Tech +(ET)
Open in Telegram
ሰላም ይህ TECH + አማርኛ ቻናል ነው በዚህ ቻናል » አዳዲስ የቴክኖሎጂ መረጃዎች » ስለኮምፒውተር , የስልክ update መረጃዎች ይለቀቃሉ ያለዎትንም እውቀት ያሳድጋሉ ። Let's Empower Africa in The Tech Industry Together
Show more780
Subscribers
No data24 hours
+17 days
No data30 days
Posts Archive
781
#Tiktok
Tiktok በአሜሪካ ዳግም ተመልሷል ❕
በBytedance ስር ያለዉ Tiktok ዳግም በአሜሪካ ተመልሷል ። እንደሚታወቀዉ ከ 1 ወር በፊት በJanuary 16 በአሜሪካ መንግስት ቲክቶክ መዘጋቱ የሚታወስ ነዉ ። አሁን ላይ ግን ከ2 ቀን በፊት ከFebruary 13 ጀምሮ ቲክቶክ በአሜሪካ ተመልሷል ፣ ይህም የሆነበት ምክንያት የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ለቻይናዉ መተግበሪያ (App) የተወሰኑ ወራቶች አስከ April 5th ጊዜ ተሰጥቶታል ። በአሜሪካ የምትገኙ አሁን ላይ ቲክቶክን በሁለቱም Apple Appstore ፣ እንዲሁም Google Playstore ላይ ስለሚገኝ አዉርዳቹ መጠቀም ትችላላቹ ።
ላልሰሙ Share አርጉላቸዉ ❕
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
781
#Vision_2030
ሳኡዲ አረቢያ Vision 2030 የሚል program በJanuary 2016 በሳኡዲ አረቢያዉ አልጋ ወራሽ ሙሀመድ ቢን ሰልማን ምክንያት ተጀምሯል ። ይህ Program በዋናነት የሳኡዲ አረቢያን የኢኮኖሚ ምንጭ ለማስፋፋት ያለመ ነዉ ። በዚህም ስር በ2030 ይጠናቀቃሉ ተብለው የሚጠበቁ ትላልቅ ፕሮጀክቶች አሉ ፣ ከነዚህም ዉስጥ እኔን ያስገረሙኝን ከFuturstic cities ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶችን በሚቀጥሉት ቀናቶች የማስመለክታቹ ይሆናል
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
#windows10
Windows 10 ከOctober 14 2025 ጀምሮ ምንም አይነት support እንደማያገኝ windows አስታወቀ።
ይህም ከMicrosoft support ማጣቱ ለwindows 10 ተጠቃሚዎችን ለደህንነት ችግር ያጋልጣል ። እንዲሁም ምንም አይነት የsoftware update አይኖረዉም ፣ አዳዲስ features አይካተቱበትም ።
ምንም ያክል 62 በመቶ የwindows ተጠቃሚ windows 10 የሚጠቀም ቢሆንም Microsoft ለwindows10 የሚሰጠዉን support እንደሚያቆም አስታዉቋል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
#OmniHuman-1
ሰሞኑን Deepseek ከተዋወቀ ቡሃላ የAI ፍልሚያዉ ተጧጡፏል ። ይህንንም ተከትሎ Bytedance (Tiktokን የሚያስተዳድረዉ ) ካምፓኒ OmniHuman-1 የሚባል Ultra - Realistic video generator AI አስተዋዉቋል ። video generate ለማረግም አንድ ፎቶ እና Motion signals እንደ audio ብቻ ያስፈልገዋል ። በዚህ AI generator የሚሰሩ ቪዲዎችን በጣም ለdetail ትኩረት ከመስጠቱ የተነሳ ፣ Real or Fake መሆናቸዉን እንኳን ለመለየት ይከብዳል ። ከላይ በቪድዪዉ ላይ የምትመለከቱት የAlbert Einstein ቪድዮም በዚሁ በOmniHuman-1 Video Generator AI የተሰራ ቪድዮ ነዉ ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
