ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more3 536
Subscribers
+2524 hours
+3407 days
+72430 days
Posts Archive
+6
''ሰላም ሳይኖር ምርጫ የለም" በማለት የባሶሊበን ወረዳ ቤተ -ንጉስ ከተማ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል።
+6
የ8 አመት የባርነት ቀንበር እና የዘንድሮው አመት ምርጫ የሚቃወም ሰልፍ በአሰተርዮ ከተማ ተካሔደ ‼️
➨➨➨➨➨➨➨➨➨➨➨➨➨➨
የጥቁር ናዚው አብይ አህመድ አገዛዝ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ እና በማፈናቀል የስልጣን ዘመኑን የሚያራዝም ስርዓት ነው እናም ወደ ስልጣን የመጣበት መጋቢት 24/2018 ዓም የስምንተኛ አመት ሲሆን ለስምንት አመት ሁሉን አቀፍ ጭፍጨፋ እና ግድያ እንዲሁም መፈናቀልን እያስተናገደ ያለው የአማራ ህዝብ አሁንም በድጋሜ ግደለን ብለን የምርጫ ፍቃድ አንሰጠውም በማለት የተቃውሞ ሰልፍ የአስተርዮ ከተማ ህዝብ ድምፁን አሰምቷል ።
በመልክታቸውም :-
1. በድሮንና በመድፍ በየቀኑ ለሚሰቃይ ህዝብ ምርጫ ቅንጦት ነው !!
2. ምርጣው ለሌላ አምስት አመት የጭፍጨፋ ፍቃድ ማስገኛ ነው !!
3. ይህ ምርጫ ሳይሆን በህዝብ ስቃይ ላይ የሚተወን ድራማ ነው !!
4. አገዛዙ በኃይል እንጂ በምርጫ አይወገድም !!
5. በድሮን እየመቱ ድምፅ ስጡኝ አይባልም !!
6. ፍትህ ለታሰሩት እና ፍትህ ለሞቱት!!
7. ብልፅግና በቃን ! ኮረኔል አብይ በቃን!!
8. የህልውና አደጋ ለተጋረጠበት ህዝብ ምርጫ ብሎ መቀለድ እራስን ማታል ነው !!
አፋብን በ7ተኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ ላይ በሰጠው የእገዳ አዋጅ መሰረት በሽዋ ቀጠና ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ቀን 24/7/2018 ዓ/ም
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ግዙፉ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ነበልባሎቹ አምስቱም ክፍለ ጦሮች በተቆጣጠሩበት ቀጠና ህዝቡ በራሱ ተነሳሽንት ሰባተኛውን ሃገር አቀፍ ምርጫ በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በተቃውሞ አውግዘዋል።
ገዳዮቻችንን በምርጫ ካርድ አናነግስም ፥ በጨረቃ ምርጫ ለዳግም ባርነትና ለእልቂት ለብልፅግና ምቹ ሆኔታ አንፈጥርም ፥ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ነፍስ ጨፍጭፎ ለሞቱት ጥላ እዲሆን ችግኝ እንትከል የሚል መሪ ለምርጫ ሳይሆን የጦር ወጀለኞች ፍርድ ቤት መቆም አለበት።
በምርጫ ህጉ መሰረት ህዝቡ የምርጫ ካርድ የሚያወጣው በፍቃደኝነቱ እጂ በአፈሙዝ ተገዶ አይደለም፥ ባርነት በቃን ነፃነት እንፈለጋልን ፥ፋኖ የአማራ ህዝብ ነፃ አውጭ ታጋይ ነው። ከፋኖ ጋር ወደፊትነፃነት ለአማራ ህዝብ።ክብር ለኢትዮጵያውያን ።ተመራጭ የለም ምርጫም አይኖርም። የንፁሃን ሞት ይቁም የሽግግር መንግስት ይዋቀር ፥ገዳይ ስርዓት ይውረድ በማለት ሌሎችን መፈክሮች የያዙ የህብረተሰቡ ክፍሎች በመዘዞ ፥ በአንኮበርና በተሬ በሌሎችም ቦታዎች ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።
