en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 401
Subscribers
+124 hours
+757 days
+1 40730 days
Posts Archive
የድሮን አሰሳ አጉት ፣ ፈልቃ ፣ ደረቋ አለ ። ጥንቃቄ !!!

ሲገኝ ጋቢ ልበስ ሲጠፋ ደበሎ ቀን መውጣቱ አይቀርም እንዲህ ብሎ ብሎ ነፍጠኛው አባቴ💙
ሲገኝ ጋቢ ልበስ ሲጠፋ ደበሎ ቀን መውጣቱ አይቀርም እንዲህ ብሎ ብሎ ነፍጠኛው አባቴ💙

ይህ ትውልድ የነፃነታችን ቀይ መስመራችን ነው አለቀ አማራነት እስከ ቀራኔዎ ድረስ የምንወጣበት ሰፊው የነፃነት ተምሳሌትነ ነው አንድ ሙህር ስለ አገሩ ታሪክ ሳያቅ ሰል አውሮፓና አሜሪካ ታሪክ ያቃል ማለት በቅሎ አባትህ ማነው ቤሉት ፈርስ አለ እንደማለት ነው። ፋኖነት የአማራው የነፃነት መንፋሳዊ እስትራቲጀካዊ ፖለቲካዊ መዋቅርን ያካተተ የአዲሱ ትውልድ ማሳያ መሳሪያችን ነው ። ለሕዝብ ታምኖ መታገል የበለጠ ክብርና ሞገስ እንዳለው በተግባር ማስረዳት ይጠበቅብናል! ፖለቲካ ቁማር ሳይሆን ጥበብ ነው፡፡ ጥበብ መሆኑን ዘንግተው በፖለቲካው ለሚቆምሩ ድኩማን ፣ እውነትን ሁሌ ስለምንይዝ እንበልጣለን እንጅ አናንስም፤ እንሸንፋለን እንጅ ፣ አንሸነፍም፤ ለሴራ ፖለቲካ እጅ አንሰጥም፤ከመሽኮርመም ፖለቲካ ወጥተን ለአማራ ህዝብ የማይቀሬ የአንድነት ህይወታችንን ትልቁን ቤታችንን ለመስራት ዝግጁ ነን!! ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ዳዊት የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ልጇን ያጣች እናት ወደ ፋኖ ገባች!! የሴቷ አርበኛ ሳራ ትባላለች:: በምዕራብ ወሎ ግንባር ጃማ ወረዳ ደጎሎ ከተማ ውስጥ ነዋሪ ስትሆን ምግብ ቤት ከፍታ ቤተሰብ ስትመራ ኖራለች:: ፋኖ ሮቤል ካሳዬ የሚባለውን ልጇን የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት አስፋልት ላይ እየገተተ አሰቃይቶታል:: ነጋ ጠባ ልጇን ዘረኛው ሰራዊት ሲያሰቃይባት እና ከፍተኛ ድብደባ ፈጽሞበት ቁስለኛ አድርጎት በስተመጨረሻም 5 ወር ከ15 ቀን ጮሪሳ አስሮ የግፍ ግፍ ፈጽሞበት ሲያበቃ ለቆት ወደ ትውልዲ አካባቢው ከተመለሰ በኋላ ወደ ፋኖ ገብቶ ነበር:: በነገራችን በዚያን ቅጽበት እስኪ ቢያንስ ቁስልህ ይዳን በማለት ዘመድ ወዳጅ ሲመክረው ከወላጅ እናቱ ጋር ስለውሳኔው በሚያወጋበት ወቅት እናቴ የልብ ቁስል ነው እንጅ የማይድነው ሰው የሚያየው የገላው ቁስልማ ቀላል ነው እንዳላት ታስታውሳለች:: ልቤ ቆስሏል ከእንግዲህ እነሱን እስከ ሞት ድረስ መዋጋት ነው ያለብኝ ብሏታል:: በዚህ ውሳኔው መሰረት በጃማ ግንባር የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ ኃይል ተቀላቅሎ በፊታውራሪነት ታግሏል:: ፋኖ ሮቤል ሞትን የማይፈራ ጀግና ታጋይ እንደነበር ጓዶቹ ይመሰክራሉ:: ሞት አይፈሬው ፋኖ ሮቤል በጃማ ግንባር ማሞ ቆላ (ወደ ሸክፍ መሄጃው ላይ) በተደረገ ትንቅንቅ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ካደረሰ በኋላ አንድ ጥይት ስትቀረው ራሱን ማጥፋቱን ነው ለማረጋገጥ የቻልኩት:: እኔ ለእናንተ እጄን አልሰጥም ብሎ ራሱን አጠፋ ያሉት ጓዶቹ ፋኖ ሮቤል እጅግ በጣም ደፋር መሆኑን ነው የመሰከሩት:: በጣም ልቤን የነካኝ ነገር ቢኖር ፋኖ ሮቤል ለእናቱ ይህ ፎቶ ማልቀሻ ይሆንሻል ብሎ አሳጥቦ ግድግዳ ላይ መስቀሉን ሲነግሩኝ ነው:: ሞትን አልፈራም የወጣሁት ልሞት ነው ይል የነበረው ጀግናው ወንድማችን ወላጅ እናትን የደጎሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች ከማፅናናት ይልቅ ይሄኔ ልጅሽ የመንግስት ሚሊሻ ቢሆን ኖሮ በካሳ መልኩ ብር ታፍሽ ነበር ይሏት እንደነበርም ነው የሰማሁት:: እሷ ግን እንኳንም ለአማራ ህዝብ ጠላት ሆኖ ታሪኩን እና ታሪኬን ያላበላሸ እንጅ ልጄን በገንዘብ የምሸጥ ሆዳም አይደለሁም እንዳውም እኔም ለአማራ እሞታለሁ ብላ ጠብመንጃ ነከሰች:: አሁን ላይ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር ፊታውራሪ ናት!! በድል ይመልስሽ እህትዋ:: የወንድማችንንም ነፍስ ይማርልን!

ሰበር ዜና ‼️ በአዲስ አበባ ከለገጣፎ አቅራቢያ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ 12 የመከላከያ አባላት መገደላቸው ተሰማ! በመከላከያ ካምፕ ውስጥ በተነሳ የእርስ በእር
ሰበር ዜና ‼️ በአዲስ አበባ ከለገጣፎ አቅራቢያ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ 12 የመከላከያ አባላት መገደላቸው ተሰማ! በመከላከያ ካምፕ ውስጥ በተነሳ የእርስ በእርስ ውጊያ የአገዛዙ ወታደሮች እርስ በእርስ ተጫርሰዋል ነው የተባለው! በካምፕ ውስጥ በነበረው የእርስ በእርስ ውጊያ 12 ወታደሮች ሲገደሉ አንድ የቡናና ሻይ ቁርስቤት ሰራተኛም በተኩስ ልውውጥ መሀል መገደሏ ተነግሯል ! የእርስ በእርስ ውጊያው የተደረገው ዛሬ ከሰአት ሲሆን ወደ ወሎ ዛሬ ትሄዳላችሁ ተብለው የነበሩ የ94ኛ ክፍለጦር ወታደሮች በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት የኦሮሚያ ልዩሀይል እና ሚሊሻ ወደ ካምፑ በመግባት የመከላከያ ዩኒፎርም እየለበሱ ከነሱ ጋር መቀላቀል ሲጀምሩ ይሄ ለምን ይሆናል የመከላከያን ስም እያጎደፍን ነው ይህን አንቀበልም ያሉ ወታደሮች መረሸናቸውን ተከትሎ ሲሆን የሚሰራው ህገወጥ ስራ ሳያንስ ጓዶቻችንን እንዴት ትረሽናላችሁ በሚል የእርስ በእርስ ውጊያ የተደረገ ሲሆን ለ1 ሰአት እርስ በእርስ ተታኩሰዋል ነው የተባለው። በዚህም 12 ወታደር ሲሞት የቆሰሉም ብዙ ናቸው። ተኩሱን ለማስቆም ከፍተኛ ጀነራሎች ወደቦታው በፍጥነት የሄዱ ሲሆን ተኩሱን አረጋግተው አሁን ተቃውሞ ያስነሱትን ወደ ወታደራዊ እስርቤት እያጋዟቸው ነው ተብሏል !

