ የትግሉ ሰማዕታት ያለኝን ታላቅ አክብሮት መግለጽ እፈልጋለሁ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በጽኑ አለት ላይ የተመሠረተ የአማራ ሕዝብን በአራቱም አቅጣጫ አቅፎ የሚያታግል ተቋም መሆኑን እየገለጽኩ ተቋማችን አፋብኃ መሠረቱ የትግሉ ሰማዕታት ደምና አጥንት ባይሆን ኖሮ ከውስጥም ከውጭም በተሰማሩ የጠላት አንጃዎች ፈርሰን፣ ተበትነን ነበር። ቅሉ የያዝነው ትግል መሠረቱ የትግሉ ሰማዕታት የተሰውለትን እውነት፣ የታገሉበትን ዕውቀት፣ የመከሩበትን ሐቀኛ አመክንዮ ያነገበ በመሆኑ ወደፊት ከመወንጨፍ ውጭ አማራጭ ስለሌለው በጽናት ከዛሬ ደርሰናል። የአፋብኃ ሠራዊት የጽናት ምንጩ አንዲት የማትተካ ሕይወታቸውን ለሕዝባቸው፣ ለታሪካቸው፣ ለባሕላቸው፣ ለእምነታቸው በጥቅሉ ለአማራዊ ማንነታቸው አሳልፈው የሰጡት የእነ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ፣ የእነ አርበኛ ዮሐንስ ዓለማየሁ፣ የእነ አርበኛ ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው)፣ የእነ አርበኛ ሃምሳ አለቃ አባይ እንዲሁም የግፍ ግዞተኛው የአርበኛ አሰግድ መኮንንም የአደራ ቃል ነው። ስለሆነም መራብን፣ መቁሰልን፣ ብርድና ሙቀቱን ሁሉ ሕይወትን ከመስጠት በታች ነውና በጽናት ታግሰን፣ ሐቀኛ የመርኅ ተቋም እንድንፈጥር በሕይወት የተለዩን አርበኞች ምኞት ነበራቸውና ለምኞታቸው ማሳኪያ፣ ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ እንዲሆን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን (አፋብኃ)ን መሠርተን በመታገል ላይ እንገኛለን። ክቡራትና ክቡራን ወገኖቻችን፦ • አፋብኃ የተሰው የትግሉ ሰማዕታት በደማቸው ቀለምነት ከትበው የሰጡን የአደራ ቤታችን ነው። አፋብኃ በየማጎሪያ ቤቱ በአማራዊ ማንነታቸው በግዞት የሚማቅቁ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች ነጻ መውጫ ተቋም ነው። አፋብኃ በዘር ተኮር ጭፍጨፋ መዋቅራዊ አዋጅ የተጨፈጨፉ ሕጻናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን የሰቆቃ ድምጽ እረፍት የሚነሳው የትግል ተቋም ነው። o አፋብኃ ውስጥ ሕጻን አይሻ መሃመድ አለች፣ o አፋብኃ ውስጥ ሃምሳ አለቃ አባይ አለ፣ o አፋብኃ ውስጥ ሜ/ጄ ውባንተ አባተ አለ፣ o አፋብኃ ውስጥ ሳጅን አደም አሊ አለ፣ o አፋብኃ ውስጥ ዮሐንስ ዓለማየሁ አለ። በመሆኑም አፋብኃ በአርበኝነት የተሰው ጓዶቻችን አደራ፣ ምኞት እንዲሁም በሕይወት የሚገኙ አደራ ተቀባይ ታማኝ አርበኞች የነፍስ ትስስር፣ አማራዊ ተጋምዶ የተሸመኑበት ተቋም መሆኑን አውቃችሁ ለዓላማችን መሳካት የሕይወት ዘመን ባለቤቶች ጭምር እንድትሆኑ ነው ይህ ሲምፖዚዬም የተዘጋጀው። • አፋብኃ በእውነት፣ ለእውነት፣ ስለእውነት የጀመርነውን ትግል ቅርጽ ፈጥሮ፣ መርኅ ሕግ እና አሠራር አበጅቶ የተገባደደውን ትግላችንን መቋጫ ተቋማችን በመሆኑ በአንድ ጎን እንተኩሳለን፣ በአንድ ጎን እናሰለጥናለን እናደራጃለን፣ በአንድ በኩል ዲፕሎማሲ፣ አድቮኬሲና ፕሮፓጋንዳ እንሠራለን። እነዚህን ሁሉ ሥራዎች ለማከናወን ብዙ የሙያ ስብጥር፣ በርካታ የሰው ኃይል አስፈላጊ ስለሆነ አፋብኃን ከመደገፍ አፋብኃ ወደ መሆን ትሸጋገሩም ዘንድ ጥብቅ ጥሪ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። ክቡራትና ክቡራን ወገኖቻችን፦ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ድርጅታዊ መርኅን አክብሮ፣ የሕዝባችንን ኅልውና በዘላቂነት ለማረጋገጥ አስቻይ የአንድነት መደላድሎችን በሰከነ ውይይት ፈትቶ እንደሚታገል በተደጋጋሚ ገልጸናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመላው ዓለም የምትገግኙ ወገኖቻችን • የሙያ ተደጋግፎት፣ • የዓላማ ተደጋግፎት፣ • የአማራዊነት ተደጋግፎት ፈጥራችሁ በምትኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ አንድ እንድትሆኑ፣ ምን እናድርግ በሚል ሁለትም፣ ሦስትም፣ በርካታም ሆናችሁ በጋራ እንድትመክሩ፣ ስለአንድነት እንድትመክሩና በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በፎክ ሚዲያ፣ በሜንስትሪም ሚዲያ የሚደረጉ መነቃቀፎችን፣ የሚቀርቡ ዘለፋዎችንና ፍረጃዎችን አስወግዳችሁ • አንድ ዓይነት ጩኸት፣ • አንድ ዓይነት ቋንቋ፣ • አንድ ዓይነት ትንፋሽ፣ • አንድ ዓይነት እርምጃዎችን ልንራመድ የምንችለው ስንቀራረብ፣ ስንነጋገር፣ አንድ ስንሆን ብቻ መሆኑን አውቃችሁ አንድ ሁኑ፣ አደራ አደራ አደራ አንድ ሁኑ። ያኔ በሁሉም ዘርፍ ተጽእኖ ፈጣሪዎች መሆን እንችላለን። • ዓለም የተጽእኖ ፈጣሪዎች፣ • ድል አድራጊነትም የተጽእኖ ፈጣሪዎች ስለሆነች ድል አድራጊነታችንን በአጭር ጊዜ እንድናደርገው አንድ እንሁን፣ ዓለም አቀፋዊ ተጽእኖም እንፍጠር። ያኔ በቀናት ውስጥ አይደለም በሰአታት ውስጥ እናሸንፋለን ማለት እፈልጋለሁ። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) አርበኛ ኢንጂኒዬር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ አመሠግናለሁ!!!! ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ‼️             የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር የየቦቅላ አባይ ብርጌድ በቀን 02/13/2017 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ላይ ልዩ ኦፕሬሽን ሰርቷል። ክብሪቶቹ ከተማ በመግባት አብማ ቀበሌ 04 ሙሉ ሆቴል ጀርባ ጎጆ መሿለኪያ አካባቢ የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት መመሸጊያ ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በቦታው የነበሩ ምሊሻዎችን ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።በባንዳ ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።ክብሪቶች የማይጨበጡ የአባይ ብርጌድ ሚሳኤሎች ናቸው። ከጉንደ ወይን ወደ ደብረ -ወርቅ ኮፖይ አድርሶ ሲመለስ ከቀኑ 8:30 ሠዓት ሽፋሬ በምትባል ንዑስ ከተማ ላይ 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር የሶማ ብርጌድ ጥቂት ሀይሎች ደፈጣ በመያዝ  አድማ ብተና በጫነ ካሶኒ ላይ የቦንብና የጥይት በረዶ በማዝነብ  ከፋተኛ ጀብ መፈፀም ተችሏል። በጠላት ላይ የደረሰ ኪሳራ፦ 6የአድማ ብተና አባላት በቦንብ ተጨፍልቀው እሰከወዳኘው ሲሸኙ    አራት የሚሆኑት የአድማ ብተና አባላት ደግሞ ከባድ ቁስለኛ ሁነው በፈለገ-ብርሀን ጤና ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ። የበተመሳሳይ አባኮስትር ብርጌድ የደፈጣ ጥቃት ሲፈፅም አብራጅት ብርጌድ ደግሞ የላምጌጅ ከተማን ተቆጣጥሮ ውሏል።    ይህ በየቦታው በሚደረገው ጥቃት የደከመው አረመኔ ሰራዊት በገፍ እጁን ለፋኖ እየሰጠ ይገኛል። 1ኛ.  አዲሱ ሞላ ከአድማ ብተና ተቀም ወደ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 1ኛክ/ጦር ባህርዳር ብርጌድ ጊወንሻለቃ የተቀላቀለ ። 