ዛታ ሚዲያ (Zata Media D$A )
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 057
Subscribers
+6824 hours
+3957 days
+1 39230 days
Posts Archive
ድርድርን እንደ ተስቦ
*****
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ የሚታገለው ለስር -ነቀል ለውጥ እንጅ በዘር ማጥፋት ወንጀል ለፍርድ ከሚቀረብው የብልፅግና ስርዓት ጋር ለመደራደር አይደለም!!
የአማራ ህዝብ የገጠመውን ብሔራዊ የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በምናደርገው ትግል ውስጥ የድርድር ነገር አይታሰብም!!
ድርድር የምናደርገው ከኢትዮጲያ ህዝብ ጋር ብቻ ነው።
ከዘር አጥፊ ስርዓት ጋር ለድርድር መቅረብ ሺንፈት፣ራስ ወዳድነት፣ገባሪነት እና ስቀቀናምነት ነው።
ባንዳነትን እና ገባሪነትን የሚፀየፈው የአማራ ህዝብ ትግል በድል የሚጠናቀቅ እንጅ" ድርድር" በሚባል ወረርሺኝ የሚቀለበስ ትግል አልጀመርንም!!
አፋብን ለስርዓት ለውጥ የሚታገል የአማራ ህዝብ ድርጅት ነው።
ነገር ግን አፋብንን እንደ አብን እና እንደ መአህድ ከፅንሱ ለማፍረስ መሞከር በፍፁም አይታሰብም!!
የአማራን ህዝብ ትግል እየሻሻጡ አረበኝነት ስላቅ ነው።
#አርበኝነት በተግባር ታግሎ በማሸነፍ የህዝባችን የቀደሙ ጥያቄዎች በክብር መመለስ እንጅ በስናዳሪነት እና በተደራዳሪነት መንፈስ ለአማራ ህዝብ እየታገልኩኝ ነው ማለት ቀልድ ነው።
ስለዚህ የአማራ ፋኖ ትግል እስከ ቀራንዮ ድረስ መሆኑ የተረጋገጠ ነው።
መንገድ ላይ በቁስ፣በስልጣን እና በአሻጥር መንገዳገድ በጠላትነት ያስፈርጃል!!
ግልፅ ጠላትነት መሆኑም ሊታወቅ ይገባል!!
አፋብን ደም የተገበረበት ድርጅት እንጅ ሱፍ እና ከረባት ለባሾች የመሰረቱት ፓርቲ አይደለም!!
ደም የገበርንበትን እና አጥንት የከሰከስንበትን ድርጅት በአመራር ስም ለማሻሻጥ ደለላ ሆኖ ለመቅረብም መንገድ ማመቻቼት በፍፁም ወንጀል ነው።
ትግላችን ፀረ-ህዝብ የሆነውን የብልፅግናን ስርዓት በመንቀል በምትኩ አድስ ስርዓት መትከል ነው።
ከዚህ ውጭ በአማራ ህዝብ እና በልጆቹ ትግል ስም የተጀመረውን አብዮት አሳልፎ ለመስጠት የሚንገዳገድ ቡድን ካለ በፍፁም ተቀባይነት የለውም።
ርባና ቢስ ሃሳብም ነው!!
በዓለም ላይ በፈፅሞ ዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ የነበሩ ስርዓቶች ሁሉ ለህግ እና ለፍትህ ቀርበዋል። በአማራ ህዝብ ላይ ፈፅሞ ዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው ስርዓትም ለፍርድ እስኪቀርብ ድረስ እንታገላለን!!
የአማራ ህዝብ ትግል በድርድር የሚመለስ ጥያቄ የለውም!!
ስለዚህ ደም የተገበረበትን ትግል ልክ እንደ 1983 እና 2010 ትግሉን ለጥገናዊ ለውጥ ማመቻቼት መሞከር የጥቁር ክህደት ጅማሮ ነው።
በዓለማችን ታሪክ የህልውና ትግል ከገጠማቸው አይሁዶች፣ሩዋንዳውያን መማር የሚቻለው ነገር ቢኖር ትግላቸውን በአሸናፊነት አጠናቀው ዘር አጥፊዎችን ለፍርድ ማቅረባቸውን ታሪክ ይናገራል።
ስለዚህ በድርድር ስም ትግሉን ለመጥለፍ አደናጋሪ ሃሳብ እና ህዝብን ባልተገባ መንገድ ለማሳሳት መሞከር በፍፁም ነውረኝነት ነው።
የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል በተወሰኑ ቡድኖች ሃላፊነት ብቻ የሚዘወር አይደለም!!
