𝗚𝗲𝗿𝗮𝗺𝗶 𝗛𝗮𝘀𝗮𝗯𝗼𝗰𝗵 ™
الذهاب إلى القناة على Telegram
This channel is your go-to source for mastering: 🧠 Mindset & Focus – Build unshakable discipline and mental clarity. 📚 Psychology & Philosophy – Understand yourself, think deeper, live better. 👔 Style & Presence – Look sharp, feel confident.
إظهار المزيد187
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-330 أيام
أرشيف المشاركات
‹‹እያንዳንዳችን በውስጣችን የሴት ምስል እንሸከማለን፤ ይህም ከእናታችን ምስል የተወሰደ ቅጂ ነው። ከዚህ በመነሳት ለሴቶች ያለን አመለካከት በእናታችን ይወሰናል፦ እናከብራቸዋለን፣ ወይ እንንቃቸዋለን አልያም ደግሞ ለእነሱ ግድ የሌለው ሰው እንሆናለን!።››
—ፍሪድሪክ ኒቼ
Armemo_offica
🎴@Enmare1988
🎴@Enmare1988
Manipulation
ብዙ ጊዜ በፍልስፍና እና የስነልቦና ውይይቶች ውስጥ በተለይም በሃይማኖት እና ፖለቲካ ርዕሶች ላይ Manipulation የሚል ቃል እንጠቀማለን። ይህ ግን ቃል ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሆነ ሃሳብም ጭምር ነው።
Manipulation ምንድን ነው? ማኒፒዩሌሽን የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ማታለል ወይም ማጭበርበር ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን ሃሳቡም:
የሰዎች ሃሳብ፣ ስሜት ወይም ድርጊት ላይ ከዕውቅናቸው ውጪ ወይም ሳያስተውሉት ተጽዕኖ ማድረስ ወይም መቆጣጠር የሚል ነው።
Manipulation ግልጽ የሆነ ስለት ያለው ዓይነት ብቻ ሳይሆን ፈገግታ የሚለብሰም ነው። ፍቅርን፣ ፍርሀትን እና ቋንቋን እንደ መሳሪያ የሚጠቀም አይነት ነው።
Manipulation ስለ ጥንካሬ አይደለም። ትክክለኛውን ስሜታዊ ጊዜ የመጠበቅ ችሎታ ነው። ስትደክሙ፣ አብሮነትን ስትራቡ ወይም ትርጉም ስፈልጉ ያውቃል። በሩን አይንኳኳም—በወረስናቸው ታሪኮች እና እኛ ለመፈተሽ በጣም በምንፈራቸው እምነቶች ውስጥ ይንሸራተታል።
ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በመተማመን ነው። አንድ ሰው የእናንተን እሴቶች ያንጸባርቃል፣ ቋንቋችሁን ይናገራል፣ ፍርሃታችሁን “ቅዱስ”፣ ህመማችሁን “የእቅዱ አካል” ብሎ ይጠራቸዋል። ድንገት ስትነቁ እሱን እየተከተላችሁ አይደለም—እሱ እንድትሆኑ የገነባላችሁን የእራሳችሁን ስሪት እየተከተላችሁ ነው።
Manipulation በሃይማኖታዊ አመራር ውስጥ እንደ መለኮታዊ ማስፈራሪያ ሆኖ ይመጣል።
“ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣ አትጠይቁ” ተብላችኋል።
ግን የእግዚአብሔር ድምፅ ጭምብል ለብሶ ወግ ቢሆንስ የሚያስተጋባው?
የገሃነም ፍርሃት፣ የመዳን ተስፋ—እነዚህ ሁልጊዜ መንፈሳዊ እውነቶች አይደሉም። ስሜታዊ መልህቆች ናቸው። እምነትን እየመረጣችሁ አይደለም። ከእሳት እየሸሻችሁ ነው።
በፖለቲካውም ውስጥ ተመሳሳይ ቲያትር ነው።
መሪዎች “እኛ የህዝብ ነን እነሱ ጠላት ናቸው” ይላሉ።
እና ልክ እንደዚህ ውስብስብነት አፈር ይበላዋል።
Manipulation ሐሰተኛ ግልጽነትን ይፈጥራል። እንድታስቡ አይፈልጉም—ቶሎ ምላሽ እንድትሰጡ ይፈልጋሉ፣ እንድታስተጋቡ።
ቁጣ ምንዛሬ ይሆናል። ታዛዥነት መልካም ባህርይ ይሆናል። ጥርጣሬ ክህደት ይሆናል።
ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ እውነተኛ ችግሮች— ድህነት፣ ኢፍትሃዊነት፣ ድንቁርና—ዝምታን ለብሰው ባሉበት ነው።
አንዳንዶች "ሁሉም Manipulation ክፉ አይደለም
አንዳንድ ጊዜ እናት ለልጇ ስለ ከባድ እውነት ለስላሳ ታሪክ ትናገራለች።
አንዳንድ ጊዜ አስተማሪ የተኛ አእምሮን ለመቀስቀስ ምቾት መንሳት ያመጣል።
ያ ጭካኔ አይደለም—ስልታዊ እንክብካቤ ነው።" ሲሉ ይሞግታሉ።
ስለዚህ ጥያቄው የሚሆነው: የማንቂያ Manipulation ስህተት ነው?
ወይስ አሳሪ ሰንሰለት ሲሆን ብቻ ነው ስህተት የሚሆነው?
እና ከዚያ Self-manipulation አለ—በጣም ቅርብ የሆነ አይነት—ራስን ማጭበርበር።
መታዘዝ ጥበብ እንደሆነ እራሳችንን እናሳምነዋለን።
የተወረሱ እሴቶችን እንደ ግላዊ እውነቶች እንቆጥራለን።
ጥርጣሬን ባላየ ፈገግ እንላለን።
ሥነ ምግባር ብለን እንጠራዋለን፤ ግን ምናልባት የተለባበሰ ፍርሃት ብቻ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ Manipulationን እንዴት እንዋጋለን?
በንዴት አይደለም። በኩራት አይደለም። በግልጽነት ብቻ።
እንጠይቃለን፡ ይህ እምነት ከየት ነው የመጣው?
የማንን ድምጽ ነው የምታዘዘው?
እያሰብኩ ነው—ወይስ ሀሳብን እየተወንኩ?
ማጭበርበር አንዴ ከተሰየመ ኃይሉን ያጣል።
እና ፍርሃት አንዴ ከተጠየቀ፣ መንገዳችንን ሊመራ አይችልም።
ቀዳማዊ ፍልስፍና
(ዮናታን በጋሻው)
@zephilosophy
በ Psychology ታሪክ ውስጥ እንደ Carl Jung እና Sigmund Freud የጠበቀ ወዳጅነት የነበራቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው። ፍሮይድ ዩንግን እንደ እንደ መንፈሳዊ ልጁ ይመለከተው ነበር። ነገር ግን ይህ ጥልቅ ወዳጅነት The Collective Unconscious በሚል አዲስ እይታ ምክንያት አበቃለት 😅
ፍሮይድ የሰው ልጅ ባህሪ ሁሉ የሚመነጨው ከ Sexual Repression ነው ብሎ ያምን ነበር። ዩንግ ግን ይህንን አልተቀበለም። የሰው ልጅ አእምሮ ከዚያ በላይ ጥልቅ ነው በማለቱ በሁለቱ መካከል የነበረው የሰባት ዓመት ወዳጅነት በ 1913 እንዳይሆን ሆኖ ተቋረጠ። ያው ፍሮይድ ተማሪው አታውቅም ሲለው የተሰማው ስሜት ነው የተሰማው ።
ከፍሮይድ ጋር መለያየቱ ለዩንግ ቀላል አልነበረም። ለስድስት ዓመታት ያህል Confrontation with the Unconscious በሚለው የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ አለፈ። በዚህ ወቅት የሚያስፈሩ ራዕዮችን ያይ ነበር ፣ እንግዳ ድምፆችን ይሰማ ነበር ። በአእምሮ ህመም የተጎዳ ሆነ።
ዩንግ በዚህ የጭንቀት ወቅት ያያቸውን እና የተሰሙትን ነገሮች በሙሉ በታዋቂው The Red Book ላይ አስፈረ። በዚህ የጨለማ ጉዞ ውስጥ ነበር ትልቁን እውነት ያገኘው፦ Archetypes!
ዩንግ እንደተረዳው እኛ ከወላጆቻችን የአይን ቀለም ወይም ቁመት ብቻ አይደለም የምንወርሰው። ይልቁንም መላውን የሰው ልጅ የሚያገናኙ Psychological Patterns እንወርሳለን።
እነዚህም፦
📌 The Hero
📌The Shadow
📌The Wise Old Man
እነዚህ ምልክቶች እና ታሪኮች በየትኛውም ባህል እና ዘመን ውስጥ በሰው ልጅ አእምሮ ውስጥ አሉ። ይህ ግኝት ስነ ልቦናን ለዘላለም ቀየረው።
ዩንግ እንደሚለው እያንዳንዳችን በውስጣችን ደብቀን የምንይዘው ለሰው የማናሳየውና እንዲያውም የእኔ አይደለም ብለን የምንክደው ጨለማ ክፍል አለን። ይህ Shadow ይባላል። እኛ መልካም ቅዱስ እና ሰላማዊ መስለን ለመታየት ስንጥር ይህ ሻዶ ግን በውስጣችን ተደብቆ እድሉን ይጠብቃል።
የካርል ዩንግ Shadow የተሰኘው እሳቤ በአጭሩ ሲገለጽ፦ የማንነታችን ጨለማ ክፍል ማለት ነው።
ይህ ክፍል እኛነታችን ሆኖ ሳለ ነገር ግን ለህብረተሰቡ ወይም ለራሳችን ካለን መልካም ግምት ጋር ስለማይሄድ ደብቀን የምንይዘው ማንነታችን ነው።
ሻዶዋችን ውስጥ የሚከተቱት ነገሮች ብዙውን ጊዜ በህብረተሰቡ ዘንድ መጥፎ ተብለው የሚታሰቡ እንደ ቁጣ ቅናት ስግብግብነት እና የፆታ ስሜቶች ናቸው። ነገር ግን ሁልጊዜ መጥፎ አይደሉም አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ያፈናቸው ጠንካራ ተሰጥኦዎቻችንም እዚያው ሊደበቁ ይችላሉ።