2ኛ. ናትናኤል አበበ የሬጅመንት ሶስት ሞርተር ምድብተኛ ከጠላት ካንፕ በመክዳት ወደ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ፫ኛ ክ/ጦር፣ የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድን የተቀላቀለ። 3ኛ. ሀብታም መለሰ የሚባል የአረመኔው አገዛዝ አሽከር የነበረ ሚሊሻ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር አብራጂት ብርጌድን ተቀላቅሏል። 4ኛ. አበረ ገበረጌታ የተባለ የአረመኔው አሽከር ሚሊሻ ከየጁቤ ከተማ በመውጣት የአብራጂት ብርጌድን የተላቅሏል። 5ኛ. እውነቱ ምትኩ የተባ  የሚኒሻ አባል ከደብረ -ወርቅ ከተማ በመክዳት  9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር ሶማ ብርጌድ ተቀላቅሏል። ሕዝባዊ ውይይቶችና ምክክሮች በአንደኛ ክፍለጦር እና 7ኛ ክፍለጦር  ነፃ ቀጠና ቀበሌዎች ተደርገዋል። በውይይቱም ሌቦችን በጥቆማ መያዝ እና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ተችሏል። አዲስ ትውልድ፡አዲስ አስተሳሰብ፡ አዲስ ተስፋ!!      አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ጳጒሜን 02/2017ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የዛሬው ዝግጅት በተመለከተ! የሚጀምርበት ሰዓት:- በኢትዮጲያ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ለሊቱ ስድስት ሰዓት ይቆያል። የመክፈቻ ንግግር በአርበኛ ዘመነ ካሴና በአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ (የተቀዳ)
+1
የዛሬው ዝግጅት በተመለከተ! የሚጀምርበት ሰዓት:- በኢትዮጲያ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ለሊቱ ስድስት ሰዓት ይቆያል። የመክፈቻ ንግግር በአርበኛ ዘመነ ካሴና በአርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ (የተቀዳ) ይቀርባል። እንግዶች:-  ጥያቄና መልሱን ከጋዜጠኞቹ ጋር በአርበኛ ብሩክ ስለሺ፣ በአርበኛ ሄኖክ አዲሴ እና አርበኛ ፕሮፌሰር ማርከው መንግሥቴ ይደረጋል። (Live) በተጨማሪም በአፋብኃ አመራሮች አፋብኃ የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች በዝርዝር ያቀርባሉ። (Live) የዛሬ ተረኛ ጋዜጠኞች ሙሉጌታ አንበርብር፣ መዓዛ መሐመድ፣ ቀለብ ስዩም እና አዲሱ ደረበ ቴክኒክ ክፍሉን ምስጋናው ከፈለኝ ይመራዋል። ዝግጁቱ በሁሉም የአማራ ሚዲያ ካውንስል አባላት እና በEMS; በFree Press እና በአንከር ሚዲያ ይተላለፋል። መልካሙን ሁሉ ይግጠመን። ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥#ህዝባዊ_ውይይቶች_እንደቀጠሉ_ናቸው‼️ በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር ኮረኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ጳግሜ በ02/13/2017 ዓ.ም በአቢዮት ፋና ቀበሌ
