ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more3 011
Subscribers
+2324 hours
+367 days
+41430 days
Posts Archive
+9
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝናግሼ አውራጃ ግሼ ክላስተር የሕዝብ ተቋማት ሠራተኞች መድረክ ተካሄደ።
ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተቆጣጠረው ግሼራቤል ወረዳ የሚገኙ የሕዝብ ተቋማት ሠራተኞች (የህዝብ ሰራተኛ)የውይይት መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ መድረኩ "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በመምከርና አቅጣጫ በማስቀመጥ እንድሁም በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የአቋም መግለጫ በማሰማት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
+5
የሚሊሻ ጋንታ መሪው እና የመከላከያ ብሬን እረዳቱ በዛሬው እለት ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል።
==========================
........ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም
1.ጌትነት ውቤ ......ሚሊሻ.54ኛ ክ/ጦር
2.መንግስቱ ይዘንጋው ...ሚሊሻ ጋንታ መሪ
3.ዳግም አለሙ ...25ክ/ጦር ብሬን ረዳት
4.ተዋቸው ተሙ....ፓራ ኮማንዶ 74ኛክ/ጦር የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+2
በቋሪት የክርስቲያን ታደለ የአባት አርበኞች ሻለቃ ለግዳጅ ዝግጁ መሆኑን አበሰረ
༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺
[ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት]
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ ጣሊያ ቀጠና የሚንቀሳቀሰውና በጀግናው #ክርስቲያን_ታደለ ስም የተሰየመው የአባት አርበኞች ሻለቃ፣ አደረጃጀቱን በማጠናከር ለማንኛውም ኦፕሬሽናል ግዳጅ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ።
የሻለቃው አመራሮች እንደገለጹት፣ ሻለቃው በሰው ኃይልና በሥነ-ልቦና ራሱን እንዲያጠናክር ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በዚህም መሰረት፦
#ወታደራዊ_አደረጃጀት፦ ሻለቃው በቲምና በጋንታ ደረጃ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተዋቅሮ ለግዳጅ ዝግጁ ሆኗል።
#የአመራር_ማሟላት፦ በሻለቃው ውስጥ የነበሩ የአመራር ክፍተቶችን ሙሉ በሙሉ በመሙላት፣ ግልጽ የሆነ የዕዝ ሰንሰለት ተፈጥሯል።
#ቅንጅታዊ_አሰራር፦ ሻለቃው ከቀጠናው የዐፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ጋር በቅርበት እንዲተሳሰር ተደርጓል።
ይህ የተጠናከረ ዝግጅት የሕዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅና የሚሰጡትን ተልእኮዎች በብቃት ለመወጣት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተስፋ ተጥሎበታል።
▶ ለሀገር ኩራት ፥ ለጠላት ስጋት!
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ የሕግ እና ስነ ስርዓት ጉባኤ እስከ ወረዳ ግዜያዊ መንግስት የፍትህ ክፍል በማቋቋም ለድርጅታችን እና ለህዝባችን የፍትህ አገልግሎት ሲሰጥ የቆዬ መሆኑ ይታወቃል።
ጉባኤው የፍትህ አሰጣጥ ስርዓቱን ለማሻሻል ባለው ቁርጠኝነት መሰረት በቴወድሮስ ዕዝ 206ኛ፣ 105ኛ እና 109ኛ ኮር ስር ለሚገኙ የኮር እና የክፍለ ጦር የህግ ክፍል ባልደረቦች እንዲሁም በኮሮች ስር ለሚገኙ 21 ወረዳወች ግዜያዊ መንግስት የህግ ክፍል ባልደረቦች በፍትሕ እና በህዝብ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል።
በሁለት የተለያዩ ማዕከሎች የተሰጠው ስልጠና በአጠቃላይ 132 ያህል የፍትህ ዘርፉ አመራር እና ባልደረቦችን ያሳተፈ ሲሆን ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋል ሰልጣኞች ወደ መደበኛ ስምሪታቸው ተመልሰዋል።
የብልፅግና አገዛዝ ምርጫ አላስመርጥም ያለን ግለሰብ በግፍ ረሸነ::
በአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመና አገር እያፈረሰ ያለው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ህጋዊ እውቅና አገኝበታለሁ ብሎ ሊያካሂደው ባሰበው ምርጫ ህልውና ይቀድማል አንመርጥም አናስመርጥም ያሉ ግለሰቦችን በግፍ እየረሸነ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተይይዞ ራያ ቆቦ ሮቢት ልዩ ቦታው ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ አቶ አበበ ደጉ ጀመረ የተባለን ግለሰብ ምርጫ አላስመርጥም ብለሃል በሚል ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም ምሽት 12:45 ገደማ ከመኖሪያ ቤቱ አውጥተው በግፍ በጥይት ደብድበው ረሽነውታል::
አቶ አበበ ደጉ እድሜው በግምት አምሳ አመት አካባቢ የሚሆን ባለትዳርና የልጆች አባት ሲሆን በአካባቢው ሚሊሻ አያሌው ዳኛው እየተመሩ በመጡ የአገዛዙ አገልጋይ ሆድ አደር አድማ ብተናዎች መኖሪያ ቤቱ ላይ በግፍ ተረሽኗል::
ህይወቱን በግፍ የተቀማው አቶ አበበ ደጉ ጀመረ የአማራ ህዝብ በብልፅግናው አገዛዝ በምድር በሰማይ በተሰማራ ሰራዊትና ጦር መሳሪያ እየተጨፈጨፈ ባለበት ባሁኑ ጊዜ በገንዘብ ተገዝቸ አስመራጭ አልሆንም በማለቱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል::
በተያያዘ ዜና አገዛዙ በራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያና ሌሎች አካባቢዎች ዛሬ ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም በገበያ እና በሌሎች የዕለት ተዕለት ተግባራት በሚከወኑባቸው ቦታዎች ሁሉ አስገድዶ የምርጫ ካርድ ለማስወጣት እየሰራ ሲሆን አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ማህበረሰቡ የመኖሪያ አካባቢውንና ቀየውን እየለቀቀ ይገኛል:: በተለይ አገዛዙ አስገድዶ አስመራጭ ያደረጋቸው ግለሰቦች እየጠፉ አገር እየለቀቁ ይገኛሉ::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና!!!
በቋራ ወረዳ ቁጥር-2 ላይ የአገዛዙ ጥምር ሀይል ከፍተኛ ሽንፈትን አስተናገደ!!!
በትናንትናው እለት ሚያዚያ 23/2018 የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት መነሻውን በሶስት አቅጣጫ ማለትም ከቁጥር-4፣ ሽንፋ፣ ቱመትና ዱባባ በማድረግ ወደ ቁጥር-1 በመጓዝ ላይ እያለ ረመጦቹ የበረሀው ፈርጦች አፋብን በላይ ዕዝ መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር ካራማራ ክ/ር በአርበኛ አጠቃ ሞገስ በተሰጠ ስምሪት፤ ጠላት ካሰበው ቦታ ቁጥር-1 ሳይደርስ ቁጥር-2 ላይ ከቀኑ 9:00_10:30 ገደማ ባላሰበው መንገድ ቀድሞ በተሰራ ኦፕሬሽን አናብስቶቹ ድል ቀንቷቸዋል።
በአማራ ህዝብ ላይ እንደ አሻንጉሊት የሚጫዎተው የአብይ አህመድ እና የምስለኔዎቹ የምርጫ መርሀግብር ድራማዊ ተውኔት ተፈፃሚነቱ የህልም እንጀራ ሆኖበት ምንም ማድረግ ሳይችል ከፍተኛ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ሀዘንተኛ ሆኖ ሁሉም ወደ መጣበት ሊመለስ ችሏል ሲል የካራማራ ክ/ር የህ/ግ አርበኛ ቴዎድሮስ ይግዛው ከስፍራው አድርሶናል።
በጥቅሉ ቀጠናው ላይ የአገዛዙ አሸርጋጅ ሰራዊትና የብልፅግና አሽከሮች ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆነዋል። በየጊዜው በሚደርስባቸው ሽንፈት ፣ ሰራዊቱም በሚያዋጣው መንገድ ከአሀዱ እየወጣ እየኮበለለ፤ ለፋኖ ትጥቁን እያስረከበ በሰላም ወደ ቤተሰቡ የሚሄደው እና መሰል የስርአቱ መቃዎስ በአጉል ምኞት የአገዛዙን እድሜ ለማስረዘም የሚጣጣረው የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮችና የአብይ አህመድ ድቅሎች ከፍተኛ የራስ ምታት ላይ ይገኛሉ።
በአውደውጊያው የተገኘ ድል: በመጣበት አስር ጎማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አስክሬኑንና ቁስለኛውን ይዞ ተመልሷል።
ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ (፪ኛ) ኮር የህ/ግ
ሚያዚያ 24/2018
206ኛ ኮር ከስናን ወረዳ ብቁ ወጣቶች ጋር
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ስናን ወረዳ ደብር ወለቄ ቀጠና የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም
=======================================
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 206ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።
በምስራቅ ጎጃም ስናን ወረዳ ወለቄ ቀጠና እንዲሁ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ወጣቶች ተሳታፊ ሁኗል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የብልፅግና የሀሰት ምርጫ ቅስቀሳና የምርጫ ካርድ እደላ ሳይሳካ ተበተነ!
