en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 256
Subscribers
-824 hours
+887 days
+1 19430 days
Posts Archive
👉የወለጋ ክ/ሐገር ፋኖ (ቢዛሞ)!! የአፋብኃ አካል ከሆነው የወለጋ ክ/ፋኖ (ቢዛሞ) ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዲያቆን ክንዱ አሸናፊ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ቆይታ አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ዛሬ ታህሳስ
+4
👉የወለጋ ክ/ሐገር ፋኖ (ቢዛሞ)!! የአፋብኃ አካል ከሆነው የወለጋ ክ/ፋኖ (ቢዛሞ) ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዲያቆን ክንዱ አሸናፊ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ቆይታ አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ዛሬ ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም በMereja TV እናቀርባለን ይጠብቁን!!

ቀይ ባህርይ የሚያስመልስ የአብይ አህመድ አየር ወለድ ኃይል ነው ኃሳብ ስጡበት

ሻለቃ አብዬ ተፈራ ብዙ ጀግኖችን ያፈራው ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ከሚተማመንባቸው መካከል ጀግና እሳት ተራምዶ ጉሮሮ የሚጨብጥ አያሌ ጀብዶችን የፈፀመው ርር ያለው የእሳት ወላፈን ሻለቃ አብዬ ተፈራ ልቡን አምኖ የመነነው ታማኝ የአማራ ልጅ ክበርልን!! የነ ደርምስ ልጅ የጎንደሬ በጋሻው ክንድ ጎንደር ከተማ፣ወገራ፣ደንቢያ፣በለሳ፣ኪንፋዝ፣አርማጭሆ፣ወልቃይት ጠገዴ፣ደጎማ ማክሰኝት፣አይባና ስሁር እንዴት ውሎ አደረ? ታማኝ፣ደፋር፣ቀና ህዝባዊ አገልጋይ ታጋያችን አብዬ ተፈራ በቀጠናው አንተና ጓዶችህ እየሰራችሁ ላላችሁት ስራ ታሪክ ሁሌም ይዘክራችኋል። በተለይ ከጓዶቻችሁ ሻምበል ሙሉሰው፣ወርቁ ዘገየ፣ደመላሽ ስመኝ እና ገብርዬ ጌታሁን እና ሌሎች ጋር ተናባችሁ እንደተለመደው ታሪክ ስሩ። የሰረገው የሞፈሪያት ካሚል የጎንደር ከተማ ኮሚቴ አናግሩት አነጋግሩት። ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

#የአባት_አርበኞች_ጦር_ጥቃት_ፈፅመዋል " ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም በ201ኛ ኮር 74 ክ/ጦር##የእናርጅ_እናውጋ_ወረዳ የዲያጠባ ቀበሌ አባት አርበኞች ጦር የገበሬውን የግል የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ የተንቀሳቀሰውን የምኒሻና እና አድማ ብተና ቡድን ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም 4 ምኒሻ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል። በዚህ የአባት አርበኞች ጦር ቁስለኛ ካደረጎቸው የሚሊሻ አባለት ፦ 1. ሞላ አንዳርጌ 2. አባትነህ ዋለ 3. ስላባት በቀለ 4. ቢሰነብት የወጉ የተባሉ የብልፅግና ተላላኪ የምኒሻ አባላት በደፈጣ ጥቃቱ በጠና ቆስለው ደ/ወርቅ ሆስፒታል መግባታቸውን አረጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት 74ኛ ክፍለ ጦር አባላት እና የቀጠናው የአረበኞች ጦር ታሪክን በተግባር ሰርተው አርያ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ አዱስተስፋ" የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት

የአረጋ ከበደ ስብሰባ በመርዓዊ ከሽፏል ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። በዛሬው ዕለት ማለትም ታህሳስ 15/2018 ዓ/ም መርዓዊ ከተማ ላይ የባንዳዎች ፊት አውራሪ አረጋ ከበደ የተመራው ልዑክ በመርዓዊ ህዝብ ፊት ተዋረደ። የመርዓዊ ህዝብ የአረጋ ከበደን ልዑክ በአዳራሽ ተገኝቶ አቀባበል እንዲያደርግና የአማራን ህዝብ ትግል ጠልፎ የሚጥል ሀሳብ እንዲሰነዝሩ ከአገዛዙ ጥሪ ቢደረግም ሜጨኞቹ ግን አንድም የብልፅግና አመራር ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም እኛ የአማራ ህዝብ ትግል ቆስቋሽም ታጋይም ነን በማለት በራቸውን ዘግተዋል። በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ቡድን ቤት ለቤት እየዞረ ወደ ስብሰባው እንዲገቡ ለማስገደድ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም የመጨረሻ ያለውን ሀይል በማሰባሰብ ከባህር ዳር ደብረ ማርቆስ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ተሳፍረው የሚንቀሳቀሱ ተሳፋሪዎችን በማስገደድ ተሳፋሪዎች የመርዓዊ ከተማ ነዋሪ መስለው እንዲሰበሰቡ ለማድረግ ቢሞክርም የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር በኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ሻለቃ ኢፌሳና አማሪት ጎደሀ ቀጠና በማካለል መርዓዊ ከተማ ላይ በሞርተርና በዲሽቃ የታገዘ ውጊያ በማድረግ ስብሰባው እንዲከሽፍ ተደርጓል። በዚህም ዕቅዱ የከሸፈበት ቡድን ያገኘውን ሁሉ በሀይል በዱላና ሰደፍ እየደበደበ የጤና መድን ክፈሉ እናንተ ሜጨኞች የፅንፈኛው ቀድኛ ደጋፊ ናችሁ በማለት በተለይ ሴቶችን እያንገላታ እንደነበር ለማረጋገጥ ችለናል። የዛሬው ድል አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የመዋቅር ማሻሻያ እና ጦሩን በኮር የማደራጀት ስራ ሰርተን ባጠናቀቅንበት ማግስትና የስርዓቱ አገልጋዮች ሜጫ ላይ የቸደራጀ የፋኖ አወቃቀር በቸለይም በቀድሞ አጠራሩ የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ የሚባለውን ሀይል ሙሉ በሙሉ ደምስሰን በትነነዋል ብለው የተለመደ የተፈበረከ ዜናቸውን ከመስራታቸውን ማግስት መርዓዊ ላይ ገብቶ የአረጋ ከበደን ስብሰባ መበተንና ጠላትን ሙትና ቁስለኛ ማድረጋችን ልዩ ያደርገዋል። ታህሳስ 15/2018 ዓ/ም የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቴዎድሮስ የደሜ

"አስቸኳይ እና እጅግ አሳሳቢ መረጃ! የመምህር ​ታድዮስ ታንቱ ሕይወት አደጋ ላይ ነው!" ​ባለፉት ሁለት ዓመታት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት አንጋፋው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ተመራማሪ ታድዮስ ታንቱ፣
"አስቸኳይ እና እጅግ አሳሳቢ መረጃ! የመምህር ​ታድዮስ ታንቱ ሕይወት አደጋ ላይ ነው!" ​ባለፉት ሁለት ዓመታት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት አንጋፋው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ተመራማሪ ታድዮስ ታንቱ፣ በአሁኑ ወቅት ሊቀለበስ በማይችል እጅግ አሳሳቢ የጤና ቀውስ ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል። ከቅርብ ቤተሰቦቻቸውና ከሕግ ባለሙያዎቻቸው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የታ የታድዮስ ሁኔታ በእጅጉ የሚያሰጋ ደረጃ ላይ ደርሷል! ​ታሪክ አዋቂውና አንጋፋው የ84 አመት ጋዜጠኛ ታድዮስ ታንቱ በሕይወት የመቆየት መብታቸው ሊከበር ይገባል! ​ይህ መልእክት ለሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲደርስ Share በማድረግ ድምፅ እንሁን!

