en
Feedback
Tech +(ET)

Tech +(ET)

Open in Telegram

ሰላም ይህ TECH + አማርኛ ቻናል ነው በዚህ ቻናል » አዳዲስ የቴክኖሎጂ መረጃዎች » ስለኮምፒውተር , የስልክ update መረጃዎች ይለቀቃሉ ያለዎትንም እውቀት ያሳድጋሉ ። Let's Empower Africa in The Tech Industry Together

Show more
Buy Ad
781
Subscribers
+124 hours
+27 days
+130 days
Posts Archive
ለwhatsapp ተጠቃሚዎች በሙሉ ማይክሮሶፍት ኮፖይለት AIን ከሁሉም ፊቸሮቹ ጋር whatsapp ላይ ማግኘት ትችላላቹ image generation ጭምር ። Microsoft's Copilot ስማርት as
ለwhatsapp ተጠቃሚዎች በሙሉ ማይክሮሶፍት ኮፖይለት AIን ከሁሉም ፊቸሮቹ ጋር whatsapp ላይ ማግኘት ትችላላቹ image generation ጭምር ። Microsoft's Copilot ስማርት assistant በይፋ WhatsApp ላይ ስራ ጀምሯል ።                  ✨#Share✨ ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

የሩስያ ሮቦቲክስ ፈጠራዎች በኢትዮጵያ ይታያሉ =============================== ከጥቅምት 14-16, 2024 በአዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ ሃውስ በደቡብ ምዕራብ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በ
የሩስያ ሮቦቲክስ ፈጠራዎች በኢትዮጵያ ይታያሉ =============================== ከጥቅምት 14-16, 2024 በአዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ ሃውስ በደቡብ ምዕራብ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በRosotrudnichestvo ስር ለተዘጋጀው "የሮቦቲክስ እና የፈጠራ ትምህርታዊ ቴክኖሎጂዎች ቀን ይቀላቀሉን። ይህ ክስተት ለተማሪዎች፣ ለመምህራን፣ ለሳይንቲስቶች እና ለሮቦቲክስ ፍላጎት ላለው ማንኛውም ሰው ክፍት ነው። ዋና ዋና ዜናዎች ንግግሮች፣ በእጅ ላይ የሚሰሩ አውደ ጥናቶች፣ የጨዋታ ውድድሮች እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ማሳያዎችን ያካትታሉ። ነጻ ምዝገባ፡ 👉 link ከነጻ መግቢያ፣ ምሳ እና መጠጦች ጋር። የቴክኖሎጂን የወደፊት እጣፈንታ ለመመርመር ይህንን እድል እንዳያመልጥዎት!                  ✨#Share✨ ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

44ኛው የጂ.አይ.ቴክስ /GITEX Global/ 2024 ኤክስፖ ተጠናቀቀ፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ180 በላይ የዓለም ሀገራት የተሳተፉበት የጂ.አይ.ቴክስ /GITEX Global/ 2024 ኤክስፖ ፍጻሜዉ
+3
44ኛው የጂ.አይ.ቴክስ /GITEX Global/ 2024 ኤክስፖ ተጠናቀቀ፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ180 በላይ የዓለም ሀገራት የተሳተፉበት የጂ.አይ.ቴክስ /GITEX Global/ 2024 ኤክስፖ ፍጻሜዉን አግኝቷል፡፡ በኤክስፖዉ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ስማርት ሲቲ እና የሳይበር ደህንነት በትኩረት ሲዳሰሱ ሰንብተዋል፡፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በፋይናንስ፣ በደህንነት እንዲሁም ጤና ላይ ሊያበረክት የሚችለዉን ሚና የሚያጎሉ ትዕይንቶች በስፋት ቀርበዋል፡፡ በኤክስፖዉ ለዕይታ ከቀረቡ እና የብዙዎችን ቀልብ ከሳቡ ፈጠራዎች መካከል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመድኃኒት ቅመማ እንዲዉል የሚያስችለዉ ግኝት ተጠቃሽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ሰዉ መሰል ሮቦቶች (humanoid robots) ትርኢቶችን አቅርበዋል፡፡ የተለያዩ ኩባንያዎችም የበራሪ ታክሲ ሞዴሎችን በኤክስፖው አስተዋዉቀዋል፡፡ 200 ኩባንያዎች 200ሺህ ዶላር ሽልማት ለማግኘት የተወዳደሩበት የጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ዉድድር (The Supernova Challenge) የኤክስፖዉ ሌላኛው ድምቀት ነበር፡፡ በመጨረሻም ፓኪስታን የቴክኖሎጂዉን ሥነ-ምህዳር ለማስፋት በሰራችዉ ስራ “Tech Destination of the Year” የሚል ስያሜን በማግኘት መርሓ ግብሩ ፍጻሜውን አድርጓል፡፡                  ✨#Share✨ ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