🥳 300+ ቤተሰብ ደርሰናል ⚡️
ሁላቹንም ለምታሳዩን ድጋፍ ከልብ እያመሰገንን ❤️
ይጨመር ፣ ይቀነስ የምትሉት ነገር ካለ ከታች ባለዉ Comment (ሀሳብ) መስጫ ስር ሀሳባቹን እንደቤታቹ ግለፁልን 🙌
781
❗️❕❗️ Opportunity Alert ❗️❕❗️
በኢትዪጽያ የArtificial Intelligence Institute Internship apply ማድረግ የምትፈልጉ ሰዎች ከታች ያለዉን Google Form በመሙላት Apply ማድረግ ትችላላቹ ። ለሌሎችም ሼር አርጉ ❕
https://forms.gle/Ejxzc8ZMTWZUp8xP9
781
#Instagram
Instagram ከዛሬ ጀምሮ ከ350 Million ተጠቃሚ በላይ ባላዉ ህንድ ሀገር ዉስጥ ለteenager ( ከ 13 - 19 እድሜ ) የሚሆን Feature አስተዋዉቋል ። ይህን Feature ከአመት በፊት በ USA , Canada, Australia እንዲሁም በUK ማስተዋወቁ የማይረሳ ነዉ ። ይህ feature የteen account ላላቸዉ በየቀኑ የMessage ገደብ ያለዉ ሲሆን ፣ እንዲሁም ለወላጆች የልጃቸዉን Instagram account ከማን ጋር እንደሚያወሩ ፣ እንዲሁም ልጃቸዉ Instagram app በቀን ዉስጥ የሚጠቀምበትን ሰዓት መወሰን ፣ በተወሰኑ ሰዐት ዉስጥም Instagram app እንዳይጠቀም ሙሉ በሙሉ block ማድረግ የሚቻልበት feature ያለዉ ነዉ ። ይሄ Feature አሁን ላይ በተወሰኑ ሀገራት ብቻ ሲሆን የሚሰራዉ ፣ በኛ ሀገርም ሲጀመር የምናሳዉቃቹ ይሆናል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
781
#1 Plantaform
በ1ኛ ደረጃ የምናየዉ Plantaform የሚባል Indoor (የቤት ዉስጥ) Gardening System ነዉ ። ይህ Gardening system የሚለየዉ ከዚህ ቀደም በምናዉቀዉ የአትክልት አበቃቀቀል መንገድ አፈር እና ዉሀን በመጠቀም ከማሳደግ ይልቅ Fogphonics በሚባል የአትክልት አበቃቀል መንገድ የዉሀ ትናኝን ብቻ በመጠቀም Nutrient rich የሆነ አትክልት ማብቀል የሚቻልበት መንገድ ነዉ ። ይህም Indoor Gardening System በቤታቸዉ ወስጥ በመትከያ ቦታ እጦት ምክንያት ማሳደግ ለማይችሉ አሪፍ ተመራጭ ነዉ ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
#2 Nvidia's new cheap
በ2ተኛ ደረጃ የምናየዉ ከAI ጋር የተገናኘ ነዉ ። እንደሚታወቀዉ አሁን ላይ ስለ AI እንደ Next Generation ማወቅ አለብን ። እናም በ2ተኛ ደረጃ የምናየዉ ከAI ጀርባ ያለዉ ፣ AI ይሄን ያክል computing power እንዲኖራቸዉ ያደረገዉን Nvidia chip ነዉ ። በዘንድሮዉ CES 2025 Nvidia Game changer የሆነ chip አስተዋዉቋል ። ይህ chip ከዚህ በፊት ሚልየን $ ወጥቶበት በመንግስት ድርጅቶች ፣ በትላልቅ organization ከሚገዙ supercomputer የተሻለ Chip ሆኖ በ3000$ ብቻ ለገበያ የሚቀርብ እንደሆነ ተገልፃል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
#3 Land Aircraft Carrier
