cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መዝሙር ዘምር ዘምር አለኝ

መንግስተ ሰማዐያት ቀርባለችና ንስሀ እንግባ

Show more
Advertising posts
1 941
Subscribers
-524 hours
-177 days
+9030 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
✞ የልቤን ሁሉ ✞ የልቤን ሁሉ ለማን ለማክር  እመቤቴ ሆይ ካንቺ በቀር  ለደካማ ሰው መጠጊያ እኮ ነሽ  ሀዘን ጭንቀቴን የምረሳብሽ  ቅዱሳን አበው አንቺን መረጡ ፪ ከሲኦል አለም ስላመለጡ  ጻዲቅ በስራው ያኔ ሲድን ፪ እጠራሻለው ድንግል አንቺን  አዝ ====== የጭንቄ ደራሽ አክሊሌ ነሽ ፪ ቂም በቀል አያውቅ የዋህ ልብሽ  ልቤ ለፍቅርሽ ሰፊ ስፍራ አለው ፪ በአዘንኩኝ ሰአት እጠራሻለው  አዝ ====== ዋሴ ነሽ ለኔ ድንግል እናቴ ፪ ስምሽ ጠበቀኝ ከልጅነቴ  ሁል ጊዜ ለኔ በጎ አረግሽልኝ  ምን ልበል ላንቺ ቃላታም የለኝ  አዝ ====== ላዘንኩኝ ለኔ ደስታዬ ነሽ ፪ ያረጋጋሽኝ ፈጥነሽ ደርሰሽ  ስምሽ ኃጥአንን የሚቀድስ፪ ከሞት ወደ ህይወት የሚመልስ  አዝ ====== የመንገዴ ስንቅ የረሀቤ መርሻ ፪ ለታመመ ሰው ነሽ መፈወሻ  ለተማጸነሽ በስምሽ አምኖ ፪ ማን አፍሮ ያውቃል አንቺን ለምኖ  
5796Loading...
02
በማህፀን ቅኔ በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ ዮሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/ የእናቱ ማህፀን የቅኔ ርስት ሆነች ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች በሃሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ አዝማች... በድንግል ማህፀን ስላየ ጌታውን ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን ትንቢቱ ሲፈፀም በሆዷ ሲነግስ ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንስ አዝማች... ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ ተፈጥሮ መች ቻለ ነብዩን ለማገድ አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና በእናቱ ማህፀን ድምጽን አሰማና አዝማች... የዮሐንስ እና ኤልሳቤጥ ገረማት ልጇ በማህፀን ቅኔ ሲቀኝባት ድምጿን ከፍ አደረገች አለም እንዲሰማ ሞላት መንፈስ ቅዱስ ለመዝሙር ለዜማ
5303Loading...
03
መዝሙር 108👏 "በቃለ ስብሀት" ዘማሪ አቤል መክብብ👏
5143Loading...
04
እዩና እመኑ ሰዎች እዩና እመኑ ሰዎች ድንጋዩ ተፈነቃቅሏል ኢየሱስ በኩለ ሌሊት በሀይሉ ሞትን ድል ነስቷል/2/ እልልታ ለዚህ ይገባል ግርግርታ ለዚህ ይገባል የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ ሲኦልም ተመሰቃቅሏል/2/ መላዕክቱ ነጭ ለብሰዉ ምስራቹን አበሰሩ ተነስቷል ኢየሱስ ብለው ለዓለም እዲናገሩ/2/ 👥@yemezmurgetemoche ✍ t.me/KIDAN_MEHRET_ENATEbot @EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
1 30813Loading...
05
✝️✝️✝️2አንችን ብቻ ቤተልሔም✝️✝️ ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ አንቺን ብቻ ቤተልሔም አንቺን ብቻ በዚያ ግርግም ዮሀንስነ በገሊላ በኤፍራታ አላየንም አንቺን ብቻ ቀራንዮ አንቺን በኮረብታ ዮሴፍንም አላየንም ሊጣስትራ ጎልጎታ አዝ... ገና በማለዳ በናዝሬቷ መቅደስ ገብርኤል በስራት ይዞ ከገሊላ ሲደርስ ያን ዜና ስሰሚ ደነገጥሽ በብርቱ አንቺ ብቻ ነበርሽ ብላቴናይቱ አዝ.... ሕፃኑን ስትወልጅ ግርግም የነበሩ የሉም በመከራው ቀራንዮን ፈሩ በልደቱ እንጂ የታሉ በሞቱ አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ አዝ... የግብፅ በረሀ አብረውሽ የወጡ በቀያፋ ግቢ እንደምን አልመጡ እርሱ ለሚገረፍ እነሱ እያፈሩ አንቺን ብቻ ትተው በመንደር ነበሩ አዝ.. ሐሙስ ዕለት ፋሲካን ሲበሉ ያመሹ አርብ ዕለት ተነሥተው ከቶ ወዴት ሸሹ ቃል ገብተው ነበር ላይክዱት መሀላ ድንግል ካንቺ በቀር ማን ነበር ሌላ አዝ... በሠላሳ ዘመን በሥጋ ወራቱ መች ነበሩ ከቶ ደቀመዛሙርቱ የእጆቹን ታምራት ቀን ከሌሊት እያየሽ በቃሉ በርታት ፊት አንቺ ነበርሽ አዝ... ቤተልሄም ያሉ ቀራንዮ የሉም ቀራንዮም ያሉ ግርግም አልነበሩም በሆነበት ዘመን በመስቀል ሞቱ አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ
1 0734Loading...