Google በሳምሰንግ ስልካችን ላይ አዳዲስ privacy feature አካቷል ። ከነዚህ ፊቸሮች መካከል : - - Theft Detection Lock - Offline Device Lock - Remote L
Google በሳምሰንግ ስልካችን ላይ አዳዲስ privacy feature አካቷል ። ከነዚህ ፊቸሮች መካከል : -     - Theft Detection Lock     - Offline Device Lock     - Remote Lock ናቸዉ ። 1) Theft Detection Lock : - ይህ ፊቸር ሌባ ስልካችሁን ከእጃቹ ላይ መንትፏቹ ሲሮጥ በmotion sensor አማካኝነት automatically lock ያረጋል ። 2) Offline Device Lock : - በዚህ ፊቸር ደግሞ ሌባው አድራሻውን እንዳታውቁበት data ካጠፋባቹ ስልኩ automatically lock ያደርጋል ። 3) Remote Lock : -ይህን ፊቸር በመጠቀም ስልክ ቁጥራችሁን android.com/lock ላይ በማስመዝገብ ስልካቹን Remotely Lock ማድረግ ትችላላቹ ። እነዚህን ፊቸሮች ON ለማድረግ ከፈለጋቹ ስልካቹ settings ውስጥ በመግባት Google የሚለዉን በመንካት ከሚመጣለቹ አማራጮች መካከል All services ሚለዉን ትነካላቹ ከዛም ከሚመመጡላቹ አማራጮች መካከል Theft Protection ሚለዉን በመንካት እነዚህን ፊቸሮች ማግኘት ትችላላቹ ።                  ✨#Share✨ ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ ለማስፋፋት ያለመ ዓለምአቀፍ ጥምረት ይፋ ሆነ፡፡ የኳታር ፋውንዴሽን (WISE) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ ስለ የሰውሰራሽ አስተውሎት
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ ለማስፋፋት ያለመ ዓለምአቀፍ ጥምረት ይፋ ሆነ፡፡ የኳታር ፋውንዴሽን (WISE) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ ስለ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ሚና ግንዛቤን ለማዳበር እንዲሁም ብቁ የሰው ኃይል ለመፍጠር ከአለማቀፉ የትምህርት ተቋምና ከአለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ምርምር ለማካሄድ ያለመ ጥምረት አድርጓል። ፋውንዴሽኑ ከአለማቀፉ የትምህርት ተቋምና ከሰባት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት የክህሎት ልማት ውስጥ ቴክኖሎጂው ያለውን ሚና ለመዳሰስ እና ለማስፋፋት የሚያስችለውን ጥምረት መስርቷል፡፡ ጥምረቱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ ለማስፋፋት ያለመ እና የቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግም እንደሚሰራ ይጠበቃል፡፡ ጥምረቱ በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ በአፍሪካ፣ በእስያ፣ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ባሉ ሃገራት ባሉ ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች ጥናቶችን እንደሚያደርግ ኤፍ.ኢ ኒውስ ድረገፅ ዘግቧል።                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

Companies Not Requiring College Degrees በሚል ታዋቂው FOX Business የሰራው ዜና » Bank Of America ,DELL, Google እና IBM ጨምሮ አለም ላይ ተፅእኖ
Companies Not Requiring College Degrees በሚል ታዋቂው FOX Business የሰራው ዜና » Bank Of America ,DELL, Google እና IBM ጨምሮ አለም ላይ ተፅእኖ የፈጠሩ ታዋቂ ካምፓኒዎች ለመቀጠር Degree አያስፈልግም ብቃቱ ነው ወሳኙ ነገር እያሉ ነው! እዚ ሀገራችን ደግሞ ለ5 ሺ ብር ደሞዝ 2ኛ ዲግሪ ፣ 13 አመት የስራ ልምድ... 😁                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