በ3ተኛ ደረጃ የምናየዉ ከXpeng Aerhot, Land Aircraft Carrier የሚባል መኪና ነዉ ። ይህ መኪና ከከሌሎች መኪና ምንድን ነዉ የሚለየዉ ካላቹኝ መኪናዉ በመሬት ላይ እንደመጓጓዣነት በተጨማሪ ከጀርባዉ ተዘርግቶ Flying Car መሆን የሚችል የድሮን ሲስተም ይዟል ። ድሮኑም በዉስጡ ሁለት ሰዉን ብቻ የመያዝ አቅም ያለዉ ሲሆን ይህን ድሮንም በአንድ click ብቻ በቀላሉ deploy ማድረግ ይቻላል ፣ ደሮኑንም ለማስነሳት መንደርደሪያ ሳያስፈልገዉ Vertical Takeoff ማረግ ይችላል ። ይህን ድሮን የያዘዘዉ መኪናም በአንድ ችርጅ እስከ 1000miles (~1600km) ድረስ መሄድ ይችላል ። መኪናዉ አሁን ላይ በገበያ ላይ ባይዉልም በ2026 በቻይና ዉስጥ ብቻ ለገበያ እንደደሚዉል እና ዋጋዉም ከ200,000$ - 300,000$ እንደሚሆን ተነግሯል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
#4 Honda 0 Saloon
በ4ተኛ ደረጃ የምናየዉ Honda 0 Saloon የሚባል የኤሌክትሪክ መኪና የምናይ ይሆናል ። ይህ መኪና በዲዛይን ደረጃ sci-fiction ላይ እንደምናያቸዉ መኪኖች ተደርጎ ነዉ የተሰራዉ ። መኪናዉንም ቻርጅ ለማድረግ ከ10 - 15 ደቂቃ ብቻ ይበቃል ፣ በአንድ ቻርጅም እስከ 300miles (~500km) ድረስ ይሄዳል ። ዉስጡም ሙሉ በሙሉ የመኪናዉ Dashboard 5 screen ሲሆን ሁሉንም ኮንትሮለር በዚህ Screen መቆጣጠር ያስችለዋል ። በዉስጡም AI Integrated ሲሆን Level 3 Autonomous driving ተገጥሞለታል ። ይህም መኪና በ2026 ተመርቶ ለገበያ ይዉላል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
+1
#5 OMNIA
በ5ኛ ደረጃ የምንመለከተዉ OMNIA የሚባል መስታወት ነዉ ። ይህ መስታወት ከሌሎች መሰታወት የሚለየዉ እንደሌሎቹ መስታወት እራስን ለመመልከት ብቻ አያገለግልም ። ይህ መስታወት ደም ግፊት ፣ የልባችንን ጤንነት ፣ የእንቅልፍ ሁኔታችንን ፣ የጤና ችግርም እንዲሁ ካለብን scan አርጎ ዉጤቱን ያሳዉቀናል ። በዙርያዉ Health sensor ሲኖረዉ ፣ AI POWERED ነዉ ። ቁመቱም 6feet ያክል ሲሆን ፣ ይህም ማንኛዉም Average ቁመት ያለዉ ሰዉን scan ማድረግ ይችላል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
#6 Roborock Saros z70
በ6ተኛ ደረጃ የምናየዉ Roborock Saros z70 የሚባል Vaccum Cleaner ነዉ ። Vaccum cleaner ምንድን ነዉ ላላቹ? Atmospheric pressuren በመጠቀም በአካባቢዉ ያሉትን ቆሻሾች የሚሰበስብ ነዉ ። ከዚህ ቀደም የነበሩት Vaccum Cleaner መሬት ከመጥረግ እና መወልወል ዉጪ ምንም ግልጋሎት አልነበራቸዉም ፣ እንዲሁም በመንገዳቸዉ እንደ ካልሲ የለ ነገር ከወደቁ መንገድ በመቀየር ሌሎች ቦታዎችን ያፀዳል ። ይህም ካልሲዉ የወደቀበት ቦታ ሳይፀዳ ያልፋል ማለት ነዉ ። ነገር ግን Roborock Saros z70 የሚባለዉ Vaccum Cleaner ግን በመንገዱ ያጋጠሙትን እስከ 300g የሚደርሱ እቃዎችን በተገጠመለት Foldable arm በማንሳት ያን አካባቢ ያፀዳል ። ቁመቱም 8cm ሲሆን ይህም በቀላሉ ከሶፋ ፣ አልጋ ስር በመግባት ያፀዳል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
+1
#7 Glidance
በ7ኛ ደረጃ የምናየዉ ደግሞ Glidance የሚባል አይነስዉራንን የሚመራ መንቀሳቀሻ ነዉ ። Glide ለዓይነ ስውራን ወይም ዝቅተኛ የማየት ችሎታ ላላቸው ሰዎች የተሰራ የመጀመሪያው ራሱን የቻለ፣ በራሱ የሚመራ መንቀሳቀሻ ነዉ ። Glide ማየት የተሳናቸው በልበ ሙሉነት፣ በምቾት እና በቀላሉ እንዲጓዙ ለመርዳት ተብሎ የተሰራ በAI-Powered የሆነ መንቀሳቀሻ ነው ።
የዚህ መንቀሳቀሻ መንገድ ፍለጋ ቴክኖሎጂ በራሱ ወደ ተፈለገዉ መንገድ ይመራናል፣ እንቅፋቶችን ያስወግዳል፣ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ላይ ይቆያል፣ እና ወደ መዳረሻዎ እዲደርሱ ያግዛል።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
