en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 389
Subscribers
+2924 hours
+2547 days
+1 45030 days
Posts Archive
የህዝብ ሰቆቃ እንደቀጠለ ነዉ አብይ ባሰማራዉ ዘራፊ ቡድን ህዝባችን መከራዉን እያየ ነዉ በዛሬ ሕዳር 26/3/2018ዓ.ም ከጧቱ 5:30 ላይ ጋይንት ንፍስ መውጫ ከከተማዋ 5ደቂቃ ወጣ ብሎ በአድማ ብ
+1
የህዝብ ሰቆቃ እንደቀጠለ ነዉ አብይ ባሰማራዉ ዘራፊ ቡድን ህዝባችን መከራዉን እያየ ነዉ  በዛሬ ሕዳር 26/3/2018ዓ.ም ከጧቱ 5:30 ላይ ጋይንት ንፍስ መውጫ ከከተማዋ 5ደቂቃ ወጣ ብሎ በአድማ ብተና እና በትራፊክ መካከል ሆነው ስድስት ወጣቶች አንድ የኮርያ ክላሽ በመያዝ  ሙሉ ከባህርዳር ወደ ወልዲያ 65ሰዎችን የጫነ የህዝብ መኪና በማስቆም ከ28 በላይ እስማርት ተች ስልክ፣ከ18ሺብር በላይ ገነዘብ ከደካሞች እየደበደቡ እንደተዘረፉ ተሳፍሪዎች ገልጸዋል ። ተሳታፊዎች አክለውም ስንዘረፋ ከዛው አከባቢ የሚኖር ካህን እያዩ ዝም አሉ ብለዋል።ልጆችም የጋይንት ልጆች እንደሆኑ ገልጸዋል። ተሳታፊዎች ገንዘባችን ሄዶ እንኳን ወንድ ልጅ በጥፊ እየተመታ ሴት ልጅ በእርግጫ እየተረገጠች ማየት ያሳዝናል ብለዋል።

#ሰበር_የምርኮ_ዜና_ሰከላ‼ ልማደኛው 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር እና 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር  በጥምረት #42_ጥቁር_ክላሽ ማርከዋል‼ በአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር እና 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ሰከላ ወረዳ አጉት ከተማና ዙሪያው ላይ ሰፊ ቦታ በሸፈነው አውደ ዉጊያ የአረመኔዉን ቡድን 42 ጥቁር ክላሽ ተረክበዉታል። 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ትናንት በሰከላ ከተማ የወረዳ አስተዳድሩን ጨምሮ ብዛት ያለዉ ሰራዊት በማስወገድ ታላቅ ጀብድ የፈፀሙ ሲሆን ዛሬ ህዳር 26/2018 ዓ.ም ደግሞ #ከሰከላ #ከማንኩሳ #ከቡሬና #ከፉነተሰላም ፔምፔ ዙ23 ይዞ #ምላስና #ብልት በመቁረጥ የስድስት ንፁሃንን ህይወት በቀጠፈበት #አጉት ቀጠና ተሰባስቦ በመምጣት ሳምንት እሁድ በአጉት ከተማ የንፁሃንን ጭፍጨፋ በመቃወም የተደረገዉን ህዝባዊ ሰልፍ ፋኖ አስገድዶን ነዉ የተሰለፍነ ለማስባልና ስሁት ፖለቲካ ትርፍ ለመስራት  ባደረጉት ሙከራ #ምላስና #ብልት በመቁረጥ ሰወ በላ ቡድን መሆኑን የተረዳው ህዝብ ከአካባቢው በመሸሽ ምንም አይነት ሰዉ ሳያገኝ ሳይሳካለቸዉ በቀሩበት ክስተት፤ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ እስከ 12:00 በዘለቀዉ ትንቅንቅ አንድ ሺአለቃ መሪ ጨምሮ ከ50 በላይ የጠላት ሀይል ተደምስሷል። ነፍሱ ያልወጣው ቁስለኛ ጭምር በመጣል የሚያነሳው ጠፋቶ በየ ጥሻዉ ወድቆ የጅብ ቀለብ ሁኗል። ከአጉት እሰከ ጅግሪታ ያለዉ ማሳ በሬሳ ተዋልቷል ከተማዋ ላይ የሚገኙ ሱቆችንና የግለሰብ ቤቶችን በመሉ እየዞሩ ሲዘርፉ በመኪና ሁሉ ሲጭኑ የዋሉት የአብይ ወንበዴዎች የዘረፉትን ሳይወስዱ ብሬንና ስናይፐሩን አስረክቦ የጨረሰዉ ቡድን ዛሬ ደግሞ #42 ጥቁር ክላሽ እና #በ10ሺዎች የሚቆጠር ተተኳሽ አስረክበዉ ሬሳቸዉን አዝረክርከዉ #ከአንድ ቲም በላይ ቁስለኛ #አስማርከዉ  አንገት ድረስ የቆፈሩትን ምሽግ ለቀው ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ሩጫ በማድረግ ቢሸሹም በዚህ ሰሃት ባሉበት ተከበዉ መውጫ አጠው ይገኛሉ። ከኮር አደረጃጅቱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰራዉ የሁለቱ ኮር ጥምረት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ በማድረግ አስደማሚ የሆነ ድል ተቀዳጅተው የጠላትን ቅስም በመስበር ምርኮ በምርኮ ተንበሽብሸዋል። የወንድሞቻችንን ደሞ ፣ የህዝባችንን አልህ፣ ቁጭት በተጠናከረ ሁኔታ፣ወኔ በተሞላበት እርምጃ መመለሱ ቀጥሏል። #ላናሸንፍ_የጀመርነዉ_ትግል_የለም_ድልችን_ቅርብ_ነው‼ #እንበርታ💪 የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት   ፋኖ አለበል አወቀ።

ዘራፊዉ የብልፅግና ሰራዊት በፋኖ አርምጃ አየተወሰደበት ነዉ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል (አፋብኃ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር በዛሬዉ ቀን 26/3/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓ
+3
ዘራፊዉ የብልፅግና ሰራዊት በፋኖ አርምጃ አየተወሰደበት ነዉ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል (አፋብኃ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር በዛሬዉ ቀን 26/3/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አሻሚት ቀበሌ ቧንቧ ዉሃ ከተባለዉ ቦታ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣዉ ይገኛል በኮሩ ሰር የሚገኙ 6ቱ ክፍለ ጦሮች የተዉጣጣ ሃይልና የኮሩ ልዩ ጥበቃ በዉጊያዉ ተሳትፈዋል አሁንም ዉጊያዉ እንደቀጠለ ሲሆን ሙሉ መረጃዉን በቀጣይ እናደርሳለን። ባንዴራዉ ግርማይ_የ4ኛ ደጃዝማች ኮር ህዝብ ግንኙነት ሰሞኑን ብልፅግና እና አንጃዎቹ የፋኖን ስም ለማጥፋት እና ህዝብን ለማወናበድ 9 የሚሆኑ ፋኖዎች ድሽቃ ይዘው እጅ ሰጡኝ እያለ ሲደሰኩር ነበር እውነታው ግን ምንም የሄደ ድሽቃ የለም በተቃራኒው ጦሩ የተሳለ ስለት እንደሆነ ማሳዎቃችን ይታወቃል ይሄው ዛሬ እውነታው ምድር የሚሆነው ነው 💪 ይቀጥላል ✊

አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ24 ስዓት የውሎ ዘገባ __፩ ዳንጉር ፣ጃዊ ፣ዳንግላ ፣አፈሳ፣ሰከላ ዙሪያ አጉት  ጠንከር ያለውጊያ ተደረገ ።   የአማራን ሕዝብ በሳምንት ውጋያ ትጥቁን አስፈተዋለሁ ብሎ የገባው የብልፅግና አረመኔ ሰራዊት በአማራ ምድር  እንደ ቆሎ እየረገፈ ፣ትጥቁንም እየፈታ ይገኛል። ለሶስት አመት አካባቢ እየተዋጋ የሚገኘው አረመኔ ሰራዊት በአማራ ፋኖ እየደረሰበት የሚገኘውን ሽንፈት በአፉ  ማመን ቢያዳግተውም በየግንባሩ ግን በርካታ ወታደሮችን እየቀበረ ፣ትጥቁንም እና ተቆጣጥሮት የነበረውን ቦታም እያስረከበ ይገኛል። በዛሬው እለትም አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና  ቴዎድሮስ ዕዝ በተለያዩ ግንባሮች መለትም በዳንጉር ፣በጃዊ ፣በዳንግላ ዙሪያ ማረሚያ ቤት አካባቢ ፣በአፈሳ፣ሰከላ ዙሪያ  አጉት  ጠንከር ያለ ውጋያ አድርጓል። 