ስቴም ፖወር ! ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች ለ3ተኛ ዙር የቀረበ ጥሪ ! ስቴም ፖወር (STEMpower) ከፊንላንድ ኤምባሲ (Embassy of Finland Ethiopia) እና ከአይቢኤም (IBM)
ስቴም ፖወር ! ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች ለ3ተኛ ዙር የቀረበ ጥሪ ! ስቴም ፖወር (STEMpower) ከፊንላንድ ኤምባሲ (Embassy of Finland Ethiopia) እና ከአይቢኤም (IBM) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሥራ አጥ ወጣት ሴቶችን ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ለመስጠት ያለመ " ትጋት " የተሰኘ ፕሮግራም አስተዋውቀዋል። ባለፉት 2 ዙሮች 1700 በላይ ለሚሆኑ ሴቶች በ Project Management, Web Development , Cyber Security, Digital Marketing , Data Analytics , Information Technology , Job Readiness , Work Readiness ስልጠና የሰጠ ከመሆኑ በተጨማሪ የስራ እድል በመፈጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል አመቻችቷል፡፡  #ነጻ በሚሰጠውና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት በሚያስገኘው በዚህ ስልጠና እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ሴቶች ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እያሳወቅን ምዝገባው የሚቆየው ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10 , 2017 ዓ/ም ሲሆን ቀድማችሁ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን፡፡ እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ከስር ባለውን ሊንክ ይመዝገቡ 👉Link: https://forms.office.com/r/bJedLrdqmd                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

ቴስላ ሮቦቫን የተሰኘ አዲስ ሾፌር አልባ ተሽከርካሪ አስተዋወቀ፡፡ ሮቦቫን የሚል መጠሪያ የተሰጠዉ ሾፌር አልባ መኪና በትናንትናዉ ዕለት ቴስላ ባዘጋጀዉ የትዉዉቅ መድረክ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ 20 ሰ
+2
ቴስላ ሮቦቫን የተሰኘ አዲስ ሾፌር አልባ ተሽከርካሪ አስተዋወቀ፡፡ ሮቦቫን የሚል መጠሪያ የተሰጠዉ ሾፌር አልባ መኪና በትናንትናዉ ዕለት ቴስላ ባዘጋጀዉ የትዉዉቅ መድረክ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ 20 ሰዎችን የመጫን አቅም ያለዉ መኪናዉ 30ሺህ ዶላር መሸጫ ዋጋ ተተምኖለታል፡፡ መኪኖቹ በዋናነት የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጡ ታስበዉ እንደተሰሩ ቴስላራቲ በድረ ገጹ አስታዉቋል፡፡ የቴስላ ባለቤት ኤለን መስክ በትውውቅ መርሓ ግብሩ ወቅት እንደተናገሩት ከአውሮፓውያኑ 2027 በፊት ተሽከርካሪዎቹን ለገበያ ለማቅረብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ ሮቦቫን ወደ ስራ ሲገባ የትራንስፖርት ዋጋ በመቀነስ ብሎም የመንገድ ላይ ቆይታን በማሳጠር ምቹ የሆነ የትራንስፖርት ሥነ ምህዳርን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡ በፈረንጆቹ 2003 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን ለመስራት የተቋቋመዉ ቴስላ አሁን ላይ ትኩረቱን ሾፌር አልባ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ማምረት ላይ አድርጓል፡፡                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

የአፍሪካ ትልቁ የቴክኖሎጂ ውድድር ነገ ጥቅምት 3 በአዲስ አበባ ይቀጥላል። ነገ በአህጉሪቷ ያሉ ብሩህ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ እና አስደናቂ ፈጠራዎችን እናያለን። በዚህ የሃካቶን ኤክስፖ ከአልጄሪያ፣ ኢት
+7
የአፍሪካ ትልቁ የቴክኖሎጂ ውድድር ነገ ጥቅምት 3 በአዲስ አበባ ይቀጥላል። ነገ በአህጉሪቷ ያሉ ብሩህ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ እና አስደናቂ ፈጠራዎችን እናያለን። በዚህ የሃካቶን ኤክስፖ ከአልጄሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ እና ቱኒዚያ የተወጣጡ የመጨረሻ ደረጃ 8 ፕሮጀክቶችን 9 የA2SV Core Development ፕሮጀክቶች እናያለን እንዳይቀሩ! የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ አፍቃሪ ከሆኑ ፣ ይህን አህጉር አቀፍ የቴክኖሎጂ ባህል ልውውጥ እንዳያመልጥዎ! የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎችን እና የእርስዎን የቴክኖሎጂ ህይወት መንገድ ይወቁ፣ ያድንኩ፣ ይማሩ፣ ይለወጡ፦ የኤግዚቢሽኑ ቀን - ጥቅምት 3 እሑድ፣ ከጠዋቱ 3 ሰኣት እስከ 12 ሰኣት። አድራሻ- ዓብረሆት ቤተመጻህፍት፣ 4 ኪሎ አዲስ አበባ መግቢያ- በነጻ ለበለጠ መረጃ: http://hackathon.a2sv.org                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

“የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያከናወነ የሚገኘው ስራ ለሌሎች ተቋማትም አቅም የፈጠረ ነው፡፡” ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክ
+9
“የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያከናወነ የሚገኘው ስራ ለሌሎች ተቋማትም አቅም የፈጠረ ነው፡፡” ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የከተማ አስተዳደሩ እና የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኢንስቲትዩቱ እየሰራቸው ስለሚገኙ ስራዎች ለልዑካኑ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ክብርት ከንቲባዋ ከጉብኝቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ የራሳችንን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ያለማንበት እና ማስተዳደር የቻልንበት መሆኑን መመልከት ችለናል ብለዋል፡፡ አሰራርን የሚያዘምኑ እና ቅልጥፍናን የሚጨምሩ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎችን በዚሁ በሀገራችን እና በኢትዮጵያውያን መሰራቱ የሚያኮራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ የተቋም ግንባታ ሂደት በቴክኖሎጂ ለደረሰበት የላቀ ደረጃ ኢንስቲትዩቱ ምስክር መሆኑን አጽንዖት ሰጥተውበታል፡፡ በሀገራችን የመረጃ አያያዝ ትልቁ ክፍተት ነው ያሉት ክብርት ከንቲባዋ፤ መረጃን በቴክኖሎጂ አስደግፎ በአግባቡ መያዝ፣ መተንተን ብሎም ለውሳኔ አሰጣጥ እንደ ግብዓት መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልጻዋል፡፡                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

ኦፕን ኤ.አይ ኦ ዋን (o1) የሚል መጠሪያ የሰጠው አዲስ ሞዴል አስተዋወቀ፡፡ በኦፕን ኤ.አይ (OpenAI) ካምፓኒ የበለፀገው ይህ ሞዴል የተወሳሰበ ችግር መፍታት እና የማሽን የማገናዘብ ችሎታዎችን
ኦፕን ኤ.አይ ኦ ዋን (o1) የሚል መጠሪያ የሰጠው አዲስ ሞዴል አስተዋወቀ፡፡ በኦፕን ኤ.አይ (OpenAI) ካምፓኒ የበለፀገው ይህ ሞዴል የተወሳሰበ ችግር መፍታት እና የማሽን የማገናዘብ ችሎታዎችን ማዳበር የሚችል ነው፡፡ ሞዴሉ እንደ ቻት ጂ.ፒ.ቲ ሞዴል ሁሉ ለጥያቄዎች ምላሽ መስጠት፣ ይዘት ማመንጨት እና ይዘትን ማጠቃለል የሚችል ነው፡፡ ሞዴሉ ማሽኖች እንደ አንድ ሰው ምላሽ ከመስጠታቸው በፊት ችግሮችን በጥልቅ ማሰብና ማሰላሰል እንዲችሉ ያደርጋል፡፡ ይህ ሞዴል የማሽን ማሰብ ሂደት እና ለጥያቄዎች የሚሰጠውን ምላሽ በፍጥነት ከፍ በማድረግ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምርን ለማሳደግ ጠቃሚ እርምጃ ነው ተብሎለታል፡፡ ኦ ዋን የማሽን እሳቤ እና በሰዎች ሁኔታዎችን የመተንተን አቅም መካከል ያለውን ክፍተት ለማስተካከል እንደ መሸጋገሪያ ሆኖ በማገዝ አዲስ ነገር ይዞ መምጣቱ ተጠቁሟል። ይህ የኦ.ዋን ሞዴል እምቅ አቅም የተላበሰ እና ውስብስብ ችግርን መፍታት ለሚፈልጉ የተለያዩ መስኮች ከፍተኛ አንድምታ እንደሚኖረው የሚዲየም ድረገፅ መረጃ ይጠቁማል። ©: የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

