en
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
3 615
Subscribers
+1324 hours
+4187 days
+1 05630 days
Posts Archive
ለደብረ ማርቆስ ከተማና ለአካባቢው ማህበረሰብ ከ206ኛ ኮር የተላለፈ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት!! የካቲት 27/2018 ዓ.ም ================================ በአማራ ህዝብ ትግ
ለደብረ ማርቆስ ከተማና ለአካባቢው ማህበረሰብ ከ206ኛ ኮር የተላለፈ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት!! የካቲት 27/2018 ዓ.ም ================================ በአማራ ህዝብ ትግል ፈር ቀዳጅ እንቅስቃሴ በማድረግ ወደር የለሽ ሚና ሲወጣ የነበረው የደብረ ማርቆስ ከተማ ማህበረሰብ ትግሉ እዚህ ደረጃ እንዲደርስና አደረጃጀቶች ጎልብተው ጠንካራ ወታደራዊ አቅም እንዲገነቡ ፣ ጠንካራ ግዳጆችን በጠላት ላይ እንዲያሳርፉ ላበረከተው ከባድ አስተዋጽኦ 206ኛ ኮር ምስጋናውን ያቀርባል። ይሁን እንጂ ይህንን የህዝብ ቀና ተሳትፎ እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀሙ አንድአንድ አካላት በኮሩ፣ በክ/ጦርና፣ በሻለቆች እንዲሁም በተዋቂ ሰዎች ስም በማጭበርበር ከህብረተሰቡ ገንዘብ እንደሚሰበስቡ ደርሰንበታል። በህዝቡ ጥያቄና ጥቆማ መሰረት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የፋይናስ መመሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 6.7 የተቀመጠው የተቋም አሰራር ይተገበር ዘንድ 206ኛ ኮር መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ የደብረ ማርቆስ ከተማ እና የአካባቢው ማህበረሰብ ከአጭበርባሪዎች እና ከዘራፊዎች እራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን። ከዚህ ጋር በተያያዘ ድርጅታዊ አሰራርን ተላልፎ ከህዝቡ ባልተገባ መንገድ ሀብት የሚሰበስቡ፣ ማህበረሰቡን የሚያጭበረብሩ አካላትን በመከታተል ኮሩ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወስድ ያረጋግጣል። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር!!

ሰበር የድምሰሳ ዜና !! የካቲት 27/06/18! ዓ.ም አፋብን ቴ/ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር እና 22ኛ ክ/ጦር በጥምረት በመልሶ-ማጥቃት በሜጫ ቀጠና በተለያዩ ግንባሮች ኮሩ ድል ተቀዳጅቷል!! ጠላት ከተለያዩ አጎራባች ወረዳዎች ጭምር ከትናት ምሽት ጀምሮ ያለዉን ሐይል እና ትጥቅ በማቀናጀት ወደ ሜጫ ቀጠና በማንቀሳቀስ የማጥቃት ዘመቻ በዛሬዉ ዕለት አድርጎል። በቀጠናዉን ላይ ያለዉን የወገን ሐይል ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ በተለይም አማሪት ቀጠና ላይ ያደረገ ሲሆን ዉጊያን እንደ ቼዝ የሚጨዋቱት የአበረ ይማም ልጆች በጠላት የዉጊያ ዕቅድ ዉስጥ ገብተዉ እንደ ሰደድ እሳት ጠላት ለብልበዉታል። ጠላት እንደ ፈረስ እየጋለበ ቢገባም እንደ ኤሊ እያዘገመ በእጀ እየተጨበጠ ተማርኮል። በዕለቱ የተገኙ ምርኮዎች:-. ➤የተደመሰ ጠላት---97 ➤የተማረከ ጠላት----35 ➤ብሬን----01 ➤አይኮም ሬዲዮን---02 ➤የክላሽ ተተኳሽ----2510 ➤የብሬን ተተኳሽ----520 ኮሩ በዕለቱ የተመዘገበዉ ድል በአማራ ህዝብ የትግል ታሪክ ዉስጥ በፊት ዓዉራሪነት ለሚወሳዉ ለአርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ መታዋሻ ይሁልኝ ብሏል። ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!! አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት 👇 https://t.me/fanofano2112

ሰበር የድምሰሳ ዜና !! የካቲት 27/06/18! ዓ.ም አፋብን ቴ/ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር እና 22ኛ ክ/ጦር በጥምረት በመልሶ-ማጥቃት በሜጫ ቀጠና በተለያዩ ግንባሮች ኮሩ ድል ተቀዳጅቷል!! ጠላት ከተለያዩ አጎራባች ወረዳዎች ጭምር ከትናት ምሽት ጀምሮ ያለዉን ሐይል እና ትጥቅ በማቀናጀት ወደ ሜጫ ቀጠና በማንቀሳቀስ የማጥቃት ዘመቻ በዛሬዉ ዕለት አድርጎል። በቀጠናዉን ላይ ያለዉን የወገን ሐይል ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ በተለይም አማሪት ቀጠና ላይ ያደረገ ሲሆን ዉጊያን እንደ ቼዝ የሚጨዋቱት የአበረ ይማም ልጆች በጠላት የዉጊያ ዕቅድ ዉስጥ ገብተዉ እንደ ሰደድ እሳት ጠላት ለብልበዉታል። ጠላት እንደ ፈረስ እየጋለበ ቢገባም እንደ ኤሊ እያዘገመ በእጀ እየተጨበጠ ተማርኮል። በዕለቱ የተገኙ ምርኮዎች:-. ➤የተደመሰ ጠላት---97 ➤የተማረከ ጠላት----35 ➤ብሬን----01 ➤አይኮም ሬዲዮን---02 ➤የክላሽ ተተኳሽ----2510 ➤የብሬን ተተኳሽ----520 ኮሩ በዕለቱ የተመዘገበዉ ድል በአማራ ህዝብ የትግል ታሪክ ዉስጥ በፊት ዓዉራሪነት ለሚወሳዉ ለአርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ መታዋሻ ይሁልኝ ብሏል። ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!! አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት

ግልጽ የዘረፋ ተግባር በደብረ ኤልያስ ከተማ‼️ በዘረፋ ተግባር የተጠመደው ደብረ ኤልያስ ከተማ ላይ ተሰብስቦ ንጹሐንን እየዘረፈ የሚገኘው የብልጽግና ካድሬ ዛሬም የተለመደ የዘረፋ ተግባሩን አጧጡፎ ይዞታል። ነገሩ እንዲህ ነው። ከሰሞኑ ለተወሰኑ ሳምንታት የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በየከተሞች ተፈጥሮ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ይህም ቢሆን ራሱ የብልጽግናው አውዳሚ ሥርዓት የፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ነው። በዚህም መሠረት በዛሬው ዕለት በብዙ መከራ ወደ ደብረ ኤልያስ ከተማ የገባውን የነዳጅ ክምችት