🔥#ህዝባዊ_ውይይቶች_እንደቀጠሉ_ናቸው‼️ በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር ኮረኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ  ጳግሜ በ02/13/2017 ዓ.ም በአቢዮት ፋና ቀበሌ ኩርኩሪት ጊዮርጊስ በጣም አመርቂ ህዝባዊ ውይይት ማካሄድ ችለናል። በእለቱ ወቅታዊ ፖለቲካዊ የትግል ሂደት የግል የጦር መሳሪያ እና ሁለንተናዊ ድጋፍን በተመለከተ ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ በጋራ ጠላትን ለማስወጣት እና በአካባቢያች ስርቆቶችን ለማስቀረት ከህዝባችን ጋር ተባብረን ለመስራት ተስማምተን ወደ ስራ ገብተናል። ©ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 1ኛክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት 02/13/2017 ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አፋጎ ወደ አፋብኃ መመለሱን ተከትሎ ያ ሁሉ መንጋ ጎጠኛ ድራሹ መጥፋቱ በጣም ነው የገረመኝ። አሁን ደግሞ አፍኃድ በአንድነቱ ዙሪያ ያለው አቋም መልካም ጅምር ነው። ነገር ግን አንድነቱ በጣም ጥንቃቄ
አፋጎ ወደ አፋብኃ መመለሱን ተከትሎ ያ ሁሉ መንጋ ጎጠኛ ድራሹ መጥፋቱ በጣም ነው የገረመኝ። አሁን ደግሞ አፍኃድ በአንድነቱ ዙሪያ ያለው አቋም መልካም ጅምር ነው። ነገር ግን አንድነቱ በጣም ጥንቃቄ የሚጠይቅ ነው። አፋሀድ ውስጥ በርካታ ብልጽግናዎች አሉ። ሲቀጥል እኛ ነፃ ለማድረግ የምንታገለውን ያህል የብልጽግና ቡድንም ሰርጎ ለመግባት በጣም ይጥራል። በጥንቃቄ አንድነቱ ካለቀ ሌላው እዳው ገብስ ነው።    በነገራችን ላይ የፋኖን አንድነት የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን 80% የብልጽግና የጸጥታ መዋቅር በአንድ እግሩ ቆሞ እየጠበቀ እንዳለ፣ በስርዓቱ በጣም እንደተማረሩ ሁሉም የጸጥታ አመራር ስራውን ትቶ ከሀገር ለመውጣት ሀብት ስብሰባ ላይ እንዳሉ(በተለይ ከፍተኛ የጸጥታ አመራሮች ከጀኔራሎች ጀምሮ) አንድ የፌደራል ፖሊስ ጓደኛዬ ነግሮኛል። እውነት ነው የምላችሁ ፋኖ ሰላሌ ደረሰ ከተባለ አአ እንኳን ጥይት የሚተኩስ አካል ቆሞ የሚገኝ አንድ ካድሬ አይኖርም ሁሉም ወደ ሞያሌ ሩጫ ነው። ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

📌የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሲምፖዚዬም ዛሬም በደማቅ ዝግጅት ይቀጥላል! በትላንትናው ዕለት ጷጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ.ም የተካኼደው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሲምፖዚዮም በዛሬው ዕለትም ልዩ ዝግጅቶችንና ሰርፕራይዞችን አካቶ ይካሄዳል። አፋብኃ ድርጅቱን እያስተዋወቀ፣ የቀጣይ የትግል ምዕራፎችን በተጠናከረ ነባራዊ ሁኔታ ለማካሄድ መሠረት እየጣለ ይገኛል። እናንተም በዚሀወ ዝግጅት ላይ እየተሳተፋችሁ፣ ድጋፍ እያደረጋችሁ አብራችሁን ቆይታ እንድታደርጉ ተጋብዛችኋል። ዝግጅቱ በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ይተላለፋል። ዝግጅቱ:- በአማራ ሚዲያ ካውንስል አባላት ሚዲያዎች በFree Press; EMS; Anchor Media እና በሌሎች የትግሉ ደጋፊዎች ይተላለፋል። ድጋፍ ማድረጊያ አማራጮች:- የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን ለመደገፍ  በ አሜሪካ Zelle 202 528 6749     Canada ላላችሁ e_transfer 780 802 5536    በዌብሳይት ለመርዳት የ ምትፈልጉ https://amharafanonationalforce.org/ የአፋብኃ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች X - https://x.com/amharafanonf?s=21 Telegram - https://t.me/AmharaFanoNationalForc ሁላችንም በሰዓቱ እንገናኝ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል - አፋብኃ!