የትግላችን ዕጣ ፋንታ ጫካ ያለው ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት የሆነ ሁሉ ሃላፊነት አለበት!!
ሁኔታው "ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ" ሆነ እንጅ አፋብን በአሁኑ ስዓት ስለ አጠቃላይ የትግሉ ሁኔታ እና ቀሪ ስራዎች ስለማስተካከል ትኩረት ሰጥቶ መስራትን እንጅ ድርድርን አስመልክቶ በሚዲያ ቀርቦ አስተያየት መስጠት ጊዜው አይደለም!!
አፋብን እንደ ድርጅት ሰራዊት ማዋሃድ፣ጠንካራ ድፕሎማሲ መስራት፣ጠንካራ ዘመቻዎችን ማቀድ፣ስትራቴጅካዊ ስራዎችን ማሰብ፣የፓለቲካ ፕሮግራም እና ማንፌስቶ ማዘጋጀት እንድሁም ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ዓላማዎችን በመለየት ድርጅቱ እግር እንድትክል ማድረግ እንጅ የድርድር አጀንዳን በዓለም አቀፍ ማዲያ ቀርቦ ማስተጋባቱ አንድምታው ድርጅታዊ ጥርጣሬን መፍጠር ነው።
ይሄ ዓይነት ልምምድ ከመርህ አንፃር ተቀባይነት የለውም። የብዙሃኑን ፍላጎትን ጭምር ያላከበረ ነው።
ስለሆነም በድርጅታችን ውስጥ በህዝብ ግንኙነትም መምሪያውም ይሁን በድርጅቱ ዋና ዋና አመራሮች የሚተላለፉ ቃለ ምልልሶች በድርጅታችን መተዳደሪያ ደንብ ተግባር እና ሃላፊነታቸው ብቻ ስለሚፈቅድላቸው ድርጅታዊ ጥሰት መፈፀም ተቀባይነት የለውም።
የህዝብ ትግል አይሸጥም ፤አይለወጥም!!
ትግላችን የአሸናፊነት ትርክትን በማንበር ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በመሆን አድስ ስርዓት የመትከል እንጅ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፈፀመ ስርዓት ጋር በሚደረግ ድርድር የሚመለስ የህዝብ ጥያቄ የለንም!!
ሰራዊት እና ህዝባችንም የድርድር ወረርሺኝን በሚያስተላልፉ አካላት ላይ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።
በአማራ ህዝብ ትግል እና በህዝባችን ጥያቄዎች ላይ ተላልፈው የተገኙትን ሁሉ ልክ እንደ ብልፅግናው ስርዓት በይፋ የምንታገላቸው ይሆናል።
በአበው ብሂል "ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት" እንደሚባለው ሆኖ እውነትን፣ሃቅን፣ፍትህን እና የወጣንበትን የትግል ዓላማ በመጠምዘዝ ትግላችን ከሃዲዱ እንዲወጣ አድስ ትርክት ለማንበር መሞከር ታሪካዊ ጠላትነት መሆኑንም ለማስገንዘብ እንወዳለን!!
