ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 416
Subscribers
+1224 hours
+287 days
+1 15930 days
Posts Archive
+4
#ህዝባችንን በእያንዳንዱ ሰሀት ውይይታችን ይቀጥላ!!!
አ ፋ ብ ሀ ምዕራብ አማራ ቀጠና 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አባኮስትር ብርጌድ 4ኛ ሻለቃ የቀሸምሽ ቀበሌ ማህበረሰብ ሙሉ ውይይት እያደረገ ይገኛል።
በስብሰባው የአባ ኮስትር ብርጌድ አመራሮች
የሻለቃ አመራሮች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣የግዜዊ አስተዳደር፣ ፍትህ አካላት በተገኙበት በወቅታዊ ሁኔታዋች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
ህዝባችን ከፋኖ ጎን ሁኖ ትግሉን እያጦጧፈው ይገኛል ፋኖ ከህዝቡ ጎን ሁኖ የተለያዩ የማህበረሰባችንን ችግሮች በመዋቅር አዋቅሮ አገልግሎት እየሰጠ ነው በማለት ማህበረሰባችን በድጋፍ እደማይለየን ምስክርነቱን አስቀምጧል።
የህዝባችንን ውይይት ይቀጥላል................
29/01/2018
Amare bamlaku
አባ ኮስትር ብርጌድ ህ/ግንኙነት
+1
ስርዓታዊ ቂልነት!
አረመኒያዊ አገዛዙ እንደ ሕዝብ ያመጣብንን መከራ "በኛ ያልፋል እንጅ መች ለማንም ይተርፋል"!!!በሚል ውስጣዊ ስሜት ከአማራ አልፎ ለሶማሊያ፣አፋር፣ትግራይ፣ቢሻንጉል ጉሙዝ፣ደቡብ፣ ኦሮሞ...ሕዝብ እንዳይሸጋገር በአጠቃላይ የመከራ ድግሱ በኛ እንዲያከትም ብሎ ሲፋለም የሚውል ፋኖ ጭራሹን ከራሱ መዋቅራዊ ክፍል ያንዱን ቀጠና ትቶ ሂዶ አንዱን ሲያጠቃ ዝምብሎ ይቀመጣል ብሎ ማመኑን ሳይ ድድብናቸው ዳርቻ እንደሌለው ተረዳሁ።
ማንም ሰው ከአከላዊ ክፍሉ ውስጥ አንዱን ካንዱ አበላልጦ ለጉዳት አሳልፎ የሚሰጥ የለም!!!የትም አትሄዳትም ትወቀጣታለህ!!!
እሸቱ ጌትነት በላይ
አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር በ2 የውጊያ ቀጠናዎች የጠላትን ኃይል ሙትና ቁስለኛ አድርጓል።
መስከረም 28/2018 ዓ.ም የጠላት ኃይል ከባህር ዳር ወደ ጎንደር በመጓዝ ላይ እያለ አርኖ ጋርኖ የተባለ ቦታ አፋብኃ በላይ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ጥቁር አምበሳ ክ/ጦርና ፋናየ ውቤ ክ/ጦር አሃዶች በጥምረት ቦታ ይዘው በሰነዘሩት ማጥቃት ድል ተቀዳጅተዋል።
ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታዎች ቀድሞ በመቆጣጠር የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሲሆን አንድ ወታደራዊ ኦራል ከጥቅም ውጭ ሁኗል።
ከአርኖ ጋርኖ መብረቃዊ ጥቃት የተረፈው የጠላት ኃይል ከማክሰኝት በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኘው ፈረንጅ ውሃ ከተባለው ቦታ ሸሽቶ እንደደረሰ ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ንስር ብርጌድ በደፈጣ በድጋሜ ተመቶ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ቀሪው ሸሽቶ ምሽት 3:00 ሰዓት ማክሰኝት ከተማ ምሽግ ተወሽቋል።
በሁለቱም አውደ ውጊያዎች የተገኙ ድሎች
15 የሞተ 23 ቁስለኛ ሁኗል።
ቁስለኞቹ በማክሰኝትና በጎንደር ህክምና ለማግኘት መግባታቸው ተረጋግጧል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መስከረም 29/2018 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
የበረሃው አናብስት ዛምበርሃ ብርጌድ የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር ዛምበርሃ ብርጌድ መስከረም 28/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ደጀን ወረዳ ጉብያ ከተማ በመግባት የጠላትን ሀይል ላይ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።
በደጀን ወረዳ ጉብያ ከተማ ከምሽቱ 1:30 ድርስ በቆየ ውጊያ በአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደረሶል።በዛምበረሃ ብርጌድ የተደቆሰው የአገዛዙ አረመኔው ሰራዊት አዳሩን ዙ23 ፔንፔ ሲተኩስ አድሯል።
አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!
