en
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
3 613
Subscribers
+1324 hours
+4187 days
+1 05630 days
Posts Archive
እጅግ የሚያኮራ፣ ከንጉሶች መንደር፣ ከእነ ምኒልክ አውድማ፣ ከታላቁ ሀገር። ከእነ ደሱ ምድር፣ መዝ ብለህ ላከኝ፣ በእነ መከታው ሰፈር፣ አብራርተህ ንገረኝ።
እጅግ የሚያኮራ፣ ከንጉሶች መንደር፣ ከእነ ምኒልክ አውድማ፣ ከታላቁ ሀገር። ከእነ ደሱ ምድር፣ መዝ ብለህ ላከኝ፣ በእነ መከታው ሰፈር፣ አብራርተህ ንገረኝ።

ፀሐይ በአማራ አድማስ ላይ ስትፈነጥቅ፣ የአፋብን ምድር በተለመደው የዝምታ ድባብ ውስጥ አልነበረችም። ይልቁንም፣ ከሩቅ የሚሰማው የእልልታና የከበሮ ድምፅ፣ የምድሪቱን ጋራና ሸለቆ እያናወጠው ነበር። ሰማዩ በአቧራና በጭስ ሳይሆን፣ በሺዎች በሚቆጠሩ የቆራጥ ልቦች ትንፋሽ የታፈነ ይመስላል። ​(201ኛው) ኮር ሰራዊት፣ እንደ ንጉሡ እንደ ቴዎድሮስ ሁሉ “ሞት ይሻላል” የሚል ጽኑ ቃል በልባቸው አንግበው፣ ለታላቁ ግዳጅ ተሰልፈዋል። ይህ ስብስብ ሰራዊት ብቻ አልነበረም፤ ከጠለቀው የህዝብ ማህፀን የወጣ፣ ለማመን የሚከብድ የሰው ማዕበል እንጂ። ​ከአፋብን ጎዳናዎች እስከ ቀጠናው ዳርቻ ድረስ፣ ጀግናው የአማራ ህዝብ እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ ነው። አዛውንቶቹ በምርኩዛቸው መሬቱን እየነኩ “አማራ የጀመረውን ሳይጨርስ አያርፍም!” እያሉ ይገዝታሉ። ወጣቱ በኩራት ደረቱን ነፍቶ፣ እናቶች ደግሞ በዝማሬ ልጆቻቸውን ለድል ይሸኛሉ። የታየው ትዕይንት ለታሪክ ጸሐፊዎች ብዕር የሚከብድ የሚመስል። አፋብን ዛሬ የጀግኖች መፈልፈያ ብቻ ሳትሆን፣ የፋኖ አባላቶቹ የብረት ጋሻቸውንና ወኔያቸውን ሰንቀው ወደፊት ሲገሰግሱ፣ ከኋላቸው ያለው ህዝባዊ ማዕበል የመከታ ምሰሶ ሆኖላቸዋል። ​ታሪክ ዛሬም በደማቅ ቀለም እየተጻፈች ነው። አማራ አንድ ጊዜ ቆርጦ ተነስቷል፤ የጀመረውን ትግል በድል ሳይቋጭ ወደኋላ እንደማይመለስ ደግሞ የአፋብን የውጊያ ተራራዎች ምስክሮች ናቸው።

ሰበር ዜና አጣዬ የአሳምነው አናብስቶች ዛሬ በወሰዱት እርምጃ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ሰፈር ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል!! ​ ​በታሪካዊቷ የአጣዬ ምድርና በኤፍራታ ግድም ወረዳዎች በዙሪያ
ሰበር ዜና አጣዬ የአሳምነው አናብስቶች ዛሬ በወሰዱት እርምጃ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ሰፈር ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል!! ​ ​በታሪካዊቷ የአጣዬ ምድርና በኤፍራታ ግድም ወረዳዎች በዙሪያው በአሉት አካባቤዎች ዛሬ ረፋዱን ልዩና አስገራሚ ወታደራዊ ክስተት የአሳምነው አናብስቶች በወሰዱት መብረቃዊ እርምጃ፣ በአካባቢው የነበረው የአብይ አህመድ ኃይል ወታደራዊ መዋቅር ከፍተኛ መናወጥ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል። ​ሆኖም የአብይ አህመድ አገዛዝ ጥምር ጦር ብሎ የሚመራው ኃይል ሚኒሻ፣ ፖሊስ እና አድማ መከላከያ ከላይ የመጣ ጥብቅ መመሪያ ነው በሚል ሰበብ ወደ አስገዳጅ ግዳጅ እንዲሰማሩ መደረጋቸው በሰራዊቱ ውስጥ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል። ይህን ተከትሎ በታችኛው አመራርና በደረጃው ባሉ የጸጥታ አባላት መካከል እርስ በእርስ የመነካከስ እና የትዕዛዝ ያለመቀበል ቅጭት ተፈጥሯል። ​በአጣዬ፣ በርግቤ እና ፈርድውሃ አካባቢዎች፣ የወንበር አስጠባቂው ኃይል የአሳምነው አናብስቶችን የክንድ ብርታት መቋቋም ተስኖታል። በተለይም በሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የአሳምነው አናብስቶች መቋቋም ባለመቻላቸው፣ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ድንጋጤና በውስጥ ሽኩቻ ውስጥ እንደሚገኙ ከስፍራው ፍኖተ አማራ ሚዲያ ምንጮችን አጋርታናለች።