አረጋ ከበደ መርዓዊ ላይ ምን ገጠመው!! VIVA👏👏👏 ቴወድሮስ ዕዝ 👉102ኛ ኮር 👉22ኛ ክ/ጦር አረጋ ከበደን መርዓዊ ላይ በሞርተር አሯሯጠችው። ባለስናፐሩ ላመነው ሰጤ ታርጌት አድርጎ አከ
አረጋ ከበደ መርዓዊ ላይ ምን ገጠመው!! VIVA👏👏👏 ቴወድሮስ  ዕዝ 👉102ኛ ኮር 👉22ኛ ክ/ጦር አረጋ ከበደን መርዓዊ ላይ በሞርተር አሯሯጠችው። ባለስናፐሩ ላመነው ሰጤ ታርጌት አድርጎ አከታትሎ በተኮሰሰው ሞርተር የብልፅግና ሽ*ፍ*ታ ካድሬዎችን መበተን ተችሏል። በዚህ ስብሰባ አረጋ ከበደን ጨምሮ ከዞን እስከ ወረዳ በተዋረድ ያሉ የብልጽግና አ*ሽ*ከ*ሮች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።አረጋ ከበደ መርዓዊ ላይ ምን ገጠመው!! VIVA👏👏👏 ቴወድሮስ  ዕዝ 👉102ኛ ኮር 👉22ኛ ክ/ጦር አረጋ ከበደን መርዓዊ ላይ በሞርተር አሯሯጠችው። ባለስናፐሩ ላመነው ሰጤ ታርጌት አድርጎ አከታትሎ በተኮሰሰው ሞርተር የብልፅግና ሽ*ፍ*ታ ካድሬዎችን መበተን ተችሏል። በዚህ ስብሰባ አረጋ ከበደን ጨምሮ ከዞን እስከ ወረዳ በተዋረድ ያሉ የብልጽግና አ*ሽ*ከ*ሮች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

ስቦ ማስከዳት የአብይ እና የብርኃኑ ጁላ ጦር እየፈራረሰ ነው በደጋ ዳሞት ወረዳ ከ23ኛ ክፍለ ጦር በቀን 15/04/2018 ዓ.ም ሁለት መሰረታዊ ወታደር እያንዳንዳቸው ጥቁር ክላሽ በመያዝ የአፋብኃ
ስቦ ማስከዳት የአብይ እና የብርኃኑ ጁላ ጦር እየፈራረሰ ነው በደጋ ዳሞት ወረዳ ከ23ኛ ክፍለ ጦር በቀን 15/04/2018 ዓ.ም ሁለት መሰረታዊ ወታደር እያንዳንዳቸው ጥቁር ክላሽ በመያዝ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ሻለቃን ተቀላቅለዋል :: 1ኛ . መሰረታዊ ወታደር አድነው እንየው         ...1ኛ ሬጅመንት ሻምበል 3 ጥቁር ክላሽ እና 91ጥይት 2ኛ.መሰረታዊ ወታደር ንግሩ ደመቀ      ..... 1ኛ ሬጅመንት ሻምበል 3 ጥቁር ክላሽ እና 110 ጥይት  በመያዝ ተቀላቀለዋል ::  በተያያዘ ከጠዋቱ 1:00 አካባቢ ፈረስ ቤት ከተማ አናብስቶቹ የደጋ ዳሞት ሻለቃ ወደ ከተማ በመግባት በቴክኒክና ሙያ አካባቢ በተቀመጠው  የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በቁጥር ያልታወቀ ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ያለምንም መስዋትነት ቀጠናውን ለቀው ወጥተዋል  :: # አዲስ ትውልድ  # አዲስ ተስፋ  # አዲስ አስተሳሰብ

