ጤናአዳም🌿 ᴛʜᴏᴜɢʜᴛs 🪮
Open in Telegram
┣✨•°➖☆ ፈዋሽ ቤት ☆➖🌥 ┣✨•°➖☆ ነፃ ሃሳቦች 🔥 ☆➖🌥 ┣✨•°➖☆ኢትዮጵያዊነት🇪🇹☆➖🌥 ┣✨•°➖☆ ኩሩው ቤተሰብ☆➖🌥 ┏━━━━━━━━━━ ┣ @tikurhabeshay
Show more5 510
Subscribers
-324 hours
-537 days
-18730 days
Posts Archive
5 510
፨ ኤሊ እና ጥንቸል ፨
በመጀመሪያ ማሙሽ ነበረ። ማሙሽም ሰዎችን አስተውሎ ማየት ይወድ ነበረ። መንደሬውም አስተያየቱን አይቶ "የልጅ ቡዳ" ይለው ነበረ።
በርግጥ ማሙሽ አያፈጥም አይባልም ... ያፈጣል!
ለማሙሽ የሰው ማንነቱ የሚታዬው ሲናገር ሳይሆን ሲያዳምጥ ነው'ና ... ሰዎች ወግ ሲሰሙ የሚቀያየረውን የፊታቸውን ገፅታ በአትኩሮት ያያል። ይታዘባል። ይወዳል። ይጠላል።
አመል ከተባለ ይሔው ነው አመሉ! ... ከዬት እንዳመጣው ግን እሱም አያውቅም። ብቻ እንዲሁ እንዲሁ ያደርገዋል።
ጎረቤቶቹን ራሱ የሚያስታውሳቸው በስማቸው ሳይሆን ላደማመጣቸው በሰጠው ቅፅል ስም ነው። "ኧረ ተው መጣ!" ይላል ባወሩት ቁጥር በየመሀሉ "ኧረ ተው?" የሚለው አባተን ሲያዬው። እያወሯት ትካዜ ውስጥ የምትገባውየምትገባውን ሸዋዬን "ወግ ለምኔ!" ይላታል። ለሌሎች ጎረቤቶችም "ጥርስ በጥርስ" "እጅ ባገጭ"፣ "ለንቦጭ ነው ጆሮዬ"፣ "የፈጣሪ ያለህ" ... እያለ እነሱ የማያውቁትን ቅፅል ስም ሰጥቷቸዋል።
አደማመጣቸውን የማይወድላቸውን ሰዎች እንኳን ቁሞ ሊያወራቸው ገና ሲያያቸው ከርቀት ነው የሚሸሻቸው። ከየትኛው ወገን እንደሚመድባቸው ለመወሰን ደግሞ ከሁለት ቀን በላይ አይፈጅበትም። ይሁን እንጂ ከተወለደ ጀምሮ ከአጠገቡ ያለችውን የወላጅ እናቱን አመል ከየትኛው እንደሚያደርገው ሊያውቅ አልቻለም።
የጓደኞቹ እናት ልጆቻቸው ጋር ሲያወሩ ሁለት አይነት አደማመጥ ነው ያላቸው። ወይ ''አታድርቀኝ" ብለው በጊዜ ያባርሩታል። አልያም ደግሞ የተገረሙ እየመሰሉ ያዳምጡታል። የሱ እናት ከሁለቱም አለመሆኗ ግራ ያጋባዋል። ወይ ተወኝ አትለው ... ወይ አትገረምለት። አንዴ ሰፌዷን አንዴ ጨርቋን እየጠለፈች ውሎውን ለማወቅ ያህል ብቻ "እሽ?" ... "ከዛስ?"... "ነው?"... "ጨረስክ?"... "በል ግባና ልብስህን ቀይረህ ምሳህን ብላ!" ትለዋለች። ሰዎች ታሪክ ሲሰሙ የሚያሳዩት ባህሪ ለሚያሳስበው ማሙሽ ይሔ የ'ናቱ አመል ምንም አልተዋጠለትም። ይጥላት?... ይውደዳት? ለመወሰን ተቸገረ። ''እንዴት ያለ ነገር ነው ጎበዝ!" ይላል ጎረቤቶቹ ዝናብ ቀርቶባቸው ግራ ሲጋቡ እንደሚሉት እያለ።