መስከረም 29/2018 ዓ.ም
ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
የበረሃው አናብስት ዛምበርሃ ብርጌድ የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለጦር ዛምበርሃ ብርጌድ መስከረም 28/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ደጀን ወረዳ ጉብያ ከተማ በመግባት የጠላትን ሀይል ላይ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።
በደጀን ወረዳ ጉብያ ከተማ ከምሽቱ 1:30 ድርስ በቆየ ውጊያ በአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደረሶል።በዛምበረሃ ብርጌድ የተደቆሰው የአገዛዙ አረመኔው ሰራዊት አዳሩን ዙ23 ፔንፔ ሲተኩስ አድሯል።
የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
"የአምባሰል ማር ቆራጭ ሲሄድ አጎንብሶ
ሲመለስ ቀጥ ይላል የልቡን አድርሶ"
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስር የልጅ እያሱ ኮር አዛዡ አርበኛ ሰለሞን አሊ!
ድል ለሰፊው የአማራ ሕዝብ!
ድል ለፋኖ!
[ የጥንቃቄ መረጃ ]
ልጅ እያሱ ኮር ዝግጁ ሁን ወራሪዉ ከአፋር ተነስቶ ገንቦ በር ደርሷል።
ጉዞአቸዉ ወደ መርሳ ነዉ ..!
ቤተ ዓምሓራ !💪
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#የጠላት_እንቅስቃሴ_መረጃ‼️
70 መኪያና የሚጠጋ የአጋዛዙ ኃይልና ሬሽን ከኩታበር ወደ ግሸን ከ5 :10 ጀምሮ ተንቀሳቅሷል‼️
29/ዐ1/2018 ዓ.ም
ሆዳንሽ ፣ ጅጋ ጠላት ለመግባት ቢሞክርም ተረግጦ ተመልሷል ።
እንዲሁም ማክሰኞ ማታ መረጃ ጥሎ ላለመሄድ ሲል ተቋማትን አቃጠለ
--------------------------------------
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ፭ኛ ክፍለጦር
አረንዛው ዳሞት ብርጌድ
⚔️⚔️⚔️⚔️⚔️⚔️⚔️⚔️⚔️
በምዕ/ጎጃም ዞን ውስጥ ከሚገኙ ከተሞች ውስጥ የዞኑ ከተማ ፍ/ሰላም በ3 እና በ7 km ርቀት የሚገኙት የሆዳንሽ ቀበሌንና የጅጋ ከተማ አስተዳድርን ለማስለቀቅ ጠላት ያለ የሌለ ኃይሉን ሰብስቦ የመጣ ቢሆንም ሆዳንሽ ልዩ ስሙ ጠሚም ሚባል ቦታ ላይ ከባድ መሳሪያ ጭኖ ቢመጣም 3 መትና ከ11 በላይ ቁስለኛ ይዞ በሩጫ ተመልሷል ።
ነገር ግን ሞኝ ቢያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር እንደሚባለው ማፈሪያ የሌለው ምሊሻ ፍ/ሰላም እየሮጠ ገብቶ መጨፈሩ ሕብረተሰቡን ሲያስገርም አምሽቷል ። በተለይም አገዛዙ ጥሎ ሲፈረጥጥ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን አቃጥሎ ወጥቷል ።
አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት
ፍሥሓ አደራው
ድል ለአማራ ፋኖ !!!
ድል ለአማራ ሕዝብ !!!