የራሳችንን ሻዶ ካልተቀበልን ያንን ባህሪ በሌሎች ሰዎች ላይ እናያለን። ለምሳሌ እኛ በውስጣችን ያለውን የቅናት ስሜት ካልተጋፈጥን በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ሁሉ ቀናተኞች እንደሆኑ አድርገን እናስባለን። ሁሉም ሰው ይቀናብኛል ፣ እኔ ቅዱስ ነኝ አይነት ሙድ የሚያራምዱና እራሳቸውን በተለየ መነጽር የሚያዩ ሰዎች የሚያስፈሩኝ ለዛ ነው።
ሻዶህን አትፍራው ይልቁንም ተጋፈጠው ሻዶዋችንን ካልተጋፈጥነው እኛን መንዳት ይጀምራል። ሳናውቀው እንቆጣለን ሳናውቀው እንቀናለን፣ ሳናውቀው ጥላቻ ውስጥ እንወድቃለን። ዩንግ እንደሚለው፦ until you make the unconscious conscious, it will direct your life and you will call it fate. ውስጣዊው ድብቅ ማንነትህን ነቅተህ ካላወቅኸው፣ ህይወትህን እየመራው እጣ ፈንታዬ ነው ትላለህ። እንደማለት
ብዙዎቻችን ከጭንቀታችን ከብቸኝነታችን እና ከውስጣዊ ትርምሳችን ለመሸሽ እንሞክራለን። ነገር ግን ዩንግ ያስተማረን Look into the abyss የሚለውን ነው። ዩንግ ከፍሮይድ ጋር ተጣልቶ ባያብድ ኖሮ ዛሬ ስለ Archetypes ወይም ስለ Collective Unconscious የምናውቀው ነገር አይኖርም ነበር። ታላቅ ለውጥ የሚመጣው ከታላቅ ስብራት በኋላ ነው። ዛሬ እየታገልክበት ያለው የውስጥ ጨለማ ምናልባትም ነገ ለምትሆነው አዲስ ማንነት እንደ ግብዓት የሚያገለግልህ ሊሆን ይችላል።
Shadowህን አትክደው ይልቁንም ተቀበለው። ምክንያቱም ሙሉ ሰው መሆን ማለት perfect መሆን ሳይሆን የራስን ጨለማ እና ብርሃን አቀናጅቶ መያዝ ማለት ነው።
"No tree, it is said, can grow to heaven unless its roots reach down to hell." — Carl Jung
Yared Girma
ነፍሴን ሳዳምጣት
ሠርክ ከሚባዝን
እንጀራን
ውበትን
ህይወትን ፍለጋ
ማነህ ያጣበቅኽኝ እንዲህ ካለ
ሥጋ
ይሄን ያክል አጥንት
ጅማት ምናምንቴ ላዪ
በመማገር
እዚህ ጥቁር ዋሻ
ግዞት ያወረድከኝ ማነህ በል
ተናገር
ፍርግርጉን አጥር
ይሄን ጥፍጥፍ ጭቃ በርቅሼልህ
ሳልበር
ከዚህ ገላ ጋራ
ማነህ ያዋደድከኝ ቶሎ በል
ተናገር
መፅሀፍ -መደድ
ገጣሚ-ኑረዲን ዒሳ
@zephilosophy
አምስቱ የማንነት ክፍሎች
ታዋቂው የስዊዘርላንድ የስነ-ልቦና ጠቢብ ካርል ዩንግ (Carl Jung) የሰው ልጅን ማንነት በአምስት በክፍሎች ከፍሎታል። ወደ ዝርዝር ትንታኔው ከመግባታችን በፊት፣ እነዚህን ማንነቶችን በአጭሩ እንመልከት፦
1. ንቁ አእምሮ (The Conscious Mind/Ego): አሁን የምናስብበት፣ የምናውቀውና "እኔ" ብለን የምንጠራው ማንነታችን ነው።
2. ጭንብል (The Persona): ለሰዎችና ለማህበረሰቡ እንዲታይልን የምንለብሰው "ጥሩ ሰው" የመምሰል ካባ።
3. ጥላ (The Shadow): የደበቅነው፣ የገፋነውና የማንቀበለው የጨለማ ማንነታችን።
4. ተቃራኒ ጾታዊ ማንነት (Anima/Animus): በወንዶች ውስጥ ያለው ሴታዊ ባህሪ እና በሴቶች ውስጥ ያለው ወንዳዊ ባህሪ።
5. እውነተኛው ማንነት (The Self): እነዚህን ሁሉ አዋህዶ የያዘውና የሰው ልጅ ሊደርስበት የሚገባው የመጨረሻው የጥበብ ደረጃ።
ይቀጥላል
#share
@enlighten_ethiopia
"እኔ ማን ነኝ?”
ብዙውን ጊዜ ስለ "እኔነት" (the self) በሚደረግ ማሰላሰል ውስጥ አንድ የተለመደ ጥያቄ ይነሳል፡- "እኔ ማን ነኝ?”