06
✞ሆሣዕና✞ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ሆሣዕና ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ህፃናቱ ሁሉ ድንጋዮች ሳይቀሩ ለዘመሩለት ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው ቅዱስ ነው መንፈሱ ሰላምን የሚሰብክ የሚናገር ፍቅርን በአህያ ውርንጫ መጥቷል ንጉሣችን አዝ= = = = = ዘንባባውን ይዘው ህፃን አዛውንቱ ልብሳቸውን ሳይቀር አንጥፈው በፊቱ ሆሳሣና ብለው ዘመሩ በእልልታ ግባ ንጉሣችን የሠራዊት ጌታ አዝ= = = = = ዘመንን ለሰጠን እንዘምርለት የምስጋናን መስዋዕት በፊቱ እንሰዋለት እንኳን እኛን ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል ከሚጠቡ አንደበት ምስጋናን ይወስዳል አዝ= = = = = መድሃኒት ለሰው ልጅ ስለተገለጠ የመርገም ጨርቃችን ስለተወጠ ሰላም በሰማያት ሆነ በምድር ክብርና ምስጋና ለእርሱ ለእግዚአብሔር አዝ= = = = = እኛ ለክርስቶስ እናስፈልጋለን ቅዱሳኑን ልኮ መፈታትን ይስጠን በትህትና ወድቀን በልባችን ይግባ እንደ ህፃናቱ እንያዝ ዘንባባ መዝሙር ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌል ፲፪፥፲፫ መዝ ፰፥፪
8402Loading...
07
#እርሱ_ነው_ቀን_የሚይወጣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ዛሬ ሞልቷል ምስጋናህ ተነሳ ልቤ ዘምር ለጌታ ለእግዚአብሔር 3 አዝ።።።።።።።።።።።።።። በገና ተነስ እንዚራ ማዳኑን እንድናወራ ብትቀርቡ ብትከተሉ ሁላችው ሆሳህና በሉ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።። እግዚአብሔር ዘመን ከሰጠ ይዘምር የተለወጠ እልልታ ይሁን ለስሙ ለዋጀን በወርቅ ደሙ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።። የክብሬ የቤቴ ጌታ የነፍሴ ባለውለታ ኤፉድ ነው በፍታ ነው ልብሴ ዘማሪ ነኝ ለንጉሴ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።። ሰገነት ላይ የወጣችው ዝምታን የመረጣችው ከአፋችው ወረት አይውጣ እሱ ነው ቀን የሚያወጣ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።
5525Loading...
08
🌿ሆሳዕና በአርያም🌿 🌿ለወልደ ዳዊት🌿 ሆሣዕና በአርያም የዳዊት ልጅ ገባ ኢየሩሳሌም(፪) ቤቱን ቢያደርጉበት የዓመጽ መደብር በጌትነት ገባ የሰው ልጅ በክብር(፪) አዝ= = = = = በአህያ ተቀምጦ ሲመጣ ቢያዩት ሕጻናት በአንድነት አመሰገኑት(፪) አዝ= = = = = ሊቃነ ካህናት በጣም ተቆጥተው ይማከሩ ጀመር ብለው እንስቀለው(፪) ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
4751Loading...
09
✞ሆሳዕና✞ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ሆሳዕና ብለን እናቅርብ ምስጋና ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለወልደ አምላክ - - - ሆሳዕና ትህትናን አሳየን - - - ሆሳዕና ስሙ ይባረክ - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለሰማይ ንጉስ - - - ሆሳዕና ግርማ ለብሶ መጣ - - - ሆሳዕና እኛን ሊቀድስ - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት - - - ሆሳዕና ነብያት በትንቢት - - - ሆሳዕና ለተናገሩለት - - - ሆሳዕና ሐዋርያት በወንጌል - - - ሆሳዕና ለሰበኩለት - - - ሆሳዕና አዝ= = = = = ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና ለአምላከ ምህረት - - - ሆሳዕና ተወልዶ ከድንግል - - - ሆሳዕና እንደ ህጻናት - - - ሆሳዕና እረኞች በዋሻ - - - ሆሳዕና የሰገዱለት - - - ሆሳዕና የአዳም ልጆች ሁሉ - - - ሆሳዕና ደግሞም መላእክት - - - ሆሳዕና ═•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ═
3982Loading...
10
✞የዘመን ፍፃሜ✞ የዘመን ፍፃሜ እስከዚህ የሌለህ ዘላለም የምትኖር (፫)ፍጹም አምላክነህ 🌿ሆሳዕና (፫) በአርያም🌿 ቡሩክ ሆሳዕና አምላከ እስራኤል ተቀምጦ መጣ (፫) በአህያ ግልገል አዝ= = = = = 🌿 ትንሹም ትልቁም በአንድነት ዘመሩ አመሰገኑት (፫) ሆሳዕና እያሉ 🌿 አዝ= = = = = በጣም ደስ ይበልሽ እልል በይጽዮን ንጉሥሽ መጣልሽ (፫) ሊሆንሽ መድኅን 🌿 🌿 ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
3611Loading...