ሰበር የድል ዜና!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦር ድልን ተቀዳጀ። የሰባት ለሰባ ክፍለጦር ደመላሽ ሻለቃ
+1
ሰበር የድል ዜና!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦር ድልን ተቀዳጀ። የሰባት ለሰባ ክፍለጦር ደመላሽ ሻለቃ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ፈረዶ ውሀ ቀበሌእና ካራለጎማ ቀበሌ ተረተር በሚባለው ቦታ ላይ ከሌሊቱ 10: 00 ሰዓት ላይ ተስበው በመግባት ዛሬም እንደ ትላንቱ በቁጥር አንድ (1) ስናይፐርን፣ ሁለት(2) ጥርጥር ክላሽ እና የተለያዩ ወታደራዊ ትጥቆች መማረክ ችለዋል ። እንዲሁም የሰባት ለሰባ ክፍለጦር ስበር ሻለቃ በላይኛው ሰራንባ የሰርዶ ቀበሌ በቴሌው ጋር በመግባት ከጠዋቱ 12: 00 ሰዓት ጀምሮ የአብይ አህመድን ወንበር አስጠባቂ መከላከያ እና የብዓዴን ቅጥረኛ ሚሊሻ ሲደቁሱት አርፍደዋል። በአውደውጊያውም የአሳምነው አናብስቶች እንደ ንስር ተወርውረው በመግባት በርካታ የአብይ አህመድ ሰራዊት በዬ ሸጡ ተዝረክርኮ እንዲቀር አድርገውታል። ሆኖም የአብይ አህመድ አገዛዝ በቁጥር የማይገለፁ ቁስለኞችንም ወደ አጣዬ ሆስፒታል ሲያመላልስ ውሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 29/06/2018 ዓ.ም

የሁለቱ ከፍተኛ ጦር መኮንኖች ወግ 1. ጀ/ል ተፈራ ማሞ የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ በአሁኑ ሰአት የአፋብን ወታደራዊ ዋና አዛዥ ኋላ ላይ በአማራ ክልል ውሃ ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ተደርገው የተመደቡ 2. ኮ/ል አለበል አማረ የቀድሞው የአማራ ክልል የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ም/ል ቢሮ ኃላፊ(በአሁኑ ጊዜ በምን ሁኔታ እንዳለ የማላውቀው) ኋላ ላይ በአማራ ክልል ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ተደርገው የተሾሙ በአማራ ክልሉ የከፍተኛ አመራሮች እልቂት ለአመታት ያህል ታስረው ከቆዩ በኋላ ከጠባቡ እስር ቤት ወደ ሰፊው እስርቤት እንደተቀላቀሉትን ደብረብርሃን ከተማ በአንድ ጠበብ ባለች አዳራሽ ውስጥ ሁለቱን ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና በወቅቱ አብሮ ታስሮ የተፈታ ለጊዜው ለደህንነቱ በማሰብ ስሙን የማልጠቅሰው ከፍተኛ የጦር መኮንን እኔና ጓዶቼ ለተወሰኑ ደቂቃ አናግረውን ነበር። እኛም በቀጥታ የጠየቅናቸው ድሮ ከነበራችሁ ደሞዝ የተሻለ ከተከፈላችሁ የተሻለ ስምና ዝና ስላላችሁ ለምን እውስጥ ሆናችሁ እኛን አታታግሉንም? ብለን ጠየቅናቸው:: የ3ቱም መልስ አጭርና ተመሳሳይ ነበር። እኛ የጦር መኮንንኖች እንጅ የውሃም የመንገድም መሀንዲሶች ስላልሆንን" ስምም ዝናም ገንዘብም አያስጨንቀን መሬት ወርደን በመስራት የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና ስጋት እንቀለብሳለን ብለው እቅጩን ነገሩ ለካ ይኸም ይቻላል እንዴ?ብለን እራሳችንን በመጠየቅ ፈጣሪ እኛንም ፍርፋሪ ዝናና ስም እንዲሁም ስልጣን ለማጀቢያነት ቢቀርብልን ቀድመን ከወጣንለት ህዝብ ጥቅም እንደማይበልጥና አሸቀንጥረን መጣል እንዳለብን ተማምነን የወጣንበት ወርቃማ ጊዜን ሳስብ "ዛሬም ይህ ማጀቢያ ቢመጣ ያለ ቅድመሁኔታ አሽቀንጥሮ መጣል እንደሚገባ ሳስብ ፍፁም ደስታ ይሰማኛል።

