cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጥርኝ ጥበብ

ጥርኝ ጥበብ ማለት አንድም እንደ ሽቶ መልካም የጥበብ መዓዛን እናገኝ ዘንድ በሽቶ ከምንገለገልባት ጥርኝ ስም ሰየምናት አንድም ከሞላ የህይወት ስብጥርጥር እና ካልገቡን የህይወት መራራነት በጥርኝ ወይም ደግሞ በትንሽ ጥበብ እፎይታን እናገኝ ዘንድ በዩቱዩብ https://www.youtube.com/@2112-trgn-tbeb በቴክቶክ tiktok.com/@trgntbebhiluabiy

Show more
Advertising posts
430
Subscribers
-124 hours
-37 days
-130 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
አንዳንድ ቀኖች አሉ መከፋታችንን የሚያጋንኑ ጥቂት ቆዛዝመን ለመላቀቅ ስንራመድ የሚጨምሩ ክስተቶች ይበረክታሉ። ለመከፋቴ መጥጊያ ያልነው ያፈሳል ሌላ የሀዘን ዝናብ ያስመታናል።መተማመናችን ሁሉ ይጠፋል። እንዲሁ መቀጠል ይሻላል ጥቂቷን መከፋት ይዞ
590Loading...
02
Media files
690Loading...
03
Media files
1122Loading...
04
Media files
1250Loading...
05
እውነት አላት... ክፍል አንድ (1) "አንዳንድ ቀን የማይጎረብጡ ውድቀቶች ሰላሞ የማይነሱ መንገጫገጮች የልብን ወዳጅ በሞት አጥቶ ወደአምላኩ ሄዴ ብሎ የሚሰማ እፎይታ ይሰማል"። አለችኝ ከልቧ እንደሆነ ፊቷ ላይ የሚነበበው የእፎይታ እና የሰላም ማገኘት አይነት ገፅታ ነው። በሁኔታዋ ደነገጥኩ ...አባቷ ከተቀበረ ገና ሶስት ቀን ታድያ ይሄ ጤንነት ነው? ወይስ ምን ያህል ክፉ ብትሆን ነው በአባቷ ሞት ማግስት ስለውድቀት እና ግልግል እየተፍለቀለቀች የምትነግረኝ... ከራሴ ጋር ሆኜ ላጠናት ልመረምራት አሰብኩ ሞከርኩ የቱም እውነት አልገለጥ አለኝ አላውቅማ እንደዚህ አይነት ሁናቴ አድሴ ነዋ አባቱ የሞተበት ልጅ ያዙኝ ልቀቁኝ በሞትኩ በሚልበት ማህበረሰብ ወጥቼ እንዴት ብዬ ይህንን ልቀበል። ኦንዳለችው እንኳን ወደፈጣሪ ሄደ ብላ ይሆን አይይይ ቢሆንም አያስደስትም በቃ ያስከፋል ስጋ አይደለም የለበሰችው ከአፈር አልተሰራችም እንዴት ልቧ ሸርተት አይልም?... መጠያየቄን አስተውላለችና "በማታውቀው እና ባልገባህ ጎጆ አትመራመር ትደክማለህ እንጅ ምንም አታገኝም ክፉ መስዬ ታይቼህ እንደሆነ አውቃለሁ እኔ የማውቀውን ብታውቅ ከሀቄ በተጠጋጋህ ነበር ግን አታውቅም ማወቅም የለብህም" ምንም ብትለኝ ሀቋ አልደርስህ አለኝ ምናልባት እውነት ይኖራታል ሀቅ ተሸክማለች ግን እውነት ሁሉ ትክክል ነው ሀቅ ሁሉ አግባብ ነው? እንጃ እውነቷ ሳይገባኝ ይቅር ይቀጥላል ...
1220Loading...
06
እናቴ ጎደለኝ የምለውን ስቆጥር ስለካ ስመትር ስለካ አንች ማለት ለእኔ ሙላቴ ነሽ ለካ በአለም ሁካታ እንዳልቆም ፈዝዤ ግራውን አለፍኩት ቀኝ እጅሽን ይዤ ሙሴ አልልሽ በትር የለም ከእጅሽ ኖህ አልልሽ መቼ መርከብ ሰራሽ ዳዊትነት እንዳልሾምሽ ወንጭፍ የለም ከመዳፍሽ ጠጠር የለም ከመሬትሽ ብቻ... በአንች መልካምነት ስንት ችግሮችን አለፍኩኝ ተከፍሎ ሳቅሁ ያለገደብ በሳቅሽ ጠጠር ጎልያድ ተጥሎ በመልካምነትሽ መርከብ ተሳፎሬ ተመስገን እያልኩኝ ደረስኩ እስከዛሬ ከቶ እንዳይነካካሽ ክፋት እና ነውር ጤና ይስጥሽና ሳመሰግን ልኑር #እናቴ የጌጥ የእኔ አምባር የእኔ እንቁ የእኔ አልማዝ ስንቴ ተጨንቀሻል በጭንቅ እንዳልያዝ የለፋሽው ልፋት ፍሬ እንዲያፈራ እናቴ የምወድሽ ደህና ሁኝ አደራ ✍ዐቢይ አለሙ(ሚተራሊዮን)
1320Loading...
07
ይናፍቀኛል ... ስም አጠራሩ ጆሮየ ላይ ያቃጭላል ። ጎራዳ አፍንጫየን ለማሳደግ በእጆቹ ሲነካኝ" እረፍ አትረፍ" ንትርኩ ይናፍቀኛል። ተገናኝተን አማይገቡኝን ነገር እያወራኝ ከንፈሮቹን ብቻ እያየሁ ፈገግ ማለት ይናፍቀኛል ። ባለማመን ዉስጥ ያለች መዉደድ ያመጣት ቅናቱ ይናፍቀኛል ። ሲስቅ የድምፁ መጎርነን ከጥርሶቹ አሰዳደር ጋር ተዳምሮ ነፍሴ ላይ የሚፈጥረብኝ ደስታ ይናፍቀኛል ። እያጣሁት እየተለያየን መሆኑን ለልቤ ሹክ ባልኩት ቁጥር ይናፍቀኛል ። ደጀ ሰላሙ ስር ተንበርክኬ በእየየ ቤቱን ያራስኩት ዉሳኔን ለግሰኝ ብየ ነበር ። መቁረጥን ወይ መቀጠልን ። በትንሽ ቅናቱ ዉስጥ እምነት አልባነት ተጨምሮ ቀና መንገዱን በኔ መወላገድ ህይወቱ ሲንጋደድ ተሰምቶኝ ነበር። ከቤቱ ሙሉነት በ ሄዋን ስም ልቡ ውስጥ ገብቸ ጥርጣሬን የጫርኩ አሳቹ እንደሆንኩ ተሰማኝ። ከጠራ ህይወቱ ድፍርሷን አኔን ጨምሬ በ ሀዘን ድባቅ እንዳስመታሁት ልቤ አረዳኝ ። መሳቅ አና ማዉራቴን ለዛ ነዉ የጠላሁት ። ፈገግታየ እምነቱን ሸረሸረበት ። ለሰዎች ቅርብነቴ የልቤን ሰዉ ለጥርጣሬ አጋለጠዉ። ልባምነቱ ከኔ እልህ ጋር አይወዳደርም። ግልፅ አንደበቱ ከኔ ዝምታ ጋር አይታሽም። ቀስ በቀስ ማዉራት ጀምሬ ነበር። ለማንም ካላወጣሁት እኔነቴ ጋር እያስተዋወኩት ነበር። ከረሳሁት ፍቅር ጋር ተላትሜ እሱን ስለማግባትም አልሜ ነበር ። ለተከታታይ ቀናቶች ዝምታን አርምሞን ከመረጥን በኋላ ሰላም አየተሰማዉ እንደሆነ ስሰማ ነው ልቤ የሸሸዉ ። "ለካ ማዉራታችን ነዉ ሰላም የነሳኝ" ማለቱን ለጆሮየ ሲያቀርቡት መለየቱን የመረጥኩት ። በመቅረብ ያደፈረስኩትን በመራቅ ለማጥራት።ለዚህ ነዉ ህይወቱን ላጠራ ያልተገባሁትን እኔን ለኖርኩበት ብቸኝነት ሰጥቸ ከኔ ነፃ እንዲወጣ መለየትን የመረጥኩት ። ብቸኝነቴ ዉስጥ ለማንም እማይብራራ የሱ ናፍቆት በቀናት ብዛት በዝምታ ተጀቡኖ ወደነበርኩበት እኔነቴ እንደሚመራኝ አዉቃለሁ።
1812Loading...
