✨ ቅዱሳት አንስት ☀️
Open in Telegram
"በፍጹም ልብሽ በእግዚአብሔር ታመኚ፥ በራስሽም ማስተዋል አትደገፊ፤ በመንገድሽ ሁሉ እርሱን እወቂ እርሱም ጎዳናሽን ያቀናልሻል፡፡ " ምሳ 3 ፤ 5-6 ✨
Show more1 564
Subscribers
-324 hours
-107 days
-430 days
Posts Archive
1 564
ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ተገናኝቶ መወያየት፥ አብሮ መሳቅ፥ ልብን ለልብ ማቀራረብ እነዚህም ድሎች ናቸው!
ነገር ግን ድልን በገንዘብ፥ ባለጠግነትን በንዋይ ብዛት ብቻ ለመለካት ስንጥር ቀስ በቀስ ከተፈጥሯችን፥ ከራሳችንም ሆነ ከእርስ በርሳችን ራቅን።
ደስታን በሩቅ አንፈልገው፥ ሰማይ ላይም አንስቀለው ከምር መካከላችን አለ፥ ፍቅር ባለበት ሁሉ ደስታ አለ፥ የፍቅር ሚዛን ገንዘብ፥ ቁስ አይደለም፤ ፍቅር የሚመዘነው በልብ ነው። የመንግሥተ ሰማይ DNA በመካከላችን ያለው ፍቅር ነው!
ስለዚህ ደስታን ከውጭ አንፈልግ፥ በፍቅራችን ውስጥ እናግኘው! ✍️ ዳዊት እንዳሻው ✨
☀️ https://t.me/Kdusat_Anst ☀️
1 564
2ኛ ቆሮ 12 : 9 ✨..... እርሱም ጸጋዬ ይበቃሻል ኀይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኀይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ..... በድካሜ ልመካ እወዳለኹ ። ❤️🩹 ☀️ https://t.me/Kdusat_Anst ☀️
1 564
✨ ዓለሙን እና በአለም ያለውን አትውደዱ ዓለሙን የሚወድ ግን የአብ ፍቅር በእርሱ የለም።ዓለሙም ያልፋል ምኞቱም ያልፋል የእግዚአብሔርን ፍቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለአለም ይኖራል።ዮሐ ፪፥፲፭ 💞 🤍
@Kdusat_Anst✨
1 564
🫶 ........ መታቀፍ መታቀፍ ብቻ አይደለም። ራሱን የቻለ ቋንቋ ነው። የፍቅር ቋንቋ .... የምቾት ቋንቋ .... ቃልኪዳን .... የማይደበዝዝ ትዝታ ነው።💞 🤍💞
@Kdusat_Anst✨
1 564
🌸 ሁሉ ባንተ እንዳለ ገብቶኛል ትርጉሙ
በሀዘን በመከራ የማመስገን ጣዕሙ
መዛል ድካም ባይጠፋም በሕይወቴ
አትተወኝ አማኑኤል አባቴ
በዘመኔ ሁሌ አለህ ከኔ ጋራ
✨ ጉልበቴ ነህ እንዳልወድቅ እንዳልፈራ ❤️🩹
☀️ https://t.me/Kdusat_Anst
1 564
🤍 ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም 🤍
መድኃኔዓለም
1 564
✨ አንተ ያደረግህልኝን ማሰብ እንዳልተው አመስጋኝ ነፍስን ስጠኝ፤በሐዘኔም ውስጥ አጽናኝ፤ በድካሜ ውስጥ ጉልበትን ስጠኝ፣ በቸርነት የላቅህ ጌታ ሆይ፤ በደሎቼን ሁሉ ይቅር በለኝ እንጂ ብዙ የሆኑትን ኃጢአቶቼን አታስብብኝ:: አቤቱ ጌታዬ፤ የኔ የክፉውን ኃጢአተኛ ጸሎት አትናቀው:: ከዚህ በፊት እንደጠበቀኝ ሁሉ ለወደፊትም እንዲጠብቀኝ በጸጋህ እስከመጨረሻው አጽናኝ:: ጥበብን ያስተማረኝ ያንተ ጸጋ ነው፤ የእርሷን [የጥበብን] መንገድ የሚከተሉ ብጹዓን ናቸው፤ የክብር አክሊልን ይቀዳጃሉና:: ጌታ ሆይ፤ ምንም የማልረባ ብሆንም ስንኳ አመሰግንሃለሁ፤ አከብርሃለውም፤ ለእኔ ያለህ ምህረት ገደብ የለውምና:: ረዳቴና ጠባቂዬ አንተ ነህ:: ስምህ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን::
ወይኩነነ በከመ ፈቃድከ አምላክነ 🤍
@Kdusat_Anst✨
1 564
💔...... እነዚያ መሸሸጊያ ያጣሁባቸው ቀናት ፤ በመኖርና ባለመኖር ሳለሁ አንተ ብቻ ነበርክ ተክለአብ 🤍! ...... አንተ ብቻ ። ታምሜ መድሀኒት ባጣሁባቸው ዓመታት ፤ እነዚያ ቸር እጆችህ ያቀፉኝ አንተ ብቻ ነበርክ 🤍
ቀንና ሌት ስርህ ተደፍቼ ባነባሁበት ሁሉ እንባዬን እየጠረጉ ሐዘኔን ያስረሱኝ ክንዶችህ በእድሜ ዘመኔ አልዘነጋቸውም። ተስፋ ባልነበረኝ ነገር ሁሉ ገብተህ እነሆ ዛሬ የምስጋና ቃል ከአፌ አይጠፋም። እስከሞት ህቅታ አመሰግንሃለሁ። አንተ ከእኔ ጋር ነህና የማያልቅ በረከትን ከእጅህ አግኝቻለሁና ! በነፍስም በሥጋም ጠብቀኸኛልና!
አባ ተክለሃይማኖት ሆይ ተመስገን! ተመስገን! ተመስገን!🤍
☀️ https://t.me/Kdusat_Anst 💫
1 564
አይኔ እንባን ያፍስ ላልቅስ ስለ ሀጢያቴ
የንስሀ ትሁን ቀሪዋ ህይወቴ
በመዳኔ ሰአት በዛሬዋ ለት
ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ከአንተ ፊት 🤍
@Kdusat_Anst✨
1 564
✨ ጌታ በአልዐዛር ሞት አዝኖ ካለቀሰ ፤ አልዐዛርንም “አልዐዛር አልዐዛር” ብሎ ጠርቶ ከመቃብር ካስነሳ ፤ለእናቱ ይህን ማድረጉ ምን ይገርማል? ከአልዐዛር ድንግል ማርያም አትቀርበውምን? ለአልዐዛር ያዘነሰ በእናቱ ይጨክናልን? 💞
✨ የድንግል ማርያም ማረጓ ሳይሆን የሚገርመው መሞቷ ነው 🤍 አርጋለች ማርያም ተነስታለች✨
ከተራራው አናት ከደጅሽ መጥቼ ሰምሮልኛል ስምሽን ጠርቼ🥰🥰እንኳን አደረሳችሁ 🥰 እንጦጦ ኪዳነምህረት🤍 ✨https://t.me/Kdusat_Anst💫
1 564
ሐዋርያት አበው እንኩዋን ደስ አላችሁ😍
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ🥹
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
🥀 አርጋለች ማርያም ተነስታለች✨🤍
ስለ ቸርነትሽ ለእኔ እናቴ ነሽ🙌
🌸 ኪ ዳ ነ ም ህ ረ ት 💝
✨https://t.me/Kdusat_Anst💫
