en
Feedback
Wellness Three

Wellness Three

Open in Telegram

Hello 👋 3

Show more
158
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-530 days
Posts Archive
Repost from N/a
የዛሬው የጤና መረጃችን ስለ ጨብጥ (Gonorrhea) በሽታ ነው። ጨብጥ በባክቴሪያ የሚመጣና በግንኙነት የሚተላለፍ የተለመደ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ነው።ወቅታዊና አስፈላጊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላች
የዛሬው የጤና መረጃችን ስለ ጨብጥ (Gonorrhea) በሽታ ነው። ጨብጥ በባክቴሪያ የሚመጣና በግንኙነት የሚተላለፍ የተለመደ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን ነው።ወቅታዊና አስፈላጊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ! 🔍 ዋና ዋና ምልክቶችብዙ ጊዜ ወንዶች ላይ ምልክት የሚያሳይ ሲሆን፣ ሴቶች ላይ ግን ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል።በወንዶች ላይ: በሚሸኑበት ጊዜ ማቃጠል፣ ከብልት ነጭ፣ ቢጫ ወይም አረንጓዴ ፈሳሽ መውጣት እና የዘር ፍሬ ማበጥ/መምታት።በሴቶች ላይ: የሴት ብልት ፈሳሽ መብዛት ወይም ቀለም መቀየር፣ በሚሸኑበት ጊዜ ማቃጠል እና ከወር አበባ ውጪ የሚታይ የደም መፍሰስ። ⚠️ ካልታከሙ ምን ሊያስከትል ይችላል?የልጅ መውለድ ችግር (መካንነት)ለኤች.አይ.ቪ (HIV) እና ለሌሎች ኢንፌክሽኖች የመጋለጥ እድልን ማሳደግኢንፌክሽኑ ወደ ደምና መገጣጠሚያዎች መሰራጨት 💊 መፍትሄው ምንድነው?ጨብጥ በሀኪም በሚታዘዝ የኣንቲባዮቲክ (Antibiotic) መድሃኒት ሙሉ በሙሉ ይድናል።ማሳሰቢያ: እራስዎን በራስዎ መድሃኒት ከመግዛት ይቆጠቡ፤ ምክንያቱም ባክቴሪያው መድሃኒት የመላመድ ባህሪ አለው። 🛡️ እንዴት መከላከል ይቻላል?ኮንዶም በአግባቡ መጠቀም።የአንድ ለአንድ ግንኙነት መወሰን።ምልክቱ ከታየ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ እና የትዳር/የፍቅር አጋርንም አብሮ ማታከም።ጤናዎ በቁጥጥርዎ ስር ነው!ይህ መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ Share ያድርጉ። 👇👇👇 Join @sexualwellness101

