en
Feedback
Tech +(ET)

Tech +(ET)

Open in Telegram

ሰላም ይህ TECH + አማርኛ ቻናል ነው በዚህ ቻናል » አዳዲስ የቴክኖሎጂ መረጃዎች » ስለኮምፒውተር , የስልክ update መረጃዎች ይለቀቃሉ ያለዎትንም እውቀት ያሳድጋሉ ። Let's Empower Africa in The Tech Industry Together

Show more
Buy Ad
780
Subscribers
No data24 hours
+17 days
No data30 days
Posts Archive
✨ ረመዳን ሙባረክ | رمصان مبارك ✨ #Ramadan_1446
✨ ረመዳን ሙባረክ | رمصان مبارك ✨ #Ramadan_1446

#NEO Gamma በ2014 የተመሰረተዉ 1x technologies የሚባለዉ የAI እና Robotics ካምፖኒ አዲስ Neo Gamma የሚባል Humanoid Robot ባሳለፍነዉ ሳምንት February 21,2025 አስተዋዉቋል ። ይሄ Humanoid Robot 1.65m ቁመት ፣ 29.94kg ክብደት ያለዉ ሲሆን ፣ የተለያዩ አገልግሎቶችንም ይሰጣል ። ከነዚህም ዉስጥ ቤት ማፅዳት ፣ ልጆች ማስጠናት ፣ ከሰዎች ጋር መነጋገር እና ሌሎች አገልግሎቶችንም ይሰጣል ፣ ሮቦቱ አንዴ ችርጅ ከተደረገ ከ2-4 ሰዐት ያገለግላል ። ነገር ግን ካምፖኒዉ አሁን ላይ የHumanoid Robot ገበያ ቀዝቃዛ ከመሆኑ አንፃር በገበያ ላይ ሮቦቱ እንደማይዉል ገልፃል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Chatgpt 4.5 በትናንትናዉ እለት OpenAi Gpt4.5 የሚባለዉን የAI ሞዴል አስተዋወቋል ። የOpenAI ዋና ስራ አስኪያጅ (CEO) የሆነዉ Sam Altman እንደተናገረዉ ይህ አዲስ የAI
#Chatgpt 4.5 በትናንትናዉ እለት OpenAi Gpt4.5 የሚባለዉን የAI ሞዴል አስተዋወቋል ። የOpenAI ዋና ስራ አስኪያጅ (CEO) የሆነዉ Sam Altman እንደተናገረዉ ይህ አዲስ የAI ሞዴል የReasoning Model እንዳልሆነ የተናገረ ሲሆን ፣ ጥያቄን በመረዳት ደረጃ የተሻለ እንደሆነ ፣ በLive chat ላይ ያለዉም ድምፅ ይበልጥ የሰዉ እንደሚመስል ተናግሯል ። ይህ የAI ሞዴል ከዚህ ቀደም ከነበረው GPT4o ጋራ ሲነፃፀር ካላቸዉ Data(መረጃ) አንፃር ይሄ የAI ሞዴል የተሻለ ሲሆን ፣ ነገር ግን በCoding , math ከGpt o3 mini ጋር ሲነፃፀፀር Gpt o3 mini የተሻለ ነዉ ። አሁን ላይ ይህን የAI ሞዴል መጠቀም የሚችሉት የChatgpt pro (200$/ወር) ተጠቃሚዎች ብቻ ሲሆኑ የChatGPT plus(20$/ወር) ተጠቃሚዎች ግን እስከ ቀጣይ ሳምንት ድረስ መጠበቅ እንዳለባቸዉ ተነግሯል           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Humanoid Robots ብዙዎቻችን በተለያየ ቦታ ስለ Humanoid Robots ሲነሳ እንሰማለን ፣ ግን ምን ያህሎቻቹ ናቹ ስለ Humanoid Robots ምንነነት የምታዉቁት ? Humanoid Ro
#Humanoid Robots ብዙዎቻችን በተለያየ ቦታ ስለ Humanoid Robots ሲነሳ እንሰማለን ፣ ግን ምን ያህሎቻቹ ናቹ ስለ Humanoid Robots ምንነነት የምታዉቁት ? Humanoid Robots የምንላቸዉ የሮቦት አይነት ሲሆኑ ሰዉን እንዲመስሉ ተደርገዉ የተሰሩ ናቸዉ ። ከላይ በምስሉ ላይም እንደምትመለከቱት ሮቦቶቹ ልክ እንደ ሰዉ ጭንቅላት ፣ እጅ ፣ እግር የተገጠመላቸዉ ሲሆን ልክ እንደ ሰዉ የተለያዩ ግልጋሎቶችን መስጠት የሚችሉም ናቸዉ  ። እነዚህ Humanoid Robots ከ1495 ጀምሮ መሰራት የጀመሩ ሲሆን የመጀመርያዉ ዘመናዊዉ Humanoid robot WABOT-1 የሚባል መራመድ ፣ መናገር የሚችል  በ1972 በJapan , Waseda University ዉስጥ ነበር የተሰራዉ ። እነዚህ ሮቦቶች ከሚሰጡዋቸዉ አገልግሎት ዉስጥ በቤት ዉስጥ ማገልገል ፣ በሆስፒታል ዉስጥ ልክ እንደ ነርስ  ፣ በመስርያ ቦታ ልክ እንደ Receptionist, Customer service ያገለግላሉ ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#PM01 በቻይና , Shenzen በሚባል ከተማ ያለዉ EngineAi የሚባል የRobotics ካምፖኒ የመጀመርያዉን Front flip (ወደፊት መገልበጥ የሚችል) PM01 የሚባል Humanoid Robot ሰራ ። ሮቦቱ ለመገልበጥ ከባድ የሆነዉን Front flip መገልበጥ የቻለ ሲሆን ይህም በRobotics ዘርፍ ትልቅ ስኬት ነዉ ። ሮቦቱ 23° ለመንቀሳቀስ Flexible አንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የተለያዩ አገልግሎቶችንም ሮቦቱ ይሰጣል ። አሁን ላይም EngineAI ሮቦቱን በገበያ ላይ ያቀረበዉ ሲሆን በ$13,000 ዶላር በመሸጥ ላይ ይገኛል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