ኦህዴድ መሩ የብልፅግና ቡድን ልጆቻቸውን አስገድዶ ወደ ውትድርና ወስዶ ላስገደለባቸው እናቶች ክብር ስንል ቀሪውን ምስል ለጊዜው ትተነዋል።
ከላይ ያያችሁት ምስል በጋሼና ግምባር ትናንት መስከረም 27/2018 ዓ/ም እና ዛሬ መስከረም 28/2018 ዓ/ም በአንሻ ሰይድ ክፍለ ጦር ብቻ ከተገደሉ የአገዛዙ ወታደሮች መካከል እጅግ በጣም ጥቂቱንና አሰሰቃቂ ያልሆኑ ያልናቸውን ምስሎሎች ነው።
አገዛዙ በግዳጅ ውትድርና አስገብቶ ትውልዱን ምን ያህል እንዳስጨረሰው ትረዳላችሁ።
በተለይ ደግሞ የደቡብ እና የኦሮሞ እናቶች ፈጣሪ ያፅናችሁ። ምንም በማታውቁት ልጆቻችሁን ከጉያችሁ ተነጥቃችሁ የአሞራ ሲሳይ ሆነው ቀሩባችሁ።
ይህ እንዳይሆን ነበር ፋኖ አስቀድሞ እጃችሁን ስጡ እያሉ ለአገዛዙ ወታደር ጥሪ ሲያቀርብ የነበረው። የሆነው ሆኗል። የቀራችሁት እራሳችሁን አድኑ።
+2
አባ ረፍርፍ ኮማንዶ ፻/አ ማናዬ መኮነንን‼️
አባ ረፍርፍ መቶ ዓለቃ ማናዬ መኮንን 30 የጠላት ሃይልን አጋድሞ በቀሪዋ 1 ጥይት ራሱን ሰዉቷል።
፻/አ ማናዬ መኮነንን በቀን 28/01/2018 ዓ/ም ከአረመኔዉ አገዛዝ ጋር ፊት ለፊት በመዋጋት 30 የአመኔዉ አገዛዝን ዶጋ አመድ አድርጎ ራሱን ለወጣለት ለሰፊዉ የአማራ ህዝብ ታምኖ ራሱን ሰዉቷል።
ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን‼️
#የፋሽስቲ ብልፅግና እንዘጭ አንቦጭ ተጀምሯል‼️
"ሊወጉኝ ነው…" ብልፅግና
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመንግሥታቱ ድርጅት በፃፈው ደብዳቤ የኤርትራ መንግሥት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) "ጽምዶ" በሚል ጥምረት ኢትዮጵያ ላይ "ጦርነት ለመክፈት" እየሰሩ ነው ሲል ከሰሰ። ሚኒስቴሩ ለተባበሩት መንግሥታት በፃፈው ደብዳቤ ሁለቱ አካላት በቅርቡ የፋኖ ታጣቂዎች በሰሜን ወሎ ዞን የምትገኘውን ወልዲያን ከተማ ለመቆጣጣር ባደረጉት ሙከራ ውስጥ እነዚህ ኃይሎች በአማካሪነት ተሳትፈዋል ሲል ወንጅሏቸዋል።
BBC
የዘመነ ትውልድ ለድል የተኳለ ነውና አሸንፈናል፥እናሸንፋለን‼️
በዓለም ህዝብ ታሪክ ውስጥ ህዝብ እንደ ህዝብ መከራ ውስጥ ሲወድቅ፣ጭቆና ፣ብዝበዛ እንዲሁም የህልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ ትውልዱን አስተባብሮ ከገጠመው የህልውና አደጋ፣ብዝበዛና ጭቆና የሚያወጣ አብዮታዊ መሪ ያስነሳል።
ኔልሰን ማንዴላ ለደቡብ አፍሪካ፣ ማህተመ ጋንዲን ለህንድ ፣ ኩዋሚ ኑኩሩማ ለጋና፣ቶማስ ሳንካራ ለቡርኪና አፋሶ፣ሳሞራ ሚሸል ለሞዛንቢክ ወዘተ አስነስቶ ፀረ ኮሌናሊዝም፣ጭቆና እና ብዝበዛን ለማስቆም ህዝባቸውን አስተባብረው ለድል የበቁ መሪዎች መካከል የሚጠቀሱ ጥቂቶች ናቸው ።
በታላቁ መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥም ነብዩ ሙሴ በፈርኦን ጭቆና ውስጥ የነበሩትን የእስራኤል ህዝቦች ነፃ ያወጣ ዘንድ ፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከንአን ያስገባቸው ዘንድ ከአምላኩ ፥ከአምላካችን የመሪነት ሚና የተሰጠው ነብይ ነበር ።
በእኛ ዘመንም የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ህዝባችንን አንቅቶ፣አደራጅቶ እና አስታጥቆ ህልውናችንን ለማረጋገጥ ለምናደርገው አብዮታዊ ትግል የመሪነት ሚናውን በአስተማማኝ ሁኔታ እየተወጡ ካሉ መሪዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው አርበኛ ዘመነ ካሴ ነው ።መሪያችንና ምልክታችን አርበኛ ዘመነ ካሴ አዲሱን ትውልድ በአዲስ አስተሳሰብ እና ተስፋ ከድል ማማ ላይ ይደርስ ዘንድ ሌት ተቀን የመሪነት ሚናውን በብቃት እየተወጣ ይገኛል ።
እኔም የዚህ ትውልድ አካል ፤የዘመነ ትውልድ በመሆኔ እድለኛ ነኝ።ላንጨርስ የጀመርነው የአማራ ህዝብ ትግል የለም ።
የእኛ ትውልድ ለመከራ ሳይሆን ለድል የተኳለ ነውና አሸንፈናል ፥ እናሸንፋለን።
ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!!