ክቡር ለተሰውት
ድል ለአማራ ህዝብ
በመተማ መስመር ታይተዋል እያሉ፡
ጎንደር ፋሲለደስ ታይተዋል እያሉ፡
ምንነው ወደ ወሎ ባልመጡብን አሉ፡
የእነ አፄዎቹ ዘር የኛ የወርቅ አምባር ፡
ምን አለ አገራችን ምንስ አለ ጎንደር፡
አባይን አቋርጠህ በድል ስትሻገር፡
የእነ አፄወቹ ዘር ሄደ ገሰገሰ ፡
ያነን የሾህ አጥር እየደመሰሰ፡
በወሎ ምድር ላይ ደሙን አፈሰሰ፡
እየተባባልን በቀን 19 /4/2018 ዓ ም እኔ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀነራል አሳምነው ፅጌ አኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉየ እና ወንድሜ ታማኙ የዘመናችን ጀግና እና የልጅ አዋቂው የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ፣ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባት ኮር ዋና አዛዥ ፋኖ አመኑ አለማንተ አንድ ላይ ተገናኝተን ወንድም አማችነትን እና ወንድማዊ አንድነትን ጥብቅ ትስስር በሚል መሪ ቃል ላይ ውይይት እያደረግን ባለንበት ቦታ የአማራ ህዝብ ቋሚ ጠላት የሆነው ብልፅግና ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ ከቡግና ወረዳ ወደ ብርኮ የሚባል ቦታ እንቅስቃሴ ያደርገ ቢሆንም በወሎ አናብስቶች እና በጎንደር ጀግኖች ተመክቶ ሊያፍን የመጣው ታፍኖ ብርኮ በተባለ ቦታ አብዛኛው ጠላት የያዘውን ተቀብለን ላይመለስ እስከዛኛው ሽኝተነዋል፡፡
ከጧት 4፡00-10:00 ሳዓት ድርስ በወሰደው አውደ ውጊያ ጠላት የሰው ሁይሉን በጣም ያጣበት፣ በርካታ ክላሽ ፣ ብሬን እና ተተኳሹን እንዲሁም የክፍለ ጦር የሰው ሀይል አመራር ተመቶ የማርክንበት እና ቅስሙን የሰበርንበት የተቀናጀ የሁለቱ ኮሮች የቅንጅት ውጊያ ያደረግንበት ነበር፡፡
እኛ የላስታ አናብስቶች እና የጎንደር አንበሶች በወሎ ምድር ላይ ያሳየነው ተጋድሎ በወሎ ሰማይ ስር ብዙ አሳምነው በጎንደር ብዙ ቴወድሮስ እንዳለ ያሳየንበት ድንቅ የውጊያ ጥበብ በየልምዳችን ተጠቅመን ጠላትን አንገት ያስደፋንበት ውጊያ ነበር፡፡
በዚህ ውጊያ ጠላትን ያከሰርንበት እኛ ያተርፍንበት እና የተማርንበት ወንድሜ አርበኛ አመኑ እና ያሉ የሰራዊት አባላትን ከኛ ከጀነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጋር በጥብቅ ያስተሳሰርንበት ነው፡፡
በነበርው አውደ ውጊያ የሁለቱ ኮሮች ቅንጅታዊ ውጊያ ስመለከት አማራ አሁንም በርካታ አሳምነው እና ቴዎድሮሶች እንዳሉ እና ትግላችን አጠናቀን የህዝብ ጠላት የሆነው ብልፅግና የምንቀብርበት ሰአዓት እሩቅ እንዳልሆነ ተርድቻለው፡፡
የተማርኩት እና የተርደውት አንድነት የሁሉም አሸናፊ እንደሆነ ነው፡፡ በነበርው ውጊያ ጠላትን አከርካሪውን የመታነው በአንድ አላማ በአንድ ልብ አንድን ቋሚ ጠላት ላይ ተናበን ሰለነበር ነው፡፡
ባጠቃላይ በአማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋን ልንመክተው የምንችለው ፣ ስራቱንም ማሸነፍ የሚቻለው አንድ ሁነን ስንቆም ብቻ እንደሆነ ተምረንበታል።
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ላስታ ጀነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ምክትል አዛዥ
አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉየ !!!
በምዕራብ ወሎ ግንባር ጠላት ይተማመንበት የነበረው ከባድ ምሽግ ተሰበረ!!