Repost from N/a
🔴 ስለ ቂጥኝ (Syphilis) ምን ያህል ያውቃሉ?ቂጥኝ (Syphilis) በባክቴሪያ የሚመጣ እና በግብረ-ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ከባድ የጤና እክል ነው። በሽታው በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ህመም ስ
🔴 ስለ ቂጥኝ (Syphilis) ምን ያህል ያውቃሉ?ቂጥኝ (Syphilis) በባክቴሪያ የሚመጣ እና በግብረ-ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ከባድ የጤና እክል ነው። በሽታው በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ህመም ስለማያሳይ ብዙ ሰዎች ሳይገነዘቡት ሊቆዩ ይችላሉ።📌 ዋና ዋና ምልክቶች (Symptoms) ደረጃ 1፦ በብልት፣ በፊንጣጣ ወይም በአፍ አካባቢ የሚወጣ ህመም የሌለው ትንሽ ቁስል (Chancre)። ደረጃ 2፦ በእጅ መዳፍ እና በእግር ጫማ ላይ የሚወጣ ሽፍታ፣ ትኩሳት፣ የሊምፍ እጢዎች ማበጥ እና የድካም ስሜት። ደረጃ 3 (የመጨረሻ ደረጃ)፦ በሽታው ሳይታከም ለዓመታት ከቆየ ልብን፣ አንጎልን እና የነርቭ ሥርዓትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል። 🤰 ከእናት ወደ ልጅ መተላለፍነፍሰ ጡር እናት በበሽታው ከተያዘች ወደ ፅንሱ ሊተላለፍ ይችላል። ይህ በፅንሱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ወይም ውርጃ ሊያስከትል ስለሚችል በቅድመ-ወሊድ ምርመራ ወቅት መታየት ይኖርበታል። 🛡️ መከላከያ መንገዶች (Prevention)ታማኝነት፦ ከአንድ ታማኝ የትዳር አጋር ጋር ብቻ መወሰን።ኮንዶም መጠቀም፦ በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶምን በአግባቡ መጠቀም።መደበኛ ምርመራ፦ ምልክቱ ባይታይም እንኳ በየጊዜው የደም ምርመራ ማድረግ። 💊 ሕክምናው ምንድነው?ቂጥኝ በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ላይ በፔኒሲሊን (Penicillin) እና በሌሎች አንቲባዮቲኮች በቀላሉ ይድናል። ዋናው ነገር በጊዜ መታየት እና ህክምናውን በአግባቡ መጨረስ ነው።👉 እራስዎን እና የሚወዱትን ሰው ይጠብቁ! ማንኛውንም ያልተለመደ ምልክት ካዩ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ይመረመሩ። 🗣️ መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ #Share ያድርጉ Join @sexualwellness101

Repost from N/a
✅ከብልት ቢጫ ወይም አረንጓዴ ፈሳሽ ✅በታችኛው የሆድ ክፍል ውስጥ ህመም ✅በቆለጥ ውስጥ ህመም ✅በሽንት ወቅት የሚቃጠል ስሜት በፊንጢጣ ውስጥ የክላሚዲያ ኢንፌክሽንም ሊከሰት ይችላል። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች የተለመዱ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ ✅ፍሳሽ ✅ሕመም ✅ከፊንጢጣ አካባቢ የሚመጣ የደም መፍሰስ በሴቶች ላይ የክላሚዲያ ምልክቶች ብዙ ሴቶች የክላሚዲያ ምልክቶችን ላያስተውሉ ይችላሉ። የተለመዱ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ የሚያሰቃይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት (dyspareunia) በታችኛው የሆድ ክፍል ውስጥ ህመም በሽንት ወቅት የሚቃጠል ስሜት የማህጸን ጫፍ እብጠት (የማህጸን ጫፍ እብጠት) በወር አበባ ጊዜያት መካከል የደም መፍሰስ የሴት ብልት ፈሳሽ ክላሚዲያ በፊንጢጣ ላይም ሊበክል ይችላል። የፊንጢጣ ክላሚዲያ ያለባቸው ሴቶች ምልክቶች ላያሳዩ ይችላሉ፣ ነገር ግን የፊንጢጣ ህመም፣ ፈሳሽ መፍሰስ እና የደም መፍሰስ ሊከሰት ይችላል።

