Princ faysel
Open in Telegram
➜ ከዚህ ቻናል አንብባችሁ በተጠቀማችሁ ቁጥር፤ይህን ደካማ እና ስህተቱ ብዙ የሆነውን ወንድማችሁን በመልካም ዱዓችሁ አስታውሱት https://t.me/princfaysel
Show more2 640
Subscribers
-324 hours
-217 days
-9730 days
Posts Archive
2 640
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إذا قال العبدُ الحمدُ للهِ كثيرًا قال اللهُ تعالى اكتُبُوا لعبدي رحمتي كثيرًا﴾
“ባሪያው፦ ‘የበዛ ምስጋና ለአላህ ይሁን’ ሲል የላቀው አላህ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ ‘የበዛ ራህመትን’ ለባሪያዬ መዝግቡለት።”
2 640
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿اقتربَتْ الساعةُ ولا يزدادُ الناسُ على الدنيا إلا حِرْصًا، ولا يزْدادُونَ من اللهِ إلا بُعدًا﴾
“ሰዓቲቱ (ትንሳዔ) ቀርባለች ሰዎች ግን በዱኒያ ላይ ጉጉትን (ፍላጎትን) እንጂ አይጨምሩም። ከአላህ መራቅን እንጂ አይጨምሩም።”
2 640
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
لو أنَّ ابنَ آدمَ هرب من رزقِه كما يهرُبُ من الموتِ، لأدركه رزقُه كما يُدرِكُه الموتُ
“የአደም ልጅ ከሞት እንደሚሸሸው ሁሉ ከሪዝቁ (ከሲሳዩ) ቢሸሽ ኖሮ ሞት እንደሚያገኘው ሲሳዩም ያገኘው ነበር።”
2 640
ይህ ከዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር የተላለፈ የበጎነት ጥሪ ነዉ !
100+ projectአባል በመሆን በምንሰራቸዉ የበጎ አድራጎት እና የወጣት ተኮር ስራዎች ላይ በቋሚነት ድጋፍ ያድርጉ ለመመዝገብ :-https://darulmemebrsfrom.netlify.app/ ለበለጠ መረጃ :- @abu_osman4 ወይንም 0939963771 ላይ አናግሩን
2 640
አንዳንድ ሰዎች ችግረኞችን፣ ለማኞችን፣ አካለ ስንኩላንን፣ የአዕምሮ በሽተኞችን፣ በረንዳ አዳሪዎችን ...ያዩና ምርር ብሏቸው አላህ ግን ለምን እንዲህ ያረጋል ብለው ሲጠይቁ እሰማለው
እንዲህ ነው ብዬ በምሳሌ ባስረዳ አልረካም ።
ግና እኔ የማውቀው አንድ ተራ የአላህ ፍጡር መሆኔን ነው። የኔ ሥራ በአላህ ማመን፣ እሱን ማምለክ፣ እሱ ሰጥ ለጥ ብሎ መታዘዝ፣ ሥራው ሁሉ ፍፁም ፍትሃዊ እንደሆነ በፀጋ መቀበል ፣ ክፍፍሉን መውደድ፣ በሚያደርገው ነገር ላይ ጥያቄ አለማንሳት፣ አለመጠራጠር፣ ቅር አለመሠኘት፣ አለማጉረምረም ነው።
ሲሻው ይቆራርጠኝ፣ ሲሻው ይፍለጠኝ፣ ሲሻው ይበጣጥሰኝ፣ ሲሻው እንደሻው ያድርገኝ፣ ... ምንም ያድርገኝ ምን እኔ ባርያው ነኝ። የሱ ንብረት ነኝ።
ገና ድሮ በአላህ አምኜያለሁ ስል ይህን ሁሉ አቋም ይዠ ነው ወዳጆቼ ።
ምንን ለምን እንደሚሠራ እሱ ያውቃል ። በጥበቡ፣ በዕውቀቱና በፍትሁ ላይ ምንም ጥያቄ አናነሳም።
ነፍሳችን ስለምታንሾካሹክልን መጥፎ ነገሮች ሁሉ
አላህ ይቅር ይበለን አመስጋኝ መሆን ይሻለናል
2 640
በልብህ ውስጥ መቼም የማይተኙ 4 ሌቦች እንዳሉ ታውቃለህ?