11
✞ ምስጋናዬን ✞ ምስጋናዬን ላምላኬ አቀርባለው በማደሪያው ገብቼ ሠግድለታለው ኤልሻዳይ ነው ጌታ ሁሉን ቻይ ይፈፀማል አምናለሁ የልቤን ጉዳይ(2) ዘንባባዬን ይዤ እደህፃናቱ ሆሣና ልበለው ሠግጄ በፈቱ ምንም ባዶብሆን እውቀት ቢጎድለኝ ለሥሙ ልዘምር ከልካይም የለኝ(2)          አዝ= = = = = አምላኬ በፈትህ ቃል አለብኝ እኔ ቋንቋዬ መዝሙር ነው ያንተ እደመሆኔ ባሚናዳ ደጃፍ በቅድመ ታቦቱ ያየክብርህ ውደር ጠራኝ ማህሌቱ (2)          አዝ= = = = = የህይወት ትርጉሜ አንተነህ ደሥታዬ ስምህን ማገልገል ክብሬነው ሥራዬ ለታመነው ጌታ ምስክር የሆኑ ከብረው ተመለሱ ለበረከት ሆኑ(2)          አዝ= = = = = መነሻዬ አንተነህ ጉልበቴና ክብሬ መድረሻዬም አንተ መደምደሚያ ቅጥሬ በፂሆን ተራራ ስትገለጥ ያኔ ነጩን ልብሥ አልብሠህ አስነሳኸኝ ለቅኔ (2)                     መዝሙር በ    ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮   
4734Loading...
12
Media files
2940Loading...
13
✞ ሆሣዕና እምርት ✞ ሆሣዕና እምርት እንተ አቡነ ዳዊት(፪) ቡርክት እንተ ትመጽእ መንግስት(፬) ትርጉም:-የታወቀችይቱ የድኅነት ቀን የምትመጣይቱ የአባታችን የዳዊት መንግስት ቡርክት ናት ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
3441Loading...
14
#ብርና_ወርቅ_ሳይዙ ብርና ወርቅ ሳይዙ ዓለማትን ዞሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ቃሉን እየዘሩ ሙታን እያስነሡ ድውያን ፈወሱ ስሙን ብቻ ይዘው(፪)ታምነው በንጉሡ ከቀራጩ መደብ ከሐጥያት ገበታ ከጥብርያዶስ ባሕር ከጠራቸው ጌታ ስሙን ተሸክመው ቃሉን መሰከሩ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ድንቅን እየሠሩ #አዝ የነገስታቱን ቃል ዛቻውን ሳይፈሩ የመንግስቱን ወንጌል ለዓለም አስተማሩ ይሻለናል አሉ ማድላት ለእግዚአብሔር ለሰው ከመታዘዝ ዘላለም ለማይኖር #አዝ ቆዳቸው ተገፎ በሰይፍ ተሰየፉ ስለጌታ ፍቅር በመከራ አለፉ የድንጋዩን ናዳ የእሣቱን ነበልባል የጀርባን ግርፋት በእምነት ታግሰዋል #አዝ ስደት ነው መከራ ረሀብ ነው ወይስ ጥም ከክርስቶስ ወንጌል ከእውነት የሚያስቆም በእርሱ ስላመኑ በፅድቅ ተጋደሉ ደግሞም በእርሱ በላይ እንዳለ በቃሉ #አዝ በዙርያችን ከበው ካሉ እንደ ደመና እነርሱን እያሰብን በእምነት እንፅና በእውነት እንደኖሩ መሥለው ክርስቶስን እኛም በኑሮችን እንምሰል እነርሱን
3583Loading...
15
✞ መቼ ነው ጌታ ✞ መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደ ቃልህ የሚሆን ጉዞዬ አልተማርኩም አልል /አስተምረኸኛል/(፪) ቃልህን እንደ ወተት /አጠጥተኸኛል/(፪)        አዝ= = = = = የታለ አኗኗሬ /አንተን የሚመስለው/(፪) በልማድ ሕይወት ነው /የምመላለሰው/(፪)         አዝ= = = = = ይህ አንደበቴማ /በቃልህ ሰልጥኗል/(፪) ልቦናዬ ከአንተ /ከፊትህ ኮብልሏል/(፪)        አዝ= = = = = አንተን እንደማውቅህ /አብዝቼ ባወራ/(፪) የተዘራው ሁሉ /ፍሬም አላፈራ/(፪)        አዝ= = = = = እዘንልኝና/መንገዴን አቅናልኝ/(፪) የአመጽ ሥራዬን /በደሌን ተውልኝ/(፪)         አዝ= = = = = ቃልህ እንዳይሰደብ /በእኔ ድካም/(፪) አርመው እርሻህን/መድኃኔዓለም/(፪)         አዝ= = = = = ከእስራቴ ፈተህ/ነጻነት ስጠኝ/(፪) በቀኝህ አቁመህ/ጌታ ሆይ ባርከኝ/(፪)         አዝ= = = = = ኃጢአት በዝቶ በእኔ /እንዳያጠፋኝ/(፪) የብርሃን ፊትህ /ይገለጽልኝ/(፪)   ዘማሪት| ፋንቱ ወልዴ "አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ ከፊትህ አትጣለኝ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ"            መዝ፶፥፲-፲፩
2613Loading...