አረመኔው አሸ ባሪ ዘር አጥ* ፊ የውንብድና ሠራዊት በገነት አቦ ከተማ ሁለት የዐማራ አባላቱን ረሸነ ═══════════❁✿❁═══════════ (ታኅሣስ 15/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙ
አረመኔው   አሸ  ባሪ ዘር አጥ* ፊ    የውንብድና ሠራዊት በገነት አቦ ከተማ ሁለት የዐማራ አባላቱን ረሸነ ═══════════❁✿❁═══════════ (ታኅሣስ 15/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) በዐፋብኀ 102ኛ ኮር የ33ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድረው ቀጠና በገነት አቦ ከተማ የመሸገው አረመኔው   አሸ  ባሪ ዘር አጥ* ፊ    የውንብድና ሠራዊት በገነት አቦ ከተማ ሁለት የዐማራ አባላቱን በግፍ ረሽኗል። አገዛዙ እነዚህን ሁለት አባላት በአደባባይ የረሸነው "ከድታችሁ ፋኖን ልትቀላቀሉ አስባችኋል" በሚል ምክንያት መኾኑን የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ያሳወቁ ቢኾንም፤ ለማኅበረሰቡ ግን "በአስገድዶ መድፈር እና በዝርፊያ ወንጀል የተገኘባቸው ናቸው" በማለት ለማስተባበል ሞክረዋል። በሟቾች ሬንጀር "ደፋሪና ዘራፊ" የሚል ጽሑፍ ጽፈው ማንም እንዳያነሳቸው በመከልከል አስከሬናቸው በአደባባይ ውሏል። በመጨረሻም በአካባቢው ቅን የሀገር ሽማግሌዎች ተማፅኖ እምነታቸውን ግምት ውስጥ ያስገባ ሥርዓተ ቃብር ሊፈጸምላቸው ችሏል። ✔ በሁለት አቅጣጫ ተሰልፈን ከምንሞት በአንድ አቅጣጫ ታግለን ሞትን እንግደል‼ ✔ ሰላም ለሁሉም ፥ ሞት ለማንም‼ ✔ ዐማራዊ አንድነት ያሸንፋል‼

ለ አንድ ሽ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠነኛ ጊዜ ልንገራችሁ ውሸታችሁን እናጋልጥ ከጅምሩ የእከካሙን ብአዴን ተልዕኮ ይዞ የመጣ ካለ ወደቤቱ ወደ ብአዴን ይመለሳል ከዛ ውጭ ንፁሀን አርሶ አደሮችን መሳሪያ አ
+2
ለ አንድ ሽ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠነኛ ጊዜ ልንገራችሁ ውሸታችሁን እናጋልጥ ከጅምሩ የእከካሙን ብአዴን ተልዕኮ ይዞ የመጣ ካለ ወደቤቱ ወደ ብአዴን ይመለሳል ከዛ ውጭ ንፁሀን አርሶ አደሮችን መሳሪያ አሲዛችሁ ፎጣ አልብሳችሁ እያንገላታችሁ ፋኖነኝ በሉ እያላችሁ ፎቶ እያነሳችሁ ትለጥፋላችሁ እንጅ #ፋኖ-ለእናንተ እጅ አይሰጥም አላስለመደም ፋኖ እጅ የሚሰጠው ለሰላምታ ብቻ ነው።

በርካታ የጎጃም አካባቢዎች የአጥፍቶ ጠፊ ድሮን ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ አስፈላጊው ጥንቃቄ ይደረግ ‼️    ➡   ባሶሊበን ዙርያ    ➡   ስናን ዙርያ    ➡   ኤልያስ    ➡   መራዊ    ➡    ሰከላ    ➡   ሽንዲ ዙርያ    ➡   ቋሪት    ➡   ድርቤቴ ዙርያ ራሳችንን እና ህዝባችንን ከአጥፍቶ ጠፊ ድሮን እራሳችንንን እንጠብቅ‼️