የብልፅግና አገዛዝ ምርጫ አስመራጭ ሰራዊት በመዘዞ ከተማ ህዝባዊ የምርጫ ተቃውሞ ሰልፉን ለማደናቀፍና ለመበተን ጣርማ በርና በደብረ ሲና ያስቀመጠውን ሰራዊት ቢያንቀሳቅስም ጀግኖቹ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ተሠማ እርገጤ ክ/ጦ 2 ሻለቃና አባት አርበኞች መዘዞ ክላስተር ሃይሌ ብርጌድ ተወሪዋሪ ሻለቃ አንድ በፊት ለፊት በቀኝ የዕዙ ተወርዋሪ ንስር ሻለቃ፥ በግራ በኩል የክፍለ ጦሩ ቃኘና የሁተኛ ሻለቃ ቃኘ በጋራ በመጣመር በጥላት ላይ የበላይነቱን በመውሰድ ጥላት አካባቢውን ጥሎ በመፈርጠጥ ወደ መጣበት ተመልሷል።
የበሌላኛው ቀጠና ብልፅግና ወንበር ጠባቂውና የውሽት ምርጫ አስመራጭ ሰራዊት መነሻውን ከመሐል ሜዳ ከተማ አድርጎ የምርጫ ምረጡልኝ ተልዕኮ ለማስፈፀም በጌራ ቀያ ወረዳ ወዠድ አድርጎ ወደ አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ወደ ዋሻ ንገት ጦርመሳያ ሲያመራ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር ሸጌ ሻለቃ ቃኘ፥ አያሌው መክት ሻለቃ ቃኘና የክ/ጦ ሞርተር ቲም ከወዠድ ቻይና ካፕ ተነስቶ ወደ ያምሳበር ሲንቀሳቀስ ደፈጣ በመያዝ ጨበጣ ተኩስ በመግጠምና በሞርተር ሽፋን በመታገዝ ጥላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተውታል። ድንገት የተፈጠረው የአየር ንብረት ጉም፥ ደመናውና ጭጋግ ከዚህ በላይ እዳይጎዳ ያደረገው ሲሆኖ ተፈጥሮውን ተገን አድርጎ ወደ ቻይና ካፕ ተመልሷል ፈርጥጦ ሄዷል።
የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር አምስቱም ሻለቃ ቃኘዎችና ሞርተር ቲም በአስደናቂ ጥምረትና መናበብ
በወዠድ፥ግሾጌ፥ሸበቶ፥አብሎሽ፥መቅደሳና አፍሶ ቀበሌዎች የገባውን ፀረ አማራ ወራሪ ሃይል ጉረሮ ለጉረሮ እየተናነቁት መቆሚያ መቀመጫ እያሳጡት ይገኛሉ።
ብልፅግና ለምርጫ ቅስቀሳ ሲል ያለ የለለ አቅሙን የሞት ሽረት እየተጠቀም ቢሆንም የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር የተቆጣጠረውን ቀጠና ብልፅግና በእግሩ ሊረግጣት አይገባም በማለት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ በማድረግ እዳይገባ አድርገውታል።
መረጃወን የክ/ጦ ህዝብ ግንኙነቶች አድርሰውናል።
፨ድል ለአማራ ህዝብ
፨ድል ለአፋብን
፨ክብር ለትግሉ ሰምአታት
፨አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን
+9
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201 ኮር 54 ክ/ጦር ዛሬ መጋቢት 24 አብይ አህመድ በአዲስ አበባ የከተማ ልደት በሚያከብርበት ቀን የመንበረ ግርፎች የተፈራ እና የመዝገበ ልጆች አንድን ሻለቃ የአብይ ጦር ዶግ አመድ አደረጉት።
ተሸናፊው የብልፅግና ሰራዊት '' የፋኖ ቤተሰቦችን" ታርጌት ያደረገ ነፃ እርምጃ ፈፀመ ።