በweb development ላይ ላላችሁ በተለይ Front end ላይ የምትሰሩ ወይም የምትማሩ አንድ ቻናል ልጠቁማቹ CODE WITH DAGIM ይባላል ! በFront end ላይ ያለዉን Experience
በweb development ላይ ላላችሁ በተለይ Front end ላይ የምትሰሩ ወይም የምትማሩ አንድ ቻናል ልጠቁማቹ CODE WITH DAGIM ይባላል ! በFront end ላይ ያለዉን Experience share የሚያደርግበት ቻናል ሲሆን ምንም አይነት ጥያቄ በFront end development ላይ ካላቹ በሱ ቻናል Comment ስር መጠየቅ ትችላላቹ ። join ለማለት ከስር ያለዉን ሊንክ ተጠቀሙ👇 🫲 Code with Dagmawi 🫱

#Scholarship_opportunity GKS Scholarship 2025 applications are now open, offering international students a golden opportunity
#Scholarship_opportunity GKS Scholarship 2025 applications are now open, offering international students a golden opportunity to pursue higher education in South Korea with full financial support. 👉Link to apply👈

የUK አርቲስቶች ድምፅ አልባ (silent) የሙዚቃ አልበም ለቀቁ! የእንግሊዝ መንግስት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ካምፓኒዎችን ለማበረታታት የCopyright መብቶችን በተመለከተ አዲስ ህግ ለማውጣት
የUK አርቲስቶች ድምፅ አልባ (silent) የሙዚቃ አልበም ለቀቁ! የእንግሊዝ መንግስት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ካምፓኒዎችን ለማበረታታት የCopyright መብቶችን በተመለከተ አዲስ ህግ ለማውጣት እየተንቀሳቀሰ ነው ። በአዲሱ ህግ መሰረት ማንኛውም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዲቨሎፐር online ላይ ያገኛቸውን የአርቲስቶች ስራ ያለማንም ፈቃድ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንሱ ግብአት ማድረግ እንዲችሉ ይፈቅዳል ። ይህን ህግ በመቃወም ሰኞ ዕለት ከ1000 አርቲስቶች በላይ በመሰባሰብ "Is This What We Want?” የተሰኘ ድምፅ አልባ አልበም ለቀዋል ። 12 ትራኮችን የያዘውና ባዶ እስቱዲዮ ውስጥ የተቀረፀው ይህ "ሙዚቃ" Spotify ላይ ተለቆ ብዙዎች ተመልክተውታል ። አርቲስቶቹ ' መንግስት የሙዚቃን ዘረፋ ህጋዊ ሊያደርግ አይገባም ' በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Waterworth Meta 50,000 km ርዝመት ያለው የኢንተርኔት ኬብል በውቅያኖሶች ስር ሊዘረጋ ነው ! የFacebook, Instagram እና WhatsApp እናት ኩባንያ የሆነው Meta የሚዘረ
+2
#Waterworth
Meta 50,000 km ርዝመት ያለው የኢንተርኔት ኬብል በውቅያኖሶች ስር ሊዘረጋ ነው !
የFacebook, Instagram እና WhatsApp እናት ኩባንያ የሆነው Meta የሚዘረጋው የኢንተርኔት መስመር 5 አህጉራትን የሚያገናኝ ሲሆን ፣ እንደ አሜሪካ፣ ብራዚል፣ ህንድና ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎች ሀገራትን በቀጥታ ያገናኛል ። ፕሮጀክቱ በተጨማሪም በዓለም በኢኮኖሚ እና ቴክኖሎጂ ላይ ትልቅ ተፅእኖ ያሳድራል  ተብሎ ይጠበቃል ። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም የአለማችን ረጅሙ የኢንተርኔት ገመድ ይሆናል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