ትናንት ለዛሬ ሌሊት ማለትም ጥር 17 ለ 18 መካነሰላም ከተማ ውስጥ በተሰራ ኦፕሬሽን የጠላት ኃይል ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። ከአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሁለት ክፍለ ጦሮች ማለትም ከኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር እና ከመብረቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አሃዶች መካነሰላም ከተማ ውስጥ የመሸገው ጠላት ይተማመንበት የነበረውን ከባድ ምሽግ ሌሊቱን ሰብረውታል። የጨላማ ውጊያ በመሆኑ የተነሳ በጠላት በኩል የደረሰውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ለማረጋገጥ ባንችልም የጠላት አከርካሪ እንደተሰበረ ለመረዳት ችለናል።
የምዕራብ ወሎዋ መካነሰላም ከተማን አስከብራለሁ በሚል እሳቤ ጠላት በርካታ ኃይል ከተማይቱ ውስጥ ቢያሰፍርም ፋኖ እንቅልፍ ነስቶታል፤ በመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሶዬ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ኔትወርኩ ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ላይ መሽጎ የነበረው ጠላት ነው በእነ ሞት አይፈሬ ሌሊቱን ተኩስ ተከፍቶበት ወታደራዊ ቁሳቁሱን ጭምር ጥሎ የፈረጠጠው።
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር አካል የሆነው 43ተኛ ክፍለ ጦር በኮሎኔል ዮሀንሥ እየተመራ በርካታ ኃይሉን ወደ መካነሰላም ከተማ አስገብቶ ስለነበር ይህን የጠላት ግሳንግስ ሰራዊት የሚካኤል አሊ ልጆች በጥይት ሲያበጥሩት አድረዋል። በሌሊቱ ኦፕሬሽን ሰራዊታችን መካነሰላም ከተማ ውስጥ የገባ ሲሆን ለትግሉ አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን እና ሌሎች ግብአቶችን ከጠላት ጊዜያዊ ካምፕ ማውጣት ችሏል::
በ4 አቅጣጫ በተደረገው የሌሊቱ ኦፕሬሽን ጠላት ይዞታውን ላለመልቀቅ የመጨረሻ አቅሙን የተጠቀመ ቢሆንም ሰራዊታችን በአየር ማረፊያ እና በሶዬ በኩል ያለውን ምሽግ በመስበሩ የተነሳ አብዛኛው የጠላት ኃይል ወደ ደሴ መስመር መጓዙ ታውቋል። በኮሎኔል ዮሀንስ የሚመራው ኃይል አቅም ስላነሰው በሚል በዛሬው ዕለት በርከት ያለ ተሽከርካሪ ወደ መካነሰላም እየተጓዘ መሆኑንም ለማረጋገጥ ችለናል ሲል የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቃለአብ ወርቅዬ ለዕዙ በላከው የአውደ ውጊያ ሪፓርት ገልጿል።
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 18 ቀን 2018 ዓ/ም
ተቋማችን !
ተቋማችን የአማራ ፋኖ ንቅናቄ (አ.ፋ.ብ.ን) ለሁሉም የዓለማችን ክፍል ለሚኖሩ አማራዎች የመጨረሻው የህልውና አደጋ መመከቻ እና ማስከበሪያ ሁኖ የሚያገለግለን በሰማዕታት ጓዶች ደም እና አጥንት የተገነባ የኮንክሪት ምሽጋችን ነው። ስለዚህ ተቋማችን ለልጆቻችን እና ለልጅ ልጆቻችን በኩራት የምናወርሳቸው በጣም ትልቁ ሀብት ነው።
