cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Khatima (ኻቲማ)

Advertising posts
301
Subscribers
No data24 hours
-27 days
+1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሱጁድ ላይ ልንረሳቸው የማይገቡ ዱአዎች ኢብን ባዝ (አሏህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ :- እነዚህን ሶስት ዱአዎች ሱጁድ ላይ እንዳትተው "الهم إني أسألك حسن الخاتمة" 1 "አላህ ሆይ መጨረሻዬን እንድታሳምርልኝእጠይቅሀለሁ " " الهم ارزقني توبة انصوحة قبل الموت" 2 አላህ ሆይ ከመሞቴ በፊት እውነተኛና ትክክለኛ ተውበትን ወፍቀኝ "الهم يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك 3  "አላህ ሆይ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ "
Show all...
ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር! ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡ የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ? የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡ የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡ “በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡ በርቱ! copy share
Show all...
~ ~ ከባዱ አደጋ ~ ~ ◍ ሸይኽ ፈውዛን እንድህ አሉ፦ 【አሁን በኡማው ላይ ከባዱ አደጋ ፣ የነዛ አላዋቂ መሃይም የሆኑ ሰዎች ጥሪ ነው ፣ ሰዎችን በአላዋቂነት ፣ በጥመት ጥሪ ያደርጋሉ።】 📚ኢዓነቱል ሙስተፊድ (1/337)            •┈┈•●◉❒ ✒ ❒◉●•┈┈• ◍ ሙሀመድ አማን አል ጃሚ እንድህ ይላሉ፦ 《 ቢዚህ ዘመን መቀላቀል ፣ መደባለቅ ፣ ተልቢስ ማድረግና ፣ ማጥመም ስለበዛ ፣ መማር ዒልምን መፈለግ በያንዳንዱ ሰው ላይ ግዴታ ነው።》 📚 ሸርሁል ዋሲጢያ (276) --
Show all...
ለጥንቃቄ‼️ ቴሌግራማቹን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ📵 ቴሌግራም ላይ ከማንኛውም ሰው በ cutt.ly ወይም bit.ly የሚጀምር ማንኛውም ሊንክ ተልኮላችሁ ስታገኙ እንዳትከፍቱት ምክንያቱም ሰሞኑን የመጣ ቫይረስ አለ ሙሉ ለሙሉ የተፃፃፋችሁትን እና Join ያደረጋችሁትን ቻናሎች ሁሉ ያጠፋውና እንደ አዲስ ነው አካውንት ክፈቱ የሚላቹ ይሔ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ነው ። 👉እንደዚህ ዓይነት ሊንኮች በምታውቋቸው ሰዎች ስም ጭምር ሊላክላችሁ ይችላል ነገር ግን በጭራሽ እንዳትከፍቱ። 👉በተጨማሪም ከሀከሮች አካውንታችሁን ለማዳን በምታስታውሱት Password Two-Step Verification On አድርጉ! Copy
Show all...
ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን? ~ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ:– "የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል። ከሶስት ሲቀር። ① ቀጣይነት ያለው ሶደቃ፣ ② ወይም ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣ ③ ወይ ደግሞ ዱዓ የሚያደርግለት ጥሩ ልጅ።" [ሙስሊም] የቱ ጋር አለህ? የቱ ጋር አለሽ? ① ከቻልን አጅሩ የማይቋረጥ ህዝብ የሚጠቅም ሶደቃ ጥለን እንለፍ። ② ወይ ደግሞ እውቀትን በማሰራጨት ላይ ድርሻ ይኑረን። (ይህም በሁለት መልኩ ሊሆን ይችላል። ተምሮ በማስተማር። ያወቁትን በማካፈል። ወይም የዑለማዎችን እውቀት በማሰራጨት።) ③ ወይ ደግሞ ልጆቻችንን በጥሩ ሁኔታ ኮትኩተን እናሳድግ። ከሁሉም አለመኖር ግን አሳዛኝ ብክነት ነው። ከነገ በፊት ዛሬ እንመልከት። ከነዚህ መስኮች ውስጥ የቱ ላይ አለን? = Copy ibnu munewor
Show all...
የትኛው ይበልጥ ይደንቅችዋል ? የረሱልን ደም ድፋ ተብሎ ደሙን ጭልጥ አርጎ የጠጣውን ሶሀባ ፍቅር? 🥺 ወይስ ሀቢቡና ለቀናት ሲለዩት ያማረ ገፅታው እና ሰውነቱ ከስቶ የጠበቃቸው ሶሀባ ፍቅር ? 😍 ነው ወይስ ሀቢቢ ከሞቱ በኋላ በህልማቸው አይቷቸው ከመጣ በኋላ አዛን ማውጣት ያቃተው ናፍቆት? 🥺🥰 አሊያም ደሞ እንደሞቱ ሲያረዱት ህልፈታቸውን በጉልበት ላለማመን ሰይፍ እመዛለሁ ያሉት ጥልቅ ፍቅር? በጦር አውድማ ከቤተሰቧ ህልፈት ባሻገር የነቢ መኖር ያስደሰታትስ ቢሆን ታሪኳ የወርቅ ብእር እንጂ ሌላ አያሻውም እንደው በመለክ እንጂ ሰው አይፅፈውም የተባለላት? ❤️ በአዛኙ ነብይ ላይ ሰላዋት እናውርድ ♥️♥️ አላሁመሰሊ ወሰሊም ዓላ ሃቢቢና ሙሐመድ ♥️ Copy
Show all...