..............የአደረጃጀት ዜና !! ........... በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር የ88ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ
+1
..............የአደረጃጀት ዜና !! ........... በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር የ88ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ። ክፍለጦሩ በአምስት  ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ። የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ ስሜነህ ሙላቱ  ፣ በአርበኛ ግሩም ምሳሌ እና በሀምሳ አለቃ ታደሰ ልንገር አስተባባሪነት ተጠናቋል ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

🔥#ለታሪክ_ይቀመጥ‼️ ታጋይ የሚታገለው ለብልጽግና ብቻ ነው ። "የባለፈው ሳምንቱንና የከዚህ በፊቱን የኦሮቶዶክሳውያንን ግድያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋም ጉባኤ የሚባለው ግድያውን የፈጸሙት ኦነግና
+1
🔥#ለታሪክ_ይቀመጥ‼️ ታጋይ የሚታገለው ለብልጽግና ብቻ ነው ። "የባለፈው ሳምንቱንና የከዚህ በፊቱን የኦሮቶዶክሳውያንን ግድያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋም ጉባኤ የሚባለው ግድያውን የፈጸሙት ኦነግና ፋኖ ናቸው የሚል በሞቱት ላይ የሚሳለቅ ሪፖርት አውጥቷል። ሪፖርቱ የብልጽግናን ስሜት ለማርካት የሄደበት ኦርቶዶክሳውያንን እንዳስቆጣ ከማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተመልክተናል። በሪፖርቱ ላይ ጉዳዩን 'ግጭት፣ ጉዳት፣ ረብሻ፣ ንክኪ' ሲልም ገልጾታል፡፡ አንዳንዴ ብቻ ሞተዋል በሚል ይገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ማንነታቸውን አላውቅም የሚላቸውን አካላት ምንም ዐይነት የሃይማኖት ወይም የብሔር አጀንዳ የላቸውም ሲልም ተናግሯል፡፡ ማንነታቸውን በውል ካላወቅክ አንዳንዳቸውን እንዴት ልታውቅ ትችላለህ? የሚል ጥያቄ ቢጠየቅ መልስ የለውም እያሉ ነው ብዙዎችም፡፡ ግድያው ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ አይደለም ይልና አንድስ እንኳን ከኦርቶዶክስ ውጭ የተገደለ ቀርቶ የተጎዳ ማቅረብ ትችላለህ ወይ ተብሎ ቢጠየቅ አሁን ትኩስ ገድሎ ካላቀረበ በስተቀር መልስ የለውም፡፡ ግን ግድያው ሃይማኖታዊ አይደለም ይላል የሃይማኖት ጉባኤው ሰብስቢ፡፡" 01/ዐ3/2018 ዓ.ም

