cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr.seyfe

የዚህ ቻናል አላማ:ለህብረተሰቡ አስፈላጊዉን የህክምና አስተምሮት እና መልክቶችን ማስተላለፍ ነው። ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለማግኘት ዘወትር ቅዳሜ ከሰአት ከ9 አስከ11 ሰአት ባለው ጊዜ ደውሉልኝ:ለህክምና አገልግሎት በአካል ለማግኘት ከፈለጋቹኝ ደዉሉልኝ

Show more
Advertising posts
737
Subscribers
No data24 hours
+17 days
-130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

➕➕ የወገብ ህመም ለሚያስቸግረው➕➕ 🖲 የወገብ ህመም ያለበት ሰው ሁሉ ሀኪምጋ መቅረብ አለበት ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ የወገብ ህመም ያለበት ሰው ላይ፣ አንዳንድ ተጨማሪ  ምልክቶች ከታዩ፣ በቶሎ ህክምና ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። 🖲 የዲስክ መንሸራተት ብቸኛው የወገብ ህመም አምጪ በሽታ አይደለም፣ የአከርካሪ አጥንት፣ የጡንቻ ፣ የነርቭ እና የውስጥ ደዌ ህመሞችም፣ የወገብ ህመምን ሊፈጥሩ ይችላሉ 🖲 አንድ ሰው ላይ ፣የወገብ ህመም መኖሩ ብቻ ሁልግዜ አሳሳቢ ችግር ነው ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ አንዳንድ ግዜ ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች፣ የወገብ ህመሙ አደገኛ መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው 🖲 የወገብ ህመም እንደቆይታ ግዜው በ 4 አይነት መንገድ ይከፈላል፣ ማለትም፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምት በታች የቆየ ከሆነ የአጭር ግዜ የወገብ ህመም ወይም ( acute back pain) ተብሎ ይጠራል። 🖲 ወይም ደሞ፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምንት እስከ 3 ወር ድረስ የቆየ ከሆነ ፣( subacute back pain) ተብሎ ይጠራል: ሲተረጎም፣ ከፍያለ ደረጃ ያለው  የአጭር ግዜ የወገብ ህመም እንደማለት ነው። 🖲 የወገብ ህመሙ ፣3 ወር እና ከዛ በላይ የቆየ ከሆነ፣ (chronic back pain) ወይም ስር የሰደደ የወገብ ህመም እንደሆነ ያመላክታል። 🖲 ከዚህ ውጪ ፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሚያጋጥም፣ በመሀል ለተወሰነ ግዜ እረፍት እየሰጠ የሚመላለስ እና ለረጅም ግዜ የሚቆይ የወገብ ህመም ያጋጥማቸዋል፣ 🖲 ይህ አይነቱ የወገብ ህመም በህክምናው (recurrent back pain ) ተብሎ ይጠራል ወይም ተመላላሽ የወገብ ህመም ማለት ነው። 🖲 የወገብ ህመምን በዚህ መልኩ በቆይታ ግዜው መከፋፈል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክኒያት፣ የወገብ ህመም መንስኤ የሆነውን በሽታ ለመለየት እና ትክክለኛውን ምርመራ እና ህክምና ለመስጠት ታስቦ ነው። 🖲 ምክኒያቱም፣ ከ 30 በላይ የሚሆኑ የበሽታ አይነቶች፣ የወገብ ህመም ስሜትን የመፍጠር አቅም ስላላቸው ማለት ነው 🖲 አብዛኛውን ግዜ፣ ከ 6 ሳምንት በታች የሚቆይ የወገብ ህመም በቀላል ህክምና ወይም በቀላል የህመም ማስታገሻዎች ብቻ የሚድን ሆኖ ይገኛል። 🖲 80 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚያጋጥመው የወገብ ህመም አይነትም፣ ይሄው አጭር የግዜ ቆይታ ያለው የወገብ ህመም ነው፣ ከነዚህ ውስጥ፣ 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች በ 6 ሳምንት ውስጥ ሲሻላቸው ይታያል። 🖲 የወገብ ህመም አሳሳቢ የሚሆነው ታዲያ መቼ ነው? አንድ ሰው በራሱ ላይም ሆነ፣ በቤተሰብ አባል ላይ የሚታይ የወገብ ህመም ሲያጋጥመው ፣ሀኪም ጋር ከመምጣቱ በፊት ምን ማድረግ አለበት? ሙሉውን መረጃ በቪዲዮ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ። የሚቀጥለውን አድራሻ በመጫን በቀጥታ መመልከት ይችላሉ። መልካም ግዜ። 👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/t0uvR99J0MQ
Show all...
የወገብ እና የጀርባ ህመም | Lower Back Pain |Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ

👍 1
➕➕ የጥፍር መሰባበር ➕➕ 🖲 በተደጋጋሚ ግዜ የጥፍር ቀለምን መቀባት እና ጠንካራ በሆነ የጥፍር ቀለም ማስለቀቂያ በተደጋጋሚ ጥፍርን መፈተግ አንዳንዴ፣ የጥፍርን ተፈጥሮአዊ ገፅታ ሊቀይር እና ጥፍር አንዲሳሳ እንዲሁም በቀላሉ እንዲሰባበር ምክኒያት ሊሆን ይችላል። 🖲አንዳንዴ፣ ጥፍር ላይ ከወትሮው ለየት ያሉ ገፅታዎች ሲታዩ፣  የበሽታ ጠቋሚ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ 🖲ከጥፍር መሳሳት መሰነጣጠቅ እና መሰባበር ጋር ተያይዘው፣ አንድ ሰው ጥፍር ላይ የሚታዩ ምልክቶች፣ የራሳቸው የሆነ ባህሪዎች እና የራሳቸው የሆነ የህክምና ስያሜዎች አሏቸው 🖲ታዲያ፣ ጠቅለል ባለ መልኩ ለመግለፅ ያህል፣ የጥፍር መሰነጣጠቅ ፣ የጥፍር በቀላሉ ተሰባሪ መሆን  እንዲሁም ጥፍር የተፈጥሮ አቅሙን ሲያጣ፣ ምክኒያቱ፣ ከተጓዳኝ የጤና ችግሮች የተነሳ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ደሞ ፣ ምንም አይነት ተጓዳኝ የጤና ችግር በሌለበት ሁኔታ፣ በራሱ ግዜ ሊፈጠርም ይችላል። 🖲በተጓዳኝ በሽታ ምክኒያት ሊከሰት የሚችል የጥፍር መሰባበር እና መሰነጣጠቅ ሲኖር ፣  አብዛኛውን ግዜ፣ የእግር እና የእጅ ጥፍርን አብሮ ሊያጠቃ የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። 🖲 በዚህን ግዜ ለተጓዳኝ የጤና ችግሮች የሚሰጥ ህክምና፣ ለችግሩ ዋነኛ መፍትሄ ይሆናል። 🖲 ከዛ ውጪ፣ ለጤናማ የጥፍር እድገት መሰረታዊ የሆኑ እንደ ባዮቲን፣ አይረን እና ዚንክ የመሳሰሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በውስጣቸው የሚይዙ ምግቦችን ማዘውተር፣ ለጥፍር ጤንነት ጉልህ ሚናን ይጫወታሉ። 🖲 ለምሰሌ፣ የዶሮ ወይም የከብት ጉበት፣ እንቁላል፣ አቮካዶ፣ አተር፣ ለውዝ ፣ ሱፍ፣ አጃ፣ ብሮኮሊ የመሳሰሉት ምግቦች በባዮቲን፣ በዚንክ እና በአይረን የበለፀጉ ምግቦች ናቸው። 🖲 ይህ የማይቻል ከሆነ ደሞ፣ እንዚህን ጠቃሚ ንጥረነገሮች በበቂ ሁኔታ የሚይዙ የቫይታሚን ሰፕልመንቶችን በቀን 1 ፍሬ ከ 3 እስከ 6 ወር ያህል መጠቀም ይቻላል። 🖲ይህን በተመለከተ፣ በምስል የተደገፈ ተጨማሪ መረጃ በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ። የሚቀጥለውን አድራሻ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። 🚩 ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ 9 እስከ 11 ሰአት ድረስ ብቻ መደወል ትችላላችሁ።📞 0974163424 ዶ/ር ሰይፈ ወርቁ 🚩ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉  @LEKETERO ወይም @Apointment1 ተጭነው ስም እና ስልክ በማስቀመጥ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። መልካም ግዜ 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/x2Z178dYa7Y
Show all...
ለተሰባበረ ጥፍር መፍትሄው | Nail fragility | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical #habesha

ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለመሰግኘት፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ ሰዓት ከ9 እስ 11 ባለው ግዜ ብቻ በ 0974163424 መደወል ይችላሉ ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ። የቴሌግራም አድራሻ 👉

https://t.me/seifemed

👍 1
➕➕ የወገብ ህመም ለሚያስቸግረው➕➕ 🖲 የወገብ ህመም ያለበት ሰው ሁሉ ሀኪምጋ መቅረብ አለበት ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ የወገብ ህመም ያለበት ሰው ላይ፣ አንዳንድ ተጨማሪ  ምልክቶች ከታዩ፣ በቶሎ ህክምና ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። 🖲 የዲስክ መንሸራተት ብቸኛው የወገብ ህመም አምጪ በሽታ አይደለም፣ የአከርካሪ አጥንት፣ የጡንቻ ፣ የነርቭ እና የውስጥ ደዌ ህመሞችም፣ የወገብ ህመምን ሊፈጥሩ ይችላሉ 🖲 አንድ ሰው ላይ ፣የወገብ ህመም መኖሩ ብቻ ሁልግዜ አሳሳቢ ችግር ነው ማለት አይደለም፣ ነገር ግን፣ አንዳንድ ግዜ ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች፣ የወገብ ህመሙ አደገኛ መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው 🖲 የወገብ ህመም እንደቆይታ ግዜው በ 4 አይነት መንገድ ይከፈላል፣ ማለትም፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምት በታች የቆየ ከሆነ የአጭር ግዜ የወገብ ህመም ወይም ( acute back pain) ተብሎ ይጠራል። 🖲 ወይም ደሞ፣ የወገብ ህመሙ ከ 6 ሳምንት እስከ 3 ወር ድረስ የቆየ ከሆነ ፣( subacute back pain) ተብሎ ይጠራል: ሲተረጎም፣ ከፍያለ ደረጃ ያለው  የአጭር ግዜ የወገብ ህመም እንደማለት ነው። 🖲 የወገብ ህመሙ ፣3 ወር እና ከዛ በላይ የቆየ ከሆነ፣ (chronic back pain) ወይም ስር የሰደደ የወገብ ህመም እንደሆነ ያመላክታል። 🖲 ከዚህ ውጪ ፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሚያጋጥም፣ በመሀል ለተወሰነ ግዜ እረፍት እየሰጠ የሚመላለስ እና ለረጅም ግዜ የሚቆይ የወገብ ህመም ያጋጥማቸዋል፣ 🖲 ይህ አይነቱ የወገብ ህመም በህክምናው (recurrent back pain ) ተብሎ ይጠራል ወይም ተመላላሽ የወገብ ህመም ማለት ነው። 🖲 የወገብ ህመምን በዚህ መልኩ በቆይታ ግዜው መከፋፈል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክኒያት፣ የወገብ ህመም መንስኤ የሆነውን በሽታ ለመለየት እና ትክክለኛውን ምርመራ እና ህክምና ለመስጠት ታስቦ ነው። 🖲 ምክኒያቱም፣ ከ 30 በላይ የሚሆኑ የበሽታ አይነቶች፣ የወገብ ህመም ስሜትን የመፍጠር አቅም ስላላቸው ማለት ነው 🖲 አብዛኛውን ግዜ፣ ከ 6 ሳምንት በታች የሚቆይ የወገብ ህመም በቀላል ህክምና ወይም በቀላል የህመም ማስታገሻዎች ብቻ የሚድን ሆኖ ይገኛል። 🖲 80 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚያጋጥመው የወገብ ህመም አይነትም፣ ይሄው አጭር የግዜ ቆይታ ያለው የወገብ ህመም ነው፣ ከነዚህ ውስጥ፣ 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች በ 6 ሳምንት ውስጥ ሲሻላቸው ይታያል። 🖲 የወገብ ህመም አሳሳቢ የሚሆነው ታዲያ መቼ ነው? አንድ ሰው በራሱ ላይም ሆነ፣ በቤተሰብ አባል ላይ የሚታይ የወገብ ህመም ሲያጋጥመው ፣ሀኪም ጋር ከመምጣቱ በፊት ምን ማድረግ አለበት? ሙሉውን መረጃ በቪዲዮ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ። የሚቀጥለውን አድራሻ በመጫን በቀጥታ መመልከት ይችላሉ። መልካም ግዜ። 👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/t0uvR99J0MQ
Show all...
የወገብ እና የጀርባ ህመም | Lower Back Pain |Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ

➕➕ የሸንተረር ህክምናው ➕➕ 🖲 ከአንድ ሰው የሰውነት ክፍል ላይ ሸንተረር በብዙ ቦታዎች  ጎልቶ ሊወጣ ይችላል። 🖲መቀመጫ፣ ሆድ፣ ዳሌ፣ ብብት፣ ጭን እና እግር የመሳሰሉት የሰውነት ቦታዎች፣ አብዛኛውን ግዜ ሸንተረር የሚወጣባቸው የሰውነት ክፍሎች ናቸው። 🖲አነዚህ የቆዳ ሸንተረሮች በህክምናው Striae ተብለው ይጠራሉ። የያዙትን ቀለም እና የወጡበትን ምክኒያት በማገናዘብም የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸዋል። 🖲በእርግዝና ምክኒያት የወጣ የቆዳ ሸንተረር ከሆነ በህክምናው Striae Gravidarum ተብሎ ይጠራል ። 🖲ከውፍረት ጋር በተያያዘ መልኩ የሚወጣ ሸንተረር ሲሆን ደሞ Striae Distensae ይባላል 🖲ከዚህ ውጪ ደሞ ፣ ከቆዳ መሳሳት ጋር በተያያዘ መልኩ የሚወጣ ሲሆን በህክምናው Striae Atrophicans በመባል ይታወቃል። 🖲እነዚህ የህክምና ስያሜዎች ሸንተረሩ የወጣበትን ምክኒያት አመላካች የሆኑ ስያሜዎች ናቸው። 🖲ከዚህ በተለየ መልኩ ደሞ የሸንተረሩን ቀለም በማገናዘብ ሸንተረሩ እንደሚይዘው ቀለም የህክምና ስያሜም ይሰጠዋል። 🖲አንድ ሸንተረር በቆዳ ላይ ሲወጣ እንደጊዜ ቆይታው 4 አይነት ቀለሞችን ሊይዝ ይችላል። 🖲ቀይ ሊሆን ይችላል፣ ጥቁር ሰማያዊ ውይም ጥቁር ሆኖ ሊወጣ ይችላል፣ እንዲሁም ነጭ የቀለም ይዘት ሊኖረው ይችላል። 🖲አዲስ ወይም በቅርቡ የወጣ የቆዳ ሸንተረር ቀይ ሆኖ ይታያል፣ ቦታውን በእጃቹ በምትዳብሱበት ግዜ አበጥ ያለና ጠንከር ያለ ይዘት ይኖረዋል። ይሄ በህክምናው strae rubra ተብሎ ይጠራል፣ ቀይ ሸንተረር እንደማለት ነው ትርጉሙ። 🖲ሸንተረርን ለማጥፋት የተዘጋጁ ብዙ አይነት የህክምና አማራጮች አሉ፣ ነገር ግን ሸንተረርን የማጥፋት አቅማቸው ሁሉም ሰው ላይ ተመሳሳይ አይደለም። 🖲ወይም አንድ ወጥ በሆነ መልኩ ሸንተረርን ከሁሉም ሰው ላይ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ የሚችል ነው ተብሎ የተቀመጠ የህክምና መንገድ የለም። እንደ ህክምና አማራጭ ሆነው የቀረቡት፣ 👉በሚቀባ መልክ የተዘጋጁ ቅባቶች፣ 👉የጨረር ህክምና፣ 👉ቆዳን የመፋቅ እና የመብጣት ህክምናዎች፣ micridermaabresion እና microneedling ይባላሉ በህክምናው 👉እና የ PRP ህክምና ናቸው 🖲 ስለነዚህ የህክምና መንገዶች በሰፊው YouTube ላይ አስቀምጫለሁ። ለመመልከት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/FNN-IicACW4
Show all...