ተቋማችን የጎንደሬነት ፣ የጎጃሜነት ፣ የሽዋየነት እና የወሎየነት ስሁት ማንነትን ሰብሮ እና አሸንፎ የወጣ የአማራዎች መሠባሰቢያ ቤት ነው። ስለዚህ በአውራጃዊ ማንነት ተቸንክራችሁ ትግሉን ለመከፋፈል የምትሞክሩ መደዴ የብአዴን ቅጥረኞች ውላችሁ በሽንፈት ስለተጠናቀቀ አማራጫችሁን ትፈልጉ ዘንድ ወንድማዊ ምክሬ ነው። ተቋማችን ለብዙ አመታት የተዘራብንን ፀረ-አማራነት ትርክት ሰባብሮ ራስ-ጠል አማራዎችን አሸንፎ ራስ-በቅ ሁኖ አማራዊ ችግሮችን ፣ በአማራዊ እሴት እና በአማራ ልጆች መፍታት እንዲችል ተደረጎ የተዋቀረ በበቁ እና በነቁ የአማራ ልጆች የሚመራ ተቋም ነው። ተቋማችን በብልፅግና የተጠለፉትን የኮሊደር ልማት ታጋዮችን እና ' ሱፍ ለባሽ ፎቶ ገጮችን ' አሸንፎ የትውልድ እዳ አድርጎ ፈተናዎችን ሁሉ በማለፍ የተመሠረተ ድርጅት ነው ።
የሚሊሻ አበል አጓጉቶት የሄደ ተክለ ብአዴን የኮሊደር ታጋይ ፎቶ ተነስቶ እና ለፍልፎ ከጨረሰ በኋላ ከእጃችን ላይ መውደቁ አይቀርም ። በአጠቃላይ አንድ ማንኪያ ቅንነት እና ቤት ዘግቶ መምከር አቅቶት የሄደን የትግል አመንዝራ ተቋማችን በጊዜ ሂደት በእጁ እንዲያስገባቸው ተደርጎ የተዋቀረ ተቋም ነው። ተቋማችን በፌክ አካውንት መሪን ከመሪ እንዳይተማመን ያደረጉትን ፣ የመሪዎችን ሰብዕና ከውስጥም ከውጭም ሁነው የሚያቆሽሹትን ፣ አስመሳይ ስም አጥፊ የውስጥ ባንዳዎች፣ በዘፈቀደ ፈገንዘብ የሚሰበሰቡትን እንዲሁም ሁሉንም የብልፅግና የፌስቡክ ሚሊሻን አሸንፎ የተመሠረተ ድርጅት ነው።
በመጨረሻም ተቋማችን የብልፅናን ስርዓተ መንግስት አፍርሶ እራሱን መንግሰት አከል ቁመና አድርጎ የተመሠረተ ድርጅት ስለሆነ ከሁሉም ፀረ-ብልግና ኃይሎች ጋር በመሆን የለመደውን የአሸናፊነት ጉዞ አጠናክሮ ስርዓት ማንበር እና ማፅናት ላይ በሙሉ ጊዜው እየሰራ ስለሚገኝ በተለያየ ምክንያት ትግሉን ሳትቀላቀሉ የቆያችሁ ወንድሞች ኑ ወደ ቤታችሁ ግቡ መልዕክቴ ነው። በእርግጥም ተቋማችን በአርበኛ ዘመነ ካሴ እየተመራ አዲስ ምዕራፍ ላይ ያደርሰናል።
አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !
©አርበኛ ግሩም ምሳሌ
+2
በአፋብን በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ስር የሚገኙት የአንዳቤት ብርጌድ ለሁለት ቀናት የዘለቀ ምክክርና ውይይት ማድረጉን አስታውቋል።
በኮሩ ስር የጉና ክፍለ ጦር ሰብሳቢ አርበኛ ወንዱአንተ አሰፋ ፣ ም/ወታደራዊ አዛዥ ኢንጅነር አበራ ንብረቱ እና ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች በሰሳተፉበት የውይይት መድረክ፡ ለብርጌዱ አባላት በወቅታዊ ጉዳይ የፖለቲካዊ ግንዛቤ ማስጨበጫና ሌሎች ስልጠናዎች በስፋት ተሰጥተዋል።
እንዲሁም በቀጣይ በወታደራዊ ስራዎች፣ በሃብት አሰባስብ፣ በፍትሕ አሰጣጥ፣ በወታደር ብወዛ፣ ከህዝብ ጋር በሚደረጉ መድረኮች በመሳሰሉት ጉዳዮች ሰፊ ውይይት ተካሄዷል ሲል መረጃውን የጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል አድርሷል።
💔💔የሀዘን መግለጫ💔💔
አርበኛ ሙልቀን መኳንንት በአማራ ፋኖ የኮማንዶና መሰረታዊ ዉትድርናን በማሰልጠን
ታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ አሰልጣኝና በርካታ ዙሮችን ያለድካም ያሰለጠነ አዲስ ትዉልድ ቀራጭ ትጉ አርበኛ ነበር።
እንዲሁም በአማራ ፋኖ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በፀደይ የኮማንዶ ማሰልጠኛ ትምህርትቤት የተሰጠውን ከጎንደርና ከጎጃም ለተወጣጣ የጋራ ሀይል የተሰጠን ታሪካዊ የአማራ የአንድነት ምሳሌ የሆነውን የኮማንዶ ስልጠና በትምህርት ቤቱ አዛዥነትና በመሪ አሰልጣኝነት አስደናቂና አይረሴ በሆነ መንገድ አሰልጥኖ አስመርቋል።
