ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more3 222
Subscribers
+2224 hours
+2707 days
+65730 days
Posts Archive
+1
የአፋብን ወሎ ጠ/ግ/ሚ/እዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክ/ጦር እና ሸዋ ጠ/ግ/አሳ/እዝ አፄ ዘርያእቆብ ኮር1 ብሩኬ ደምሴ ክ/ጦር ከሁለቱም እዞች በስራ ስምሪት ላይ ያሉ የእዝና የኮር አመራሮች የክ/ጦር አመራሮችን ያካተተ በቀጠናዊ ጉዳይ ላይ በቀን 07/08/2018 ዓ.ም የጋራ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም ላይ የሁለቱም የእዝ ክ/ጦሮች በቅርበት ተደራራሽ ከመሆናቸው አንጻር በሚሸፍኑት ቀጠና ላይ የጋራ ጠንካራ ሀይል በመያዝ ኦፐሬሽን ከመስራት ጀምሮ በማህበረሰብ አያያዝ ፣ በማህበራዊ ፍትህ ፣ በምርኮኛ አያያዝ ፣ በሰራዊት ግንባታ እና በቀጠናው ቀጣይነት ላለው አጠቃላይ የትግል ሁኔታ በጋራ እቅድ ለመንቀሳቀስ ጭምር አጀንዳዎች ላይ ለሌሎችም እዞች ፈር ቀዳጅ የሆነውና የተጀመረውን አንድነት ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተደርጓል።
ይህ ጅምር ተጠናክሮ የሚቀጥል እና ክ/ጦሮቹ በየግዜው የተሰሩ ስራዎችን ለኮር እና እዞቻቸው የጋራ ሪፖርት እንደሚልኩ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመቀጠል የጋራ ውይይቱን መሰረት በማድረግ በቀን 09/08/2018 ዓ.ም በግሼራቤል ወረዳ ደል ቀበሌ በጋራ የህዝብ ውይይት እና የግንዛቤ ፈጠራ የተደረገ ሲሆን ህዝቡ ከፋኖ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን በራሱ ማስተዳደር የሚችልበትን የቀበሌ መዋቅር ማሻሻያ ማድረግ ተችሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ
ሚያዝያ 10/08/2018 ዓ.ም
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር በልጓማ ከተማ ባካሄደው ተጋድሎ በርካታ የጠላት ወታደሮችን በመደምሰስና ሁለት የጠላት ተሽከርካሪዎችን በማውደም አንፀባራቂ ድል ተቀዳጀ!
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ስር ከሚገኙት ከ33ኛ ክ/ጦር እና ከ71ኛ ክ/ጦር የተወጣጡ አሃዶች በጋራ በመሆን ትናንት ሚያዚያ 08/2018 ዓ/ም በልጓማ ከተማ በወሰዱት ስልታዊ እርምጃ የጠላት ኃይልን አሽመድምደውና አፍረክርከው ታላቅ ድል አስነዝግበዋል።
በከተማዋ የ33ኛ ክ/ጦር አርበኞች የጠላት ኃይልን በስልታዊ ማጥቃት ሦስትና አራት ቦታ ቆርጠው ሲያሽመደምዱት በተመሣሣይ፡ የ71ኛ ክ/ጦር አርበኞች በከተማዋ ውጊያ ከመሳተፍ ጀምሮ ተጨማሪ ጠላት እንዳይገባም ሆነ ከውስጥ ያለው እንዳይወጣ የልጓማ ከተማ መግቢያ መውጫ አቅጣጫዎችን ክርችም አድርገው በመዝጋት ድንቅ የተናበበ ተጋድሎ በማድረግ ነው የጠላት አከርካሪን መስበር የቻሉት።
በተጋድሎው አንድ አይሱዙ እና አንድ ወታደራዊ ፓትሮል ሙሉ ወታደሮች ከነ ተሽከርካሪዎቹ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ ዶግ አመድ መደረጋቸው ታውቋል።
የፋኖ የከተማ ውስጥ ለውስጥ ውጊያ መሃንዲሶች በፊታውራሪነት በመሩት በዚህ ተጋድሎ፡ የጠላት የቁም ምሽጎች ጭምር ተደረማምሰዋል፡ በርካታ ክላሾች ከነተተኳሾቻቸው እንዲሁም ወታደሮችና ካድሬዎች በፋኖ ተማርከዋል።
ልጓማ ከተማን በመቆለፍና ጠላትን በመቁረጥ በተወሰደ እርምጃ፡ በተሽከርካሪ ላይ እንዳሉ ከተመቱት በተጨማሪ ሌሎች በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል።
በዚህ ተጋድሎ ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ስልታዊ እርምጃ መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል የዘፈቀደ የሞርታር ድብደባ በመፈፀም በልጓማ ከተማ ማንፁኋኖችን መግደሉ ታውቋል።
ከተገደሉት ንፁኋኖች በተጨማሪ በርካታ ሀብት ንብረት ወድሟል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 09/2018 ዓ.ም
" የህዝብን መከራ እናጋልጥ"