Repost from N/a
🗣️ክላሚዲያ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ኢንፌክሽን (STI) ሲሆን በባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣ ነው። ክላሚዲያ trachomatis (ሲ. ትራኮማቲስ) አንድ ሰው በበሽታው ከተያዘ በኋላ ክላሚዲ
🗣️ክላሚዲያ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ኢንፌክሽን (STI) ሲሆን በባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣ ነው። ክላሚዲያ trachomatis (ሲ. ትራኮማቲስ) አንድ ሰው በበሽታው ከተያዘ በኋላ ክላሚዲያን በብልት፣ በፊንጢጣ ወይም በአፍ በሚፈጸም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለባልደረባው ሊያስተላልፍ ይችላል። ባልደረባዎች በክላሚዲያ ባክቴሪያ የተበከሉ የወሲብ መጫወቻዎችን ሲጋሩ ኢንፌክሽኖችም ሊከሰቱ ይችላሉ። በግምቶች መሠረት ከ40% እስከ 96% የሚሆኑት ክላሚዲያ ያለባቸው ሰዎች ምንም ምልክት ላይኖራቸው ይችላል። ሆኖም ግን፣ ያልታከመ ክላሚዲያ ከባድ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። 🗣️የክላሚዲያ የህይወት ዑደት የክላሚዲያ ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድናቸው? በመነሻ ደረጃ ላይ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች በሚከተሉት ምክንያቶች ይከሰታሉ ክላሚዲያ trachomatis ብዙውን ጊዜ ጥቂት ወይም ምንም ምልክቶች አያመጡም። ምልክቶቹ ቢከሰቱም እንኳ ብዙውን ጊዜ መለስተኛ እና በቀላሉ ችላ ሊባሉ ይችላሉ። ምልክቶቹ በወንዶችና በሴቶች መካከል ትንሽ ሊለያዩ ይችላሉ። 🗣️በወንዶች ላይ የክላሚዲያ ምልክቶች ብዙ ወንዶች ክላሚዲያ ያለባቸው ምንም አይነት ምልክት አያስተውሉም። በጣም የተለመዱት ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ Join @sexualwellness101

Repost from N/a
1k Subscriber Challenge Join @sexualwellness101 💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
1k Subscriber Challenge Join @sexualwellness101 💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪

Repost from N/a
✍️እየጨመረ የመጣው የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ 👉የተለያዩ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች #የኤች_አይ_ቪ_ኤድስ ቫይረስ ስርጭትን እየጨመሩት መጥተዋል ከነዚህም ውስጥ ✅የደም አይነቴ O ስለሆነ የኤች አይ
✍️እየጨመረ የመጣው የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ 👉የተለያዩ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች #የኤች_አይ_ቪ_ኤድስ ቫይረስ ስርጭትን እየጨመሩት መጥተዋል ከነዚህም ውስጥ ✅የደም አይነቴ O ስለሆነ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ አይዘኝም ✅ለትንሽ ደቂቃ ጾታዊ ግንኙነት ባደረግ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ አይዘኝም ✅ወዲያው #የዘር ፈሳሽ ከፈሰሰኝ አይዘኝም ✅ወዲያው ከታጠብኩ አይዘኝም ✅ኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ እና #አባላዘር በሽታዎች መያዝን ከመፍራት ይልቅ እርግዝና እንዳይፈጠር ትኩረት መስጠት 📌መፍትሄው ✅ማንኛውም ሰው እራሱን ከኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ እና ከአባላዘር በሽታዎች መጠበቅ ይገባዋል። ✅የተለያዩ ትምህርቶች ሰለ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ እና የአባላዘር በሽታዎች መሰጠት ያስፈልጋል ✅በተጨማሪም አንዳንድ አጠራጣሪ ነገሮች ሲታዩ የጤና ባለሞያ ማማከር አስፈላጊ ነው። Join @sexualwellness101

Repost from N/a
ወንዶች በምን ምክንያት መካን ይሆናሉ? መካንነት በአብዛኛው የሴት ተደርጎ ይሳላል ነገር ግን መካንነት የሚመጣው 1/3ተኛው ከወንዱ፣ 1/3ተኛው ከሴቷ እና 1/3ተኛው ከሁለቱም ችግር ነው። በዚህ ጽሁ
ወንዶች በምን ምክንያት መካን ይሆናሉ? መካንነት በአብዛኛው የሴት ተደርጎ ይሳላል ነገር ግን መካንነት የሚመጣው 1/3ተኛው ከወንዱ፣ 1/3ተኛው ከሴቷ እና 1/3ተኛው ከሁለቱም ችግር ነው። በዚህ ጽሁፍ የምናየው የወንዶች መካንነት እንዴት ይመጣል የሚለውን ነው። ከነዚህም ውስጥ አንደኛው #የስፐርም ችግር ነው ይህም የስፐርም መጠን ማነስ ፣ ከቅርጹ ማነስ እና መንቀሳቀስ ሲያቅተው መካንነት በወንዶች ላይ ያስከትላል። ሌላኛው የዘር #ፍሬ ላይ የደም ስር ማበጥ ነው ይህ ደግሞ ደም እንዳይመላለስ ስለሚያረግ ይህም በስፐርም አካባቢ ሙቀት በመጨመር የስፐርም ቁጥር እንዲቀነስ ያደርጋል በዚህም የተነሳ በወንዶች ላይ መካንነት ሊያስከትል ይችላል። በተጨማሪም ስፐርም በትክክለኛው መንገድ መውጣት ሲያቅተው እና ወደ ሽንት ፊኛ ሲገባ የስፐርምን ትክክለኛውን መንገድ ጠብቆ የመውጣት ሂደት ስለሚያቆም ለመካንነት ያጋልጣል። ሌላኛው መካንነትን ከሚያስከትሉ ነገሮች ውስጥ ስፐርምን የሚያመርቱ ሆርሞኖች ሲያንሱ ነው። ምክኒያቱም እነዚህ ሆርሞኖች ዋነኛ ስራቸው እስፐርም ማምረት ስለሆነ ምርቱን ሲያቆሙ ለመካንነት የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል። እንዲሁም የተለያይዩ መድሃኒቶች መወሰድ በተለይም የደብርት፣ የካንሰር፣ የደም ግፊት መድሃኒቶች የስፐርም ጥራትን በመቀነስ ለመካንነት ሊያጋልጡ ይችላሉ። በመጨረሻም መካንነት እና ሌሎች የስነ ተዋልዶ ጉዳዮች ዙሪያ የጤና ባለሙያ በማማከር ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ። Join @sexualwellness101

Repost from N/a
1k Subscriber Challenge Join @sexualwellness101 💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
1k Subscriber Challenge Join @sexualwellness101 💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪

Repost from N/a
✍️#ቪያግራ ተጠቅመን ለምን ለወጥ አያመጣም ? 👉ቪያግራ ወደ #ብልት የሚሄደውን #የደም ፍሰት ለጊዜው በመጨመር የወንድ ብልት ቀጥ እንዲል እና ጥንካሬ እንዲኖረው ያደርጋል። 👉ነገር ግን ቪያግራ
✍️#ቪያግራ ተጠቅመን ለምን ለወጥ አያመጣም ? 👉ቪያግራ ወደ #ብልት የሚሄደውን #የደም ፍሰት ለጊዜው በመጨመር የወንድ ብልት ቀጥ እንዲል እና ጥንካሬ እንዲኖረው ያደርጋል። 👉ነገር ግን ቪያግራ የጾታው ፍላጎትን አይጨምርም 👉ቪያግራ ዋነኛ ስራው የጾታው ፍላጎት ኖሯቸው ብልታቸው አልቆም ሲል የደም ፍሰት ለጊዜው በመጨመር የወንድ ብልት ቀጥ እንዲል እና ጥንካሬ እንዲኖረውማድረግ ነው። 👉እንዲሁም አብዛኛው ሰው ቪያግራን ዝም ብሎ ከፋርማሲ ያለ ሀኪም ፍቃድ ይገዛል ነገርግን ከብዙ ነገሮች አንጻር ተመርምሮ በሀኪም ቢታዘዝ ይመከራል። Join @sexualwellness101