ከደብረታቦር ከተማ በቅርብ ርቀት አቄቶ አከባቢ በአገዛዙ ኃይሎች ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት 20 ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ። መነሻቸውን የደቡብ ጎንደር ዞን መቀመጫ ከሆነችው ደብረ ታቦር ከተማ አድርገው ወደ እስቴ መካነየሱስ ከተማ ሲጓዙ የነበሩ የፀረ አማራው አገዛዝ ስልጣን አስጠባቂ ወታደሮች፡ ልዩ ስሙ አቄቶ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ሲደርሱ በተፈፀመባቸው ደፈጣ ጥቃት 13 ወታደሮች ሲገደሉ፡ ሰባት ወታደሮች ደግሞ በከባድ ሁኔታ መቁሰላቸውን መረብ ሚዲያ በአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ከሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማመጋገጥ ችሏል።በዚህ ደፈጣ ጥቃት ከተገደሉ የአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሕዝብን አደራ በምስር ወጥ ለውጠው እጃቸውን ለአገዛዙ ሰጥተው የነበሩ ከሃዲ ባንዳዎች ይገኙበታል ተብሏል። ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ጳጉሜ 01/2017 ዓ/ም ሲሆን፡ ጥቃቱን በመፈፀም ድል የተቀዳጁት ደግሞ አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር በጉና ክፍለ ጦር መቅደላ አምባ ብርጌድ ስር የሚገኙት የናደው ሻለቃ አባላት መሆናቸውን መረብ ሚዲያ ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ጳግሜ 2/2017/ዓ.ም ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

''፻ አለቃ አዳነ ጤና የህይወት ታሪክ" ፻ አለቃ አዳነ ጤና በደባይ ጥላትግን ወረዳ መውላድ ቀበሌ በ1983 ዓ.ም ተወለደ።፻ አለቃ አዳነ ጤና በአማራ በፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዥ በመሆን አገልግሏል።መቶ አለቃ አዳነ ጤና በተሰጠው የስራ ኃላፊነት በብቃት በመወጣቱ የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ዛሬ ላይ ላለበት አቋም እንዲበቃ አድርጓል። ፻ አለቃ አዳነ ጤና በአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር ከሚገኙ አምስቱ ብርጌዶች የደጀኑ ዛንበርሀ ብርጌድ፣የሸበል በረንታው ሽፈረው ገርበው ብርጌድ፣የእነማዮ አባ ኮስትር ብርጌድ፣የደባይ ጥላትግኑ ደባይ ጮቄ ብርጌድ፣የእናርጅ እናውጋው ሶማ ብርጌድን በማደራጀት በክፍለ ጦሩ የውጊያ ዕቅድ በማውጣት ታላላቅ የተጠኑ አውደ ውጊያዎችን አድረጓል። መቶ አለቃ አዳነ ጤና በደብረ ማርቆስ ሁለት ጊዜ የከተማ ልዩ ኦፕሬሽን እንዲሁም በደብረወርቅ ጠባቢት ሚካኤል ላይ ጠላትን የረፈረፈ ጀግና ነበር።ደብረወርቅ ጠባቢት ሚካኤል ላይ በመራው አውደ ውጊያ የመቁሰል አደጋ ቢገጥመውም የኔ መቁሰል ከወገኔ ስቃይ አይበልጥም በማለት ትግሉን ወደፊት በመምራት የራሱን አሻራ አስቀምጧል። መቶ አለቃ አዳነ ጤና መስከረም 26/2017ዓ.ም በደባይ ጥላትግን ወረዳ የሚገኜው የጠላት ሀይልን ለመደምሰስ ከአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ውጊያውን በመንደፍ በደባይ ጥላትግን ወረዳ የሚገኜውን ደባይ ጮቄ ብርጌድ እና የእነማዩ አባ ኮስትር ብርጌድን በመምራት በደባይ ጥላትግን ወረዳ ቁይ ከተማን በመቆጣጠርና እስረኞችን በማስለቀቅ በተደረገው ትንቅንቅ የተገኘው ድል የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ፻ አለቃ አዳነ ህዳር 27/2017 ዓ.ም በተወለደ በ34 ዓመቱ በአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች በደጋ ዳሞት/ፈረስቤት በነበርው የክፍለ ጦሩ በነበርው ስብሰባ እንደተመለሰ የጠላት ጥምር ጦር በእነማይ ወረዳ እና ደባይ ጥላትግን ወረዳ የጮቄ ተራራማ ቦታዎችን ለመያዝ አራት ቀን በተንቀሳቀሰበት ሰዓት በደባይ ጥላትግን ወረዳ ናብራ ከተማ የሚገኜው ናብራ የመጀመርያ ደርጃ ት/ቤት በተፈፀመ የድሮን ጥቃት አብርውት ከነበሩ የትግል ጓዶች ፋኖ አባይነህ ምህረቱ፣፻ አለቃ ንጉስ ደጓለ፣፻ አለቃ፣ፋኖ ሙንየ አስማረ ጋር ለአማራ ህዝብ አንድያ ነፍሱን አሳለፎ ሰጠ። ይህ ጀግና በአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ደባይ ጮቄ ብርጌድ የዳማ 3ኛ ሻለቃ #መቶ-አለቃ አዳነ ጤና ሻለቃ ተብሎ ተሰይሞለታል። ወንድማችን ፻አለቃ አዳነ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑራት😭😭😭 ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አፋብኃ የሴት ፋኖዎች💪💪💪 ====================== የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር #ደጋዳሞት_ብርጌድ_የሴት_ፋኖ አባላት።
