en
Feedback
የሀዋሳ ታቦር ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን (Hawassa Tabour 7th day Adventist INternational Church

የሀዋሳ ታቦር ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን (Hawassa Tabour 7th day Adventist INternational Church

Open in Telegram

እግዚአብሄርን ለመገናኘት ተዘጋጅ

Show more
1 069
Subscribers
+524 hours
+157 days
+4530 days
Posts Archive
The Seventh-day Adventist Church has passed 24 million members worldwide, according to the advance release of the 2026 Annual Statistical Report from the General Conference. Africa accounted for more than 81% of the church’s net membership growth in 2025. The new figures come as Adventists worldwide launch OneVoice27, a global evangelistic initiative focused on digital and personal outreach. 🔗Read more: https://spectrummagazine.org/current-share/adventist-membership-passes-24-million-as-onevoice27-launches #AdventistNews #Membership #OneVoice27

ሰላም ሰላም! ይህ ከሀዋሳ መናኸሪያ አጥቢያ ቤ/ክ የተላለፈ መልዕክት ነው:: ------ እንደምን ሰነበታችሁ ወገኖች! እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ከጳጉሜ 01/2018 እስከ መስከረም 02/2019
ሰላም ሰላም! ይህ ከሀዋሳ መናኸሪያ አጥቢያ ቤ/ክ የተላለፈ መልዕክት ነው:: ------ እንደምን ሰነበታችሁ ወገኖች! እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ከጳጉሜ 01/2018 እስከ መስከረም 02/2019 ዓ.ም የሚካሄደውን የቤተሰብ ሥልጠና መከታተል የምንፈልጉ ወገኖች በሙሉ: ቅደመ ሁኔታዎችን ለማሟላትና በመጨረሻው ቀን ለተሳታፊ ባለትዳሮች የሚሰጠውን ሰርትፊኬት ለማዘጋጀት እንዲረዳን ስማችሁን ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ወንጌላዊያን ወይንም ሽማግሌዎች በመስጠት ወይም ከሥር በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር እየደወላችሁ እንድታስመዘግቡ እያሳሰብን፤ እነዚሁ ጥንዶች ከመጀመሪያው የማክሰኞ ምሽት የቤተሰብ ትምህርት አንስቶ እስከ ሰንበት ጠዋት የጋብቻ ተሀድሶ ድረስ ትምህርቶቹን ያለ ማቋረጥ እንዲከታተሉ የሚጠበቅ ሲሆን ይህንን ላደረጉ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን እና ኢትዮ ባርናባስ የወንጌል አገልግሎት ያዘጋጁት የምስክር ወረቀት በሰንበት ቀን ዋናው አገልግሎት ላይ የሚሰጥ ይሆናል። ማሳሰቢያ: ከሐሙሱ የባለ ትዳሮች ስልጠና በስተቀር ሁላችንም በሁሉም መንፈሳዊ ፕሮግራሞች የተጋበዝን ስለሆነ ተገኝተን ሌሎችንም እንጋብዝ ጌታ ይባርካችሁ! 0916836762

ቀን ነሀሴ 23,2018:ሀዋሳ ማስታወቂያ! የኢሌደር ጴጥሮስ ጎዴቦ ባለቤት ወ/ሮ አበባይቱ ጊቻሞ እናታቸውን ቀብረው የመጡ መሆኑን ተከትሎ ቤተክርስቲያናችን የማፅናኛ ፕሮግራም ዛሬ ከሰዓት ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በመኖሪያ ቤታቸው አዘጋጅታለች። በመሆኑም ቤተክርስቲያናችን ለእህታችንና ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እየተመኘች ምዕመንም በፕሮግራሙ በመገኘት እንድታፅናኑ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን! ተባረኩ አድራሻ- ከሚሽን መካነ መቃብር በኩል ከመጡ የአድቬንቲስት 2ኛ ደረጃ ት/ ቤትን(High School) እንደጨረሱ ባለው ወደ ግራ በሚያስገባው መግቢያ ሲገቡ ከፈርኒችር ቤቱ ቀጠወሎ(ጀርባ)ያለው ግቢ::

ከደቡብ ግሪን ኢት/ ሰበካ የጎዳና ፈላጊ ክለብ በሐዋሳ ካምፖሬ ጉዞ መልስ በአንድ አገልጋይ ላይ ከአቅም በላይ የሆነ አደጋ ደርሶበት ሐዋሳ ያኔት ሆስፒታል የራስ ቅል ቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለት በ
+1
ከደቡብ ግሪን ኢት/ ሰበካ የጎዳና ፈላጊ ክለብ በሐዋሳ ካምፖሬ ጉዞ መልስ  በአንድ አገልጋይ ላይ ከአቅም በላይ የሆነ አደጋ ደርሶበት ሐዋሳ ያኔት ሆስፒታል የራስ ቅል ቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለት በአሳሳቢ ሆኔታ ላይ (@Hawassa referral hospital) ስላለ እባካችሁ እንጸልይለት የበኩላችንንም ድጋፍ እናድርግለት:: የጎዳና ፈላጊው ስም ሺበሺ ደምሴ ሲሆን ፀልዩለት እንደግፍ :: አከዉንት ቁጥር 1000235484017 አያሌው ደምሴ ጌታ ይባርካችሁ!