በቀላሉ ሊተወው አልቻለም። ትምህርት ቤት ከሔደ በኋላ ቀኑን ሙሉ የሚጨነቀው ሲመለስ ውሎውን እንዴት እንደሚተርክላት ነው። ሲጨነቅ ውሎ መጥቶ ሲተርክላትም ግን "እሺ!"... "ከዛስ?"..."ነው?"... "ጨረስክ?"... በል ግባና ለ
5 510
ሁሉም አዳም ሔዋን አለቸው ሁሉም ሄዋን አዳም አለላት አንተ/አንቺ እስካሁን ምንም ከሌላችሁ እባቡ ናችሁ ማለት ነው።
✍️ከጥልቁ
5 510
እኔ ምለዉ እቺ ሀገር እኛ የማናውቀው ሱስ አለባት እንዴ? 😂
እኔ ነፍስ ካወኩበት ጀምሮ ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ፣ ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም እየዞረች ስትቀፍል ፣ ወዲ በሉ ስትል "ብድር ስጡኝ" ስትል ነው የማያት።
እኔ አሁን ሁለት ጠጉር አወጣሁ ፤ እሷ ግን አሁንም እየቀፈለች ነው።
የሚያስገርመው ደግሞ መቀፈልን እንደ ስራ ይዛ ሳታፍር በዜና ላይ "እንዲህ ያህል ብድር ተፈራርመናል" ብላ በኩራት ታወራለች።
የማናዉቀዉ ሱስ እማ አለባት ? 🤔
5 510
“ልብሷን አውልቃ ቀና ስትል፣ አይናችን ተጋጨ።
“ጨነቀህ እንዴ?” አለችኝ።
“ምኑ?”
“ሰውነቴ…”
“ለምን ይጨንቀኛል?”
“በጣም ወፍራም ነኝ እኮ…”
“ብትሆኚስ?”
“ብዙ ወንዶች ቀጭን ሴቶችን ይወዳሉ ብዬ ነው።”
“እኔ ግን ቀጭን ሴት ምርጫዬ አይደለችም።”
ትንሽ ዝም ካለች በኋላ፦
“እና ውፍረቴ አያስጨንቅህም?”
“በፍጹም።”
“እርግጠኛ ነህ?”
“አዎ… ከላይ ልሁን ካልሽኝ ብቻ ነው የሚያስጨንቀኝ! 🤪”
5 510
+5
LEO MESSI has Retired from International Football..💔
We knew at The World Cup Final we just didn't wanna believe it.. Farewell The greatest of all time.. Your Country will always be Tankful for having you..
We will always love you Leo ⚡️
5 510
የማይወዳደር እኩያ የሚያጣ
ከልቤ ግርጌ ስር አንዳች ስሜት ወጣ
ተሰማኝ ወደድኩህ ያንተን ጣዕም ለየሁኝ
ቆዳዬ ቀመሰህ ምላሴን ከዳሁኝ
ከየትኛው አካሌ ፍቅርህ የወደቀው
የሚያርበተብተኝ ጥፍሬን የሚነዝረው
አካልስ አለ ወይ የሚታይ ሚቀመስ
ሴትነት ገላዬን ነክቶ ሚያጎለምስ
ንገረኝ አንተዬ ከደጅ እንዳያድር ዳስም ልጣልለት
እንዲህ ያለ ፍቅር አያድርም ከኔ ቤት
በአዳፋዬ ባያድፍ ንፁህ ጥሩ ፍቅርህ
ከቆሸሸ ገላ ከዚህ በድን ይሽሽ
እንዲህ ያለ ልመና ሚዛን አያነሳም
የፍቅር ባህሪ ዙፋንን አይሻም
የት ጋር ነው የሚሰማኝ ምኔን ነው የያዝከው
የት ጋር ነው ያገኘኸኝ ምኔን ነው ያጣኸው
ብቻ ከልቤ ስር ስሜቴ ይፈልቃል
የደረስክበትን ያልደረስክበትን
ረቂቁ ፍቅርህ እሱ ብቻ ያውቃል።
✍ ረድኤት ተረፈ🤎
