ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more3 641
Subscribers
+2024 hours
+3787 days
+1 08530 days
Posts Archive
ያ የበሻሻው ጨቅላ፣ ትላንት ፊቱ ላይ የተስፋ መቁረጥ ጥላ አጥልቶ ታየ። የሥልጣን መንበሩ እንደ ሸክላ ሲሰነጠቅ የታየው ይመስል፣ በሰራዊት ታጥሮ ወደ ወለጋ አቀና። በዚያም የፍርሃትና የክፋት መርዝ የታጨቀበትን ንግግር ለሕዝቡ አፈሰሰ። "አማራና ትግሬ ተባብረው መንበራችሁን ሊቀሙባችሁ ነው፤ ተነሱ፣ መክቱ!" እያለ የገዛ ወገኑን በጥርጣሬ ሰይፍ ሊያስታጥቅ ሞከረ። ትላንት በወለጋ የፈሰሰውን ደም ከትግራዩ እልቂት ጋር እያነጻጸረ፣ "እኛ የፈጀነው ይበልጣል" ብሎ ሲፎክር አንደበቱ አልተሳሰረም ነበር። የሰው ልጅ ትውስታ አጭር ይመስለዋል፤ ነገር ግን ያ የፈሰሰው ደም ገና አልደረቀም።
የኦሮሞ ሕዝብ ግን ቆም ብሎ ማሰብ ይኖርበታል። እነዚህ ኃይሎች የሚመጡት ለሕዝቡ ሳይሆን፣ ለዚያ ለበሻሻው ልዑልና ለኦህዴድ ወንበር እንደሆነ ሊገነዘብ ይገባል። "የሰራኸውን በደል ዋጋህን ክፈል" ሊለው እንጂ፣ ሕዝቡን ሊወጋ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በተለይ ደግሞ በምቾት ዓለም ውስጥ ሆነው "መሪ ነን" የሚሉ ድሬዎችና የሜንጫ አቀንቃኞች፣ ይህንን እውነት በድፍረት መናገር ካልቻሉ የታሪክ ተጠያቂዎች ይሆናሉ። አብይ አህመድ ወደ የትኛውም አቅጣጫ ሲንቀሳቀስ፣ ከጀርባው የአማራን መሬት የማጥፋትና የመቆራረስ ተንኮል አዝሎ እንደሆነ ትላንት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ላይ የተፈጸመው ሴራ ህያው ምስክር ነው።
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ፍኖተ አማራ ለየት የሚያደርገው የአማራ ፋኖ የታጋዮች ሚዲያ መሆኑ ነው እሱም መሬት ላይ ተራራና ገደሉን ብርዱንና ፀሐይኑ አብረን ተቋቁመን መስራታችን ነው ለዚህም ጠላቶቻችን አጀንዳ ይዘው እየመጡ ነው እኛም አለን ብለናል ከዛሬ ቀን ጀምሮ እንወያያለን እንሰለጥናል ሚዲያችን አብረን እናሳድጋለን ከአማራ የቁርጥ ቀን ልጆቹ ጋር አብረን ተራራና ብርዱን ወጠን ወርደን አውደ ውጊያዎች አብርን እየሰራን እንገኛለን ይወዳጁን!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+7
ፋኖን ልናፈርስ ነው" የሚሉን ኃይላት፣ እኛ እነሱን እያፈረስናቸው እንደሆነ በተግባር እያዩት ነው። ፋኖ መፍረስ የማይችል የሕዝብ የልብ ትርታ መሆኑን ዘንግተውታል። እኛን ለመበተን የሚመጡት ሁሉ ራሳቸው ተበትነውና ደብዛቸው ጠፍቶ ይቀራሉ። የአማራ ፋኖ የአሸናፊነት ተምሳሌት እንጂ የሚፈርስ ግንብ አይደለም።
የአማራ ፍኖዎች አምሮብን፣ የቆራጥነት መንፈስ ተላብሰን የአማራን ሕዝብ የመኖር ነፃነት እና ሰላም ለማረጋገጥ በብርሃን ፍጥነት እየገሰገስን ነው። "ፋኖ ትጥቁን ፈታ" የሚለው የነሱ ምኞት ቢሆንም፣ እውነታው ግን እኛ ዘጠና ሺህ (90,000) የሚጠጋ የጠላት ትጥቅ ማርከን ወደ ካምፓችን ገቢ ማድረጋችን ነው። Dawit Amhara
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
በገነባናት ሀገር ላይ ባይተዋር መሆን አብቅቷል! 70 ሚሊዮን አማራ በገነባትና ባቆማት ሀገር ላይ የመኖር ዋስትናው የሚረጋገጠው በሌሎች በጎ ፈቃድ ሳይሆን በራሱ ክንድና በተጋድሎው ብቻ ነው።
እውነተኛ ሰላም የሚመጣው አንባገነንነት ሲሸነፍና የህዝብ ክብር ሲመለስ ነው። እኛ የምንታገለው ለመኖር ብቻ ሳይሆን ተከብሮ ለመኖር ነው።
ታሪክ የሰራ ህዝብ የታሪክ ተገዢ አይሆንም። የሀገሪቱን ምሶሶ አቁመን ዛሬ ዋስትና ስናጣ፣ አማራጭ የሌለው የህልውና ትግል ውስጥ ገብተናል።
አንባገነንነትን አሽቀንጥረን የምንጥለው፣ ፍትህና እኩልነት የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው። ተከባብረን ሳይሆን ተከብረን የምንኖርባትን ዓለም በደማችን እንጽፋለን!
የአማራ ፋኖ — የህልውናችን አለኝታ!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ
©️Asefa T Mengesha
በርታልኝ ወንድሜ!
የአርመኔው አብይ አህመድ ኃይል አፈሳ- በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች አፈሳው ተጧጡፎ ቀጥሏል። መታወቂያቸውን እየቀሙ በአንድ ጆንያ እየሰበሰቡ ይገኛል የአዲስ አበባ ወጣቶችን በመኪና እየጫኑ ነው። በአለም ባንክ፤ ቤተል፤ በአየርጤና፤ ጆሞ፤ በቃሊቲ፤ የካ፤ በመገናኛ፤ ላም በረት የብልፅግና አፈሳ ቀጥሏል።
አማራ 4 ኪሎ ስለገባ የምትፈርስ ኢትዮጵያ ካለች ዛሬ ማታ በአናቷና በአፍጢሟ ትተከል!! መንገዱን ጨርቅ ያርግላት።
አሁን እኛ እየጠየቅን ያለነዉ ከአፈር አንስተን የመሰረትነውን ሀገር፣ 3ሺህ ዘመን የመራነዉ ቤተመንግሥትና ዙፋን መልሱልን ነዉ። ምክንያቱም እዛ ዉስጥ ሆናችሁ ስለምትገሉን ማለት ነዉ።
እኛ አማሮች ይሄንን ሀገር በሆነ ወቅትና ግዜ ሁሉም ነገር የረጋ የተረጋጋ የሰከነ የተስተካከለ መስሎን በአደራና በኮንትራት የሰጠናችሁ ሀገር መንበሩን ስልጣኑን በአሻን
ሰዓት መልሰን ለመዉሰድ እና ለመቀበል ነዉ።
የሰጠናችሁን ወንበርና ሃላፊነት እኛኑ ማጥቂያና መግደያ አርጋቹህታል አልቻላችሁበትም መልሱልን እያልን ነዉ።
እያልናችሁ ያለነዉ ለአምጪዉ እንዲከፈል ህግ ያስገድዳል ነዉ።
በእርግጥ ይገባናል እንካችሁ ብላችሁ በፍቃደኝነት ወንበር አትመልሱም። እኛም ቂል አደለንም ነገር ግን በግብግብም ሆነ በግልግል ግን የአያቶቻችን ዙፋን ይመለሳል። እንደ እኔ አያቶቼ ላኑርህ ያለህ ከሌለ እንደ አያቶችህ ላኑርህ ግን አይባልም።
አማራ ከ 4 ኪሎ ቤተመንግሥት አይቀርም!
+3
በትረ መንግስቱ የኛ ነው!