ከመሰረታዊ አባልነት እስከ ክፍለጦር አመራርነት ትልቅ ዋጋ በመክፈል በትግል ያደገ ጀግና በተዋጊነቱ በተሰበሩ ምሽጎች ጠላት የሚመሰክርለት መሬትን ባግባቡ መጠቀም የሚችል ብቁ ወታደራዊ መሪ ሆኖ የአማራን ህዝብ ወደነፃነት ለማድረስ በቃል የማይገለፅ ዋጋ ከፍሏል።
ትናንት ጥር 17 /2018 ዓ/ም አንድ ታጋይ ለህዝቡና ለሀገሩ መክፈል የሚችለዉን ውድ የክብር መሰዋእትነት በመክፈል ለአማራና ለአማራነት ከፍታ የአባቶቹን ታሪክ በመድገም ለአዲሱ ትውልድ ክብርንና አርበኝነትን አውርሶን በክብር ተሰዉቷል።
በዚህ አማራዉ በአንድነት ብሩህ ተስፋ ይዞ ትግሉ በአዲስ መንፈስ መቀጣጠል በጀመረበት ተላላኪዉ ፣ሰላቶዉና አስመሳዩ እየጠራ ሚናውን እየለየ ከየቤቱ ያለዉ አማራ ለመሰልጠንና ለመደራጀት እየተራወጠ ባለበት በዚህ ወቅት አርበኛ ሙሉቀን መኳንንት (ቅርጢ) እጅግ ከማንም በላይ በምታስፈልገን በዚህ ወቅት በክብር መሥዋዕትነት ቢለየንም በልጅ እድሜህ በወታደራዊ እዉቀት አባት ሆነህ ባፈራሀቸው ልጆችህ ተተኪውን ትውልድ በብቃት እናሰለጥነዋለን እናደራጀዋለን። እኛንም ለጠላት እጅ ከመስጠትና ምቾት ፈልጎ በአማራ ህዝብ ደምና እንባ ተረማምዶ ለጠላት ከማደር ጠብቆ ያንተንና የእነ ውባንተ አባተን የክብር መሰዋእትነት ለመቀበል ያብቃን ።
ለትግል ወንድሞቹና ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እመኛለሁ ።ክብር ለትግሉ ሰማእታት
✍️ አርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል
የአፋብን ስልጠና መምሪያ ኃላፊ
@highlight ልባሙ ፋኖ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከታፈሱ 1330 ወጣቶች መካከል 850 የሚደርሱት ከደብረ ማርቆስ ማሰልጠኛ ካምፕ መጥፋታቸው ተረጋግጧል"‼️
እነዚህ አራት ወጣቶች ደረጀ ጎሹ፣ ደሳለኝ ወርቁ፣ እንዳለ ይበልጣልና ዝጋለ ሰጤ ይባላሉ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ከመርጡለ ማርያም ከተማ መሐል አደባባይ ታፍሰው ድቅድቅ ባለው ጨለማ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ ከተጓዙ 110 ወጣቶች መካከል ይገኙ ነበር።
ደሳለኝ ወርቁ በመርጡለ ማርያም ከተማ ዙሪያ የሸዋት ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ከአመታት በፊት በደረሰበት የአንጀት መታጠፍ በቀዶ ጥገና ህክምና ህይወቱ የተረፈች መሆኑን የሚመሰክር ለምጽ በሆዱ መሀል ተመልክተናል። ቀሪ ሶስት ወጣቶች ከተሰማሩበት የጉልበት ስራ በሚኒሻዎች ታፍሰው ከደሳለኝ ወርቁ ጋር በአንድ መኪና ተጭነው ደብረ ማርቆስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እራሳቸውን ማግኘታቸውንም ከታፋሾች አንደበት ሰምተናል።
ሚኒሻዎች እየደበደቡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከወሰዱን በኋላ ስልካችንን ቀምተው ምሽት በአንድ መኪና አጭቀው የወሰዱን 60 የመርጡለ ማርያም ከተማ ወጣቶችና 50 የዙሪያ ቀበሌ ወጣቶች በድምራችን 110 ሁነን ደብረ ማርቆስ ከተማ ስንደርስ ከምስራቅ ጎጃም ዞንo ወረዳዎች ታፍሰው ከመጡት ጋር 1330 እንሆን ነበር ያሉት ወጣቶቹ በወታደራዊ ካምፕ ለ10 ቀናት መቆየታቸውን ያስታውሳሉ ።