#NGAT የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለፈተና ማዕከልነት የመረጡ ተፈታኞች ብቻ የፈተናው ጊዜ የተለወጠ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡
+1
#NGAT የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለፈተና ማዕከልነት የመረጡ ተፈታኞች ብቻ የፈተናው ጊዜ የተለወጠ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ በሌሎች የፈተና ጣቢያዎች (ዩኒቨርሲቲዎች) ፈተናውን ለመውሰድ ያመለከቱ በሙሉ፣ ፈተናው በተያዘው ዕቅድ መሰረት ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል፡፡ Via @tikvahuniversity                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

⚜️Digital Marketing ተከታታይ ትምህርት ክፍል 1 🤔ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድነው? 👉ዲጂታል ማርኬቲንግ ኢንተርኔት እና ሌሎች ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እንደ ሞባይል ስልኮች፣ ዴስክቶፕ ኮምፒ
⚜️Digital Marketing ተከታታይ              ትምህርት                ክፍል  1 🤔ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድነው? 👉ዲጂታል ማርኬቲንግ ኢንተርኔት እና ሌሎች ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እንደ ሞባይል ስልኮች፣ ዴስክቶፕ ኮምፒተሮች እና ሌሎች ዲጂታል ሚዲያዎችን በመጠቀም ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን  ማስተዋወቅ ነው። 👉ደንበኞች ጋር ለመድረስ እና ለማሳተፍ ዲጂታል ቻናሎችን የሚጠቀም ማንኛውም የግብይት አይነት ነው። 🫵 የዲጂታል ማርኬቲንግ አይነቶች ❕ 👀 Pay-Per-Click (PPC) Advertising ፡ PPc የዲጂታል ማርኬቲንግ  ወሳኝ ገጽታ ነው ። ይህ ሞዴል በተለምዶ እንደ ጎግል ካሉ የመጀመሪያ ደረጃ የፍለጋ ፕሮግራሞች ጋር የተቆራኘ እና የተገናኘ ነው ነው። 🤩 Social Media Marketing (SMM) ፡ የማህበራዊ ሚዲያ ግብይት የምርት ስሞችን ለመገንባት፣ ሽያጮችን ከደንበኞች ጋር መስተጋብር ለመፍጠር የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን መጠቀም ነው። » ታዋቂ ማህበራዊ ሚዲያዎች ለገበያ እና ለብራንዲንግ ግቦች የሚያገለግሉ የዲጂታል ግብይት ቁልፍ አካል ናቸው። 🔥Content Marketing ፡ ማለት ተመልካቾችን ለመሳብ፣ ለማሳተፍ እና ለማቆየት ጠቃሚ፣ ተዛማጅነት ያላቸውን እንደ ጽሑፎች፣ ቪዲዮዎች፣ ፖድካስቶች እና ሌሎችንም መፍጠር እና ማጋራትን የሚያካትት ስትራቴጂያዊ አካሄድ ነው። ~ ይህ የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ ከፍተኛ ጥራት ያለው ይዘትን በማቅረብ ከታለመላቸው ታዳሚዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመገንባት ላይ ያተኩራል።                           ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

📌የተረጋገጠ መረጃ🤝 ✨ኦርጅናል የሳምሰንግ ቻርጀር ከ ኮፒው ቻርጀር መለያ መንገድ🔥                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

ውድ የ TECH +👨‍💻 አባላት በሙሉ የምፖስታቸውን ፖስቶች እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉን #MUTE ካደረጉት እንዳሉም አይቆጠርም😞 ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ከታች #MUTE የሚል ካለ ምንም አ
ውድ የ TECH +👨‍💻 አባላት በሙሉ የምፖስታቸውን ፖስቶች እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉን #MUTE ካደረጉት እንዳሉም አይቆጠርም😞 ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ከታች #MUTE የሚል ካለ ምንም አይንኩት 👍 #UNMUTE❕ የሚል ካለ ደሞ አንድ ግዜ በመጫን #MUTE ላይ በማድረግና የምንለቃቸውን ፖስቶች ሼር በማድረግ አብራችሁን ሁኑ 🫵                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

