Yeshurun Library
Open in Telegram
598
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+730 days
Posts Archive
በወንድማችን የተዘጋጀች በጣም አሪፍ ስራ እነሆኝ! 😁 ነገረ ማርያም ላይ ተቀምማ የተሰደረች የምር አሪፍ ክታብ ናት። ለምታነቧት ሚዛናዊ ስራ ወንድማችን አቅርቦልናል። አንብባችሁ ተጠቀሙ። በተለይ የአማርኛ ንባብ ላይ ትኩረት ለምታደርጉ ሰዎች አያምልጣችሁ። ሌሎቻችሁም ጥሩ ጽሁፍ ካላችሁ አናግሩኝ በሸልፋችን ላይ ለሸልፈኞቻችን እናኖራለን
ሰሞኑ የአዳኛችንን የኢየሱስ የልደት መታሰቢያ በአል ስለሆነ እነዚህን የሰባኪያን ሁሉ ቁንጮ የሆነውን የ ቻርልስ እስፐርጀን ሰርመኖችን ብታነቡ አበረታታለሁ። ያው የእስፐርጀን ሰርመኖችን ማንበብ ሆነ መስማት በምድር እጅግ ውቡ ነገር ነው 😁
በተሃድሶ ነገረ መለኮት ጥናታችን አንድ የተወደደ ወንድም በትምህርቶቹ ላይ የጥንት አባቶችን ምን ብለው እንዳስተማሩ ማስረጃዎችን ብታቀርብልን ብሎኛል። በውነቱ ጥሩ ጥያቄ ነው። ግን እንደ አዳሳዊያን ስልታዊ በሆነ መንገድ አባቶች የጸጋ አስተምህሮ ላይ በተደራጀ መንገድ ማስረጃ ማቅረብ አስቸጋሪ ቢሆንም ትምህርቶቹ በአባቶች ጽሁፍ ውስጥ ፍራግመንትድ በሆኑ መንገዶች ማግኘት ግን ይቻላል። ለዚህም ጆን ጊል ጥሩ ስራ ሰርቷል ብዬ አምናለሁ። በአምስቱ የጸጋ ትምህርቶች ላይ የአባቶች ጽሁፎችን ማንበብ ለምትፈልጉ ይህን መጸሃፍ ተመልከቱ።
አደራ አናክሮኒዝም በሆነ መነጽር አባቶችን እንደ ኦርቶዶክሳዊያንና ካቶሊካዊያን ሰዎች እንዳታነቡ። በጥቂቱ የጸጋ አስተምህሮ በአባቶች ጽሁፍ ውስጥ እንዴት እንደተገለጡ በጥቂቱ እንድታዩ ብቻ ነው። ከኛ ወገንም ስታነቡ ደስ ብሏችሁ አባቶች እንደ አዳሳዊያን የጸጋ ትምህርትን በተደራጀ መንገድ ያስተምሩ ነበር ብላችሁ ጮቤ እንዳትረግጡ 😁
ክርስቲያን ነን የምንል ሰዎች በመጸሃፍት ራሳችንን ለመመርመር ከፈለግን በኔ ንባብ በዚህ የፒውሪታንስ መጸሃፍ ራሳችንን ማየት አለብን ብዬ አምናለሁ። ደግሞ የግል ምልከታዬ ስለሆነ ኧረ በመንፈስ ቅዱስና በቃሉ እንጂ ማንም በጸሃፈው መጸሃፍ ክርስትናዬን አላስፈትሸውም ካላችሁም ደግ ነው።
ያው የፒውሪታንሶችን ስራዎችን በደንብ እንድታውቁ አደርጋችኋለሁ ብዬ ሰነፍሁ። ዲቮሽናል መጸሃፍት ሲጠማችሁ እንደኔ ሮጣችሁ ወደ ፒውሪታንሶች መሸሽ አሪፍ አማራጭ ነው። ለመንፈሳዊ ድርቀት የሚወሰዱ አሪፍ ክኒን አላቸው። ጀማሪ ክርስቲያኖች ባያነቡ ይመከራሉ። ትንሽ የሚያስደነግጥ ነገር ሳይኖራቸው አይቀርም።