አፋብኃ የሴት ፋኖዎች💪💪💪 ====================== የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር #ደጋዳሞት_ብርጌድ_የሴት_ፋኖ አባላት። ጳጉሜ/02/13/2017 ዓ.ም ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

◊◊ የአደረጃጀት ዜና        የአማራ ህዝብ ትግል ዘመን ተሻጋሪ ሁነቶችን እያለፈ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሷል። በእነዚህ ዘመን ተሻጋሪና ተቀያያሪ ሁነቶች ውስጥ የትግሉ እድገትና እመርታ የሚጠቀስ ነው። ሆኖም በዚህ የትግል እድገት ውስጥ የሰው ሃይል፣ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊ ፣ ዲኘሎማሲያዊ ብሎም ወታደራዊ አደረጃጀት ቅርጽና ወጥ የሆነ የአሰራር መርሆዎች ተዘርግተውለት ወደ ተሻለ የትግል ምዕራፍ መሸጋገር ላይ እንገኛለን። በዚህም የተነሳ ትግላችን ባሳየው ለውጥና እድገት እንዲሁም በርቀት የምንመለከተውን ትልቁን የአላማችንን ስእል ለማሳካት የአመራር ድልድል / Reform  አስፈላጊ ሆኖ ተገንቷል።        በመሆኑም  ከዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር አብራክ የሚጠቀሰው ንስር በለሳ ቅጣው ክ/ጦር  የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የክ/ጦሩ አባላት በሙሉ በተገኙበት የአመራር ድልድሉ ተሰርቷል።          1/    ዋና ሰብሳቢ _ አርበኛ ባንተ ዘለቀ 2/    ም/ሰብሳቢ_አርበኛ አብራራው ፀጋየ 3/   ወታደራዊ አዛዥ___አርበኛ ይዘዝ ፍቃዴ 4/   ም/ወታደራዊ አዛዥ__አርበኛ ሙሉቀን ዮሃንስ 5/    ዘመቻ ዘርፍ ኃላፊ___አርበኛ አድኖ አስማረ 6/  ም/ዘመቻ ዘርፍ ኃላፊ _አርበኛ ታድሎ ባብየ 7/   ጽ/ቤት ኃላፊ ___አርበኛ ባምላኩ ምህረት 8/   ፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ___ አርበኛ ጣማለው ወልዴ 9/   ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ_አርበኛ መልከ ጸዴቅ 10/   ፋይናስ  ኃላፊ__አርበኛ ቢክስ ተዘራ 11/   ሎጅስቲክ ኃላፊ _አርበኛ ደሞዝ ማሞ 12/  አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ __አርበኛ ማስረሻ አለምነው 13/  ህ/አስተዳደር ኃላፊ _አርበኛ ሻ/ ኤርሚያስ 14/  አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ____አርበኛ አዛናው አሻግሬ 15/  ት/ትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ __አርበኛ ሰፊ መብራት 16/  ህግና ስነምግባር ኃላፊ _አርበኛ አቤሴሎም ተበጀ 17/  መረጃና ደንነት ኃላፊ _+_+**         በስተ መጨረሻም የተመረጡ የክ/ጦሩ አመራሮች ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን የኮሩ የስራ አስፈፃሚ አባላትም መልእክት በማስተላለፍ የእለቱ ኘሮግራም ተቋጭቷል።  አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግ/ቴዎ/፭ኛ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ➤አብነት ሞላ                                       ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ከተማዋን ተቆጣጠሩ በዘመቻ ሰመአታት በርካታ ተጋድሎወችን ሲያደርግ የሰነበተው አፋብሀ ምእራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ሀዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለጦር በባሶ ሊበን ወረዳ የምትገኘውን ታዳጊ ከተማ #የ