የክፍለ ጦሩ የአሠራር እና የአደረጃጀት ተግባራት ማስተካከያ ተሰጠ ═══════════❁✿❁═══════════ (ታኅሣስ 15/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) በዐፋብኀ 102ኛ ኮር የ33ኛ ክፍለ ጦር የአሠራር እና የአደረጃጀት ተግባራት የሚመለከታቸው የድርጅቱ አመራሮች በተገኙበት ተገመገሙ። በአዲሱ የዐፋብኀ መዋቅር ግንባታ 33ኛ ክ/ጦር ውስጥ በአሠራር እና በአደረጃጀት ዙሪያ የታዩ ተግዳሮቶች በዝርዝር ተገምግመው  የመፍትሔ አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል። በዕለቱ የተገኙት የድርጅቱ አመራሮች በአዲሱ መዋቅር አስፈላጊነት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተውበታል። የቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አስተዳደር አርበኛ ኢንጂጂነር ማንችሎት እሱባለው፣ የቴዎድሮስ ዕዝ ጤና መምሪያ ሓላፊ ዶክተር እንዳላማው፣ የቴዎድሮስ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ም/አዛዥ ፶ አለቃ መኰንን ይፍሩ፣ እና የ5ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች የግምገማው ተሳታፊዎች ነበሩ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ አበጀ ጥበቡ ብርጌድ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ድቾ ቀበሌ ሻሽበር ከተማ ላይ ታላቅ ጀብዱ ፈፅማ ውላለች። የበረሀዋ ፈርጥ አፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ አበጀ ጥበቡ ብርጌድ በትናንትናው  እለት ማለትም ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም ከንጋት 12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7:00 ሰዓት ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ገዳ ኮማንዶ፣ኮሬ ነጌኛ፣ጋቻና ሲርና ፣ሚሊሻ ና ፖሊስ ጋር ባደረገችው ተጋድሎ ታላቅ ጀብድ መፈፀም ችላለች ።በተጋድሎውም 66 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ቁጥሩ ለመቁጠር የሚያዳግት ቁስለኛ በማድረግ ሶስት ምሽጎችን በማስለቀቅ ተራራ ላይ ሰቅላ ቁም ስቅሉን ስታሳየው ውላለች ።ሙሉለሙሉ ይደመስሱኛል በማለት ጭንቀት ውስጥ የገባው የሺመልስ ግብስብ በተለያዩ አቅጣጫዎች ባደረገው የድረሱልኝ ጥሪ ከቱሉጋና፣ከጊዳ አያና ከወረዳው ማለት ነው ፣ከጉትን እንድሁም ከኡኬ ና ከነቀምት ያለየለለ ኃይሉን አሟጦ ሲመጣ ወደኋላ ሲያፈገፍጉለት የፈሪ በትር ሆድ ይገትር እንድሉ የሁሌም ተግባሩ የሆነው የኦሮሙማው ስርዓት ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊቱ እንደደረሰ ቤት ማቃጠል፣ንብረት ማውደም ና በመዝረፍ በርካታ ሰዎችን በማፈናቀል ግፍ ፈፅመዋል።አሁንም የነውር መገለጫው የሆነውን ተግባሩን እሰከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ቤት በማቃጠል ላይ ነው ። ጠላት ምሽግ የተሰበረባቸው ቦታዎች 1) ስላሴ ሰፈር 2) ጎጃም ሰፈር 3) ቀበሌ 4)ረጋሳ ፎቅ ናቸው።   ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን   የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ   አበጀ ጥበቡ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ፋኖ ብርሌው ስብሀት         ታህሳስ 15/2018 ዓ/ም

እነዚህ የፋሽሽቱ ብልፅግና ቅጥረኛ ሰዎች በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል ውስጥ ለተቸገሩ ማህበረሰቦች ከመንግስት ውጭ ማንም ሰው እርዳታ እዳያደርግላይቸው በሚል ለእርዳታ በተሰማሩ ሰዎች ላይ የተቃውሞ ዘመቻ ጀምረዋል። እዚህ ላይ አንድ መረሳት የለበት ነገር አለ። እሄም ምንድነው ከአመት በፊት የኦሮምያ ክልል ፕሬዘዳንት የሆነው ሽመልስ አብዲሳ የኦምያ ክልል ብልፅግና ፓሪቲን ስብሰባ ሲመራ ከተሰብሳቢዎች ዘንድ በሰሜኑ ክፍል እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ለተነሳለት ጥያቄ እንዲህ ሲል ነበር መልስ የሰጠ፦ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ሰው ሰራሽ በሽታዎች እና አፋጣኝ እርሐብ ይኖራል ስለዚህ ያ የሰሜኑ ህዝብ በሚገጥመው በሽታም ሆነ ርሐብ ለህመሙ እና ለርሐቡ ማስታገሻ መዳኒትም ሆነ ምግብ ቢለምነን የምንሰጠው መድሀኒትም ሆነ ምግብ አይኖርም፤ የውጭ ግብረሰናይ ድርጅቶች ለመርዳት ቢፈልጉ እንኳን የኛን ፈቃድ ማግኜት አለባቸው መድሐኒትም ሆነ አልሚ ምግብ ይዞ የሚመጣ የውጭ መንግስት ቢኖር አዲስ አበባ ላይ ተቀብለን ለራሳችን እናውለዋለን እንጅ ለሰሜኑ ህዝብ በተለይም ለአማራው ነፍጠኛ የሚደርስ አንዳችም ነገር አይኖርም። በዚህ ረገድ በተያዘ የእረጅም ጊዜ እቅድ ነው ያነን ህዝብ ቁጥሩን አሽቆልቁለን ከዮም እና ከአንጋቶም ያነሰ የፖለቲካ ድርሻ እንዳይኖረው እስኪሆን ድረስ የምናሽመደምደው። ለዚህም ነው አሁን ላይ ቅጥረኞቹ እሄ እቅድ ይሳካ ዘንድ እየተረባረቡ ያለ!!