የብልፅግና መከላከያ ሰራዊትና የአድማ ብተና አባላት የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ! የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከየ አቅጣጫው እየፈረሰ ሲሆን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 49ኛ ክፍለ
+5
የብልፅግና መከላከያ ሰራዊትና የአድማ ብተና አባላት  የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ!  የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከየ አቅጣጫው እየፈረሰ ሲሆን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 49ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሻለቃ አጃቢ አንድ ጥርጥር ጥቁር ክላሽ በመያዝ 58ኛ ክፍለ ጦር 1 ስናይፐር በመያዝና 1 ጥቁር ክላሽ በመያዝ እንድሁም 2 የአድማ ብተና አባል ከነ ሙሉ ትጥቃቸውና ተተኳሽ ባጠቃላይ አንድ ስናይፐርና አራት ክላሽ በመያዝ የካቲት 28/2018 ዓ.ም ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል:: አመራሮቹም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: ባለፉት ሶስት ቀናቶች ሁለት ስናፐርና ብዙ ክላሾች ወደ ኮሩ ገቢ ሆኗል:: ከመከላከያ ኮብልለው ፋኖን የተቀላቀሉት የ49ኛ ክፍለ ጦር የሻለቃ አጃቢ እንድሁም የሰራዊት አባላትና የአድማ ብተና አባላት ከፍተኛ መኮነኖች የሚያወርዱልን ተልዕኮ በመጀመሪያ ፋኖን እናጠፋለን፣ ቀጥለን ወያኔን እናጠፋለን፣ በመጨረሻም ኤርትራን በመዋጋት ወደብ እናስመልሳለን እያሉ ነው ሲሉ የብልፅግናን እብደት በመግለፅ ለዚህ ውሳኔ መብቃታቸውን ተናገዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 28/2018 ዓ.ም

ወለጋ የደም መሬት! "አማራን ከወለጋ ማፅዳት" በማለት ከቤተመንግስቱ አራጅ ቡድን ትዕዛዝ ተሰጦት የጫካው ቡድን እየተገበረ ይገኛል። ዛሬም የአማራ ሞት በወለጋ አልቀረም፤ እናት የ8 ወር ልጇን በሆዷ
+1
ወለጋ የደም መሬት! "አማራን ከወለጋ ማፅዳት" በማለት ከቤተመንግስቱ አራጅ ቡድን ትዕዛዝ ተሰጦት የጫካው ቡድን እየተገበረ ይገኛል። ዛሬም የአማራ ሞት በወለጋ አልቀረም፤ እናት የ8 ወር ልጇን በሆዷ እንደያዘች በዱላ ቀጥቅ*ጠው ገደሏት😭😭😭 የአብይ አህመድ ስልጣን የሚጠናው አማራን መግደል  በሚል መፈክር በየትኛውም የኢትዮጵያ ኮርነር እየሆነ ያለውን ማየት በቂ ነው። የሚገደለው አማራ ብቻና ብቻ ነው። እኛ ግን ለጫካ ስልጣን ብለን በመሀይም መንጋዎች አማካኝነት ስንጮህ እንውላለን😥

የደራ ሰቆቃ የንጹሃን ደም ፍትህ ይሻል! በደራ ምድር የንጹሃን እህቶቻችን፣ የናቶቻችን አባት እና ወንድሞቻችን ደም እንደ ጎርፍ ይፈሳል! ዛሬም በደራ ሰማይ ስር የሚሰማው የሕፃናት አሰቃቂ ጩኸት እን
የደራ ሰቆቃ የንጹሃን ደም ፍትህ ይሻል! በደራ ምድር የንጹሃን እህቶቻችን፣ የናቶቻችን አባት እና ወንድሞቻችን ደም እንደ ጎርፍ ይፈሳል! ዛሬም በደራ ሰማይ ስር የሚሰማው የሕፃናት አሰቃቂ ጩኸት እንጂ የሰላም ዜማ አይደለም። ያለምንም ጥፋታቸው የታረዱ ወገኖቻችን ደም ከምድር ወደ ሰማይ እየጮኸ ፍትህን ይማጸናል። ይህ ደም ዝም አይልም! በደራ አፈር ላይ የሚንከባለለው እያንዳንዱ የእንባ ጠብታ፣ የኢትዮጵያ እናቶች የሚረግፉት መራራ ሐዘን እና የሕፃናት ያልተቀደሰ መስዋዕትነት እስከ ሰማይ ድረስ ይደርሳል። ዓለም ሆይ ስሚ! የደራን ልብ ሰባሪ ጩኸት አድምጪ! ኢትዮጵያ ሆይ ንቂ! የልጆችሽ ደም በከንቱ ፈሶ እንዳይቀር ድምፅሽን አሰሚ! ፍትህ እስኪነግሥ፣ ግፈኞች ለፍርድ እስኪቀርቡ እና እውነት በጠራራ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ዝምታን አንመርጥም! ደማቸው አይረሳም፣ ድምፃቸውም አይጠፋም! #ፍትህ_ለደራ #የንጹሃን_ደም_አይረሳም ✍️ሽመልስ ንጉሴ