በደብረ ማርቆስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ በገባን በሁለተኛው ቀን ለሁለት ከፍለው ወደ አዳራሽ ወስደው የሀይማኖት አባቶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ሽማግሌዎች የሚደበደቡበትን video እንድንመለከት ካደረጉን በኋላ ከዚህ ወጣችሁ ብትጠፉ ጥንፈኛው እንደዚህ ያሰቃያችኋል እያሉ ሲያሸማቅቁን እኛ እየሳቅን እንመለከታቸው ነበር እያሉ በፈገግታ የገጠማቸውን ነገር ሁሉ እያወጉን አረፈድን።
ለቀን ስራ ይሆናል ብለን በለበስነው ልብስ ስፖርት ሲያሰሩን የነበሩትም ከታፈሱት ውስጥ ግዙፍ ሰውነት ያላቸው ተመርጠው ሲሆን ከ45 ቀን በኋላ ፓራ ኮማንዶ ሁነን እንደምንመረቅ ተነግሮን ስልጠና ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ ቀን በቀን ወጣቶች እየጠፉ ወደ ሀገራቸው ሲሔዱ እኛም ጠፍተን ወደ እናተ መጠናል አዚህ ከመጣን በኋላ አስፈላጊው እንክብካቤ ተደርጎልናል በማለት ለ206ኛ ኮር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
"ፓራ ኮማንዶ "ወይንስ "ፋራ ኮማንዶ" የሚለው ሳይገባን በቀን ስራ ልብሳችን እና በባዶ እግራችን አሰልጥነው ወደ ጦርነት ሊማግዱን መሆኑን በመረዳት በማሰልጠኛ ከነበረው 1330 ታፋኝ መካከል 850 የምንሆነው እየጠፋን ወደ ፋኖ ተቀላቅለናል ያሉት እነዚህ ወጣቶች የአረመኔው ስርዓት ሰሞኑን በከተማዎች እያደረገ ያለውን የወጣቶችን አፈሳ እና ስቃይ ትክዝ እያሉ አጫውተውናል ።
በስርዓቱ ታፍሰው ከማሰልጠኛ የወጡትን ወጣቶች በመንከባከብ ላይ የሚገኘው 206ኛ ኮር በመርጡለ ማርያም ከተማ በስራ ላይ የነበሩ ወጣት ልጆቻችሁን የተነጠቃችሁ እና የጠፉባችሁ የእነዚህ ወጣት ቤተሰቦች
ዛሬ ልጆቻችሁ ከወንድሞቻቸው ጎን በአስተማማኝ ሁኔታ ይገኛሉና ልጆቻችሁን ትረከቡ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
©የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል!
18/ዐ5/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ ስለ ድርጅታችን ምስረታ እና ሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ማብራሪያ የሰጡበትን የቢቢሲ ሀተታ ይፋ ሆኗል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpv7xmwdpn7o?utm_sf_cserv_ref=485274381864409&at_campaign_type=owned&at_link_id=F0FEA36C-FA72-11F0-A824-D57B9E085C29&utm_sf_post_ref=659413842&at_link_type=web_link&at_bbc_team=editorial&at_ptr_name=facebook_page&at_link_origin=BBC_News_Amharic&at_medium=social&at_campaign=Social_Flow&at_format=link&fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAc3J0YwZhcHBfaWQPMjc1MjU0NjkyNTk4Mjc5AAEe_z9i4i2OFHT-1sXSYMKxmmU3n4GZNgiLKaA18EKIiWUJ7ePOHT8SY06FrBU_aem_de3xgqGfYWAXm8UKv2lG-g
+2
ፋኖዎችን መቋቋም ያቃተው የፎገራ ብልፅግና!
ታገይ ፋኖ በለጠ ዳኛው ይባላል ዛሬ የፎገራ ወረታው ብልፅግና ቤቱን አቃጥሎበታል። ቤቱ ተቃጥሎበትም ይሁን ከገዳዩ ስርዓት የሚጠበቅ ነው ብሎ እንደምታዩት በፈገግታ ላይ ይገኛል።
በላይ ዘለቀ ''ልጅ ከሀገር አይበልጥም'' እንዳለው ፋኖዎቻችን ፅናታችሁ ይለያል። በርቱልን!