👍 6
Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ: 🛑❌እነዚህን አጭበርባሪ ሌቦች ለፖሊስ በማጋለጥ ተባበሩኝ።🔴❌❌❗️❗️ ከዚህ በታች ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው። 🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው። 🟢የኔ ትክክለኛው የፌስቡክ አካውንት ይሄ ነው https://fb.me/seifemedfb 🔴እኔ አሁንም ወደፊትም ምንም አይነት መዳኒት አልሸጥም፣ በኔ ስም እና ፎቶ መዳኒት ሲሸጥ ካያችሁ እባካችሁ በቶሎ ለፖሊስ አመልክቱ። ዶ/ር ሰይፈ 🔴🔴🔴እባካችሁ ሼር ሼር ሼር ሼር 🛑❌እነዚህን አጭበርባሪ ሌቦች ለፖሊስ በማጋለጥ ተባበሩኝ።🔴❌❌❗️❗️ ከዚህ በላይ ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው። 🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው። 🟢የኔ ትክክለኛው የፌስቡክ አካውንት ይሄ ነው https://fb.me/seifemedfb 🔴እኔ አሁንም ወደፊትም ምንም አይነት መዳኒት አልሸጥም፣ በኔ ስም እና ፎቶ መዳኒት ሲሸጥ ካያችሁ እባካችሁ በቶሎ ለፖሊስ አመልክቱ። ዶ/ር ሰይፈ 🔴🔴🔴እባካችሁ ሼር ሼር ሼር ሼር
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 7
➕➕የዓይን ዙሪያ ጥቁረት➕➕ 🖲 የዓይን ዙሪያ ጥቁረት፣ አብዛኛውን ግዜ በቀላሉ የሚጠፋ ጥቁረት አይደለም 🖲አንዳንዴ ፣እንደ ጥቁረቱ ይዘት እና እንደ መጣበት ምክኒያት ህክምና ሲደረግ፣ አንዳንዱ ሙሉበሙሉ የሚጠፋ፣ አብዛኛው ደሞ፣ በከፊል ወይም በመጠኑ ብቻ የሚደበዝዝ ሆኖ ይገኛል። 🖲ምክኒያቱም፣ በዓይን ዙሪያ ያለ ቆዳ ከሌላው ቆዳ የበለጠ ስስ ከመሆኑ የተነሳ፣ ቆዳው ላይ የሚፈጠር ጥቁረት አብዛኛውን ግዜ ከቆዳው ስር ስለሚጠራቀም ነው። 🖲 የዓይን ዙሪያ ጥቁረት፣ አራት መነሻ መሰረቶች አሉት፣ የመጀመሪያው በዓይን ዙሪያ ላይ ያለው ቆዳ ፣ በተፈጥሮም ሆነ  በተለያዩ ምክኒያቶች ቀለሙ ከልክ ያለፈ ሆኖ ሲገኝ ነው። 🖲 ሁለተኛው መነሻ መሰረት ደሞ ፣ከቆዳው ስር ያሉ ደም ስሮች ገነው በሚታዩበት ግዜ ነው። የዚህ አይነቱ ሁኔታ፣ በተለይ ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች፣ በዓይናቸው ዙሪያ ያለው ቆዳ የሳሳ ይሆንና አንዳንዴ በዙሪያው ያለው ደምስር ጎልቶ ሲወጣ በዓይናቸው ዙሪያ ጥቁረትን ሊፈጥርባቸው ይችላል። 🖲 ሶስተኛው መነሻ መሰረት ፣ በዓይን ዙሪያ የሚፈጠር እብጠት ወይም መሰርጎድ ሲኖር ፣ በቦታው ላይ የሚፈጥረው ጥላ የዓይን ዙሪያ ጥቁረት ሆኖ ሊታይ ይችላል። 🖲 አራተኛው እና የመጨረሻው ምክኒያት ደሞ፣ አንድ ሰው ላይ እነዚህ ሶስት መነሻ መሰረቶች ተደራርበው በሚከሰቱበት ግዜ ነው። ለምሳሌ፣ በዓይን ዙሪያ ገኖ የሚታይ ደምስር ያለበት ሰው፣ በተጨማሪም የዓይን ስር እብጠት ወይም መሰርጎድ ሲኖረው የጥቁረቱ መነሻ የተደራረበ ይሆናል ማለት ነው። 🖲 ታዲያ፣ አንድ ሰው የዓይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ መጀመሪያ የዓይን ዙሪያ ጥቁረቱ የተፈጠረው ከተጓዳኝ የቆዳ ችግር አለመሆኑን ሀኪም ጋር ቀርቦ ማረጋገጥ አለበት። 🖲 ማድያትም ሆነ፣ ማንኛውም ቁጣን የሚፈጥር የቆዳ ችግር ካለ፣ ጥቁረትን የሚጀምር እና የሚያባብስ ምክኒያት ስለሚሆን ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል። 🖲 ከዛ ውጪ፣ እንደ እንቅልፍ ማጣት፣ ከፍተኛ የህይወት ጫና መኖር፣ የአልኮል መጠጦችን ከልክ ባለፈ መልኩ መጠጣት፣ እና፣ ራስን ለከፍተኛ የፀሀይ ጨረር ማጋለጥ የመሳሰሉ ምክኒያቶች፣ የአይን ዙሪያ ጥቁረትን የሚያባብሱ ናቸው፣ 🖲 ለዚህም ሲባል፣ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ፣ በቂ እረፍት እና በቂ ውሀ መጠጣት፣ እንዲሁም ደሞ፣ ወደፀሀይ ሲወጣ ዓይንን በአግባቡ የሚሸፍን የፀሀይ መከላከያ መነፅሮችን መጠቀም ያስፈልጋል። 🖲 በተጨማሪም፣ ከተቻለ፣ የሚኒራል ይዘት ያላቸውን፣ ለዓይን ዙሪያ ቆዳ የተዘጋጁ የፀሀይ መከላከያ ክሬሞችን ብቻ መጠቀም እና ፀሀይ ላይ ከ ሁለት ሰአት በላይ መቆየት ግዴታ ከሆነ ፣ ደግሞ መቀባት ያስፈልጋል 🖲 ከዛ ውጪ፣ የአይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ የሚረዱ ፣በሚቀባ መልክ የተዘጋጁ የተለያዩ ክሬሞች አሉ። እነዚህ ክሬሞች ያላቸው አቅም እና ውጤታማነታቸው ከሰው ሰው የተለያየ ነው። 🖲 ታዲያ፣ አብዛኛውን ግዜ፣ የዓይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ ሲታሰብ፣ አንድ ክሬም ብቻ መጠቀም ያንን ያህል አጥጋቢ ለውጥን አያስገኝም። በተለያየ መንገድ ጥቁረቱን ለመቀነስ እንዲያስችል ከ አንድ በላይ ክሬሞችን መጠቀም ተመራጭ ነው። 🔵 ስለነዚህ ክሬሞች አይነት እና አጠቃቀማቸውን በተመለከተ፣ የበለጠ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ። የሚቀጥለውን አድራሻ ተጭናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ። 👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/8weptclRps4
Show all...
የአይን ስር ቅባቶች | Topicals for Dark Circle | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ | #medical #habesha #drseife

ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለመሰግኘት፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ ሰዓት ከ9 እስ 11 ባለው ግዜ ብቻ በ 0974163424 መደወል ይችላሉ ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ። የቴሌግራም አድራሻ 👉

https://t.me/seifemed

👍 7
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት/ወንድሞቻችን እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ! መልካም በአል!
Show all...
🙏 4
➕➕ ሽበት ለሚያስቸግረው ➕➕ 🖲  የአንድ ሰውን እድሜ ተንተርሰው ከሚመጡ የተፈጥሮ ለውጦች መሀል አንደኛው የሽበት መውጣት ሆኖ ሳለ ነገር ግን ሽበት ሁልግዜ የእድሜ መግፋትን ብቻ አመላካች አይደለም። 🖲 የአንድ ሰው ፀጉር ያለግዜው ሲሸብት ታዲያ፣ በማህበረሰብ ዘንድ የእድሜ መግፋትን የሚያመላክት ሆኖ ስለሚታይ፣ ከስነውበት አኳያ የስነልቦና ጫና ማሳደሩ የማይቀር ነው። 🖲 ካለግዜው የሚመጣ ሽበት ሲኖር አንዳንድ ሰው ላይ የስነልቦና ጫና ከመፍጠሩ ባሻገር ሊያደርስ የሚችለው ተጨባጭ የጤና እክል አይኖርም። 🖲 አንድ ሰው ላይ በተፈጥሮ ሽበት የሚጀምርበት እድሜ ፣በዘር የተለያየ ነው፣ ያም ማለት ከአፍሪካውያኖች ፀጉር ይልቅ፣ የምእራባውያን እና የእሲያውያን ፀጉር ቀድሞ ይሸብታል። 🖲በአፍሪካውያኖች ወይም በጥቁር ማህበረሰቦች ላይ፣ ሽበት ከ 34 እስከ 54 አመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ይጀምራል ፣ ለዚህም አማካዩ እድሜ 43 አመት ነው። 🖲 ከ6 እስከ 23 በመቶ የሚሆኑ አፍሪካውያን ወይም የጥቁር ማህበረሰቦች፣ እድሜያቸው 50 አመት ሲደርስ፣ ግማሽ የሚሆነው የራስ ቅላቸው ላይ ያለው ፀጉር ይሸብታል። 🖲 በዚህ መሰረት ታዲያ፣ በጥቁር ማህበረሰቦች ዘንድ፣ ያለግዜው የሚመጣ ሽበት የሚባለው፣ ሽበቱ የጀመረው ከ 30 አመት እድሜ በታች የሆነ ሰው ላይ ከሆነ ነው። 🖲 ካለግዜው የሚመጣ ሽበትን ከሚያስከትሉ ምክኒያቶች ውስጥ አብላጫውን ድርሻ የሚይዘው ተፈጥሮ ነው፣ በቤተሰብ የሚኖር ቀድሞ የሚመጣ ተፈጥሮአዊ ሽበት፣ በልጆች ላይም ሊከሰት ይችላል። 🖲 በዚህ ቪዲዮ ላይ የፀጉር ቀለም አይነቶችን በተመለከተ፣ እና ሽበት ያለግዜው የሚጀምርበትን ምክኒያት፣ እንዲሁም በህክምናው ዘርፍ የሚደረገውን ሁኔታ አብራርቻለሁ። 🖲 ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።     👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/-WVnwP0pMiQ
Show all...
ሽበት ያለግዜው ሲመጣ | premature gray hair | Dr.Seife | ዶ/ር ሰይፈ