እንኳን ዛሬ
ጥንቅቅ ያለ ግዙፍ ሰራዊት ገንብተን
ህዝባችንን በተለይ በፖለቲካ አንቅተን
እስከ አፍንጫንች ታጥቀን
ጽድት ያል ድርጅት መስርተን
የማያወላውሉ መሪዎች ሰይመን
ከ3ዓመት በላይ የውጊያ ልምድ ይዘን
እንኳን አሁን ይቅርና የዛሬ አምስት አመት "ሶስት ክላሽ" ብቻ ይዘን በነበረበት ወቅት እንኳ ቤተ መንግስቱን እንደምረከብ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ቤተ መንግስቱ የኛው ነው፡፡ እየመጣን ነው፡፡ የማያዳግም ለውጥ በኢትዮጵያ እናነብራለን፡፡
ድል ለፋኖ ድል ለአማራ!
በየአቅጣጫው የጠላት ሀይል እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው‼️
የካቲት 14/2018 ዓ/ም የምህርት አዋጁን የተቀበሉ የአገዛዙ የአድማ ብተና አባላት ዛሬም እንደትናንቱ ከጠላት ካፕ በመኮብለል 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር የፋኖ አባላትን እየተቀላቀሉ ነው።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የምህረት አዋጂ ማውጣቱ ተከትሎ በብዛት የጠላት ሀይል በየአቅጣጫው በመፈራረስ የፋኖን ሀይል እየተቀላቀለ ነው።የምህረት አዋጁን የተቀበሉ አባላት፦
1ኛ ረዳት ሳጅን ሀብቴ ላቀው
2ኛ ኮንስታብል ወርቅየ አበበ
3ኛ ኮንስታብል ሰኢድ ሁሴን የተባሉ የአድማ ብተና አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ሻውራ አካባቢ ከሚንቀሳቀሰው የጠላት ሀይል በመውጣት የ105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር የፋኖ አባላት ተቀላቅለዋል።
አባላቱም ከአረመኔው አገዛዝ ጋር በመሆን የአማራን ህዝብ ሲቃይና መከራ በማራዘማችን ይቅርታ እንጠይቃለን፣ከዚህ በኋላ ግን ከህዝባችንና ከፋኖ ወንድሞቻችን ጋር በመሆን አረመኔውን አገዛዝ ለመፋለምና ለማስወገድ ቃል እንገባለን ብለዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
አፋብን ያቀረበውን የምህርት አዋጅ ዕድል ተጠቅመው 14 የአገዛዙ ወታደሮች ጉና ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ!!
በፋኖ መምሕር ያሬድ ገደፋው
==========================
የካቲት 14
13/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር
ድርጅቱ ባወጠው አዋጅ መሰረት የብልፅግና አገዛዝ ለእኩይ ተግባር ሲጠቀምባቸው የነበሩ 14 የሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላት አንዳቤት ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
የምህርት አዋጅ የተቀበሉት የአገዛዙ ሃይል "በተሳሳተ መንገድ ከጨፍጫፊው ስርዓት ጋር ተሰልፈን የአማራን ህዝብ ስንገድል፣ ስናስገድል እና ስናሰቃይ በመቆየታችን ተፀፅተናል በማለት ቀጣይ ግን ለህዝባችን ውድ ህይወታችን ጨሞረን ለመካስ ተዘጋጅተናል ያሉት የምህርት አዋጁን እንድንቀበል ህይወታችን ለታደገን ለአፋብን ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል"።
➡️ የምህርት አዋጁን የተቀበሉ ታጣቂዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ተቀምጠዋል።
1.በላይ ባንቴ ➜ ሚሊሻ
2.ሃብታሙ ካሴ ➡️ሚሊሻ
3.ቢሆነኝ ተረፈ➜ሚሊሻ 4.መንግስቱ አዳምጤ➜አድማ ብተና
5.ተመስገን ተረፈ ➜ሚሊሻ
6 ሸገው ማለደ➜ሚሊሻ
7.ስማቸው ውበት➜ሚሊሻ
8.ተመስገን ሉሌ ➜ሚሊሻ
9.እንየው አስፊ➜ሚሊሻ
10.ጌጡ ገብሩ ሚሊሻ
11.አብራረው አማረ ➜አድማ ብተና
12.አብቧል ውዱ➜አድማ ብተና
13.አዳምጤ እንደሸው➜ሚሊሻ
14.ቸርነት አዳሙ ➜ሚሊሻ የምህረት አዋጁን የተቀላቀሉ ናቸው።
በመጨረሻም የምህረት አዋጅ ሲደረግላቸው የጉና ክፍለ ጦር ፣ የአንዳቤ ብርጌድ እንዲሁም የአንዳቤት ወረዳ የፋኖ ጊዜያዊ መንግሰት አመራሮች በተገኙበት የፖለቲካ ግንዛቤ ማስጨበጫ እውቀት በሰፊው ተሰጣቷቸው የተቁሙን ፎረም በመሙላት የፋኖ አባላትን እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ፋኖ መምህር ያሬድ ገደፍው የጉና ክፍለ ጦር ህ/ ግ ሃላፊ
የጄኔራል ተፈራ ማሞ ወደፊት መምጣት ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊ እንደ blessing የሚቆጠር ወርቃማ አጋጣሚ ነው!!