16
✞ አድዋ ኢትዮጵያ ✞ ጌታችን ሆይ ቀኝህ ኃይልህ ተከበረ አድዋ ኢትዮጵያ ላይ ጠላትን ሰበረ አምላከ ጊዮርጊስ ጠላትን ሰበረ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ነዓ በፈረስ ኃያል በጉልበቱ ሲታበይ ሲመካ የእግዚአብሔር ፍትሕ አድዋ ላይ ፈካ ረድኤት እግዚአብሔር በጊዮርጊስ ዘልዳ ለኢትዮጵያ ንጋት ለአፍሪካ ማለዳ          /አዝ = = = = = የንጹህ ምንጭ ውኃ ትውፊት ሐዋርያ የእግዚአብሔር እጅ ቅርበት ለኢትዮጵያ ታቦተ ጊዮርጊስ የአምላክ ቃልኪዳን ለወራሪ መቅሰፍት ለሀገራችን መድኀን          /አዝ = = = = = ሃይማኖት እንደ ድር በአንድ አስተሳሰረ ኢትዮጵያዊነትን በአንድ ልብ መከረ ቀጸላ መንግሥቱን ማርያምን ብሎ ምኒልክ ዘመረ አማሌቅን ጥሎ          /አዝ = = = = = የታመነውን ሕዝብ እርሱን የሚመራ ሊያከብረው ይዋጋል ከጠላቱ ጋራ የፈርኦንን ስጥመት በዓድዋ ሲደግም አምላከ ጊዮርጊስ ድንቅ እውነት ለዓለም          /አዝ = = = = = አንችን የሚጠሉ ይፈሩ ይሳቀቁ እጁን በአንቺ ዐይተው ከእግርሽ ሥር ይውደቁ የነፃነት ፊደል የክብር መማሪያ የእውነት መጽሐፍ ነሽ ቅድስት ኢትዮጵያ ዘማሪ ዲ/ን ልዑል ሰገድ ጌታቸው
2841Loading...
17
ፍቅርህ ማረከኝ ✞ ፍቅርህ ማረከኝ በህይወቴ በዘመኔ/2/ እግዚአብሔር ለኔ መድኃኒቴ ፍቅርህ  ማረከኝ በህይወ ቴ በዘመኔ ተገዝቻለው በወርቅ ደምህ አለምን ትቼ ላገለግልህ ሞትህ ህይወቴ ለኔ ሆኖኛል ባንተ መከራ ሸክሜ ርቋል በክብር ቆሜ እዘምራለሁ እንደ አቅሜ አገንሀለሁ          /አዝ===== ምድርና ሰማይ እልል ይበሉ ምስጋና ላንተ ይድረስ እያሉ መሳይ የለህም ለቅድስና አቀርባለሁኝ ላንተ ምስጋና ጣቴ በገናን ይደረድራል   በቀን በሌሊት ያመሰግናል          /አዝ===== ክብርህን አይተው ጠላቶች ፈሩ በጌትነትህ ወድቀው ተገዙ  እንዲህ ነህ አምላክ እንዲህ ነህ ጌታ ሁሉን በፍቅር የምትረታ በአንተ ተመካነን በፈጣሪያችን አዳኝ በሆንከው በንጉሳችነን
3827Loading...
18
🌹ያችን ቀን እናፍቃለሁ🌹 ያችን ቀን እናፍቃለሁ አይቀርም ይሳካል ህልሜ ምስክር እሆነዋለሁ በአውደ ምረቱ ቆሜ ደግሞም ባይሆንልኝ ያሰብኩት በቀኑ ለኔ አስቦልኝ ነው አባት በመሆኑ ድንጋይ ዳቦ መስሎኝ ለማኘክ ስሞክር ጌታ ከለከለኝ ጥርሴ እንዳይሰበር አዝ... ስላደረክልኝ ስለ ፀሌቴ መልስ ተመስገን አምላኬ ስምህም ይቀደስ ያልተቀበልኩትም ያልሆነ በህይወቴ ለበጎ ነውና ተመስገን አባቴ አዝ...... እድል ፋንታየ ነህ ተስፋ አደርግሀለው የማዳንህን ቀን እጠባበቃለሁ አንተን ለናፈቀች ለተጨነቀች ነፍስ ትደርስላታለህ እንባዋን ልታብስ አዝ...... ወንድሞቸ ጠልተው ቢሸጡኝ ባንድነት በፊድፍራ ጎጆ ብኖር በባርነት በሀሰት ወንጅላ በወህኒ ባድር ለኔ መሰላል ነው መውጫ ወደ ክብር አዝ..... ልጁ ዳቦ ሲለው ድንጋይ የሚሰጠው ከሰው ልጆች መሀል ከቶስ እርሱ ማነው መልካም ካደረገ የምድራዊይዩ አባት ከዚህም ይሰፋል ያንተ መልካምነት
3425Loading...
19
\\\\\ \\\\አንተ ቢቻ ንጉስ/// አንተ ቢቻ ንጉስ አንተ ቢቻ ዳኛ (2) ተመስገን ኢየሱስ የነብሴ መጽናኛ አዝ ሰለ ፍቅር ሁሌ ባነባ ላፈስልህ የቅኔ መባ ላንተ ቅኔ አይሁንም ካሳ እስከ ሽበት ስምክን ባነሳ ላንተ ቅኔ አይሁንም ካሳ እስከ እድሜ ልኬ ስምክን ባነሳ አዝ ያሰተማረከኝ የውዴን ፊደል የተከልከው የልቤን ወደል እያነቃኝ አመልክሃለሁ ካንተ ወዲያ ማንን አውቃለሁ (2) አዝ ሰውነቴ እጅ እንዲጸዳ ህሊናዬን አንተ እንዲረዳ ተጸየፈ የሰውን መረኩዝ ስታበራ አበራ የልቤ መቅረዝ(2) አዝ ከእንቅብ በታች መቼ ተነሳሁ በተራራ ሁሌም አጠናሁ መገዛቴ ለፍቅር ቀንበር ሰው አረገኝ አንስቶ ከአፈር
2674Loading...