ትግል ይቀጥላል።
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ ትናንት ጥር 16/2018 ለዛሬ ጥር 17/2018 አጥቢያ ለሊቱን በአንድ ተሽከርካሪ ተሳፍረው በከተማዋ ከስላሴ ካምፕ ወደ የጁቤ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ከባድ የቦምብ ጥቃት በመፈፀም አንፀባራቂ ድል አስመዝግበዋል።
በዚህ ኦፕሬሽን አንድ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ 14 ወታደሮች ሲገደሉ 15 ወታደሮች ከቀላል እስከ ከባድ ቆስለው ለሕክምና ወደ ደብረማርቆስ አጠቃላይ ሆስፒታል መወሰዳቸውን መረብ ሚዲያ ከ206ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።
በቀጠናው ፀረ አማራ ኃይሎችን እግር ተወርች አስሮ የሚገኘው 206ኛ ኮር በደብረ ማርቆስ ከተማ በተደጋጋሚ በሌሊትና በቀን በጠላት ላይ ያነጣጠረ የተሳካ የቦንብ ጥቃት በመፈፀም ድል ማስመዝገቡን ቀጥሏል::
ፍኖተ-አማራ ሚዲያዎች ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም ገፃችን👉
+1
አገዛዙ ንፁሀንን ጨፈጨፈ !
ቀን /17/05/2018ዓ.ም
የአገዛዙ ሠራዊት የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ በሚል ስበብ ንፁሀንን በጅምላ ጨፈጨፈ ።የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ቴወድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር ቀጠና ደቡብ ሜጫ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ የፋኖ ዘውዱ ሙላት ቤተሰቦችን የአገዛዙ ሰራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ገሏቸዋል ። አቶ ሙላት አድማስ ይኖሩበት በነበረው ደቡብ ሜጫ ከስራ ውጭ ምንም የማያቁ በማህበረሰቡ ዘንድ አንቱ የተባሉ የተከበሩ ሰው ነበሩ ።ነገርግን ጠላት ደቡብ ሜጫ ወረዳ መሀለገነት ከተማ እንደገባ ጀምሮ ልጃችሁ ፋኖ ነው በሚል ስበብ ሀብት ንብረታቸውን ዘርፎ አፈናቅሎ ቤታቸውን የሚኒሻ መኖሪያ አድርጎት ቆይቷል ። አቶ ሙላት አድማስ ይኖሩበት ከነበረው መሀለገነት ከተማ ተፈናቅለው ተወልደው ወደ አደጉበት ቀበሌ አዲስ ዓለም ቀበሌ ተሰደው ይኖሩ ነበር ።
ይህ አረመኒ ሰራዊት ግን በትላንትናው እለት ለደም ግብሩ ተሰደው ተጎሳቅለው ኑሯቸውን እየገፉ ባሉበት ቦታ ድረስ ሄዶ በቀ16/05/2018ዓም ከ16ዓመት ልጃቸው እና የእህታቸው ልጅ ጨምሮ በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ገሏቸዋል ። ለዚህ ጥቃት ሰለባ የሆኑት የፋኖ ዘውዱ ወላጅ አባት አቶ ሙላት አድማስ እና ታናሽ ወንድሙ ይኸነው ሙላት እንዲሁም የአቶ ሙላት የእህት ልጅ ውዱ መልኬ የተባሉ የ54እና 16 እንዲሁም 22 ዓመት እድሜ ክልል ያላቸው ናቸው ።
ለዚህ ነው ይህ ስርዓት ጨፍጫፊ ነው የምንለው ለዚህ ነው !
ይህ ስርዓት ደምግብሩ ነው የምንለው !
ለዚህም ነው አራዊት ሰራዊት ነው የምንለው !
ህፃን አዋቂ ሳይል ንፁሀንን በጅምላ የሚጨርስ አላማ የሌለው ስብስብ ነው የምንለው ለዚህ ነው።
©የኮሩ ሕዝብ ግንኙነት
## መረጃ ጎንደር
ዛሬ ጥር 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ከንፋስ መውጫ ወደ ደብረ ታቦር እጅ የሰጡ የብልጽግና ወዶ ገቦችን ይዞ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረን ኃይል ዘበራ የተባለ ቦታላይ በደፈጣ ተመታ።
በተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዥ ተመስገን አብርሃም አማካኝነት በተጣላ ደፈጣ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮችና እጅ የሰጡ አካላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲያስተናግድ ተደርጓል።በዚህ የደፋጣ ልዩ ኦፕሬሽን እጅ የሰጡ እና የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ አካላት 5 ሙት ሲሆን ከ10 በላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።
ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር
ሮቤል በእደማርያም