ሚያዚያ:-24/2018ዓ/ም
አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ውስጥ ጨፍጫፊው ብልፅግና ለሚያደርገው የውሸት ምርጫ በቀን 24/08/2018 ዓ.ም ቅዳሜ ለገበያ የሔደውን ህዝብ በግዴታ የምርጫ ካርድ ውሰዱ በሚል በሶስት ቦታዎች ማለትም አዲስ ፋና ትምህርት ቤት፣ሙጃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና መጋዘን ላይ ባዘጋጀው በግድ ካርድ ውሰዱ የሚል ህብረተሰቡን ሰላም የመንሳት ዕቅድ አስቦ ቢሰራም ጀብደኞቹ የ14ኛ ክፍለ ጦር ሰርጎ ገቦች እንዲበተንና ያሰበውን ሳያሳካ ቀርቷል።
በኦፕሬሽኑም አራት የመከላከያ አባላት ሙት ከአምስት በላይ ቁስለኛ ሆነዋል ።
በዚህ የተናደደው የአብይ ስልጣን አስጠባቂ ሰራዊት ሞርተር 120 በመወርወር መላው የግዳንን ማህበረሰብ ሲያሸብር ውሏል።ለበዓል ገበያ የሔደውን ህብረተሰብም ድንጋጤ ውስጥ እንዲገባና ከተማው ምስቅልቅሉ እንዲወጣ ሲያደርግ አርፍዷል።
ህዝብን በውሸት እያታለለ ስለምርጫ እየደሰኮረ ያለው ብልፅግና ምርጫው እንደማይሳካለት እየተረዳ በመምጣቱ ተስፋ ስለቆረጠ በግዴለሽነት ህዝብን ለመጨፍጨፍ በመዘጋጀት ላይ ያለ ይመስላል ።በመሆኑም ይህንን አስከፊ ስርዓት አምርረን በመታገል የድል ፅዋን መጎንጨት ያስፈልጋል ።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል መረጃውን የ14ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አድርሷል ።
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ:- 24/2018 ዓ/ም
የብልፅግና የሀሰት ምርጫ ቅስቀሳና የምርጫ ካርድ እደላ ሳይሳካ ተበተነ!
ሚያዚያ:-24/2018ዓ/ም
አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ውስጥ ጨፍጫፊው ብልፅግና ለሚያደርገው የውሸት ምርጫ በቀን 24/08/2018 ዓ.ም ቅዳሜ ለገበያ የሔደውን ህዝብ በግዴታ የምርጫ ካርድ ውሰዱ በሚል በሶስት ቦታዎች ማለትም አዲስ ፋና ትምህርት ቤት፣ሙጃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና መጋዘን ላይ ባዘጋጀው በግድ ካርድ ውሰዱ የሚል ህብረተሰቡን ሰላም የመንሳት ዕቅድ አስቦ ቢሰራም ጀብደኞቹ የ14ኛ ክፍለ ጦር ሰርጎ ገቦች እንዲበተንና ያሰበውን ሳያሳካ ቀርቷል።
በኦፕሬሽኑም አራት የመከላከያ አባላት ሙት ከአምስት በላይ ቁስለኛ ሆነዋል ።
በዚህ የተናደደው የአብይ ስልጣን አስጠባቂ ሰራዊት ሞርተር 120 በመወርወር መላው የግዳንን ማህበረሰብ ሲያሸብር ውሏል።ለበዓል ገበያ የሔደውን ህብረተሰብም ድንጋጤ ውስጥ እንዲገባና ከተማው ምስቅልቅሉ እንዲወጣ ሲያደርግ አርፍዷል።
ህዝብን በውሸት እያታለለ ስለምርጫ እየደሰኮረ ያለው ብልፅግና ምርጫው እንደማይሳካለት እየተረዳ በመምጣቱ ተስፋ ስለቆረጠ በግዴለሽነት ህዝብን ለመጨፍጨፍ በመዘጋጀት ላይ ያለ ይመስላል ።በመሆኑም ይህንን አስከፊ ስርዓት አምርረን በመታገል የድል ፅዋን መጎንጨት ያስፈልጋል ።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል መረጃውን የ14ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አድርሷል ።
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ:- 24/2018 ዓ/ም
#የአሳምነው_ልጆች_በሸዋ_በአይነቱ_ለየት_ያለ_ድል_ተቀዳጁ‼️
ሚያዚያ 24/2018ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባላ ክፍለ ጦር የአገዛዙን ወራሪ ኃይል በመደምሰስ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።
በትላንትናው ዕለት ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የነበልባል ክፍለ ጦር ምኒልክ ሻንበል የፋኖ አባላቶች በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ወረዳ ልዩ ቦታው በሙክየ ሀሮ ቀበሌ በሰፈረው የኦሮሚያ ሚሊሻ ላይ ድል ተቀዳጅቷል።
ይህ ሀይል እነ ሽመልስ አብዲሳ ስውር የጥፋት ተልዕኳቸውን በአማራ ህዝብ ላይ ለመፈፀም ያዘጋጁት እንደሆነ ከተያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከተወጣጡ ከምርኮኞች አንደበት ማረጋገጥ ተችሏል።
በተጨማሪም በአካባቢው ሰፍረው በቆዩባቸው ቀናቶች በማህበረሰቡ ላይ የተለያዩ ግፎችንና በደሎችን ሲያደርሱ እንደነበርም ለጊዜው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰቦች እንዲህ በማለት አጋርተውናል።
1ኛ. ከ 70 በላይ የሚሆን የአካባቢውን ማህበረሰብ ቁጥሩን ለማሳሳት አስረዋል የት እንዳደረሳቸውም አይታወቅም ሲል ተናግሯል።
2ኛ. በአካባቢው አማራ አይኑር የተባለ እስኪመስል የተገኘውን ሁሉ ድብደባ "ዘረፋ"የሴቶች አስገድዶ ደፈራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።
3ኛ. በስብሰባ ሰበብ ሴቶችንና ህፃናትን በመሰብሰብ ብዙ ጊዜ ምክንያቱ ባልታወቀ ነገር በመመረዝ እንዲታመሙ ተደርገዋል በዚህም መቋቋም ያቃታቸው ህፃናት እንደሞቱ አስረድቶናል።
ታዲያ በዚህ ሰቆቃና በደል ውስጥ በሀይል ለማኖር በማሰብ ከተለያየ ቦታ በአፈሳ አምጥቶ ያሰፈራቸውን ከ67 በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያ ሚሊሻ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀሩ በነበልባል ክፍለ ጦር በምኒልክ ሻምበል ፋኖ አባላቶች ተደምስስዋል ።
👉በእዚህም አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች‼️
✅1ኛ. 25 ክላሽ
✅2ኛ. 50 ካዝና
✅3ኛ. 150 የክላሽ ተተኳሽ
✅4ኛ. 25 የወገብ ትጥቅ
✅5ኛ. 7 ምርኮኛ
✅6ኛ. የተደመሰሱ 60 በላይ
በተየያዘ ዜና የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር 3ተኛ ሰላም ሰው ሻለቃ በኦሮሚያ ክልል ሀሙሥ ገበያ አቅራቢያ ልዩ ቦታው ዘንጎ ኪዳነ ምህረት ተብሎ ከሚጠራው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ምሸግ ላይ በመግባት መብረቃዊ ጥቃት በማድረሥ 8 ሙትና 4 ቁሥለኛ ሆኗል።
ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ‼️
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 24/2018ዓ.ም
ሰበር ዜና‼️
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር በጠላት ላይ ታላቅ ድል ፈፀመ ።
ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም፡ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር ሚኒሊክ ሻምበል ፋኖ አባላቶች በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ወረዳ በሙክየ ኃሮ ቀበሌ በሰፈረው የኦሮሚያ ሰላም አሰከባሪ ሚሊሻ ላይ ድል ማድረጉ ተገለፀ ።
ይህ ኃይል እነ ሽመልስ አብዲሳ ስውር የጥፋት ተልዕኳቸውን በአማራ ህዝብ ላይ ለመፈፀም ያዘጋጁት እንደሆነ ከምርኮኞች አንደበት ማረጋገጥ ተችሏል ። በተጨማሪም በአካባቢው ሰፍረው በቆዩባቸው ቀናቶች በማህበረሰቡ ላይ የተለያዩ ግፎችንና በደሎችን ሲያደርሱ እንደነበረና ከሰባ (70) በላይ የሚሆን የአካባቢውን ማህበረሰብ ቁጥሩን ለማሳሳት አስረዋል የት እንዳደረሷቸው አይታወቅም ። በሌላ በኩል፤ በአከባቢው 'አማራ አይኑር' የተባለ እስኪመስል የተገኘውን ሁሉ ድብደባ ፥ ዘረፋ የሴቶች አስገድዶ ደፈራ ተጠናክሯል ነው የተባለው፤ እንዲሁም በስብሰባ ሰበብ ሴቶችንና ህፃናትን በመሰብሰብ ብዙ ጊዜ ምክንያቱ ባልታወቀ ነገር በመመረዝ እንዲታመሙ ተደርገዋል፤ በዚህም መቋቋም ያቃታቸው ህፃናት እንደሞቱ፤ ለጊዜው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰቦች ተናግረዋል ።