እስኪ ወደ ሽዋ አንድ ጀግና ላስተዋውቃችሁ ​ዶ/ር አብደላ እንድሪስ በዋናነት በጦርነት ግንባር ቀርቦ በመዋጋት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በፋኖ ንቅናቄ ውስጥ የሞራልና የስትራቴጂ መሪ በመሆን የሚሰራ አርበኛ የአማራይቱ ልጅ ​የፋኖ አንድነት: በደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሽዋ ፋኖን ከተለያዩ ክፍሎች በማደራጀትና በማዋሀድ ለትግሉ ስኬት ቁልፍ ሚና በመጫወት ግንባር ቀደም ከሚሰለፉት የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች አንዱ ነው። ​የሞራል ልዕልና: ለፋኖ ተዋጊዎችና ለህዝቡ ትግሉን የመምራት፣ የማነሳሳት እና የጽናት ምልክት በመሆን እየሰራ ያለ ጀግና ብቁ አርቆ አሳቤ በትምህርት ደረጃ የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) ያለው ። የፋኖ እንቅስቃሴን ከፖለቲካ እና ከስትራቴጂ አንፃር የመምራት ብቃት ከመኖሩም በላይ ከወታደሩ እስከ ማህበራዊ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚወዱት ​በአጭሩ፣ ዶ/ር አብደላ እንድሪስ የሸዋ ፋኖ እንቅስቃሴን የሚወክል፣ የሚያደራጅ እና ስትራቴጂያካዊ መረጃዎችን የሚያቀርቡ ቁልፍ ጀግና ነው። የጋራ ማንነት እና አንድነት ​የጋራ ስነ-ልቦና አማራነትን እጅግ አብልጦ የሚውድ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ እና ሌሎች የአማራ የሆኑ ህዝቦች የጋራ የሆነውን ማንነት (የጋራ ስሜት፣ ታሪክ፣ እሴት) በማመን እና መተሳሰሩን በማጠናከር ላይ ያለ ለህዝቡ ያለው ፍቅር የጀግንነት እና የፍቅር እሴቶችን የሚንጸባረቅ በዘመናዊው ትግል ውስጥ ያለው ትርጉም ​የህልውና ጥያቄ: በዘመናዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አማራነት የህዝብን መብትና ደህንነት ማስከበር ከሚለው ጥያቄ ጋር አብልጦ የሚወድ ሰው ማለት የህዝቡን ህልውና (መኖር) አደጋ ላይ የሚያደርሱ ነገሮችን በመከላከል እና በማንነቱ ሳይሸማቀቅ ለመቆም ከፍተኛ ዝግጁነት ያለውን የ​ታማኝነትና ጥብቅና:  ለህዝቡ መብት መቆም፣ መስዋዕትነት መክፈል፣ እና ከማንነቱ ጋር ያዛመደ ጀግና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ሆኖ በመስራት የአማራን ህዝብ ነፃ ለማውጣት በከፈትኛ ተነሳሽነት ሞራል እየሰራ ያለ ጀግና ቅንነት፤ትህትናን በደሙ አዋህዶ የያዝ የአሳምነው ልጅ ለዘመናት እንደ አረም አንቆ ይዞ ወደ ማቅና መቀመቅ አውርዶ ሥራዓት አልበኝነትን አንግሶና ነግሶ በሁለት ስለት ቢላዋ ህዝብና ሀገርና በማፍረስና በማጥፋት ካለው ደናቁርትና እና እውነትን አንግበው በዕውቀት ልህቀት ተፈጥሮአዊና ሰባአዊ መብቶች ተከብረው በህይወት የመኖር ህልውናን ለማስክበር የሚያስችል ህዝባዊ የፖለቲካ ልዕልና ለማረጋገጥ እውነትን በሸፍጥ መቃብር ላይ ለመትከል ህዝባዊ ዓላማን ከአነገቡ ልህቃን ታጋዮች ጋር እየታገለ ያለ የዘመናችን አሳምነው ዶክተር አብደላ እንድሪስ  ለህልውናቸውና ለነጻነታቸው ከሚታገሉት ጀግኖች ዶክተር አንዱ ነው።

የመልሶ ማደራጀት ተግባሩ የቀጠናውን ትግል ከፍ እንደሚያደርገው ተገለፀ። ህዳር 1/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ መዋቅራዊ ማሻሻያ በማድረግ አደረጃጀቱን በኮር ደረጃ ያሳደገ ሲሆን የመልሶ ማደ
+6
የመልሶ ማደራጀት ተግባሩ የቀጠናውን ትግል ከፍ እንደሚያደርገው ተገለፀ። ህዳር 1/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ መዋቅራዊ ማሻሻያ በማድረግ አደረጃጀቱን በኮር ደረጃ ያሳደገ ሲሆን የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን በማጠናከር ጠንካራ ሻለቃዎችን እና ክ/ጦሮችን ያካተተው አዲሱ የኮር አደረጃት የቀጠናውን ትግል ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል።  ማዕከላዊነትን በጠበቀ መልኩ ፕሮፌሽናል ሰራዊት ለመገንባት በሚደረገው ሒደት አዳዲስ የተሻሻሉ አደረጃጀቶችን ፣አሰራሮችና መመሪያዎችን መከተል አስፈላጊ ሁኖ በተገኘበት ሁሉ ድርጅታዊ ለውጦችን ተቀብሎና አክብሮ ድርጅታዊ ተልዕኮን ተቀብሎ መፈፀምና ማስፈፀም እንደሚገባ በተገለፀበት መድረክ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ከ206ኛ ኮር አመራሮች ጋር በመልሶ ማደረጃት ወቅት የተፈፀሙ አብይ ተግባራትን በመገምገም የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል። ከተቀመጠለት የጊዜ ሴላዳ በተሻለ ፍጥነት አደረጃጀቱን በማጠናከር በስሩ ያሉ ክ/ጦሮቹን ያዋቀረው 206ኛ ኮር የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ ለመፈፀም በሚያችል ቁመና ላይ መገኘቱን በነበረው የስራ ግምገማ ተረጋግጧል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!  ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ:: ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ ከመርጦ ወደ ወልድያ ከ
+4
ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ:: ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 6ኛ ሻለቃ ከመርጦ ወደ ወልድያ ከተማ ይጓዝ የነበረ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ አማይ ሜጫ ደፈጣ በመያዝ በፈፀሙበት ጥቅት ኦራል ላይ የነበረውን ሙሉ ለሙሉ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በእግር ይጓዝ የነበረውን ከሙትና ቁስለኛ የተረፈውን ብትንትኑን በማውጣት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል:: በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት ላይ የሚወሰደው እርምጃ በደፈጣ ጥቃት ረፍት በመንስስትና በማዋከብ እንዲማረር በማድረግ ሲያመች በመደበኛ ውጊያ በመደምሰስና በመማረክ ብሎም በማስኮብለል አገዛዙን የማፈራረሱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 1/2018 ዓ.ም