08
በሚዛን ስንለካ ስራዬ መዛኝ ነው የሰውን ክብደት ስለካ እውላለሁ። ሚዛኔ ሰውነታቸውን እኔ ደግሞ ሀሳባቸውን እንመዝናለን ሰው በጠፋ ሰዓት የማዋራት ሚዛኔን ነው። ሳቄ ነው የምላት እርሷን  ማንም እየረገጣት እየደለቃት በምትሰጠኝ ሳንቲም የእኔ ሆድ ሞልቶ ስቄ ስለምውል ሳቄ ናት።ስንት አይነት እግርን ትችላለች ስንት አይነት ጫማን ትሸከማለች አንዳንድ ቀንማ ከጫማቸው ክብደት በላይ በንፅህና ጉድለት የሸተተ ጫማ ተረግጧት ትውልና ስታስነጥስ ትሰነብታለች ያን ሰሞን እንዴት ነው የምታሳዝነኝ መሰለቻሁ።አሞኛል ልረፍ አትልም ሁሌ ትረገጥልኛለች።እንዳልኳችሁ ሳቄ ሰውነት እኔ አመለካከት እና ሀሳብ እንመዝናለን። አንዳንድ ሰው አለ የሚስቱን ሞት የልጆቹን ርሀብ በትከሻው ተሸክሞ ይመጣና ሲመዘን በኪሎው ይደነግጣል አደነጋገጡ ራሱ  አምስት ኪሎ  ያስቀንሳል።ወትሮስ የቤቱን ድምቀት የጎጆውን ምሰሶ በሞት የተነጠቀ ልጆቹ የራበኝ ሰቆቃቸውን እንደ እለት ኪዳን የሚያሰሙት ወጣት መፋፋት አምሮት ኖሯል። ሳቄ ከትከሻዋ ወርዶ አምስት ብር ሲሰጠኝ አይታ አዘነችለት "አሁን ይሄኔ እኮ ምናለ ዳቦ በገዛሁበት እያለ ነው ዝንብ ያረፈበት ያህል ሳይሰማኝ ወርዶ አምስት ብር ሙሉ ይከፍላል ምስኪን " ንግግሯ አንጀቴን ይበላኝና ልመልስለት እቃጣለሁ ከዚያ የእኔስ ልጆች ከራስ በላይ ...እተወዋለሁ። ደግሞ አንዳንድ ቀን ጅምር ኮንደሚኒየም የሚያክል ሰው ይመጣል ገና ወደእኛ ሲቀርብ ሁለታችንም እንሳቀቃለን። ሳቄ በመለኪያዋ ራሷን ስትለካ አስር ኪሎ ቀንሳለች ሰማይ የተደፋባት ያህል ሲጫናት አይጥ በወጥመድ ስትገባ የምታሰማውን ሲቃ ታሰማለች።ከብዙ የመቶ እና ሁለት መቶ ብሮች መሀከል አምስት ብር አውጥቶ ይሰጠኛል።ያኔ ነው ሳቄ ሀዘኗ የሚበረታው "ለዚህ ነው ህብረሰረሰሬ እስኪቆረጥ የተሸከምኩት"እንደማልቀስ ይቃጣታል ሚዛኔ ታሳዝነኛለች ብዙ ጉዶችን ትቸከማለች።አንዳንዴ ኢትዮጵያን ትመስላለች ብዙ ቀጫጭን ለጋሶችን በተሸከመች ሀገር ጥቂት ወፋፍራም ስስታሞች ያጎብጧታል።
2090Loading...
09
Media files
1860Loading...
10
ሰባት ሆነን ነበር ትምርት ቤት የምንሄደው አንለያይም። እናጠናለን አቅማችን ፥ ኑሯችን ፥ ጥረታችን ተመሳሳይ ነበር። ማትሪክ ደረሰ ፤ አጠናን ተፈተንን ፤ ፕሪፕ ስንገባ ምን እንደምንመርጥ እቅዳችን አውጠነጠንን ፤ ውጤት ከብዙ ጥበቃ በሆላ ወጣ ተባለ ፤ ልንቀበል ሄድን... ሁሉም አለፉ ከኔ በቀር። ከውጤት መልስ አብርያቸው ነበርኩ እንደልባቸው ድላቸውን እንዳያጣጥሙ አደረኳቸው። ጓደኞቼ ፣የሰፈሩ ሰዎች፣ የጓደኞቼ  ቤተሰቦቾ  አይዞህ አሉኝ አዘኑልኝ። ውጤቴን ለቤተሰቦቼ አሳየኋቸው እቤት እከሌስ እከሌስ እንዴት ሆነ ሲሉኝ ከኔ በቀር ሁሉም አልፈዋል አልኳቸው። ለመጀመርያ ግዜ ከቤት መውጣት ደበረኝ። አለመርባት ስሜት ተሰማኝ.. እድል የለኝም አልኩ.. ምን አለ ሞቼ ብሆን አልኩ.. ድብርት አከሳኝ። አብሮ አደጎቼ ጋ መሆን አልፈለኩም ነበር። ኋላ የምቀር መሰለኝ ....የሆንኩትን የገጠመኝን ቀላል እንደሆነ የሚያሳምነኝ አንድም አላገኘሁም። መውደቅን ፥ ማነስን ፥ ብቻዬን ተጋፈጥኩት። እናቴ ብቻ ናት የራሱ ጉዳይ አንተ ብቻ ደና ሁንልኝ ያለቺኝ ዋናው ጤና ነው የሚቀጥለው ታሻሽላለህ አለቺኝ። ደግሜ መፈተን እንደማልችል አልገባትም ነበር። . . . አጎቴ ገራዥ ነበረው እሱ ጋ መዋል ጀመርኩ። የማታ Auto mechanic መማር  ጀመርኩ። ጎበዝ ባለሙያ ሆንኩኝ። practically እወቀቱን ሳየው ስለምውል theory ቀለለኝ። ከክፍሉ አንደኛ እየወጣሁ ስራ ቦታም ጎበዝ መካንኪ ሆንኩኝ። ብቻ መቆም ለመድኩኝ ብቻ መውደቅ ምን ምን እንደሚል ጌታዬ አስተማረኝ የወደቀ ሰው እንዴት እንደሚፅናና ተማርኩኝ መውደቅ ሁሉ መውደቅ እንዳይደለ ተማርኩ ዛሬ ሃብታም ነኝ። የመኪና  'spare part' አስመጪ እና ላኪ ሆኛለሁ። ጌታ ኋላ የቀረን ግምባር ቀደም ማድረግ እንደሚችል ፤ በሁሉም ሰው  የታዘነለትን ፥ በሁሉም ዘንድ የሚያኮራበት ሰው ማድረግ እንደሚችል አይቻለሁ። ያኔ ብቻዬን ስሆን የተሰማኝ ውድቀት የወለደልኝ ጥንካሬ እና ብስለት ዛሬ ድረስ ስንቴ አሻግሮኛል...! አንዳንዴ ተለይቶ የመውደቅ መጨረሻ ድልም ሊሆን ይቻላል!!   
2040Loading...
11
አንዳንዴ የአንድ ቀን ውሳኔዎቻችን ደግሞ የወራት የአመታትን ጥያቄዎች ይመልሳሉ።የወድድናቸውን ልናገኝ የጓጓንላቸውን የእኛ ለማድረግ ብዙ የታገልናቸውን ያነባንላቸውን ስንት አቡነዘበሰማያት የደግምናላቸውን ሰዎች እንረሳና የአንድ ቀን ውሳኔዎቻችን ታሪክ ይቀይራሉ።ስንት ዘመን በፍቅር የከነፍክላትን ሴት በአንድ ቀን የምታስረሳህ ትመጣለች ምኗን ወደድክላት ስትባል መልስ እሰከምታጣ ትወዳታለህ። አስበህበት ነው የጀመርከው ስትባል ማሰብ ራሱ ምን ነበር ትላለህ። ያጣናቸውን እያጣናቸው ያለውን እንዳናስተውል የሚያደርጉ ሰዎች በህይወት ይመጣሉ። አንዳንድ የልብ ጓደኞች ደግሞ አሉ የህይወትህ በረከት የሆኑ እነርሱን ካወክ ጀምሮ መንገድህ የተቀየረ ህይወት የተቃና የሚያደርጉ ተዓምራቶች በህይወት የሚበረክቱበት ድንገት ወደህይወትህ ገብተው ድንገተኛ በረከቶችን የሚያስከትሉ መሳቃቸው ሳቅን የሚወልድልህ ላገኘኋቸው ስኬቶች በሙሉ ማንጋጠጣቸው እንዳለ ታስተውላለህ። ህይወት እንደዚህ ናት መነጠቅህን እስክትረሳ ሰው ትሰጥሀለች። ሰው መኖርህን እስክትዘነጋ ሰው ትነጥቅሀለች ለሁሉም ተራ መጠበቅ ነው
1761Loading...
12
ሳቀ ሳቀ ይሉኛል ጠፋለት ከአይኑ ላይ እምባ ስንቱን ጉድ በአንች እንደከላሁ የህይወቴን ስርጉብጥ ጉድባ ሳቀ ሳቀ ይሉኛል ጠፋለት ከፊቱ ሀዘን ለልቤ ምን እንደሰራሽ አይችሉም አንችን መመዘን ጠፋለት አለቀ ሲሉኝ እድገቱ ቁልቁሊት ሆነ ወሪያቸው ተቀየረና ይሄ ልጅ እንዴት ገነነ እንዴት ከፍ ከፍ አልል እንዴትስ ገነነ አልባል ንጉስነት ማን ይነፍገዋል ወትሮንስ የንግስትን ባል
2130Loading...
13
ግዙፍ የሚመስሉን ዉሳኔወች ሁሉ ለመወሰን ምንአልባትም አመታትን ወራትን ቀናትን መጠበቅ አይገባን ይሆናል, የወደድናቸዉ ልናገኝ የጓጓንላቸዉ , እነሱን ላለማጣት ከህሊናችን ጋር ቀን ከሌሊት የተዋጋንላቸዉ ሰወች ምንአልባትም የኛ አደሉም። ስለነሱ ያነባነዉ የታፈነ እንባም በረጋ ፀሎት ታሽቶ ምላሹ ማጣት ይሆናል። ላጣናቸዉ እያጣናቸዉ ላለነዉ, ላለማጣት እግዜሩ ደጀ ሰላም ተንበርክከን ሰተህ አትንሳኝ በሚል ወቀሳ ስለነሱ የሞገትንላቸዉ, ህይወታችን ውስጥ እንደቀልድ ገብተዉ ከልብ ሰገባችን ለማዉጣት የሚያታግሉንን ሁሉ አንድም በፀሎት አንድም በአርምሞ እናልፋቸዋለን። ማጣትን ለማጣት ብቸኝነት ሸጋ ነዉ ። ላለማጣት ከፈጠራቸዉ ጋር ታግለን መዳረሻዉ እራሱ ማጣት ሲሆንብን አደለም አንደበት ህሊና ከትናንት መነጋገር ይቸግረዋል ። ዝምታ ድብቅነት ሳይሆን ይመምን በፈገግታ ማስመሸጊያ ቦታ ነዉ።
2604Loading...
14
ረዥሙን ፍቅር በአንድ ቀን ናደችው የእድሜ ልኳን ታሪክ ደብዳቤውን ሁሉ ቀዳ ማገደችው ፀዳ ግሳንግሱ ጋብ አለ ማልቀሱ ደህና ነሽ? በኸኸኸኸኸኸወጣም ደህና ነኝ ረዥም ፈገግታ ያልተለመደ ሳቅ የምታፍለቀልቅ ሴት ልጅ አመሏ ቁስ ስትደብቅ ደህና ነሽ ደህና ነኝ😃😴😁
2480Loading...