ታዲያ በዚህ ሰቆቃና በደል ውስጥ አገዛዙ በሀይል ለማኖር በማሰብ ከተለያየ ቦታ ሰብስቦ አምጥቶ ያሰፈራቸውን ከ86 በላይ የኦሮሚያ ሰላም አሰከባሪ ሚሊሻ ለወሬ ነጋሪም ሳይቀሩ በነበልባል ክፍለ ጦር በሚኒሊክ ሻንበል ፋኖ አባላቶች መደምሰሳውቸው ነው የተገለፀው ።
▪️በዚህ አውደ ውጊያ የተገኙ ድሎች ፦
➣ ሃያ አምስት (25) ሁለት እግር ክላሽ ።
➣ አምሳ (50) የክላሽ ካዝና ።
➣ መቶ አምሳ(150) የክላሽ ተተኳሽ ።
➣ ሃያ አምስት(25) የገብ ትጥቅ፤
መማረክ ተችሏል ።
የእነ ሽመልስ አብዲሳ ሴራን የተረዱና ስልጣን ለመጠበቅ ህይወታችንን አንሰዋም ያሉ፤ ቁጥራቸው ሰባት(7) የሚሆኑ በአካል መማረክ ሲቻል እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑትን ቁጥራቸው ከ80 በላይ የሚሆኑት በሚኒሊክ ሻንበል ፋኖ አባላቶች ወደ ማይቀረው ዓለም ተልከዋል፤ በዚህም ነበልባሎቹ ፋኖ የአርበኛ አስማረ ዳኜን ታሪክ ደግመውታል፤ በማለት የነበልባል ክ/ር ሪፖርተራችን መረጃውን አድርሶናል ።
- "ህልውናችን በተባበ ክንዳችን !"
- ክብር ለእውነትና በጀግንነት ለተሰዉ ለትግሉ ሰማዕታት !!
- ድል ለአማራ ፋኖ !!!
© አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕ ከሰም ፪ኛ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ እና ህ/ግንኙነት መምሪያ ።
▪ አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ።
+3
#አፋብን_ሸዋ_ጠቅላይ_ግዛት_አሳምነው_ዕዝ✅✅
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝ ማማ ምድር ወረዳ(ባሽ ክላስተር) የሕዝብ ተቋማት ሠራተኞች መድረክ መካሄዱን ቀጥሏል።
ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተቆጣጠረው መንዝ ማማ ምድር ወረዳ ስር በሚገኘው ባሽ ክላስተር፣ የሚገኙ የሕዝብ ተቋማት ሠራተኞች (የህዝብ ሰራተኛው)የውይይት መድረክ ትናንት ሚያዚያ 23 በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ መድረኩ "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በሰፊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በመምከርና አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።
የህዝብ ሰራተኞችም በአስተያዬታቸው ውይይቱ አስፈላጊና ለህዝባችሁ ያላችሁን ክብር የተረዳንበት ለወደፊቱም ከናንተ ጎን እንድንሰለፍ ያስቻለና የታመነ ተቋም ነው ብለዋል።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል በሁለት እጅ እነሴ ወረዳ አስቴሪዮ ቀጠና የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
.......ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 201ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።
በሁለት እጅ እነሴ ወረዳ አስቴሪየ ቀበሌ ውይይት የተደረገ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ ወጣቱ ተሳታፊ ሁኗል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