ፅናት ቁርጠኝነት ትዕግስት ልበ ሙሉነት አዋቂነት ቅንነት ጥንቅቅ ያለ የጀግንነት ጥግ አባ መቻል ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የወንዶች ቁና🦾🦾 ለማንኛውም መቀሌ ሆስፒታል ይሄንን ይመስላል😜
ፅናት ቁርጠኝነት ትዕግስት ልበ ሙሉነት አዋቂነት ቅንነት ጥንቅቅ ያለ የጀግንነት ጥግ አባ መቻል ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የወንዶች ቁና🦾🦾 ለማንኛውም መቀሌ ሆስፒታል ይሄንን ይመስላል😜

ከመካነሰላም ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አባይ በር መቅደላ ከተማ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም በፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት በግፍ የተረሸኑ ወጣቶች! ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የአውደ ውጊያ ሽንፈቱን መቀበል ሲያቅተው ንፁሃን ወጣቶች ላይ ነፃ እርምጃ መውሰዱንና ባደባባይ በግፍ መረሸኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል! ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና መካነሰላም ከተማ ዙሪያ በኢንጅነር ደሳለኝ ክፍለጦር የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ሲያቅተው ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኘው በተለምዶ አባይ በር እየተባለች በምትጠራው መቅደላ ከተማ አምስት ንፁሃን ወጣቶች ላይ ነፃ እርምጃ በመውሰድ በግፍ አስፓልት ላይ ባደባባይ ረሽኗል:: በግፍ የተረሸኑት ወጣቶች ስም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፦ 1. ይታገስ አረጋ 2. መቻል ደርብ 3. እሸቱ ብሬ 4. ስመኘው ጥጋቡ 5. ሀብቴ አቢ ታመነ ሲሆኑ ሁሉም የአንድ ሰፈር የመቅደላ ከተማ ልጆች ናቸው። ይህ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ፀረ-አማራ ተግባር ከክልሉ ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ በሰፊው ሲፈፀም የነበረ ያለና ታግለን ካላሸነፍነውና ካላስቆምነው ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ዘር ማጥፋት ዛሬ በሁሉም አማራ በር ላይ እያንኳኳ ያለ የእልቂት ድግስ ነው:: ስለሆነም የአማራ ህዝብ ሆይ በተለይ የአማራ ወጣቶች ጠላቶቻችን ሞት እልቂት ደግሰው ሞታችንን መዋቅራዊና ህገ-መንግስታዊ አድርገው የህዝባችን የጅምላ ሞት ቁጥር ሆኖ እንዲለመድ በማድረግ አማራው ሃይማኖት መንግስትና አገር አልባ እንዲሆን ተግተው ቀን ተሌት እየሰሩ ነውና አንተም ሞትህን እቤትህ ቁጭ ብለህ እያየኸው ከምትቀበለው ታግለህ ገዳይህን ገለህ ሞትህን እንድታስቆምና ሁለንተናዊ ህልውናህን እንድታረጋግጥ ዛሬም ባለመታከትና ፍፁም ተስፋ ባለመቁረጥ ጥሪያችንን እናቀርብልሃለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 1/2018 ዓ.ም