20
✞ ቤተክርስቲያን አንተውም ከቶ ✞ ቤተክርስቲያን አንተውም ከቶ የሰጠን አምላክ በደሙ መስርቶ የሰጠን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ የአምላካችን ቤት አንተውም ከቶ ሁሉንም በሁሉም ለሚሞላው ጌታ ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ በክብር በሞገስ በፀጋ ተሞልታ ደምቃ ትኖራለች በዓለም አብርታ(፪)      አዝ= = = = = ዳቢሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ ወጥመድ ቢዘረጋ በጉዟችን ሁሉ እንሻገራለን የአምላክ ስም ጠርተን አንዳች አይነካም እሱን ተጠግተን(፪)      አዝ= = = = = በስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት ስለስሙ መኖር በስሙ መሞትን ጠላት ዳቢሎስን ምን ባያስደስት ይህ ነው ክርስትና ይሄነው ህይወት(፪)      አዝ= = = = = ከትውልድ ለትውልድ የምናስረክበው ለልጅ ልጅ አውርሰን ደስ የምንሰኘው አይደለም ብርናወርቅ አይደለም ሌላ ሀብት ሐይማኖታችን ነው የኛ እርስት ጉልት(፪)        
2053Loading...
21
✞በገና አንስተን✞ በገና አንስተን መሰንቆን እናመስግነው ስምህን /እንደ አንተ ጌታ ማንም የለም ክበር ተመስገን ለዘላለም/(፪)       ዓለም ሞኝነት ይመስለዋል ለአንተ መንበርከክ ይከብደዋል /ፍቅርህን ቀምሰን ዝም አንልም እንዘምራለን ለዘላለም/(፪)   አዝ= = = = = ፈውስን ስትሰጠን ስትባርከን ፍቅርህን ልከህ ስትጎበኘን /ጉልበት ይፀናል በአንተ ጸጋ ማን ነው ሚከፍለው የአንተን ዋጋ/(፪) አዝ= = = = = ስንዘምርልህ የሚስቁ ብዙ ሜልኮሎች ዛሬም አሉ /ከኛ የሆነ ምንም የለም አምላክ ስለአንተ ዝም አንልም/(፪) አዝ= = = = = ሞኝነት ለኔ መች ሆነና ፊትህ ያቆመኝ ለምስጋና /እንድቀኝልህ ግድ የሚለኝ ፍቅርህ ብቻ ነውየማርከኝ/(፪)
2060Loading...
22
https://t.me/fkremarekegn
1990Loading...
23
✞ ​​የሲሎንዲስ ጥበብ የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ የናሆም መድሐኒት እወድሻለሁ ማርያም አከብርሻለሁ ማርያም እወድሻለሁ/፪/ አዝ____ ተጨንቄአለሁ ልንገርሽ ምሥጥረኛዬ እናቴ ነሽ ሠው የአልሠማውን ብርቱ ምሥጢር ድንግል ሆይ ለአንቺ ለአማክር ለቁሥለኛውም መድሐኒቱ ለአዳም ዘር ሁሉ ነሽ ሕይወቱ መፍትሔ አለ በእጅሽ ተንበርክኬ ልማጸንሽ አዝ____ ሳልናገረው ይገባሻል የውሥጤ ሁሉ ይታይሻል ድርሽ እናቴ ተረጅኝ ያለ አንቺ ለእኔ ማን አለኝ ደሥታዬ ደሥታ የሚሆነው በሐዘኔም የምጽናናው አንቺ ከእኔ ጋር ስለ ሆንሽ ተጽናንቻለሁ በሥምሽ አዝ____ ወንድሞቼ እንኳን ቢሸጡኝ ሠው ሁሉ ጠላት ቢሆነኝ በእመ አምላክ ሐይል ከብሬአለሁ በጠላት ላይ ሠልጥኛለሁ የረሱኝ ሁሉ የአስቡኛል የተጣሉኝም የአከብሩኛል አንቺ አንግሠሽኝ አልወድቅም እቆማለሁኝ ዘለዓለም አዝ____ መንገዴ ረዝሞ ደክሜብሽ መከራው በዝቶ ታምሜብሽ ወድቄ ሳዝን ድረሽልኝ ለባርያሽ ሐይሉን እንድትሠጪኝ ፍቅርሽ በውስጤ ተንሠራፋ በእናትነትሽ ልቤ ሠፋ የሚለያየን ማንም የለም ማርያም ልበልሽ ለዘለዓለም                   መዝሙር            ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
2093Loading...
24
Media files
1870Loading...
25
Media files
1950Loading...
26
✞ ቅዱስ ላሊበላ ✞ ቅዱስ ላሊበላ ላሊበላ ቅዱስ ላሊበላ ላሊበላ ዕፁብ ነው ድንቅ ነው የሠራው ምሳሌም የለው [፪]        አዝ ====== ዘውትር ብመላለስ................ላሊበላ ዐይኔም አይጠግበው...........ላሊበላ የሠው ስራ አይደለም............ላሊበላ የሥላሴ ነው........................ላሊበላ        አዝ ====== በማህጸን ሳለ.................ላሊበላ ስለተመረጠ...................ላሊበላ ቤተ-መቅደስ ሠራ...........ላሊበላ ድንጋዩ ያጌጠ................ላሊበላ        አዝ ====== የአሰራሩ ዘይቤ............ላሊበላ ከላይ ወደ ታች.............ላሊበላ ስነ ሕንጻው ሲታይ.........ላሊበላ የማይሰለች.................ላሊበላ ላዩ አረንጓዴ ነው...........ላሊበላ ውስጠኛው ባሕር.........ላሊበላ ጸበሉ የፈለቀው............ላሊበላ ከቋጥኙ ስር................ላሊበላ        አዝ ====== በዕምነት የመጡ..............ላሊበላ ከቤተ ጊዮርጊስ................ላሊበላ አንቀላፉ  በዚያው.............ላሊበላ ምፅአት እስኪደርስ............ላሊበላ ማርኳቸዋልና....................ላሊበላ የእግዚአብሔር ቅዱስ.........ላሊበላ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇    
1750Loading...