የአሳምነው ልጆች ይችሉበታል እመለስበታለሁ እስከዛው ሸር ጆይን
የአሳምነው ልጆች ይችሉበታል እመለስበታለሁ እስከዛው ሸር ጆይን

በትውልድ ላይ የታወጀ ጦርነት‼️ የካቲት 28/2018 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ ሰፍሮ የሚገኘውና ራሱን "ጥምር ጦር" ብሎ የሚጠራው የአብይ አህመድ ወራሪ ኃይል፣ ወደ ሮቡ ገበያ "ሬሽን" ለማድረስ በሚያደርገው እንቅስቃሴ በንጹሃን ዜጎች እና በሕዝብ የልማት ተቋማት ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ቀጥሏል። ከቅርብ ቀናት ወዲህ በእነራታ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመው መጠነ ሰፊ ውድመትና ዘረፋ ደግሞ የሥርዓቱን አማራን የማጥፋትና የማደንቆር ስልታዊ ዘመቻ በግልጽ ያሳየ ሆኗል። የትምህርት ቤቱ መቃጠልና የንብረት ዘረፋ በተመለከተ ከስፍራው ሒደን እንዳረጋገጥነው ትምህርት ቤቱ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ደረጃ ፈራርሷል። የጥፋት ኃይሉ በመድፍ፣ በBM-107፣ በዙ-23 እና ቦሞርታር ጋር በመታጀብ በንፅሀን አርሶ አደሮች ላይ እየተኮሰ ሲቪሊያንን እና የሲቪሊያንን ንብረት ከማውደሙ ባሻር በትምህርት ቤቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት የሚከተሉትን ያካትታል፦ 👉የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ዘረፋና ውድመት፦ ለተማሪዎች መማሪያና ለአስተዳደር ሥራ ይውሉ የነበሩ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮችና የድምፅ ማጉያ መሣሪያዎች ተዘርፈዋል። መውሰድ ያልቻሉትን ደግሞ ሰባብረውና በትነውት ሄደዋል። 👉የመረጃና የሰነድ ጥፋት፦ የትውልድ ታሪክና የተማሪዎች መረጃ የያዙ ሰነዶች፣ መጻሕፍትና ልዩ ልዩ የመማሪያ ግብዓቶች ከየመደርደሪያው ተዘርክረው መሬት ላይ እንዲረግጡ፣ እንዲቀደዱና እንደቃጣሉ ተደርጓል። 👉የቁሳቁስ መፈራረስ፦ ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮችና ሰነድ ማስቀመጫ ቁምሳጥኖች ተሰባብረው ከጥቅም ውጭ ሆነዋል። መጋዘኖች ተበርብረው ሙሉ በሙሉ የሚኒ ሚዲያ አልባሳትና ጨርቃጨርቆች ተዘርፈዋል የተወሰኑቱ ደግሞ ተቀዳደው ጥቅም በማይሰጡበት ደረጃ ላይ ሆነዋል። በአካባቢው ያገኘናቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን እንደነጋገርነው ከሆነም "ይህ ድርጊት የሚያሳየው የሥርዓቱ ፀብ ከፋኖ ጋር ብቻ ሳይሆን ከአማራ ሕዝብና ከአማራው መጻኢ ዕድል ጋር መሆኑን ነው" ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በምሬት የደረሰባቸውን በደልና የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በቁጣ ይናገራሉ። የአካባቢው ማኅበረሰብ እንደገለጸው፣ ፋኖ አካባቢውን ተቆጣጥሮ በነበረበት ወቅት ለትምህርት ቤቱ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ ያደርግ ነበር። ይሁን እንጂ "መንግሥት ነኝ" የሚለው ኃይል ወደ ስፍራው ሲገባ የታየው ግን ተቋሙን ማውደም፣ መዝረፍና የወደፊት ተስፋ የሆኑ ሕፃናትን የመማሪያ ክፍል ማዘጋት ሆኗል። "ፋኖ ሲያቅፈው፣ ወራሪው አጠፋው" ሲሉም የደረሰውን ውድመት በቁጭት ይናገራሉ። ይህ በሲቪል ተቋማት ላይ የሚፈጸም ጥቃት ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል መሆኑን የታዘቡ ባለሙያዎች፣ ለደረሰው ውድመት አካባቢውን ተቆጣጥሮ የነበረው ኃይል ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆኑን አሳስበዋል። አንድነታችን በተባበረ ክንዳችን! አዲስ ትውልትድ! አዲሰ አሰተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! አፍብን 206ኛ ኮር የንጉስ ተክለሃይማኖት ( ደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር) ጊዜያዊ መንግስት ሚዲያና ከምኒኬሽን:

