Tech +(ET)
Open in Telegram
ሰላም ይህ TECH + አማርኛ ቻናል ነው በዚህ ቻናል » አዳዲስ የቴክኖሎጂ መረጃዎች » ስለኮምፒውተር , የስልክ update መረጃዎች ይለቀቃሉ ያለዎትንም እውቀት ያሳድጋሉ ። Let's Empower Africa in The Tech Industry Together
Show more780
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-130 days
Posts Archive
780
#Ad
🫴 ቴሌግራም ፕሪምየም በቅናሽ ከእኛ ያግኙ 🚨
✨የ 3 ወር 3000 I 2100 | በ2000 ብር
✨የ 6 ወር 3500 | 2800 | በ2700 ብር
✨የ 12 ወር 5500 | 4900 | በ4800 ብር
የክፍያ አማራጭ
» telebirr
» CBE (Commercial Bank of Ethiopia)
» BOA (Bank of Abyssinia)
📥 የምትከፍሉበትን አካዉንት SafaPath በማናገር ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ከከፈላቹ በኋላ ፕሪምየም የሚገዛለት የአካውንትዎን username ይልኩልናል በአጭር ጊዜ ውስጥ አካዉንታቹ Premium ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ 🫴 SafaPath
780
#Schedule_Messages
ዛሬ በቴሌግራም ዉስጥ እኔ ከምጠቀምባቸዉ የቴሌግራም ፊቸሮች ዉሰጥ አብዛኞቻቹን ሊጠቅም ይችላል የምለዉን የማጋራቹ ይሆናል ፣ ይሄ ፊቸር Schedule Message ይባላል ፣ የሚጠቅመዉም አንድን ሚሴጅ ለሰዉ በሆነ ሰአት መላክ ፈልጋቹ ግን በዛ ሰአት ኦንላይን መሆን ባትችሉ እና ግን በዛ ሰአት ያንን ሚሴጅ መላክ ቢኖርባቹ ሚሴጁን መላክ የሚያስችላቹ ፊቸር ነዉ ፣ እንዴት ይሄንን ፊቸር መጠቀም እንደምትችሉ በኮመንት ስር የማጋራችሁ ይሆናል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#Tropic
በኢንግላንድ (UK) የሚገኘዉ Tropic የሚባል የBiotech ድርጅት ሰሞኑን CRISPR በሚባል gene መቀየር በሚያስችል ቴክኖሎጂ የሰሩት ሙዝ ሳይበላሽ ለብዙ ጊዜ እንዲቆይ አስችሎታል ፣ ይህ ቴክኖሎጂ በሙዙ ውስጥ የሚገኙ እና ሙዙን በፍጥነት እንዲበስል የሚያደርጉ ኢንዛይሞችን (enzymes) በማስቆም ሙዙ እንዳይበላሽ ይረዳል ። ግኝቱም በብዙ ሀገራት ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን እንደምናዉቀዉ ሙዝ ቶሎ የሚበስል ፍራፍሬ በመሆኑ ቶሎ ካልተበላ የሚባክን በመሆኑ ይሄ ግኝት ግን ሙዙ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ በማስቆየት የምግብ ብክነትን ለማስቀረት በጣም ይጠቅማል ተብሏል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#Tropic
በኢንግላንድ (UK) የሚገኘዉ Tropic የሚባል የBiotech ድርጅት ሰሞኑን CRISPR በሚባል gene መቀየር በሚያስችል ቴክኖሎጂ የሰሩት ሙዝ ሳይበላሽ ለብዙ ጊዜ እንዲቆይ አስችሎታል ፣ ይህ ቴክኖሎጂ በሙዙ ውስጥ የሚገኙ እና ሙዙን በፍጥነት እንዲበስል የሚያደርጉ ኢንዛይሞችን (enzymes) በማስቆም ሙዙ እንዳይበላሽ ይረዳል ። ግኝቱም በብዙ ሀገራት ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን እንደምናዉቀዉ ሙዝ ቶሎ የሚበስል ፍራፍሬ በመሆኑ ቶሎ ካልተበላ የሚባክን በመሆኑ ይሄ ግኝት ግን ሙዙ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ በማስቆየት የምግብ ብክነትን ለማስቀረት በጣም ይጠቅማል ተብሏል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#Estonia