ሰላም የTech+ ቤተሰብ! 🙏 ያለፉትን ሁለት ቀኖች ምንም አይነት መረጃ ስላለቀኩላቹ ከልብ ይቅርታ ማለት እፈልጋለሁ ፣ ትንሽ አልመቻችልክ ብሎኝ ነዉ 🙌።

#Passport አዲሱ ፖስፖርት ዛሬ ይፋ ተደረገ! የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዝየም አዲሱን ኤሌክትሮኒክስ ፖስፖርት (E - passport) አስተዋወቀ ።
+2
#Passport
አዲሱ ፖስፖርት ዛሬ ይፋ ተደረገ!
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዝየም አዲሱን ኤሌክትሮኒክስ ፖስፖርት (E - passport) አስተዋወቀ ። ፖስፖርቱ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሚስጥራዊ ህትመትና ቴክኖሎጂ ልምድ አለው ከተባለው የጃፓኑ ቶፓን ሴኩሪቲ ጋር በመተባበር የተሰራ ነዉ ። ይህም ፓስፖርት ደህንነትን ያጠናክራል ፣ የጉዞ ሰነዶችን እና የሀገሪቱን የኢሚግሬሽን ስርዓት ዘመናዊ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Ali-Express Ali-Express ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ_ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ! በ2010 የተመሠረተዉ አለም አቀፉ የonline ግብይት (E-Commerce) ተቋ
#Ali-Express
Ali-Express ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ_ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ!
በ2010 የተመሠረተዉ አለም አቀፉ  የonline ግብይት (E-Commerce) ተቋም Ali-express እንደገለፀው ከየካቲት 17 (February 24) ጀምሮ የበርካታ አፍሪካ አገራትን ገንዘብ ጥቅም ላይ ያውላል ፡፡  ከእነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፤ ግብፅ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል ፡፡ የክፍያ መፈፀሚያ ገንዘቦችን ማስፋፋት ያስፈለገው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ ለመሆን በማሰብ እንደሆነ የጠቀሰው Ali-Express በተጨማሪም በአለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቀረት እንደሆነ አስረድቷል፡፡           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