15
እኛ ያመጣናቸው እነርሱ በለጡን እየጎተንት ወደ ቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ይዘነው ገባን።የገዛንለትን ነጠላ ዘርግቶ ለመልበስ ግራ ሲጋባ ከሶስታችን መሀከል አንድኛው ተጠግቶ በአንገቱ ስል አመሳቅሎ አጣፋለትና "እንዲህ አይሰገድም እሽ እሽ ምግብስ በልተሀል ኧረ አልበላሁም አዎ ምን ሆነሀላ ውሀ ራሱ ከጠጣህ ነገር ተበላሽቷል በቃ አይ እንደዚያ አላደረኩም" ይቁነጠነጣል...በመሀል 1000 ሰግደን ለመውጣት የምንገፋፋው እኛ ቆመን ሳለ እርሱ ስድስት ሰባት ጊዜ ከፍ ዝቅ ብሎ ጉልበቱ እንደተብረከረከ ሰው በግንባሩ መሬቱን ተደግፎት ቀረ። እንግድህ ላለመነሳት ምክንያት እየፈጠረ መሆኑ ነው ቀና ማለት እንደከበደው ሰው ቁና ቁና ሲተነፍስ ይሰማናል።... "ቃል እንደጓደኛ ይሄንን ልጅ ምንም መላ አናበጅለትም ማለት ነው"አለ ቢታንያ ወደ አንገቴ ተጠግቶ ... እኔ ደግሞ የአናንያን ህይወት እየሄደ ካለበት ቁልቁለት ለመመለስ መሞከር ውሀን ሽቅብ የማፍሰስ ያህል ድካሙ ብቻ ነው የሚታየኝ። ለጓደኛ በዚህ ልክ መጠን ዝሎ መኖር ቢያሳፍርም... "ሱስ እኮ ነው እየበዛ በጣም ብሶበታል የት እናስጠምቀው በእናትህ" የየግል አስተያየታችንን ለጣጥፈን ስናበቃ ካጎነበሰበት በርከክ ብሎ አንገቱን ደፍቶ ነጠላውን አናቱ ላይ ጎዝጉዞ ተቀመጠ። ለካ መቆም ቢያፍር ነው እንባ አርግዞ የወደቀው ድንገት ቀና ሲል ደንግጠን ተያየን በስጋው ላይ እንደተቆጣ የሚያሳብቁት የደም ስሮች ከወደግንባሩ እንድህ ተከታትለው ለመሰለፍ ምን አነቃቃቸው ከምኔው ፊቱ በእምባ ረጠበ አያስቀናም ልታፀድቁ በገሰፃችሁት ሰው ተሰብካችሁ እንደመሄድ ያለ ስብከት ወደየት ይገኛል። የእኛ ፀፀት አርባአንድ ኪራላይሶን ብለን ከአይናችን ካልወረደ ለእርሱ በሰባት ዝቅ ማለት በዘነበለት እምባ እንዴት አይቀናም አምላኩ በልቡ አደባባይ በታተመለት ሰው ቁኑ ሀቁም ይሄው ነው። በልምድ መመላለስ የፀና ሐዋርያም አንዳንድ ጊዜ ሊያፀድቅ ይዞ ከመጣው ወንበዴ ተምሮ ይሄዳል።... ፀሀፊ ✍ ጌታሁን ደጉ
2520Loading...
16
ትናንት የነበሩኝ መጥፎ ሆነው ሳይሆን ዛሬ ያሉኝ የተሻሉ ስለሆኑ ነው።
2121Loading...
17
ልጅ እንደሆኑ አይቀርም መቼም አደግናታ ለሁሉ ነገር እይታችን ተቀየረ የህይወት ፍልስፍና ይሉት ቀመር አዘጋጀን። ምክንያታዊነት ይሉት ማሰሮ አዘጋጀን የነፃነት ዘመን አከተመ ለሁሉም ነገር ቀመር እና ልኬት ተሰነቀለት። እያንዳንዷን እርምጃ በጥንቃቄ እና በቆጠራ ሆነ ... አንድ እርምጃ እገሌን ይከፋው ይሆን ሁለት እርምጃ ባላስቀናኋት ሶስት እርምጃ ነውር ቢሆንስ አራት እርምጃ የሰው ሁሌም የሰው ነው . . . የገደብ ህይወት ይጀመራል አንዳንዴ ግን ማደግ ማሰሮ የሚመስልበት ጊዜ አለ።
2500Loading...
18
የእልፍ ዘመን በደል በእልፍ አርምሞ ቢያልፍም በሀገር የመጡ እለት ሞት አይታለፍም ያንን የጦር ገበሬ የአባት ቃል ጠባቂ ፍታ ቢሉት ከፋው የሀገር አስታጣቂ ይሙት አትበሉ አይሙት ጠላታችን አይከደን ጥርሱ የሀገር ሰላም መሆን ሞት አይደል ወይ ለእርሱ
2510Loading...
19
ከወደድካት ካፈቀርካት እስኪ ፃፋት እንዴት ያለ እውነቴን ላስረዳቸው ከቃል በላይ እንደሆነች አልገባቸው ካገኘኋት ከታደልኳት በማግስቱ እንደሆነ ሞቴ ሞቱ ውብ እጇን እንደጨበጥኩ ያን እለቴን ከሀዘን ጋር መፋታቴን የደስታዬ ሀሁ ፊደል እንደሆነች እንዳልፅፋት እርሷ ራሷ ፊደሌ ነች ይሄ እውነት ካልገባቸው... ካልተረዱት የልቤን ቃል ከተፃፈው ሁሉ በላይ በልብ ያለ ሀቅ ይልቃል ከዐቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
2903Loading...
20
የእኔ ለእኔ ፀሎተኛ አይከደን የአይኗ ሽፋፍ አትለኝ ከአጠገቤ ሀዘን ጭንቄን በድል እንዳልፍ አይታጠፍ የግንዷ ዘርፍ ዘወትር ዝርጉ ለፈጣሪ አይጨፈን ውብ አይኖቿ ተማፅኖዬን ተናጋሪ አንጋጭ ባልኳት ሁሉ ከእግዜር ጋር ተማካሪ ከቀዳሁት ከተማፅኖ ከተዋስኩት ከፀሎቷ ልለማመን ከፈጣሪ ስለሰላም ደህንነቷ ህሊናዬን ማስተዋሌን ቢጠብቃት ትዝታዬን በቸር እጁ ቢጎበኛት ልመፃፀን ሸብረክ ይበል ድኩም ልቤ አኑራት ነው ተማፅኖዬ 'ምናገረው ተስገብግቤ ከዐቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
2413Loading...
21
ይመጣል ብየ ለልቤ ነግሬዉ ነበር... ኮቴ በሰማሁ ቁጡር ዉስጤ ከቀረ ጠረኑ ጋር አዋኅጀ ልቤን አስበረግገዋለሁ ነበረ... እማይመጣን ለ ሰከንድ በተስፋ መጠበቅ ለካ የዘመናትን ያክል እሩቅ ነዉ... ብቻየን ስሆን ከራሴ ዉጭ የጠበኩበትን ነገር አላስታዉስም አብሮነት ዉስጥ ማጣትን ሳንለማመድ መግባት ለመሰበር እራስን እንደማመቻቸት ይመስለኛል። ላጣዉ እንደምችል ለልቤ አልነገርኩትም ነበር , በረከትነቱን ስጦታየ ነህ ብየ ተቀብየዉ ነበር ። አንዳንድ በረከቶች መዳረሻቸዉን በወጉ አያዉቁም ። ለመስጠት ያልቸገረንን ልብ ለመመለስ አንሟሟታለን ። ስሰጠዉ ስፈቅድለት ያልከበደኝን ለነበረዉ ማንነቴ አስረክቦኝ ሲሄድ የሰጠኋትን ለማባበል ግን ብርታትን አጣሁ። ህመሜን በዝምታየ ደበኩት። ብሶቴን በአርምሞየ ሸሸኩት። ....እሱ ወደፊት ሄደ, ያጣኋትን እኔን ለማባበል እኔም ወደኋላ ቀረሁ።
2331Loading...
22
"አመሰግናለሁ ቻዉ" ሲለኝ እጆቼ ይንቀጠቀጡ ነበር .... በሱ አለመታመኔ እልህ ዉስጥ መሸገኝ። እነደታመንኩለት ለማስረዳት ከአይኖቼ ውጭ ቃላት አጣሁ አይኔን ማመን አልፈለገም ። ፍቅሬን ከ እልህ ጋር ተናንቄ ላቆየዉ እየሞከርኩ መሆኔን ሴትነቴ ቆይ ብሎ እጁን ለመያዝ እንዳገዳገደኝ አልገባዉም። እግሮቹ እንደወጡ አለመታመን አለመፈለግ ከተስፋ መንጠፍ ጋር ተባብረዉ ሰዉ አየኝ አላየኝ ሳይሉ አንኖቼ የእንባ ጎርፍን ለጉንጮቼ አስረከቡ። ሰቶ ይነሳል? ወይስ ከጅምሩም አልተሰጠኝም ? እንባዋን በሳቋ እምትደብቀዋን እኔን አጣኅት ። ስለ እሱ ነበር ብየ ማዉራትን ፈራሁት ። ለካ እንደዚህ ወድጀዋለሁ ። ማጣትን ካጣሁት ስለቆየሁ ይሆን የኔ እሱን ማጣት ማመን የቸገረኝ። እንባን እፈራዉ ነበር። ለ እንባየ ቦታ እመርጥለት ነበረ። ከሱ መሄድ በኋላ አይኖቼ ቦታ እስክመርት አልታገሱኝም ። ጥሎኝ የሄደበት ቦታ ላይ አፌን አፍኘ እንዲወርድ ፈቀድኩለት። ሲሄድ አይኑን ለማስተዋል ሞክሬ ነበር መከፋትን ግን አጣሁበት ። በመሄዱ ደስተኛ የሆነ ያክል ተሰማኝ ። በአይኖቹ ተገላገልኩሽ ያለኝ መሰለኝ። ዞር ብሎ እንኳን አላየኝም ነበር ልብ ካልፈለገ አይንም ማየት አይሻም አደል።? ልቡን ከልክሎኝ እንደነበር ያልተከፋ ገፁ ላይ እጁን ለሰላምታ ዘርግቶ አመሰግናለሁ ሲል ነበር የተገለጠልኝ። ሁሉም እዉነት ማረጋገጫ አላዉ? ጊዜ እና ቦታ የማይመርጡ ህመሞች እንዳሉ አሳይቶኝ ሄደ። ሲመጡ እድለኝነትን አከናንበዉን ሲሄዱ አለመፈለግን የሚሰጡንን አሉ። ቢያጡን ከህይወታቸዉ ጥርኝ የማይጎድልባቸዉ። የኛን መሄድም መምጣትም በ "አመሰግናለሁ" ብቻ መቋጨት የሚችሉ ። ያልወደዱን የወደዱን የሚመስሉ ። ያላመኑን ያመኑን የሚመስሉ ። እኔን ማጣቱ ፊቱ ላይ መከፋትን አለመጫሩን ሳይ ያልገለጥኩለት መዉደዴ ምን ያህል ገዝፎ እንደነበር ገባኝ ። ደስ ብሎት ሊያቅፋት ሊያወራት እሚችለዉን እንስት ስም ለ ልቤ ለመጀመሪያ ግዜ ሹክ አልኩት ። እንባን ያለሰቀቀን አለቀስቁት። ሳያምነኝ መቶ ሳያምነኝ ሄደ ። ፍቅሩን በዝምታየ በድብቅ እንድይዘዉ አደረገኝ ። ሁሉም እዉነት ማረጋገጫ የለዉም።
2342Loading...
23
አንዳንድ ቀኞች አሉ ዙሪያችንን ያለውን ሁሉ እንዳናስተውል የሚጋርዱን።ሀዘንን የሚያሸብቡ ክፉን የሚያስታውሱ ያልፉ ይሆን የሚባሉ ቀኖች። እንድሁ ቁዘማ ቁዘማ የሚያሰኙ ደርሶ የአስቴር አወቀና የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃን የሚያስመኙ። ግን የምር ያልፉ ይሆን?
140Loading...
24
"ሰይጣን አሳስቶት ነዉ " .... የትኛዉም ድርጊት የ አድራጊዉን መልካም ፈቃድ ይጠይቃል , ያለፍቃዳችን የገባዉ የትኛዉ ጥርጣሬ ነዉ? አሳሳቻችን እስክንጠራዉ በር ላይ ነዉ ሚቆመዉ , ስሙን ያለመጥራት መብት ግን አለን። ሰይጣን አሳስቶት ነዉ.... ወዳጁን የሚወድ ጠላት ነዉ ያለን ባቀረብነዉ ቁጥር የሚያቀለን , በጠራነዉ ቅፅበት ለማጣመመ የሚምዘገወግ, ያለመጥራጥ ፈቃድ ግን አለን ። ቢያንስ ዝምታን እንልመድ እስክንጠራ ባለችዉ ሰአት ህሊና ለማሰብ ፋታ ያገኛልና።
2140Loading...
25
አንዳንድ ቀኖች አሉኝ ዙሪያችንን ያለውን ሁሉ እንዳናስተውል የሚጋርዱን።ሀዘንን የሚያሸብቡ ክፉን የሚያስታውሱ ያልፉ ይሆን የሚባሉ ቀኖች። እንድሁ ቁዘማ ቁዘማ የሚያሰኙ ደርሶ የአስቴር አወቀና የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃን የሚያስመኙ። ግን የምር ያልፉ ይሆን?
2442Loading...
26
አንዳንድ ቀን አእምሮዬ እንድህ ይጠይቀኛል
2180Loading...
27
"አንዳንድ ጊዜ አለማወቅህ አለመቻልህ ፈጦ ሲወጣ ከሰዎች ፊት ሲያቆምህ ሲያለማምንህ ሲያመፃፅንህ እንደማየት መጥፎ የለም" ...ይህንን ስትነግረኝ የሀዘን ደመና ፊቷን ሸፍኖታል እምባ ከአይኖቿ እያረዘረዙ ነው መከፋቷ ብቻ ሳይሆን ስብራቷ ከገጿ ይነበባል። ምነው ምን ሆነሽ ነው...አልኳት ስሜቷን ለማንበብ እየሞከርኩ የማዘኗን ነገር ቢያሳብቅም መርምሬ ላገኘው ያልቻልኩት ሀዘን ነው። አሉ ደግሞ አንዳንድ ስብራቶች የኔ ያልናቸው ሰዎች ራሱ የማይረዷቸው እንኳንስ በማየት በመነጋገርም ለሌላው የማይገቡ ጥልቅ ስቅራቶች ለሰሚው ቀላል የሆኑ ለኗሪ የሚከብዱ... "የሆንኩት ካየየኸው ይገዝፋል ካወራሁትም ከማወራም ይልቃል ለዚህ ደግሞ ቃል ማባከን ምኔ ነው የሆንኩትን አለም አትገጥመውም አለም አትስለውም አለም አትዘፍነውም ከጥላሁን ገሰሰ ንፋሽ ያልፋል ከሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ብዕር ይልቃል ከስብሀት ገብረእግዚአብሔር ልቅ ብዕር ይንቦረቀቃል ከሰዓሊ ቸርነት ሸራ ይሰፋል ጥበብ ብትጠበብ ሀዘኔን መግለፅ አልችልም ታድያ በምንኛ ቋንቋ ላስረዳህ እኔ የውስጤን ለመናገር እንደ ሐዋርያት መንፈስቅዱስ ወርዶ በቋንቋ በረከት እስኪያጥለቀልቀኝ በፀሎት ተግቼ መጠበቅ ነው የሚሻለኝ" አፌን ከፍቼ አሰማታለሁ ላቋርጣት ብልስ ምን ላወራ ለምዶኝ በወሬ መሀል እ...እና እሽ የሚሉ ፊደላት ማስገባት አልወድም እርሷም ይህንን ስለምታውቅ ነው በነፃነት እየሰማኋት እንደሆነ አውቃ የምታወራኝ። "አለማወቅን አለመቻልን ማወቅ መታደል ነው ሌሎች እንድያውቁት ማድረግ ግን ሽንፈት ነው መቼም ካልቸገረህ በቀር ድክመትህን ወደህ ለሰዎች አትገልጥም የገለጥክ ቀን ግን የምርም ቸግሮሀል አጣብቂኝ ውስጥ ነህ" ... አይኖቿ ማፍሰስ ጀምረዋል ከዚህ በላይ መቋጠር ቢቸግራቸው ጉንጮቿን በትኩስ እምባዋ ያጥባሉ ጥቂት ዝም አለችና አየችኝ። "ይልቅ ና እቀፈኝ እቅፍህ ውስጥ በደበቅ ዘመናትን ከማውራት ይበልጣል የጣቶችህ ፀጉሬን መንክታ ከናፍር ከማልፋት ይልቃል ና እቀፈኝና ዝም እንበል" አቀፍኳት የሎሬት ብዕር የማይገልፀው ሀሳቧን በሎሬት ግጥም አጅቤ አቀፍኳት አብረን ዝም እንበል ከሰው መንጋ እንገንጠል ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል በእፎይታ ጥላ እንጠለል ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል . . . ከዐቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
2341Loading...
28
ተገብታህ አይደለም ታድለሀት ነው። ባላሰብከው ሰዓት በፍጥነት ወደህይወትህ የመጣችው ቀላል ስለሆነች ሳይሆን ከአንተ የሆነ ጥሩ ነገር ማየት የምትችል ማስተዋል ያላት ስለሆነች ነው ወይም መልካም ማንነት እንድኖርህ ቀብድ እየተቀበልክ ነው።
2194Loading...
29
ነጎደ እልፍ አመታት ሞዠቁት የእድሜን ቋጠሮ ልመለስ ቀን ስጠኝ እያልኩ እንደ አምናው ዛሬም ቀጠሮ አትፈልግ ዘንድሮም ፍሬ እንቡጥ ገና አላፈራሁ አንድ ብቻ ታገሰኝ አምላክ ሆይ መቆረጥ ፈራሁ አውቃለሁ የዛሬአመት እንድሁ ነበር ፀሎቴ ከዛሬ ነገ ስቆጥር ነጎደ ድንገት ቀናቴ ይህች አመት ታገሰኝ ለአመቱ ፍሬ እይዛለሁ እንድሁ ምሳር ቢያገኘኝ ለአንተ ምን እበጃለሁ በፍቅር እንድለማመን እንድሆን የቤትህ ታማኝ ምሳሯ ትለፈኝ ዛሬ ይህችን አመት ታገሰኝ
2241Loading...
30
ሀሉም ኑረት ኑረት አደለም.. ስለዘላለማዊ አብሮነት ተሰብከዉ በስመ ፈተና በእንጥልጥል የቀሩ መኖሮች መኖር አደሉም ፍቅርን ባለማመን እሳቤ ሽርሽሮ ወደፊትን በጥርጣሬ ያነጣጠሩ መኖሮች መኖር አደሉም። ሁሉም ማቀፍ ማቀፍ አደለም... እልፍ ቅሬታን አቅርሮ ዝምታን በሳቅ ሸብበዉ የተዘረጉ ትክሻን የሻቱ ማቀፎች ሁሉ ማቀፍ አይደሉም። ከ ተመልካች አይን ሽሽት አልቃሻ ብሌንን በጠራጊ መዳፍ ሞዥቆ እየየን ትራስ ስር ለማድረግ የተዘረጋ እቅፍ ..... ሁሉም መሳቅ መሳቅ አይደለም... ፈግ መሳቅም አለ።
2270Loading...
31
መታመን ከራስ ላልሰረገ ዉጫዊ አካል ሳይሆን ያለምንም ማመንታት እዉነታዉ ለተገለጠላት ነፍስያ በህሊና ሳይገረፋ ለከበረች አኔነት ነዉ። ለራሱ የታመነ ነዉ ሌላ ማንነትን የሚያሳምነዉ። ሰዉነት ዉስጥ እራስን ሳያቀርቡ መቅረብ የለም , ለመቅረብም ለመዉጣትም የሚያሸማቅቀንን ሀቅ በአርምሞ ህግ ከእራስ ጋር ተሞግቶ ነዉ የሚፈታዉ። ለራስ መታመን ይቀድማል
2000Loading...
32
በዝምታ ዉስጥ የሚታለፉ መከፋቶች ስኬትን ያሰምራሉ። አንዳንድ ጩኸቶች ደግሞ ከዝምታም በላይ ክብረትን መተንፈስን ይለግሳሉ። ለጯሂም ለዝምተኛም የተገባች አንዲት እዉነት አለች።
10Loading...
33
በዝምታ ዉስጥ የሚታለፉ መከፋቶች ስኬትን ያሰምራሉ። አንዳንድ ጩኸቶች ደግሞ ከዝምታም በላይ ክብረትን መተንፈስን ይለግሳሉ። ለጯሂም ለዝምተኛም የተገባች አንዲት እዉነት አለች።
1840Loading...
34
ባለማመን የተጀቦነ አብሮነት ብቸኝነትን ያስናፍቃል። ብቸኝነት ዉስጥ ለሌሎች የሚብራራ ህይወት የለም፡ ነፍስ እና ህሊና ተስማምተዉ የሚያኖሩን እኔነት ነዉ ብቸኝነት ማለት ። አብሮነት በ ፍቅር አና በማመን ሲገነባ ትንሿ ብቸኝነት ዉስጥ ጥርኝ ቅመም እንደመጨመር ነዉ, አብሮነት ዉስጥ ደስታን መለማመድ አለ አብሮነት ዉስጥ ማጣትን በእንባ ሞሽሮ ማግባት አለ አብሮነት ዉስጥ ................አሉ
1670Loading...
35
እያንዳንዱ ቀን አዝሎ የሚያሻግረንን ወይ ጥሎ የሚደቁሰንን ፈተና ይዞ ይመጣል ። በማለፍ እና ባለማለፍ : በማመንና ባለማመን: በመኖርና ባለመኖር ፡ በመታመንና ባለመታመን መንታ መንገድ ላይ ያለ አንሽታ የሚጥሉን ፈተናወች እልፍ ናቸዉ። ምንአልባትም ስቀን አንሸሽጋቸዉም። ምንአልባትም አልቅሰን አይወጡልንም። በመሳቅም በማልቀስም የተዋጀ ዝምታ ዉስጥ የሚከቱን አነዚያ ፈተናወች ድብቅ ያሰኙናል ። ወዶ የተደበቀ ይኖር ይሆን ? ሁሉም እዉነት ይወራ ይሆን?
1761Loading...
36
ድብቅ ናት አሉኝ ልጅቷን እያዩ... እንዴት? አልኩኝ አያየኋት ትናንቷን አታወራም ዛሬዋን አትናገርም ወደፊቷን አታሳይም ሁሌ ፈገግ ትላለች ። አሉኝ ቀስ ብለዉ እያንሿካሾኩ። ድብቅነቷን ተደብቀዉ ያወሩታል። እራስን አለማጋለጥን በድብቅነት አዉዝቶ ሀጢአት ነዉ ያለዉ ማን ይሆን ? ነዉ ወይስ በመዋሸት እና በድብቅነት ዉስጥ ያለዉ ልዩነት አልገባቸዉም? ዛሬን የሚያናዉዝ ትናንት ሰለምን ይወራል ? ነገን የሚያከሽፍ ዛሬ ለምን ይቀነቀናል? በዝምታ ዉስጥ መኖር ለምን ይጎረብጠናል? ዝምታን ፡ችሎ ማለፍን ፡ስቆ ማዝገምን ፡ ከድብቅነት ጎራ ያስመሸጋቸዉ ማን ይሆን? ድብቅነቷ ዉስጥ እልፍ ተዝታ , ግዙፍ ተስፋ, ነጥፎ ያደቀቃት ዛሬ, የታመነችለት ግን ያላመኗት አኗሪወች ኑረዉ ቢሆንስ? ፈራጅን ፈረዱበት ይላል አባቴ። ድብቅነቷን ተደብቀዉ ሲያወሩልኝ ስቄ ተራመድኩት።
1901Loading...
37
ሁሉም የራሱ ድክመት አለበት። እስኪ በፀሎት እንተሳሰብ
1750Loading...
38
ብዙ ትማራለህ ጥቂቱን ታወራለህ ምክንያቱም በመኖር የሚነገር ስላለ
1921Loading...
39
ሁሉ አይፖሰትም እንጅ...
1891Loading...
40
ፍቅሩምስጢር የማይነገር የማይለካ አንገትደፊ እኔን ከሳቅ ሊያለካካ ስለመወደድ የማይዘምር ዝምተኛ ባለ አርምሞ ልጄንይላል እርሱ ራሱ ጠና ታሞ ዝምስለፍቅሩ ቅንጣት ቃላትማይተነፍስ ከመንጋውፊት ጠብታ እንባንየማያፈስ ሁሉንየሚችል መሬት ባህሪ የታደለው የኔ አባት ይሄው ዛሬ ልደቱ ነው አባትዬ እወድሀለሁ ነፍ አመት ኑርልኝ
1990Loading...
አንዳንድ ቀኖች አሉ መከፋታችንን የሚያጋንኑ ጥቂት ቆዛዝመን ለመላቀቅ ስንራመድ የሚጨምሩ ክስተቶች ይበረክታሉ። ለመከፋቴ መጥጊያ ያልነው ያፈሳል ሌላ የሀዘን ዝናብ ያስመታናል።መተማመናችን ሁሉ ይጠፋል። እንዲሁ መቀጠል ይሻላል ጥቂቷን መከፋት ይዞ
Show all...
🥰 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1 1🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 4 2👏 1
እውነት አላት... ክፍል አንድ (1) "አንዳንድ ቀን የማይጎረብጡ ውድቀቶች ሰላሞ የማይነሱ መንገጫገጮች የልብን ወዳጅ በሞት አጥቶ ወደአምላኩ ሄዴ ብሎ የሚሰማ እፎይታ ይሰማል"። አለችኝ ከልቧ እንደሆነ ፊቷ ላይ የሚነበበው የእፎይታ እና የሰላም ማገኘት አይነት ገፅታ ነው። በሁኔታዋ ደነገጥኩ ...አባቷ ከተቀበረ ገና ሶስት ቀን ታድያ ይሄ ጤንነት ነው? ወይስ ምን ያህል ክፉ ብትሆን ነው በአባቷ ሞት ማግስት ስለውድቀት እና ግልግል እየተፍለቀለቀች የምትነግረኝ... ከራሴ ጋር ሆኜ ላጠናት ልመረምራት አሰብኩ ሞከርኩ የቱም እውነት አልገለጥ አለኝ አላውቅማ እንደዚህ አይነት ሁናቴ አድሴ ነዋ አባቱ የሞተበት ልጅ ያዙኝ ልቀቁኝ በሞትኩ በሚልበት ማህበረሰብ ወጥቼ እንዴት ብዬ ይህንን ልቀበል። ኦንዳለችው እንኳን ወደፈጣሪ ሄደ ብላ ይሆን አይይይ ቢሆንም አያስደስትም በቃ ያስከፋል ስጋ አይደለም የለበሰችው ከአፈር አልተሰራችም እንዴት ልቧ ሸርተት አይልም?... መጠያየቄን አስተውላለችና "በማታውቀው እና ባልገባህ ጎጆ አትመራመር ትደክማለህ እንጅ ምንም አታገኝም ክፉ መስዬ ታይቼህ እንደሆነ አውቃለሁ እኔ የማውቀውን ብታውቅ ከሀቄ በተጠጋጋህ ነበር ግን አታውቅም ማወቅም የለብህም" ምንም ብትለኝ ሀቋ አልደርስህ አለኝ ምናልባት እውነት ይኖራታል ሀቅ ተሸክማለች ግን እውነት ሁሉ ትክክል ነው ሀቅ ሁሉ አግባብ ነው? እንጃ እውነቷ ሳይገባኝ ይቅር ይቀጥላል ...
Show all...
👍 3 1
እናቴ ጎደለኝ የምለውን ስቆጥር ስለካ ስመትር ስለካ አንች ማለት ለእኔ ሙላቴ ነሽ ለካ በአለም ሁካታ እንዳልቆም ፈዝዤ ግራውን አለፍኩት ቀኝ እጅሽን ይዤ ሙሴ አልልሽ በትር የለም ከእጅሽ ኖህ አልልሽ መቼ መርከብ ሰራሽ ዳዊትነት እንዳልሾምሽ ወንጭፍ የለም ከመዳፍሽ ጠጠር የለም ከመሬትሽ ብቻ... በአንች መልካምነት ስንት ችግሮችን አለፍኩኝ ተከፍሎ ሳቅሁ ያለገደብ በሳቅሽ ጠጠር ጎልያድ ተጥሎ በመልካምነትሽ መርከብ ተሳፎሬ ተመስገን እያልኩኝ ደረስኩ እስከዛሬ ከቶ እንዳይነካካሽ ክፋት እና ነውር ጤና ይስጥሽና ሳመሰግን ልኑር #እናቴ የጌጥ የእኔ አምባር የእኔ እንቁ የእኔ አልማዝ ስንቴ ተጨንቀሻል በጭንቅ እንዳልያዝ የለፋሽው ልፋት ፍሬ እንዲያፈራ እናቴ የምወድሽ ደህና ሁኝ አደራ ✍ዐቢይ አለሙ(ሚተራሊዮን)
Show all...