27
✞ፀጋህ ይብዛልኝ✞ ፀጋህ ይብዛልኝ ምህረትህ አይራቀኝ አማኑኤል ሆይ ስራ ደነቀኝ ተመስገን ልበል ላቅርብ ምስጋና 2 በአንተ ቸርነት ቆሚያለሁ እና 2 ፀጋህ በዝቶልኝ እዘምርልሃለሁ በምስጋና ላይ ምስጋና አበዛለሁ አለኝ ሺ ቃላት አለኝ ብዙ ቋንቋ አንተን መግለጫ ለዓለም የሚበቃ አዝ የተናገርከው የአሰብክልኝ ሆነ የልቤም መሻት ይህንን ነበረ አስተካከልከኝ ከኃያላን ጋራ አማኑኤል ሆይ እፁብ የአንተ ስራ አዝ በለምለሙ መስክ አሳድገህኛል ያን የጭንቁን ቀን አሳልፈህኛል የምስጋና እርሻ ሆነልኝ ደጃፌ አባት ሆይ ስልህ ማርማር አለው አፌ አዝ በአዝን ብደሰት ብወድቅም ብነሳ እስከ አሁን አለሁ ከአንተ የተነሳ መረቤን ጥዬ ተስፋ አደርግሃለሁ እንደ ምትሞላው እተማመናለሁ
1921Loading...
28
Media files
2290Loading...
29
Media files
2010Loading...
30
Media files
2271Loading...
31
Media files
2200Loading...
32
Media files
2200Loading...
33
Media files
4580Loading...
34
Media files
5000Loading...
35
✝️ናታኒም ነኝ✝️ ናታኒም ነኝ በአገልግሎቴ አይከፋኝም ታናሽነቴ እጠርጋለሁ ደጅህን ጌታ ዝቅ ብዬ ለአንተ ውለታ ከነገደ ሌዊ ባልሆንም ባልሾምም እንደ አሮን የዜማ እቃ ባልይዝ በገና ላመስግንህ በትህትና እደጅ ሆኜ ከአንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር ቆጥረህልኝ እንደ ዋጋ አከበርከኝ በአንተ ፀጋ     አዝ===== ከእረኝነከ እረኝነችት ከታናሽ ስፍራ ለንግስና ምንም ብጠራ ከቀንዲሉ ቀርቧል ኀሳቤ ልቀኝልህ ተነጥፎ ልቤ እደጅ ሆኜ ከአንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር ቆጥረህልኝ እንደ ዋጋ አከበርከኝ በአንተ ፀጋ     አዝ===== ሳይከብድብኝ የዓለም ዝና ተንበርክኬ ልስጥህ ምስጋና ምክንያት አለኝ ለማዘንበሌ ናታኒም ነኝ ይህች ናት ቃሌ እደጅ ሆኜ ከአንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር ቆጥረህልኝ እንደ ዋጋ አከበርከኝ በአንተ ፀጋ     አዝ===== እንኳን ልቆም በፍታን ለብሼ አፍርሀለው እኔ አጎንብሼ የትምክኅት ካባዬን ጥዬ ከመቅደስህ ልግባ ጌታዬ እደጅ ሆኜ ከአንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር ቆጥረህልኝ እንደ ዋጋ አከበርከኝ በአንተ ፀጋ | በዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻድቅ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
4682Loading...
36
❤️ #ኦ_እንዳንተ_ያለ ======//======= ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይሞላል አይኔ ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለኔ ወዳጅ እና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ ምን አለኝ እና ልስጥህ የሚነገር ሚወራ እኔስ ተሸንፌያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ ተሰድጄ ብወጣ ወተሀል ከእኔ ጋር ትላንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ ወጥመዴን ስበር እና አፌን ሙለው በእልልታ በስረኞች መሀል ሆኜ ሰንሰለት ለብሻለው አለም እውነት የላትም ፍትህ ከአንተ እሻለው መቼ ታፅናናኛለህ ወዳጅ እና ዘመዴ አውጣኝ(*2)ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ ደክመህ አልፈህልኛል እጆቼን አበርትተህ ሁሌ በሬ ላይ ቆመህ ደጃፌን የምትመታ ግባ የክብር ንጉስ ብያለው ማራናታ/5/
1691Loading...
37
Media files
4970Loading...
