en
Feedback
መራኁት

መራኁት

Open in Telegram

መራኁት ማለት መፍቻ፣ መክፈቻ፣ ቁልፍ ማለት ነው። ጥያቄዎቻችንን ቋጠሮአችንን በአባቶች ትምህርት እየፈታን አብረን እንጓዛለን። Tiktok: @mera_hut YouTube: @merahuut https://t.me/merahutchat

Show more
5 994
Subscribers
-124 hours
-127 days
-2830 days
Posts Archive
photo content

የክፍል አንድ ንባባችን እነሆ☺️ ዘውትር ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በ voice chat የምንቀጥል ይሆናል፣ እግዚአብሔር ያስፈጽመን። ለወዳጆቻችን ማጋራትን አንርሳ፤ ዛሬ ማታ እንገናኝ።

photo content

የመጽሐፍ ንባብ intro.m4a1.59 MB

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን! በመደበኛነት እዚህ ቻናል ላይ ትምህርት ለመስጠት ሐሳቦች ቢኖሩንም በሁኔታዎች አለመመቻቸት ምክንያት እስካሁን መጀመር አልቻልንም። መሰብሰባችን በከንቱ እንዳይሆን ግን ብርትት ብለን በጋራ መጽሐፍ የምናነብበትን ሁኔታ እያመቻቸን ነው😊 እናንተ ብቻ ፍቃደኛ ሁኑልን እና በጋራ እናነባለን። ምን ትላላችሁ?
Anonymous voting

https://vt.tiktok.com/ZSxccy4vm/ የወደፊት ሚስቴ😁

ምናልባት ያልሰማ ካለ ነገ የሐዋርያት ጾም ይገባል። ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲሆን የግድ የምንጾመው እንጂ በፍቃዳችን የምንተወው አይደለም፣ ስለዚህ ሁላችንም እየጾምን እየጸለይን ለነፍሳችን የሚበጀውን እንድናደርግ በፍጹም ፍቅር አሳስባለሁ። ብዙ ጸሎት የሚያሻኝ ደካማ ወንድማችሁን ብስራተ ገብርኤል ብላችሁ አስቡኝ😊

ይህችን ትምህርት ሳትሰሟት ዓመት ሞላት😒

እንኳን ለበዓለ ሐምሳ በሰላም አደረሰን😊 https://vt.tiktok.com/ZSxtGyThT/

ተመልሰናል😊 እስቲ አድምጡት እና እንወያያለን። https://vt.tiktok.com/ZSxsRY9vq/

ሰላም ተወዳጆች እሑድ ግንቦት 16 እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጥዋት 4:30 ጀምሮ ሰፊ ጉባኤ በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አዳራሽ ይኖረናል። መምህራን መዘምራን የተጋበዙ ሲሆን ስናገለግላቸው ከነበሩ ነዳያን መካከል እግዚአብሔር የፈቀደላቸው በዕለቱ ሥጋ ወደሙ ይቀበላሉ እኛም አብረናቸው እንቆርባለን። ብዙ በረከት ያለበት ጉባኤ ስለሆነ እንደማያመልጣችሁ ባለ ብዙ ተስፋ ነን😊። ለመቁረብ የተዘጋጃችሁ ወንድም እኅቶች ቅዳሜ ማታ እስከ 3:00 ባለው ሰዓት ድረስ እዛው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገናኝተን አብረን የምናድር ይሆናል። ቸር ያድርሰን😊

ዛሬ ልጅ ወይም ታናናሽ እኅት ወንድም ላላችሁ ሰዎች የሚሆን ጥሩ ድኅረ ገጽ አግኝቼ ምናልባት ከጠቀማችሁ በሚል ላስተዋውቅላችሁ ወደድኩ። check them out. ዛሬ ኦርቶጆይ(Orthojoy) የሚባል  የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ድረገፅ ይዘንላችው ቀርበናል።  ዕድሜያቸው ከ7-14 ላሉ ልጆች በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል። በውስጡም 👉 መንፈሳዊ ተረቶች 👉 የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ 👉 የገዳማት ታሪክ 👉የስዕል ማቅለም እና 👉ቃላት መገጣጠም ያካትታል። በየሳምንቱ 3 ትምህርቶች ይለቀቃሉ። በዚህ ተጠቃሚ የሚሆኑት ኢትዮጵያውን፣ በውጭ የሚገኙ ዲያስፖራዎች እንዲሁም በአኅት አብያተክርስቲያን(ግብፅ ፣ ኤርትራ ፣ ሶርያ፣ አርመንያ) ለሚገኙ ልጆች ተዘጋጅቷል። የድረገጽ ዋና ጥቅም 1. ልጆች መንፈሳዊ ተረት በሚያነቡበት ግዜ ሥርዓትን፣ መንፈሳዊ በሆነ መንገድ ችግር አፈታትን፣ ቤተሰብ ማክበርን እንዲሁም ከጓደኞቻቸው/ ከሌሎች ሰዎች ጋር እግዚአብሔር በሚወደው መልኩ እንዴት መኖር እንደሚችሉ ለማስተማር ይረዳል። 2. መጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ከብሉይና ከሐዲስ በማወጣጣት ልጆች ከታሪኩ መማር እንዴት እንደሚችሉ ያሳያል 3. የቤተክርስቲያን / ገዳማት ታሪክ በተለይም ኢትዮጵያ እና አኅት አብያተክርስቲያናት የሚገኙ ከ1700 በላይ ያስቆጠሩ ገዳማት ታሪኮች ሲኖሩት ልጆች ለቤተክርስቲያን ያላቸው ፍቅር እንዲጨምር እና የሀገራቸውን ብሎም የአኅት አብያተክርስቲያናት እውቀታቸው እንዲጨምር ይረዳል። 4. የሥዕል ማቅለምና የቃላት መገጣጠም በውስጡ ሲኖር ልጆች ቅዱሳንን፣ ቤተክርስቲያንን እና የቤተክርስቲያን መገልገያዎችን በማቅለም በጨዋታ መልክ ዕውቀታቸው እንዲጨምር ይረዳል። በተጨማሪም የቃላት መገጣጠም በቤተክርስቲያን የምንጠቀማቸውን ቃላት ልጆች እንዲያቁት በጨዋታ መልክ በመፈልግ ይማራሉ። በአጠቃላይ ልጆች ከትምህርት ጋር እንዳይሰለቹ አዝናኝ አስተማሪ በሆነ መንገድ አጠር አድርገን አቅርበናል። ይህንን ለማግኘት www.orthojoy.org ላይ በመግባት መመዝገብ ይችላሉ። በተጨማሪም ዕድሜያቸው ከ3-6 ላሉት ህጻናት መንፈሳዊ መለማመጃ ወረቀቶችን ከጭቃ ቀለም እና መቀስ ጋር አዘጋጅተናል። ማንኛውንም ጥያቄ/ ሐሳብ በ0972237501 በመደወል ማግኝት ይችላሉ። በተጨማሪም የማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉ Website- www.orthojoy.org Tiktok- https://www.tiktok.com/@orthojoy21?_r=1 Telegram- https://t.me/Orthojoy Instagram- orthojoy21 0997287825

Until it happens to you, you think you are too careful to make that mistake, too smart to fall for that trap, too mature to lose control, too private to get exposed, too religious to drift, too responsible to collapse. Life has a way of dismantling every identity built on certainty."

ሰላም ተወዳጆች፣ እስቲ እዚህ ቻናል ላይ መቀላቀላችሁ ካልቀረ ትንሽም ቢሆን እንድትጠቀሙ የሆነ ትምህርት ነገር ብንማር ብዬ እያሰብኩ ነበር፣ ምን ትላላችሁ? ምንስ እንማር?

"የተናገርከው ነገር ምንም ያህል እውነት ቢሆን በፍቅር ካልተናገርከው ከውሸት የማይሻል ጥቅም አልባ ነው!" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳጆች የት አላችሁ😊 በመልዕል ሚዲያ ፀሐይ ዘልዳ የተሰኘ አዲስ መዝሙር ይዘን ብቅ ብለናል። አትጋበዙም ወይ😁