ጄኔራሉ አማራነትን እና ኢትዮጵያዊነትን ማጣጣም ከሚችሉ ሀገር እና ህዝብ ወዳድ ዜጎች መካከል ቀዳሚው ነው:: እንደ ሌሎች የህዳጣን ጄኔራሎች የታህታይ ምስቅልቅል (Inferiority complex) የሌለበት ምሉዕ ስብዕና ያለው ይህ ጄኔራል ለኢትዮጵያን መርዛማ ፓለቲካ እንደ panacea ያገለግላል ጤናማ political community ይፈጠር ዘንድም የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ::
የእውነት ሰው እና ጀግና ወታደር መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ እሴት ነው:: በደግነት እና ጀግንነት ማንም አያህለውም:: ለየትኛውም ብሄር ብሄረሰብ ጥላቻ የለውም:: እንዲህ አይነት መሪ ማግኘታችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር ለመስራት ጭምር ይረዳናል::
ጄኔራል ተፈራ ማሞ ወታደሩን እየመራና ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ እየሰበሰበው ለድል የማንበቃበት ምንም ምክንያት የለም::
ድል ለአማራ ልጅ!!
መምህራችን - ኮሎኔል ሙላቴ ሲሳይ👤
ከUN ከ12 በላይ የስልጠና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ተቀብሏል:: የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ተቋም መምህር እና ተመራማሪም ነበር:: የኮሎኔልነት ማዕረግ ሊሰጠው ወራት ሲቀሩ ነው ወደ ፋኖ የመጣው:: የእሱ አቻዎች ባለፈው ክረምት የማዕረግ እድገት አግኝተዋል:: ይህ ወንድማችን የፋኖን ትግል በእውቀት ይመራሉ ከምንላቸው ታጋዮች እና አታጋዮች መካከል አንዱ ነው:: በሶማ ስም የቴወድሮስ እዝን ማሰልጠኛ ተቋም በመመስረት ወታደራዊ አመራሮችን የማብቃት ስራ ሲሰራ እናውቀዋለን:: በነገራችን ላይ ሚሊተሪ ሳይንስ ነክ ዶክመንቶችን ማንበብ ስፈልግ እኔም መልዕክት በመፃፍ እባክህን ላክልኝ የምለው እሱን ነው:: ከማሰልጠኛ ማንዋሎቹ ብዛት ያላቸውን ልኮልኛል:: የማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ሳልገባ Theoretically የተሻለ ወታደር መሆን የሚያስችለኝን እውቀት አስገብይቶኛል:: የተግባሩን ደግሞ ጠላት ላይ በመለማመድ master ማድረግ የእኔ ፈንታ ነው::
ጦር ልመዱ!
ጦር ልምዱን ይወዳል!
ያለመደውማ እንደ እንቧይ ይናዳል!
ሲባል ሰምተናል:: ጦር ልምድን ስለሚወድ ነው በለመደው መደመደው የሚባለው::
ይህ ትግል በእውነት እና በእውቀት እንድሁም በጠንካራ አመክንዮ ይመራ ዘንድ እንደ ኮሎኔል Mulatie Sisay ያሉ የሚሊተሪ ሳይንስ ሰዎች ያስፈልጉናል:: በሰፈር ስሌት እና በኮታ የምንጓዝ ከሆነ ለእውቀት እና እውነት ቦታ ልንሰጥ ስለማንችል ትግሉንም ማስቀጠል ይከብደናል:: ሁላችንም ተገዥ መሆን ያለብን ለእውቀት እና እውነት ነው::
እውቀት እና እውነት ይምራን!!