🥳 ቤተሰብ 500+ Member ደርሰናል ሁላቹም ለምታሳዪን ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን ❤️           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Grok-3 Grok-3 አሁን ላይ ለሁሉም ክፍት ነዉ ። እንደሚታወቀዉ Grok-3 በያዝነዉ ሳምንት ሰኞ እለት በElon Musk xAI በሚባለዉ አዲሱ የAI ካምፖኒ መለቀቁ ይታወሳል ። ከዛሬም ጀምሮ
#Grok-3 Grok-3 አሁን ላይ ለሁሉም ክፍት ነዉ ። እንደሚታወቀዉ Grok-3 በያዝነዉ ሳምንት ሰኞ እለት በElon Musk xAI በሚባለዉ አዲሱ የAI ካምፖኒ መለቀቁ ይታወሳል ። ከዛሬም ጀምሮ ሁላቹም Grok website ላይ ገብታቹ መጠቀም የምትችሉ ሲሆን ፣ አንዲሁም Grok AI በApp መልኩም ስላላቸዉ ከዌብሳይታቸዉ ላይ አዉርዳቹ መጠቀም እንደምትችሉ ተገልፃል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Apple በዛሬዉ እለት Apple IPhone 16e የሚባል የስልክ ሞዴል አስተዋወዉቋል ። ስልኩ 6.1-inch OLED display ያለዉ ሲሆን እስካሁን ከነበሩት 6 inch Iphone የተሻለ የባ
+1
#Apple በዛሬዉ እለት Apple IPhone 16e የሚባል የስልክ ሞዴል አስተዋወዉቋል ። ስልኩ 6.1-inch OLED display ያለዉ ሲሆን እስካሁን ከነበሩት 6 inch Iphone የተሻለ የባትሪ ቆይታ አለዉ ። ሌላዉ በዉስጡ c1 5G የሚባል ሞደም ለሀይል ቁጠባ የተገጠመለት ሲሆን ፣ እንዲሁም 48MP telephoto shot የጀርባ ካሜራ ሲኖረዉ telephoto shot መሆኑ የስልኩ ዉፍረት ሳይጨምር High level optical zoom እንዲኖረዉ ይረዳል ። በዋጋ ደረጃ ደግሞ ከዚህ ቀደም ከነበሩት እንደ IPhone 15 ካሉት የተሻለ ዋጋ ያለዉ ሲሆን በFebruary 28 በገበያ ላይም በ 599$ ይዉላል ተብሏል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Ethio_telecom Ethio telecom በጣም ፈጣን የሆነ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ station አስጀመረች ። ይሄም የሆነዉ ከሁለት ቀን በፊት በየካቲት 9 ሲሆን ይህም የኤሌክትሪክ
#Ethio_telecom Ethio telecom በጣም ፈጣን የሆነ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ station አስጀመረች ። ይሄም የሆነዉ ከሁለት ቀን በፊት በየካቲት 9 ሲሆን ይህም የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ station የሚገኘዉ ከመገናኛ - ቦሌ ባለዉ መንገድ በሁለቱም side እንደሚገኘም ተገልፃል ። ይሄ ቻርጅ ማድረጊያ 600kw ሲሆን አብዛኛዎችን የኤሌክትሪክ መኪና በ15 ደቂቃ ብቻ ቻርጅ ማድረግ የሚችል ነዉ ። ሌላዉ ይሄ ችርጅ ማድረጊያ AI powered ሲሆን ፣ ይሄም የተለያዩ የመኪናዎች ባትሪ የተለያየ የሀይል መጠን ሰለሚቀበሉ ፣ ይሄም AI ለነዚህ መኪናዎች የሚያስፈልጋቸዉን የሀይል መጠን Adjust ለማድረግ በዋናነት ይጠቅማል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#The_Line ዛሬ ደግሞ ከሳኡዲ የ2030 ትላልቅ ፕሮጀክት ዉስጥ የምናየዉ The Line የሚባለዉን ቀጥ ያለ መስመር ያለዉ Futuristic ከተማ ነዉ ። በእቅዳቸዉ መሰረት The line 170K
+3
#The_Line ዛሬ ደግሞ ከሳኡዲ የ2030 ትላልቅ ፕሮጀክት ዉስጥ የምናየዉ The Line የሚባለዉን ቀጥ ያለ መስመር ያለዉ Futuristic ከተማ ነዉ ። በእቅዳቸዉ መሰረት The line 170Km ርዝመት ፣ 200 meter ስፋት እና 500 meter ከፍታ ይኖረዋል ። ከዚህ እቅድ ዉስጥ ያስገረመኘ በዚህ ቀጥ ያለ መስመር ከተማ ዉስጥ ወደ ~10 Million ሰዉ ገደማ ይኖርበታል ተብሏል ፣ እንዲሁም ምንም አይነት አስፖልት ፣ መኪና አይኖርም ተብሏል ። በዚህ ከተማ ዉስጥ በጣም ፈጣን መጓጓዣ ይኖራል ይህም ከመሬት ስር ሲሆን ሙሉ ከተማዋን በ20 ደቂቃ ብቻ መጓዝ የሚችል ይሆናል ተብሏል ። ሌላዉ ከተማዉ በእግር ለመጓዝ በጣም ምቹ ተደርጋ የምትሰራ ሲሆን ካለንበት ሆነን በ5 ደቂቃ ብቻ በቀን ዉስጥ የሚያስፈልጉንን ምግቦች ወይ እቃዎች (Basic needs) በቀላሉ የምናገኝ ይሆናል ። በቴክኖሎጂ ዘርፍም እንዲሁ ሁሉም ቤቶች ስማርት ቤቶች ሲሆኑ ፣ ድሮኖች ፣ እንዲሁም ሁሉም በሚባል ደረጃ የፍሳሽ አወጋገገድ ሲስተሙ በAI የሚሰራ ይሆናል ። የተወሰኑትን ቴክኖሎጂዎች ብቻ ነዉ የጠቀስኩላቹ ከነዚህም በላይ ብዙ Advanced Technologies በተግባር ላይ ይዉላሉ ተብሎ ይጠበቃል ። በተጨማሪም ይሄ ከተማ አሁን ላይ ከላይ በምስሉ ላይ እንደምታዪት በግንባታ ላይ ነዉ ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