Hello dears, We received requests that some couldn't apply for the Space Science virtual session to be held at Hawassa American Corner announced earlier. Having arranged with the central organizers of the training we got permission to accommodate a few more trainees for that on a new link: https://tally.so/r/gDPxVJ?address=Hawassa So, please get registered as soon as possible and let us know if you face any inconvenience while registering. You may reach us at: hawassaac@gmail.com Kind regards,

ሰላም ቤተሰብ! ይህ ነገር ከ9-12 ክፍል ላሉ ወጣቶቻችን ሳይጠቅም ይቀራል? እስኪ ተመልከቱት። ተባረኩ!

የውስጥ ብርሃንህ አይጥፋ!! ''ብርሃን በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም።” — ዮሐንስ 1፥5 💨. በሕይወት መንገድ ላይ አውሎ ነፋሶች፣ እንቅፋቶች እና ጨለማ ጊዜያት መምጣታቸው አይቀርም። 👉🏻 ነገር ግን እወቀው—በመንገድህ ላይ የመጣው ፈተና ሁሉ አንተን ለመስበር ሳይሆን፣ በውስጥህ ያለውን የእምነት ጥንካሬ እና ብርሃን ለማውጣት የተዘጋጀ ነው። 👉🏻 መንፈሳዊነት ማለት ችግሮች አለመኖራቸው አይደለም፤ ይልቁንም በችግርህ መካከል የሚደግፍህ፣ የሚያበረታታህ እና ከፊትህ የሚቀድም አምላክ እንዳለ አጥብቀህ ማመን ነው! ‼️ ልታስታውሳቸው የሚገቡ ዋና ዋና እውነቶች፡ 🥇ተስፋ አትቁረጥ: የዛሬው ጨለማና ድካም የነገው አዲስ ንጋት መጀመሪያ ነው። 🥈 በጊዜው ይከናወናል: ያሰብከው ነገር ሁሉ ባሰብከው ፍጥነት ባይሆን እንኳ፣ አምላክ ሁሉንም ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ ይሰራዋል። 🥉የውስጥ ሰላምህን ጠብቅ: ውጫዊው ዓለም ቢናወጥም፣ በጸሎትና በእምነት የሚገኘውን የውስጥህን ሰላም ማንም እንዲወስድብህ አትፍቀድ። ‼️ ዛሬ ያጋጠመህ ድካም ወይም ፈተና የጉዞህ ማብቂያ ሳይሆን፣ የአዲሱ ምዕራፍህ መጀመሪያ ነው። ✅ እግርህ ቢዝል እንኳ መንፈስህ አይዳከም፤ በውስጥህ ያለው እምነት ከማንኛውም ውጫዊ ፈተና ይበልጣል! 🎖️ጨለማ፣ ፈተና እና ችግር ቢመጡም፣ የእምነትና የተስፋ ብርሃን በመጨረሻ በጨለማ አይሸነፍም

የምትፀልየው ሀና.. የምትወልደው ፍናና 👉🏻 ሌሎች ሲያሸንፉ ሲሳካላቸው መፀለያችሁን አታቁሙ! 👉🏻 የናንተ ነገር ዘግይቶ ሳይሆን በልዩ ሁኔታ እየተዘጋጀ ስለሆነ ነው። 🙏🏽 ዛሬ ሀና ትፀልያለ
የምትፀልየው ሀና.. የምትወልደው ፍናና 👉🏻 ሌሎች ሲያሸንፉ ሲሳካላቸው መፀለያችሁን አታቁሙ! 👉🏻 የናንተ ነገር ዘግይቶ ሳይሆን በልዩ ሁኔታ እየተዘጋጀ ስለሆነ ነው። 🙏🏽 ዛሬ ሀና ትፀልያለች ...ፍናና ትወልዳለች። 🙌ነገ ግን ሳሙኤል ይወለዳል። ሳሙኤላችሁ ይወለዳል። 🙏🏽መፀለያችሁን አታቋርጡ! keep on praying ነገ ሳሙኤል ይወለዳል ካነበብኩት!!

ሰላም ቤተሰብ! በጌታ ጸጋ ይህንን "የደቀ መዝሙርነት መመሪያ" የተሰኘ መጽሐፍ ከተወሰኑ ጊዜያት ቀደም ብዬ የማንበብ ዕድሉን አግኝቼ ነበር። እንዲህ ተጠናቅቆ ግን ለንባብ መብቃቱን የተረዳሁት ዘግይቼ ነው። ለማንኛውም እነዚህን የእንግሊዝኛና አማርኛ መጽሐፍትንም ሆነ ሌሎች የተባረኩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግብዓቶችን ከዕዝራ ሴሚናሪ (Ezra Seminary) ድረ-ገጽ እንዲሁም መተግበሪያ ያገኛሉ። እንደ ግል ፣ እንደ ቤ/ክ ፣ በቡድን ብናጠናቸው ትልልቅ በረከቶችን እናገኝባቸዋለን። በተለይም ደግሞ ጌጣ ጌጥን በተመለከተ የያዛቸው ሀሳቦች ሙሉ መጽሐፉን ላነበበ ሰው በእርግጥም ቤ/ክ በጉዳዩ ላይ ምን ያህል ምሉዕ የሆነ መረዳት እንዳላት እና እኛም ልንቀበለው እንደሚገባ አሳማኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ጌታ ቢፈቅድ የዚህኑ መጽሐፍ ንባብ በድምጽ / በቪዲዮ በቅርቡ እናገኛለን ብለን እናምናለን። ተባረኩ!

Seventh Day Adventist Church East Ethiopian Union Pathfinder Camporee on Sidaama Broadcasting Corporation (SBC) Amharic News 05.12.2018 Praise God!