ይህ ጥያቄ ምክንያታዊ እና እንዲያውም አስፈላጊ ጥያቄ እንደሆነ ይታሰባል። እያንዳንዱ የሚያሰላስል የሰው ልጅ በመጨረሻ ሊመልሰው የሚገባው ጥያቄ እንደሆነም ይታመናል። ሆኖም በጥንቃቄ በመረመርነው ቁጥር ውስንነቱ ይበልጥ ይገለጣል። ጥያቄው በራሱ "እኔነት" (the self) የምንለው ነገር ተፈጥሮው ቋሚና አስቀድሞ የተሰራ ሆኖ ተለይቶ ስም እስኪሰጠው የሚጠብቅ ነገር እንደሆነ ይገምታል። ምናልባት ይበልጥ ሐቀኛው ጥያቄ “እኔ ማን ነኝ?” የሚለው ሳይሆን “እኔ ምን እየሆንኩ ነው?” (ወደ ምን እየተቀየርኩ ነው?) የሚለው ነው።
ሰው መሆን ማለት የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረስ ማለት አይደለም። መንቀሳቀስ፣ መለወጥ፣ በሽግግር ውስጥ መኖር ማለት ነው። ከቁሶች በተለየ መልኩ የሰው ልጆች ፈጽሞ ያለቁ (የተጠናቀቁ) አይደሉም። ወንበር ሊቀመጡበት ሲቻል የተጠናቀቀ ነው። ህንጻ ሲቆም የተጠናቀቀ ነው። ሰው ግን መጠናቀቅን ይቃረናል። ከተወለድንበት ቅጽበት ጀምሮ፣ ያልተጠናቀቅን፣ ክፍት፣ ለጊዜ፣ ለልምድ እና ለለውጥ የተጋለጥን ፍጡራን ነን። ይህ ያልተጠናቀቀ ተፈጥሯችን ብዙውን ጊዜ እንደ ድክመት ይቆጠራል።ብዙዎቻችን "እኔነት" የሆነ ቦታ በውስጣችን የተቀበረ የጠፋ እቃ ይመስል "ራሳችንን ስለማግኘት" እናወራለን። ነገር ግን ፍልስፍና ይበልጥ የሚረብሽ እና ይበልጥ ሐቀኛ የሆነ ነገር ይጠቁማል፡ ምናልባትም በፍለጋ የሚገኝ “የተጠናቀቀ እኔነት” ላይኖር ይችላል።
ፍሬድሪክ ኒቼ “ማንነትህን ሁን” (Become who you are) ሲል ይህንን ውጥረት ገልጾታል። አባባሉ ብዙውን ጊዜ እንደ አነቃቂ ምክር ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፤ ነገር ግን ፍልስፍናዊ ጥልቀቱ እምብዛም አይስተዋልም። ኒቼ በግራ መጋባት ንብርብሮች ስር የተደበቀ እውነተኛ እኔነት አለ እያለ አልነበረም። ይልቅም ወደ አንድ ተግባር እየጠቆመ ነበር። መሆን (Becoming) ግኝት ሳይሆን ፈጠራ ነው። የተወለድነው ማንነታችንን ይዘን አይደለም። በጊዜ፣ በምርጫ፣ በትግልና በትርጓሜ አማካኝነት ራሳችንን መቅረጽ አለብን።
ሲሞን ዲ ቦቮር፣ “ሰው ሆኖ አይወለድም፤ ይሆናል እንጂ” (One is not born, but rather becomes) ብላ ስትጽፍ ይህንን ሃሳብ ይበልጥ ግልጽ አድርጋዋለች። በዚህ እይታ ማንነት ስጦታ አይደለም። ሂደት ነው። ቀስ ብሎ፣ ብዙ ጊዜ በህመም እና አልፎ አልፎ ብቻ በእቅድ መሠረት ይገለጣል። በኪሳራ፣ በፍቅር፣ በብስጭት፣ በእውቀት እንለወጣለን። እና ሆኖም ግን ይህንን እውነት እንቃወማለን። ዘለቄታን እንፈልጋለን። ከፊታችን የሆነ ቦታ ከአሁን በኋላ የማይጠራጠር፣ የማይታገል፣ ጎዶሎነት የማይሰማው የመጨረሻ እና በራስ መተማመን ያለው የራሳችን ስሪት እንዳለ ማመን እንፈልጋለን።
ግን አለመጠናቀቅ (ጎዶሎነት) ጉድለት ባይሆንስ? የመሆን ዋነኛው ሁኔታ እሱ ቢሆንስ?
ዘመናዊ ሕይወት በማንነት አባዜ ተጠምዷል። በሙያ፣ በእምነት፣ በርዕዮተ-ዓለም፣ በስኬት ወይም በደረጃ ራሳችንን እንድንገልጽ ያለማቋረጥ እንጠየቃለን። ነገር ግን ማንነት በስያሜዎች መያዝ ለሚያስችል በቂ ጊዜ አይቆምም። ዣን ፖል ሳርተር “ህልውና ከምንነት ይቀድማል” (existence precedes essence) በማለት ተከራክሯል፤ ማለትም መጀመሪያ እንኖራለን (እንገኛለን) በኋላም በተግባር ራሳችንን እንገልጻለን። ተገፎ እንዲወጣ የሚጠበቅ ቋሚ የሰው ልጅ ተፈጥሮ የለም። ያሉት ምርጫዎችና ከእነሱ ጋር የሚመጣው ኃላፊነት ብቻ ነው።