የአገዛዙ ግፍ በቅዱስ ላሊበላ ከተማ! ከሰሞኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ 303ኛ አሳምነው ኮር ልዩ ኦፕሬሽን ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ዘልቆ በመግባት የላስታ ወረዳ ብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ኃላፊ የሆነችውን ወ/ሮ የኔነሽ መላኩን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወቃል። የብልጽግናው አገዛዝ የራሱን አመራር ማስለቀቅ ሲያቅተው የጦርነቱ ተሳታፊ ያልሆኑና የግል ሕይወታቸውን የሚኖሩ የፋኖ ቤተሰቦችን እያሳደደ እያሰረ እንደሚገኝ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። አሸባሪ ነው ሲሉት መንግስት ነኝ መንግስት ነው ሲሉት ወንበዴ ሆኖ የሚገኘው አገዛዝ በሰማይም በምድርም አለኝ የሚለውን ጦር አሰማርቶ ገጥሞ ማሸነፍ ያልቻለውን የፋኖ ክንድ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ በላስታ ወረዳ የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ፣ ፋኖ ዘመድ አላችሁ በማለት ከመኖክሴ እሰከ ህፃን ልጅ አፍኖ ማሰርና መሰወር ላይ ይገኛል። በዚህም በዛሬው ዕለት የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ብቻ ከ10 በላይ እናቶችን ጨምሮ በርካታ ንፁሀን ታስረዋል። 1ኛ. የሚኒሊክ እዝ ማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ የአለምነው መብራቱ እናት 2ኛ.  የሚኒሊክ እዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ የአርበኛ ወንድሙ ማሩ ባለቤት እና እናት 3ኛ. የላስታ ኮር አስተዳደር ኃላፊ የአርበኛ ሞላ አዳነ ወንድም 4ኛ. የአርበኛ ጣሰው አጋዡ ባለቤት 5ኛ. የላስታ ኮር ህግ ክፍል ኃላፊ የአርበኛ ዋኘው አደራ ወንድም 6ኛ. የላስታ ኮር መሳሪያ ጥገና ዘርፍ የአርበኛ ተመቼ  ቢራራ ባለቤት 7ኛ. የላስታ ኮር ወታደራዊ አማካሪ የአርበኛ  ሻንበል  ወዳጅ  ባለቤት 8ኛ. የፋኖ  ተፈራ  እባቡ  እናት 9ኛ. የፋኖ    አበባው  እህቶች 10ኛ. የፋኒት ብርቄ  እህት እና ሌሎችም በዛሬው ዕለት በአገዛዙ ሰራዊቶች እንደተወሰዱ ታውቋል።

አሁንም እየከዳ ፋኖን መቀላቀሉ ቀጥሏል ! ዛሬ 28/06/2018 ዓ.ም ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር የቢተወደድ አያሌው መኮነን ሻለቃን የተቀላቀለው ወጣት እንደተናገረው ሁሉም ከድቶ ቤ
አሁንም እየከዳ ፋኖን መቀላቀሉ ቀጥሏል ! ዛሬ 28/06/2018 ዓ.ም ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር የቢተወደድ አያሌው መኮነን ሻለቃን የተቀላቀለው ወጣት እንደተናገረው ሁሉም ከድቶ ቤተሰቡን መሔድ ነው የሚፈልገው ብሏል ። ፋኖነት ተመርጦ የሚገኝ የህልውናችን ማስጠበቂያ ኃይላችን ነው ። ይቀጥላል !