Repost from N/a
✅አቁሞ መቀጠል ይህም በጾታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፈሳሽ ሊመጣ ሲል የወንዱ ብልት እዛው የሴትዋ ብልት ወስጥ ሆኖ ለ 10 ሰከንድ ከእንቅስቃሴ ገታ በማለት ከዚያም ብልቱ ሲረጋጋ ጾታዊ ግንኙነት መቀጠል ሌላኛው አማራጭ ነው ✅ጤናም የአኗኗር መንገድ መከተል ከተለያዩ ሱሶች መቆጠብ ማለትም ጫት፣ ሲጋራ፣ አልኮል ፣ #ፖርኖግራፊ እንዲሁም ሌሎች ጤናችንን ሊጎዱ ከሚችሉ ነገሮች መቆጠብ በጣም አስፈላጊ ነው። 👉ጣፋጭ እና ጮማ መቀነስ ያስፈልጋል እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬ መመገብ ይመረጣል Join @sexualwellness101

Repost from N/a
✍️#በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ፈጥኖ መጨረስን ለማሻሻል የሚረዱ መፍትሄዎች 👉እነዚህ #በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ፈጥኖ መጨረስን ለማሻሻል የሚረዱ መፍትሄዎች በቤት ውስጥ ልናደርጋቸው የምንችላቸው እና ከ
✍️#በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ፈጥኖ መጨረስን ለማሻሻል የሚረዱ መፍትሄዎች 👉እነዚህ #በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ፈጥኖ መጨረስን ለማሻሻል የሚረዱ መፍትሄዎች በቤት ውስጥ ልናደርጋቸው የምንችላቸው እና ከሶስት እስከ ስድስት ወር ሊወስዱ የሚችሉ ናቸው። እስክ 70 % አዋጪ መንገድ ነው እንዲሁም ምንም አይነት ጉዳት የለውም። ✅KEGEL Exercise መስራት ነው ይህም #KEGEL Exercise ትኩረት የሚያረገው ሽንት በሚሸናበት ሰዐት ሽንትን ለማቋረጥ በምንጠቀመው ጡንቻ ላይ ነው።  á‹­áˆ… ጡንቻ #በጾታዊ በግንኙነት ወቅት #የዘር ፈሳሽ ለመቆጣጠር የምንጠቀመው ክፍል ነው ስለዚህ ይህንን ጡንቻ ማሰራት በግንኙነት ወቅት ስነፈተ ወሲብን ለመቆጣጠር ያግዛል                                                                                               đŸ‘‰áˆľáˆˆá‹šáˆ… ይህን KEGEL Exercise ከ5 እስከ 10 ሰከንድ በተደጋጋሚ በቀን ውስጥ 20 እስከ 30 ጊዜ መስራት። ✅#ጭንቀት መቀነስ ይህም የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም ይቻላል አተነፋፈስ በማስተካከል፣ በጸሎት እንዲሁም ሌሎች አመራጮችን በመጠቀም ጭንቀትን መቀነስ ይቻላል። Join @sexualwellness101