ሞትክ ማለት እዛው በስብሰህ ቀረህ ማለት አይደለም!ይሄ የካፊር አስተሳሰብ ነው! ሞትክ ማለት ከስራህ ጋር ተገኘህ ማለት ነው!! እዚህ ዱንያ ላይ የሰራሃው ስራ ነው አኼራ ላይ ያንተን ማንነት የሚወስነው❗️❗️   ምን ላይ ነህ!? ማን ላይ ነሽ!? ራሳችንን እንፈትሽ! ሙስሊም ስለሆን ብቻ ጀነት የለም ወይም ስማችን የሚስሊም ስለሆነ ብቻ ጀነት አንደምገባ የምናስብ አለን እውነታው ግን እንደዛ አይደለም! ጀነት ማንም ሩጦ ሂዶ የሚገባበት የዱንያ ቤት አይደለም። እንዘጋጅ እንሽቀዳደም! ከወንጀል እንራቅ ወደ አላህ እንመለስ!   የሙሂ ማስታወሻዎች  
Show all...
አላህ ረመዷናችንን ይቀበለን
Show all...
Repost from N/a
በፊትና ዘመን ለአንድ ወጣት ከሐጅ ይልቅ ማግባት ይበልጣል ይላሉ አል-ኢማም አል-ቡኻሪይ። በርግጥ አቅሙ ለቻለ ሐጅ ዋጂብ'ኮ ነው። ግን ፊትና ካለና ከትዳር ውጭ መቋቋም የማይችለው ፊትና ከሆነ ማግባቱ የበለጠ ይወጅበበታል። الزواج للشباب في زمن الفتن، أوجب مـن الحج! إذا كان الرجل يحتاج إلى الزواج ، ويشق عليه تأخيره فإنه يقدم الزواج على الحج . أما إذا كان لا يحتاج إلى الزواج فإنه يقدم الحج . قال ابن قدامة رحمه الله في "المغني" (5/12) : وَإِنْ احْتَاجَ إلَى النِّكَاحِ , وَخَافَ عَلَى نَفْسِهِ الْعَنَتَ ( أي المشقة ) , قَدَّمَ التَّزْوِيجَ , لأَنَّهُ وَاجِبٌ عَلَيْهِ , وَلا غِنَى بِهِ عَنْهُ , فَهُوَ كَنَفَقَتِهِ , وَإِنْ لَمْ يَخَفْ , قَدَّمَ الْحَجَّ ; لأَنَّ النِّكَاحَ تَطَوُّعٌ , فَلا يُقَدَّمُ عَلَى الْحَجَّ الْوَاجِبِ اهـ . وانظر أيضاً : "المجموع" (7/71) للنووي . وسئل الشيخ ابن عثيمن رحمه الله : هل يجوز تأجيل الحج إلى ما بعد الزواج للمستطيع ، وذلك لما يقابل الشباب في هذا الزمن من المغريات والفتن صغيرة كانت أم كبيرة ؟ فأجاب : لا شك أن الزواج مع الشهوة والإلحاح أولى من الحج لأن الإنسان إذا كانت لديه شهوة ملحة فإن تزوجه حينئذٍ من ضروريات حياته ، فهو مثل الأكل والشرب ، ولهذا يجوز لمن احتاج إلى الزواج وليس عنده مال أن يدفع إليه من الزكاة ما يُزوج به ، كما يعطى الفقير ما يقتات به وما يلبسه ويستر به عورته من الزكاة . وعلى هذا فنقول : إنه إذا كان محتاجاً إلى النكاح فإنه يقدم النكاح على الحج لأن الله سبحانه وتعالى اشترط في وجوب الحج الاستطاعة فقال : ( وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنْ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلا ) آل عمران / 97 . أما من كان شاباً ولا يهمه أن يتزوج هذا العام أو الذي بعده فإنه يقدم الحج لأنه ليس في ضرورة إلى تقديم النكاح اهـ فتاوى منار الإسلام (2/375) .
Show all...
ሶላት የተወ ሰው የሚኖረውን ብይን (ሑክም) በተመለከተ ከጥንት ጀምሮ በዑለማእ መካከል የሃሳብ ልዩነት አለ። 1፦ ከፊሎቹ ከኢስላም ይወጣል ሲሉ 2፦ ሌሎቹ ደግሞ ወንጀለኛ ቢሆንም ከኢስላም አይወጣም ብለዋል። በሁለቱም አቋሞች በኩል ታላላቅ ዑለማኦች አሉ። አቅሙ ያለው ሰው መረጃዎቹን ፈትሾና አበጥሮ ከሁለቱ አቋሞች ውስጥ ሚዛን የሚደፋውን መውሰድ ይጠበቅበታል። ከዚህ አልፎ ጉዳዩን በሌላኛው በኩል ያሉትን ዓሊሞች በቢድዐ ለመወንጀል ማዋል ግን ተገቢ አይደለም። ይሁን እንጂ አንዳንዶች "ሶላት የተወ ሰው ከኢስላም አይወጣም" የሚሉ ዓሊሞችን በኢርጃእ ሲወነጅሉ ይታያሉ። ይሄ የተሳሳተ አካሄድ ነው። =ibnu munewor
Show all...