ድል ለአማራ ልጅ!!
ፍኖተ አማራ ሚዲያ መቀመጫውን ግንባር ላይ በማድረግ የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀትና ለማስተባበር እየሰራች ትገኛለች ። ሚዲያችን የሕዝባችንን ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች በማንገብ ለላቀ ተጠቃሚነት በቆራጥነት ይሠራል፦ ፖለቲካዊ፡ የመብትና የሥልጣን ባለቤትነትን ማረጋገጥ።ማህበራዊ፡ የአንድነትና የማንነት ትስስርን ማጠናከር። ኢኮኖሚያዊ፡ የሕዝባችንን ተጠቃሚነትና እውነተኛ ታሪካችንን ለዓለም ማሳወቅ። ወደዱም ጠሉም፣ የታሪካችን አዲስ ምዕራፍ በእጃችን እንዲፃፍ ሃያ አራት ስዓት እየሰራን እንገኛለን።
ከአሁኑ ስዓት ጀምር በእኔ ላይ ያነጣጠረ ሰፊ የጥልሸት ዘመቻ ተከፍቶብኛል። መቀመጫቸውን አዲስ አበባ እና ግብፅ ያደረጉ ኃይሎች፣ አማራ መስለው በመቅረብ የሚዲያችንን ድምፅ ለማጥፋትና ስሜን ለማጉደፍ እየሠሩ ይገኛሉ። ይህ የሆነው የሚዲያችን ይዘት "አማራነት" ላይ ብቻ ያተኮረ በመሆኑ ነው።ስለሆነም፣ እውነተኛ አማራ የሆናችሁ ሁሉ ይህ ድምፅ ለሁሉም እንዲደርስና ሚዲያው እንዲጠናከር፣ በአማራ ፋኖና በትግል ጓዶቼ ስም የደገፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
የቴሌግራም ሌንክ ከታች አስቀምጫለሁ አመሰግናለሁ።
አባናደው ክፍለጦር በሁለት አውደ ግንባሮች ባደረገው ተጋድሎ 29 የአገዛዙ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጉ ታወቀ!
በነዚህ ሁለት ግንባሮች ላይ በተደረገ ውጊያ ከተገደሉ ወታደሮች በተጨማሪ የቆሰሉ ወታደሮችን የገዛ ጓዶቻቸው ትጥቃቸውን ገፈው ጥለዋቸው ሄደዋል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አባናደው ክፍለጦር ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረገው ተጋድሎ የጠላት አከርካሪን በመስበር አንፀባራቂ ድል መቀዳጀቱን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ተጋድሎው የተደረገው በምስራቅ አማራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች መካከል አንዷ በሆነችው ከላላ ወረዳ ልዩ ስሙ ባከት ተብሎ በሚጠራው አከባቢና ሻፊ ላይ ነው።
የመጀመሪያው ውጊያ በከላላ ወረዳ ልዩ ስሙ ባከት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ሲሆን በዚህ ግንባር ለተከታታይ 8:00 ሰዓታት ከባድ የሆነ የጨበጣ ውጊያ መደረጉን ክፍለጦሩ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
በውጊያው ሰባት የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ 15 ወታደሮች ደግሞ ክፉኛ ቆስለው በሞትና በሕይወት መካከል ይገኛሉ።
በዚህ ግንባር በተደረገ ውጊያ ከተገደሉ ሰባት ወታደሮች በተጨማሪ የቆሰሉ 15 ወታደሮችን የገዛ ጓዶቻቸው ትጥቃቸውን ገፈው በአከባቢው ጎራዴ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ጥለዋቸው መሄዳቸውን ነው መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው።
በአውደ ግንባሩ ከዙ23 ጀምሮ ሌሎች ከባባድ መሣሪያዎችን ታጥቆ ለወረራ ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ ጥቃት በመክፈት
ድል የተቀዳጁት በአባናደው ክፍለጦር ስር ከመሀመድ ዳውድ ሬጅመንት የተወጣጡ የፋኖ አባላት ናቸው።