38
#ሆረ_ኢየሱስ ሆረ ኢየሱስ (2) እምገሊላ ሀበ ዮርዳኖስ ሄደ ኢየሱስ (2) ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ አዝ...................... ኢየሱስ ሊጠመቅ መጣ ከገሊላ ዮርዳኖስም ሸሸ ሄደ ወደሃላ ተፈወሰ (3) ያዳም ልጅ በመላ እም ገሊላ (3) ሀበ ዮርዳኖስ አዝ............................ አብም መሰከረ ተገልጦ ነገረ የባህሪ አምላክ እግዚአብሄር ነው አለ መንፈስ ቅዱስ በርግብ ተገልጦ ሲበር መሰከሰ (3) የወልድን ክብር አዝ........................... የእዳ ደብዳቤው አለ ዮርዳኖስ ፅፈቱ ተሻረ ተጠምቆ ኢየሱስ ተሰረዘ (3) የአዳም ልጅ ክስ አዝ.................................. ሚስጥረ ስላሴ ታየ በገሀድ በባሪያው ሲጠመቅ እግዚአብሄር ወልድ ተይዞልን (3) በፍቅር ገመድ @mezmure1
1560Loading...
39
#ጥምቀተ_ባሕር ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ /2ጊዜ/ ሀሌ ሉያ /4ጊዜ/ ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች አልችለውም ብላ ወደ ፊት ሸሸች ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ ዮርዳኖስም ሸሸ ቀረ ወደ ኋላ #አዝ - - - - - አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና #አዝ - - - - - - ጌታችን ሲጠመቅ በ30 ዓመት ባሕር ኮበለለች ግዑዟ መሬት ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ ከሩቅ መቷልና አብ ታላቁ እንግዳ #አዝ - - - - - - - እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ የፃድቃን መሰላል ድህነታችን ለእኛ ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇               •➢ ሼር // SHARE  @mezmure1
1590Loading...
40
#በእደ_ዮሐንስ_ተጠምቀ በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ (2) ሰማያዊ [5] እየሱስ ናዝራዊ እኽ ሰማያዊ [5] ኢየሱስ ናዝራዊ #አዝ.... አዳም ያጠፋውን ልጅነት ሊያስመልስ በሰላሳ ዘመን ተጠመቀ ኢየሱስ እረሱ አምላክ ሲሆን ፈጥሮ የሚገዛ ወርደ ወደ ምድረ እንዲሆነን ቤዛ እኽ  ሰማያዊ [5] ኢየሱስ ናዝራዊ #አዝ..... ሊያጠፋው አቅልጦ እንደ አምላክነቱ ረግጦ ሊሰረዝ እንደሰውነቱ የፍጥረቱ ጌታ በዮረዲያኖስ ቆሟል የእዳውን ፅፍት በስልጣኑ ሽሯል እኽ ሰማያዊ [5] ኢየሱስ ናዝራዊ #አዝ.... የአድነት ሶስትነት ተገልጧል ሚስጥሩ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ መምህሩ አብም በደመና ለልጁ መስክሯል በሃምሳለ ርግብ መንፍስ ቅዱስ ወረዷል እኽ ሰማያዊ [5] ኢየሱስ ናዝራዊ #አዝ..... ሲነገር እንዲኖር የረሱ ትህትና ለዓለም እንዲገለጥ የባሪያው ልዕልና ተጠማቂው ሔደ ወደ አጥማቂው አምላክ የሰራልን ስረዓቱ ይህ ነው በእደ ዮሐንስ  ተጠምቀ እየሱስ ናዝራዊ  [2] ሰማያዊ  [5 ] ኢየሱስ ናዝራዊ      ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇              
1660Loading...
✞ የልቤን ሁሉ ✞ የልቤን ሁሉ ለማን ለማክር  እመቤቴ ሆይ ካንቺ በቀር  ለደካማ ሰው መጠጊያ እኮ ነሽ  ሀዘን ጭንቀቴን የምረሳብሽ  ቅዱሳን አበው አንቺን መረጡ ፪ ከሲኦል አለም ስላመለጡ  ጻዲቅ በስራው ያኔ ሲድን ፪ እጠራሻለው ድንግል አንቺን  አዝ ====== የጭንቄ ደራሽ አክሊሌ ነሽ ፪ ቂም በቀል አያውቅ የዋህ ልብሽ  ልቤ ለፍቅርሽ ሰፊ ስፍራ አለው ፪ በአዘንኩኝ ሰአት እጠራሻለው  አዝ ====== ዋሴ ነሽ ለኔ ድንግል እናቴ ፪ ስምሽ ጠበቀኝ ከልጅነቴ  ሁል ጊዜ ለኔ በጎ አረግሽልኝ  ምን ልበል ላንቺ ቃላታም የለኝ  አዝ ====== ላዘንኩኝ ለኔ ደስታዬ ነሽ ፪ ያረጋጋሽኝ ፈጥነሽ ደርሰሽ  ስምሽ ኃጥአንን የሚቀድስ፪ ከሞት ወደ ህይወት የሚመልስ  አዝ ====== የመንገዴ ስንቅ የረሀቤ መርሻ ፪ ለታመመ ሰው ነሽ መፈወሻ  ለተማጸነሽ በስምሽ አምኖ ፪ ማን አፍሮ ያውቃል አንቺን ለምኖ  
Show all...
5👏 1
በማህፀን ቅኔ በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ ዮሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/ የእናቱ ማህፀን የቅኔ ርስት ሆነች ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች በሃሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ አዝማች... በድንግል ማህፀን ስላየ ጌታውን ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን ትንቢቱ ሲፈፀም በሆዷ ሲነግስ ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንስ አዝማች... ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ ተፈጥሮ መች ቻለ ነብዩን ለማገድ አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና በእናቱ ማህፀን ድምጽን አሰማና አዝማች... የዮሐንስ እና ኤልሳቤጥ ገረማት ልጇ በማህፀን ቅኔ ሲቀኝባት ድምጿን ከፍ አደረገች አለም እንዲሰማ ሞላት መንፈስ ቅዱስ ለመዝሙር ለዜማ
Show all...