👍 3 1
➕➕ የፊት ክሬሞችን ከመምረጣችሁ በፊት ➕➕ 🖲 መቼም ግዜ ቢሆን የፊት ቅባቶችን ከገበያ ስትገዙ: ለምን እንደምትገዙ እና የገዛችሁት ቅባት ከቆዳችሁ ጋር እንደሚሄድ እና እንደማይሄድ ካላወቃችሁ: እንዲሁም ደሞ የገዛችሁአቸው ቅባቶች: ጥራት የሌላቸው እና ይዘታቸው የማይታወቅ ከሆነ: 🖲 አንዳንዴ ሊመልስ ለማይችል የቆዳ ጠባሳ ከመጋለጥ ባሻገር: አንዳንድ ቅባቶች በድብቅ ከሚይዙት መዳኒት የጎንዮሽ ጉዳት የተነሳ: ለአንዳንድ የውስጥ ደዌ በሽታዎችም የመጋለጥ እድል አለ:: 🖲እዚህ ቪዲዮ ላይ የቀረበው መረጃ አንዳንድ የፊት ቅባቶች ውስጥ ሊጨመሩ የሚችሉ መዳኒቶችን እና: ሊያስከትሉ የሚችሉትን የጎንዮሽ ጉዳት ማስተማሪያ ነው:: አመሰግናለሁ እነዚህን የፊት ክሬሞች እባካችሁ አትጠቀሟቸው https://youtu.be/kzdE58BkHiA
Show all...
እነዚህን የፊት ክሬሞች ከመጠቀማችሁ በፊት... | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ

🖲 መቼም ግዜ ቢሆን የፊት ቅባቶችን ከገበያ ስትገዙ: ለምን እንደምትገዙ እና የገዛችሁት ቅባት ከቆዳችሁ ጋር እንደሚሄድ እና እንደማይሄድ ካላወቃችሁ: እንዲሁም ደሞ የገዛችሁአቸው ቅባቶች: ጥራት የሌላቸው እና ይዘታቸው የማይታወቅ ከሆነ: 🖲አንዳንዴ ሊመልስ ለማይችል የቆዳ ጠባሳ ከመጋለጥ ባሻገር: አንዳንድ ቅባቶች በድብቅ ከሚይዙት መዳኒት የጎንዮሽ ጉዳት የተነሳ: ለአንዳንድ የውስጥ ደዌ በሽታዎችም የመጋለጥ እድል አለ:: 🖲እዚህ ቪዲዮ ላይ የቀረበው መረጃ አንዳንድ የፊት ቅባቶች ውስጥ ሊጨመሩ የሚችሉ መዳኒቶችን እና: ሊያስከትሉ የሚችሉትን የጎንዮሽ ጉዳት ማስተማሪያ ነው:: አመሰግናለሁ

👍 4