Repost from N/a
ስለ BLUE BALLS / የዘር ፍሬ ህመም /ሰማያዊ የዘር ፍሬ ምን ያውቃሉ 📌ሴቶች በወር አበባ ጊዜ ህመም እንደሚያጋጥማቸው ወንዶችስ ተመሳሳይ ህመም ያጋጥማቸዋልን ? 📌blueballs /ሰማያዊ
ሾለ BLUE BALLS / የዘር ፍሬ ህመም /ሰማያዊ የዘር ፍሬ ምን ያውቃሉ 📌ሴቶች በወር አበባ ጊዜ ህመም እንደሚያጋጥማቸው ወንዶችስ ተመሳሳይ ህመም ያጋጥማቸዋልን ? 📌blueballs /ሰማያዊ የዘር ፍሬ ህመም  የሚባለው በወንዶች ላይ የሚያጋጥም ችግር ሲሆን ይህም የሚከሰተዉ ወንዶች ረዘም ላለ ጊዜ በወሲብ ተነቃቅተው (ለምሣሌ በመሳሳም ፤ በመተሻሸት) ቆይተው ያለ ወሲብ ወይም ያለ እርካታ / orgasm ሲያቆሙ የዘር ፍሬያቸው ላይ  ከፍተኛ የህመም ስሜት ያጋጥማቸዋል ። 📌ይህ ህመም ጊዜያዊ ሲሆን ምንም የጤና ጉዳት አያስከትልም ። እንዲሁም ህመሙ ከተወሰነ ቆይታ በኋላ በራሱ ጊዜ ወይም ደግሞ የዘር ፈሳሽን በማፍሰስ ይጠፋል። 📌ሰማያዊ የዘር ፍሬ የተባለበት ምክንያት በተወሰነ መልኩ የዘር ፍሬው ላይ ያለው ቆዳ ወደ ሰማያዊ ስለሚቀየርና ወንዶችን የሀዘን ስሜት እንዲሰማቸው ስለሚያደርግ ነው (ሰማያዊ = ሀዘን)። 📌ይህ ችግር ከጊዜያዊ ህመም ባሻገር ምንም አይነት የጤና ጉዳት አያመጣም ነገር ግን የህመም ስሜቱ ከባድ ሊሆን ይችላል። 📌 መፍትሔ ፦ ቀዝቃዛ ሻወር ፤ በጀርባ መተኛትና እንቅስቃሴ ለተወሰነ ሰዓት መቀነስ ፤ በበረዶ ወይም ሞቅ ባለ ውሃ በጨርቅ የዘር ፍሬን ለማ  10 ደቂቃ መያዝ። 📌ከጊዜ በኋላ ህመሙ ካልጠፉ ሀኪሞትን ያማክሩ። 🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳🔳 Join the channel 🔥 🔥 🔥 @sexualwellness101

Repost from N/a
✍️#መድሃኒትን ተጠቅሞ ተደጋጋሚ #ውርጃ ማድረግ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች 📌በተደጋጋሚ በመድሃኒት በመጠቀም ውርጃ ሲደረግ ✅#በማህጸን ላይ #ኢንፌክሽን እንዲጨምር ያደርጋል ✅ድጋሚ እርግዝና እንዳይፈ
✍️#መድሃኒትን ተጠቅሞ ተደጋጋሚ #ውርጃ ማድረግ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች 📌በተደጋጋሚ በመድሃኒት በመጠቀም ውርጃ ሲደረግ ✅#በማህጸን ላይ #ኢንፌክሽን እንዲጨምር ያደርጋል ✅ድጋሚ እርግዝና እንዳይፈጠር ሊያረግ ይችላል ✅ከማህጸን ውጭ እርግዝና እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል ✅የወደፊት የማርገዝ እድል ይቀንሳል ✅ወደፊት እርግዝና በሚፈጠርበት ሰዐት ለድግምግሞሽ ውርጃ ሊጋለጡ ይችላሉ ✅ያለጊዜው ለሚመጣ ምጥ ተጋላጭ ይሆናሉ 👉ስለሆነም ከእነዚህ ጉዳቶች እራስን ለማራቅ ተመራጩ መፍትሄ #የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም ነው። በወሊድ መቆጣጠሪያው አይነት እና ተስማሚነት ዙሪያ የጤና ባለሙያ በማማከር ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ። Join @sexualwellness101

Repost from N/a
@sexualwellness101 ∆∆ join

Repost from N/a

Repost from N/a
📌በተለይም ለስኳር ህመም ተብሎ የሚወሰደው metformin በከፍተኛ ደረጃ የቴስቴስትሮን መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል። ይህንንም ተያይዞ metformin መወሰድ ማቆም ደግሞ የስኳር መጠን እንዲጨምር እና ለሌላ ከባድ አደጋ ያጋልጣል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ቁልፍ መፍትሄው ከዶክተር ጋር በመመካከር የስኳር እና የቴስቴስትሮን መጠን መከታተል እናም ደግሞ መድሃኒት በመቀየር መቆጣጠር ይቻላል። ✅በመጨረሻም የልብ ድካም፣ የኩላሊት እና የጉበት ድክመት ያለባቸው ስዎች የቴስቴስትሮን መጠናቸው ሊቀንስ ይችላሉ። ❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️