በተመሣሣይ በቀጥናው ሻፊ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአባናደው ክፍለጦር ስር የሸዋንግዛው ሬጅመንት አባላት ባደረጉት ተጋድሎ ከሰባት ወታደሮች በላይ ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን በርካታ የጠላት ወታደራዊ ንብረቶችም በፋኖ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
አማራ መስላችሁ ከአብይ አህመድ የደህንነት መዋቅር ጋር በመሰለፍ፣ እኔን ከምወዳቸው ወንድሞቼና ቤተሰቦቼ ጋር ለማጣላት የምትደክሙ ሆድ አምላኮች፤ ጥረታችሁ ከንቱ ነው። እኔ እንደ እናንተ በጎጥ የጠበብኩ ሳልሆን፣ በአማራነቴ ብቻ በስርዓቱ ግፍ ስለተፈጸመብኝ ወደ ነፃነት ትግሉ የገባሁ ኩሩ አማራ ነኝ።
እኔን ለማሸማቀቅና ህይወቴን በፈጠራ ወሬ ለማበላሸት የምትኳትኑ ድኩማን፣ አርፋችሁ ብትቀመጡ ይበጃችኋል። እናንተ የሄዳችሁበትን ያህል እኔም መሄድ እንደምችል እንዳትረሱ። መልዕክቴ አልቋል!
Dawit Amhara
*ሰበር ዜና*
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር በ13/06/18 ውጊያ የዕለቱ ታጋድሎ።
እራሱን ጥምር ኃይል እያለ የሚጠራው ጨፍጫፊውና አራጁ የአብይ አህመድ የገብሥ ገለባ ሰራዊት ወደ ጎርፎ ከተማ ለመግባት ያደረገው ሙከራ በጀግኖቹ በ ኃይለማርያም ማሞ ፋኖ ተጋድሎ ሳይሳካለት ቀርቷል።
በሶስት አቅጣጫ ወደ ጎርፎ ከተማ ለመግባት ዓመታዊ የእግዚአብሔር አብን ክብረ በዓል ለማደናቀፍ አስቦ ለሊት ሲነጋጋ በግምት 11:30 ጀምሮ በጎርፎ የቁር ጎጥ አቅጣጫ የተንቀሳቀስውን የጠላት ኃይል ጀግኖቹ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ሻለቃ አንድ ቤዛ ሬጅመንት ደፈጣ በማድረግ (2) አብሪውን የቀነደሹት ሲሆን ሶስት የሚሆኑ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።
በሌላ በኩል ከማለዳው በግምት 12:00 አካባቢ በመክበቢያን ማርያም ወደ ጎርፎ ከተማ ለመግባት የተንቀሳቀሰውን የጠላት ኃይል የኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ቃኚ ሻለቃ የደፈጣ ጥቃት በማድረግ የጠላትን ኃይል አራግፈውታል።
ይህን ጥቃት መቋቋም ያቃተው ጠላት ከሀገረ ማርያም ከተማ ተጨማሪ ኃይል እንዲላክለት በመጠየቅ በግምት ከጠዋቱ ሁለት ሰአት አካባቢ ሁለት አይሱዙ መኪና ተጨማሪ ኃይል የተላከለት ቢሆንም በቁና ተራራ እና አካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሰው ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር ዳኛቸው ሻለቃ የደፈጣ ጥቃት ተመቶ መንገድ ላይ በአራት ጠላት ላይ ጥቃት በማድረሥ ለእርዳታው ሳይደርሥ ቀርቷል።
በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት የጎርፎ ከተማን ለመያዝ ያቀደው የጠላት እንቅስቃሴ በከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለጦር የተሳካ የደፈጣ ጥቃቶች እቅዱ ሳይሳካ ከመቅረቱም በላይ የጠላት ኃይል በርካታ ሙት እና ቀስለኛ ሆኖ የተቀጠቀጠው የጠላት ኃይል ቁስለኞቹን እና አስክሬኖቹን ጭኖ ተመልሷል።
ዘገባውን ያደረሰን የኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር ሪፖርተር አረበኛ ሀቀኛው ይታፈር ነው!!!!
➔ድል ለአፋብን!!!!
➔ድል ለአማራ ህዝብ!!!
@የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!!
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
