cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጥርኝ ጥበብ

ጥርኝ ጥበብ ማለት አንድም እንደ ሽቶ መልካም የጥበብ መዓዛን እናገኝ ዘንድ በሽቶ ከምንገለገልባት ጥርኝ ስም ሰየምናት አንድም ከሞላ የህይወት ስብጥርጥር እና ካልገቡን የህይወት መራራነት በጥርኝ ወይም ደግሞ በትንሽ ጥበብ እፎይታን እናገኝ ዘንድ በዩቱዩብ https://www.youtube.com/@2112-trgn-tbeb በቴክቶክ tiktok.com/@trgntbebhiluabiy

Show more
Advertising posts
435
Subscribers
+124 hours
+87 days
+1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ይመጣል ብየ ለልቤ ነግሬዉ ነበር... ኮቴ በሰማሁ ቁጡር ዉስጤ ከቀረ ጠረኑ ጋር አዋኅጀ ልቤን አስበረግገዋለሁ ነበረ... እማይመጣን ለ ሰከንድ በተስፋ መጠበቅ ለካ የዘመናትን ያክል እሩቅ ነዉ... ብቻየን ስሆን ከራሴ ዉጭ የጠበኩበትን ነገር አላስታዉስም አብሮነት ዉስጥ ማጣትን ሳንለማመድ መግባት ለመሰበር እራስን እንደማመቻቸት ይመስለኛል። ላጣዉ እንደምችል ለልቤ አልነገርኩትም ነበር , በረከትነቱን ስጦታየ ነህ ብየ ተቀብየዉ ነበር ። አንዳንድ በረከቶች መዳረሻቸዉን በወጉ አያዉቁም ። ለመስጠት ያልቸገረንን ልብ ለመመለስ አንሟሟታለን ። ስሰጠዉ ስፈቅድለት ያልከበደኝን ለነበረዉ ማንነቴ አስረክቦኝ ሲሄድ የሰጠኋትን ለማባበል ግን ብርታትን አጣሁ። ህመሜን በዝምታየ ደበኩት። ብሶቴን በአርምሞየ ሸሸኩት። ....እሱ ወደፊት ሄደ, ያጣኋትን እኔን ለማባበል እኔም ወደኋላ ቀረሁ።
Show all...
👍 1
"አመሰግናለሁ ቻዉ" ሲለኝ እጆቼ ይንቀጠቀጡ ነበር .... በሱ አለመታመኔ እልህ ዉስጥ መሸገኝ። እነደታመንኩለት ለማስረዳት ከአይኖቼ ውጭ ቃላት አጣሁ አይኔን ማመን አልፈለገም ። ፍቅሬን ከ እልህ ጋር ተናንቄ ላቆየዉ እየሞከርኩ መሆኔን ሴትነቴ ቆይ ብሎ እጁን ለመያዝ እንዳገዳገደኝ አልገባዉም። እግሮቹ እንደወጡ አለመታመን አለመፈለግ ከተስፋ መንጠፍ ጋር ተባብረዉ ሰዉ አየኝ አላየኝ ሳይሉ አንኖቼ የእንባ ጎርፍን ለጉንጮቼ አስረከቡ። ሰቶ ይነሳል? ወይስ ከጅምሩም አልተሰጠኝም ? እንባዋን በሳቋ እምትደብቀዋን እኔን አጣኅት ። ስለ እሱ ነበር ብየ ማዉራትን ፈራሁት ። ለካ እንደዚህ ወድጀዋለሁ ። ማጣትን ካጣሁት ስለቆየሁ ይሆን የኔ እሱን ማጣት ማመን የቸገረኝ። እንባን እፈራዉ ነበር። ለ እንባየ ቦታ እመርጥለት ነበረ። ከሱ መሄድ በኋላ አይኖቼ ቦታ እስክመርት አልታገሱኝም ። ጥሎኝ የሄደበት ቦታ ላይ አፌን አፍኘ እንዲወርድ ፈቀድኩለት። ሲሄድ አይኑን ለማስተዋል ሞክሬ ነበር መከፋትን ግን አጣሁበት ። በመሄዱ ደስተኛ የሆነ ያክል ተሰማኝ ። በአይኖቹ ተገላገልኩሽ ያለኝ መሰለኝ። ዞር ብሎ እንኳን አላየኝም ነበር ልብ ካልፈለገ አይንም ማየት አይሻም አደል።? ልቡን ከልክሎኝ እንደነበር ያልተከፋ ገፁ ላይ እጁን ለሰላምታ ዘርግቶ አመሰግናለሁ ሲል ነበር የተገለጠልኝ። ሁሉም እዉነት ማረጋገጫ አላዉ? ጊዜ እና ቦታ የማይመርጡ ህመሞች እንዳሉ አሳይቶኝ ሄደ። ሲመጡ እድለኝነትን አከናንበዉን ሲሄዱ አለመፈለግን የሚሰጡንን አሉ። ቢያጡን ከህይወታቸዉ ጥርኝ የማይጎድልባቸዉ። የኛን መሄድም መምጣትም በ "አመሰግናለሁ" ብቻ መቋጨት የሚችሉ ። ያልወደዱን የወደዱን የሚመስሉ ። ያላመኑን ያመኑን የሚመስሉ ። እኔን ማጣቱ ፊቱ ላይ መከፋትን አለመጫሩን ሳይ ያልገለጥኩለት መዉደዴ ምን ያህል ገዝፎ እንደነበር ገባኝ ። ደስ ብሎት ሊያቅፋት ሊያወራት እሚችለዉን እንስት ስም ለ ልቤ ለመጀመሪያ ግዜ ሹክ አልኩት ። እንባን ያለሰቀቀን አለቀስቁት። ሳያምነኝ መቶ ሳያምነኝ ሄደ ። ፍቅሩን በዝምታየ በድብቅ እንድይዘዉ አደረገኝ ። ሁሉም እዉነት ማረጋገጫ የለዉም።
Show all...
👍 3
አንዳንድ ቀኞች አሉ ዙሪያችንን ያለውን ሁሉ እንዳናስተውል የሚጋርዱን።ሀዘንን የሚያሸብቡ ክፉን የሚያስታውሱ ያልፉ ይሆን የሚባሉ ቀኖች። እንድሁ ቁዘማ ቁዘማ የሚያሰኙ ደርሶ የአስቴር አወቀና የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃን የሚያስመኙ። ግን የምር ያልፉ ይሆን?
Show all...
👍 1
"ሰይጣን አሳስቶት ነዉ " .... የትኛዉም ድርጊት የ አድራጊዉን መልካም ፈቃድ ይጠይቃል , ያለፍቃዳችን የገባዉ የትኛዉ ጥርጣሬ ነዉ? አሳሳቻችን እስክንጠራዉ በር ላይ ነዉ ሚቆመዉ , ስሙን ያለመጥራት መብት ግን አለን። ሰይጣን አሳስቶት ነዉ.... ወዳጁን የሚወድ ጠላት ነዉ ያለን ባቀረብነዉ ቁጥር የሚያቀለን , በጠራነዉ ቅፅበት ለማጣመመ የሚምዘገወግ, ያለመጥራጥ ፈቃድ ግን አለን ። ቢያንስ ዝምታን እንልመድ እስክንጠራ ባለችዉ ሰአት ህሊና ለማሰብ ፋታ ያገኛልና።
Show all...
👍 3
አንዳንድ ቀኖች አሉኝ ዙሪያችንን ያለውን ሁሉ እንዳናስተውል የሚጋርዱን።ሀዘንን የሚያሸብቡ ክፉን የሚያስታውሱ ያልፉ ይሆን የሚባሉ ቀኖች። እንድሁ ቁዘማ ቁዘማ የሚያሰኙ ደርሶ የአስቴር አወቀና የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃን የሚያስመኙ። ግን የምር ያልፉ ይሆን?
Show all...
👏 1😢 1
አንዳንድ ቀን አእምሮዬ እንድህ ይጠይቀኛል
Show all...
👍 2
"አንዳንድ ጊዜ አለማወቅህ አለመቻልህ ፈጦ ሲወጣ ከሰዎች ፊት ሲያቆምህ ሲያለማምንህ ሲያመፃፅንህ እንደማየት መጥፎ የለም" ...ይህንን ስትነግረኝ የሀዘን ደመና ፊቷን ሸፍኖታል እምባ ከአይኖቿ እያረዘረዙ ነው መከፋቷ ብቻ ሳይሆን ስብራቷ ከገጿ ይነበባል። ምነው ምን ሆነሽ ነው...አልኳት ስሜቷን ለማንበብ እየሞከርኩ የማዘኗን ነገር ቢያሳብቅም መርምሬ ላገኘው ያልቻልኩት ሀዘን ነው። አሉ ደግሞ አንዳንድ ስብራቶች የኔ ያልናቸው ሰዎች ራሱ የማይረዷቸው እንኳንስ በማየት በመነጋገርም ለሌላው የማይገቡ ጥልቅ ስቅራቶች ለሰሚው ቀላል የሆኑ ለኗሪ የሚከብዱ... "የሆንኩት ካየየኸው ይገዝፋል ካወራሁትም ከማወራም ይልቃል ለዚህ ደግሞ ቃል ማባከን ምኔ ነው የሆንኩትን አለም አትገጥመውም አለም አትስለውም አለም አትዘፍነውም ከጥላሁን ገሰሰ ንፋሽ ያልፋል ከሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ብዕር ይልቃል ከስብሀት ገብረእግዚአብሔር ልቅ ብዕር ይንቦረቀቃል ከሰዓሊ ቸርነት ሸራ ይሰፋል ጥበብ ብትጠበብ ሀዘኔን መግለፅ አልችልም ታድያ በምንኛ ቋንቋ ላስረዳህ እኔ የውስጤን ለመናገር እንደ ሐዋርያት መንፈስቅዱስ ወርዶ በቋንቋ በረከት እስኪያጥለቀልቀኝ በፀሎት ተግቼ መጠበቅ ነው የሚሻለኝ" አፌን ከፍቼ አሰማታለሁ ላቋርጣት ብልስ ምን ላወራ ለምዶኝ በወሬ መሀል እ...