1🔥 1
ይናፍቀኛል ... ስም አጠራሩ ጆሮየ ላይ ያቃጭላል ። ጎራዳ አፍንጫየን ለማሳደግ በእጆቹ ሲነካኝ" እረፍ አትረፍ" ንትርኩ ይናፍቀኛል። ተገናኝተን አማይገቡኝን ነገር እያወራኝ ከንፈሮቹን ብቻ እያየሁ ፈገግ ማለት ይናፍቀኛል ። ባለማመን ዉስጥ ያለች መዉደድ ያመጣት ቅናቱ ይናፍቀኛል ። ሲስቅ የድምፁ መጎርነን ከጥርሶቹ አሰዳደር ጋር ተዳምሮ ነፍሴ ላይ የሚፈጥረብኝ ደስታ ይናፍቀኛል ። እያጣሁት እየተለያየን መሆኑን ለልቤ ሹክ ባልኩት ቁጥር ይናፍቀኛል ። ደጀ ሰላሙ ስር ተንበርክኬ በእየየ ቤቱን ያራስኩት ዉሳኔን ለግሰኝ ብየ ነበር ። መቁረጥን ወይ መቀጠልን ። በትንሽ ቅናቱ ዉስጥ እምነት አልባነት ተጨምሮ ቀና መንገዱን በኔ መወላገድ ህይወቱ ሲንጋደድ ተሰምቶኝ ነበር። ከቤቱ ሙሉነት በ ሄዋን ስም ልቡ ውስጥ ገብቸ ጥርጣሬን የጫርኩ አሳቹ እንደሆንኩ ተሰማኝ። ከጠራ ህይወቱ ድፍርሷን አኔን ጨምሬ በ ሀዘን ድባቅ እንዳስመታሁት ልቤ አረዳኝ ። መሳቅ አና ማዉራቴን ለዛ ነዉ የጠላሁት ። ፈገግታየ እምነቱን ሸረሸረበት ። ለሰዎች ቅርብነቴ የልቤን ሰዉ ለጥርጣሬ አጋለጠዉ። ልባምነቱ ከኔ እልህ ጋር አይወዳደርም። ግልፅ አንደበቱ ከኔ ዝምታ ጋር አይታሽም። ቀስ በቀስ ማዉራት ጀምሬ ነበር። ለማንም ካላወጣሁት እኔነቴ ጋር እያስተዋወኩት ነበር። ከረሳሁት ፍቅር ጋር ተላትሜ እሱን ስለማግባትም አልሜ ነበር ። ለተከታታይ ቀናቶች ዝምታን አርምሞን ከመረጥን በኋላ ሰላም አየተሰማዉ እንደሆነ ስሰማ ነው ልቤ የሸሸዉ ። "ለካ ማዉራታችን ነዉ ሰላም የነሳኝ" ማለቱን ለጆሮየ ሲያቀርቡት መለየቱን የመረጥኩት ። በመቅረብ ያደፈረስኩትን በመራቅ ለማጥራት።ለዚህ ነዉ ህይወቱን ላጠራ ያልተገባሁትን እኔን ለኖርኩበት ብቸኝነት ሰጥቸ ከኔ ነፃ እንዲወጣ መለየትን የመረጥኩት ። ብቸኝነቴ ዉስጥ ለማንም እማይብራራ የሱ ናፍቆት በቀናት ብዛት በዝምታ ተጀቡኖ ወደነበርኩበት እኔነቴ እንደሚመራኝ አዉቃለሁ።
Show all...
4👏 2🔥 1🥰 1
በሚዛን ስንለካ ስራዬ መዛኝ ነው የሰውን ክብደት ስለካ እውላለሁ። ሚዛኔ ሰውነታቸውን እኔ ደግሞ ሀሳባቸውን እንመዝናለን ሰው በጠፋ ሰዓት የማዋራት ሚዛኔን ነው። ሳቄ ነው የምላት እርሷን  ማንም እየረገጣት እየደለቃት በምትሰጠኝ ሳንቲም የእኔ ሆድ ሞልቶ ስቄ ስለምውል ሳቄ ናት።ስንት አይነት እግርን ትችላለች ስንት አይነት ጫማን ትሸከማለች አንዳንድ ቀንማ ከጫማቸው ክብደት በላይ በንፅህና ጉድለት የሸተተ ጫማ ተረግጧት ትውልና ስታስነጥስ ትሰነብታለች ያን ሰሞን እንዴት ነው የምታሳዝነኝ መሰለቻሁ።አሞኛል ልረፍ አትልም ሁሌ ትረገጥልኛለች።እንዳልኳችሁ ሳቄ ሰውነት እኔ አመለካከት እና ሀሳብ እንመዝናለን። አንዳንድ ሰው አለ የሚስቱን ሞት የልጆቹን ርሀብ በትከሻው ተሸክሞ ይመጣና ሲመዘን በኪሎው ይደነግጣል አደነጋገጡ ራሱ  አምስት ኪሎ  ያስቀንሳል።ወትሮስ የቤቱን ድምቀት የጎጆውን ምሰሶ በሞት የተነጠቀ ልጆቹ የራበኝ ሰቆቃቸውን እንደ እለት ኪዳን የሚያሰሙት ወጣት መፋፋት አምሮት ኖሯል። ሳቄ ከትከሻዋ ወርዶ አምስት ብር ሲሰጠኝ አይታ አዘነችለት "አሁን ይሄኔ እኮ ምናለ ዳቦ በገዛሁበት እያለ ነው ዝንብ ያረፈበት ያህል ሳይሰማኝ ወርዶ አምስት ብር ሙሉ ይከፍላል ምስኪን " ንግግሯ አንጀቴን ይበላኝና ልመልስለት እቃጣለሁ ከዚያ የእኔስ ልጆች ከራስ በላይ ...እተወዋለሁ። ደግሞ አንዳንድ ቀን ጅምር ኮንደሚኒየም የሚያክል ሰው ይመጣል ገና ወደእኛ ሲቀርብ ሁለታችንም እንሳቀቃለን። ሳቄ በመለኪያዋ ራሷን ስትለካ አስር ኪሎ ቀንሳለች ሰማይ የተደፋባት ያህል ሲጫናት አይጥ በወጥመድ ስትገባ የምታሰማውን ሲቃ ታሰማለች።ከብዙ የመቶ እና ሁለት መቶ ብሮች መሀከል አምስት ብር አውጥቶ ይሰጠኛል።ያኔ ነው ሳቄ ሀዘኗ የሚበረታው "ለዚህ ነው ህብረሰረሰሬ እስኪቆረጥ የተሸከምኩት"እንደማልቀስ ይቃጣታል ሚዛኔ ታሳዝነኛለች ብዙ ጉዶችን ትቸከማለች።አንዳንዴ ኢትዮጵያን ትመስላለች ብዙ ቀጫጭን ለጋሶችን በተሸከመች ሀገር ጥቂት ወፋፍራም ስስታሞች ያጎብጧታል።
Show all...
👍 5

👍 5🔥 1🥰 1