Hailemichael Bayeh
[ አፋብኃ ]??
ጠላት ትኩረቱ ወሎ/ቤተ ዐማራ/ላይ አድርጓል። በዚህ ሶስት ቀን ብቻ ከተነገረን መረጃ በአንፃራዊነት 400 ገደማ መኪና የጠላት ሰራዊት ደሴ እና ሃራ ወልዲያ ተራግፏል!!የአፋብኃ ሌሎች ዕዞች ምን እያሰባችሁ ነው??የቀጠና ውጊያ ይቁም!!
አርበኛ አሸናፊ ገናን !
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የጥንቃቄ መልእክት#
አገዛዙ የመጨረሻ ኦፕሬሽን ያለውን የጥቅምት ወር ዘመቻ ፋኖ ያለበትን ቦታ (ማዘዣ ጣቢያ) ላይ በሌሊት #ከበባ በመፈፀም ለመደምሰስ ስላሰበና እየሞከረውም ስለሆነ የአማራ ፋኖ መረጃችሁን (ደህንነታችሁን) እንዲሁም #ዋርድያችሁን በማጠናከር ራሳችሁን ከጥቃት እንድትከላከሉ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን በአራቱም የፈኖ ቀጠናዎች‼️
29/ዐ1/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘራያቆብ አንደኛ ኮር የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ከአውደ ውጊ ጎን ለጎን የገበሬውን ሰብል በመሰብሰብ ትልቅ ስራ ሰርተዋል!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘራያቆብ አንደኛ ኮር በስሩ ከሚገኙት ግዙፉ ክፍለ ጦርች ውስጥ አንዱ የሆነው የዐፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር ነው ፋኖ የህዝብ ልጅ ነው ስንል በምክንያት ስለሆነም ነው እንደሚታወቀው ከመስከረም ጀምሮ ገበሬው የአመቱን ሰብል የሚሰበስብበት ወቅትም ነው።
የዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር በማጀቴ ዙሪያ በታች ጨፋ በኦሮሞ ልዩ ዞን የሚያስተዳድሩት የኦሮሞ ሚኒሻዎችና የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሚኒሻዎች የተቆጣጠሩት ቦታ በመሆኑ የአማራን ማህብረሰብ ሰብል በሚሰበሰቡበት ወቅት በእየቀኑ በአማራው ገበሬው ላይ ዲሽቃና ብሬን በመጥመድ እየተኮሱ አላሰበሰሰብ በማለት ያስቸገሩ መሆናቸውን የሰሙ የዐፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር አናብስቶች ዛሬ ወደ እዚህ ቀጠና በመግባት ከአውደ ውጊያ ጎን ለጎን የገበሬውን የአመቱን ሰብል በሰላም እንዲሰበሰቡ አድርገዋል።
በመሆኑም በማጀቴ ዙሪያ ያሉት ገበሬዎችም በሰላም ሰብላችን በመሰብሰባችሁ ተደስተው ፍኖ ማለት እኛ ነን። በልጆቻችን ዛሬ ኮርተናልናለ በርቱልን ፈጣሪ ይጠብቃችሁ በማለት አመስግነውን በሰላም ወደ ስራችን ተመልሰናል ሲል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘራያቆብ ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ መረጃውን አድርሶናል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘራያቆብ አንደኛ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር
መስከረም 28/01/2018 ዓ.ም
+2
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ አራተኛ ደጃዝማች ኮር በመተማ ሽመለ ጋራ ድል ተቀዳጅቷል።
ዝርዝር መረጃዉን እንመለስበታለን!!