77:44:66፣55 እና 22 ክፍለጦር ጠላትን በተለያዩ ግንባሮች ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ እና 105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ በጥምረት ዐባይ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: ሁለቱ ኮሮች በጥምረት አባይ ድልድይና አፈሳ መግቢያ ላይ  ዛሬ ህዳር 26/2018 ዓ/ም ማለዳ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀን 6:00 ሰዓት ድረስ ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሠራዊት ጋር በመፋለም ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: ጠላት ድልበትግል/ናዳ/ ከተማን እና አፈሳ ከተማን ለመቆጣጠር ከገርጨጭ ከተማና ከወተት አባይ ከተማ በርካታ ሃይል በመያዝና ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሣሪያ በመታገዝ አፈሳ ከተማ መግቢያ ዐባይ ድልድይ ላይ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ እና 105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ በጥምረት የጠላትን ሠራዊት ለጊዜው በስም ያልታወቁ አመራሮችን ጨምሮ በመደምሰስና በማቁሰል ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ብሎም ቀጠናውን በማስከበር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: በዚህ በድንቅ መናበብ በተመዘገበ ታላቅ  ድል የጠላት ሠራዊት በሁሉም አቅጣጫ የተመታ ሲሆን አስከሬንና ቁስለኛውንም እያነሳ ወደመጣበት አቅጣጫ ሸሽቷል:: በተመሳሳይ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር በጃዊ ቀጠና ዘንዘን ከተባለ ቦታ ላይ ከጠላት ጋር በተደረገ የእጅ በእጅ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ:- የክ/ጦሩ ተወርዋሪ ቃኝ እና መሀንዲስ ሻለቃ፣ 2ኛ ሻለቃ፣ 4ኛ ሻለቃ በጥምረት ያስገኙት ድሎች: 1ኛ.ከ30 በላይ የአብይ ወንበር ጠባቂ ሰራዊት አባላትን መደምሰስ ሲቻል በርካቶችን ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። 2ኛ.22 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ መማረክ (ማግኘት) ተችሏል። 3ኛ.490 የብሬን ጥይት፣2 ሸንሸል፣ከ1000 በላይ የክላሽ ተተኳሽ፣14 የእጅ ቦንቦች፣ 01 የስናይፐር መነፀር (ክሻፋ) የመሳሰሉትን የጠላት ቁሳቁሶች መማረክ (ማግኘት) ተችሏል። በሌላ መረጃ በትናንትናዉ እለት የ105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ መተከል ዳንጉር ወረዳ ኤልፍኝ ከተባለ ቦታ ላይ ከጠላት ጋር በተደረገ ትንቅንቅ ድል መገኘቱን የዘገብን መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም ከ10 በላይ የጠላት ኃይል ተደምስሷል። በርካቶችንም ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። በርካታ ተተኳሾችን እና ትጥቆችን ማግኘት የተቻለ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን። የሰደድ እሳት የሆነዉ ነበልባሉ ፋኖ የአብይን ገረድ ሰራዊት እየለበለበ አስከሬኑን እያዝረከረከ ወደ ማምቡክ እንዲፈረጥጥ አድርጎታል። ___፪ በተደጋጋሚ በተለያዩ የግንባር ውጊያዎች ሽንፈቱን የተጎናፀፈው አረመኔ ሰራዊት  የጥላቻ ጥጉን  የገበሬውን  ሀብትና ንብረት በማውደም እያሳየ ነው።     አማራ የሆነን ሁሉ ባንዳ ብሎ የፈረጀው የብልፅግና ስርዓት በደረሰበት ሁሉ የደረሰ ሰብልን እያቃጠለ፣ የሚያገኘውን ማህበሰሰብ እያፈነ  ገንዘብ እየተቀበለ ይገኛል።  