በአግባቡና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለተጠቃሚው በማድረስ ፈንታ በስርቆትና ዘረፋ ወዝ የጠገበው ይህ ስብስብ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ገንዘብ እየተቀበለ ሕብረተሰቡን እየበዘበዘ ይገኛል። እንደ መዥገር ተጣብቆ ማሕበረሰቡን እየመጠመጠ የሚገኘው የብልጽግና የሌባ ስብስብ በዛሬው ዕለት በካሶኒና ሲኖትራክ 2000 ብር፤ በአይሱዙ፣ ኦባማና የሕዝብ ማመላለሻ 1000 ብር፤እንዲሁም በባጃጅ 500 ብር በመቀበል ከፍተኛ ዘረፋ እየፈጸመ ይገኛል። የካቲት 27/2018 ዓ.ም ድል ለሕዝባችን ©የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት 27/ዐ6/2018 ዓ.ም

201ኛ ኮር ህግ አና ስነ_ሰርዓት በዘርፉ ለ54ክ/ጦር ለ3 ወረዳወች ቢቡኝ፣ ሰዴ፣ ሞጣ ሁለት እጁ እነሴ አመራሮች ግምገማ እና የአቅም ማጎልበቻ ስለጠና ተሰጠ። ➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾ የካቲት 2
+2
201ኛ ኮር ህግ አና ስነ_ሰርዓት በዘርፉ ለ54ክ/ጦር ለ3 ወረዳወች ቢቡኝ፣ ሰዴ፣ ሞጣ ሁለት እጁ እነሴ አመራሮች ግምገማ እና የአቅም ማጎልበቻ ስለጠና ተሰጠ። ➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾ የካቲት 27/2018 ዓ.ም ከመቸውንም ጊዜ በላይ የድርጅታችን ዋነኛ ቀይ መስመር የሆነው ህዝባችን ስለሆነ በእያንዳንድ አገልግሎት አሰጣጥ በተደራጀ ግልፅ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በየአካባቢው ፍትህን የማረጋገጥ ስራ ከምንም በላይ ነገሮችን በሽምግልና እንዲፈቱ በማድረግ መሠራት እንዳለበት እና በድርጅታችን መመሪያ መሰረት ተጠያቂነትን ለማስፈን ችግሮችን በመለየት የአቅም ማጎልበት እና ክፍተቶችን በመሙላት የግንዛቤ ትምህርተ በመስጠት የቀጣይ ስራ አቅጣጫወችን መስጠት ተችሏል። < ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም > የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የህግና ስነ_ስርዓት ኃላፊ ዋና ሳጅን አንላይ አምባየ

የአድማ ብተና አመራሮች ፋኖን ተቀላቀሉ‼️ የካቲት 27/2018 ዓ/ም የአድማ ብተና አባላት ዛሬም እንደትናንቱ ከጠላት ካፕ በመኮብለል 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር የፋኖ አባላትን እየተቀላቀሉ ነው። 1ኛ ግርማ ገበያነህ ቲም መሪ 2ኛ ይገርማል ታገለ መቶ መሪ የተባሉ የአድማ ብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከይስማላ አካባቢ ከሚንቀሳቀሰው የጠላት ሀይል በመውጣት የ105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር የፋኖ አባላት ተቀላቅለዋል። አባላቱም የአብይ አህመድና የሽመልስ አብዲሳ ተልኮና ሴራ አውቀነዋል፣አማራን እርስበርሱ ማጋደልና በኛ ደም ስልጣናቸውን ማሥቀጠል ይፈልጋሉ ብለዋል። አባላቱም አክለው አገዛዙ ጋር በመሆን የአማራን ህዝብ ሲቃይና መከራ በማራዘማችን ይቅርታ እንጠይቃለን፣ከዚህ በኋላ ግን ከህዝባችንና ከፋኖ ወንድሞቻችን ጋር በመሆን የአረመኔውን አገዛዝ ለመፋለምና ለማስወገድ ቃል እንገባለን ብለዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️‼️ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት አበጀ በለው ገርዬ

የአማራ ፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተአታተለ ሁሌም ለመላው የትግሉ ደጋፊዎች የሚያደርሰው የTikur Sewu የፊስ ቡክ አካውንት በአገዛዙ ተዝግቶ በአዲስ አካውንት ተመልሰናል ስለዚህ ከታች ሊንኩን አስቀምጣለሁ ይወዳጁት!! https://www.facebook.com/profile.php?id=61586419632071

303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር መጠነኛ የአመራር ማሻሻያ አደረገ!        የካቲት:-27/2018 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር የካቲት 23/2018 ዓ/ም የኮሩን አመራር መልሶ ማደራጀቱ ይታወቃል። ስለሆነም አንዳንድ የአመራር ቦታዎች ካለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ የአመራር ብቃት፣ ሙያና ተገቢነት፣ የስራ ልምድ መጠነኛ ማሻሻያ አድርጓል። በዚህ መልሶ ማደራጀት መሠረት 1ኛ. የሰው ኃይል መምሪያ:- አርበኛ ባለሟል ሽመልስ እና 2ኛ. ኦዲተር:- አርበኛ ጥጋቡ ሲሳይን ኮሩ የመደበ ሲሆን 3ኛ. የኮሩ ፖለቲካ አማካሪ ተመድበው የነበሩት አቶ ፍቅረማርያም ደሴ በሌሉበት፣ ባልተገኙበት ተመድበው የነበረ ቢሆንም ኮሩ ይህንን አይነት አሰራር በማስተካከል ከዛሬ የካቲት 27/2018 ዓ/ም ጀምሮ ከተመደቡበት ኃላፊነት ያነሳቸው መሆኑንና በአጭር ጊዜ ውስጥ በሌላ አማካሪ እንደሚተካቸው ኮሩ ያሳስባል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 27/2018 ዓ.ም

ሃያ አምስት (25) የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት በሻምበል አዛዣቸው እየተመሩ ፋኖን ተቀላቀሉ! የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር ሃያ አምስት (25) አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በሻምበል አዛዣቸው እየተመሩ ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ! የብልፅግናው አገዛዝ ያለ ጦርነት መኖር እንደማይችልና አሁንም በኢትዮጵያውያን መካከል ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማካሄድ ዝግጅት መጨረሱን ተከትሎ ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም በርካታ የብልፅግና ጥምር ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለ ሲሆን ደቡብ ወሎ ዞን እየተንቀሳቀሰ ያለው 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 83ኛ ክፍለ ጦር የሰራዊቱ አባላት ክፍላቸው ውጊያ እያደረገ ባለበት ሁኔታ ተደራጅተው ወደኋላ በመውጣት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል:: ይሄ ክፍል በቅርቡ ሁለት ሞርተር በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ከእግረኛ ሰራዊቱ ጋር ተንታና መቅደላ ላይ መማረኩ ይታወሳል:: በመጨረሻም ብልፅግና ሰራዊቱን ገዥ በሆነ አገርና ህዝብ አሻጋሪ አጀንዳ የሚይዝበትና የሚያታግልበት ሁኔታ እንደሌለና ከዚህ በኋላ በውሸት ሰራዊቱን የሚያስጨርስበት ጊዜ ማብቃቱን የሰራዊቱ አመራሮችን ጨምሮ እየፈረሰ በቡድን ፋኖን መቀላቀሉ ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ የሰራዊቱ አባላቶች ገልፀዋል::  መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 27/2018 ዓ.ም

Kaleb Solomon በአራት ኪሎ ጀንበር ላይ የቆመ ግርዶሽ ። አማራ መሲሑን እያገኘ ይመስላል ዘንዘልማ ላይ የፈሰሰው ደም በእጥፍ ከሚወራረድበት ዋዜማ ላይ ቆመናል አማራ ሙሴውን አስበልቶ ኢያሱውን ላለመስደገም በሚፋለምበት ታሪካዊ ጊዜ ላይ ቆሟል ። ኢያሱ በገባዖን ፀሀይን እንዳቆመ የአራት ኪሎን ፀሀይ የሚጋርድ ሌላ ኢያሱም ከአማራ ምድር ተወልዷል ። ከአራት ኪሎው ፀሀይ በፊትም የባህርዳሩ ጀንበር ይጠልቃል ። አሁን የአማራ ሰማይ ፋኖ ከሚባል ፀሀይ ውጪ ሌላ ፀሀይ የሚሸከምበት ጊዜው አብቅቷል አፈሙዞች ሁሉ ወደ ባህርዳርና አዲሳባ ይዞራሉ ። ከዳግማይ ሰኔ 15 በፊት ። አርበኛ ዘመነ ካሴ ይባላል የአማራን መከራ መስቀል ተሸክሞ የቀራኒዮን ተራራ መውጣት ከጀመረ ሰነባብቷል ከሆሳዕና በኋላ ያለችው አርብም ፋኖ መንደር ገብታለች ። ከፅንሰቱ ጀምሮ ተስፋውን ለማጨለም የተነሳው ሄሮድስ ዐቢይ "ዓሳውን ለመያዝ ባህሩን አምሰው" በሚል ብሂል የነቃና የተደራጀ አማራ እንዳይፈጠር በርካታ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አሻጥሮችን ፈፅሟል ። : በአሳምነው መቃብር ላይ ተሞሽሮ በአማራው ሰቆቃ ላይ ዳንኪራ ረግጧል እነዚህ ሁሉ ፋኖን ተወልዶ ከመዳኽ ድኾ ከመቆም ቆሞ ከመራመድ አላስቆሙትም ። አሁን ፋኖ ዘንዶ አህሎ ፋሽስቱን ሊውጠው እንደሚያገሳ አንበሳ ዙሪያውን እየዞረው ይገኛል ። አፋብን የነ አይሻ ሰዒድ የእምባ መልስ ። የአፋብን አዲሱ ግምባር ባህርዳርና አራት ኪሎ ነው አማራው ከጀርባ የተመታው ከባህርዳርና ከአራት ኪሎ ምሽግ ነው ። በትላንት ቁስሉ ላይ ተጨማሪ ጨው የሚነሰንስ የሞት አዋጅ የታወጀበት እና ህልውናውን አደጋ ውስጥ የሚጥል ቃታ የተሳበበት ከሁለቱ ምሽጎች ነው ዛሬ የአብይን ስልጣን ለማፅናት ውድ ነብሱን ለኦሮሙማ የሚያከራይ አማራ የለም እንደ ውሻ ጃስ ብለህ በትግራይ ላይ ፈተህ የምትለቀው አንገቱ ላይ ሰንሰለት የታሰረለት ፋኖ የለም ዛሬ አማራው የኦህዴድ የሳሎን ውሻ አይደለም ! ትግራይ ስምረትና TPF የሚባሉ እንግዴዎችን እንዳበቀለች ሁሉ አማራውም አንድ ብአዴን የሚባል የመንደር ውሻ አለው ይህ ውሻ ከአራት ኪሎ መመሪያ ተቀብሎ ፋኖን አዳክሞ ለመበተን የሴራ ጅራፉን ገምዶ መጋረፍ ከጀመረ ሰነባብቷል ። ፋሽስቱ ጭንቅላቱ አራት ኪሎ ይሁን እንጂ አንገቱ ባህርዳር ነው ፋኖ መብረቃዊ ጥቃት ከፍቶ ይህን አንገት በመቁረጥ በ45 ደቂቃ ኦፕሬሽን የባህርዳርን የሀይልና የስልጣን ሞኖፖሊ ያለ ምንም ከልካይ ይቆጣጠራል ። የአገዛዙ የባህርዳር የሀይል ክምችት እየሳሳ ነው አገዛዙ ትግራይን ለመውጋትና አስመራን ለመጨበጥ በተንቀሳቀሰ ቅፅበት በባህርዳርና በአማራ ላይ ያለው የብረት መዳፉ ሙሉ ለሙሉ ይሰበራል ። : የአረጋ ከበደ የዕዝ ማዕከልም የከሀዲ ፖለቲከኞች ስደተኛ ካምፕ ወደ ሆነችው አዲሳባ ይዛወራል ከባህርዳር እየተነሱ ትግራይንና ኤርትራን የሚደበድቡ የጦር ጀቶችም በፋኖ ምትና ጥቃት ያፈገፍጋሉ ። አብይ አሁን ደጀኔ የሚለው የአማራ ህዝብ የለም እርግጥ ስኳድና ተከዜ ዘብ በሚባሉ ወይዛዝርቶች ቀሚስ ስር ይሸሸግ ይሆናል ። ፋኖ ባህርዳርን ሙሉ ለሙሉ በተቆጣጠረ ቅፅበት የአገዛዙ የሀይል ሚዛን ሙሉ ለሙሉ ይናጋል የአራት ኪሎ መንገድም የውሃ ጉዞ ይሆናል ። አፋብን ሸዋ ቀጠና ትንፋሹ በአገዛዙ አንገት ላይ የሚሰማ የሰሜኑ የእሳት አጥር ነው ይፋት ጣርማ በርና ኤፍራታ ግድም ላይ እግሩን ተክሎ አራት ኪሎን በመድፍ ርቀት የሚያይ ስትራቴጂክ ቀጠና ነው ። : ይህ ሀይል ሸማቂው ኮማንዶ የሚንቀሳቀስበት ነው የፋሽቱን ሀይል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየሳበ እረፍት የሚከለክል ወደ መሀል ኦሮሚያ ዕምብርትና ወደ ኃላ አማራ እየተሳበ የሶስቱን ዕዞች የሚያገናኝ ድልድይና የመሀል ተጫዋች ነው በተለያዩ ግጥሚያዎች ራሱን እየፈተሸ በልምድ አየጎለበተ የሄደ ትኩረት የሚስብ አስፈሪ ሀይል ነው ይህ ቀጠና በኤርትራና በትግራይ ሀይሎች ጭምር ሰፊ ቦታ የሚሰጠው ስትራቴጂክ ከባቢና የስበት ማዕከል ነው ። ምስራቅ አማራ ቀጠና ቤተ-አማራ ወሎ ይህ ሀይል ከትግራይ ሀይሎች ጋር በጥቅሻ ተግባብቶ ለመንቀሳቀስ ደቂቃ የማይፈጅበት የውህደት ኬምስትሪው በአግባቡ የተሰራና በተደጋጋሚ ድሎች የጎለበተ ነው በዚህ ቀጠና ውስጥ የሚንቀሳቀሰው "የምኒልክ ዕዝ" ጠላትን እንደ ጉንዳን የሚበትን በሰርጂካል ኦፕሬሽን ቆርጦ የሚጥል ከቦ የሚውጥ ስቦ የሚመታ ስሙ በብልፅግና ሰራዊት ውስጥ በፍርሃት የሚነሳ የአገዛዙ Nightmare ነው  ሀይሉ ያለው ስሙ ላይ ነው "ምኒልክ ዕዝ" 💪 ! በጀነራል ትኩዕ ባዕታ የሚመራው የኤርትራ ጦር  በኢትዮጵያ ድንበሮች ሲያደርገውን የነበረውን ቃኝ እንቅስቃሴ አጠናቆ ጥሶ መግባት ጀምሯል አፋር ግምባር ብረት እየተንጋጋ ታንክና መድፍ እየተንቆራጠጠ ነው : ምንም እንኳን የአፋር ሜዳማ ከባቢዎች የአየር የበላይነት ላለው ሀይል አስተማማኝ ቢሆኑም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ታጣቂ ሀይሎች የተሻለ የአየር ሀይል አቅም ያለው ሻዕቢያ ነው በዚህ ከባቢ ብልፅግናን በተሻለ መመከት የሚችለውም ራሱ ሻዕቢያ ነው TDF የሻዕቢያን የአየር ሽፋንና ከለላ ከተጠቀመ ወደዚህ ቀጠና ገብቶ የኢትዮ ጅቡቲን መንገድ በቀላሉ መቁረጥ ይቻለዋል ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሞክሮ ያልተሳካለት በአየር ላይ በተወሰደበት ብልጫ መሆኑን ልብ ይሏል ። ይቀጥላል.........

⚫️#መረጃ_ወለጋ‼️ የጫካው ኦነግ ሼኔ ዛሬ የካቲት 26/2018 ዓ.ም ምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ የጫካውን ተዕልኮውን ጨርሶ በይፋ በቀኑ ወደ አንገር ጉትን ከተማ አስተዳደር ፀፈት ቤት መግባቱን
+1
⚫️#መረጃ_ወለጋ‼️ የጫካው ኦነግ ሼኔ ዛሬ የካቲት 26/2018 ዓ.ም ምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ የጫካውን ተዕልኮውን ጨርሶ በይፋ በቀኑ ወደ አንገር ጉትን ከተማ አስተዳደር ፀፈት ቤት መግባቱን በፎቶ አስገድፈው ምጮች #ለአንገር_ሚዲያ ገልጸዋል። በተያያዘ ዜና ሆሮ ጉድሮ ወለጋ አቤ ደንጎሮ ወረዳ ውባንጪ የገባው የኦነግእና ገዳ ኮማንዶ መከላከያ ሰራዊት ጥምር ጦር የአማራዎችን ንብረት እየዘረፈና የቤት እቃወችን ሳይቀር በመኪና እየጫነው። በዚህ የተደናገጡት የአከባቢው ኗሪወች ከተማዋን ለቀው የወጡ ሲሆን የአገዛዙ ጥምር ጦር የማህበረሰቡን ንብረት እያጫነ ነው። የአማራውን ንብረት ጪኖ እደጨረሰ ሙሉ ውባንጪን #በእሳት ሊቃጥላት እንደሆነ #ለአንገር_ሚዲያ ምጮች ገልጸዋል። 27/ዐ6/2018 ዓ.ም

+4
➺➺ለጀግናው ሲሳይ ታደሰ ወልዴ የ100,000ሽ ብር እና አንድ ክላሽ ስጦታ ተበረከተለት ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ የአማራ ህዝብ አብዮት ከተጀመረ ጀምሮ ላለፉት ሶስት እንደ ህዝብ እያስመዘገብነው ባለው አኩሪ ድል መካከል እጅን በአፍ የሚያስጭን ልዮ ጀብድ እየፈፀሙ ጎልተው የሚታዩ በታሪክ እና በትውልድ ፊት ሲታወስ የሚኖር ታሪክ የሰሩ በርካታ ተናጠላዊ ጀግኖች እንዳሉን በዘመናችን ለማየት በቅተናል። ከእነዚህ ጀግኖች መካከል አንተም በቀን 17/06/2018 ዓ.ም ከነበረበት የጠላት 25ክ/ጦር ካምፕ ውስጥ ሶስት የአረመኔው አገዛዝ አባላት በመምታት አሬት ክላሽ በመያዝ ልዩነቶች ጀብድ ፈፅመህ የወገን 54ኛ ክፍለ ጦር ስለተቀላቀልክ ይህ የጀግንነት የክብር ምስክር ወረቀት ከ 50,000(ሀምሳ ሽ ብር) ከማበረታቻ ሽልማት ጋር በአክብሮት ተሰጥቶታል። በተጨማሪም በክፍለ ጦሩ በኩል የ50,000 (ሃምሳ ሽ ብር)እና አንድ ክላሽ በመስጠት በርታ በማለት በድርጅቱ አመራሮች እና በኮሩ ሰብሳቢ ስጦታው ተበርክቶለታል ። የካቲት 27/2018 ዓ.ም የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛኮር ህዝብ ግንኙነት

⚠️ URGENT: በብዛት WhatsApp, Telegram & Facebook Hack እየተደረገ ነው። Link, SMS,  OTP, Verification Code,  Voicemail ወይም ሌላ ነገር ከማንም ሰው ወይም ድርጅት ቢላክላችሁ አትክፍቱ። የላከላችሁ ሰው የቅርብ ቢሆን እንኳን ምን አስቦ እንደ ላከ ደውላችሁ ጠይቁት። ሰዒድ አህመድ የዘርፉ ባለሙያ

+4
