ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 134
Subscribers
No data24 hours
+4247 days
+1 14930 days
Posts Archive
+2
#ጀግንነት፡ የደም እና የዘር አሻራ
ጀግንነት በድንገት የሚከሰት ሳይሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ በደም ውስጥ የሚፈስ ታላቅ ቅርስ ነው። አንድ ሰው ለሀገሩ፣ ለክብሩና ላመነበት ዓላማ በፅናት እንዲቆም የሚያደርገው ያ የጀግናው አባቱ ወኔና የደፋሯ እናቱ ወተት ነው።
#የዘር_ሐረግ እና ጀግንነት የደም ውርስ፡ የአንበሳ ልጅ አንበሳ እንዲሉ፣ ጀግንነት ከወላጆች ወደ ልጆች የሚተላለፍ የማይታይ ግን ጠንካራ ሰንሰለት ነው። የታሪካዊ ጀግኖች ልጆች በችግር ጊዜ የሚሳዩት ጥንካሬ ምንጩ ያ ተፈጥሯዊ የዘር ግንድ ነው።
#የተጋድሎ_ታሪክ፡ አንድ ትውልድ በመስዋዕትነትና በድል ውስጥ ሲያልፍ፣ ያንን ድል የማስጠበቅ ወኔ በዘሩ ውስጥ ተቀርጾ ይቀራል። ይህ "የጀግንነት ጂን" (Heroic Gene) በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ማንነትን ይወስናል።
#የመንፈስ_ጥንካሬ፡ ጀግንነት በልምምድ ብቻ የሚገኝ ሳይሆን፣ ከማንነት ጋር አብሮ የሚወለድ ነው። በፍርሃት ቦታ ወኔን፣ በመሸሽ ቦታ መጋፈጥን የሚመርጥ ልብ ከጥሩ ዘር የሚገኝ ስጦታ ነው።
"የጀግና ዘር መሆን ማለት በፈተና ወቅት የማይናወጥ የሞራል እና የልብ ጥንካሬን ከቀደምቶች መውረስ ማለት ነው።"
በመሆኑም ጀግንነት ዝም ብሎ የሚመጣ ሳይሆን፣ በደም ውስጥ የሚኖር፣ በዘር የሚተላለፍና በታሪክ የሚረጋገጥ የታላቅነት መገለጫ ነው። አርበኛ እንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሽዋ የአማራው ድምፅ አልባው ሚሳኤል
ተቋማዊነት (Institutionalism) እና ግለሰባዊ ፍላጎቶች ለድርጅታዊ መርሆዎች መገዛት ለድል ዋስትና ናቸው።
ድርጅት ማለት የብዙ ሰዎች ስብስብ ብቻ አይደለም፤ ድርጅት ማለት "የጋራ ሕግ፣ የጋራ ዕዝ እና የጋራ ራዕይ" የሚገዛው ሕያው አካል ነው። በአንድ ድርጅት ውስጥ ትልቁ "ንጉሥ" ሕጉና መመሪያው ነው። መሪውም ሆነ ተራው ታጋይ ለዚህ ሕግ እኩል ተገዢ ናቸው። ይህ ሲሆን ትግሉ የግለሰቦች "ንብረት" መሆኑ ያበቃና የሕዝብ "ተቋም" ይሆናል። ይኽም ማለት፤ ውሳኔዎች በግለሰቦች ስሜት ወይም በቡድን ፍላጎት ሳይሆን፣ በድርጅታዊ ምክክርና በስትራቴጂያዊ ጥቅም ላይ ተመስርተው መወሰን አለባቸው።
ማንኛውም የነፃነት ትግል ከስሜታዊነት ወጥቶ ወደ ስልታዊ ድል የሚሸጋገረው፣ በትግሉ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ለተቋማዊ መመሪያዎችና መርሆዎች ራሳቸውን ሲያስገዙ ብቻ ነው። ግለሰቦች ያልፋሉ፤ ድርጅት ግን የትግሉን ራዕይ ሰንቆ ለትውልድ ይሻገራል።
ትግሉ የሚገነባው ድርጅት የነገዋን ሀገር መልክ የሚወስን "ጥላ" ነው። ዛሬ በጦር ሜዳ ላይ ለሕግና ለተቋም የማይገዛ አመራር፣ ነገ ሀገር ሲይዝ አምባገነን መሆኑ አይቀሬ ነው። ስለዚህ ተቋማዊ አሰራርን ዛሬ በትግሉ መሃል ማምጣት፣ የሕዝቡን እጣ-ፋንታ በአስተማማኝ መሠረት ላይ ማስቀመጥ ማለት ነው።
ስለሆነም፤ እኛ ዛሬ የምንዋደቀው ለግለሰብ ዝና ወይም ለቡድን የበላይነት አይደለም። እኛ የምንዋደቀው የሕዝብን ነፃነት ለሚያረጋግጥ ዘላቂ ተቋም ነው። ግለሰቦች ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ፤ ድርጅቱ ግን እንደ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ መውለብለብ አለበት። በትግሉ ውስጥ ለሥርዓትና ለሕግ መገዛት ድልን ማፋጠን ብቻ ሳይሆን፣ ድሉን ቀጣይነት ያለው የማድረግ ምስጢር ነው።
አፋብንን ለመፍጠርም ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን በመምከር፣በመገሰፅ፣ አቅጣጫ በማስቀመጥ፣መመሪያ በማውጣት፣ የግል ፍላጎትን ለትግሉ በመተው፣ በዋናነት ከጥንስሱ እሰከ ፍፃሜው በርካታ መስዋዕትነት የከፈለ አለ። ዘመናትን ህልም የሆነውን ተቋም በመርህ፣በአሰራር ፣በህግ እና በራዕይ ለማነፅ የሁሉም መሪዎች ፣የተመሪዎች ፣የደጋፊዎች እና የህዝቡ ሚና ጉልህ ነውና ከግለሰባዊነት ከፍያለ እይታ እንዲኖረን ስል ጥሪየን አስተላልፋለሁ።
ግለሰቦች ለድርጅት፣ ድርጅት ለሕዝብ!
ትዕግሥት ፣ፅናት ፣ፍቅር ፣እምነት ፣እውነት።
ፅና!
እንኳን ለመድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !!!
ቀን 10/05/2018 ዓ.ም
የጥምቀት በዓል በአለማቀፍ ደረጃ በይኒስኮ የተመዘገበ እየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በሰላሳ (30) አመቱ በማየ ዮርዳኖስ ባህር በይኃንስ አጠመቀው የተጠመቀ ይድናል እኛም የእሱ ልጆች ወዶ በተወለደ በአርባ ቀን ሴት ደግሞ በተወለደች በሰማንያ ቀናችን እንጠመቃለን ።
የጥምቀት በዓልን ስናከብር በፍቅር በመተሳሰብ ዕሳቤ የተለያዩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ጨዋታወችን እንደ እየ አካባቢው እየተጫወትን እናከብራለን ታቦቶች ህጋችን ከምንግዜውም በተለየ መልኩ ክብረ በዓል ጥምቀት ለየት የሚያደርገው በየአድባራቱ ያሉት ታቦቶች ወጠው ክብረ በዓሉ በፍቅርና በጥበብ ይከበራል።
ይሄንን ተረድተን መላ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ አመራሮች እና ሰራዊታችን ይሄን በዓል በደመቀ መልኩ እዲከበር ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት መብታችን ሳይሆን ግዴታችን ነው።
በዓሉ በሰላም እዲከበር ሁላችንም የበኩላችንን እየተወጣን ለዚች ለተባረከች ቀን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን ለማክበር በኤፍራታና ግድም ወረዳ በጋዲሎ ሜዳ ለማክበር ሽር ጉድ ስትሉ ቆይታችሁ በ ድንገተኛ አዳጋ በመኪና ደርሶባችሁ በግምት ከ50-80 ሜትር ጥልቀት ገደል ገብታችሁ ምንም ሳይነካችሁ ለተረፋችው ወድሞቼ እና ለትግል ጓዶቼ እንኳን ለዚች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ።
1.አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ
2.አርበኛ (ሸበቶ) ሰይድ ደምስ
3.አርበኛ ሀብታሙ መሳፍት
4.አርበኛ ዋሲሁን በየነ
5.አርበኛ አክሊል
6. አርበኛ ዳንኤል
ለፈጣሪ የሚሳነው ነገር የለም ስድስቱ ወድሞቻችን በጋራ በአንድ ተሽከርካሪ ሲጓዙ ሁሉም በሰላም ተርፈዋል ከባድ ጉዳት እኳን የደረሰበት የለም ። ታጋይ ወድሞቻችን ሁላችሁም ክብረ በዓሉን አክብራችሁ ስትመለሱ የተሰው ወንድሞቻችን አስባችሁ እንደምትውሉ ተስፋ አለኝ።
መላ የክርስትና እምነት ተከታዎች እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ በሰላም እየተከበረ የዛሬ አመትም ሁላችንንም በሰላም ያድርሰን። አማራ የተበደለ የተጎዳ ህዝብ ነው !!!
ክብር ለተሰውት ጓዶቻችን !!!
የአማራን ህዝብ መዳኛ የፋኖን አድነት የአበሰርንበት ቀን መሆኑ መላ ሰራዊታችን እና ህዝባችን የተደሰተበት ቀን ነው ።
"ለመላ የክርሶትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራ ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ"
የሰው ልጅ ዕፀ-በለስን በላ፡፡ ከዚህም የተነሣ ሰው ሁሉ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ከፍዳና ከመርገም በታች ሆኖ መኖር ጀመረ፡፡ አምላክ መሀሪና ይቅር ባይ፣ ቸርና አዛኝ ነዉና የሰዉን ልጅ እንዲሁ-በነፃ ይታደገው ዘንድ ወደደ፡፡
የሰው ልጅም ወደ አምላኩ መልሶ ይታረቅ የደረግለት ዘንድ የልጅነት ስልጣንንም ያገኝ ዘንድ ከውሃና ከመንፈስ እንደገና መወለድ አስፈለገው፡፡
ዉድ የአማራ ህዝብ ሆይ አንተ ስጋና አጥንትህ በሰቆቃና መከራ የሚማስን ነፍስና መንፈስህ በጭንቀትና መረበሽ የሚባዝን ፍጡር እንኳን ለጥምቀት በአል አደረሰህ፡፡
በነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ይመስገን!
መፅሐፍ እንደሚለዉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰላሳ ዘመኑ በባህረ ዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ ተጠምቀ፡፡ በወቅቱም ሰው ሁሉ ይድን ዘንድ ዳግመኛ መወለድ እንዳለበት ለዚህም ደግሞ መጠመቅ እንደሚያስፈልገዉ ተናገረ፡፡ በዚህም የተነሣ የጥምቀትን ትምህርት ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰዉ ልጅ እንዳስተማረ እንረዳለን።
ምድራዊዉ ግፈኛ መንግስት አቃለለዉ፣ አዋረደዉ፣ ደግሞም በርኩሰቱ አረከሰዉ እንጂ አንተ የሀገሬ ህዝብ እማ ልክ እንደማንኛዉም ሰዉ አምላክህ ክብሩን ትቶ፣ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ የታደገህና የልጅነት ስልጣንን የተሰጠህ የተከበርክ ክቡር ፍጡር ነህ፡፡ ግና ምን ያደርጋል!? ሰማያዊዉ አምላክ ቤተ መቅደስ ብሎ የጠራህ የሰዉ ዘር አካል እንዳልሆንክ ሁሉ የምድሩ ገዢ ክብርህን፤ገፎ ስጋና ደምህን ለአለቃዉ ለዲያብሎስ ግብር ሲያቀርብ ይዉላል፡፡ አንድ ነገር እርግጥ ነው! አቤል ያፈሰሰዉ የቃየል ደም ከምድር ወደ ሰማይ እንደጮኸ ሁሉ በአብይ እና መሰሎቹ ሻጥረኞች አገዛዝ በከንቱ የሚፈሰው የአማራ ደምም እንዲሁ ነዉ! ደግሞስ የማን ትዐቢትና ጭካኔ ለዘላለም ፀንቶ ቁሞ ሰምተናል!? የሳኦል ወይስ የሞሶሎኒ???
በመሆኑም ይህንን በአዓል ስናከብር በትግላችን ቁርጠኝነት በእምነታችን ባለን ፅናት የተደገፈ በመሆኑ አለመናወጡን ከንቱም አለመሆኑን በኩራት ሀሴት እያደረግን ነው፡፡
ሁሌም ከጥምቀት በዓል በፊት የከተራ በዓልን መታደም የ ሀይማኖታችን ትዉፊት አካል ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ጥምቀት በአል ስነ-ስርዓት እንደ ድልድይ ለሚያሸጋግረን የከተራ በአል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለሁ፡፡ ከተራ የሚለዉ ቃል ከበበ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ቃል ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት እንደሆነ የቋንቋዉ ሊቃዉንት ያስረዳሉ፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ-ህጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፤ ዳስ ይጥላል፤የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆናቸው እንዲጠራቀም ይከተራል ፤ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡ የእኛም ትግል የከተራ ባህሪን የተላበሰ በመሆኑ እንሰበሰባለን፤ ዉሀዉ ለማብዛት ሰዎቹ እንዳደረጉት እኛም እንድንበዛ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ የተጠመቀው እንደ አይሁድ ሥርዓት ለመንጻት ወይም እንደ ዮሐንስ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት አልነበረም። ይልቁንም ከዚህ ለየት ያለ ያዉም በእለት ተእለት ኑሮአችን ስርአትና መመሪያ ሆነው የሚያገለግሉ በርካታ አስደናቂ ህግጋትን ሲያመለክተን ነው ፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተከታዮቹ አርአያ ይሆን ዘንድ የእጁ ፍጥረት በሆነው በአገልጋዩ በዮሐንስ እጅ ተጠምቋል። እራሱ ዮሐንስ እኔ በአንተ ልጠመቅ ይገባኛል እንጂ አንተ በእኔ እንዴት ትጠመቃለህ ብሎ በግርምትም ግራ በመጋባትም እስኪጠይቅ ድረስ እጅግ አስደናቂ ትህትናን አስተምሮናል፡፡ የእኛ የትግል መስመርም እርስ በርስ በመከባበር፣ ለህዝባችን ያለንን ፍቅርና ጥልቅ ስሜት በትህትናዊ ድርጊታችን በማሳየት ጌታ በመጨረሻም ዲያብሎስን ድል አድረጎ የሰዉን ልጅ ክብር እንደመለሰለት እኛም የአብይን እና ሻጥረኞቹን አገዛዝ እና የበላይነት ገርስሰን የአማራን ህልውናና ክብር እንመልሳለን፡፡
የክርስቶስ ኢየሱስ መጠመቅ የሚያሰተምረን ሁለተኛዉ ነገር አረአያነትን ነው፡፡ ጥምቀት ዳግመኛ ከእግዚአብሔር የምንወለድበት ማለትም የልጅነት ጸጋን የምንጎናጸፍበት ምሥጢር ነው። ያለጥምቀት የዘላለም ሕይወት እንደማይገን ሁሉ ያለመራራ ትግል የአማራ ክብርና ህልዉና አይመለስም፡፡ የሰው ልጅ ለመዳን መጠመቅ ስላለበት ክርስቶስ እራሱ በመጠመቅ አርአያ እንደሆነ ሁሉ እኛም መራራዉን ትግልና ጽዋ እየተጎነጨን ህዝባችንን ነጸ ለማዉጣት ፊት ለፊት እየተዋደቅን እንገኛለን፡፡ ታገሉ ማለትን ታግለን ተዋደቁ ማለትን ወድቀ አሸንፉ ማለትን አሸንፈን በማሳየት አማራን ወደ ክብሩና እኩልነቱ እናመጣዋለን፡፡
ዲያብሎስ አዳምና ሔዋንን ካሳተ በኋላ በጨለማ መጋረጃ ጋርዶ አገዛዙን አጸናባቸው። የእርሱ ባሪያዎች መሆናቸውን አምነው እንዲቀበሉና የባርነት ማረጋገጫ ደብዳቤ በዕብነ ሩካብ ጽፈው እንዲያመጡ ነገራቸው፡፡ ይህንን ቢያደርጉ የአገዛዝ ጭቆናዉ እንደሚቀልላቸዉና እንደሚጠቀሙ ሰበካቸዉ፡፡ እነርሱም ቃሉን ፈጸሙ፡ ሰይጣንም ጽሁፉን ወስዶ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱንም በሲኦል በር አኖረዉ፡፡ ፍቃደኛ ባሪያ ሆነዉ ሰቆቃና ስቃይ መቀበል ጀመሩ፡፡ ዛሬም በተራ ነገር እየተደለሉ ቋንጃዉ እንደተቆረጠ ባሪያ ከአገዛዙ እግር ስር ፍርፋሪ በመልቀም የተሰማሩ እነ ሆድ-አምላኩ ማፈሪያ ከርሳሞች በህዝባችን መሀል አሉ፡፡ ነገር ግን ልክ ጌታ በተጠመቀ ጊዜ ዮርዳኖስ ያለውን የዕዳ ደብዳቤ እንዳጠፋዉ፤ በሲኦል የነበረዉን ደግሞ በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ እንደደመሰሰዉ እኛም በሚስማማቸው መንገድና ቋንቋ እያነጋገርን እነዚህ ከሀዲያን ላይ የሰፈረዉን ርኩሰትና የተጠናወታቸዉን የእዳ ጽህፈት እናጠፋዋለን፡፡
እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት፣ ሦስት ሲሆን አንድ መሆኑ በዘመነ ብሉይ በሁሉም ዘንድ እንደ አዲስ ጎልቶ የማይታወቅ ምሥጢር ነበር። ሦስትነቱን በትምህርት ከመግለጡ በፊት በጥምቀቱ ወቅት በገሃድ እንዲገለጥ አድርጓል። ሦስቱ አካላት በአንድ ቅጽበት በአንድ ቦታ ማንነታቸውን ገልጠዋል፡፡ አንድነታቸዉና ሶስትነታቸው ረቂቅ የሆነ የአምላክ ባህረ ጥበብ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ምንም እንኳ ከስላሴ ባህሪ ጋር የሚስተካከል ነገር ባይኖርም በአሀዱና ሰለስቱ መካከል ያለዉ ዉህደት ዉስብስብነትና ጥንካሬ ፋኖ ከራሱ፣ ፋኖ እርስ በርሱ እና ፋኖ ከህዝቡ ጋር ካለው የማይገለጥ ጠንካራ ግንኙነት ጋር ይመሳሰላል፡፡ ሚስጥረ ስላሴ ረቂቅና ጥልቅ ጥበብ እንደሆነ ሁሉ የእኛም ግንኙነትና አንድነት እንዲሁ መሆኑን ለጠላቶቻችን አስረግጠን መናገር እንፈልጋለን፡፡
በመሆኑም የዘንድሮን ጥምቀት ስናከብር የትግላችንን መፋፋም እና የድላችንን መቃረብ ለህዝባችን እያበሰርን ነው፡፡ በመሆኑም ልክ እንደ ከተራ ተከትረን፣ እንደ ስላሴ ረቂቃዊ ዉህደት ፈጥረን፤ ትግልን እንደ-ጥምቀት መዳኛ አድረግን፣ መራራ ጽዋን በአረአያነት እየተጎነጨን፣ ብሎም ለህዝባችን ትሁትና መስዋእት እየሆን ወደ የማቀረዉ የአርነት ዘመን እንደምንደርስ እያረጋገጥን ነው፡፡
በጥምቀቱ መዳን እንደተረጋገጠ በትግላችንም ነጻነት ይረጋገጣል።
መልካም ከተራ
ጥር 10/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና!!
ደጃዝማች 4ኛ ኮር አጣናዉ ዋሴ ክፍለ ጦር በዛሬዉ ቀን 10/05/2018 ዓ.ም በመተማ ወረዳ ወዳንበሶ ቀበሌ ከጠላት ሀይል ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ በማድረግ የጠላትን ምሽግ በመስበር ወዳንበሶ ከተማን ቁጥጥር ስር አዉሏል።
በጠዋቱ የጀመረዉ ዉጊያ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ረመጡ ደጀን ክፍለ ጦር ወደፊት እየተጠጋ ይገኛል።
የአፋብን |ቴዎድሮስ ዕዝ አንድነቱን ምክንያት ድል ተቀዳጀደ
____፩
ጠላትን በደፈጣ መምታት ተችሏል!!!
በዛሬዉ እለት በቀን 10/05/2018 ዓ.ም በአማራ ፋኖ አንድነት ብስራት ማግስት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ በጠላት ላይ በወሰደችው የደፈጣ እርምጃ ከጃሂማላ ወደ ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ሲገባ የነበረን ሃይል ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት አካባቢ በርካታ ጠላትን መደምሰስ ችላለች።
____፪
206ኛ ኮር አንድነነቱን ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በደብረ ማርቆስ ከተማ በመሸገው የጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈፅሟል ።
በትናትናው እለት ይፋ የተደረገውን የአፋብን ምስራት ምክንያት በማድረግ ደስታቸውን ጠላትን በመደምሰስ አንድነቱን በድል የጀመሩት 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ሌሊቱን ደብረ ማርቆስ ከተማ በመግባት ጠላትን በተኛበት አፈር አልብሰውታል።
ከሌሊቱ 6:00 ጀምሮ በከተማዋ በመዘዋወር ጠላትን ሲያድኑ የነበሩት የኮሩ አዳኝ ቡድን በ4ኛ ፖሊስ ጣቢያ የቦንብ ጥቃት በማድረስ በርካታ ፖሊሶች ተገድለዋል ።
በአዲሱ ዩኒቨርስቲ እና ውሀ ጋኑ አካቢባቢ ተነጥፎ የነበረው የአረመኔው ሰራዊት ባልጠበቀው ስዓት በደረሰበት ጉዳት ብሬን ኳሹን ጨምሮ በርካታ የሰራዊት አባላት መገደላቸው ታውቋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ጥር 10/2018 ዓ.ም
206ኛ ኮር አንድነነቱን ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በደብረ ማርቆስ ከተማ በመሸገው የጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈፅሟል ።
ጥር 10/ 2018 ዓ.ም
===================================
በትናትናው እለት ይፋ የተደረገውን የአፋብን ምስራት ምክንያት በማድረግ ደስታቸውን ጠላትን በመደምሰስ አንድነቱን በድል የጀመሩት 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ሌሊቱን ደብረ ማርቆስ ከተማ በመግባት ጠላትን በተኛበት አፈር አልብሰውታል።
ከሌሊቱ 6:00 ጀምሮ በከተማዋ በመዘዋወር ጠላትን ሲያድኑ የነበሩት የኮሩ አዳኝ ቡድን በ4ኛ ፖሊስ ጣቢያ የቦንብ ጥቃት በማድረስ በርካታ ፖሊሶች ተገድለዋል ።
በአዲሱ ዩኒቨርስቲ እና ውሀ ጋኑ አካቢባቢ ተነጥፎ የነበረው የአረመኔው ሰራዊት ባልጠበቀው ስዓት በደረሰበት ጉዳት ብሬን ኳሹን ጨምሮ በርካታ የሰራዊት አባላት መገደላቸው ታውቋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
በመላው አማራ የድሮን ቅኝት የተካሄደና እየተካሄደ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ብርሸለቆ ቀጠናና አካባቢው በስፋት ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ ጥንቃቄ አይለየን‼️
10/ዐ5/2018 ዓ.ም
ፋኖው ጀነራል ተፈራ ማሞ
**
👉በኢህዴን ዘመን የኮማንዶ ስልጠና ወስዶ የጓድ መሪ ሆነ።
👉 ከእዚያም የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገቡ የኮማንዶ መቶ መሪ ሆነ:: የተሰጠዉን ግዳጅ በብቃት ስለተወጣ የእግረኛ ኃይል አዛዥ ሆነ ።
👉የሻለቃ አዛዥ
👉የክፍለ ጦር ም/ክ አዛዥ
👉የክፍለ ጦር አዛዥ
ከድል በኋላ ደግሞ
👉የፓራ ኮማንዶ አዛዥ
👉የ21ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ
👉የ33ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ
👉የ108ኛ ኮር ምክትል አዛዥ
👉የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ሆኖ በመፈንቅለ መንግስት እስከ ታሰረበት ጊዜ ድረስ አገልግሏል !!
አሁን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወታደራዊ አዛዥ በመሆን ኃላፊነት ተሰጥቶታል !!
እንድታደርጉ ጥሪ እያቀረብን በእኛ በኩል አስፈላጊውን ትብብር እንደምናደርግ ልናሳውቅ እንወዳለን።
፮) መልዕክት ለመለዮ ለባሹና ሚሊሻ
የአገዛዙ የስልጣን ምንጭ ህዝብ ሳይሆን የመለዮ ለባሾች ደም እንደሆነ ለእናንተ የተሰወረ አይደለም፡፡ አገዛዙ የስልጣን እድሜውን እስካራዘመለት ድረስ ለህይዎታችሁ ደንታ የሌለው መሆኑም ከእናንተ የተሰወረ አይደለም፡፡ የፋኖ ትግል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተከብሮ የሚኖርባት ሀገር መገንባት፣ የእናንተ መለዮ ለባሾች ደህንነት እና ክብር ተጠብቆ ሀገራችሁን እንድታገለግሉ የምትከፍሉት የህይወት መስዋዕትነትም ትርጉም እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ ሞታችሁ ለሀገራችሁ ሳይሆን ለአንድ በሰው ደም ለማይጠረቃ አገዛዝ መሆኑን ተረድታችሁ ወደ ፋኖ ትግል እንድትቀላቀሉ ጥሪ እያቀረብን ሙሉ መዋቅራችን ከመቼውም ጊዜ በተለዬ እናንተን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለድርጅታችን ሞስረታ ስኬት ለተጉ ሁሉ የላቅ ክብር ያለው መሆኑን እየገለጽን በተለይም ፦
1) ለመላው የአማራ ህዝብና ለሃገር ወዳድ ኢትዮጲያውያን፤ ለማይቋረጠው ልባዊ ድጋፋችሁና ለምክራችሁ፥ ለግሳፂያችሁ እናመሰግናለን። ልፋታችሁ ይህን አንድነት ወልዷል።
2) ለመላው ፋኖ አባላት፤ ለፍፁም ንፁህ ጓዳዊ ግፊታችሁ እና አንድነት ናፋቂነታችሁ እናመሰግናለን። የእናንተ የቀን ከሌት ጉትጎታና ውትወታ ባይኖር ሰንፈን የምንዝል አንታጣም ነበር። ደማችሁም ግፊታችሁም አንድነቱን ወልዷል።
3) ለመላው የሁለቱ ድርጅቶች አመራሮች፤ በተለይ በዚህኛው የአንድነት ሂደት ላሳያችሁት አመራርና ቁርጠኝነት ከፍተኛ ምስጋና ይገባችኋል።
በተለይ የአንድነት ሂደቱን ያሳለጣችሁ የሁለቱ ድርጅቶች የቴክኒካል ኮሚቴ አባላት እጅግ ታላቅ ክብር ይገባችኋል። ያሳያችሁት የአመራር ብቃት፥ ጥበብና መፍትሄ አፍላቂነት ልዩ ነበር።
4) ሂደቱን ለታዘቡ ሽማግሌዎች፤ በልኡል አስፋወሰን አስራተ ካሳ የሚመራው አምባሳደር ብ/መስቀል ነጋ እና ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ሰባት አባላትን ያካታተው የታዛቢወች ቡድን ሂደቱን በገለልተኛነት በመከታተል ፣ ቴክኒካል ኮሚቴው በጠየቃቸው ጊዜ ሁሉ የመፈትሔ ሀሳብ በማቅረብ ላደረጉት አስተዋጽኦ ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን።
በመጨረሻም ድርጅቱን ለማዋለድ ከተከፈለው መስዋዕትነት ባልተናነሰ ድርጅቱን በዘላቂነት ለማጽናት የሚገጥሙ ፈተናዎችን ለማሸነፍ ከላይ የተጠቀሳችሁ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ገንቢ ሚና እንድትጫወጡ ታሪካዊ ጥሪ እናቀርባለን።
አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር፤ አርበኛ መከታው ማሞ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፤ አርበኛ ሐብቴ ወልዴ ምክትል ሊቀመንበር ለወታደራዊ ጉዳዮች፤ አርበኛ ሔኖክ አዲሴ ምክትል ሊቀመንበር ለፖለቲካዊ ጉዳዮች በማድረግ ሰይሟል።
እንዲሁም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ከታች ለተዘረዘሩት መምሪያዎች አመራሮችን መድቧል፦
ወታደራዊ አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ
ም/ወታደራዊ አዛዥ - አርበኛ ምሬ ወዳጆ
ም/አዛዥ ለወ/አስተዳደር - አርበኛ ዝናቡ ልንገረው
ወ/ስልጠና መምሪያ - አርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል
ልዩ ዘመቻ - አርበኛ ድርሳን ብርሀኔ
ዘመቻ መምሪያ - አርበኛ ባዩ አለባቸው
ፖለቲካ መምሪያ - አርበኛ ጌታ አስራዳ
አደረጃጀት መምሪያ - አርበኛ ምንተስኖት ወንድአፈራሁ
ድርጅት ጽ/ቤት - አርበኛ አስቻለው በለጠ
የህዝብ ግንኙነት - አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
የህዝብ አስተዳደር መምሪያ - አርበኛ ዘመነ ምህረት
ፋይናንስ እና ግዢ አስተዳደር - አርበኛ አሻግሬ ባዬ
ፖሊሲ እና ስትራቴጂ - አርበኛ እስክንድር ነጋ
አጋርነት እና ትብብር - አርበኛ አበበ ፈንታው
የውጭ ጉዳይ መምሪያ - አርበኛ ብሩክ ስለሺ
በዚህ ታሪካዊ እለት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቀጣዮችን መልዕክቶች ያቀርባል።
፩) መልዕክት ለድርጅታችን ሠራዊት፦
ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈልክበት ያለው ትግል ፍሬ እንዲያፈራ እና የተሟላ አሸናፊነት እንዲረጋገጥ የአደረጃጀት አንድነት የግድ እንደሆነ በተደጋጋሚ የተነሳው ሀሳብ ተገቢውን መልስ አግኝቶ የፋኖ አንድነት ተበስሯል። ይህ ትልቅ የምስራች የሚያስገኘውን ተጨማሪ አቅም በመጠቀም በጽናት እና ቁርጠኝነት ትግሉን እንድትቀጥል ጥሪ እናቀርባለን። በትግል ሂደት አዲሱ ትውልድ በብሔራዊ ቁጭት እና ንቃት ያገኘውን የአስተሳሰብ አቅም በመጠቀም ውስጣዊ ትግል የሚፈልጉ ነባር ዕክሎችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ መታገል እንዲቀጥል እያሳሰብን የድርጅት ውህደትን ተከትሎ ለሚመጡ የመዋቅር እና የአሰራር ማሻሻያዎች ተገቢውን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በቅንነት መተባበር አስፈላጊ እንደሆነ እንገልፃለን። በተጨማሪም በየደረጃው ያለው መዋቅር ለቀጣይ ግዳጆች የሚያስፈልገው ወትሮ ዝግጁነት እንዲያረጋግጥ በጥብቅ እናሳስባለን።
፪) መልዕክት ለህዝባችን ፦
የትግሉ ደጀን የሆነው ህዝባችን በመድረኮች ሲያቀርብ ለነበረው የአንድነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን በድጋሚ እያበሰርን እስካሁን ትግሉን በባለቤትነት በመውሰድ በትዕግስት የድርሻውን ሀላፊነት ወስዶ የፈጸመውን ትልቅ ብሔራዊ ጀብድ የአንድነትን ጉልበት ተጠቅሞ አንደ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል እናሳስባለን።
፫) መልዕክት ለአማራ ዲያስፖራ፦
በተለያዩ የአለም ክፍል የሚገኘው የአማራ ዲያስፖራ በትግሉ መጀመሪያ ወቅት ሲያደርገው የነበረው የነቃ ተሳትፎ በሂደት በተፈጠሩ የአመለካከት መዛነፎች እና ጣልቃ ገብነቶች በተለይም የአደረጃጀት አንድነት ባለመምጣቱ ምክንያት በነበረው ግለት አለመቀጠሉን እና አቅሙን ተጠቅሞ ትግሉን በሚገባው መልክ ማገዝ አለመቻሉን አስተውለናል። ሆኖም ሠራዊቱ ፣ ህዝቡ እና አብዛኛው ዲያስፖራው በጉጉት ሲጠብቀው የቆየው የፋኖ አንድነት ተጠናቆ ውህድ ድርጅት ለመመስረት በቅቷል። በዚህም እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ለቀጣዩ የትግል ምዕራፍ ከእናንተ የሚጠበቀውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲያስችል በራስ ተነሳሽነት የአደረጃጀት አንድነት ከመፍጠር በተጨማሪም ትግሉን አስመልክቶ ከድርጅታችን የሚሰጡ አቅጣጫ እና መመሪያዎችን በቅንነት እንድትተገብሩ ከወዲሁ እናሳስባለን።
፬) መልዕክት በጸረ አገዛዝ የትግል መስመር ላሉ ብሔራዊ የትግል ሀይሎች እና የማህበረሰብ ክፍል፦
ሃገራችን አሁን ባለችበት ነባራዊ ሁኔታ በይፋ የዘር ፍጅት ያልታወጀበት እና የህልውና አደጋ ያላንዣበበት ኢትዮጲያዊ ወገን አለ ብለን አናምንም። ሁሉም ህዝብ ህልውናው አደጋ ውስጥ ነው። ኢትዮጲያ የገደል ጠርዝ ላይ ናት። በመሆኑም የፋኖ ትግል ለአማራ ህዝብ ህልውናና ለሌሎች ኢትዮጲያውያን ወገኖችም ጭምር ፖለቲካዊ መዳን ወሳኝ መፍትሄ ያዘለ ነው። የአማራ ድል ለጉራጌውም፥ ለትግሬውም፥ ለኦሮሞውም፥ ለጉምዙም፥ ለአፋሩም፥ ለሶማሌውም፥ ለወላይታውም፥ ለሲዳማውም፥ ለጋሞው እና ለሌሎችም ህዝቦች ድል ነው። በመሆኑም ሁሉም የፖለቲካ ቡድኖች እና ልሂቃን በጋራ በመቆም ለጋራ እጣ ፋንታ መታገል ይኖርባቸዋል። የዳር ተመልካች መሆን ለወረፋ ጥቃትና ጥፋት ይዳርጋልና።
አብይ የአፍሪካ ቀንድ ሹል ቀንድ ነው። ሁሉንም እየወጋ ሁሉንም እያደማ ነው። ሁሉንም የቀጠናው ህዝቦች ቤት በእጁም በእግሩም እየረበሼ ነው። ስለሆነም ዘር አጥፊውን የአብይ አህመድ አገዛዝ ለማስወገድ ኢትዮጲያውያን ወገኖች ብቻ ሳይሆኑ የቀጠናው ሃይሎች መተባበር አለባቸው። ይህን አገዛዝ ለማስወገድና ቀጠናውን ለማረጋጋት የሚደረጉ ትብብሮች በሙሉ ልክ ናቸው። የቀጠናው ህዝቦች ረፍትና ልማት ይሻሉ።ይገባቼውማል።
አረመኔው አገዛዝ የሚከተለው ከፋፍሎ የማጥቃት እና የማስጠቃት ስልት ጊዚያዊ የስልጣን ዕፎይታ የፈጠረለት ቢሆንም ይህንን በመገንዘብ በትብብር አገዛዙን በማስወገድ ላይ የታዩ መግባባቶችን ማሳደግ እና የአገዛዙን ዕድሜ ማሳጠር አስፈላጊ ነው። ለዚህም የፋኖ አንድነት የፈጠረውን ተጨማሪ አቅም እና ዕድል እንዲሁም በእስካሁኑ ሂደት በጸረ አገዛዝ ትግል አስፈላጊነት ላይ የታዩ መግባባቶች የተሟላ በማቀናጀት የዘር ማጥፋት ጦርነት ከመመከት ወደ ስትራቴጂካዊ ማጥቃት በመቀየር አገዛዙን ለማስወገድ እንድንሰራ ጥሪ እናቀርባለን።
፭) መልዕክት ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ ፦
አብይ አህመድ መሩ የብልጽግና አገዛዝ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ላሉት ወደ ስምንት ለሚጠጉ አመታት በህዝቦች ላይ ከፍተኛ እልቂት መፈጸሙ እንደሚታወቅ እሙን ነው። አገዛዙ ሀገሪቱን የማያባራ ጦርነት ውስጥ በማስገባት በሁሉም ክልሎች ከፍተኛ ሰብአዊ ውድመት፣ ኢኮኖሚያዊ ድቀት እና ማህበራዊ ቀውስን አስከትሏል። ይህ አገዛዝ ጸረ ህዝብ በመሆኑ ችግሩ የማይታከም፣ ከስህተቱ የማይማር እና አንዳች ተአማኒነት ያልታየበትም ነው። የአገዛዙ የጦረኝነት ባህሪ ከኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግርነት አልፎ ቀጠናዊ ሰላም እና መረጋጋት ላይ ተጨባጭ አደጋ ከፈጠረ ውሎ አድሯል። አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀው የዘር ማጥፋት ጦርነት እና የተከሰተው የህልውና አደጋ ጦርነቱን ከመቀልበስ ውጭ ሌላ አማራጭ ባለመኖሩ ፋኖ በህዝባዊ የትግል መስመር አገዛዙን ላለፉት 30 ወራት እየታገለም ይገኛል። ከፋኖም በተጨማሪ ሌሎች ጸረ አገዛዝ ብሔራዊ ሀይሎች በዚህ ህዝባዊ የትግል መስመር ውስጥ የህዝባቸውን ህልውና ለማረጋገጥ በትግል ላይ ይገኛሉ።
ይህን ህዝባዊ፣ ሀገራዊ ብሎም ቀጠናዊ አደጋ ማስወገድ እና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ብሎም ተራዛሚ ቀጠናዊ ጦርነቶችን ማስወገድ አለምአቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነም እናምናለን። ከዚህም በመነሳት ጸረ ህዝብ እና ጸረ ሰላም ለሆነው የብልጽግና ሀይል የሚደረገውን ድጋፍ በማቆም እንዲሁም አስፈላጊውን ጫና በማድረግ የአገዛዙን የጥፋት አቅም በማሳጣት እንድትተባበሩ ጥሪ እናቀርባለን። በተጨማሪም የፋኖን እና የሌሎችን የጸረ አገዛዝ ትግል የሚያደርጉ ሀይሎችን ትብብር በተቻለው አቅም እንድትደግፉ ጥሪ እናቀርባለን። የዕርዳታ ድርጅቶችም በጦርነቱ ለተጎዳው ህዝባችን አስፈላጊውን ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስለት የሚቻለውን
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
ጥር 09 2018
እነሆ ዛሬ ጥር 09 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያን እና ቀጠናውን የሚያተራምሰው የብልፅግና ቡድን እስትንፋስ የሚፈልቅበትን ሸለቆ የሚዘጋ ታሪካዊ ውሳኔ ወስነናል። ጓዶቻችን ለከፈሉት መስዋዕትነት የሚመጥን ተልዕኮን መከወን ግዴታችን የሆነ እኛ የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች አመራሮች የአብይ አህመድ የስልጣን እድሜ የሚበቅልበትን ንቃቃት በፍፁም ወንድማማችነት እና አንድነት ደፍነነዋል። የአማራ ትግል አንድ ይሆን ዘንድ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል እና የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት አመራሮች ድፍረትን፣ ሆደ ሰፊነትን፣ ቆራጥነትን እና ለህዝብ መታመንን በሚጠይቀው ታሪካዊ ውሳኔያችን የፋኖን አንድነት እውን ማድረግ ችለናል። ለመላው የአማራ ህዝብ እንዲሁም ለመላው ኢትዮጲያውያን እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን‼ አንድ መሪ፣ አንድ ድርጅት ሰይመናል።
አሁን ወደ ስትራቴጅካዊ ግባችን የሚወስደን ምእራፍ ወለል ብሎ ተከፍቷል። ሜዳውም ፈረሱም በእጃችን ሆኗል።
እንደ ብዙዎቹ ነባር የዓለም ስልጣኔወች ሁሉ ለረጅም ዘመናት በታሪካዊ መሰናክሎች ያልተደናቀፈ ቅብብሎሽ ያለው የግርማዊ ትላንት የታሪክ ባለቤት የሆነው የአማራ ሕዝብ እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቶዎች ለሚበልጡ ዓመታት በተለይም ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የስልጣኔ ግጭት በወለደው የትውልዶች ጦርነት እየተፈተኑ ይገኛሉ። በዘመናዊው ታሪካችን በቀጥታ አማራን ዒላማ ያደረገው ተከታታይ ዘመቻ በውስጣዊ ድክመቶቻችን ታግዞ ሁሉንም ህዝቦች በተገቢው መልኩ አሳታፊ ባልሆኑ የአሸናፊዎች ስርአት ሀገራችን ያልተረጋጋና እና የመፍረስ ስጋት ያለባት ሀገረ መንግስት ሲያደርግ ህዝባችንንም ለከፋ የመጥፋት (ህልውና) አደጋ አጋልጦታል። ይህንን በራሳችን ወገኖች ኢትዮጵያዊያን ባለቤትነትና ቅጥረኝነት የሚመራ ውስብስብ ሀገራዊ እና ህዝባዊ አደጋ ለመረዳት እና የጋራ መግባባት ለመፍጠር ብሎም መፍትሔ ለማበጀት ብዙ ማገዶ ፈጅቷል።
የአማራ ሕዝብ ራሱን በመዘንጋትና ሀገሩን በማስቀደም እየኖረ በራሱም ሆነ በሀገሩ ላይ የተፈጠረውን ታላቅ ተቃርኖ በጊዜው ባለመረዳቱ ራሱን ያገኘው ሀገሩን ተነጥቆ ሀገር አልባ ሆኖ እንዲሁም መንግስት መር በሆነ የዘር ማጥፋት በከፋ የመጥፋት አደጋ ውስጥ ሆኖ ነው። በእርግጥ አማራው በመጥፋት ላይ ያለ ህዝብ ነው። ይህንን ህዝባዊ አደጋ ለመቀልበስ ብሎም ሁለንተናዊ ህዝባዊ ጥቅሞቹን ለማስከበርና አዲስ ስልጣኔ ለመገንባት አዲስ አማራዊ አብዮት በማካሄድ ላይ እንገኛለን። የዚህ ህዝባዊ ቁጣ መነሻ ምክንያት የህልውና አደጋው ቢሆንም አደጋውን ከመቀልበስ ባሻገር ግዙፍ ራዕይ የቀነበበ ህዝባዊና ሀገራዊ እንዲሁም ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ መሻቶችን ቀርጿል።
የአዲሱ የአማራ ልሂቅ ራስ ጠል ዕሳቤ እና ባህል፣ የህዝባችን ፖለቲካዊ ድብታ እና ራስን ማግለል፣ በጥገኝነት በራስ ህዝብ ላይ የመቆመር ዝንባሌ፣ ያልተደራጀ እና የማይተመማን ፖለቲካዊ ማህበረሰብ መፈጠር፣ በጠላት ፍላጎት ልክ የተቀረጹ መጥፎ ኤሊቶች የስልጣን ወንበር ይዘው አማራን እንዳይደራጅ መከልከል/መከላከል እንደ ህዝብ የመጥፋትን ስጋት ላስከተለ የህልውና አደጋ አጋልጠውናል።
ይህን የገጠመንን እንደ ህዝብ የመጥፋት አደጋ ለመቀልበስ ስንነሳ ብሎም ለብዙ አስርት አመታት ያጣነውን በራስ ሀሳብ መደራጀት ማስመለስ ተከትሎ ከመጥፋት ለመዳን የሚያስችለንን ትግል ማድረግ ችለናል። ትግሉም ስደተኛውን ፖለቲካችንን ህዝባዊ በሆነ ዕሳቤ እና አደረጃጀት መሬት ላይ በመተከሉም ሊጸና ችሏል።
እንደ ማህበረሰብ ያጋጠመን ውስጣዊ የመበስበስ አደጋ ትግሉ በተፈለገው ፍጥነት እንዳያድግ እና ወደ ስትራቴጂካዊ አሸናፊነት እንዳያመራ በእጅጉ ፈትነውናል፡፡ ጠላቶቻችን በየጊዜው የተቃርኖ ቅኝትን ወደ ውስጥ በማስረግ ብሔራዊ አንድነታችንን ፈትነውታል። ይሁንና አዲሱ ትውልድ በፍጹም ብሔራዊ ቁጭት በመነሳት ይህን ፈተና በጀግንነት ተጋፍጦታል። አሸንፏልም። በዚህም ከውድቀት የሚነሳበትን እና ከልዩነት ግርዶሽ ወደ በብሔራዊ አንድነት በመሻገር ህዝባዊ አሸናፊነት የሚያረጋግጥበትን ብሔራዊ ንቃት ተጠቅሞ የአደረጃጀት አንድነትን በትግል ለማሳካት ችሏል።
ባለፉት ጊዜያት ባልተማከለ አደረጃጀት በቁርጠኝነት በተከፈለው የህይወት መስዋዕትነት የተገኙ ድሎች የአገዛዙ የስልጣን ምንጭ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊት በማፈራረስ አገዛዙን ተራ የአራት ኪሎ ሸማቂ እንዲሆን አድርገነዋል፡፡ ትግሉ ያልተማከለ አደረጃጀት ስልትን መጠቀሙ ተለዋዋጭ እና ለአገዛዙ እንዳይመች በማድረግ በአጭር ጊዜ አገዛዙን በማያንሰራራበት ደረጃ ማዳከም ተችሏል፡፡ የአገዛዙን ጀነራሎች የጦር አዛዥነታቸውን እረስተው ምላሳቸው ብቻ የቀራቸው ተራ ካድሪዎች አድርገናቸዋል፡፡ የትግሉ መጀመሪያው ምዕራፍ በድል በመጠናቀቁ የአገዛዙ ሰራዊት በመፈራረሱ ፋኖ ወደ ተተኪ ሰራዊትነት ማደግ ስላለበት እና ፖለቲካውን አደራጅቶ መምራት በማስፈለጉ አንድ የፋኖ አደረጃጀት ለመፍጠር በተደጋጋሚ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በሂደቱም የትግሉ የዕድገት ደረጃ የራሱን ድርሻ የሚወስድ ቢሆንም ነባር የተቃርኖ ቅኝቶች እና ሰራጊ የፍላጎት ቡድኖች ጣልቃ ገብነት እና መርዛማ የጠላት እጆች ዋና ፈተናዎች ነበሩ፡፡ እነዚህን ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮችን ተቋቁመን በዚህ የተባረከ ቀን ዛሬ የአንድነት ሪቫን ተቆርጧል።ፋኖ አንድ ሆኗል።
በድጋሜ እንኳን ደስ ያለን‼
በዚህ የአደረጃጀት አንድነት የአማራ ትግል ነባር እና ብልሹ ራስ ጠል እና በታኝ ዕሳቤ እና አሰላለፎችን አሸንፏል። ጎታች ከሆኑ አሰላለፎች በመላቀቅ የውድቀትን ረግረግ በብሔራዊ ንቃቱ ተሻግሯል። በሠራዊቱ እና በደጀኑ ህዝብ ውስጥ ሲብሰለሰል የኖረውን ጥያቄ መልሷል፡፡ በአማራ አንድነት ላይ የነበሩ የተሳሳቱ እና አሉታዊ ምልከታዎችን አርሟል።
ዛሬ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)/ሲመሰረት በቀደሙ የአደረጃጀት አንድነት የማምጣት ሂደት ወቅት የታዩ ድክመቶች እና ክፍተቶችን በማረም እንዲሁም የሁሉንም ባለድርሻዎች ተሳትፎ እና ትምምን በመፍጠር ጭምር ነው። ይህ ውህድ ድርጅት የአላማ እና የአስተሳሰብ አንድነት ላይ የተመሠረተ ነው። በዚህም ድርጅታችን የሚመራበት ርዕዮተ አለም "የአማራ ብሔርተኝነት" ሲሆን ይህም የወቅቱን የህልውና ትግል ከማሸነፍ ጀምሮ በዘላቂነት የህዝቡን ህልውና እንዲሁም ማንነቱን በማረጋገጥ መብት እና ጥቅሞቹን ለማስከበር የምንታገልበት የአስተሳሰብ ቅኝት ይሆናል። የአማራ ብሔርተኝነት በራስ በቅነት ሁለንተናዊ ውስጣዊ አቅምን በመገንባት በሀገራዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ማዕቀፍ ውስጥ የህዝባችንን ህልውና በማረጋገጥ መብት እና ጥቅሞቹን በማስጠበቅ የሌሎች ኢትዮጵያውያን የቡድን እና የግለሰብ መብቶች የሚከበርበት ስርዓት በማንበር በፍትሀዊ እና ሰላማዊ አብሮነት የሀገር ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚተጋ ነው።
በርካታ ቀናትን በወሰደ ጥልቅ ፖለቲካዊ ውይይቶች፣ ቅንነትን እና ወንድማማችነትን ያስቀደመው የድርጅት ምስረታ ሂደት በርካታ ምዕራፎችን ያለፈ ነው። የመግባቢያ ቃል ኪዳን ሰነድን በመፈራረም የተጀመረው ሂደት የድርጅቱን መመስረቻ ሰነድ (ሕገ ደንብ) በማፅደቅ እና ከፍተኛ አመራሩን በመሰየም በስኬት ተጠናቋል። በዚህም መሰረት
ለምን እና እስከምን ድረስ እንዲሁም እንዴት መታገል እንዳለበት ጠንቅቆ የተረዳ፣ የበቃና የነቃ ኃይል ነው።.....የዐምሓራ ፋኖ!
👉የትግሉን ማርሽ ቀያሪ የምስራች ትሰሙ ዘንድ ሰአቱ አሁን ነው!
ፍኖተ አማራዊያን ነን መረጃ አጥማጆች!
የቴሌግራም ገፃችን👉