ኢማም አል-ገዛሊ (ራ. ዓ)እንዳብራሩት እነዚህ ሌቦች መሣሪያ አይታጠቁም፣ ነገር ግን የልብህን ብርሃን በዝምታ ይሰርቁታል። እነሱም: —
1.ስሜት (ሻህዋ)፦ ደስታን ቃል ይገባል፣ ግን መቼም አይረካም።
2.ቁጣ፦ በፍጥነት ካልጠፋች ቀድማ ያንተን ልብ የምታቃጥል እሳት ናት።
3.የዝና ፍቅር፦ ለአላህ የሚሰራን ንጹህ ስራ ይሰርቃል፤ የሰዎችን አድናቆት ብቻ እንድትሻ ያደርጋል።
4.የሀብት ፍቅር፦ ገንዘብን መሣሪያ ማድረግ ሲገባህ የልብህ ግብ ሲሆን ባሪያ ያደርግሃል።
★መፍትሄው
እነዚህ ሌቦች የውስጥ ሰላምን ያውካሉ፣ ኢባዳን የተራራ ያህል ያከብዳሉ። ፈውሳቸው ዘወትር ራስን መመርመር ሲሆን፥ ይህም ስሜትን በመቃወም፣ ቁጣን በትዕግስት በመስበር፣ ክብርን ለአላህ ብቻ በመስጠት እና ሀብትን በእጅ እንጂ በልብ ውስጥ ባለማስቀመጥ ይገለጻል።
[በሰለዋት የደመቀ በመልካም ስራ የታጀበ ጁምዓ ይሁንልን
2 640
መንገድ ላይ ሰወችን የሚያሰቃዩ ችግሮችን ማስወገድ የኢማን ክፍል ከሆነ...የልቦችን ስቃይ ማቅለልና ማስወገድስ የትኛው ከፍ ያለ የኢማን ክፍል ሊሆን እንደሚችል አስብት ...
የልብ ስሜት ከእግር ይበልጣልና
2 640
ዱንያ ምን ያህል ብጠብብህ
አላህ በሮችን ያለ ቁልፍ እንዳልፈጠራቸው አትርሳ
ባሪያወቹ በሩን እንዲያንኮኩ ሲፈልግ ይፈትናቸዋል አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላም በባሪያው ልብ ውስጥ ከሱ የሚተልቅ ምንም ነገር እንደሌለ ሲመለከት ፈረጃውን ይፈቅድለታል ። ልብህን በአላህ ላይ አንጠልጥል..
2 640
ልብህን ማን እንደሚገባው ማወቅ ከፈለክ
ያንተን ደስታ በህይወቱ ላይ ቅድሚያ ለሚሰጥ አድርግ
ልቦች በቆንጆ ቃላት አይወሰዱም ስሜትን ጠብቀው ለደስታችን ልቦችን ለሚጠብቁ ነው ።
ውዴታውን ለሁሉም ሁኔታወች ላይ ዋጋ ያደርጋል
2 640
ሰው ማለት ሌላ ነገር አይደለም ልክ እንደናንተው የሆነ ሌላ እናንተን ነው !
የሆነ ነገር ስታስቡ ለሀሳባችሁ መሳካት ውር ውር የሚል ሮቦት አይደለም ። በዚህ እሳቤ እየኖርን ነው የተቸገርነው ።
2 640
ምስጋና ለእርሱ ....
በውዱእ ውስጥ ወንጀል ማጥራትን ላደረገው ጌታ ፤ በሱጁድ ውስጥ ሀዘንን ማራገፍ ላደረገው አላህ ፤ በልብ ውስጥ ቁርአንን ብርሀን ላደረገው ዐዚዝ ፤ በመስጠት ውስጥ ደስታን ላደረገው ከሪም ፤ ከሀዘን በኋላ ደስታን ላደረገው ረሂም ምስጋና የተገባው ነው 🤲
2 640
ነገሮች ሁሉ በተወሳሰቡበት በዚህ ዘመን አንዳንድ ጊዜ ጥግ መያዝን የመሠለ ነገር ይሆን?!
ከአብዛኛው ሰው ዉሎ መራቅ፣ መገለል።
ጥግ ይዘህ ራስህን መገምገም።
ስለ ጥፋትህ፣ ስለ ጉድለትህ፣ ስለ ድክመትህ ከአላህ ጋር ማውራት፣ ማንሾካሾክ።
ነገሮችን ቁጭ ብለን ስናስባቸው ይደክማል ። ከአላህ ጋር ስናንሾካሹክ ቀለል ይላል።
አምላካችን ሆይ! አትተወን፣ አታርቀን፣ አትጥላን
2 640
:اللهم صل على سيدنا محمد عبدك ونبيك ورسولك، النبي الأمي، وعلى آله وأزواجه وذريته وسلم. عدد خلقك، ورضا نفسك، وزنة عرشك، ومداد كليماتك.