#Adv                                                        🔥 Dogs, Notcoin, Toncoin, usdt  ኖሯችሁ Wallet Verify አድርጎ P2p ላይ መሸጥ ላልቻላችሁ እኛ እየገዛን ነው 🔥 ~~~~ » Dogs ✨                                                                » Not✨                                                                » USDT✨ ~~~~ TON ለመግዛት, መሸጥ የምትፈልጉ @CO_NN_ECT

የወደፊቱ የአለማችን የኢንተርኔት አብዮት Starlink ምንድን ነው? Starlink በኤለን መስክ ድርጅት SpaceX የተመሰረተ የሳተላይት ኢንተርኔት project ነው። የዚህ ፕሮጀክት ተቀዳሚ ተልዕ
የወደፊቱ የአለማችን የኢንተርኔት አብዮት Starlink ምንድን ነው? Starlink በኤለን መስክ ድርጅት SpaceX የተመሰረተ የሳተላይት ኢንተርኔት project ነው። የዚህ ፕሮጀክት ተቀዳሚ ተልዕኮው በዓለም ዙሪያ ላሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማያገኙ ገጠራማና ሩቅ የአለም ክፍሎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ብዙ ቁጥር ያላቸው Low Earth Orbit (LEO) ሳተላይቶችን በጋራ በማሰማራት የፋይበር ኦፕቲክና የሞባይል ኔትዎርክ ግንኙነት የማያገኙ አካባቢዎችን አስተማማኝና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማቅረብ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ዋና ዋና ባህሪያቶች ⚫️Global Coverage: የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት መላው ፕላኔት የሚሸፍን ሲሆን ይህም ቀደም ሲል የኢንተርኔት ግንኙነት የማያገኙ የአለማችን ክልሎችን ተደራሽ ያደርጋል። ⚫️High-Speed Internet: ስታርሊንክ ከባህላዊ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር የሚወዳደር የብሮድባንድ ፍጥነትን የሚያቀርብ ሲሆን Online Gaming, Video Conferencingና የመሳሰሉ real-time online ስራዎችን በጥሩ ፍጥነት መከወን ያስችላል። ⚫️Easy Installation: StarLink ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነችና በቀላሉ ከታ ቦታ ማንቀሳቀስ የምትቻል Dish ሲኖረው ማንኛውም ቦታ ላይ በማስቀመጥ እራሷን ከሳተላይት ጋር ማስተካከል ትችላለች። ከዚህ በተጨማሪ LTE connection ላላቸው የሞባይል ቀፎዎች የፅሁፍና የድምጽ መልዕክት እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛሉ ተብሏል።                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

Hacking Exposed Network Security & Solutions Contents -Footprinting -Scanning -Denial of Service (DOS) attack -Web hacking                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

🤝P2P ምንድነው ?🧐 ~ P2P ማለት peer to peer ሲሆን ይህም ሲብራራ Binance ላይ የሚገኙ የክሪፕቶከረንሲ ንግድ ተጠቃሚዎች ያላቸውን መሸጥ እንዲሁም የሌላቸውን የሚገዙበት መንገድ ነ
🤝P2P ምንድነው ?🧐 ~ P2P ማለት peer to peer ሲሆን ይህም ሲብራራ Binance ላይ የሚገኙ የክሪፕቶከረንሲ ንግድ ተጠቃሚዎች ያላቸውን መሸጥ እንዲሁም የሌላቸውን የሚገዙበት መንገድ ነው ። 🤗 P2P ምን ጠቀሜታዎች አሉት ? ~ P2P ወይም ደሞ peer to peer ለሰዎች የፈለጉትን የክሪፕቶ ከረንሲ ልውውጥ ለመፈፀም ይረዳል እንዲሁም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት የዶላር አቅርቦትን ለማግኘት ቀላሉ መንገድ ነው ''የዋጋው መወደድ እንዳለ ሆኖ'' ይህ እንዳለ ሆኖ ከP2P ገዝተን በምናገኘው ዶላር የተለያዩ online payment መፈፀም እንችላለን። 👀 P2P እንዴት መጠቀም እንችላለን ❕ ~ P2P ለመጠቀም በመጀመሪያ verify የሆነ የ binance አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል verify ለማድረግ የራሳችን የሆነ national id ወይም passport መጠቀም እንችላለን ። 😑 P2P risk አለው ወይ ? ~ P2P ትክክለኛ ሻጭ እና ገዢዎች እንዳሉት ሁሉ scammer (ሌቦችም ይገኙበታል) ስለዚህ የምንገዛው ወይም የምንሸጥለትን ሰው ለይተን ማወቅ አለብን እንዴት ማወቅ እንችላለን ? binance የራሱ የሆነ የ feedback platform አለው ይህ ማለት አንድ ሰው ለሚሰራው ስራ ከተጠቃሚዎቹ የሚያገኘው ምላሽ አለ ያ ምላሽ public የሆነ ሲሆን ጥሩም ሆነ መጥፎ የተሰጠው feedback በፊት ለፊት ገፁ ላይ ይታያል ያንን በመመልከት እንዲሁም ያከናወናቸው ንግድ ብዛት ፣ ከፈፀማቸው ሽያጭ ወይም ግዢ ስንቱን በትክክለኛ መንገድ እንደጨረሰ ፣ እንዲሁም በፐርሰንት ምን ያክል የተአማኒነት ደረጃ እንዳለው በማየት እራሳችንን ከሌቦች መጠበቅ እንችላለን ። 😮‍💨                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️