👍 1
መዝሙር 108👏 "በቃለ ስብሀት" ዘማሪ አቤል መክብብ👏
Show all...
👍 1 1
እዩና እመኑ ሰዎች እዩና እመኑ ሰዎች ድንጋዩ ተፈነቃቅሏል ኢየሱስ በኩለ ሌሊት በሀይሉ ሞትን ድል ነስቷል/2/ እልልታ ለዚህ ይገባል ግርግርታ ለዚህ ይገባል የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ ሲኦልም ተመሰቃቅሏል/2/ መላዕክቱ ነጭ ለብሰዉ ምስራቹን አበሰሩ ተነስቷል ኢየሱስ ብለው ለዓለም እዲናገሩ/2/ 👥@yemezmurgetemochet.me/KIDAN_MEHRET_ENATEbot @EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
Show all...
8👏 1
✝️✝️✝️2አንችን ብቻ ቤተልሔም✝️✝️ ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ አንቺን ብቻ ቤተልሔም አንቺን ብቻ በዚያ ግርግም ዮሀንስነ በገሊላ በኤፍራታ አላየንም አንቺን ብቻ ቀራንዮ አንቺን በኮረብታ ዮሴፍንም አላየንም ሊጣስትራ ጎልጎታ አዝ... ገና በማለዳ በናዝሬቷ መቅደስ ገብርኤል በስራት ይዞ ከገሊላ ሲደርስ ያን ዜና ስሰሚ ደነገጥሽ በብርቱ አንቺ ብቻ ነበርሽ ብላቴናይቱ አዝ.... ሕፃኑን ስትወልጅ ግርግም የነበሩ የሉም በመከራው ቀራንዮን ፈሩ በልደቱ እንጂ የታሉ በሞቱ አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ አዝ... የግብፅ በረሀ አብረውሽ የወጡ በቀያፋ ግቢ እንደምን አልመጡ እርሱ ለሚገረፍ እነሱ እያፈሩ አንቺን ብቻ ትተው በመንደር ነበሩ አዝ.. ሐሙስ ዕለት ፋሲካን ሲበሉ ያመሹ አርብ ዕለት ተነሥተው ከቶ ወዴት ሸሹ ቃል ገብተው ነበር ላይክዱት መሀላ ድንግል ካንቺ በቀር ማን ነበር ሌላ አዝ... በሠላሳ ዘመን በሥጋ ወራቱ መች ነበሩ ከቶ ደቀመዛሙርቱ የእጆቹን ታምራት ቀን ከሌሊት እያየሽ በቃሉ በርታት ፊት አንቺ ነበርሽ አዝ... ቤተልሄም ያሉ ቀራንዮ የሉም ቀራንዮም ያሉ ግርግም አልነበሩም በሆነበት ዘመን በመስቀል ሞቱ አብረሹ ነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ
Show all...
👍 4
✞ሆሣዕና✞ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ሆሣዕና ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ህፃናቱ ሁሉ ድንጋዮች ሳይቀሩ ለዘመሩለት ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው ቅዱስ ነው መንፈሱ ሰላምን የሚሰብክ የሚናገር ፍቅርን በአህያ ውርንጫ መጥቷል ንጉሣችን አዝ= = = = = ዘንባባውን ይዘው ህፃን አዛውንቱ ልብሳቸውን ሳይቀር አንጥፈው በፊቱ ሆሳሣና ብለው ዘመሩ በእልልታ ግባ ንጉሣችን የሠራዊት ጌታ አዝ= = = = = ዘመንን ለሰጠን እንዘምርለት የምስጋናን መስዋዕት በፊቱ እንሰዋለት እንኳን እኛን ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል ከሚጠቡ አንደበት ምስጋናን ይወስዳል አዝ= = = = = መድሃኒት ለሰው ልጅ ስለተገለጠ የመርገም ጨርቃችን ስለተወጠ ሰላም በሰማያት ሆነ በምድር ክብርና ምስጋና ለእርሱ ለእግዚአብሔር አዝ= = = = = እኛ ለክርስቶስ እናስፈልጋለን ቅዱሳኑን ልኮ መፈታትን ይስጠን በትህትና ወድቀን በልባችን ይግባ እንደ ህፃናቱ እንያዝ ዘንባባ መዝሙር ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ የዮሐንስ ወንጌል ፲፪፥፲፫ መዝ ፰፥፪
Show all...
#እርሱ_ነው_ቀን_የሚይወጣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ዛሬ ሞልቷል ምስጋናህ ተነሳ ልቤ ዘምር ለጌታ ለእግዚአብሔር 3 አዝ።።።።።።።።።።።።።። በገና ተነስ እንዚራ ማዳኑን እንድናወራ ብትቀርቡ ብትከተሉ ሁላችው ሆሳህና በሉ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።። እግዚአብሔር ዘመን ከሰጠ ይዘምር የተለወጠ እልልታ ይሁን ለስሙ ለዋጀን በወርቅ ደሙ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።። የክብሬ የቤቴ ጌታ የነፍሴ ባለውለታ ኤፉድ ነው በፍታ ነው ልብሴ ዘማሪ ነኝ ለንጉሴ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።።። ሰገነት ላይ የወጣችው ዝምታን የመረጣችው ከአፋችው ወረት አይውጣ እሱ ነው ቀን የሚያወጣ 2 አዝ።።።።።።።።።።።።።።።
Show all...
1