ይህ ሐሳብ በእውነቱ ይረብሻል። ቋሚ እኔነት ከሌለ ምንም ዋስትናዎች የሉም ማለት ነው። ዛሬ ያላችሁ ማንነት ነገ የምትሆኑትን አያረጋግጥም። እያንዳንዱ ውሳኔ ይቀርጻቹሃል፤ ነገር ግን የትኛውም ውሳኔ አያጠናቅቃችሁም። እምቢታ፣ ማመንታት እና ዝምታ እንኳን በ"እኔነት" ግንባታ ውስጥ ይሳተፋሉ። ምን ዓይነት መዋቅር እየፈጠርን እንደሆነ ሳናውቅ እንኳን ሁልጊዜም ራሳችንን እየገነባን ነው። ይህ እርግጠኛ መሆን አለመቻል ጭንቀት ይፈጥራል። ነገር ግን ጭንቀት የግድ የድክመት ምልክት አይደለም። ሶረን ኬርኬጋርድ ጭንቀትን “የነጻነት ማዞር” (the dizziness of freedom) ሲል ገልጾታል። የሚከሰተው የሆነ ነገር ስለተበላሸ ሳይሆን የሆነ ነገር ክፍት ስለሆነ ነው። ሕይወታችሁ አስቀድሞ የተወሰነ እንዳልሆነ፣ መምረጥ እንዳለባችሁ፣ ማንም ለእናንተ ሊመርጥላችሁ እንደማይችል መረዳት ነጻ አውጪም አስፈሪም ነው።
ነጻነት ከባድ ነው፤ ኃላፊነትን ይጠይቃል። ከምርጫዎቻችን መዘዞች እና ወደ ኋላ መመለስ ካለመቻል ጋር እንድንኖር ያስገድደናል። ፍርሃት የሚሰማን አቅም ስለሌለን ሳይሆን ስለምናውቅ (aware ስለሆንን) ነው። የተሳሳተውን መምረጥን እንፈራለን። ሕይወታችንን ማባከንን እንፈራለን። ለራሳችን እንግዳ መሆንን እንፈራለን። ሆኖም ፍርሃት በዚህ አተያይ የ“መሆን” ጠላት አይደለም። እንደነቃን (aware እንደሆንን) ማስረጃ ነው።
ሰው መሆን ማለት እርግጠኛ አለመሆንን ማስወገድ ሳይሆን እርግጠኝነት በማጣት ውስጥ እንዴት መኖር እንዳለብን መማር ነው። ጥርጣሬ የእድገት ተቃራኒ አይደለም፤ ብዙውን ጊዜ አብሮት የሚሄድ ጓደኛ ነው። ግራ መጋባት ሁልጊዜ ውድቀትን አያመለክትም፤ አንዳንዴ የጥልቀት ምልክትም ነው።
በዚህ ሂደት ውስጥ ጊዜ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ለውጥ እየሆነ እያለ እምብዛም አናስተውለውም። ረቂቅ ነው። በፀጥታ ይከማቻል። የምንገነዘበው ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት እና ድሮ እንደነበርን አይነት ሰው እንዳልሆንን ስንረዳ ብቻ ነው። ሄንሪ በርግሰን ጊዜን በሰዓቶች በኩል ሳይሆን በሕያው ተሞክሮ በኩል የተሻለ እንደምንረዳው ተከራክሯል። የአንድ አፍታ ህመም ማለቂያ በሌለው ሁኔታ ሊለጠጥ ይችላል፣ የዓመታት ልማድ ደግሞ ያለምንም ትውስታ ሊጠፋ ይችላል። ሆኖም ሁለቱም አሻራ ይተዋሉ።
ሄራክሊተስ በታዋቂው የወንዝ ምሳሌ ይህንን እውነት ገልጾታል፡ ማንም ሰው ወደ አንድ ወንዝ ሁለት ጊዜ አይገባም፣ ምክንያቱም ወንዙም ሆነ ሰውዬው እንደነበሩ አይቆዩምና። ጊዜ ይቀርጽናል እንጂ ዝም ብሎ በላያችን ላይ አያልፍም። የተወሰኑ ክፍሎቻችንን እየሸረሸረ ሌሎቹን ይገልጣል። ይወስዳል ግን ይሰጣልም።
በጊዜ መጨረሻ ላይ የሚጠብቀን የመጨረሻ የ"እኔነት" ስሪት የለም። መሆን (Becoming) ማብቂያ ነጥብ የለውም። ሕይወት ወደ እርግጠኝነት ወይም ወደ ፍጽምና እንድንደርስ አትጠይቀንም። የምትጠይቀን እንድንቀጥል ብቻ ነው፤ በአስተውሎት፣ በሐቀኝነት፣ በድፍረት።
ኒቼ በአንድ ወቅት አንድ ሰው የሚደንስ ኮከብን ለመውለድ በውስጡ ትርምስ ሊኖረው ይገባል ብሎ ጽፏል። ትርምስ በዚህ አተያይ ሊወገድ የሚገባው ሥርዓት አልባነት አይደለም። እምቅ አቅም ነው። ለውጥን የሚፈቅድ ክፍትነት ነው። ሙሉ በሙሉ መኖር ማለት ከትርምስ ማምለጥ ሳይሆን በትርምስ ውስጥ ትርጉምን እንዴት መቅረጽ እንዳለብን መማር ነው።