የዘመኑ ጊዜ የሰጠው ኦሮሙማው ብልፅግና በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅመው ህዝባዊ ፍዳና ታሪካዊ ጠባሳ ማስቀመጡንና ይበልጥ አማራ መሬት ላይ እንዳይኖር ምኞቱን ቀጥሎበታል።ምንም እንኳ የአማራን ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ያልፈፀመው ግፍ ባይኖርም የሚዲያ ላይ ሀገር አሳዳጊው ፋሽስቱ ብልፅግና የመከራ በትሩን እየቀያየረ ትውልድ የማይረሳው በደል እየፈፀመ ይገኛል።ይህ ፋሽስታዊ የህፃን ዕሳቤ ያለው አገዛዝ ህዝብንና ታሪክን እየበደለ፣ሀገራችንን ደግሞ ልትወጣው ወደ ማትችለው ገደል እየከተታት ይገኛል።የህዝብ እምባና ሀዘን ግድ የማይሰጠው ይህ ጊዜ ሰጥ ነገን ያላዬ አገዛዝ በተለያዩ የአማራ ክልል ግዛቶች ላይ ተዘርዝረው የማያልቁ ግፎችን እየፈፀመ ይገኛል።ለምሳሌ ያህል:-
1.እነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ በህትመት ስራ ኑሯቸውን የሚገፉ አማራዎች ያለ ምንም ምክንያት መስሪያ ቦታቸው በአገዛዙ ከተዘጋ ሁለት(2) ሳምንት አልፎታል።
2.በሁሉም የክልሉ ቀጠናዎች የነዳጅ ፍጆታ ለህዝብ ሳይሆን ለአገዛዙ ብቻ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።
3.ማዳበሪያ አንድ ኩንታል ጥቁር 11300 ሀተብር፣ነጭ 10000 ብር ሲሸጥ ለፍዳ መታወቂያ ከግለሰብ 500 ብር፣ለሚሊሻ ከግለሰብ አንድ ሺ(1000)ብር በአጠቃላይ አስር አይነት ካርኒ አለ በዚህ መልኩ ህዝብ እየተሰቃዬ ነው።
እንዳንጠይቅ መልስ የለሽ ሆነና ነገሩ፣
ያለ ሀገር ኑሮ ሆነብን ቀመሩ።
ጊዜና ወንበሩ ድንገት ተገናኝተው፣
ሀገር በላ ሆኑ ሀገርን ከድተው። እንዲሉ መከራ በመከራ ግፍ በግፍ መደጋገም ሆነ።ስለሆነም መሬት ላይ የለን እውነታና የአማራን ህዝብ በደል ለአለም ማሳወቅና በታሪክ ከትቦ ለትውልድ ማስተላለፍ የዜግነት ግዴታችን ነው።
ድል ለተገፋው ለአማራ ህዝብ
ድል ለአፋብን
እናሸንፋለን
ቀኘ ነኝ
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ስር የሚገኙት የ71ኛ ክፍለ ጦር አርበኞች ትናንት ሚያዚያ 08/2018 ዓ/ም በስድስት የተለያዩ ግንባሮች ባካሄዱት ኦፕሬሽኖች፡ የአገዛዙ ወታደሮችና ካድሬዎችን በመደምሰስ፡ የምርጫ ቁሳቁሶችም በማውደም ድል አስመዝግበዋል‼️
ኦፕሬሽኑ የአገዛዙን ወታደራዊና አስተዳደራዊ መዋቅር ክፉኛ ያናጋ ነው ተብሏል። በመጀመሪያው ግንባር በክፍለጦሩ ስር ከአንደኛና ከሁለተኛ ሬጅመንቶች የተወጣጡ አሀዶች በጋራ ባከናወኑት ተጋድሎ ባከት ላይ ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል።
ከልጓማና ከቲርቲራ ተውጣጥቶ ወደ ባከት የተላከው የፀረ አማራው አገዛዝ ሰራዊትና ካድሬ በሞርታር ድብደባ ህዝብን ለማሸበር ቢሞክርም፡ አርበኞች በወሰዱት ፈጣን እርምጃ 18 ወታደሮችና ካድሬዎች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል።
በሁለተኛ ግንባር በመረቆ አካባቢ ሲሆን፡ የአባናደው ቃኝ ቡድን በወሰደው መብረቃዊ ደፈጣ በ14 የአገዛዙ ወታደሮች ተደምስሰዋል።
በፓትሮል ተሽከርካሪ ተሳፍረው እየተጓዙ በነበሩ የአገዛዙ ኃይሎች ላይ ነው እርምጃው የተወሰደው። በዚህም ከወታደሮቹ በተጨማሪ ተሽከርካሪው መውደሙ ታውቋል።
በሶስተኛው ግንባር፡ በክፍለጦሩ የሸዋንግዛው ሬጅመንት አባላት ፈረስ ሜዳ ተብሎ ለሚጠራው ስፍራ ላይ በወሰዱት የተሳካ እርምጃ 11 የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል።
በተጨማሪም በአራተኛውና አምስተኛው ግንባር በክፍለጦሩ ስር ከ1ኛና ከ2ኛ ሬጅመንቶች የተወጣጡ አሃዶች በጋራ በመሆን በአከባቢው ኩታና አጋሙ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በፈፀሙት ጥቃት ሰባት ወታደሮችን ሲገድሉ፡ በተጨማሪም ልጓማ ላይ ውጊያ እያደረገ ለነበረው የወገን ጦር ጫና እንዳይበዛበት በልጓማና በቲርቲራ መካከል ያለውን መስመር በመዝጋት የአገዛዙን እንቅስቃሴ ሽባ አድርገውታል።
ስድስተኛው ግንባር ከጃማ የ71ኛ ክፍለጦር አርበኞች ከ33ኛ ክፍለ ጦር አርበኞች ጋር በጋራ በመሆን ልጓማ ከተማ ላይ የነበረውን ጦር ደምስሰው ከተማዋን ሙሉ በሙሉ የተቶጣጠሩበትን ድል አስመዝግበዋል።
በከተማዋ የሚገኘውን የብልፅግና ቢሮ በመስበር ህዝብን ለማሳሳት የተዘጋጀውን የምርጫ ካርድና መዝገብ በማቃጠል የአገዛዙን የውሸት ምርጫ ድራማ አክሽፈውታል።
በአጠቃላይ ሳጅን አባናደው ክፍለጦር በትናንቱ ተጋድሎ 26 የአገዛዙ ወታደርችን ሲገድል 24 ወታደሮችን ደግሞ ቆለዋል። እንዲሁም አንዲት ወታደራዊ ፓትሮል ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ መውደሟ ተረጋግጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
© ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሚያዚያ 9/2018 ዓ.ም
ከአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት (አሳምነው ዕዝ) የተሰጠ መግለጫ!
