ጤናአዳም🌿 ᴛʜᴏᴜɢʜᴛs 🪮
Open in Telegram
┣✨•°➖☆ ፈዋሽ ቤት ☆➖🌥 ┣✨•°➖☆ ነፃ ሃሳቦች 🔥 ☆➖🌥 ┣✨•°➖☆ኢትዮጵያዊነት🇪🇹☆➖🌥 ┣✨•°➖☆ ኩሩው ቤተሰብ☆➖🌥 ┏━━━━━━━━━━ ┣ @tikurhabeshay
Show more5 510
Subscribers
-324 hours
-537 days
-18730 days
Posts Archive
5 510
እያንዳንዳችን ተበላሽቶ ለሚመጣው ትውልድ ተወቃሾች ነን። ትል ከበላው ፍሬ ደና ዘር አይወጣ! ለሌላ ሰው ግድ የማይሰጠን ራስ ወዳድ።
5 510
፨ ኤሊ እና ጥንቸል ፨
በመጀመሪያ ማሙሽ ነበረ። ማሙሽም ሰዎችን አስተውሎ ማየት ይወድ ነበረ። መንደሬውም አስተያየቱን አይቶ "የልጅ ቡዳ" ይለው ነበረ።
በርግጥ ማሙሽ አያፈጥም አይባልም ... ያፈጣል!
ለማሙሽ የሰው ማንነቱ የሚታዬው ሲናገር ሳይሆን ሲያዳምጥ ነው'ና ... ሰዎች ወግ ሲሰሙ የሚቀያየረውን የፊታቸውን ገፅታ በአትኩሮት ያያል። ይታዘባል። ይወዳል። ይጠላል።
አመል ከተባለ ይሔው ነው አመሉ! ... ከዬት እንዳመጣው ግን እሱም አያውቅም። ብቻ እንዲሁ እንዲሁ ያደርገዋል።
ጎረቤቶቹን ራሱ የሚያስታውሳቸው በስማቸው ሳይሆን ላደማመጣቸው በሰጠው ቅፅል ስም ነው። "ኧረ ተው መጣ!" ይላል ባወሩት ቁጥር በየመሀሉ "ኧረ ተው?" የሚለው አባተን ሲያዬው። እያወሯት ትካዜ ውስጥ የምትገባውየምትገባውን ሸዋዬን "ወግ ለምኔ!" ይላታል። ለሌሎች ጎረቤቶችም "ጥርስ በጥርስ" "እጅ ባገጭ"፣ "ለንቦጭ ነው ጆሮዬ"፣ "የፈጣሪ ያለህ" ... እያለ እነሱ የማያውቁትን ቅፅል ስም ሰጥቷቸዋል።
አደማመጣቸውን የማይወድላቸውን ሰዎች እንኳን ቁሞ ሊያወራቸው ገና ሲያያቸው ከርቀት ነው የሚሸሻቸው። ከየትኛው ወገን እንደሚመድባቸው ለመወሰን ደግሞ ከሁለት ቀን በላይ አይፈጅበትም። ይሁን እንጂ ከተወለደ ጀምሮ ከአጠገቡ ያለችውን የወላጅ እናቱን አመል ከየትኛው እንደሚያደርገው ሊያውቅ አልቻለም።
የጓደኞቹ እናት ልጆቻቸው ጋር ሲያወሩ ሁለት አይነት አደማመጥ ነው ያላቸው። ወይ ''አታድርቀኝ" ብለው በጊዜ ያባርሩታል። አልያም ደግሞ የተገረሙ እየመሰሉ ያዳምጡታል። የሱ እናት ከሁለቱም አለመሆኗ ግራ ያጋባዋል። ወይ ተወኝ አትለው ... ወይ አትገረምለት። አንዴ ሰፌዷን አንዴ ጨርቋን እየጠለፈች ውሎውን ለማወቅ ያህል ብቻ "እሽ?" ... "ከዛስ?"... "ነው?"... "ጨረስክ?"... "በል ግባና ልብስህን ቀይረህ ምሳህን ብላ!" ትለዋለች። ሰዎች ታሪክ ሲሰሙ የሚያሳዩት ባህሪ ለሚያሳስበው ማሙሽ ይሔ የ'ናቱ አመል ምንም አልተዋጠለትም። ይጥላት?... ይውደዳት? ለመወሰን ተቸገረ። ''እንዴት ያለ ነገር ነው ጎበዝ!" ይላል ጎረቤቶቹ ዝናብ ቀርቶባቸው ግራ ሲጋቡ እንደሚሉት እያለ።
በቀላሉ ሊተወው አልቻለም። ትምህርት ቤት ከሔደ በኋላ ቀኑን ሙሉ የሚጨነቀው ሲመለስ ውሎውን እንዴት እንደሚተርክላት ነው። ሲጨነቅ ውሎ መጥቶ ሲተርክላትም ግን "እሺ!"... "ከዛስ?"..."ነው?"... "ጨረስክ?"... በል ግባና ለ