Repost from N/a
✍️የቴስቴስትሮን ወይም የወንድ ሆርሞን ምንድን ነው? እንዴት ሊቀንስ ይችላል? 👉የቴስቴስትሮን ሆርሞን ማለት ወንዶችን ጺም እንዲያበቅሉ ፣ ድምጻችው እንዲጎረንን እና በአጠቃላይ ወንዶችን ወንድ የሚ
✍️የቴስቴስትሮን ወይም የወንድ ሆርሞን ምንድን ነው? እንዴት ሊቀንስ ይችላል? 👉የቴስቴስትሮን ሆርሞን ማለት ወንዶችን ጺም እንዲያበቅሉ ፣ ድምጻችው እንዲጎረንን እና በአጠቃላይ ወንዶችን ወንድ የሚያስመሰል ሆርሞን ነው።  ይህ ሆርሞን በሚቀንስበት ወቅት ወንዶች በከፍተኛ ደረጃ ለሰንፈተ ወሲብ ይጋለጣሉ። ከዚህም ጋር በተያያዘ የተለያዩ መንሴዎች ይጠቀሳሉ።       📌ቴስቴስትሮን ሆርሞን እንዴት ይቀንሳል? ✅የመጀመሪያው ከፍተኛ የሰውነት ክብደት መጨመር ሲሆን ይህም ለቴስቴስትሮን መቀነስ ጉልህ ሚና አለው ከዚህም ጋር በተያያዘ የተስትካከለ የሰውነት አቋም ለቴስቴስትሮን ሆርሞን እጅግ ጠቃሚ ነው። ✅ሁለተኛው ሀይለኛ ማንኮራፋት (Obstructive sleep apnea) ያለባችው ሰዎች ሲሆኑ በዝህም የተነሳ የቴስቴስትሮን ሆርሞናቸው ሊቀንስ ይችላል። ✅በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ የኤችአይቪ ኤድስ (HIV/AIDS) ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች ለዝህ ተጋላጭ ናቸው።  በተለይም ለረጅም ጊዜ ሳይቆጣጠሩት ሲቀሩ የቴስቴስትሮን መጠናቸው ይቀንሳል። ✅በአራተኛ ደረጃ የስኳር ህመም (Type 2 Diabetes) ታማሚ ከሆኑ እንዲሁ የቴስቴስትሮን ሆርሞን መቀነስ ሊጋለጡ ይችላሉ ። ይህም የሚሆነው የስኳር መጠን ለረጅም ጊዜ ከፍ ብሎ በሚቆይበት ጊዜ ነው። ከዚህም ጋር በተያያዘ የተለያዩ የምንወስዳቸው መድሃኒቶች ለቴስቴስትሮን መጠን መቀነስ ሊያጋልጡን ይችላሉ።                                                                                                                          🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑🔑 @sexualwellness101

Repost from N/a
የልብ ህመም ካለብዎት: ለልብ ህመም ናይትሬት (nitrate) የያዙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ። እነዚህን መድሃኒቶች ከናይትሬት ጋር አብሮ መውሰድ ለሞት ሊዳርግ የሚችል ከባድ የደም ግፊት መቀነስ ሊያስከትል ይችላል።   የደም ግፊት ችግር ካለብዎት: ዝቅተኛም ሆነ ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብዎ።   የጉበት ወይም የኩላሊት በሽታ ካለብዎት: የመድሃኒቱ ተጽእኖ በሰውነትዎ ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ ሊራዘም ስለሚችል የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያባብስ ይችላል።   ከሀኪም ወይም ከሳይኮሎጂስት ጋር መነጋገር: የስንፈተ ወሲብ መንስኤ የአእምሮ ጭንቀት ወይም ስነልቦናዊ ከሆነ ከሙያተኛ ጋር መነጋገር ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።    እነዚህ ምክሮች ከመድኃኒቱ ጋር ተዳምረው የበለጠ ውጤታማነት እንዲያገኙ ይረዳዎታል። ◽◽◽◽◽◽◽◽◽◽◽◽◽◽◽◽◽ @sexualwellness101