በአዴት አንጋር ፣ሰቀለ ማርያም እና ዴንሳ ባታ አካባቢ ሊጥ ፣ዱቄት ፣የተከዘነ እህል ፣ በርቤሬ  በመዝረፍና በመበተን የቆመ ሰብል በማቃጠል የጥላቻ ጥጉን በሚገባ አሳይቷል። የአለም አቀፍ የጦር ህጎችን በመጣስ ምንም የማያውቁ ንፁሃንን እየጨፈጨፈ እና ሀብት ንብረታቸውን እያወደመ የሚገኘውን የብልፅግና ስርዓት በየትኛውም መልኩ ልንዋጋው ይገባል። ለዚህም ሁሉም  በከተማም በገጠርም የሚገኝ ማህበረሰብ የሚሰጠውን  ግዳጅ   በአግባቡ  ለመወጣት  ዝግጁ መሆን ይገባል ። አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!   ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            ህዳር 25/2018 ዓ.ም

አርበኛ ዝናቡ ልንገረው ፺፱ኛ ክፍለጦር ሲዋቀር በስብሰባው ተገኝቶ የተናገረው ድንቅ ነቫራዊ ሀቅ ንግግር እንዲህ ይላል። <<ብዙ አቅም ያላቸው ለሰብሳቢነት የሚመጥኑ ሰዎች አሉን ነገር ግን
አርበኛ ዝናቡ ልንገረው ፺፱ኛ ክፍለጦር ሲዋቀር በስብሰባው ተገኝቶ የተናገረው ድንቅ ነቫራዊ ሀቅ ንግግር እንዲህ ይላል። <<ብዙ አቅም ያላቸው ለሰብሳቢነት የሚመጥኑ ሰዎች አሉን ነገር ግን መቶ አቅም ያላቸው ሰዎች ቢኖሩ ሰብሳቢ እምናደርግ ግን አንዱን ነው ።ሁሉም ሰብሳቢ አይሆንም፡ሁሉም ጦር አዛዥ አይሆንም። እኛ ነፃነት ናፍቆን የናፈቀንን ነፃነት ለማግኘት ለትግል ወጣን እንጅ የሥራ እድል መፍጠርያ ማሽኖች አይደለንም። አቅም ያላቸውን ሁሉ ሰብስቦ ሰብሳቢ ወይም ጦር አዛዥ አልያም ከየላ አንድ የሥራ ዘርፍ ላይ ማድረግ እንደማይቻል አለም ላይ ያለ እውነታነው።ስለሆነም በአንፃራዊነት ሰዎች ቦታ ይኖራቸዋል እንጅ።ይህን በመረዳት የሞት እጣ በሆነ ኃላፊነት ሳንሸናጓ የቅንነት ስንቅን ይዘን የመላው የአማራዊያንን የኅልውና ትግል ለፍፃሜ ልናደርስ ይገባናል>>ሲል ይገልፃል። @Dega Damot Gojjam

የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ እና 105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ በጥምረት አባይ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ። የሁለቱ ኮሮች በጥምረት አባይ ድል
የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ እና 105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ በጥምረት አባይ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ። የሁለቱ ኮሮች በጥምረት አባይ ድልድይና አፈሳ መግቢያ ላይ እና ትናንት ህዳር 25/2018 ዓ/ም ማለዳ 2:00 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀን 6:00 ሰአት ድረስ ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር በመፋለም ታላቅ ድል አስመዝግበዋል። ጠላት ድልበትግል /ናዳ/ ከተማን እና አፈሳ ከተማን ተመቆጣጠር ከገርጨጭ ከተማና ከወተት አባይ ከተማ በርካታ ሀይል በመያዝና ከነፍስ ወከፍ እክከጠቡድን መሳሪያ በመታገዝ አፈሳ ከተማ መግቢያ አባይ ድልድይ ላይ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ እና 105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ የተውጣጡ ሻለቆች በጥምረት የጠላትን ሰራዊት ለጊዜው በስም ያልታወቁ አመራሮችን ጨምሮ በመደምሰስና በማቁሰል ከባድ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ብሎም ቀጠናውንና ከተሞቹን በማስከበር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል ። በዚህ በድንቅ መናበብ በተመዘገበ ታላቅ ፍልሚያና ድል የጠላት ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ የተመታ ሲሆን አስክሬንና ቁስለኛውንም እያነሳ ወደመጣበት አቅጣጫ ሸሽቷል። በዚህ ታላቅ ተጋድሎ ከባድ ምት የተመታዉ የአገዛዙ ሰራዊት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ ሲሆን የስርአቱ ሰራዊት አመራሮች ተከበናል መላም የለን እያሉ ወደ ከዳንግላ ከተማ ተጨማሪ ሀይል በማስመጣት እግሬ አውጭኝ እያሉ ነዉ። አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ እና የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር አመራሮች!! ✅ ደራሲ እና መምህር አርበኛ አንተነህ ድረስ የበላይ ዕዝ የጥናትና ምርምር መምሪያ አላፊ ! ✅
+2
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ እና የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር አመራሮች!! ✅ ደራሲ እና መምህር አርበኛ አንተነህ ድረስ የበላይ ዕዝ የጥናትና ምርምር መምሪያ አላፊ ! ✅ አርበኛ መምህር ጸዳሉ ሙላት የበላይ ዕዝ ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ አላፊ ✅አርበኛ አመኑ አለምአንተ የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ሰብሳቢ! ✅አርበኛ መምህር ጌታቸው አዱኛ የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ምክትል ሰብሳቢ ✅አርበኛ በላይነው የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ወታደራዊ አዛዥ እና ሌሎችም ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች! ድል ለአማራ ፋኖ

#በቢቸና_ከተማ_የአገዛዙ_ሀይል_ንፁሀንን_ረሽኗል! የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ በቢቸና ከተማ ፍራሽ ሰፍቶ ይተዳደር የነበረን #ዘውዱ_ዳኘ የተባለ የእነቆራ ቀበሌ ንፁሃን ግለሰብን በግፍ እረሽኗል። ስርአቱ
+1
#በቢቸና_ከተማ_የአገዛዙ_ሀይል_ንፁሀንን_ረሽኗል! የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ በቢቸና ከተማ ፍራሽ ሰፍቶ ይተዳደር የነበረን #ዘውዱ_ዳኘ የተባለ የእነቆራ ቀበሌ ንፁሃን ግለሰብን በግፍ እረሽኗል። ስርአቱ በሰፊው ንፁሀንን ያለበቂ ምክኒያት በየከተማው ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል የፋኖን ተመሳሳይ ልብስ እና ትጥቅ በመጠቀም በእገታ ብር እየተቀበለ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ ዝርፊያወች ላይ የተሰማራ መሆኑን በሁሉም ቀበሌወች የግለሰቦችን ሀብት ንብረት እየጫነ እየወሰደ ስለሆነ ሁሉም እራሳቹሁን የመከላከል ስራ እንድትወጡ። ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት             ህዳር 26/2018 ዓ.ም                                                                                              አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!

https://youtu.be/0KrV2DcpY10?si=HoJtDoi_iE-tMsN0 ህዝባችን እደዚህ በሰነ ልቦና እና በፖለቲካ ንቃተ ህሌና ሊታጠቅ ይገባል።

ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ  ኃይል አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር  የተሰጠጠ መግለጫ እንደሚታወቀው የአሸባሪው አብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ጅምላ ጭፍጨፋ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል ከዚህም አልፎ አማራ በሄደበት ሁሉ እንደጠላት ተቆጥሮ ባቀናት ሀገር ላይ መኖር አትችልም ተብሎ በየጊዜው ይፈናቀላል ይገደላል። በዚያም የአማራ ፈኖን ምት መቋቋም ያልቻለው ገዳይ ስረዓት ንፁሀንን እየጨፈጨፈና እየዘረፈ ይገኛል ። ስለዚህ አማራ በኢኮኖሚ እንዲዳከም የገዢው ብልፅልና ባለሀብቶችን እያሰረ እየዘርፈ መሆኑ ይታወቃል:: ስሞኑንሞ  በተለያዩ የክልላችን ቦታዎች ለአብነትም በአዋባል ወረዳ ሉማሜ ከተማ ላይ የብልፅግና ቅለብ ካድሬዎች የተበጀተውን አመታዊ የወረዳ በጀት በ5 ወር በመጨረሳቸው  ለሚኒሻ ፦ አድማ ብተና የሚከፈል ደመወዝ እና የስራ ማስኬጃ ገንዘብ በመጥፋቱና የሊዝ ቦታ እንሸጣለን በሚል ሰበብ ከባለሀብቶች እና የከተማው ነዋሪዎች ገንዘብ ለመሰብሰብ  ለአብነትም በደጀን ወረዳ 37 የከተማ ቦታወችን ለመሸጥ ማስታወቂያ በመለጠፍ ለማጫረት በዝግጅት ላይ ይገኛል። ስለዚህ 1ኛ   ማንኛውሞ ግለሰብ በዚህ ጊዜ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር እንጅ ቤት የምንሰራበት የገንዘብ መጠን የምናሳድግበት ጊዜ ስላልሆነ ፋኖ ከተደራጀበት እና ስርዓቱ ከፈረሰበት ጊዜ ከ  ሀምሌ 26/2015 አ.ም ጀምሮ የገዛው ቦታ ከህግ አግባብ ዉጭ መሆኑን እንዲያውቅና አማራን እየጨፈጭፈ ላለው ስርዓት ተባባሪ መሆኑን ተገንዝቦ ከዚህ ድርጊቱ እንደታቀብ እናሳስባለን። 2ኛ   ይህን አማራ ጠል ስርዓት ተባብሮ መጣል ሲገባ የሊዝ ቦታ የሚገዛ ማንኛው ተቋምም ሆነ ግለሰብ የገዛው ቦታ እንደሚወረስና እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እንዳዉቅና ከድርጊቱ እንድታቀብ ::ይህን ትዕዛዝ ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ግለስብ ሆነ ተቋም  የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን ። አድስ ትውልድ ,አድስ አስተሳሰብ ,አድስ ተስፋ !!! ጋዜጠኛ ሐብታሙ ጌታቸው የአፋብኃ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት     ህዳር 26/2018 ዓ.ም

ከመቶ በላይ ጠላት ተደመሰሰ!! ልማደኛዉ ደጅአዝማች 4ኛ ኮር በመተማ ወረዳ ሽመለ ጋራ ቀበሌ በቀን 25/3 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00ሰአት ጀምሮ ቀበሌ ሆርጃሙስ ክሬቸሩ እና ቁጥር 1 መውጫ አዲስ አለም አካባቢ በ3 አቅጣጫ የመጣዉን ፋሽስቱ አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጠንካራ ጥቃት በመክፈት ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል። ከ6 ክፍለጦር የተዉጣጣ የበላይ ዕዝ 4ኛ ኮር ሰራዊት በወሰደዉ የተሳካ ማጥቃት ከ100 በላይ ሲደመሰስ ከ55 በላይ ቁስለኛ ሁኗል። በተጨማሪም ሲጓጓዙበት የነበረዉ ተሽኸርካሪ በተሰነዘረበት ጥቃት ከጥቅም ዉጭ ሁኗል። በላይ ዕዝ በጀመረዉ ጥልቅ የማጥራትና የማረም ስራ ተሞርዶ ስሉ እየሆነ የሚገኘዉ ደጃዝማች ኮር ይህን ዉጤታማ የድምሰሳ ዉጊያ ግዳጅ ሲፈፅም ያለ መስዋትነት ነዉ ። ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን !! አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ህዳር 26/2018 ዓ .ም ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