#8 Aurzen zip
በ8ኛ ደረጃ ደግሞ Aurzen zip የምትባል projector የምናይ ይሆናል ። ከዚህ በፊት ፕሮጀክተር ሲባል የምናዉቀው ተልቅ ፣ ግድግዳ ላይ ወይ የሚሰቀል ነዉ ። ነገር ግን Aurzen zip የምትባለዉ projector ከIphone የምታንስ ስትሆን እንዲሁም 3.1 x 3.1inch እና 277g ብቻ ነዉ የምትመዝነዉ ። ይህቺ projector ምንም ያክል በsize ብታንስም 720px High Definition ፣ 4k video support ፣ እንዲሁም እስከ 80 inch ድረስ project ማድረግ የምትችል projector ነች ። ይህች projector አሁን ላይ ገበያ ላይ የዋለች ሲሆን ከ250$ የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ በመሸጥ ላይም ትገኛለች ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
+1
#9 Roborock zeo one
በ9ኛ ደረጃ የምናየዉ Roborock zeo one የሚባል የልብስ ማጠቢያ ማሽን ነዉ ። ይህ ልብስ ማጠቢያ ከሌሎቹ የሚለየዉ AI POWERED ሲሆን እንደ ማጠቢያም ማድረቅያም ማገልገሉም ለየት ያረገዋል ። ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ልብስ ማጠቢያ ለመስራት የተሞከረ ቢሆንም በHeating system ላይ ችግር ነበረባቸዉ ። Roborock zeo one ልብስ ማጠቢያም zeolite Technology የሚባል እንዲሁም የchemical Engineering ጥበብን በመጠቀም ችግሩን ሊቀርፍ ችሏል ። ይህ የልብስ ማጠቢያ በተገጠመለት Sensor አማካኝነት የልብሱን ጨርቅ አይነት ለይቶ አስፈላጊዉን ሙቀት ይሰጣል ። በCapacity ደረጃ ስናይ ደግሞ እስከ 10kg የሚሆኑ ልብሶችን በአንድ ዙር የማጠብ አቅም አለው ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
#10 Lenovo Thinkbook plus Gen6
በ10ኛ ደረጃ ምንመለከተው Lenovo Thinkbook plus Gen6 ይህ ላፕቶፕ የመጀመርያዉ Rollable ላፕቶፕ ነዉ። በአንድ click ብቻ 14inch የነበረዉን ላፕቶፕ ወደ 16.7inch Roll ማድረግ የሚችል ፊቸር ያለዉ ላፕቶፕ ነዉ። ይህም በተለያዩ ሙያ ላሉ እንደ ፕሮዲዉሰር ፣ ኢዲተር ፣ ፀሃፊዎች እንዲሁም ሰፋ ያለ ስክሪን ለሚያስፈልጋቸዉ አሪፍ ተመራጭ ነዉ። ይህ ላፕቶፕ አሁን ላይ ለገበያ ባይዉልም በያዝነዉ አመት ከ3-4 ወር በኋላ ለገበያ የሚቀርብ ይሆናል።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
781
ምን ያህላቹ ስለ CES ታዉቃላችሁ?🧐
🫴 CES(Consumer Electronics Show) በ Consumer Technology Association የሚዘጋጅ አመታዊ የቴክኖሎጂ ምርቶች የሚተዋወቁበት ዝግጅት ነው። በጥር (January) ወር በዊንቸስተር፣ ኔቫዳ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የላስ ቬጋስ ኮንቬንሽን ሴንተር የሚካሄድ ነዉ። በዚህ ዝግጅት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ይተዋወቃሉ ። በዚህ Tech+ Channel ሁሉንም በአመታዊዉ CES የተዋወወቁትን Product ባይሆንም Top 10 ምንላቸዉን በዚህ ቻናል የምናጋራቹ ይሆናል 🙌
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