የመሆን አርክቴክቸር ከእርግጠኝነት፣ ከስኬት ወይም ከመጠናቀቅ አይገነባም። የሚገነባው ከእንቅስቃሴ፣ ከግንዛቤ እና ያልተጠናቀቁ ሆኖ ከመቆየት ድፍረት ነው።
✍️ዮናታን በጋሻው (ቀዳማዊ ፍልስፍና)
@Kedamawi369
ቀቢፀ ተስፋ
አዝናለሁ። በመንፈሴ ብሩህ አይደለሁም። የራሴን ማንነት የማውቅበት ዕድልና ፋታ አልነበረኝም። አንድ ማለዳ በእኔና በካህኑ አባቴ ክፍል መካከል ከቤቱ መሠረት ጋር ለዘመናት ቆሞ የነበረው ግድግዳ ከሥፍራው በአንዳች ተአምር ተነሥቶ አገኘሁት። ከድንጋጤዬ ጋር የአንድ ቁራ ማስካካት በጆሮዬ ገባ። ግድግዳውን ምን ወሰደው? ቀን እየመጣ ቀን እየሄደ በድካም ታከትኩ። ነፍሴ እየተረበሸች እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም። የማስተናግዳቸው ስሜቶች ቋሚ አይደሉም። በኅሊናዬ ውስጥ የሚፈራረቁት ዐሳቦች ያረገርጋሉ። የምኖርበት ዓለምና ሀገር ሥርዐትና ቅርጽ አልባ ናቸው። ድሀ ተበደለ፣ ፍርድ ተጓደለ ብሎ በአደባባይ የሚጮኽ የለም። ውስጥ ለውስጥ ጨለማ ይንሰራፋል። የትውልድ ተስፋ ይሞታል። በአርባና በሰማንያ የማይቆርጥ ኀዘን ልብ ሰርስሮ ይገባል። የወጣት ወንዶች እሳትነት ይከስማል። የኮረዶች አበባነትም ይጠወልጋል። ጌታዬ ሆይ እንዴት እንደሚኖር ሳላውቅ ለሰጠኸኝ ሕይወት “ይቅር” አልልህም። ደግሞም ዓይኖቼን አንሥቼ እሳት ወይ አበባ ያልኾንኩበት ዕድሜዬን ከመኖር እንዳትቈጥረው እለምንሃለሁ።
✍️እሱባለው አበራ
#Nomorewar
@zephilosophy
⛔️ርዕስ:- የፍልስፍና ሀሁ
ደራሲ:- ፖል ክሌንማን
ትርጉም:- ራሴላስ ጋሻነህ
ይዘት:- philosophy ( ፍልስፍና )
የገፅ ብዛት:- 333
<አዕምሮ የበላይ ከሆነ : አስሮ የሚወስን ሀይል ይሆናል>
አብዛኛውን ጊዜ ነፍሳችሁ :የማሰብ ሀይላችሁ እና ውሳኔ አሰጣጣቹ በጥልቅ የፍቅር ስሜታችሁ እና በፍላጎታችሁ ላይ ጦርነት የሚያውጅበት የጦር ግንባር ነው።
ማሰብ ሀይላችሁ(አዕምሮአችሁ) እና ጥልቅ የፍቅር ስሜታችሁ የባህር ተጓዥ ለሆነው ነፍሳችሁ መቅዘፊያ ሸራዎች ናቸው። መቅዘፊያችሁ(ሸራዎቻችሁ) ቢቀደዱ ተገልብጣችሁ ከመንሳፈፍ ወይም በረጋው ባህር ከመገተር በስተቀር ምንም ልታደርጉ አትችሉም.......
የማሰብ ሀይል ሁልጊዜ የበላይ ከሆነ: አስሮ የሚወስን ሀይል አይሆንምን? ጥልቅ የፍቅር ስሜትስ ቢሆን ተቆጣጣሪ ከሌለው ለገዛ ራሱ ጥፋት የሚነድ ነበልባል አይሆንምን?..........
ስለዚህ የማሰብ ሃይላችሁ በሀሴት ይዘምር ዘንድ ነፍሳችሁ እስከ ጥልቅ የፍቅር ስሜታችሁ ድረስ ያወድሰው። ራሱን አቃጥሎ ከገደለ ቡሃላ ከአመድ ውስጥ ነፍስ ዘርቶ እንደሚነሳ የፊኒክስ ወፍ ጥልቅ የፍቅር ስሜታችሁም በገዛ እራሱ የእለት ተእለት ትንሳኤ ውስጥ ይኖር ዘንድ የማሰብ ሃይላችሁ ይምራው .........
በቤታችሁ ውስጥ #ሁለት ተወዳጅ እንግዶችን በምታዩበት አይን ፍርድ አሰጣጣችሁንና ፍላጎታችሁንም እንደነሱ እንድትቆጥሯቸው እመክራቹሀለሁ ......
.
በእርግጥ ለአንዱ እንግዳ ከለሌላው የበለጠ ክብር አትሰጡም። ለአንዱ አብዝቶ የተጨነቀስ የሁለቱንም ፍቅርና እምነት ያጣ የለምን?.......
ሰላምና እርጋታውን ያገኛችሁ ጊዜ:...ልባችሁ በፀጥታ "እግዚአብሄር በአእምሮአችን ውስጥ ይደር" ይበል.....