የገጠምነው ጠላት የተሸነፈ ነው። ፖለቲካው የተምታታበት፤ ከራሱ አልፎ ውሸት እና ማጭበርበርን ለዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር ያስተማረ፤ የሚያደርገው መላ ቅጡ የጠፋበት፤ በህዝብ የተናቀ፤ በዓለም ፊት ሞገስ ያጣ አገዛዝ ነው። ይህ ውጤት እንዲመጣ ላለፉት ድፍን አራት ዓመታት እና ከዚያ በላይ በጠራ መስመር፣ በፅናት እና በድፍረት በመታገላችን እና በማታገላችን ኩራት ይሰማናል። ከብዙ መስዋዕትነት በኋላ ይህንን ትግል ከግለሰቦች ተፅእኖ አውጥተን የትውልድ አድርገነዋል። የአማራ የህልውና ትግል ማንም በኪሱ ይዞት የሚዞር አጀንዳ አይደለም። የሆነ ቡድን ወይም ግለሰብ ሲፈልግ የሚያነሳው ሳይፈልግ የሚጥለው እንዳይሆን አድርገነዋል። የፋኖን እንቅስቃሴ ከመንደር አውጥተን የቀጠናው ተፅእኖ ፈጣሪ ኃይል ማድረግ ችለናል። የአማራን ፖለቲካም ዓለም በአንክሮ እንዲያየው ማድረግ ተችሏል። የቀጠናውን ኃይሎች የማስተባበር ኃላፊነትን መሸከም የሚችል የአመራር ቋት በመፈጠር ላይ ነው። ድንጋይ ነክሰን ከነጣቂወች እና ከሰንጣቂወች የጠበቅነውን ትግል ለባለአደራው ትዉልድ እናስረክበዋለን። መሪያቸው በጠላት ጫና በተሰደዱ እና መንግስታዊ መዋቅር በፈረሰ ግዜም ጭምር ሀገር ያቆዩ፤ የኢትዮጵያን ህብራዊ ማንነት ከቅኝ ገዥወች የጠበቁት የአርበኞቹ ልጆች ነን። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ድል ተጎናፀፉ:: ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር 4ኛ (በረኸኛው) ሻለቃ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ካራኤላ እና አጣዋ ጋሪያ ላይ ጠላት ኮንክሪት ምሽግ ሰርቶ ከመሸገበት ድረስ ትናትና ህዳር 25/2018 ዓ.ም ምሽት በመግባት በርካታ ሃይሉን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል:: ጠላት ወደሚመታበትና በጅምላ ወደሚማረክበት ቦታ ተስቦ የገባ ሲሆን በተደጋጋሚ የደፈጣ ጥቃት እየተመታ ሲሆን መካናይዝዱንም ማሸሽ ጀምሯል:: በቀጣይም በደፈጣ እና በሽምቅ ውጊያ የማሰላቸት የማሸማቀቅና የማፍረስ ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥልና ባመች ጊዜ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ወደሚደመሰስበትና ወደሚማረክበት መደበኛ ተጋድሎ በማስገባት ድል እናደርገዋለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምኒልክ ዕዝ ህዳር 26/2018 ዓ.ም

መኖር ማለት ፎቅ መገንባት ነውን? መኖር ማለት ቤት መስራት ነውን? መኖር ማለት መኪና መግዛት ነውን? መኖር ማለት ስልጣን መያዝስ ነውን? በእውነቱ እኛ ስለተመቸን ብቻ ሌሎች ሲገደሉ ሲፈናቀሉ ዝም ብሎ መመልከት እና ተባባሪ መሆን ይህ መኖር ነውን ? ህሊናችንን ሽጠን የምንኖረው የተደላቀቀ ኑሮ እረፍት ይሰጠናል? በሰው ደም፣ በሰው አጥንት ተረማምደን የምንበላውስ ይመጥነናል? መኖር ማለት የምትኖርለት አላማ የምትሞትለት እውነት ሲኖርህ ነው ፤ መኖር ማለት በንፁህ ህሊና ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ስታስብና ከፀፀት ስትድን ነው፤ ያለበለዚያ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው። ከእውነት ሸሽቶ በህዝብ ተጠልቶ ከመኖር እንደተወደዱ መሞትን እመርጣለሁ!!! ፈጣሪ ህሊናን ከመሸጥ ይሰውረን። ✍️ Ayinades Walelgne የአቶ ሰጤ በዚህ ውሰጥ ነው የሚሰቃየው