ሰበር የአማራ ክልሉ ፕሬዚዳንት ተብዬ አቶ አረጋ ከበደ ላሊበላ ላይ ጥቃት ተፈፀመባቸው! በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር  3ኛ ሻለቃና የክፍለ ጦሩ ሜካናይዝድ በጋራ  በመሆን ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 እስከ  ረፋዱ 3:30 ሰዓት  በወሰዱት ጥቃት የክልሉ ፕሬዝዳንት ነኝ የሚሉት ቀንድ አውጣ አረጋ ከበደ ከባህርዳር ኤርፖርት በመነሳት ላሊበላ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ወደ ላሊበላ ከተማ በማቅናት ላይ እያሉ ሹምሽሃ አየር ማረፊያ አጠገብ ልዩ ስሙ በርታ በተባለ ቦታ ድንገተኛና የተጠና ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። በተወሰደባቸውም መብረቃዊ ጥቃት ከ10 በላይ ቀይ ቦኔት ለባሽ አጃቢዎቻቸው የተደመሰሱባቸው ሲሆን ፕሬዝዳንቱም ለጥቂት ከፋኖ በትር እንዳመለጡና ከአየር ማረፊያው ቅርብ እንደነበሩ እና መንገድ ቀይረው በሌላ አቅጣጫ እንደፈረጠጡ ታውቋል። በመጨረሻም አገዛዙ ብልፅግና የመጨረሻው ህቅታ ላይ እንደሚገኝና የአለባብሰው ቢያርሱ የአዳራሽ ዲስኩር ህዝቡን እንደማያደናግረውና የፋኖ የድል ችቦና የአማራ ህዝብ ሰቆቃ የሚያበቃበት  ዘመን እውን እየሆነ መምጣቱን የተከዜ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለጦር  ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጅነር አማረ ካሳ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም

ሰበር የአማራ ክልሉ ፕሬዚዳንት ተብዬ አቶ አረጋ ከበደ ላሊበላ ላይ ጥቃት ተፈፀመባቸው! በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር  3ኛ ሻለቃና የክፍለ ጦሩ ሜካናይዝድ በጋራ  በመሆን ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 እስከ  ረፋዱ 3:30 ሰዓት  በወሰዱት ጥቃት የክልሉ ፕሬዝዳንት ነኝ የሚሉት ቀንድ አውጣ አረጋ ከበደ ከባህርዳር ኤርፖርት በመነሳት ላሊበላ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ወደ ላሊበላ ከተማ በማቅናት ላይ እያሉ ሹምሽሃ አየር ማረፊያ አጠገብ ልዩ ስሙ በርታ በተባለ ቦታ ድንገተኛና የተጠና ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። በተወሰደባቸውም መብረቃዊ ጥቃት ከ10 በላይ ቀይ ቦኔት ለባሽ አጃቢዎቻቸው የተደመሰሱባቸው ሲሆን ፕሬዝዳንቱም ለጥቂት ከፋኖ በትር እንዳመለጡና ከአየር ማረፊያው ቅርብ እንደነበሩ እና መንገድ ቀይረው በሌላ አቅጣጫ እንደፈረጠጡ ታውቋል። በመጨረሻም አገዛዙ ብልፅግና የመጨረሻው ህቅታ ላይ እንደሚገኝና የአለባብሰው ቢያርሱ የአዳራሽ ዲስኩር ህዝቡን እንደማያደናግረውና የፋኖ የድል ችቦና የአማራ ህዝብ ሰቆቃ የሚያበቃበት  ዘመን እውን እየሆነ መምጣቱን የተከዜ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለጦር  ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጅነር አማረ ካሳ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም

ሰበር ዜና! የአማራ ክልሉ ፕሬዚዳንት ተብዬ አቶ አረጋ ከበደ ላሊበላ ላይ ጥቃት ተፈፀመባቸው! በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃና የክፍለ ጦሩ ሜካናይዝድ በጋራ በመሆን ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 እስከ ረፋዱ 3:30 ሰዓት በወሰዱት ጥቃት የክልሉ ፕሬዝዳንት ነኝ የሚሉት ቀንድ አውጣ አረጋ ከበደ ከባህርዳር ኤርፖርት በመነሳት ላሊበላ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ወደ ላሊበላ ከተማ በማቅናት ላይ እያሉ ሹምሽሃ አየር ማረፊያ አጠገብ ልዩ ስሙ በርታ በተባለ ቦታ ድንገተኛና የተጠና ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። በተወሰደባቸውም መብረቃዊ ጥቃት ከ10 በላይ ቀይ ቦኔት ለባሽ አጃቢዎቻቸው የተደመሰሱባቸው ሲሆን ፕሬዝዳንቱም ለጥቂት ከፋኖ በትር እንዳመለጡና ከአየር ማረፊያው ቅርብ እንደነበሩ እና መንገድ ቀይረው በሌላ አቅጣጫ እንደፈረጠጡ ታውቋል። በመጨረሻም አገዛዙ ብልፅግና የመጨረሻው ህቅታ ላይ እንደሚገኝና የአለባብሰው ቢያርሱ የአዳራሽ ዲስኩር ህዝቡን እንደማያደናግረውና የፋኖ የድል ችቦና የአማራ ህዝብ ሰቆቃ የሚያበቃበት ዘመን እውን እየሆነ መምጣቱን የተከዜ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጅነር አማረ ካሳ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 01/ 2018 ዓ.ም

ከጠላት ወደ ሰፊ ሻለቃ ሰርጎ የገባው ባንዳ #ደግሰራ-ታረቀኝ የጓዳኛውኝ መሳሪያ ሰርቆ መግባቱን በተለያዩ የስርዓቱ መገልገያ ሚዲያዎች አየተሰራጨ ይገኛል... (አፋብኃ ምዕ/ ቴዎድሮስ ዕዝ ጥቅምት 0
ከጠላት ወደ ሰፊ ሻለቃ ሰርጎ የገባው ባንዳ #ደግሰራ-ታረቀኝ የጓዳኛውኝ መሳሪያ ሰርቆ መግባቱን በተለያዩ የስርዓቱ መገልገያ ሚዲያዎች አየተሰራጨ ይገኛል... (አፋብኃ ምዕ/ ቴዎድሮስ ዕዝ ጥቅምት 01 2018 ዓ.ም) ይህ የአረመኔው ስርዓት ፈረስ የሆነው ባንዳ #ደግሰራ-ታረቀኝ ከብርሸለቆ ማሰልጠኛ ተቋም ወጥቶ ወደ ሰፊ ሻለቃ የተቀላቀለ ሲሆን፣ ለሰው አዛኞች በቡሬ ዳሞት ብርጌድ ስር የምትገኘዋ ሰፊ ሻለቃ የለበሰውን በጭቃ የተለወሰውን ልብሱን አውልቀው አዲስ ልብስ አልብሰው ሰውነቱን አጥበው ምግብ አብልተው አጠጥቱው በተለየ እንክብካቤ ላይ መቆየቱ ይታወቃል። ባንዳው #ደግሰራ-ታረቀኝ የተዋለለትን ውለታ ወደ ጎን በመተው አምኖት ከሚንቀሳቀሰው ጓዱ ጥቁር መሳሪያ ሰርቆ ለጡት ቆራጩ ስርዓት እጅ ሰጥቷል። ይህን አስመልክቶ በሁሉም አቅጣጫ የምትገኙ የፋኖ አባላቶች ስርዓቱ አስርጎ እያስገባ ከአንዴም ሁለቴም አላማውኝ እያከናወነ መሆኑን የሚታወቅ ሁኖ ሳለ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስል መልዕክቴን አስተላልፋለሁ። ➧ መረጃውን ያደረስኋችሁ ፋኖ ጋዜጠኛ አይቸው ጌታሰው ነኝ። #ድሉ-የኛ-ነው