በእግዚአብሄር አፅናፈ ክበብ ውስጥ ያላችሁ እስትንፋስ ናችሁና.... በእግዚአብሄር ጫካ ውስጥ የምትገኙ ቅጠልም ናችሁና እናንተም በአእምሮ ሀይል ውስጥ ልታድሩ እና በጥልቅ የፍቅር ስሜት ልትንቀሳቀሱ ይገባችኋል።
ካህሊል ጂብራን
@zephilosophy
‹‹ለማወቅ የሚኖርንም ሰው እወዳለሁ . . .የማወቅ ፍላጎቱም በምድር ላይ ታላቅ ሰው ይኖር ዘንድ ምክንያት ሁኗልና . . .ምንም እንኳን በዚያ ሂደት የራሱን ውድቀት እንደሚያፋጥን ባውቅም እውቀትን የሚፈልጋት እሱ ታላቅ ሰው ነው፡፡ከመልካም ስራው በፊት መልካም ቃላት የሚናገርና ከተናገረውም በላይ የሚሰራ ሰው እወዳለሁ . . . ቢያንስ ቃሉን አክባሪ ነውና . . .የቱንም ያህል አምላኩ ቢቀጣው አምላኩን የሚወድ ሰው ደግሞ አከብራለሁ፤ ምክንያቱም አምላኩን የሚወድ ሰው በቁጣው ውስጥም ማለፍ ይችላልና . . . ነፍሱ እየደማች ጥንካሬ ያልተለያትን ሰው እወዳለሁ፣ ድልድዩ የተሰራው ለእንደሱ ዓይነቱ ነውና . . .ከጠቆረው ደመና ዕለት ዕለት ‹ጠብታወች› ወደምድር ይወርዳሉ . . . እነዚህ ጠብታወች ሰዎች ቢሆኑም የሚናገሩት የምስራች ግን የመብረቁን መምጣት ነው . . . እነሆ መብረቁ ደግሞ ታላቅ ሰው ነው . . . ››
ዛራቱስትራ
ፍሬድሪክ ኒቼ
@zephilosophy
«ስለፍቅር ሲባል የተደረገ [ነገር] ከሞራል መመዘኛዎች በላይ ነው! »
Beyond good and evil, Frederick Nietzsche, page 153
[ፈላስፎች ወይም ጉሩዎች በኖሩበት ዘመን ስለጭንቀት ምን ብለዋል? ]
🗯️
“ከኒሂሊስት ይልቅ መጨነቅ እመርጣለሁ። ለእናንተ "ለምን?" የሚለው ጥያቄ ምንም ይሁን ምን ጠንካራ አድርጉት። በጣም አስቸጋሪ የሆኑትን የህይወት ክፍሎችን ለማሸነፍ ቁልፉ ይህ ነው። ኒሂሊዝም ጭንቀት ሊሆን ይችላል ፥ ጭንቀት ሁሉ ግን ኒሂሊዝም አይደለም!”
-Friedrich Nietzsche
“ ምኞቶች ጭንቀትን አይፈጥሩም.. ጭንቀት ግን ምኞትን ይፈጥራል።”
-Osho
“በሰዎች ጉዳይ ውስጥ ትልቅ ጭንቀት የሚገባው ምንም ነገር የለም፤ የምንጨነቀው ስላደረግነው ነገር ሳይሆን የተደረገው ነገር ስለሚያመጣው ውጤት ነው!”
-Plato
“በጠያቂው ጥያቄ ላይ የምጨነቅ ፍልስፍናዊው ፍጡር ነኝ፤ ጭንቀቴም መጠን ያለው ጥያቄ ነው።”
-Aristotle
“ብቸኛው እውነታ በመላው ፍጥረታት ሰንሰለት ውስጥ "ጭንቀት" ነው መደቀኑ ነው። በዓለም ላይ ለጠጠፉ ሰዎች እና አቅጣጫዎች መነሻ ይህ ጭንቀት ነው። ጭንቀት አጭርና ጊዜያዊ ፍርሃት ነው። ነገር ግን ያ ፍርሃት በራሱ የምናውቅ ከሆነ ጭንቀት ይሆናል። ጭንቀት existence ያተኮረበት የሰው ልጅ ዘላለማዊ የአየር ንብረት ነው።”
-Albert Camus
“የምንኖርበትና የምንደሰትበት የወደፊት ህይወታችንን የምንፈጥርበት በአሁኑ ወቅት ላይ ነው። እናም ውድ ጊዜያችንን በጭንቀት እሳት ለማቃጠል ከወሰንን ያ በራሳችን ምርጫ እና ውሳኔ ነው። የመንፈስ ጭንቀት ካለባችሁ ባለፈ ጊዜ ውስጥ እየኖራችሁ ነው፤ ጭንቀት ብቻ ከሆነ ስለወደፊታችን እያሰብን ነው!።”
-Gutama Buddha
“የሚያስጨንቀኝ ነገር ካላገኘሁ እራሱ ያስጨንቀኛል!”
-Schopenhauer
(የማን አሳብ ሚዛን ይደፋል? )Repost from ብሔረ የድሮ መፃሕፍቶች
[ፈላስፎች ወይም ጉሩዎች በኖሩበት ዘመን ስለጭንቀት ምን ብለዋል? ]
🗯️
“ከኒሂሊስት ይልቅ መጨነቅ እመርጣለሁ። ለእናንተ "ለምን?" የሚለው ጥያቄ ምንም ይሁን ምን ጠንካራ አድርጉት። በጣም አስቸጋሪ የሆኑትን የህይወት ክፍሎችን ለማሸነፍ ቁልፉ ይህ ነው። ኒሂሊዝም ጭንቀት ሊሆን ይችላል ፥ ጭንቀት ሁሉ ግን ኒሂሊዝም አይደለም!”
-Friedrich Nietzsche
“ ምኞቶች ጭንቀትን አይፈጥሩም.. ጭንቀት ግን ምኞትን ይፈጥራል።”
-Osho
“በሰዎች ጉዳይ ውስጥ ትልቅ ጭንቀት የሚገባው ምንም ነገር የለም፤ የምንጨነቀው ስላደረግነው ነገር ሳይሆን የተደረገው ነገር ስለሚያመጣው ውጤት ነው!”