+1
ከተማዋን ተቆጣጠሩ በዘመቻ ሰመአታት በርካታ ተጋድሎወችን ሲያደርግ የሰነበተው አፋብሀ ምእራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ሀዲስ ዓለማየሁ 7ኛ  ክፍለጦር በባሶ ሊበን ወረዳ የምትገኘውን ታዳጊ ከተማ #የላምጌጅን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል። ጠላትም ወደ ወረዳው ዋና ከተማ የጁቤ ጓዙን እያንጠባጠበ ፈርጥጧል። ህዝቡም በአደባባይ ደስታውን እየገለጸ ነው። በዘመቻ ሰማእታት ሀዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለጦር ከዚህ በፊት ኮርክ ከተማን በቋሚነት መቆጣጠሩ የሚታወስ ነው። አበጀ በለው ገርዬ ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

በጎንደር ከተማ አፈሳ ተጀመረ ትላንት ማምሻውን ጀምሮ ዛሬም የነቁ ወጣቶች ላይ እና የፋኖ ቤተሰቦች ላይ ያነጣጠረ አፈሳ መጀመሩን ምንጮች ለኢትዮ 251 ገልፀዋል። ከፌደራል በመጡ ደህንነቶች አፈሳው እንደሚመራ የተገለፀ ሲሆን ፌደራል ፖሊስ፣ መከላከያ ፣ ምሊሻ ሌሎችም የአገዛዙ የፀጥታ ሀይሎች እየተሳተፉበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እንደ መረጃ ምንጮቻችን ገለጻ፣ በተለይ ባለፉት ወራት አገዛዙ ጎንደር ከተማ ላይ በርካታ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ሀይሎችን እንዳስገባና  እንዳሰማራ ምንጮች የገለፁ ሲሆን ጎንደር ከተማ ላይ የሚፈፀሙ እገታዎች ግን እንደተስፋፉ ገልፀዋል። እገታዎቹ የአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎች እንደሚሳተፉባቸው ለማወቅ ተችሏል። ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 04 የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ተወስዳ የተገደለችው ቤተሰብ አስተዳዳሪና የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ራሔል አፈና እና ግድያ ጀርባ በአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎች እንደተመራ በስፋት እየተገለፀ ነው። የዛሬ አመት ማለትም ነሐሴ 27 2016 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ኖላዊት ዘገየ የተባለች የሁለት አመት ልጅ ታግታ ተገድላ በወላጆቿ መኖሪያ ቤት አስክሬኗ ተጥሎ መገኘቱ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶ እንደነበር የሚታወስ ነው። የክልሉ መንግስት በወቅቱ የመንግስት የፀጥታ አካላት በህፃኗ ግድያ መሳተፋቸውን አምነው መግለፃቸው በወቅቱ አናጋጋሪ ሆኖ ነበር። አሁንም በክልሉ ላይ የሚደረጉ አፈና፣ ግድያ ሌሎች ወንጀሎች በአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎች እንደሚመሩ ምንጮች ገልፀዋል። አገዛዙ ከተለያዩ አካባቢዎች ምርጥ 10 ብሎ የሰበሰባቸው ሚሊሻዎች በበርካታ ወንጀሎች የተጨማለቁ እና አብዛኛዎቹ በደም ምክንያት ወደ ትውልድ አካባቢያቸው መመለስ የማይችሉ እንደሆኑ የመረጃ ምንጮች የገለፁ ሲሆን፤ በአገዛዙ በኩልም ነፃ የዘረፋና የእገታ ስልጣን እንደተሰጣቸው ታውቋል። በጎንደር ከተማ ከፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን በናቃቸው የሚመራው ምርጥ 10 ተብሎ የሚጠራው የአገዛዙ ሚሊሻ  ከደፈጫ እስከ አንቦ በር ፈንጠርን ይዞ  ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ አፈናና በደል እያደረሰ እንደሆነ የኢትዮ 251 ምንጮች ገልፀዋል። ትላንት ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት የተጀመረው አፈሳም መቀመጫውን ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ያደረገ የፌደራል ደህንነቶች እንደሚመራ እና ከሌሎች የአገዛዙ ፀጥታ አካላት ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ለማወቅ ተችሏል። የጎንደር ከተማ ወጣት ጥንቃቄ እንዲያደርግና ራሱን እንዲከላከል የመረጃ ምንጮች አክለው ገልጸውናል። ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk