ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 061
Subscribers
+224 hours
+4287 days
+1 25730 days
Posts Archive
የመሀልሜዳ ህዝብ በመድረክ ብልፅግናን ተቃወመዋል ። ተቃውሞው ምንድነው ?
በመሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ብልፅግና በ15/05/2018 ዓ.ም አጠቃላይ ህዝቡን ሰብስቦ ነበረ አዲስ ገነበሁት ባለው አዳራሽ ላይ አጀደው ምን ነበር ?
አጀንዳ፦1. ክልላችንን ከፋኖ አፅድተነዋል የሚል ነበር
ከመድረክ የቀበሌ ፣ የከተማ አስተዳደር እና የዞን አመራሮች ተገኝተው የፋኖ አመራሮች እና ሰራዊት እጅ እየሰጡ ነው ። ብለው ሲደሰኩሩ የ01 ቀበሌ ህዝብ ነዋሪዎች ያነሱት ጥያቄዎች ።
1. መግስት የፋኖ ደጋፊ ብሎ ያሰራቸውን የህሊና እስረኞች ይፈቱ?
2. መግስት ነጥሎ አማራን በድሏል ይቅርታ ይጠይቅ ጥፋቱን ይመን ?
3. ህዝቡን በኑሮ ውድነት እየተጠበሰ ነው የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት አልቻለም ?
4.አማራ ከቅዬው ተፈናቅሎ እየኖረ ነው በዳቦ ስም ሸኔ እያለ የዘር ጭፍጨፋ ተደርጎብናል ለዚህ ተጠያቂው መግስት ነው ።
5. እኛን ሰብስባችሁ አትስደቡን ሚኒሻ ከ12.00 ጀምሮ በግፍ እየደበደበን ነው አስቁሙልን ?
6. ፋኖ ይዞት ወደ ጫካ የወጠው ጥያቄ የአማራ ህዝብ ጥያቄ ነው ጥያቄዎቹ አልተመለሱም መመለስ አለባቸው ።
እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን ጠይቀዋል ለጥያቄው ምን ተመለሰ
ህዝቡ ሲጠይቅ ጭብጫቦ በዝቶ ስለነበረ አመርቂ መልስ ሳይሰጥ ህዝቡ አመራሮቹ እደተቀመጡ ትተዋቸው ነው የሂዱት የመረጃ ምንጫችን ከቦተው ነው ።
ትተዋቸው ሲሄዱ ምን አሉ አንድ አመራር ከባድ ነው ብዓሉም ላይ ወጣቱ ጨፈረብን ሌላ መድረክ መከላከያ ይሰብስብ አለ ምን ይመስላችኋል ገምቱ ? ለመረጃ ጥራት ደውላችሁ አረጋግጡ ?
ህዝብ ከጣለ መድረክም መምራት አይቻልም !!!
የፋኖ ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ነው !!!
"የአማራ ችግር የሚፈታዉ በአማራዎች ብቻ ነዉ፡፡"
የአፋብን ወታደራዊ አዛዠ ጄኔራል ተፈራ ማሞ!
ነፍስ የሚያረካ ንግግር ነው።
ሌሎች ብሔሮች የሚታገልላቸው ልጆች አሉት።
ቀን/16/05/2018 ዓ.ም
የአባቶቻችንን ታሪክ በውርደትም ሆነ በኩራት ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ ባለብን የዜግነት ግዴታ አንፃር በአሁኑ ጊዜ በታሪክ ፊት ተጋልጠን የምንገኝ መሆኑን እንደገና ላስታውሳችሁ እገደዳለሁ፡፡
በጠላት ወረራ ጊዜ የአማራ ሕዝብ በሶስት ተከፍሎ
እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ከነዚህም አንደኛው ውርደትን በመጥላት ለነፃነቱና ለክብሩ ሲል ቤት ንብረቱን ትቶ ወደ አርበኝነት በመግባት የዱር ገደሉን ኑሮ በመጀመር ታሪክ ሰርቶ ያለፈና የኖረ ነው፡፡
ሁለተኛው አገር ሲረጋ እመለሳለሁ ብሎ ሕይወቱን ለማዳን ሲል
የተሰደደ ነበር፡፡ ሶስተኛውና የመጨረሻው ለሆዱ አድሮ የጠላት
መሣሪያ በመሆን ወገኑን ከሚጨፈጭፈው የአገዛዙ ጦር ጋር
ያበረው ነው፡፡
ሆዱን ለመሙላትና የማይቀረውን ሞት ለግዜው ለማዘግየት
ሲል የውርደትን መንገድ የመረጠው ከንቱ በትዝብት ውስጥ ወደቀ
እንጂ የአማራ አርበኞች ድል አድራጊነት አልቀረም፡፡ ወገኑን
የከዳውና ለሆዱ ያደረው ባንዳም ከውርደት በቀር ትርፍ ሕይወትና
ትርፍ ኑሮ አልኖረም፡፡ ዛሬም ቢሆንም እንደዚህ ያሉ ለማንኛውም
ወገን የማይጠቅሙ የሕዝብ ጠላቶች የሃገርና የወገንን ጉዳይ ለጥቃቅን ጥቅማቸው የሚሸጡ የትውልድ አተላ ስለሆኑ እግዚአብሔር በቸርነቱና በኃይሉ ቀናውን አስተሳሰብ እንዲሰጣቸው እየተመኘሁ ይህን ከመሰለው የትውልድና የታሪክ አተላነት የሚላቀቁበትን ልብ ለማግኘት በቂ ጊዜ ስላላቸው ማሰብና ደጋግመው ማሰላሰል ከዚያም ስለአቋማቸው መወሰን ይኖርባቸው እላለሁ፡፡
ለወገን ውድቀትና መጠቃት ለአገር መዋረድና መበታተን
በትልቅ ጥላቻ መገድል የሰብአዊ መብት መታፈን መሣሪያ የሚሆኑ ሆዳም አማሃሮች ካሉ አጥብቀን እንመክራቸዋለን፡፡ በተለይም ወጣቱ ክፍል የአባቶቹን ዓላማ ያለጥርጥር እንደሚያነሳ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡
በሌላ በኩል ለአማሃራው ሕዝብ ሕጋዊ መብት
መጠበቅና ለአንድነትና ሉአላዊነት መከበር የሚያደርገውን
ትግል በቆራጥነት መቀጠሉን ይገፋበታል፡፡ ይህ ትግል ዓላማው
ስለሆነም በማንኛውም ቦታ የሚፈጽሙትን ህዝቡን የሚጎዱ
እንቅስቃሴዎች መታገሉን በግንባር ቀደምትነት ማስተባበሩን
ይቀጥላል፡፡ በመጨረሻም ላሳስባችሁ የምፈልገው ዛሬ ዓለም በሥነ ጥበብ መጥቃ በመሄድ አገርን በማልማትና የሕዝብን ማህበራዊ ፍላጎት
በማርካት ከፍተኛ እርምጃ የሚካሄድበት ጊዜ መሆኑን ነው፡፡ በዚህም መሰረት አገራቸው ምድረ በዳ የሆኑ አገሮችም እንኳን በሰላም በመግባባትና በመተባበር በመስራታቸው ለሕዝባቸው ብዙ ጥቅም እያስገኙ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ አገራችን በምድር ላይ ያለች ገነት መሆኗን
ሙሶሎኒ ሳይቀር ሲመሰከር ለወታደሮቹ ባደረገው ንግግር ‹‹ይህችን የምድር ገነት ውረሱ›› ነበር ያላቸው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ሕዝቡም ሆነ ለአማራ ህዝብ ለትግል የወጣነው የፋኖ አካላቶችበሰላምና በእኩልነት ተፈቃቅሮ መሥራቱ ጥቅሙ
የሁላችንም መሆኑን ተገንዝበን በመሃላችን ያለውን ልዩነት ከማስፋፋት ይልቅ በመሃላችን ሊጎለብት የሚችለውን ስምምነታችንን እንዲጠናከር በማድረግ አርቀን እንድንመለከት ጥሪ አቀርባለሁ፡፡
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ዘመቻ
አሳልፍ ደስታ (ቀጭን )
+1
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የቴዎድሮስ ዕዝ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መምሪያ የፋይናንስ ቲሙ ስብሰባ አደረገ።
አንድ ድርጅት ጠንካራ እንዲሆን ከተፈለገ ሁሉም መዋቅሮቹ በደምብና መመሪያ የተደራጁ ሊሆን ይገባል። በደምብና መመሪያ ከተደራጁት መዋቅሮቻችንም አንዱ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቲም አንዱ ነው።
ለአፋብን የጀርባ አጥንት የሆነው የፋይናንስ ቲሙ ባደረገው ስብሰባም የቴዎድሮስ ዕዝ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ኃላፊው ፋኖ Simeneh Mulatu Tafere እና ም/ ኃላፊው ፋኖ ዳኛው ሽባባው በተገኙበት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን የገመገመ ሲሆን ለቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባውን የቋጨን ሲሆን የስራ ስምሪት በመያዝ ጨርሰናል።
የደጋው መብረቅ ኮር በሁለት የክፍለ ጦር ቃኝዎች ድል ሲያደርግ፤በሌላ ክስተት ጋሸና ከተማ ላይ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት እርስ በርሱ ተታኩሶ ሰብዓዊ ኪሳራ አስተናግዷል::
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ቀኝአዝማች ተበጄ ወርቁ ክፍለ ጦር እና አንሻ ክፍለ ጦር የጥላትን ሰራዊት በመቀባበል ሙት ቁስለኛና ምርኮኛ ተደርጓል!
ጥር 16/2018 ዓ/ም መነሻውን ከጋሸና አድርጎ ሲጓዝ በነበረ በጥላት ሀይል ላይ የተጠና ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን ከጋሸና በ5 ኪ/ሜ እርቀት ላይ በምትገኝ ገጣጢት ተብላ በምትጠራ ቦታ ላይ የቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ቃኝ በጥላት ሰራዊት ላይ ስድስት የድምሰሳና ዘጠኙ ደግሞ ከባድ ቁስለኛ እርምጃ ሲወሰድ፤ አንሻ ክፍለ ጦር ቃኝ ደግሞ በአርቢት ምድር ሌላ በተያዘ የደፈጣ ኦፕሬሽ ከቀኝ አዝማች ተበጀ ወርቁ ቃኝ ግስላዎች ለማምለጥ ተበታቶኖ ሲፈረጥጥ በነበረ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊትን እስከ ነፍሱ ተማርኳል።
ገጣጢት ላይ በተደረገበት የደፈጣ ቅጥቀጣና የአርቢት ደፈጣዊ መማረክ የተነሳ በጋሸና ከተማ እረፋድ ላይ የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት የእርስ በርስ ተኩስ መሀል ከተማ ላይ ተኩስ ልውውጥ እያደረገ ያረፈደ ሲሆን በዚህም የእርስ በርስ ተኩስ በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል። ሽፈትንና ውድቀትን በተለይ ከአማራ የፋኖ አንድነት ማግስት በተፋጠነ ሁኔታ እያስተናገደ ያለው የጁላ ሰራዊትና የአቶ አብይ አህመድ ስርዓት ውድቀቱ እየተፋጠነ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ጥር 16/2018 ዓ.ም
+1
መላው አማራ ሸር ሊያደርገው የሚገባ ንቃ አማራ
ትናንት ትጥቅ ይዘው ወደ ፋኖ የተቀላቀሉ የሚኒሻ አባላትን" በሚመለከት የሚሰራጩ መረጃዎች ፍጹም ከእውነት የራቁና የህዝብን ስነ-ልቦና ለመረበሽ የታቀዱ የሳይበር ጥቃት አካላት ናቸው። የብልፅግና ውሸት እንዲህ ነው።
+3
ሰባት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ሰባት ጥቁር ክላሽና ከ1400 በላይ ተተኳሽ በመያዝ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ!
ከአንድነቱ ብስራት ማግስት እየተናደ የሚገኘው የብልፅግና ወንበር ጠባቂ መከላከያ ሰራዊት ስድስት የ61ኛ ክፍለ ጦር እና አንድ የ65ኛ ክፍለ ጦር ባጠቃላይ ሰባት አባላቶቹ ምኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነው ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
👉ሰባት ክላሽ፣ከ1400 በላይ የክላሽ ተተኳሽ፣14 የእጅ ቦምብ፣ሰባት የወገብና የደረት ትጥቅ በመያዝ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር አካል የሆነውን ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
ፋኖን የተቀላቀሉት የመከላከያ አባላት አክለውም የሀገሪቱ መከላከያ ተቋም የሀገር ዳር ደንበርና ሉዓላዊነትን ከማስከበር በተቃራኒ የአማራን ህዝብ ለሚጨፈጭፈው፣ለሚያርደውና አማራ ሀገር እንደሌለው ለሚያሳድደው የብልፅግና መንግስት ተባባሪ አንሆንም፣ህዝባችንን አናሳዝንም በማለት ፋኖን የተቀላቀሉ ሲሆን በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ እንደሆኑና ከዚህ በኋላ የአማራን ህዝብ ለመካስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ የፀዳው አመረ
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 16/2018 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወታደራዊ አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከኢትዮ ኒውስ ጋዜጠኞች ጋር ሰፊ ቃለ-መጠይቅ አድርገዋል።
- የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታና አደረጃጀት በተመለከተ
- የአማራ ፋኖ የጦር አደረጃጀት ብቃትና የማጥቃት አቅምን በተመለከተ
- ትግሉ ተጠልፏል ለሚሉና እጅ የሰጡ ግለሰቦችን በተመለከተ
- የብልፅግና ጦር መፈረካከስንና የሰራዊቱ መበተንን በተመለከተ
- አብይ አህመድ በጀኔራሉቹ ተስፋ ቆርጦ እየሱስና ድሮኖቹን መምረጡን
- የባጫ ደበሌ የሽምቅ ውጊያ ሀሳብን በተመለከተ
- የትግራይ ፣ የኤርትራና ሌሎች ኃይሎችንና ግንኙነትን በተመለከተ
- ቀይ ባህርና የአማራ ኃይል እና መሬትን በተመክተ
- የአማራ ብሔርተኝነት መሰረታዊ የፋኖ ኃይል ግንባታ ማዕከልነትን በተመለከተ
- ወደ ብልፅግና የገቡ የትግራይ ጀኔራሎች ያስጀመሩት የብልፅግና ሽምቅ ውጊያ ሙከራ ክሽፈትን
- የፋኖ አመራር ብቃት፣ ስብጥርና የተዋጊ ኃይሉ ቁመናን
- የሽምቅ ውጊያ በአማራ የተዋጊነት መንፈስ፣ በአማራ ምድርና ልምድ አንፃር
- የአማራ ልዩ ኃይል ፣ ፖሊስ ሚኒሻና የመከላከያ ሰራዊት ሆነው የሚያገለግሉትን በተመለከተ
- የትግሉ ደጋፊዎችና ሌሎች ኃይሎች በተመለከተ
እና ሌሎች ጉዳዩችን የተመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ግልፅ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዛሬ በኢትዮጵያ የሰአት አቆጣጠር ምሽት 12:30 ላይ በኢትዮ ኒውስ ይተላለፋል።
+2
"ተኩላን በማመንና በመምከር ወደ በግነት መቀየር አይቻልም" ። ተኩላ ተኩላ ነው!!
ድሮ ድሮ አንድ የግል የሚዲያ መስሪያ ቤት ተቀጥሬ በመስራበት ወቅት ለመስክ ጥናት ( field host's cop) ለመስራት በምንወጣበት ወቅት የቀን አበል ይታሰብልን ነበር ። ታዲያ ሁሌም እማልወደው ነገር የቀን አበል መቀበያ "መገጣጠሚያ" የሚባል ደብዳቤ ማስራትና የክፍያ ቀን ገንዘብ ቤት ገብቶ ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ተሰልፎ መጠብቅ ነበር። በጣም ነው እምጠላው ላቤን ጠብ አድርጌ የሰራውትን የትርፍ ጊዜ የስራ ክፍያ ለመውሰድ ለልመና የቆመ አቅመ ደካማ( በተለምዶ የኔ ብጤ) የሆንኩ ያክል ይሰማኝ ነበር። በዚህ ምክኒያት ሁሉም ተቀብለው ከጨረሱ በኋላ ሂጄ እቀበል ነበር ፣መቼስ አልተወው ነገር የደከምኩበት ነው።
እና ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ ፣ ብልጽግና ለተልዕኮ ወደ ፋኖ አስርጎ ያስገባቸው የመስክ ሰራቶኛች( host's coper) ከመስክ ጥናት መልስ የተሰራላቸውን መገጣጠሚያ በመያዝ በቁመት ቅደም ተከተል ተሰልፈው ከአንዱ ቢሮ ወደ ሌላ ቢሮ እየተዟዟሩ ካስጨረሱ በኋላ የውሎ አበላቸው ሲወስዱ ሳይ ያን ጊዜ አስተውሶኝ ነው ።
እናንተስ በወንድሞቻችን ደም እንጀራችሁን አበሰላችሁ ፣የእኛ ወንድሞች ደምስ ፈሶ ፣" ደም ከልቪ" ሆኖ ይቅር ማለት ነው?
ብቻ ቀን ጠብቁ ፋኖ ስልጣን ሲይዝ ወደ ህግ ተጠፍንጋችሁ እምትቀርቡና መልስ እምትሰጡበት ይሆናል።
የማይበስል ድንጋይ ለመቀቅል ስንት ማገዶ ጨረስን ።
አንዳንድ ነገሮች ላይ እንዲህም እናውራ መሰለኝ!
1. ወታደራዊ አመራር አይዋሽም። ሲናገር በአሀዝ፣ ሁኔታና ተጨባጭነት ያቀርባል። ለፕሮፓጋንዳ የምናወራው ውሸት ሳይሆን ለሀቅ የምንናገረው እውነት ቢኖር ትግሉ ሶስት ወሳኝ የትግል ምዕራፍ የእድገት ደረጃዎችን አልፏል። በስትራቴጂካል ድል ይጠብቁን።
2. ባህርዳር ላይ የመሸገው የአብይ አገዛዝ ሀይል በምናውቃቸው አብሮ አደግ ወጣቶች በኩል የህዝብ በደል ትብብርን እያገኘ ነው። በመሆኑም ከንፁሀን እገታ ጀርባ የአገዛዙን ይሁንታ ያገኙ በርካታ ወጣቶች እጃቸው እንዳለበት ዝርዝር ማስረጃ አለን። የድምፅ ቅጅ፣ ባንክ ትራንዛክሽንና የውሎ ትስስር ማስረጃዎች ቀስ እያሉ ሂደቱን ጠብቀው ይገለፃሉ። እነዚህ አካላት ጋር በማንኛውም ሰዓት ልንፈራረድበት የምንችልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። እነዚህ አካላት የእገታ ሰነዳቸው የሚያነፃፅረው ደግሞ ፍፁም ንፁህ፣ ሰርቶ አደር ነጋዴ፣ ህክምና ባለሙያ፣ ቅቡልነት ያላቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን ትኩረት ያደረገ የደም ንግድ ሲሆን ከአረፈደ አራዳ ሚሊሻ እስከ ብርጋዴል ጀኔራል የገበያው ትስስር ፈጣሪ ናቸው። ለሆድ አምላካቸው ማለት የምንፈልገው ነገር “አንተዛዘብ እረፍት አድርጉ” ብቻ ነው።
3. የትግሉ አጋር መሆን የምትፈልጉ አካላት ፋኖ በየትኛውም ቀጠና ውስጥ ይዘትና ቅርፁን ቀይሮ ከጎንህ ስላለ ነካ አድርገህ ጠይቅና ተቀላቀል፤ አግዘው። ከጎንህ ግራና ቀኝ ወይም ከፊትና ኋላ ሲራመድ የምታያቸው አራት ሰዎች ካሉ ሶስቱ የፋኖ አባል ነው። ሳትፈራራ ተነጋገር። አይቀሬ ለሆነው የድል ብስራት የራስህን ሚጢጢዬ አሻራ አሳርፍ። አካላችን መሆን ለምትፈልጉ ሁሉ በራችን ክፍት ነው።
Manchilot Esun
+3
የአገዛዙ ተቋሙ እየተናደ ነው‼️
ጥር16/2018 ዓ.ም
ስቦ ማስከዳት:➔
ከአንድነቱ ምስረታ ጋር ተያይዞ በዛሬው እለት ሁለት የመከላከያ አባላት 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
1.ልንገረው ዘዉድ....25ኛ ክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት
2.አሸናፊ አሰፋ......25ኛ ክ/ጦር 6ኛ ሬጅመንት ሰዴ ወረዳ መሽጎ ከነበረው ካምፕ በመውጣት በዛሬው እለት54ኛ ክፍ ለጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
🔥#ወታደራዊ_አፈሳ‼️
በምዕራብ አማራ ቀጠና (ጎጃም ላይ) ከሰሞኑን ከፍተኛ ወታደራዊ አፈሳ እየተደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በደንበጫ ፣ በጅጋ፣ በቡሬ ፣በፍኖተሰላም ፣በቢቸና ፣በደባይ ጥላት ግን፣ በባህርዳር እና ደብረማርቆስ በርካታ ወጣቶችን በማፈን ላይ ይገኛሉ።
በዚህ አፈና የ10 አመት ህፃናት ሁሉ መታፈሳቸውን የአይን እማኞች ለንስር አማራ ገልፀዋል‼️
ስለሆነም ከአሸባሪው ወታደራዊ አፈሳ ራስን ለመጠበቅ እንቅስቃሴን መገደብ ወይንም አናብስቱ ወደተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች መሄድ ይጠበቃል‼️
#33ኛን #ክፍለ-ጦር #እንደ_ንሥር_ያደሰ_ትምህርታዊ_ግምገማ_ተካሄደ
══════════🕊❁✿❁🕊══════════
(ጥር 16/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት)
የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዐፋብን) 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር በውስጡ የነበሩ ችግሮችን አርሞ ወደ ተሟላ አቅሙ ተመለሰ።
ከድርጅት አመራር እስከ ሬጅመንት አመራርና አባላት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ምክክር በክፍለ-ጦሩ የነበሩ ችግሮች በጥልቀት ተነስተዋል።
በየደረጃው ለተነሱ ችግሮችም በሚመለከታቸው የድርጅቱ እና የኮሩ አመራሮች ጥልቅ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ መግባባት ተችሏል።
የማስተካከያ ሀሳብ እና ውሳኔ ለሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎችም ከሚመለከታቸው የድርጅቱ አመራሮች መፍትሔ ተቀምጧል።
ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የዐፋብን አመራሮች የአባላትን መብትና ደኅንነት ለማስጠበቅ በአግባቡ ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠይቋል።
በተያያዘም በሕዝቡ እና በድርጅቱ ሕልውና ላይ ችግር ለሚፈጥሩ ማንኛውም አይነት አዝማሚያዎችና ድርጊቶች ያለ ምሕረት ሊሠራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የክፍለ-ጦሩን ቁመና በተፈተሸበት በዚህ ምክክር፤ ድርጅቱ የሕዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች ማስመለስ የሚችሉ ጥራት ያላቸው መሪዎችን እና አባላትን ለማፍራት አልሞ መሥራት እንዳለበትም በተሳታፊዎች ተነስቷል።
በባህል እና በአኗኗር ታሪካዊ አንድነት የነበራቸው የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ እና የአርበኛ ዮሐንስ ዓለማየሁ ልጆች በነበራቸው ምክክር አስቸጋሪ የተባሉ የአሠራር ክፍተቶችን በጋራ አርመው ጠላትን ለመደምሰስ የሚያስችል ቁመና ይዘው ወጥተዋል።
የ102ኛ ኮሩ 33ኛ ክፍለ-ጦር የጋራ ችግሮችን በግምገማ በመፍታት ለሚሰጡ አዳዲስ ግዳጆች በተሟላ አቅም ላይ መኾኑ ተረጋግጧል።
በመጨረሻም 102ኛ ኮር ባልተሟሉ የሬጅመንት አመራሮችም አመራር የመተካት ሥራ ሠርቶ የቀጣይ አቅጣጫወችን በማስቀመጥ እና ለአመራሩ እና ለአባላት የሥራ ስምሪት በመስጠት ምክክሩ ተቋጭቷል።
የድርጅቱ ልዩ ዘመቻ ም/አዛዥ ፶ አለቃ መኰንን ይፍሩ፣ የ102ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ዘውዳለም አዱኛ፣ የ102ኛ ኮር ጊዜያዊ መንግሥት ሰብሳቢ አርበኛ ይፍረድ ውዴ፣ የ102ኛ ኮር ጦር አዛዥ ፻ አለቃ ይንገሥ ብርሃኔ፣ የ102ኛ ኮር ም/ጦር አዛዥ ፶ አለቃ መኳንንት አበጀ፣ የ102ኛ ኮር ጦር አዛዥ ፻ አለቃ ሥራው ወ/እግዚአብሔር፣ የ102ኛ ኮር የፖለቲካ ዘርፍ አርበኛ ማንችሎት ጥላሁን፣ የ102ኛ ኮር ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አርበኛ ትዕዛዙ በቀለ፣ የ102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ አርበኛ ታደሠ አስማረ፣ የ102ኛ ኮር ኦርዲናንስ ፻ አለቃ አዳሙ እንዳለው፣ የ102ኛ ኮር ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር አርበኛ ፀጋየ ፈንታሁን እና የ33ኛ ክፍለ ጦር ሙሉ አመራሮች፣ የ33ኛ ክፍለ ጦር ሬጅመንት መሪዎች፣ እንዲሁም የ33ኛ ክፍለ ጦር የጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች በውይይቱ ተገኝተዋል።
ነፃነታችን በክንዳችን ይረጋገጣል‼
+5
ግርም የሚለኝ ነገር እጅ ሰጡ የሚባሉት ሃይሎች እጅ የሚሰጡት ለማነው ለብልፅግና/ለጨፍላቂው ስርዓት መጀመሪያ ወደ ትግል ስንገባ አላማ ኖሮን ሊሆን ይገባል አላማ የሌው ታጋይ እንሰሳ ነው ህዝቤ እየተሰቃየ በማንነቱ ተለይቶ እየተገደለ ባለበት ስዓት እጅ መስጠት አላማቢስነት ነው ለእኔ ይህን ህዝብ ታግለን ነፃ እንደምናወጣው እርግጠኛ ነኝ የብላኝላቸው በሆዳቸው የህዝብን ትግል አሳልፈው ለሸጡት ባንዳዎች! የእኛ ትግል በግለሰብ ላይ የተንጠለጠለ ሳይሆን ድርጅታዊ አሰራርን የሚከተል በመርህ እና በአሰራር የሚያምን የህዝብን ጥያቄ ለማስመለስ የሚታገል እንጂ ማንም ባንዳ እንደ ፈለገ የሚያሽከረክረው ትግል አልጀመርንም ዛሬም ነገም አሸናፊዎች እኛው ፋኖዎች ነን ምክንያቱም ማሰልጠን ማደራጀት ማሰታጠቅ የዘወትር ስራችን ስለሆነ አፋብንን ይዘን ወደ ፊት። ጀግኖች በስራ ላይ ናቸው ለማለት ነው።
+1
ማስጠንቀቂያ ለከተማ ወጣቶች
በምዕራብ አማራ ቀጠና ጥምቀትን ሲያከብሩ የፋኖን ስም ጠርተው ጨፍረዋል በማለት የብልፅግና ሰራዊት እያፈነ ይገኛል።
እስካሁን በቡሬ ፣በፍኖተሰላም ፣በቢቸና ፣በደባይ ጥላት ግን፣ በባህርዳር እና ደብረማርቆስ በርካታ ወጣቶችን በማፈን ላይ ይገኛሉ። በቢቸና ከተማ ያፈኗቸውን ሁለት ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሏቸው ሲሆን ሌሎችን ወደአልታወቀ ቦታ እንደወሰዷቸው አረጋግጠናል።
በመሆኑም ከተማ ላይ ከብልፅግና ጉጇ ስር የምትገኙ የአማራ የቁርጥ ቀን ወጣቶች ራሳችሁን ጠብቁ ።ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ ወንዶች ቦታ ተቀላቀሉ ።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር በጊዜያዊ አመራሮች የተሰጠ የአደረጃጀት መግለጫ፡-
የአደረጃጀታችን መነሻው መሰዋትነት፣ ፅናት፣ ሃቀኝነት፣ ታማኝነት፤ አገር ሰሪነት፣ ለአማራነታቸው መሰዋዕት ለሆኑ ጀግኖች መታመን፣ ከፍያለው ደሴን በሕይወት ሳለ ብቻ ሳይሆን ተሰውቶም የምኮራበትና የምንመካበት እንስፍስፍ ልጆቹ አለን።
''ከማይመስልህ ጋር አትጠመድ'' እንደሚባለው፤ ከማይመስሉን ጋር ጎን ለጎን እየተጠራጠሩ ከመኖር፤ መመንጠሩ የተሻለ በመሆኑ ፤ የብብት መዥገሮችን አራግፈን እንደ ንስር ታድሰን፣ እንደ ዝሆን ገዝፈን፣ እንደ ነብር ተቆጥተን፣ የምንነሳ የከፍያለው ልጆች እንጂ፤ የንዋይ ፍቅር አሳብዶን፤ የከተማ ቦታ አማሎን እርካሽ የብልፅግና ስልጣን ፈልገን ጫካ አልወጣንም።
የአባቶቻችን እና የወንድሞቻችን እርም የምንበላ ከዳተኞችም አይደለንም። ክህደት ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፤ እንዲህ ዓይን ያወጣ እና ያገጠጠ ሳይጣናዊ ክህደት ግን አይተንም ሰምተንም አናውቅም፡፡
ዛሬ በአደባባይ ክህደታቸውንና ነውራቸውን ያሳዩን፤ የውስልትና ፓለቲካቸውን የጀመሩት፤ በታላቁ አርበኛ በአባታችን ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው ደሴ መስዋዕት፤ ያዘኑ መስለው ውስጥ ውስጡን ግን፤ ‹‹እንደሳር ውስጥ እባብ እና የጭቃ ውስጥ እሾህ›› በለስላሳ ባህሪ አታለው ነው ኢያጎአዊ ድርጊታቸውን የጀመሩት፡፡
ከዳተኞቹ ከስራዓቱ ጋር የጀመሩትን ውስልትና ቀደም አድርገው እንደጀመሩት መረጃዎች ቢጠቁሙም፤ አሊቧልታ ነው በማለት ነገሩን በትዕግስት ይዘነው ቆይተናል።
ከሳይጣናዊ ምክክራቸው ከታቀብን እና ከተገለልን የቡድን መሳሪያ ሳይቀር በወገን ጥይት ናዳ እየወረደብን በውስጥ ታጋዮች እየተፈትነን ዘጠኝ የጨለማ ወራትን አሳልፈናል።
ዛሬን በእሳት የተፈተን ነገን በተስፋ እስከ ቀራኒዮ የምንፋለም እንጂ፤ በድብብቆሽ ፓለቲካ እጃችንን አንከርፍፈን ለጨፍጫፊ ኦሮሙማ ስርዓት እጅ የምንሰጥ የሚሊሻ ልጆች አይደለንም።
ስለሆነም የገብርዬ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበረው ግለሰብ አዲሱ ደባልቄ እና የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ የነበረው አዳነ ተስፋ ወደ ገዳያችን ብልጽግና ሲገቡ፤ በተቋማችን ላይ በመጠኑም ቢሆን የትጥቅ እና የስንቅ ጉድለት ቢያደርሱም፤ ትናንትም ህዝባችን ነገም ህዝባችን የትግላችን መሠረት በመሆኑ፤ አንገታችንን ቀና አድርገን የምንሄድ የዳግማዊ ገብርዬ ልጆች ነን።
በመሆኑም ''በህይወት ኖሮ ከመቆሸሽ ሞቶ መወደስን'' የምንመረጥ የስመኘው መብራቱ (ጋሼ) የቃል ዕዳ ያለብን አቡነ ጴጥሮሶች ነን፡፡ ፈንገሶችን አራግፈን በንፁህ ህሊና የምናስብ በጤነኛ ሳምባ የምንተነፍስ ዮቶራዊያን ነን።
በዚህ መሠረት አንዳንድ ነገሮችን ለድርጅታችን አፋብን፤ ለተከበረው ሰራዊታችን፤ ለመላው ህዝባችን፤ ለመላው በሃገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የትግላችን ደጋፊዎች ማሳሳብ የምንፈልገው ነገር፤ ቢኖር እንደሚከተለው ነው።
1ኛ, መላ የአማራ ህዝብ በተለይም በቀጠናችን ለሚገኘው ለራስ-ጋይንት ህዝብ፡- የብአዴን ማደጎ-ቤት ልጆች በሰሩት የጠራራ ፀሃይ ክህደት ብንበሳጭም፤ የእውነት ልጆቻችሁ ከጎናችሁ መሆናችንን፡፡
2ኛ. ለድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፡- ከደረሰብን ድንገታዊ የውስጥ ጥቃት የሚታደግ የሃሳብ፣ የገንዘብ እንዲሁም የአደረጃጀት ድጋፍ እንዲደረግልን ስንል ጥሪ እናቀርባለን፡፡
3ኛ. ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ደጋፊዎች፡- ጥቅመኞች ትግላችንን በአደባባይ ሲሸጡት ሞራላችሁ ቢሰበርም፤ ታማኝ ወንድምና እህቶቻችሁ እንዲሁም ልጆቻችሁ ክንዳችንን ሳንንተራስ፤ ትከሻችን ዝሎ የአማራን ህዝብ ለጨፍጫፊ ስርዓት አሳልፈን አንሰጥም፤
4. ለመላ ሠራዊታችን፡- እንደምታውቁት የትግላችን የጥቅም ወንድማማቾች እንጂ ሃቀኛ ታጋይ እንዳልሄደ ጠንቅቃችሁ ብታውቁም፤ የፍርሃትም ሆነ የመረበሽ ነገር እንዳልገጠማችሁ በትናንቱ የውስጥ ከሃዲዎችን እና የጠላትን የጋራ ውጊያ ሰብራችሁ መኪና እና ዲሽቃ የተቀባላችሁ፤ ዘረ-ከፍያለዋዊያን መሆናችሁን በተግባር አሳይታችኋል፡፡ ወደፊትም በጀግንነት እና በታማኝነት እንድትቀጥሉ እናሳስባለን።
5ኛ በዓመታዊ የፋኖ ድጋፍ ሰበብ ሕብረሰባችን መቀነት የፈቱ ሠራዊታችን የበተኑ አመራር ነን ተብዬወች፤ በአማራ ትግል ስም የሸቀጡ መሆናቸውን የአማራ ህዝብ በጥቁር የታርክ መዝገብ እንዲያስቀምጥልን የአማራ የህልውና ትግል ህዝብና ደጋፊ አደራውን እንሰጣለን።
በመሆኑም እኝህና መሠል ጉዳዮችን ለማስተካከል ወቅታዊ ፈተናዎችን ለመወጣት የሰራዊታችን እና የሕዝባችን ሞራል ለመካስ እንደ ገብርዬ ክፍለ ጦር ጊዜያዊ አደረጃጀት የሠራን መሆኑን እየገለጽን፤ ቀጣይ ድርጅቱ (አፋብን) በሚያወረደው መመሪያ መሠረት አደረጃጀቱ እንደገና እንደሚዋቀር ለመግለጽ እንፈልጋለን፡፡
በዚህም መሠረት የጊዜያዊ አደረጃጀቱ መሪዎችን ሰይመናል።
1. አርበኛ ኢ/ር ደመወዝ ግዳፍ -----ጊዜያዊ ሰብሳቢ
2. አርበኛ ክንድሰው ከፍያለው ----- ምክትል ሰብሳቢ
3. አርበኛ ያለው ጥላሁን -----ወታደራዊ አዛዥ
4. አርበኛ አንዷለም አዳሙ ----ዘመቻ መምሪያ
5. አርበኛ አማረ ጌታው ------ምክትል ዘመቻ
6. አርበኛ ሲሳይ ------- ልዩ ዘመቻ (ልዩ ኦፕሬሽን)
7. አርበኛ ብርሃን ጌታው ------ፓለቲካ ዘርፍ
8. አርበኛ ዘላለም በላይነው -----ፋይናስ ክፍል
9. አርበኛ ልየው ተካልኝ -------ሕዝብ ግንኙት
በማድረግ አደራጅተን፤ እንዲሁም በአራት ብርጌድ አመራር እና በሶስት ወረዳ የሚንቀሳቀስ ግዙፍ የተጠረነፈ ሠራዊት ይዘን ወደ ስራ የገባን መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ፡- ለረጅም ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የአማራ ፋኖ አንድነትን በሙሉ ድምጽ የተቀብልን እና በድርጅታችን አፋብን እንዲሁም ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፍተኛ አመራሮቻችን በሚሰጡን አቅጣጫ የምንመራ መሆኑን እየገለጽን፤ አስፈላጊውን የገንዘብም ሆነ የሃሳብ ድጋፍ እንዲደረግልን በታጋያችን እና በተገፋው ሕዝባችን ስም እንጠይቃለን።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር፦
አርበኛ ኢንጂነር ደመወዝ ግዳፍ
ጊዜያዊ ሰብሳቢ፤
የወረኢሉ ከተማ ከንቲባ የግል አጃቢ ለጥምቀት በዓል ባንዲራ ሰቅለሃል ያለውን አቶ ጥላየ ሃይሉ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ ግለሰብ በግፍ ረሸነ::
በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ከተማ ከንቲባ የግል አጃቢ የሆነ ታጣቂ ጥር 14/2018 ዓ.ም ምሽት 1:45 ገደማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ኮከብ የሌለው ባንዲራ ለጥምቀት በዓል ከተማዋ ላይ ስትሰቅል ነበር በሚል ሰበብ አቶ ጥላየ ሃይሉ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ ግለሰብ ላይ ነፃ እርምጃ በመውሰድ በግፍ ረሽኖታል::
ነፃ እርምጃ የተወሰደበት እድሜው 35 አመት የሆነ የወረኢሉ ከተማ ነዋሪ ግለሰብ አቶ ጥላየ ሃይሉ ጦር መሳሪያ ያልታጠቀና በንግድ ስራ ይተዳደር የነበረ ነው::
በሌላ በኩል በጃማ ከተማ እና ሚዳ/መራኛ መካከል ልዩ ስሙ ካራ ምሽግ የተባለ ቦታ ላይ አንድ ሾፌር በአገዛዙ ታጣቂዎች በግፍ የተገደለና አስከሬኑ ሜዳ ላይ ወድቆ የተገኘ ሲሆን የብልፅግና ታጣቂዎች ግለሰቡን በግፍ የገደሉት የያዘውን 70000 (ሰባ ሽ) ብር ለመውሰድ መሆኑንና ግፈኛ ታጣቂዎቹም እንደሚታወቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 16/2018 ዓ.ም