አስቸኳይ የጥንቃቄ ጥሪ የአገዛዙ "የጸጥታ ዘመቻ" እና የታቀዱ ሴራዎች! ለመላው የአማራ ሕዝብ፣ በተለይም ለከተማ ነዋሪዎች፤ አምባገነኑ የብልጽግና አገዛዝ ሥልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት "የይስሙላ ምርጫ" እንዳይደናቀፍበኝ በሚል፣ አዲስና አደገኛ የሆነ የማፈንና የማጥፋት እርምጃ መጀመሩን የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሰውናል። አገዛዙ "ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ" በሚል ሰበብ፣ በከተሞች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያላቸውን ዜጎች ለይቶ ለማጥቃት አቅዷል። በአገዛዙ የታቀዱት የጥቃት ዒላማዎች፤ የሚከተሉትን የኅብረተሰብ ክፍሎች በአንደኛ ደረጃ ስጋትነት ፈርጆ የማሳደድ ዘመቻ ከፍቷል። ንቁ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች፤ ለትግሉ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ ተብለው የሚጠረጠሩ፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎችና ወጣቶች፤ እውነትን የሚያሰራጩና ሕዝቡን የሚያነቁ። የሃይማኖት አባቶች፤ ስለ ፍትሕና ስለ ሕዝብ መከራ የሚናገሩ መሪዎች እንዲሁም በመንግሥት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የመንግሥት ሠራተኞች፤ የአገዛዙ ካድሬዎች እየፈጸሙት ያለውን ዝርፊያ የሚቃወሙትን "የቀኘ አባል ናቸው" በማለት ለማሰር ታስቧል። እስሩን ለመፈጸም አገዛዙ የነደፈው ስልታዊ ሴራ፤ የታሰሩ ዜጎች እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸውና ድምፃቸው እንዳይሰማ ራቅ ወዳሉ ወታደራዊ ካምፖችና ማጎሪያዎች የማጋዝ ሥራ እንዲመሰራ አቅዷል። በተጨማሪ፤ "አስቸጋሪ" ያላቸውን ግለሰቦች በአገዛዙ ታጣቂ ታቅዶ በሚፈጸም ግድያ በማከናውን በግርግር ወይም "ባልታወቁ ሰዎች" ጥቃት እንዲገደሉ ትዕዛዝ ማውረዱ ተረጋግጧል። አረመኔው አገዛዝ ይህን የንጹሐን ዜጎችን ግድያ ሲፈጽም "የፋኖ ሴል" በሚል ስም በማጥፋት ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት እንደሚሞክረም ይጠበቃል። ስለሆነም፤ ማኅበረሰቡ ይኽን የአገዛዙን ጅምላ እስር እና የጥፋት ሴራ ለማክሸፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ እያቀረብን፤ ይህንን የጥፋት ዘመቻ ለመቀልበስ እያንዳንዱ ዜጋ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲያደርግ ጥሪ ይቀርባል፦ 1ኛ። መረጃ መለዋወጥ፤ ማንኛውም ግለሰብ በጸጥታ ኃይሎች ሲወሰድ ወይም ሲታሰር፣ ወዲያውኑ ለቤተሰብ፣ ለጎረቤትና ለማኅበራዊ ሚዲያ እንዲደርስ ማድረግ። ድምፅን አለማጥፋት ዋነኛው መከላከያ ነው። 2ኛ. የጋራ ጥበቃ በማድረግ፤ በየመንደሩና በየአካባቢው እንግዳ እንቅስቃሴዎችን መከታተል፤ በተለይ በሃይማኖት አባቶችና በታወቁ አንቂዎች ዙሪያ ማኅበረሰቡ የጋራ ጥበቃ እንዲያደርግ ይመከራል። 3ኛ. መደበቅና መጠንቀቅ፤ ስጋት ያለባቸው ወጣቶችና አንቂዎች አድራሻቸውን በየጊዜው በመቀየርና በብቸኝነት ከመንቀሳቀስ በመቆጠብ ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው። 4ኛም የሴራ ግድያዎችን ማጋለጥ፤ በከተማ ውስጥ የሚፈጠሩ ድንገተኛ ግርግሮችንና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን በንቃት መከታተልና በአገዛዙ የሚላኩ "ገዳዮችን" በሕዝብ ዓይን መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን። አገዛዙ ሕዝቡን በማሰርና በመግደል የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም የሚያደርገው ጥረት የሽንፈቱ መጀመሪያ እንጂ መዳኛ ሊሆን አይችልም። የንጹሐን ዜጎች መታሰርና መሰደድ ትግሉን ይበልጥ የሚያፋፍም እንጂ የሚያቀዘቅዝ አይደለም። ሕዝቡ በአንድነት በመቆም ይህንን የጭለማ ዘመቻ ማክሸፍ አለበት። ውድቀት ለወንጀለኛውና ለአረመኔው አገዛዝ! እስቲበል አለሙ ዘሪሁን

የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት በጀኔራል ሰለሞን ኢታፋ የሚመራው ደቡብ ዕዝ አባላቶች ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ! የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከየ አቅጣጫው እየፈረሰ ሲሆን የደቡብ ዕዝ 205
የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት በጀኔራል ሰለሞን ኢታፋ የሚመራው ደቡብ ዕዝ አባላቶች ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ!  የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ከየ አቅጣጫው እየፈረሰ ሲሆን የደቡብ ዕዝ 205ኛ ኮር 42ኛ ክፍለ ጦር ሁለት አባላቶች ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: አመራሮቹም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 28/2018 ዓ.ም