-Plato
“በጠያቂው ጥያቄ ላይ የምጨነቅ ፍልስፍናዊው ፍጡር ነኝ፤ ጭንቀቴም መጠን ያለው ጥያቄ ነው።”
-Aristotle
“ብቸኛው እውነታ በመላው ፍጥረታት ሰንሰለት ውስጥ "ጭንቀት" ነው መደቀኑ ነው። በዓለም ላይ ለጠጠፉ ሰዎች እና አቅጣጫዎች መነሻ ይህ ጭንቀት ነው። ጭንቀት አጭርና ጊዜያዊ ፍርሃት ነው። ነገር ግን ያ ፍርሃት በራሱ የምናውቅ ከሆነ ጭንቀት ይሆናል። ጭንቀት existence ያተኮረበት የሰው ልጅ ዘላለማዊ የአየር ንብረት ነው።”
-Albert Camus
“የምንኖርበትና የምንደሰትበት የወደፊት ህይወታችንን የምንፈጥርበት በአሁኑ ወቅት ላይ ነው። እናም ውድ ጊዜያችንን በጭንቀት እሳት ለማቃጠል ከወሰንን ያ በራሳችን ምርጫ እና ውሳኔ ነው። የመንፈስ ጭንቀት ካለባችሁ ባለፈ ጊዜ ውስጥ እየኖራችሁ ነው፤ ጭንቀት ብቻ ከሆነ ስለወደፊታችን እያሰብን ነው!።”
-Gutama Buddha
“የሚያስጨንቀኝ ነገር ካላገኘሁ እራሱ ያስጨንቀኛል!”
-Schopenhauer
(የማን አሳብ ሚዛን ይደፋል? )▌የብርሃን ብቸኝነት©
መንቃት ጉዞ ነው እንጂ መድረሻ አይደለም። ማታለያዎችን መግፈፍ፣ የማይመቹ እውነቶችን መጋፈጥ እና ጥያቄ ከማይቀርብባቸውን እምነቶች የጋራ ግዴለሽነት ባለፈ መራመድ ነው።
ሆኖም ታሪክ አንድ ከባድ እውነት በጆሯችን ያንሻኮሻኩል—ብርሃንን የሚሹ ሁልጊዜ በጥላ ውስጥ በሚቀሩት ይገፋሉ!
ብርሃናቸው የእውቀትን፣ የግንዛቤን እና ምናልባትም መንፈሳዊ መሻገርን፣ ዕድገትን የማምጣት ሃይል አለው። ነገር ግን ያ ብርሃናቸው የመገለላቸው ምክንያት ሲሆን ማየት ያማል።
ማህበረሰቡ የራሱን ፈጠራ የለመደና የራሱን ውሸት የሚያምን በመሆኑ የእምነቶቹን ክፍተት እና ስህተት የሚያሳዩትን አይወድም። ይልቁንም ይፈራቸዋል፣ ይጠላቸዋል፣ ያፌዝባቸዋል፣ እና ድምፃቸውን ለማፈን ይፈልጋል።
ይህንን እውነት በታሪክ ውስጥ በግልጽ ማየት እንችላለን። ሶቅራጥስ ወጣቶችን በማበላሸት ተወገዘ። ጋሊልዮ ዶግማን በመቃወም ተሰደደ። ኒቼ ሀሳቦቹ የተለመደ አስተሳሰብን ያናወጡ እና ያወኩ ናቸው ተብለው ተነቅፏል።
እነዚህ አእምሮዎች ብርሃንን ቢያንጸባርቁም ግን በዙሪያቸው ያለው ማህበረሰብ የጨለማነትን ምቾት በመምረጡ ወደ ኋላ ተገፍተዋል።...
ዮናታን በጋሻው
@ETHIO_PDF_BOOKS1 @ETHIO_PDF_BOOKS1
ሴትና ፈጣሪ
ከፈጣሪህ በላይ ዉደደኝ አለችኝ
እሱን በመፈለግ ስደክም እያየችኝ
እኔን አምልክ አለኝ እሱም ተደብቆ
ሕይወቴ እንደጫማ በእሷ መንገድ አልቆ ።
እናም ግራ ገባት ነፍሴ መሃል ሆና
አምላኬ ከሴት ጋር እየተቀናና ።
ጲላጦስ ( ኃይለጊዮርጊስ ማሞ )2001 ዓ.ም
«ፀሀይ ስትወጣና ስትጠልቅ ከሩቅ ተመልክታችሁ ልትደነቁ፤ልትደመሙ ትችላላችሁ። ነገርግን አጠገባችሁ ያለውን ተአምር አላስተዋላችሁም። አጠገባችሁ ያለው ተአምር ትልቋን ፀሀይ የተመለከተው ትንሹ አይናችሁና ፀሀይ መሆኗን ያረጋገጠላችሁ አእምሯችሁ ነበር ቅርብ ያለው ተአምር።»
➾ ኦሾ
🛡 Freud & Defense Mechanisms: How the Mind Protects Itself (Long Version)
Freud believed the mind doesn’t just sit there passively taking life in — it protects itself.
When reality feels overwhelming, painful, embarrassing, or emotionally threatening, the mind quietly activates psychological “shields.”
He called these defense mechanisms.
They’re unconscious — meaning we don’t choose them.
They act automatically to reduce stress, guilt, fear, shame, or inner conflict.
And here’s the twist:
They can help us survive emotionally…
but they can also distort reality.
⚙️ Why Do We Use Defense Mechanisms?
Because life isn’t gentle.
We deal with:
rejection
criticism
failure
guilt
anger
loss
desire we don’t want to admit
emotions we don’t know how to handle
When these feelings hit, the ego steps in and says:
“Okay, how do I protect this person from emotional overload?”
So it bends reality… just a little.
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