በሰሜን Europe የምትገኘዉ ኢስቶኒያ (Estonia) በሀገር ደረጃ ChatGPT በትምህርት ቤቶች ዉስጥ የትምህርት ሂደቱን ለማሻሻል መጠቀም እንደሚጀምሩ ገልፀዋል ፣ በዚህች ሀገር የሚገኙ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ከSeptember 1,2025 ጀምሮ ይሄን አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን ይህም የEstonia መንግስት ከOpenai ጋር ባደረጉት ስምምነት ነዉ ፣ ይህም ስምምነት ለተማሪዎች በትምህርታቸዉ ላይ የሚያግዝ ፣ እንዲሁም ለአስተማሪዎች ደግሞ የሚያስተምሩትን ነገር በማዘጋጀት ይረዳቸዋል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#ጥንቃቄ
ሰማኑን በቴሌግራም የቴሌግራም ፕሪምየም በነፃ ተቀብለዋል የሚል ከስሩ ሊንክ ያለው በብዙ ቻናሎች እየተሰራጨ ነው ። ይሄ ሊንክ ከተጫናችሁት አካውንታችሁ 100% ይጠለፋል ፣ በምታውቁት ሰው ቢላክላቹም የሱ አካዉንት ተጠልፍ ሊሆን ይችላል እና ሊንኩን በፍፁም እንዳትነኩት ። በስህተት የከፈታችሁ ካላችሁ በአስቸኳይ ይህን አድርጉ በመጀመሪያ ፕሮፋይላችሁ ላይ ወዳለው Settings ላይ ግቡ Devices የሚለውን ከነካቹት ቡሃላ የሚያጠራጥር ነገር ካያቹ በቀይ የተፃፈውን Terminat All Other Sessions የሚለውን ተጫኑና ከሁሉም አካውንታችሁ Login ከተባለባቸው ዲቫይሶች ውጡ ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#Telegram
Telegram አዲስ Update አዉጥቷል ። አዲሱ Update ላይ ብዙ ለዉጦች ያሉ ሲሆን ከነሱም ዉስጥ እኔን የተመቸኝ በኮንታክታቹ ዉስጥ የሌለ ከዚህ ቀደም ያላናገራቹት ሰዉ እናንተን Inbox ሲያረግላቹ የሰዉየዉ ስልክ ቁጥር የተከፈተበት ሀገር ፣ መቼ የProfile ፎቶዋቸዉን ፣ ስማቸዉን እንደቀየሩ ፣ መቼ አካዉንቱ እንደተከፈተ እንዲሁም Verified የተደረገ Official አካዉንት ከሆነ ከላይ በመሰሉ ላይ እንደምትመለከቱት ያሳያችዋል ። ይሄ አዲስ ፊቸር የተመቸኝ በዋናነት አብዛኛዎቹ በTelegram የሚያጭበረብሩ ( Scammers ) የሚጠቀሙት ስልክ የዉጭ ሀገረ ሲሆን እንዲሁም አንድ ሰዉ ካጭበረበሩ ቡሃላ የአካዉንታቸዉን ፎቶ እና ስም ስለሚቀይሩ እነሱን ለመከላከል ስለሚረዳ ነዉ ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
የመጀመርያው Biocomputer ተሰራ!በላብራቶሪ ውስጥ ያደጉ የሰዉ ኒዉሮኖችን በመጠቀም ማስላት (Compute) የሚችል Cortical CL1 የተባለ የመጀመርያዉ Biocomputer March 2 ላይ Cortical Labs በሚባል ድርጅት ተዋዉቋል ። እነዚህ ኒዉሮኖች Silicon Chips ላይ የተገጠሙ ሲሆኑ ይህም ኮምፒተሩ በራሱ ልክ እንደ ተፈጥሯዊ ጭንቅላት መማር ፣ ማሰብ ፣ መላመድ እንዲችል ያስችለዋል ፣ ከዚህም በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ካሉ ኮምፒተሮች ሀይል ይቆጥባል ተብሎ ይታሰባል ። እነዚህ ኮምፒተሮች በዋናነት አሁን የተሰሩት የሰዉ ኒዉሮኖችን ሪሰርች ( ለማጥናት ) ሲሆን ማንኛዉም ድርጅት ይሄንን Biocomputer መግዛት ከፈለገም ከ35,000$ ጀምሮ በCortical Labs ዌብሳይት ላይ መግዛት እንደሚችል ተገልፃል ። ✨ #Share ✨ Source | English | Amharic
780
#Anker Solix Cloax