መጋቢት 24/2018 ዓ.ም
መሬት ላይ በፋኖ ሃይሎች የተሸነፈው የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት ከፖለቲካ ጋር ፍፁም ግንኙነት የሌላቸውን ንፁህ ዜጎችን ጨፍጭፏል። በምርጫ እድሜውን ለማራዘም እየተፍጨረጨረ የሚገኘው አረመኒው የአብይ አህመድ ሥርዓት ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና በሜጫ ወረዳ ኩድሚ ጊዮርጊስ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው "የፋኖ አምላኬ ሰማኸኝ(ሙጅብ) አባት የሆኑት አቶ ሰማኸኝ ካሴን " ሀገር ሰላም ብለው በተቀመጡበት መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ በግፍ በጥይት ደብድቦ ገሏቸዋል ።
አገዛዙ ከአቶ ሰማኸኝ ካሴ በተጨማሪ 👇🏻
1ኛ. ዶ/ር ካሳሁን ተስፋ - የህክምና ባለሙያ
2ኛ. ፀጋየ - የባጃጅ አሽከርካሪ
3ኛ. ሰለሞን ሞላልኝ - ንፁህ ገበሬ መራዊ ገበያ ሁለት በሬ ሸጦ በመመለስ ላይ እያለ የሸጠበትን ከ150 ሺ ብር በላይ ከኪሱ አውጠው ወስደዋል።
4ኛ. ዮሐንስ ያዛቸው - የህክምና ባለሙያ
5ኛ. ሳሙኤል ግርማ - የህክምና ባለሙያ
የተባሉ ህይወታቸውን ለመቀየር ደፋ ቀና እያሉ ባሉበት ሁኔታ ጨፍጭፏቸው ሄዷል።
ይህ አረመኒ ሰራዊት ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር ያሳየበት መሆኑንም የህክምና ባለሙያዎችን ጭምር በመግደል አረጋግጧል።
➡️አዲስ ትውልድ!!
➡️አዲስ አስተሳሰብ !!
➡️አዲስ ተስፋ !!
ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አስደማሜውን አቋሙን በጀግኖቹ ልጆች ሊያበስርን ዝግጁቱን ጨርሷል!! አዲስ መረጃ ይኖረናል ሸርና ጆይን በማድርግ ይወዳጁን አላችሁ ውድ አማራዊያን የቴሌግራም ሊንካችን ይወዳጁን በድጋሜ!!
+3
በመላው አማራ የሚገኝ የማህበረሰብ ክፍል በአደባባይ በመውጣት የአገዛዙ የሐሰት ምርጫ መጋቢት 24/2018 ዓ.ም እየተቃወመ ይገኛል።
የአማራን ህዝብ በአማራነቱ ብቻ በድሮን እየገደላችሁ በሐሰተኛ ምርጫ ለቀጣይ 5 ዓመት ባርነት አንቀበልም በማለት እነማይ ወረዳ የቀበኃና እና ዴንሳ እነቆራ ቀበሌዎች ላይ ከባድ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂዶል።
#የድል_ዜና
የጀግናው የሻለቃ መንበሩ ጌጋዬ (መምቤ) ደም በእጥፍ ተመልሷል።
201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ድል ተቀዳጄ።
<>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
54ኛ ክ/ጦር ተወርዋሪ ኃይሏንና ሻለቆችን በጋራ በሰራው የተጠና ኦፕሬሽን ሞጣ ሙገር ከተማ ላይ በጠላት ላይ ድልን ተቀዳጄ
መጋ,24/7/2018ዓ/ም አነጋግ 11:45ሰዓት የተጀመረው ሞጣ ሙገር የነበረው የአብይ አህመድ ሰራዊትና ግብረአበሮቹ ወደ አመድነት ተቀይረዋል።