ዳግማዊ የአሩሲ ጭፍጨፋ በመሃል አማራ ሳይንት! የአማራን ህዝብ በማንነቱ ብቻ እየጨፈጨፈ ያለው ስርዓት፣ ዛሬ ማለትም የካቲት 28/2018 ዓ.ም ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ የመሃል አማራ ሳይንትን ህዝብ ቤተክርስቲያን ላይ በመድፍ ጨፍጭፏል፡፡ ይህ ጨፍጫፊ መንግስት የአማራን ህዝብ ታሪክ ከማጥፋት አልፎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን የማዳከሙን ስራ ገዳማትን ኢላማ ያደረገ ሲሆን ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ታዕከ ነገስት አትሮንሰ ማርያም ቤተ-ክርስቲያንን በመድፍ በመደብደብ 26 ሰዎች የተጎዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አስተዳዳሪውንና አቃቢዋን እንዲሁም ሶስት ዲያቆናትን ባጠቃላይ ባጠቃላይ አምስት ሲሞቱ ፣21 ከባድ ቁስለኞች ሆነዋል፡፡ በደቡብ ወሎዞን መሀል ሳይንት ወረዳ የምትገኘው ታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ታዕካ ነገስት አትሮንሰ ማርያም ቤተክርስቲያን መሷእተ ኦሪት ከሚሰዋባቸው የኦሪት ቤተክርስቲያን አንዷ ስትሆን ቤተክርስቲያኗ ከአመተ አለም ጀምራ ምእመኖቿን ስታገለግል የቆየች ሲሆን የአፄ በእደማርያምን ጨምሮ የብዙ ነገስታት መቃብር ዛሬም ድረስ በቦታው ይገኛል:: ጨፈፍጫፊው መንግሥት ቤተክርስቲያኗን ኢላማ ያደረገበት ምክንያት በርካታ የታሪክ መዛግብቶች ያሉባት በመሆኗ፣ በርካታ የአብነት ተማሪዎች የሚማሩባት በመሆኗ ኦርቶዶክስን ማዳከም አማራን የማዳከሚያ አንዱ ስልት በመሆኑ ነው፡፡ ይህንን አፀያፊ ተግባር የሰው ልጅ በሙሉ ሊያወግዘው ይገባል እያልን የአማራ ፋኖም አንደነቱን የበለጠ በማጠናከር ህዝቡን ሊታደግ የሚገባበት ጊዜ ላይ መሆኑን ያሳየ ነው:: ሠማዕት ወገኖቻችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፦ 1. ቆሞስ አባ ሞገስ ፍስሃ የሞቱ፡አትሮንሰ ማርያም 2. እማሆይ ድንቄ ተከለ አቃቢ የሞቱ፡ አትሮንሰ ማርያም 3. ዳቆን መዝገቡ መኮነን ፡ሜስ ቁስቋም ማርያም እግሩ የተቆረጠ ከባድ ቁስለኛ 4. አባ አካልነው መንግስቱ፡አትሮንሰ ማርያም 5. አባ ምናሴ ታረቀ የቆሰለ ፡አትሮንሰ ማርያም 6. ዳቆን በአማን ....መገጣ የሞተ 7. ዳቆን በለጠ አስቻለው የሞተ፡አትሮንሰ ማርያም 8. ዳቆን ዋሲሁን አስቻለው ቁስለኛ፡ አትሮንሰ ማርያም 9. ዳቆን ዳዊት ...፡የሾብ ከባድ ቁስለኛ 10. ክነፈርግብ አንዳርጌ የሞተ ዛሬ ቅዳሴ የቀደሰ የሞተ ፡አትሮንሰ ማርያም 11. ዳቆን አይመረ መርሻ ከባድ ቁስለኛ ዛሬ የቀደሰ አማኑኤል፡ አትሮንሰ ማርያም 12. ዳቆን ህሩይ... ፡አባ ሩፋኤል 13. ዳቆን አብርሃም ሙሉሰው ፡አትሮንስማርያም 14. ዳቆን ሰምረ ስመኘው ቁስለኛ ፡ዘቃ ጊዮርጊስ 15. ዳቆን ጣሰው በላቸዉ  ፡አትሮንስ ማርያም 16. ዳቆን ሙሉቀን ወንድም ፡አትሮንስ ማርያም 117 ሊቀ መዘምር አየን ብርሃኑ፡ አትሮንስ ማርያም 18. ወንዴ ታዬ የቤተክርስቲያኗ ዘበኛ ፡አትሮንሰ ማርያም 19. ሰርኬ አካልነው ፍትሃት የምታስፈታ ፡አትሮንሰ ማርያም 20. መምሬ ይታያል አካልነው ፍትሃት የሚያስፈታ፡ አትሮንሰ ማርያም 21. ጎበዜ አገኘሁ ቁስለኛ፡ አትሮንሰ ማርያም 22. መሪጌታ ሳህለ ማርያም ስለሽ ከባድ ቁስለኛ፡ አትሮንሰ ማርያም 23. የቻለ ማንደፍሮ ፡፡አትሮንሰ ማርያም 24. ወርቄ ይታያል ፡አትሮንሰ ማርያም 25. ዳቆን ልዑል  ... ፡ዮሐንስ በሁኔታው የተደናገጡት የገዳሟ የአብነት ተማሪዎች በሙሉ ለቀው ተሰደዋል:: ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩትና ከተጨፈጨፉት  ምዕመናኖች መካከል አምስቱ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አስራ አንዱ እጅና እግራቸው የተቆረጠ እንዲሁም አስሩ መካከለኛና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው:: ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ የካቲት 28/2018 ዓ.ም