በ2011 የተመሰረተዉ Anker Solix የተባለ ድርጅት በዘንድሮዉ MWC25 Solar Cell ያለዉ ጃኬት አስተዋዉቋል ። ይህ ጃኬት ባለዉ Solar cell አማካኝነት ከፀሀይ በሚያገኘዉ ሀይል በዉስጡ ባለዉ 30Watt USB - C አማካኝነት ስልካችንን ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል ሲሆን ጃኬቱ ቻርጅ ከማድረግ በተጨማሪ በብርድ ወቅት ብርድ እንዳይሰማን ሙቀት ያመነጭልናል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
ውድ የ TECH + አባላት በሙሉ የምፖስታቸውን ፖስቶች እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉን #MUTE ካደረጉት እንዳሉ አይቆጠርም 😶🌫
ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ከታች #MUTE የሚል ካለ ምንም አይንኩት 👍
#UNMUTE❕ የሚል ካለ ደሞ አንድ ግዜ በመጫን #MUTE ላይ በማድረግና የምንለቃቸውን ፖስቶች ሼር በማድረግ አብራችሁን ሁኑ ❤️
✨#Share✨
⚜ Tech plus amharic ⚜
780
#Lenovo Thinkbook Flip
በትናንትናው እለት በተጠናቀቀው MWC25 , Lenovo አዲስ የላፕቶፕ ሞዴል አስተዋውቋል ። ይህ አዲስ ያስተዋወቀዉ የላፕቶፕ ሞዴል 13.1inch OLED display ያለዉ ሲሆን ረዘም ያለ ስክሪን ካስፈለገን ግን ወደ 18.1inch መርዘም የሚችል ሲሆን ከዚህ ቀደም Lenovo በCES25 ካስተዋወቀዉ Lenovo Thinkbook Plus gen6 Rollable ላፕቶፕ ይሄ የሚለየዉ ከላይ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት መታጠፍ መቻሉ ላፕቶፑን አጣጥፈን እንደ ታብሌት ማስጠቀም ማስቻሉ ነዉ ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
780
#Realme
በፈረንጆቹ 2018 በቻይና ዉስጥ የተመሰረተዉ የስልክ አምራች ድርጅት Realme በዘንድሮዉ MWC ( Mobile World Congress ) ከጀርባዉ የካሜራ ሌንስ (Lens) መገጠም የሚችልበት ስልክ አስተዋወቀ ። ለጊዜዉ ስልኩ በገበያ ላይ የሚዉል ባይሆንም ይሄ የRealme አዲስ ያስተዋወቀዉ ስልክ ብዙዎችን አስገርሟል ። Realme በዋናነት ይሄን ስልክ የሰራበት ምክንያት በስልካችን የምናነሳቸዉን ፎቶዎች ይበልጥ ለማሻሻል ሲሆን በተገጠመለት 1-inch Sony CMOS Sensor አማካኝነት DSLR ወይም Mirrorless camera Lenses ከስልኩ ጀርባ መግጠም የሚያስችል ሲሆን ይህም ልክ በካሜራ እንደምንነሳዉ ፎቶግራፍ የተሻለ ፎቶ መነሳት እንድንችል ይረዳናል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#Infinix
የቻይናዉ ስልክ አምራች ድርጅት Infinix በዘንድሮዉ MWC ( Mobile World Congress ) በፀሀይ ብርሀን (Solar) ስልክን ቻርጅ ማድረግ የሚችል Cover አስተዋወቀ ። ይሄ Cover በWireless ቻርጅ መደረግ ለሚችሉ ስልኮች ብቻ የሚሰራ ሲሆን ከቨሩ በዉስጡ እስከ 2W power መያዝ የሚችል ነዉ ። ይሄ ከቨር የስልክን ባትሪ ለማራዘም በዋናነት የተሰራ ሲሆን በዉስጡም MPPT ( Maximum Power Point Tracking ) ያለዉ ሲሆን ይህም ወደ ከቨሩ የሚገባዉን ሀይል በመመጠን ከመጠን በላይ እንዳይግል ያረገዋል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
ምን ያህላቹ ስለ MWC Barcelona ታዉቃላችሁ?🧐