Repost from N/a
የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) መድኃኒቶች! የስንፈተ ወሲብ ችግርን ለማከም በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የ PDE5 inhibitors በመባል የሚታወቁ መድኃኒቶች ናቸው። እነዚህ
የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) መድኃኒቶች! የስንፈተ ወሲብ ችግርን ለማከም በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የ PDE5 inhibitors በመባል የሚታወቁ መድኃኒቶች ናቸው። እነዚህ መድኃኒቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ: Sildenafil (Viagra) Tadalafil (Cialis) Vardenafil (Levitra) Avanafil (Stendra) እንዴት ነው የሚሰሩት? እነዚህ መድሃኒቶች የሚሰሩት በብልት ውስጥ ያሉ የደም ስሮች እንዲከፈቱ እና የደም ዝውውር እንዲጨምር በማድረግ ነው። ይህ የሚሆነው PDE5 የሚባለውን ኢንዛይም (enzyme) በመከላከል ነው።       የ PDE5 ኢንዛይም የብልት ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ እና የደም ፍሰት እንዲቀንስ ያደርጋል። ስለዚህ እነዚህ መድሃኒቶች የ PDE5 ኢንዛይምን ሲገቱት የብልት ጡንቻዎች ዘና እንዲሉ በማድረግ ደም በቀላሉ ወደ ብልቱ እንዲፈስ ያደርጋሉ፣ ይህም ለግንኙነት የሚያስችል ጥንካሬ ያለው ብልት እንዲቆም ይረዳል። ማን መውሰድ የለበትም? እነዚህን መድሃኒቶች ከመውሰድዎ በፊት የጤና ሁኔታዎን ለሀኪምዎ መንገር በጣም አስፈላጊ ነው። በተለይም የሚከተሉት የጤና ህመሞች ካሉዎት እነዚህን መድሃኒቶች መውሰድ የለብዎትም:  đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸đŸ”¸ @sexualwellness101

Repost from N/a
✍️የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ወይም ማነስ ለመካንነት ሊያጋልጥ ይችላል? 👉#የታይሮይድ ሆርሞን የዘር ፈሳሽ ምርት እና እድገትን ይቆጣጠራል። 👉የታይሮይድ ሆርሞን ከመጠን በላይም ከሆነ ወይም ከመጠ
✍️የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ወይም ማነስ ለመካንነት ሊያጋልጥ ይችላል? 👉#የታይሮይድ ሆርሞን የዘር ፈሳሽ ምርት እና እድገትን ይቆጣጠራል። 👉የታይሮይድ ሆርሞን ከመጠን በላይም ከሆነ ወይም ከመጠን በታችም ሲሆን በዘር ፈሳሽ ምርት ላይ ተጽእኖ ያሳድራል 👉የታይሮይድ ሆርሞን በከፍተኛ ደርጃ በሚመርትበት ወቅት በዘር ፈሳሽ ምርት ላይ ከሚያስከትላቸው ጉዳቶች ውስጥ ✅የዘር ፈሳሽ መጠን ሊቀንስ ይችላል ✅የዘር ፈሳሽ ቁጥር ይቀንሳል ✅የዘር ፈሳሽ ቅርጽ ያዛባል ✅የዘር ፈሳሽ እንቅስቃሴ እንዲቀንስ ያደርጋል 👉በዚህም የተነሳ #በመካነንት ምርምራ ላይ አንድ ከሚደርጉ ምርመራዎች ወስጥ የታይሮይድ ሆርሞን መጠን አንድ እና ዋነኛው ነው። 🛑ምክንያቱም ወንዶችን መካን የማድረግ አቅም ስላለው። Join @sexualwellness101