:::::::ነገረ ማስረሻ ሰልቅጤ።።።።።። አንድ ሚዲያ ላይ የሰማሁት ማስረሻ ሰጤ እያላችሁ አትጥሩት ሲሉ ሰማሁና ለምን ስል ምክኒያቱም እንዲህ አይነት መናኛ ልጅ የወለዱ አባት በልጃቸው ምክኒያት ለ
:::::::ነገረ ማስረሻ ሰልቅጤ።።።።።። አንድ ሚዲያ ላይ የሰማሁት ማስረሻ ሰጤ እያላችሁ አትጥሩት ሲሉ ሰማሁና ለምን ስል ምክኒያቱም እንዲህ አይነት መናኛ ልጅ የወለዱ አባት በልጃቸው ምክኒያት ለቤተሰቦቻቸውም ክብር ሲባል የእሳቸው ስም ባይነሳ ከዚያ ይልቅ ማስረሻ ሰልቅጤ በሚል ይስተካከል አሉኝ። እውነት ለመናገር የአማራ ህዝብ በእነ አረጋ ከበደ አይነት ሀገር አጥፊ ውሻታም የአማራን ማህበረሰብ ስሪት የማይመጥኑ አለም ይታዘበናል የማይሉ ሞራለ ቢሶች ሲመራ ማየት እጅግ በጣም ያበሳጫል አማራ ሰው የለውም እንዴ ያስብላል። ኢጋድና አፍሪካ ህብረትም ነገሩን ሳይመረምሩ የፕሮፖጋንዳው ተጋሪ ሲሆኑ ሳይ አፍሪካን በአለም አደባባይ ባዶ ማማ ላይ የሰቀሉ ድርጅቶች ሆነዋል። ብልፅግና በዚህ ልክ ከፀዳሉ ደሴና ከአንዳንድ ሰሞኑን የሰላምን አማራጭ ተቀበሉ ከሚባሉት ሌቦች ያልተሻልን ሰው ማስረሻ ሰልቅጤን አስገብቶ ለፕሮፖጋንዳ በውሸት ይህን ያህል እርቀት መጓዝ አንድም ስርዓቱ መፈረካከሱና ወዥንብር ውስጥ መግባቱን የሚያመላክት ሲሆን ሁለትም ውሸታቸውን በአደባባይ አጥበው ያሰጡበት ነው። ይህ ደግሞ ለፋኖ ትልቅ የፖለቲካ ድል ነው። ስለዚህ ፋኖ በተቀናጀ መልኩ የአፍሪካ ህብረትንም ኢጋድንም ይቅርታ እንዲጠይቁ ጫና ማድረግና ከውሸቱ ፕሮፖጋንዳ እራሳቸውን እንዲያርቁ ብዙ ስራ ይጠበቅበታል። ታሪካዊ ድርድር ብየዋል ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ላይ አንድ ግለሰብ እራሱን እንደ ድርጅት ቆጥሮ የተደራደረ ማስረሻ ሰልቅጤ ብል ማጋነን አይሆንም። አፋሀድን ኢጋድን አዩንና ብልፅግናን ሰልቅጦ ውሸትን በአደባባይ ለአለሙ ማህበረሰብ ስላስረዳልን በጣም ሊመሰገን ይገባዋል እድሉን ከተጠቀመበት ለፋኖ ትልቅ የፖለቲካ ድል ነው። ፋኖ ይችላል ብልፅግና ትልቅ ነጥብ ጥሏል

ከመቶ በላይ ጠላት ተደመሰሰ!! ልማደኛው  ደጃዝማች 4ኛ ኮር  በመተማ ወረዳ ሽመለ ጋራ ቀበሌ በቀን 25/32018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ቀበሌ  ሆርጃሙስ ክሬቸሩ እና ቁጥር 1መዉጫ አዲስ አለም አካባቢ በ3 አቅጣጫ የመጣዉን ፋሽሽቱ አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጠንካራ ጥቃት በመክፈት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል።   ከ6 ክፍለ ጦር የተዉጣጣ የበላይ ዕዝ 4ኛ ኮር ሰራዊት በወሰደዉ የተሳካ ማጥቃት  ከ100 በላይ ሲደመሰስ   ከ55 በላይ ቁስለኛ ሁኗል።   በተጨማሪም ሲጓጓዙበት የነበረው ተሽኸርካሪ በተሰነዘረበት ጥቃት ከጥቅም ውጭ ሁኗል።    በላይ ዕዝ  በጀመረው ጥልቅ የማጥራትና የማረም ስራ ተሞርዶ ስሉ እየሆነ የሚገኘው ደጃዝማች ኮር ይህን ውጤታማ የድምሰሳ ውጊያ ግዳጅ ሲፈፅም ያለ መስዕዋትነት ነው።       ፈህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!          አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ            ህዳር 26/2018 ዓ.ም