#አስቸኳይ_የድሮን_ቅኝት_መረጃ‼️
ከለሊቱ 10:13
የድሮን ቅኝት በሀብሩ ወረዳ ጎንደር መተማ በጎጃም ደጋ ዳሞት ባህርዳር ወረኡሉ በመርሳና አካባቢዉን ጨምርሮ 29/1/2018 ዓ/ም አጥቢያ ከለሊቱ 10:10 ጀመሮ ቅኝት እየተደረገ ነዉ መረጃዉ ይድረስ ዘንድ ሸርና ጆይን አድርጉ ለአናብስቶች ‼️
27/ዐ1/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
"በጋሸና ካሉ ሦስት ምሽጎች ሁለቱ ተሰብረዋል!" አርበኛ አበበ ፈንታውን
መስከረም 28 ቀን 2018 ዓም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በሁሉም ቀጠናዎች ጠንካራ ታጋድሎ እያደረገ መሆኑን የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የሕዝብ ግንኙንተ ኃላፊ አርበኛ አበበ ፈንታውን አስታወቀ።
በሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ ኮር አሐድ የሆኑ ክፍለ ጦሮች ወደ ተቆጣጠሯቸው ከተሞች ከፍተኛ ኃይል አሰልፎ ጠላት ለማጥቃት መሞከሩን ፤ ይህን ጦር በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት ወደ መጣበት በመመለስ አስደናቂ ጀብድ መፈፀሙን አርበኛው በማብራሪያው አክሏል።
ሰሞኑን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝም የዞንና የወረዳ ከተሞችን እየተቆጣጠረ ያለበት ሁኔታ መኖሩን በመግለፅ አዲስ አለም ከተማን ለመውረር ከጅጋና ከደንበጫ ከተማ በብረት ለበስ በዙ 23 እና በከባባድ መሳሪያዎች ታጅቦ የመጣን የጠላት ኃይል በመከላከልና መልሶ በማጥቃት ተቀጥቅጦ መመለሱንም አስታውቋል።
በምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝም በአርበኛ አደም አሊ የታወጀው ዘመቻ መቀጠሉንና የዞን ከተሞችን ፤ የወረዳ ከተሞችንና በርካታ የሚባሉ ወታደራዊ ገዢ መሬቶችን በሰሜን ወሎ፣ደቡብ ወሎና ምዕራብ ወሎ አጠቃላይ ቤተ አምሐራ ቀጠና መቆጣጠር መቻሉን ገልጿል።
ሙጃ ገዢ የሚባል የአገዛዙ የዘመቻ ስምሪታቸው ማዘዣና በርካታ ቀጠናዎችን አስተሳስረው ይመሩበት የነበረ ቦታ ነበር ያለው አርበኛው እሱን በመቆጣጠራችን ነው ጠላት እንዲፍረከረክ ያደረግነው ሲል አስታውቋል።
ሌላኛው ጣላት የተሰባሰበበት ገዢ መሬት ጋሸና መሆኑንና ይኽም ስትራቴጂክ ቦታ ወደ ተለያየ አቀጣጫ የሚወስድ የዘመቻ ስምሪት መነሻ መሆኑንና በዚህም ካሉት ሦስት ምሽጎች ሁለቱን ምሽጎች በመስበር ከተማዋን በከፊል የተቆጣጠርንበት ሀኔታ ላይ ነን ያለ ሲሆን በቀጣይም ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ወታደራዊ የበላይነት መኖሩን አስታውቋል።
በጋሸና ሁለቱ ምሽጎች ሲሰበሩ በየመጠጥ ቤቱ ተቀምጦ የነበረ ስነ ልቡናው የተሰለበ ሰራዊት መሳሪያውን እየጣለ ሲሸሽ የነበረበት ሁኔታን መታዘቡን የገለፀው አርበኛው በእግረኛ ያጣውን ድል የመጨረሻ አቅሙን በመጠቀም ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ፤ ነገር ግን የፋኖ ኃይል ከፍትኛ ጥንቃቄ ስለሚያደርግ ጉዳት እንዳልደረሰበትና በዘፈቀደ የሚጣለው ድሮን ንፁኃንን እንደጎዳ ገልጿል።
አክሎም አርበኛው ሚኒሻ ፣ አድማ ብተና ፣ ፖሊስና ሆድ አደር ባንዳዎች ውጊያውን አበላሻችሁ በሚል ተረሽነዋል እርስ በእርስ በመጠራጠር ያሉ ናቸው በዚህም በቅርቡ በርካታ የቤተ አማራ አካባቢዎች ነጻ የሚወጡበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመዋል።
ከወልድያ እስከ ሐይቅ ጃሪ ፤ ከወልድያ ወደ ባሕር ዳር መስመር እስከ ጋሸና ያሉ ዋና መስመሮች በምስራቅ አማራ ምንሊክ ዕዝ መያዛቸውን፤ ከጋሽና በኋላ ያሉትን ደሞ በሰሜን አማራ ቀጠና በበላይ ዘለቀ ዕዝ መያዙን በመግለፅ አጠቃላይ አማራ ክልል የገባው ኃይል ባሕር እንደገባ ይቁጠረው ሲል አርበኛው ገልጿል።
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የሕዝብ ግንኙንተ ኃላፊ አርበኛ አበበ ፈንታውን ማብራሪያ ሊንኩን በመጫን ማግኘት ይችላሉ...