እና እሽ የሚሉ ፊደላት ማስገባት አልወድም እርሷም ይህንን ስለምታውቅ ነው በነፃነት እየሰማኋት እንደሆነ አውቃ የምታወራኝ። "አለማወቅን አለመቻልን ማወቅ መታደል ነው ሌሎች እንድያውቁት ማድረግ ግን ሽንፈት ነው መቼም ካልቸገረህ በቀር ድክመትህን ወደህ ለሰዎች አትገልጥም የገለጥክ ቀን ግን የምርም ቸግሮሀል አጣብቂኝ ውስጥ ነህ" ... አይኖቿ ማፍሰስ ጀምረዋል ከዚህ በላይ መቋጠር ቢቸግራቸው ጉንጮቿን በትኩስ እምባዋ ያጥባሉ ጥቂት ዝም አለችና አየችኝ። "ይልቅ ና እቀፈኝ እቅፍህ ውስጥ በደበቅ ዘመናትን ከማውራት ይበልጣል የጣቶችህ ፀጉሬን መንክታ ከናፍር ከማልፋት ይልቃል ና እቀፈኝና ዝም እንበል" አቀፍኳት የሎሬት ብዕር የማይገልፀው ሀሳቧን በሎሬት ግጥም አጅቤ አቀፍኳት አብረን ዝም እንበል ከሰው መንጋ እንገንጠል ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል በእፎይታ ጥላ እንጠለል ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል . . . ከዐቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
Show all...
2🥰 1👏 1
ተገብታህ አይደለም ታድለሀት ነው። ባላሰብከው ሰዓት በፍጥነት ወደህይወትህ የመጣችው ቀላል ስለሆነች ሳይሆን ከአንተ የሆነ ጥሩ ነገር ማየት የምትችል ማስተዋል ያላት ስለሆነች ነው ወይም መልካም ማንነት እንድኖርህ ቀብድ እየተቀበልክ ነው።
Show all...
🥰 4🔥 2 1
ነጎደ እልፍ አመታት ሞዠቁት የእድሜን ቋጠሮ ልመለስ ቀን ስጠኝ እያልኩ እንደ አምናው ዛሬም ቀጠሮ አትፈልግ ዘንድሮም ፍሬ እንቡጥ ገና አላፈራሁ አንድ ብቻ ታገሰኝ አምላክ ሆይ መቆረጥ ፈራሁ አውቃለሁ የዛሬአመት እንድሁ ነበር ፀሎቴ ከዛሬ ነገ ስቆጥር ነጎደ ድንገት ቀናቴ ይህች አመት ታገሰኝ ለአመቱ ፍሬ እይዛለሁ እንድሁ ምሳር ቢያገኘኝ ለአንተ ምን እበጃለሁ በፍቅር እንድለማመን እንድሆን የቤትህ ታማኝ ምሳሯ ትለፈኝ ዛሬ ይህችን አመት ታገሰኝ
Show all...
👍 2🔥 1🥰 1
ሀሉም ኑረት ኑረት አደለም.. ስለዘላለማዊ አብሮነት ተሰብከዉ በስመ ፈተና በእንጥልጥል የቀሩ መኖሮች መኖር አደሉም ፍቅርን ባለማመን እሳቤ ሽርሽሮ ወደፊትን በጥርጣሬ ያነጣጠሩ መኖሮች መኖር አደሉም። ሁሉም ማቀፍ ማቀፍ አደለም... እልፍ ቅሬታን አቅርሮ ዝምታን በሳቅ ሸብበዉ የተዘረጉ ትክሻን የሻቱ ማቀፎች ሁሉ ማቀፍ አይደሉም። ከ ተመልካች አይን ሽሽት አልቃሻ ብሌንን በጠራጊ መዳፍ ሞዥቆ እየየን ትራስ ስር ለማድረግ የተዘረጋ እቅፍ ..... ሁሉም መሳቅ መሳቅ አይደለም... ፈግ መሳቅም አለ።
Show all...
👍 2