ጨለማው የጎጃምን ተራሮች እንደ ኩታ ለብሷቸዋል። በአንድ በኩል የፕሮፓጋንዳው ማዕበል እንደ ክፉ ነፋስ ይነፍሳል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የጠመንጃው ጩኸት ያስተጋባል። ​ከሳምንት በፊት ነበር የአብይ አህመድ የቴክኖሎጂ አዳራሾች ውስጥ የሚርመሰመሱት የሳይበር ዘመቻ አድራጊዎች በቁልፍ ሰሌዳዎቻቸው አማካኝነት የአርበኛ ሀብታሙ የሱፍን ስም ለማጠልሸት መርዛቸውን መርጨት የጀመሩት። ዓላማቸው አንድ ነበር በአማራ ፋኖዎች መካከል የጥርጣሬን ዘር መዝራትና ህዝቡን ከተዋጊው መነጠል። "ሀብታሙ የለም ሀብታሙ እጁን ሰጥቷል የሚሉ ወሬዎች እንደ ሰደድ እሳት ማህበራዊ ሚዲያውን አጥለቀለቁት። ​ነገር ግን ሀቅና ወሬ ለየቅል ናቸው። አርበኛ ሀብታሙ ከአብይ አህመድ አገዛዝ ነፃ በወጡት ቀጠናዎች ከወሬው ማዕበል ይልቅ በተግባር ማዕበል ውስጥ እየዋኘ ይገኛል። ​ሆኖም እኛ የምንዋጋው ለወሬ ሳይሆን ለህልውና ነው" የሚለው ንግግሩ የሰሙትን ሁሉ ልብ ያሞቃል። ሆኖም ​አርበኛው ለአማራ ህዝብ፣ በውጭም በውስጥም ላላችሁ ደጋፊዎች እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፏል፦ ​ወንድማችሁ በስራ ላይ ነው! በጠላት የሳይበር ጩኸት አትሸበሩ። እኛ እዚህ ሜዳው ላይ፣ እውነትን በደማችን እየፃፍን ነው። የነፃነት ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል።Dawit Amhara ከግንባር

#የአደረጃጀት_ዜና‼️ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር የ22ኛ፣ 31ኛ እና 34ኛ ክፍለ ጦር ምስረታ ተጠናቋል። የጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ አካል የሆነው የደጋው መብረቅ ኮር ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ አስደማሚ ተጋድሎዎችን እየፈፀመ ይገኛል። በስሩ የሚገኙትን አምስት ክፍለጦሮችን በማስተሳሰር  እረፍት አልባ አውደ ውጊያወችን በመፈፀም በጠላት ላይ በቀጠናው ፍፁም የበላይነት ወስዷል። ድርጅታችን ባወረደው መምሪያ መሰረት ኮራችንን አሁናዊ የትግላችንን አቋም በሚመጥን መልኩ የኮር አደረጃጀት ማሻሻያ አድርገናል። በአፋብን ምኒልክ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለ ጦር መልሶ ማደራጀት ለበርካታ ቀናት ውይይት ከተደረገበት በኋላ አደረጃጀቱ ተሰርቷል። ከዚህ በፊት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ም/አ/ቀ ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር በሚል ይጠራ የነበረው፤አሁን 106ኛ ኮር በሚል መጠሪያ ስም ተሰይሟል። እንዲሁም በደጋው መብረቅ ኮር ስር የነበሩትን ታሪካዊቷ ፅናት ክፍለጦር ፣ ጀብደኛዋ አንሻ ሰይድ ክፍለጦር፣ ምሽግ ሰባሪዋ ደጀን ክፍለጦር፣ ነበልባሏ ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለጦር፣ ተናደረፊዋ ሰንጥቅ ክፍለጦሮች እንዲሁም የወሎ ቤተ-አምሓራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አሃድ የነበሩትን ክፍለጠሮች ወደ ሶስት በማዋሃድ አዲሱን 106ኛ ኮርን አዋቅረናል። ስለሆነም  የሶስቱ ክፍለ ጦሮች ስያሜ፦           ✅22ኛ           ✅31ኛ እና           ✅34ኛ ክፍለጦር ተብለው ስያሜው በመስጠት የኮሩን መልሶ ማደራጀት ተግባር ተጠናቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር የካቲት 26/2018 ዓ.ም