#ረሃብና_ጥሙ_ጊዜ_አይሰጥም! በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅና በእርዳታ አቅርቦት ችግር ከፍተኛ ረሃብ መከሰቱንና በመድኃኒት እጦት ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን መገንዘብ ችለናል። ችግሩ ከሰሞኑ በይፋ ይነገር እንጂ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በተመሳሳይ ኹኔታ በሰቆቃ የሚያሳልፉ በርካታ ወገኖቻችን መኖራቸው ይታወቃል። በተለይ በስደተኞች መጠለያ ያሉ፣ በድርቅ ምክንያት ማምረት ያልቻሉ፣ በአጠቃላይ ክልሉ እጅግ አውዳሚ ከኾነ ጦርነት ማግስት ውስጥ መገኘቱና መሰል ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች ችግሮች መፈጠራቸው አይቀሬ በመኾኑ ቅድመ ጥንቃቄና ሰብዓዊ ቀውሶች ሲከሰቱ አፋጣኝ መድረሻ የመፍትሔ አማራጮች ማስቀመጥና ከቁጥጥር ውጭ ከመኾናቸው በፊት መድረስ ይገባ ነበር። አኹን ላይ በተለይ ሕፃፅ በሚባለው መጠለያ ጣቢያ ያሉ ዜጎች በረሃብና መድኃኒት እጦት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው በመኾኑ መላው ኢትዮጵያውያን ተረባርበው የዕለት ጉርሳቸውንና በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ኹኔታ መፍጠር የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ኾኖ አግኝተነዋል።  በትግራይ ያለውን እጅግ የባሰበትና ጊዜ የማይሰጠውን ኹኔታ አነሳን እንጂ ችግሩ በአማራ ክልል ባሉ እንደ ደብረ ብርሃን፣ ጃራ፣... መጠለያ ያሉ ወገኖቻችን በመኖርና በመሞት መሐል ኾነው ቀናቸውን እንደሚገፉ ይታወቃል። ስለኾነም፣ 1. በውጭም በውስጥም ያሉ ኢትዮጵያውያን በሚቻለው አቅም ኹሉ ተረባርቦ በረሃብና መድኃኒት እጦት የሚሰቃዩ ወገኖቻችንን እንዲታደጋቸው፣ በዘላቂነትም እንዲያቋቁማቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።  2. ዓለምአቀፍና ረጂ ተቋማት ለእነዚኽ በከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ላሉ ዜጎች አፋጣኝ እርዳታና ዘላቂ መቋቋሚያ ፕሮጀክቶችን እንዲተገብሩ ተማጽኗችንን እናቀርባለን። 3. የፌዴራል መንግሥትና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እነዚኽን ወገኖች የፖለቲካ ቁማር መያዣ ከማድረግ እንዲቆጠቡ፣ እርዳታዎችን በቀናነት እንዲያሳልጡ እንዲኹም ወደዳግም ግጭት ከሚገፋ አባባሽ ምክንያቶች እንዲቆጠቡ በአደራ ጭምር እናሳስባለን። በመጨረሻም እናት ፓርቲ ለእነዚኽ በሰቆቃ ላሉ ወግኖቻችን ለመድረስ በሚደረገው ርብርብ ከዚኽ ቀደም ስናደርግ እንደቆየነው የድርሻችንን እንደምንወጣ ለማሳወቅ እንወዳለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ ታኅሣስ ፲፭ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