በሸኔ እና በአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ ኃይል ሰባት ንፁሀን ዜጎች ተገደሉ !! በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ውስጥ ባለፉት ሁለት ቀናት በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሰዋል። በተለይ አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰቦች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈጸመ ይገኛል። መጀመሪያ የተፈጸመድ እሑድ የካቲት 19 ማታ ሲሆን፣ በደንበዛ ጅብ በሚባል ቀበሌ ላይ ነበር። በዚህ ጥቃት ቁጥር የማይታወቅ መኖሪያ ቤቶች እና ንብረቶች ወድመዋል። ነዋሪዎቹ ከዶሮ፣ ከብት እና ሌላ ንብረታቸው ጋር ምንም ሳይዙ ለሕይወታቸው በመሸሽ ላይ ናቸው። አርብ ማታ (የካቲት 21) ደግሞ ጥቃቱ በጊርሚ ጎባ እና በቢስጭኖ ጤራ ቀበሌዎች ላይ ተከስቷል። በዚህ የዘመቻ ማግስት ብቻ ሰባት ንፁሀን ዜጎች የተገደሉ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል አሮጊቶች እንደሚገኙበትና አንዲት አሮጊት በመኝታ አልጋዋ ላይ እንደነበረች እሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋለች። በተለይም ሰዎችን እየጎተቱ እሳት ውስጥ እየከተቱ ቤት ዘግተው ነው ያቃጠሏቸው። በእውነት ከእግዚአብሔር የተፈጠሩ ፍጡራን በማይመስል መልኩ ግፍን ተፈፅሟል። ጥቃቱን የፈጸሙት የሽመልስ አብዲሳ የዳቦ ስም ታጣቂዎች ሸኔ ሲሆኑ ከባድ መሳሪያ ጭምር በመያዝ RPG እና ስናይፐር ይዘው እንዲሁም በዚህ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ናቸው። የኦሮሞ የእነሱ ሰው ቤቱ አይቃጠልም... ይሄንን ሕዝብ ደግሞ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እየታገሉ እየሰሩ ይገኛል። በሌሊቱ አንድ የአካባቢው ነዋሪ እስከ ፌዴራል ደረጃ ድረስ ቢደውልም በዚህ ሰዓት መንቀሳቀስ መውጣት አንችልም" የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ከገዥው ስርዓህ መልስ ተስጥቷል ። ሆኖም ነዋሪው በማህበረሰቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በተመለከተ ከሸኔ ታጣቂዎች ባሻገር በአካባቢው ያሉ የፖለቲካ አካላትንም በሕዝቡ ላይ ይሄንን ግፍ እየሰሩ ያሉት የብልፅግና አባል ሰዎች ናቸው እነዚህ አካላት ከሸኔ ታጣቂዎች ጋር በመቀናጀት ወይም መረጃ እየሰጡ ማህበረሰቡን ለጥቃት እያደረጉ ይገኛሉ። ሆኖም አሁን ላይ ሴቶች፣ ሕፃናት እና አረጋውያን ጨምሮ በርካታ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀበሌዎቻቸው ተፈናቅለው በአባይ በረሃ አካባቢ ለሕይወታቸው ሲሉ በመሰደድ ላይ ናቸው። ማህበርሰቡም እኛ ወዴት እንደምንደርስ ግራ ገብቶን ነው ያለነው ብለዋል። ማንም የደረሰለት አካል የለም እስከ አሁን ድረስ" በማለት ተስፋ መቁረጣቸውን ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !! የካቲት 28/06/2018 ዓ.ም