🫴 MWC( Mobile World Congress) ልክ እንደ CES አመታዊ የቴክኖሎጂ ምርቶች የሚተዋወቁበት ዝግጅት ነው። በየአመቱ የሚዘጋጀዉ ይሄ ዝግጅት በSpain , Barcelona Fira Gran Via አዳራሽ ዉስጥ የሚካሄድ ሲሆን ፣ ከ2700 በላይ ድርጅቶች እና ከ101,000 በላይ ታዳሚዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ። የዚህም አመት ከmarch 3 - march 6 የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ ትላልቅ ድርጅቶችም እንደ Samsung, Huawei, Lenovo ያሉ ድርጅቶች አዳዲስ ምርት ካላቸዉ የሚያስተዋወቁበት ነዉ ። በዚህ Tech+ Channel ከዚህ ቀደም በCES25 ላይ የተዋወቁትን አስገራሚ ምርቶች እንዳጋራሁዋቹ በMWC25 ላይ ያስገረሙኝን ከነገ ጀምሮ ለእናንተ የማቀርብላቹ ይሆናል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#Blue Box
Steve Jobs አፕልን ከመመስረቱ በፊት ከጓደኛዉ Steve Wozinak ጋር Blue Box የሚባል Device ሰርተዉ ነበር ይህም በ1970ዎቹ የርቀት ስልክ ለመደዋወል ልክ እንደ ቅንጡ የሚታይበት ጊዜ ነበር ፣ በጣም ዉድም ነበር ፣ በደቂቃ 0.7$ ይቆጥር ነበር ። ነገር ግን እነ Steve የሰሩት ይሄ ህገወጥ Device በነፃ የተፈለገዉን ርቀት ያክል ማስደወል የሚያስችል ነበር ። Steve በሽያጭ ላይ ጓደኛዉ ደግሞ በማምረቱ ላይ ይሄንን Device በ170$ ይሸጡ ነበር !
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#Oura Ring 4
ከላይ በፎቶዉ ላይ የምታዩት ቀለበት Oura Health በሚባል ህክምናን በቴክኖሎጂ ለማሻሻል በሚሰራ ድርጅት የተሰራ Smart ቀለበት ሲሆን ፣ ቀለበቱ በተገጠመለት Smart Sensing Technology የእንቅልፍ ሁኔታችንን ፣ የጤናችንን ሁኔታ ፣ የሰውነት ሙቀታችንን ፣ እንዲሁም የጭንቀት ደረጃችንን መለካት የሚችል ቀለበት ነዉ ። ቀለበቱ የተሰራዉ ሙሉ በሙሉ በTitanium ሲሆን ይህም ቀለበቱ ቀለል ያለ እና ምቾት እንዲኖረዉ ያደርገዋል ። ሌላዉ ቀለበቱ በቻርጅ የሚሰራ ሲሆን በአንድ ቻርጅም እስከ 8 ቀን ድረስ ማገልገል ይችላል ። ይሄ ቀለበት በገበያ ላይ ያለ ሲሆን በOura ዌብሳይት ላይ ከ$349 ጀምሮ በመሸጥ ላይም ይገኛል ።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
780
#Instagram
INSTAGRAM Reels ( አጫጭር ቪድዮ ) ብቻ የሚለቀቅበት ራሱን የቻለ App ሊለቅ ይችላል ተባለ ። የInstagram Head ( ዋና ) Adam Mosseri ለInstagram ሰራተኞች ሲናገር እንደተሰማዉ እና ሌሎች እንደ BBC, CNET, THE VERGE የሚባሉት ትላልቅ ሚድያዎች እንደዘገቡት በቅርቡ Instagram እራሱን የቻለ አጫጭር ቪድዮ ብቻ የሚለቀቅበት App እንደሚለቅ ዘግበዋል ። ይሄ App በዋናነት በአሜሪካ ከ170 ሚልየን በላይ ተጠቃሚ ያለዉ TIKTOK በአሜሪካ ዉስጥ የወደፊት እጣፈንታዉ ስላልታወቀ የቲክቶክን ተጠቃሚ ወደ አዲሱ የInstagram አጫጭር ቪድዮ ብቻ የሚለቀቅበት App Shift ለማድረግ የታሰበ ሲሆን ፣ ከዚህም በተጨማሪ እንደሚታወቀዉ Instagram ፎቶ , ቪድዮ የሚለቀቅበት App ነዉ ፣ ነገር ግን አሁን ይሄ እራሱን የቻለ አጫጭር ቪድዮ ብቻ የሚለቀቅበት App ከተለቀቀ በInstagram ላይ ፍቶ ብቻ ሼር የሚደረግበት App ይሆናል ፣ ይህም User experience ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል።
✨ #Share ✨
Source | English | Amharic