👉 binance ምንድነው ? binance በክሪፕቶከረንሲ ላይ የሚሰራ በእለታዊ የንግድ ልውውጥ በክርፒቶ ከረንሲ የምንዛሬ ልውውጥን የሚሰራ አለምአቀፍ ኩባንያ ነው ። binance 2017 በቻይና ው
👉 binance ምንድነው ? binance በክሪፕቶከረንሲ ላይ የሚሰራ በእለታዊ የንግድ ልውውጥ በክርፒቶ ከረንሲ የምንዛሬ ልውውጥን የሚሰራ አለምአቀፍ ኩባንያ ነው ። binance 2017 በቻይና ውስጥ የንግድ ሶፍትዌርን በፈጠረው ቻንግፔንግ ዣኦ ነው የተመሰረተው ። ሆኖም የቻይና መንግስት ክሪፕቶከረንሲ ኩባንያዎች ላይ ገደብ በመጣሉ ወደ ጃፓን ሊዘዋወር ችሏል በአሁን ሰአት binance በ ዩናይትድ ስቴት ይገኛል ። 👉 የ binance ጠቀሜታ ምንድነው ? binance የተለያዩ ነጋዴዎችን (trader) ምንዛሬዎችን እንዲሰሩ እንዲሸጡ እና እንዲለዋወጡ የሚያስችል ቀዳሚ የ 𝕔𝕣𝕪𝕡𝕥𝕠𝕔𝕦𝕣𝕣𝕖𝕟𝕔𝕪 ኩባንያ ነው ። እንዲሁም በ 𝕔𝕣𝕪𝕡𝕥𝕠𝕔𝕦𝕣𝕣𝕖𝕟𝕔𝕪 ላይ የሚገኙ የተለያዩ ኮይኖችን exchange ለማድረግ ይረዳል ለምሳሌነት ያክል በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተደራሽነትን ያተረፈው ቢትኮይን መጥቀስ ይቻላል 👉 Binance ኢትዮጵያ ሆነን እንዴት እንጠቀማለን ? binance በአለም አቀፍ ደረጃ እገዳ ከጣሉ አንድ አንድ ሀገሮች ውጪ በሁሉም ሀገር መጠቀም ይቻላል የሚያስፈልገን (email or phone number ) እንዲሁም national id or passport ነው በኢትዮጵያ ለምንገኝ የታደሰ ፓስፖርት ብንጠቀም የተሻለ ነው ። ከላይ እንደጠቀስኩት ኢትዮጵያ ላይ በብዛት ለዶላር ግብይት ነው የምንጠቀመው ለማንኛውም የውጪ payment ዶላር በ binance ላይ ከሚገኘው P2P platform በመግዛት መጠቀም ይቻላል በ P2P platform ገዢዎችም ሆነ ሻጮች ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው የምንጠቀመው የክፍያ መንገድ የሀገር ውስጥ ባንኮችን በመሆኑ የፈለግነውን ክፍያ ለመፈፀም ቀላል ይሆንልናል ።                  ✨#Share✨      ⚜️ @Tech_plus_amharic ⚜️