+2
#Trojena ዛሬ ከሳኡዲ የ2030 እቅዶች ዉስጥ የምናየዉ Trojena የሚባለዉን ፕሮጀክት ነዉ ። ይሄ ፕሮጀክት የሚገኘዉ በሳኡዲ አረቢያ ሳራዋት በሚባለዉ ተራራ ሲሆን በዋናነነት ለEntertainment የሚገነባ ትልቅ ፕሮጀክት ነዉ ። በዚህ ከተማም የተለያዩ መዝናኛዎች እንደ Hiking, Biking ,water sports , skydiving, concerts , festivals ,skiing ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። በቴክኖሎጂ ዘርፍም  Advanced የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ ይዉላሉ ፣ ከነዚህም ዉስጥ smart cooling technologies ፣ AI powered city management ፣ IOT integration ፣ Robots ፣ Self driving vehicles እንዲሁም Augmented Reality እና Holographs በብዛት ጥቅም ላይ  ይዉላሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ይሄ ፕሮጀክት አሁን ላይ በግንባታ ላይ ያለ ሲሆን ከ2030 በፊት ተጠናቆ የ2029 የኤስያዉን የበረዶ ላይ ዉድድር ያዘጋጃል ተብሎ ይጠበቃል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Grok-3 የElon Musk Startup AI ካምፓኒ xAI በነገዉ እለት Grok-3 የሚባል AI Model እንደሚለቅ አስታዉቋል ። ይህም AI Model እስካሁን ካየናቸዉ AI models በReas
#Grok-3 የElon Musk Startup AI ካምፓኒ xAI በነገዉ እለት Grok-3 የሚባል AI Model እንደሚለቅ አስታዉቋል ። ይህም AI Model እስካሁን ካየናቸዉ AI models በReasoning በጣም የተሻለ እንደሆነ Elon Musk በትዊተር ገፁ የገለፀ ሲሆን ፣ እንዲሁም ነፃ እና ገደብ የሌለው እንደሆነ እና ከነገ ጀምሮ ለሁሉም ክፍት እንደሚሆን ገልፃል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic

#Oxagon ዛሬ የምናየዉ ከሳኡዲ የ2030 ትላልቅ ፕሮጀክት ዉስጥ አንዱ የሆነዉን Oxagon City የሚባለዉ የባህር ላይ ፕሮጀክት ነዉ ። ይህ ፕሮጀክት የሚገኘዉ በሳኡዲ አረቢያ ቀይ ባህር ዳርቻ
+1
#Oxagon ዛሬ የምናየዉ ከሳኡዲ የ2030 ትላልቅ ፕሮጀክት ዉስጥ አንዱ የሆነዉን Oxagon City የሚባለዉ የባህር ላይ ፕሮጀክት ነዉ ። ይህ ፕሮጀክት የሚገኘዉ በሳኡዲ አረቢያ ቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ሲሆን በዋናነት Industry city በመባልም ይጠቀሳል ። በዚህ ኢንዱስትሪ ዞን የሚጠቀሙት Industry 4.0 የሚባለዉ ማለትም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጥሬ እቃዎችን ማምረት ፣ በአጠቃላይ የIndustry process በAI ፣ Robotics ፣ እንዲሁም  በIot (Internet of Things) የሚከናወን ይሆናል ።  በአጠቃላይ ይሄም ከተማ Renewable Energy ብቻ የሚጠቀም ሲሆን በከተማዉ ዉስጥ ያሉትም መንቀሳቀሻዎችም ሁሉም ኤሌክትሪክ ብቻ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል ። አሁን ላይ ይሄ ከተማ ግንባታ ላይ ሲሆን የተወሰነ ክፍሉም የተጠናቀቀ ሲሆን በ2030 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ።           ✨ #Share ✨ SourceEnglish  |  Amharic