ምሽጉን በ3ደቂቃ ሰብሮ መግባት ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሁኖ የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጦ ወደ ከተማና ወደጫካ ፈርጥጧል። ከጫካ ለቀማ ላይ ነን
በዛሬው አውደ ውጊያ
👁
1➔የተደመሰሰ መከላከያ➔ 42
2➔የተደመሰሰ ሚኒሻ ➔ 29
3➔በእጅ የተያዘ 1ሻበል ባሻና 4መሰረታዊ ወታደር ይቀጥላል ከለቀማው (ጫቃ)😄
5➔ከ40በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ገቢ ተደርጓል።
ጭማሪ Loading --------------^^^^
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኮር 54ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት
+5
ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም "ሰላም ሳይኖር ምርጫ ሊኖር አይችልም:
ገዳዮቻችንን በምርጫ ካርድ አናነግስም" በሚል መሪ ቃል በመላው አማራ ክልል ምርጫውን የሚቃወም የህዝብ ድምፅ እየተስተጋባ ነው።
በደብረማርቆስ ዙሪያ በደብረ ዘይት ቀበሌ እየተካሄደ ያለ ትዕይንተ ህዝብ ነው።
#ሸዋ_መዘዞ_ከተማ👏
ዛሬ መጋቢት 24 2018 ዓ. ም "ገዳዮቻችንን፣ በምርጫ ካርድ አናነግስም፣ በጨረቃ ምርጫ ዳግም ለባርነትና ለእልቂት ለብልፅግና ምቹ ሁኔታን አንፈጥርም በማለት መላው የአማራ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጣ
"አበባው ለኔ... እሾሁ ለናንተ!"
አብይ አህመድ በቤተ-መንግስት ኮሪደር ላይ ስለ ብልጽግና ተረክ እያላዘነና የውሸት አበባ እያሳየን ባለበት በዚህ ቅጽበት፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ግን የኢትዮጵያን ካርታ በደም ቀለም ነክሮ "ሞት ይሸታችኋልና ዞር በሉ" ብሎ ዓለምን አስጠንቅቋል።
"እባብ ለጠላትህ፣ ርግብ ለወዳጅህ" እንደሚባለው ሳይሆን፣ የእርሱ አስተዳደር ለህዝቡ እባብ ሆኖ ለካሜራ ግን ርግብ ለመምሰል የሚሄድበት ርቀት መጨረሻም በነጩ ቤተመንግስት በአደባባይ ተጋልጧል።
ከአማራ እስከ ኦሮሚያ፣ ከትግራይ እስከ አፋር ያለውን ምድር የመከራ አውድማ አድርጎት ሳለ፣ እርሱ ግን አሁንም በፓርኮች ግንባታ ስም የሰቆቃችንን አቧራ ሊያብስ ይሞክራል።
"መሸጥ ካቃተው ነጋዴ በላይ ጩኸቱ አይሰማም" እንዲሉ፣ አብይና ግብረ-አበሮቹ "ሰላም ነው" ብለው ቢጮሁም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምስክርነት ግን የብልጽግናን ጭንብል አውልቆ ጥሎታል።
ሀገሪቱን በፈንጂ፣ በእገታና በጦርነት አረንቋ ውስጥ ዘፍቆ ስለ ሽርሽር ማውራት በቁም መቃብር ላይ የመጨፈር ያህል እብደት ነው።
ይህ የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ግልጽ መልዕክት አለው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ዓለምም የአብይን የቅዠት ጉዞ ሰልችቶታል። በመጨረሻም በቲቪ መስኮት የሚረጨው የብልጽግና ፕሮፖጋንዳ መሬት ላይ ባለው የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ እገዳ ድባቅ ተመትቶ ፍርክስክሱ ወጥቷል።