"ጀግና በክብር ይወድቃል እንጂ አይንበረከክም!"
በሸዋ ምድር አናት ላይ፣ ታሪክ የማይረሳውና ትውልድ የሚዘክረው የጀግንነት ታሪክ ዳግም ተፅፏል።
የብልፅግና አገዛዝ በንፁሃን ደም የጨቀየውን እጁን ወደ አርበኞች መኖሪያ ቢዘረጋም፣ ያገኘው ግን የሞት ፅዋንና የታሪክ ውርደትን ብቻ ነው።
ገና በለጋነቱ ለሀገሩ ዳር ድንበር ደረቱን ሰጥቶ፣ በጥይት መካከል ተመትሮ ያለፈ የቁርጥ ቀን ጀግና አርበኛ ይማነ ።
ይህ ታላቅ አርበኛ በጣርማ በር ወረዳ በወፍ ዋሻ ቀበሌ ተወልዶ ሕይወቱን በሙሉ ለሕዝብ ነፃነትና ለፍትህ ገብሯል።
የብልፅግና ሠራዊት አርበኛ ይማነን በቤተሰቡ መካከል በድንገት ቢከበውም፣ ጀግናው አርበኛ ግን "ለወራሪ እጅ መስጠት የሞት ሞት ነው" በማለት የአንበሳን ግሳት አግስቶ፣ ብቻውን ሆኖ በደርዘን የሚቆጠሩትን የአገዛዙን ቅጥረኞች ወደ ሲኦል በመሸኘት፣ በመጨረሻም ከልቡ ፍሬ ከሆነችው ሴት ልጁ ፍሬ ይማነ ጋር በመሆን ለነፃነት ሲል በክብር ወድቋል።
ከጎኑ ሆና እንደ አባቷ የጥላትን አፈሙዝ ስትጋፈጥ የነበረችው ወጣት ልጁ ፍሬ ይማነም በወጣትነት ዕድሜዋ ለክብርና ለማንነት መሞት ታላቅ ሹመት መሆኑን ለትውልድ አሳይታ ከአባቷ ጋር በእኩልነት ተሰውታለች።
አርበኛ ይማነ ሀብተየስ፣ የነፃነት ተጋድሎው ዳር እንዲደርስ ሕዝቡን በማደራጀትና በክላስተር አመራርነት በላቀ ጀብዱ ሲያገለግል የቆየ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበር።
ይህ መስዋዕትነትም የትውልድ ዕዳ እንጂ የለቅሶ ማስታወሻ አይደለም!
የብልፅግና ሠራዊት በጦር ሜዳ የገጠመውን ሽንፈት በንፁሃን ላይ ለመበቀል የሚያደርገው ጥረትም ዛሬም ቀጥሏል።
በሌላኛው የጎበዝ አለቃ አርበኛ ደረጄ ጉልቴ መኖሪያ ቤት ላይ የተፈፀመው ወረራም የአገዛዙን የሞራል ውድቀትና ፈሪነት ማሳያ ነው።
ገና የ9 ዓመት ዕንጭጭ ሳለች በብልፅግና አረመኔ ሠራዊት ጥይት ተመታ ህይወቷ ያለፈው ህፃን ሰናይትም አገዛዙ በአርበኛ ደረጄ መኖሪያ ቤት ላይ በከፈተው ጥቃት ህይወቷ አልፏል። የአርበኛው ባለቤት እመቤት ልኬለህም በዚሁ ጥቃት ክፉኛ ቆስላለች።
አርበኛ ደረጄ ጉልቴ በቤቱ ላይ የተከፈተውን ድንገተኛ ከበባ በመስበርና በርካታ የአገዛዙን ወታደሮች በመደምሰስና ከበባውን በመበጠስ በጀግንነት መውጣት ቢችልም፣ የልጁን ሕይወት የቀማው ይህ ስርዓት ዋጋ የሚከፍልበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
የብልፅግና አገዛዝ የጥፋት መንገድ መጨረሻው መቃብር መሆኑን አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት (አሳምነው ዕዝ) በጽኑ ያምናል። በንፁሃን ደም የነከረው እጁ ዛሬ በጀግኖች አርበኞች ክንድ እየተቆረጠ ይገኛል።
እኛ የአርበኞቹን አደራ፣ የሕፃናቱን ለቅሶና የአባቶችን ፅናት ስንቅ አድርገን ትግሉን ዳር እንደምናደርስ ቃል እንገባለን።
የአርበኛው ይማነ ሀብተየስና የልጁ የፍሬ ይማነ ደም፣ እንዲሁም የሕፃን ሰናይት ደረጄ ነፍስ በከንቱ አይቀሩም!
"የአማራ ህዝብ በነፃነትና በክብር ይኖራል!"
"የጀግኖች አደራ አይበተንም!"
ውድቀት ለደም መጣጩ የብልፅግና አገዛዝ!
ሚያዝያ 9/2018ዓ.ም
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ!
ከ1ቲም በላይ 12 አባላት የፓራ ኮማንዶ ጋንታ መሪ የሚሊሻ ሻንበል መሪው እና የ25ክ/ጦር አባሎች 201ኛ ኮር 74 እና 54ኛ ክ\ጦርን ተቀላቅለዋል❗️
..............ሚያዚያ 09/2018 ዓ.ም
ያለ አንድ ጥይት ተኩስ ተቋሙን እያፈረስነው ነው የጠላት ሀይል ላይ በደረሰበት ጉዳት ስነልቦናው የተሸረሸረው የስርአቱ አገልጋይ አባል የነበሩት በየተራ ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ ነው።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
ከተራቁጥር# 01_10ያሉት 74ኛ ክፍለጦርን የተቀላቀሉ ናቸው
1ኛ.ወንዴ ጌታ........ፓራኮማንዶ
2ኛ.ታዴ ፈንጌ ...የፓራ ኮማንዶ ጋንታ መሪ
3ኛ.እንደገና መልካሙ .....ፓራ ኮማንዶ
4ኛ.ይገረም አድኛ...........ፓራ ኮማንዶ
5ኛ.ወንድማለም ደምስ.......ፓራ ኮማንዶ
6ኛ.ምንአይቶ አብራራው ...ሁለት ክላሽ ይዞ የወጣ
7ኛ.ምኒችል ይታየው...አድማ ብተና
8ኛ.አዲስ አሸነፍ .....የሚሊሻ ሻንበል መሪ
9ኛ.ገረመው መኮነን .........ሚሊሻ
10.አዲሱ ደረጀ..........ሚሊሻ
11ኛ.ሀይለማርያም ከፋለ....25ክ/ጦር መከላከያ
12ኛ.ጌታው አንበርብር .....25ክ/ጦር መከላከያ
ስርዓቱ ምንም አቅም የሌለው መሆኑን በሰሞኑ የተሰሩ ስራወችን በአይናችን አይተናል ሴራውን ተረድተናል መተኪያ የሌለው ህይወታችን መገበር አንፈልግም በማለት በዛሬዉ እለት ቆንጆወችን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
#መሪነት_በሻለቃ_ሙላቴ_ሲሳይ_እይታ‼️
👉መሪነት ሲባል ብዙዎቻችን በአእምሮአችን የሚሳለው ሁሉንም ትዕዛዝ የሚያስተላልፍ፣ በመድረክ ላይ የሚደምቅና ሰዎችን በራሱ የግል ተሰጥኦ ዙሪያ የሚያሰልፍ ግለሰብ ነው።
👉መሪነት በስሩ ያሉ ተካታዮች አንድን ተግባር ለማከናወን የማይፈልጉትን ተግባር ጭምር ወደውና ፈቅደው፣ በፍፁም ቁርጠኝነትና ፈቃደኝነት ሙሉ አቅማቸውን እንዲያረባርቡ የማሳመን፣ የማግባባት እና የማነሳሳት ልዩ ጥበብ ነው።
👉እውነተኛው መሪ የሰዎችን ትኩረት ወደ ራሱ ማንነት ሳይሆን ወደ ላቀውና የጋራ ወደሆነው ራዕይ እንዲያዩ የሚያደርግ ልዩ ተሰጥኦ ነው።
👉ሰዎችን ለአንድ የጋራ አላማ (common goal) ማሰለፍ ማለት የሁሉንም ልዩነት አጥፍቶ አንድ ዓይነት ማድረግ ማለት አይደለም። ይልቁንም ማእድናት ተቀላቅለው ውድና ማራኪ ጌጥ እንደሚሆኑት ሁሉ፣ እያንዳንዱ ሰው ያለውን ልዩ ተሰጥኦ እና ጥበብ ደምሮ ለቆመለት የጋራ ግብ እንዲያውለው የማሳመን እና የማነሳሳት ጥበብ ነው።
👉 ''እኔ '' ከሚል ግለሰባዊ አመለካከት ወጥተን "እኛ'' ''የእኔ ከማለት ይልቅ የእኛ'' ወደሚል የቲም አስተሳሰብ በመላበስ በተገኘው ድልና ስኬት የቅንጅት መንፈስ መኖሩን ማስረፅ ነው።
(''Leaders build teamsprit rather than group'')
ትልቅ ውጤት የሚገኘው ብቁ ሰዎችን በአንድ ክፍል ውስጥ ስለሰበሰብን ብቻ ሳይሆን በመካከላቸው ያለው መተሳሰብና ቅንጅት እንደ ማጣበቂያ ሆኖ በአንድነት እንዲያራምዳቸው ሲደረግ ነው።
👉መሪነት የሰዎችን አቅም አስተባብሮ ወደ አንድ ታላቅ ውጤት የሚቀይር የውሕደት ጥበብ እንደመሆኑ እያንዳንዱ አባል በዚያ ሂደት ውስጥ የራሱ የሆነ ክብርና ድርሻ አለው።
👉በአጠቃላይ አንድ ጥሩ መሪ በርካታ የመሪነት መገለጫ ባሃርያት(Qualites of leaders) ቢኖሩትም ዋና ዋናወቹን እንደሚከተለው እንዳስሳለን፡-
✔️አርአያነት (being role Modeling Behavior) ሰዎች መሪው የሚናገረውን ሳይሆን የሚሰራውን ነው የሚከተሉት፤ በተግባር ስለሰራኸው ጉዳይ ብቻ ስትናገር እንኳን ወገን ጠላትህም ከልቡ ያዳሞጥሃል።
#መሪ እንደ ህክምና ባለሙያ ''የምልህን እንጅ የማደርገውን አታድርግ'' ማለት ሳይሆን እንደ ሃይማኖት አባት ሁኖ እና ኑሮ ማሳየት አለበት።
✔️ቡድን ስራ ባህል (Team work) ብቻውን ሩጦ ስኬታማ የሚሆን መሪ ወይም የተወሰነ ቡድን ብቻ የለም። በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ተሰጥኦዎችን አስተባብሮ ለተወጣለት ለአንድ ዓላማ ማሰለፍ ትልቁ የመሪ ጥበብ ነው።
✔️በምሳሌነት መምራት (Leading by Example) በሠራዊቱ እና ሕዝቡ ዘንድ እንዲታመን ከፈለገ ራስን ታማኝ ማድረግ አለበት፤ ሠራዊቱ ከልቡ እንዲታገል መሪ ነን የምንል ቀድሞ ሜዳ መገኘት አለበት። ተግባር ከቃል በላይ ይናገራል።
✔️ተከታታይ ትምህርት (Continues Learning) “ሁሉንም አውቃለሁ” ከሚል ትዕቢት ወጥቶ በየቀኑ ከሚፈጠሩ ክስተቶችና ስህተቶች የሚማር ሁልጊዜ ትኩስ ነው፤ ለሕዝብ የተናገሩትን መሬት ላይ በተግባር ሁኖ መገኘት አለበት።
✔️ትሁትነት(Being Humbel)
መሪ ስትሆን እዩኝ እዩኝ ባይ አትሆንም፣ አትፈኮስም ይልቁንስ የአገልጋይነት መንፈስ ትላበሳለህ፣ የተከታዮችህን ስሜት ትረዳለህ ትጠብቃለህ።
👉በጥቅሉ የአንድ መሪ የመምራት ብቃት ከሚለካባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ውስጥ በቀውስ ውስጥ በትዕግሥት እና በጥበብ አልፎ ድርጅትን ለቀጣይ ተልዕኮ ማሻገር ሲቻል ነው።
©ሻለቃ ሙላቴ ሲሳይ
09/ዐ8/2018 ዓ.ም
አድማ ብተናዎች ድሽቃውን እንዳይሰራ አድርገውት መጡ!!
በመካነሰላም ግንባር አድማ ብተና እየፈረሰ ሲሆን የ22ኛ ሻለቃ አድማ ብተና የድሽቃ ምድብተኞችን ፋኖ ተቀብሏል:: የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ሰብሳቢ ሻለቃ አብነው ታደሰ እና የስራ አስፈጻሚ አርበኛ ተስፋው አማረ፣ የ29ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ ስንደው ገዜ እና የክፍለ ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ መብራቱ ጫብሲ፣ የክፍለ ጦሩ ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ መምህር አለማየሁ እንድሁም የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ አስማማው ፈንታው ለአድማ ብተና አባላቱ ደማቅ እና ወንድማዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል:: አንድ በግ ታርዶ ስርግና ምላሽ በመሰለ አግባብ አቀባበል የተደረገላቸው ከጠላት የከዱ አድማ ብተናዎች ወደየ ቤተሰቦቻቸው መሄድ ከፈለጉ የመሳሪያ ዋጋ እንድከፈላቸው የሚል ትእዛዝ የወረደ ሲሆን አልያ ደግሞ እንታገላለን ካሉ ከነ መሳሪያቸው እንድታገሉ የሚል አቅጣጫም ተሰጥቷል::
የድሽቃ ምድብተኞች ወደ ፋኖ የመጡት ቀን እና ማታ በየተራ ሲሆን አንዱ ሻለቃ አብነው ጋ ሲገባ ሌሎች የክፍለ ጦሩ አመራሮች ወዳሉበት ስፍራ ተጉዘው ተደብልቀዋል:: ከ87ኛ ክፍለ ጦር የከዱ መከላከከያዎችም አሉ::
አልበላሽምን ምን አመጣው?
ቴዲ አፍሮ የሕዝብን ልብ እንደ ሰደድ እሳት ሲያነቃቃው፣ በቤተ-መንግስት ሰገነት ላይ ያሉት ባለስልጣናት ግን "ጩኸት አያናውጠንም" በሚል የውሸት ጀግንነት ራሳቸውን እያታለሉ ቀጥለዋል።
" የውኃ ሙላት የቤት መሠረቱን እየናደው፣ ባለቤቱ ግን ጣሪያው ላይ ወጥቶ ይፎክራል"እንደሚባለው የሞኝ ፖለቲካ ነው።
በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን "ተራ መዝናኛ" የተባለው ጥበብ ዙፋኑን እንደገለባ እንዳላረገፈው ሁሉ፣ ዛሬም የሕዝብን የመቆጫ ድምፅ "ጩኸት" ብሎ ማጣጣል የመጨረሻው የውድቀት ዋዜማ ምልክት ነው።
ታሪክ እንደሚመሰክረው የሕዝብ ቁጣ በዜማ ሲቀመም ከመድፍና ከጠመንጃ በላይ የመገርሰስ ኃይል አለው። መሠረቱ በሚናድ ቤት ጣሪያ ላይ ሆኖ እንደአብይ አህመድ መደንፋት ግን የውስጥን ፍርሃት በውጭ ፉከራ ለመሸፈን የሚደረግ ከንቱ ፕሮፓጋንዳ ነው።
ይህ "ጩኸት" ተራ ድምፅ ሳይሆን፣ የስርዓቱን ግብዓተ-መሬት የሚያፋጥን የለውጥ ማዕበል መሆኑን ገዢዎች በቅርቡ ይረዱታል።
''ዩቲዩብ ላይ ድሮን አለመተኮሱ የማይቻል ቢሆንበት ነው'ጂ!'' የፓለቲከኛ ጌትነት ወርቁ መልዕክት
ስሙኝ የአስተሳሰብና ትርክት ልዩነት እንጂ ተራ ቂምና የተለመደው ዓይነት አፈና አይደለም!
ብልጽግና "የወል ትርክት" በሚሉት አጥፊ መዶሻ ኢትዮጵያዊ እሴትን ሲንድ፣ ትዝታን ሲያጠፋና ወርዶ ወርዶ የነጠላ ጥለት ሲቀድ በከረመበት ፍርስራሽ ላይኮ ነው ልጁ ብቅ ብሎ አዲስ የግንብ ጡብ የደረደረበትና የጥፋቱን ቋያ ውሐ የቸለሰበት። እና ቢከለክል ምን ይገርማል?! ዩቲዩብ ላይ ራሱ ድሮን አለመተኮሱ የማይቻል ቢሆንበት ነው'ጂ!
የረባም ዘፈን አድማጭ አይደለሁም። አንዱ ሁለቱ ግን እንደብሔራዊ መዝሙርና የቅኝ ግዛት ነጻነት የትግል ዜማ ዓይነት ነገር ይቃጣቸዋል ልበል?!
በዚሁ አጋጣሚ እንደ ባለዘይት ብቅ እያልክ ትውልዱን ከቁዘማና "አልቆልናል" መንፈስ ቁስል እየቀባህ ስለምትፈውስ ምሥጋናዬ ይድረስህ!
ምሶሶው ዘመም ጣራውም ያፈሳል
ሃገር የሞተበት የት ሄዶ ያለቅሳል
ባሳደገኝ ቀዬ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰው ሆኜ እንደሌለው ሃገር
ያቆምኳትን ሰንደቅ ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ ባንዲራዬን ላንሳት...
ሆ ሆ...
ጌትነት ወርቁ
♦ ይህም ይመዝገብ፦ ቴዲ አፍሮ እና የሸገር ዕንባ፦ "መሃል ገቡና አቆሙን ከዳር!"
ቴዲ አፍሮ “አዲስ አበባ አዶ ሸገሩ... በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር፤ መሃል ገቡና አቆሙን ከዳር” ሲል፣ የአዲስ አበባን ልጅ ወቅታዊ መሪር ስቃይ በሁለት ስንኞች ገልጦታል። ዛሬ አዲስ አበባ በኢኮኖሚ አሻጥርና በፖለቲካ ሴራ ልጆቿን እየተነጠቀች፣ ማንነቷን እየተገፈፈች ትገኛለች። ይህም ይመዝገብ!
🩸 የታሪክ ምስክርነት፦ ቀዳሚ መስዋዕት!
የአዲስ አበባ ልጅ ለሀገሩ ዲሞክራሲና ነጻነት የከፈለው ዋጋ ወደር የለውም።
በ1997 ዓ.ም፦ ሰኔና ጥቅምት ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች በአጋዚ ጥይት ደረታቸውን ሰጥተው "ድምጻችን ይከበር" ብለዋል። ዛሬ በቤተ-መንግሥት ያሉት ሳይቀሩ የሥልጣን መሰላል የሆነቸው ያ መስዋዕትነት ነው።
በ2010 ዓ.ም፦ ለውጥ መጣ ሲባል ሰኔ 16 ላይ የአዲስ አበባ ልጅ መስቀል አደባባይን በድጋፍ ማዕበል አጥለቅልቆ ተቀብሏል።
📸 ፎቶው የሚናገረው ሐቅ፦ መስከረም 4 ቀን 2011 ዓ.ም
ብዙዎች "ለውጡ የይስሙላ ነው" ብለው ሳይጠረጥሩ፣ የአዲስ አበባ ወጣት ግን ገና በማለዳው ክህደቱን አውቆታል። በቡራዩ፣ በሰበታና በአዲስ አበባ ዙሪያ ወንድሞቻችን (አማራ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ጋሞ...) በማንነታቸው ሲጨፈጨፉ፣ አዲስ አበባ "በቃ" ብላ አደባባይ ወጣች።
ይህም ይመዝገብ! የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የመጀመሪያውን ጥይት ያስተኮሰው በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ ነው።
ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት፣ ፍል ውሃና አምባሳደር አካባቢ የተቀረጸው ፎቶ ታሪክን በሰነድነት ያዘለ ነው።
በግልጽ እንደሚታየው፣ የአገዛዙ ወታደራዊ ኃይል (ሪፐብሊካን ጋርድ ተብሎ የሚጠራው)፣ የአልሞ ተኳሾችን (Sniper) በመጠቀም በንጹሐንና ባልታጠቁ ወጣቶች ላይ በጠራራ ፀሐይ ጥይት ሲተኩስ ነበር።
ይህ ፎቶ፣ ያኔ በአደባባይ የተገደሉት ንጹሐን ወጣቶች፣ የዚህ አገዛዝ ጨካኝነት የመጀመሪያ ማህተሞች መሆናቸውን ያረጋግጣል። ይህም ይመዝገብ!
የዛሬው በደል፦ በገዛ ከተማው ባይተዋር!
ዛሬ የአዲስ አበባ ልጅ፦
በፖለቲካ፦ መሪነቱን ተነጥቆ በማንነት ኮታ በሚመጡ ካድሬዎች እንዲገዛ ተፈርዶበታል።
በኢኮኖሚ፦ ከቤት ንብረቱ እየተፈናቀለ፣ የንግድ ቦታዎቹ እየተቀሙ ለደጋፊዎች ታድለዋል።
በማህበራዊ፦ "ባላባትና መጤ" በሚል የከፋፋይ ትርክት፣ ለዘመናት የገነባውን አብሮነቱን ሊያፈርሱት ሌት ተቀን ይሰራሉ።
ቴዲ አፍሮ “ባይተዋር ሰው ሆኜ እንደሌለው ሀገር” ሲል፣ ያቆማትን ከተማ በእሳት ለሚፈትኑትና ኢትዮጵያዊነትን ለሚገፉት ካድሬዎች ታላቅ መልዕክት አስተላልፏል። ጀግኖች በአርበኝነት ባቆሟት ከተማ ላይ፣ ዛሬ ኢትዮጵያዊነትን ማሳደድ የታሪክ ትልቅ ውርደት ነው።
አዲስ አበባን "ለእኛ ብቻ" ብለው ሊያጥሯት የሚሞክሩ አካላት፣ የሰኔ 97ቱንና የመስከረም 2011ዱን ወጣት ወኔ ዘንግተውታል። የአዲስ አበባ ልጅ ትዕግስተኛ ቢሆንም፣ ባንዲራው ሲገፋና ማንነቱ ሲናቅ ግን እንደ ነብር መቆጣት ያውቅበታል።
ይህም ይመዝገብ! አዲስ አበባ የሁሉ ናት፤ የሁሉ ሆናም ትቀጥላለች! በካድሬ ሴራ "ዳር የቆመው" የአዲስ አበባ ልጅ፣ ነገም እንደ ትናንቱ ለሀገሩ የቁርጥ ቀን ልጅ ሆኖ ይነሳል።
“ወይድ! አትንገረኝ ማንነቷን... ምጥ አታስተምር ልጅ እናቷን!”
ባንዲራየን አንሳው! 💪 💚💛❤
ይሄው ነው ልኩ የቴዎድሮስ ካሳሁን!
Dawit Amhara ከንጉስቹ መንደር!!
ሚያዝያ 09/08/2018 ዓ.ም
ስሙኝ የአስተሳሰብና ትርክት ልዩነት እንጂ ተራ ቂምና የተለመደው ዓይነት አፈና አይደለም!
ብልጽግና "የወል ትርክት" በሚሉት አጥፊ መዶሻ ኢትዮጵያዊ እሴትን ሲንድ፣ ትዝታን ሲያጠፋና ወርዶ ወርዶ የነጠላ ጥለት ሲቀድ በከረመበት ፍርስራሽ ላይኮ ነው ልጁ ብቅ ብሎ አዲስ የግንብ ጡብ የደረደረበትና የጥፋቱን ቋያ ውሐ የቸለሰበት። እና ቢከለክል ምን ይገርማል?! ዩቲዩብ ላይ ራሱ ድሮን አለመተኮሱ የማይቻል ቢኾንበት ነው'ጂ!
የረባም ዘፈን አድማጭ አይደለኹም። አንዱ ኹለቱ ግን እንደብሔራዊ መዝሙርና የቅኝ ግዛት ነጻነት የትግል ዜማ ዓይነት ነገር ይቃጣቸዋል ልበል?!
በዚኹ አጋጣሚ እንደ ባለዘይት ብቅ እያልክ ትውልዱን ከቁዘማና "አልቆልናል" መንፈስ ቁስል እየቀባህ ስለምትፈውስ ምሥጋናዬ ይድረስህ!
ምሶሶው ዘመም ጣራውም ያፈሳል
ሃገር የሞተበት የት ሄዶ ያለቅሳል
ባሳደገኝ ቀዬ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰው ሆኜ እንደሌለው ሃገር
ያቆምኳትን ሰንደቅ ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ ባንዲራዬን ላንሳት...
ሆ ሆ...
ጌትነት ወርቁ
የብልፅግና አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመው ያለውን ግፍ እና በመረዳት ከህዳር 10/2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 08/2018 ዓ.ም 77 የአገዛዙ ሰራዊት አባላት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #64ኛ_ክ/ጦር ተቀላቅለዋል።
1ኛ. ዘመነ ወርቁ ይበላል መኬ
2ኛ.ሙሉቀን ንጉስ መኬ
3ኛ. አንደበት ሞላ ሚኒሻ
4ኛ. ዘነበዉ ደሴ ሚኒሻ
5ኛ. በላይነህ ካሳ መኬ
6ኛ. ደመቀ አሰፋ መኬ
7ኛ. አዲሴ ያዜ መኬ
8ኛ. ጊዜአለው ክንዱ መኬ
9ኛ.መንግስቱ በላቸው ሚኒሻ
10ኛ. አየነው እንዳይፈር መኬ
11ኛ. አለበል አምሳሎ መኬ
12ኛ. ወንዱ አንተ መኬ
13ኛ. ሀብታሙ ፀጋው መኬ
14ኛ.መንግስቱ በላቸው ሚኒሻ
15ኛ. እሱባለው ደርጀው ሚኒሻ
16ኛ. ዘሩ ባዩ ሚኒሻ
17ኛ. አለወንድ ተሜ መኬ
18ኛ. ታዘብ ሞገስ መኬ
19ኛ.አበራ ጫልቂሳ መኬ
20ኛ.ሞላልኝ መልካም መኬ
21ኛ.አማኑኤል የሽዋስ መኬ
22ኛ.ነፃነት አበበ መኬ
23ኛ.ማሩ ውለተው መኬ
24ኛ.ዮኋንስ ምስጋነው መኬ
25ኛ.ግዛቸው ክንፉ መኬ
26ኛ.ደሳለኝ ደሞዝ መኬ
27ኛ.ብርሀኑ ጥላሁን መኬ
28ኛ.ሞሀበው እንዳልኬ መኬ
26ኛ.ሞገስ ዳዊት መኬ
27ኛ.ሞላልኝ ይበን መኬ
28ኛ.ይበልጣል አዱኛው መኬ
29ኛ. ሞላልኝ መኬ
30ኛ.መስፍኔ መለሰ መኬ
31ኛ.ፅሃው አለባቸው ሚሊሻ
32ኛ.ዳኔል ዋለ መኬ
33ኛ.ጌትነት ፀጋው መኬ
34ኛ.ስጦታው መሌ መኬ
35ኛ.እሸት ይመር መኬ
36ኛ. በልስቲ ጋሻው ፓራ ኮማንዶ
37ኛ.10 ዓለቃ አሰግድ አስጠራው መኬ
38ኛ.አክሊሉ ባይነስ መኬ
39ኛ. ደጓለ ታደሰ ፓራ ኮማንዶ
40ኛ. ኤሊያስ ጫሌ አዳነ መኬ
41ኛ.ባንቴ ጌታቸው ሚሊሻ
42ኛ.አይዋ አልማው ሚሊሻ
43ኛ. ከድር አብዲ መኬ
44ኛ.ገመቹ ገመዳ መኬ
45ኛ. ሀይሉ ሙንየ እንግዳ መኬ
46ኛ. ምኒችል ቡችል ሚሊሻ
47ኛ. ጌታው መሌ ሚሊሻ
48ኛ. ታደሰ ደሴ ሚሊሻ
49ኛ. ዛኪር ንጋቱ መኬ
50ኛ. ገረመው ለሙ መኬ
51ኛ.መሀመድ ደምሴ መኬ
52ኛ.ቢኒያም ግዛቸው መኬ
53ኛ. ይበልጣል አይዋ ሚኒሻ
54ኛ. አቃተ አስረስ ሚኒሻ
55ኛ. እያዩ መሰረት ሚኒሻ
56ኛ. ንጉሱ ደመቀ ሚኒሻ
57ኛ. ይላቅ ወንዳለ መኬ
58ኛ. ይልቃል አበጀ መኬ
59ኛ.ክንዱ አማኑኤል መኬ
60ኛ.10 አለቃ እሱባለው መኬ
61ኛ.ጂብሪል አህመድ መኬ
62ኛ.አቡ ጉልቱ መኬ
63ኛ.ንጉሴ ቀቡ መኬ
64ኛ. ታምሩ እማኝ መኬ
65ኛ. ይሁኔ ውዱ ሚኒሻ
66ኛ. እሸቱ አለማየሁ ሚኒሻ
67ኛ. መሰረት በልስቲ ፓራ ኮማንዶ
68ኛ. ታሪኩ በለይ ሚሊሻ
69ኛ. አራገው ደጀኔ መኬ
70ኛ. ደሳለኝ አባቴነህ ፓራ ኮማንዶ
71ኛ. መላኩ አያሌው ሚኒሻ
72ኛ. ደስታው መንበሩ ሚሊሻ
73ኛ. ውዱ ውል ሚሊሻ
74ኛ.ተጎዳ ሰውነት ሚሊሻ
75ኛ.የቻለ ፍሬው ፓራ ኮማዶ
76ኛ. ታደሰ ቢተው ፓራ ኮማንዶ
77ኛ. ኮንስታብል ሀብታሙ ደስአለኝ የተባሉ የፖሊስ እና ስማቸው ያልተዘረዘሩ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት በቅርብ ቀን የአማራ ትግል ወደ አንድ መምጣቱን በመገንዘብ የአገዛዙ ሰራዊት በጅምላ እየተናደ መሆኑንን እና አገዛዙ በሀገር መስራቹ የአማራ ህዝብ ላይ ከባድ ወንጀሎችን እየሰራ መሆኑን ክ/ጦሩን የተቀላቀሉ የአገዛዙ ኃይሎች አሳውቀዋል።
እራሱን መንግስት አድርጎ የሚንቀሳቀሰው አሸባሪው፣ ዘራፊው፣ ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ቡድን ለሰራዊቱ የሚሰጠው ትዛዝ ሀገር የሚያፈርሱ፣ አንዱን ብሔር ከአንዱ ብሔር የሚያጋጩ ትዛዞች እንደሚሰጣቸው በግልፅ አስረድተዋል።
ይህ አገዛዝ በዚህ ሰዓት ሀገር የመምራት አቅም እንደሌለው ዜጎች በገዛ ሀገራችው በሰላም ወጥተው በሰላም እንዳይንቀሳቀሱ የጦርነት ጉሰማ፣ የሀይማኖት ግጭቶት፣ የብሔር ግጭት የመሳሰሉት ነገሮች ላይ ብቻ ተጠምድ ሀገር ለመበታተን ተልዕኮ ይዞ እንደሚሰራ ከመከላከያ፣ ከሚሊሻ፣ ከአድማ ብተና፣ ከፖሊስ ተቋም የወጡ የአገዛዙ ሰራዊት አባሎች በሰፊው አስረድተዋል።
የአገዛዙ ሰራዊቱ አባላት በአገዛዙ ተስፋ መቁረጣቸውን የአማራ ህዝብም የኢትዮጵያ ህዝብም በአማራ ፋኖ ተስፋ ማድርግ እንዳለበት በፋኖ የተረፈው የአገዛዙ ሰራዊት በጅምላ እየከዳ እንደሚገኝ 64ኛ ክፍለ ጦር የተቀላቀሉት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት አሳውቀዋል።
በመከላከያ ተቋም ውስጥ የአማራ፣ደቡብ፣ሱማሌ እና አፋር የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በብሄራቸው ብቻ ተለይተው ከፍተኛ ድብደባ እና ብዙ ግፎች ይፈፀማሉ። የመከላከያ ቁመና የደከመነ ነው። መከላከያ የሞተ ቁመና ነው ያለው። የመከላከያ ሰራዊት ተበትኖል። በስነልቦና እና በስሜት በጀግንነት እየተጎዳ ነው ያለው። መከላከያ ህዝቡን በሙሉ እየጎዳ ነው ያለው። ይህ ሁሉ የሚሆነው መከላከያ ህዝቡን ከማገልገል ይልቅ ለግለሰብ ቁማርተኛ ፖለቲከኞች ቅጥረኛ ሆኖ ህዝቡ ላይ ብዙ ግፎችን እነፈፀመ ይገኛል።
አማራ ክልልን ለመውረር የገበው ዘራፊ ሰራዊት ፋኖን ገጥሞ ማሸነፍ የሚችል ሰራዊት አይደለም። የፋኖ ሰራዊት የሀገርን ዳር ድንበር የሚስከብር የውጭ ወራሪን የሚጠብቅ ጀግና ሰራዊት መኖሩን ለህዝባችን እና ለትግሉ ደጋፊ በሙሉ ይድርስ ብለዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
የካቲት 08/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
